Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
Author: Yismake Worku
ዴርቶጋዳ በ ፪፼፩ዓ.ም.በደራሲ ይስማዕከ ወርቁ የቀረበ ልብ-ወለድ ሲሆን ሳይንሳዊ ዘዉግ ያለዉ የኢትዮጵያን አንድነት የሚስብክ መጽሀፍ ነዉ።መጽሀፉ ለዶ/ር ኢ/ር ቅጣዉ እጅጉ ማስታወሻነት ተበርክቷል።ከብዙ በጥቂቱ ገፀ-ባህሪያቱ ሻጊዝ እጅጉ(በእዉኑ አለም ቅጣዉ እጅጉ )፣ሚራዥ፣ሲፓራ፣ሜሮዳ፣ዣንጊዳ፣ጌራ፣አባ ፊንህሰ፣አባ ዠንበሩ ..። ዴርቶጋዳን የኢትዮጵያን ስነ-ጽሁፍ አንድ እርምጃ ወደፊት ያራመደ ብለዉ ብዙ የኢትዮጵያ ሙህራን ጽፈዋል.ይስማዕከ የዴርቶጋዳን ቀጣይ ክፍል ዴርቶጋዳ ፪(ራማቶሃራን)ለህትመት ዴርቶጋዳን በጻፈ በአመቱ ፪፼፪ አብቅቷል። ይህ ያለዉን ችሎታ ያሳየናል።አንዳንድ ጥራዝ ንጠቅ ሀያሲያን ይስማዕከን ሲተቹ ይስማዕከ የሰጠዉ መልስ "ትችቶች ምንም መጥፎ ቢሆኑ ይበልጥ እንድሰራ ያደርጉኛል"።ቢሆንም ቅሉ ይስማዕከ በስራዎቹ በኢትዮጵያዊያን ልብ ዉስጥ ለዘላለም ይኖራል።ይስማዕከ በመጽሀፉ ብዙ ነገሮችን ለመጥቀስ ሞክሯል ስለ መልካም አስተዳደር እጦት በኢትዮጵያ፣ስለ ጥንት ኢትዮጵያዊያን ጀግንነትና ተጋድሎ፣ስለ ፍቅር፤ስለ ኢትዮጵያዊያን ሙህሮች... በአሁኑ ሰዓት ይስማዕከ ዴርቶጋዳ ፫(ዣንቶዣራን) ፅፎ ለህትመት አብቅቷል፡፡