Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
መጽሐፍ ፀሐፊ ይህን መጽሐፍ ያለ ደራሲው ፈቃድ በማንኛውም መንገድ ማባዛት በሕግ የተከለከለ ነው ልእ ክክ ዚኢሃብ ወምሕረቱ ጴ ጉታእዜርከ እብከ ርር ጅዩኩ ከዐከፎኪቓዌርሃከርዐቧ አሳታሚ ጌጃ ቃለ ሕይወት የሥነ ጽሑፍ ክፍል መጋቢት ዓም ይህ መጽሐፍ አመክንዮንና እምነትን የሚያየው አፋትቶ ሳይሆን ኖርማን ጋይዝለር እንደ ደመደመው «ለአውግስጢኖስ የአመክንዮ አገዛው ሰው በወንጌል እንዲያምን ከማመኑ በፊት ሲያምንና ካመነም በኋላ በጥቅም ላይ መዋሉ ነበር ቶማስ አኪውነስ ሥራ ላይ ትኩረት ማድረግን እንጂ የአሠራሩን ምስጢር የማወቅ ግዴታ አይጭንብንም አብርፃም «የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል ሲል ሁሉን ነገር ሰሁሉ ቻይ አምላክ አስ ረከበ እንጂ ምርምር ውስጥ አልገባም» ዘፍ አምነት ምንድን ነው። መጽሐፌ ውስጥ ከገጽ ካለው ክፍል በስፋት ልጥቀስ ም መጠቀም አንደ መንፈሳ ድ መቀጠር ብዙ ሰዎች « ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል» ኛ ቆሮ የሚለውን የጳውሎስን አሳብ በተሳሳተ መልኩ በመረዳት ለዕ ውቀት የሚሰጡት ስፍራ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም መንፈሳዊነት ማለት ነው። ወይስ ደግሞ ዕውቀት ከቶውነ አንደማያስፈልገን ነው።ን ወደሚል ነገር ሲመጣ ብፓ ነው አመክንዮን በሚመለከት የአገራችን ባህል አጁን ዘርግቶ የሚቀበለው ነገር አይመስልም እንደ ዕድል ሆኖ ከልጅነታችን ጀምሮ በዕ ድሜ ከአንድ ስው መብለጥም ሆነ ማነስ ከብስለት አኳያ የራሱ የሆነ ድርሻ ቢኖረውም አመክንዮን መጻረር ግን የለበትም በሌላ ጐኑ ባህላችን ማንበብንመመራመርን ለሁለንተናዊ ዕድገት አዎንታዊ ጊስ መቀባበልን ስለማያበረታታ ወይም እነፒህ ነገሮች አጥጋቢ በሆነ መልኩ የባህላችን አካል ባለመሆናቸው አመክንዮ ተዳፍኖአል ማለት ይቻላል ከዚህ የተነሣም አንድን ነገር ሰው ብቻ አይደለም ሌላም ነገር ሟች ሊሆን ይቸችላል ወፎች ከብት ወዘተዋና ነጥቡ መንስኤ ፃሳቦችን በመገንባት ድምዳሜ ላይ መድረስ መልክ ባለው መንገድ የተጀመረው የሥነ አመክንዮ ጥበብ በዘረጋው በአርስጣጣሊስ ነው ። ምህረቱ ጴጉታ ክርስቲያን የሆንኩት ለምንድር ነው።
ለዚህም ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ይህ ምክንያት የለሽ ሞኝነት እንደሆነ አምናለሁ የማይቻል ነገር መሆኑ የተረጋገጠ ነው ብሷል ጠርጡሊያን ለፅውቀት የእግዚአብሔር መናገር በቂ ነው በመገለጥ ወደ ዕውቀት እንመጣለን ብሎ ያምናል ጠርጡሊያን እንዲህ ዓይነት አቋም የያዘበት ዐቢይ ምክንያት ወደ ተሳሳተ ፍልስፍና እንገባለን የሚል ሥጋት ስለነበረው ነው በሌላ በኩል የአሌክሳንደሪያው ቀለሜንጦስ የምጡቅ ዕውቀታዊነት አራማጅ ሲሆን የአረማውያን አስተሳሰብ ለክርስቲያን ዐቃቤ እምነትላዩዐር አዎንታዊ ጠቀሜታ አለው ብሎ በጽኑ ያምናል ቀለሜንጦስ እግዚአብሔር ለእሥራኤል ሕግን እንደሰጠ ለክርስትና እምነት ጥርጊያ መንገድ ይመቻች ዘንድ ፍልስፍናን ለግሪክ ሰጥቷል ብሎ አምኗል ዛሬ በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ በጥቅሉ ከአመክንዮና ከእምነት አኳያ በፅውቀት ይሁን ያለ እውቀት ሁለት አመለካከቶች ይንጸባረቃሉ አንዳንዶቹ አመክንዮን የእምነት ጠላት አድርገው የሚመለከቱት ሲሆኑ ሌሎች ግን ለአመክንዮ የጎላውን ሥፍራ ይሰጣሉ በዚህ መሃል ሚዛናዊነትን ለመጠበቅ የሚጥሩም አልጠፉም ይህ መጽሐፍ በአምነትና በአመክንዮ መካከል ሚዛናዊነትን እንድ ንጠብቅ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደርጋል በፄ መረዳት እምነትና አመክንዮ ተደጋጋፊና ተሟሟይ ናቸው አመክንዮ ምክንያቶችን በማቅረብና በማሣሄስ መረጃዎችን የማጣራትና የመገምገም የአአምሮ የማሰብ ችሎታና ሂደት ነውፎ እምነት ግን ከዚህ ይለያል እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እምነት እውነትን ማመንንና በእግዚአብሔር መደ ገፍን የሚያሳይ ነው ይሁንና በአመክንዮና በእምነት መካከል ስላለው ግንኙነትና መደጋገፍ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር ያለ መሆኑ አሌ የማይባል ነገር ነው እምነት በአመክንዮ ላይ የተመሰረተ ባይሆንም በአመክንዮ ግን ሊደገፍ ይችላል ለምሳሌ በእምነት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለማምከን አመክንዮ ለዐቃቤ እምነት አገልግሎት ዐቢይ ሚና ይጫወታል የዚህ መጽሐፍ ፀሐፊ ከዚህ በፊት በእስልምና ዙሪያ ባሉ ወሳኝ ጥያቄዎች ላይ መልስ የያዘ መጽሐፍ የጻፈና በበርካታ መንፈሳዊ መጻሕፍትና ጋዜጦች ላይ ጠቃሚ ሂሳዊ መጣጥፎችን ፏል እንዲሁም በነገረ መለኮት ትምህርት እስከ አሁን ድረስ ባለው ተሰጥኦና ሸክም ዙሪያ በማስተማር ላይ ይገኛል በአብያተ ክርስቲያናት መድረኮች በተለያዩ ሥልጠናዎ ችና ዐውደ ጥናቶች ላይ ጠቃሚ ትምህርቶችን ሰጥቷል ሑፎችንም አቅርቧል ይህም ልምዱ ለዚህ መጽሐፍ መጻፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል የዚህ መጽሐፍ ፀሐፊ እምነትና አመክንዮ ስላላቸው ግንኙነት ለወንጌላውያን አማኞች በተረዳው ባስተዋለው መጠን ጽፏል በተለይም በኛ አገር በአመክንዮና በእምነት መካከል ስላለው ግንኙነት ያለውን አመለካከት ስንመለከት የግንዛቤ ማነስና አመክንዮ የእምነት ጠላት ተደርጎ የሚታይበት ሁኔታ ያለ በመሆኑ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ አሁን በዚህ መጽሐፍ ያቀረበው ትንታኔ የተሳሳቱ አመለ ካከቶችን ለማቃናትና ሚዛናዊ ግንዛቤን ለማምጣት የማይናቅ ሚና ይጫወታል ብዬ አምናለሁ ይህንን መጽሐፍ በኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት ያሉ የቤክን አገልጋዮች የነገረ መለኮት መምህራንና ተማሪዎች እንዲያነቡት አበረታታለሁ ከፍተኛ ጠቀሜታም እንዳለው አምናለሁ ዮናስ አስፋው የምስክር መጽሔት አዘጋጅና የነገረ መለኮት መምህር ማውጫ ህከሀጠበ ርዕስ ዞ መክፈቻ የኅ መቅድም ኮፎቬቤር መግቢያ በሆሰህርክከክ »»«ህ» የእምነትና አመክንዮ ትርጓሜ ሀ አመክንዮ ለ እምነት ከ ታሪካዊ ዳራ በር ሀ ሀ አውግስጢኖስ ዓም ለህባህከበ ለ ቶማስ አኪውነስ ዓም ፐከዕ ላበሀበ ሐ ማርቲን ሉተር ዓም አበክ ሀከ መ ጆን ካልቪን ዓም ገከበ በ ረ ብሌዝ ፓስካል ዓም ሰ የታሪካዊ ዳራ ግምገማ ህበ እምነትና አመክንዮ በተለያዩ ሰዎች እይታ በክ ሃርኬ ከ ከ ክበ ሀ መገለጥ ብቻ ክነ ዚርክ የእምነትና የአመክንዮ ዝምድና ከር ልበከቼ ጳቫከ በ ክ የእምነትና አመክንዮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቶች ቨር ዐህሀዐክ ሀ እምነት የጠ ለ አመክንዮ ዐ በእምነትና በአመክንዮ ዙሪያ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች እብርዐበር አመክንዮን መጠቀም እንደ መንፈሳዊ ድካም መቁጠር አመክንዮ በመንፈስ ቅዱስ ያለመደገፍ ያለመታመን ውጤት ነው ብሎ ማሰብ አመክንዮ በባሕሳችን ውስጥ የሚበረታታና የሚሞገስ አይደለም ስለ እምነት ያሉን የተሳሳቱ አመሰካከቶች አመክንዮን እንደ ሁለንተና የማየት ችግር ማጠቃለያ የቁልፍ ሰዎች ማንነት መግለጫ መፍትሔ ቃላት የግርጌ ማስታወሻ የክ ዋቤ መጻሕፍት ቨኦከሃ ንዑሳን አርእስቶች መቅድም ሀወርሼር የዛሬ አንድ ዓመት ከሦስት ወር በፊት ነበር ይህን አነስ ያለ መጽሐፍ በመጣጥፍ መልክ የጻፍኩት በጊዜው ከሌሎች ሰዎች መጣጥፎች ጋር አንድ ላይ ታትሞ በመጽሐፍ መልክ እንዲዘጋጅ ታስቦ ነበር ይህም ሃሳብ የመነጨው በወንድም ተስፋዬ ሮበሌ ነበር ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች የታሰበው ሳይሆን ዘገየ እንግዲህ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ የራ ሴን መጣጥፍ ወደ አነስተኛ መጽሐፍ ለማሳደግ በልቤ ትልቅ ሸክም ተሰማኝ እነሆ መጣጥፍ ይህን መጽሐፍ ወለደ ስለ እምነት የሚወራውን ያህል ስለ አመክንዮ አይነገርም በተለይም በአገራችን ዐውድ ባብዛኛው እምነትን በሚመለከት ይጻፋል ይሰበካል ይዘመራ ል በአጭሩ እምነት በሃሳብ ደረጃ ግልጽ የሆነ ነገር እንደሆነ ብዙዎች ያምናሉ ይህ ማለት ግን ሁሉ ሰው ስለ እምነት ያለው ግንዛቤ በቂ ነው ማለት አይደለም ስለ እምነት ብዙ ይባል እንጂ በርግጠኝነት ስለ አመክንዮ የእምነትን ያህል አይወራም በስብከትም ሆነ በትምህርት ውስጥ አመክንዮ እንግዳ የሆነ ሐሳብ ነው በአንድ ጎኑ ስለ አምነት መወራቱ መልካም ሆኖ አመክንዮ ደግሞ የተሰጠው ሥፍራ ከዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ አሳዛኝ ከመሆን አልፎ በአዲሱ ትው ልድ ሕይወት ውስጥ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል እንግዲህ በዚህ አነስ ባለ መጽሐፍ ውስጥ ሊሠራ የተሞከረው ነገር ቢኖር ይህንኑ በእምነትና በአመክንዮ መካከል የተፈጠረውን ክፍተት በተቻለ መጠን ለማጥበብ መሞከርና ሕዝበ ክርስቲያኑን በእምነትና በአመክንዮ መካከል ያለውን ዝምድና በሚገባ እንዲ ረዳ በተቻለ መጠን መርዳት ነው በዚህ ሥራ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ ብዙ ሰዎች ናቸው ወንድን ተስፋዬ ሮበሌን የመጀመሪያውን ረቂቅ መላልሶ በማንበብ ጠቃሚሜ የሆኑ አስተያየቶችን ስለለገሰልኝ አመሰግ ነዋለሁ። አነዚህና እነዚህን መሰል ጉዳዮች ይህ ጽሑፍ ትኩ ረቱን ሰጥቶ ከሚታገላቸው ጥያቄዎች ውስጥ የሚካተቱ ይሆናሉ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዐላማ በእምነትና በአመክንዮ መካከል ያለውን ዝምድና መቃኘት ይሆናል ይህንም ለማድረግ የሚከተሉትን አቅጣጫዎች ይከተላል በምዕራፍ የእምነትና የአመክንዮ ትርጓሜ ይተነተናል በምዕራፍ በእምነትና በአመክንዮ ላይ የታሪካዊ ዳራ ቅኝት ይደረጋል በምዕራፍ እምነትና አመክንዮ በተለያዩ ሰዎች እይታ ምን እንደሚመስል ቅኝት ይደረጋል በምዕራፍ የእምነትና የአመክንዮ ዝምድና ይታያል በምዕራፍ የእምነትና የአመክንዮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ይተነተናል በምዕራፍ በእምነትና በአመክንዮ ዙሪያ የሚነሱ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች ይቀርባሉ በምዕራፍ ማጠቃለያ ይሆናል ምዕራፍ አንድ እምነትና አመክንዮ አምነትና አመክንዮ እምብዛም ለመረዳት የማይከበዱ የሚመስሉ ሆኖም ግን ለብዙ ዘመናት የነገረመለኮታውያንንና ፈላስፎችን እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ዘንባሌው ያላቸውን ሳይንቲስቶች ሳይቀር ያወዛገቡ ነገሮች ናቸውበዚህ ዙሪያ እየተደረገ ያለ ውይይትም እስከ ዛሬ ቀጥላሏል እኔም በዚህ ስፍራ ወደ ጽሑፌ ዋና ሃሳብ መግባት የምፈልገው የአምነትንና የአመክንዮን ትርጓሜ በማስቀመጥ ይሆናል «አመክንዮ ርበ ማለት ምክንያት ሰጠ ምክንያት ቀረበ ከሚለው የግእዝ ቃል የመጣ ነዐ አንድ የፍልስፍና መዝገበ ቃላት ደግሞ «አመክንዮ ሰዎች አንዲያስቡ የሚያደርጋቸው ኃይል ላይ እንዲደርሱ የሚያበቃቸው ነው በማለት ይፈታዋል በሌላ የፍልስፍና መጽሐፍ ውስጥ እንደተቀመጠው ደግሞ «አመክንዮ የሰው አእምሮ አውነትን ፈልጎ የሚያገኝበት የተፈጥሮ ችሉታ ነው ለታላቁ የነገረ መለኮት ሊቅና ፈላስፋ አውግስጢኖስ «አመክንዮ በሌሎች ነገሮች መካከል ሰዎች ያላቸው የሚያስቡበት ማዕከል ሩህኔ ነው በዚህም ቁሳዊ ያልሆኑ እውነታዎችን ዓለም ማየትና ማወቅ የሚችሉበት ነው ይህም እግዚአብሔርን ጭምር ያጠቃልላል ከላይ የተቀመጡ ትርጓሜዎች ስለ አመክንዮ ምንነት መሠረታዊ የሆነ ግንዛቤ ሊያስጨብጡን የሚችሉ ናቸው የራሴን ማጠቃለያ ከመስጠቴ በፊት ግን የአምነትን ትርጓሜ ማየታችን ደግሞ የበለጠውን አምነትንና አመክንዮን በሚመለከት የምናደርገውን ውይይት በተቃና መልኩ እንድንከታተል ያስችለናል እምነት በብዙ ዐይነት መንገድ ሊፈታ ይችላል ለዚህ መንሥኤው የየሰው የዛይማኖት የንጽሮተ ዓለም ካሣፎክና የባሕል ዳራ አንድ ዐይነት ባለመሆኑ ነው ዝ በ ዓም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል ያሳተመው የአማርኛ መዝገበ ቃላት እምነትን «ፃይማኖትአምልኮ እርግጠኝነት ኃላፊነትና ታማኝነት»በማለት አስቀምጦታል በስተ ፈን ኢቫንስ በተዘጋጀ የፍልስፍና መዝገበ ቃላት ውስጥ ደግሞ «እምነት በክርስትና ውስጥ በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ የአለኝታ ፍላጎት ነው ይህም ከአግዚአብሔር ጋር ተገቢ የሆነ ኅብረት ለመመሥረት የሚያስችሉትን ስለ እግዚአብሔር የሚታመኑ ነገሮችንና ደግነቱን ያጠቃልላል በርካታ የነገረ መለኮት ምሁራን እምነት ፈርጀ ብዙ እንደ ሆነ ይገምታሉ ይህ ደግሞ አለኝታ ማድረግ በቃላት የተገለጹ እምነቶችንና በታዛዥነት ለመኖር ፈቃደኛ መሆንን ያጠቃልላል እስከ አሁን ካየነው ለቀቅ ባለ መልኩ ደግሞ «እምነትኔ የሚል ቃል ለተ ለያዩ የዛፃይማኖት ክፍሎችና ዓለማዊ ለሆኑ ሀ የአምነት ጉራዎችም ጭምር በጥቅም ላይ የሚውል ነው ቃሉ በዋና ዋና የዓለም እምነቶች ውስጥ ፃይማኖት ከሚል ቃል ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ጥቅም ላይ ውሏል የሃይማኖት ፍልስፍና በሚል መጽሐፉ ውስጥ ኢቫንስ አክሎ የእምነትን ተፈጥሮ በግልጽ አስቀምጦታል «እምነት በሕ የሚል ቃል የሚያሳየው አንድ አማኝ መረጃ አድርጎ በመደገፍም ሆነ በተቃራኒ መልኩ ወደ ዛይማኖታዊ እውነት የሚያመጣቸውን ግምቶች አቋሞችና ፍላጎቶች ወይም ዝንባሌዎችን ነው «እምነት መሰጠትን ያካትታል» «አምነት ኅሊናዊ ህከክርሄ የሆነውን የሰዎች ምርጫ ያመለክታል ይህም ክርስቲያን በመሆን ውስጥ ሊገለጽ የሚችለውን ወጥ የሆነ የመሰጠትን ዐይነት ለማመልክት ነው ወደ ሚቀጥለው ትንታኔ ለመሄድ እስከ አሁን የተመለከትናቸውን የአመክንዮና የእምነት ትርጓሜ ዎች ጠቅለል ባለ መልኩ ማስቀመጥ ጠቃሚ ነውወ ዌእፎክንዮ ርኪ አመክንዮ ከማሰብ ጋር የተቁቄራኝ ነው ስለ ሆነም አመክንዮ አንድን አሳብ መመርመር ድምዳሜ መፈለግ ማውጣት ወይም ማውረድ በሚል መልኩ ሊታይ ይችላል አሁን እዚህ ከያዝነው ጭብጥ አኳያ ግን አመክንዮ መገናኘት ያለበት መመርመር ወይም ድምዳሜ መፈለግ ከሚለው አሳብ ጋር ይሆናል «ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ አለማሰብ ምን እንደሚመስል ማሰብ ሊቸግረው ይችላል ላለማሰብ ጥረት ቢያደርግም ላለማሰብ እንኳ ማሰብ ስለሚኖርበት አለማሰብ እንደሚቻል መገመት የማይቻል ባይሆንም የሚከብድ አካሄድ ይሁሆናል ሰው በተፈጥሮው የሚያስብ ፍጡር ነው ሆኖም ስለ አንድ ነገር በጭፍን ነገሮችን ሳያገናዝብ አቅጣጫ የለሽ ማሰብ የሚያስብ ከሆነ ባወጣኝ ቦታ አወጣለሁ ብሎ የሚያስብ በመሆነ አስተሳሰቡ ራሱ ግልጽ ላይሆን ይችላል ይህም ከአመክንዮ መራቅን ሊያሳይ የሚችል አካሄድ ነው አስተሳሰባችን አመክንዮአዊ አንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ ተለይቶ የሚታወቀው አስተሳሰባችን ከሎጂክ ወይም አቅጣጫ ከሚያስይዙ የአስተሳሰብ መርሖች ጋር ሲስማማ ነው ሥነ አመክንዮ በሥርዐት የማሰብ ጥበብ ሲሆን የራሱ የሆኑ መርሖች ደግሞ አሉት ለምሳሌ ሦስቱን ብቻ አንመልከት ሁ የተቃርኖ ሕግ ከር ሕነ ክዐከክክቨርቨርክ አንድ ነገር በአንድ ጊዜ አንድም ሌላም ነገር ሊሆን አይችልም ለምሳሌሀ» «ሀ» አና «ለ» በአንድ ጊዜና መንገድ «ሀ»ም «ለም ሊሆን አይችልም ለሊ ዘ ሉው ኦፍ ኤክስክሉድድ ምድል ከበር ይኒርህበዩ ዝፎ አንድ ነገር ይህ ወይም ያ ነው ለምሳሌመኪና መኪና ወይም አይደለም ሐ ቭዝ ሎዉ ኦፍ አይደንቲቲ ከኗ ሕጡ። ጆ ለምሳሌ አውግስጢኖስ እምነትና አመክንዮን በተለየ መልኩ የሚያይበት መንገድ እንደ ሆነ ተደርጎ ሊታይ እንደሚችል በአንዳንዶች ዘንድ ይታመናል አመክንዮ አርስጣጣሊሳዊ ለዘክሀ ሥነ አመክንዮ በመሆኑ ፈንታ እንደ አውግስጢኖስ መረዳት አመክንዮ በሥነ ልቡናዊ አካፄድ የአእምሮ «ዕይታ» በሀበ ነው የዚህ «ማየት» መጨረሻው ዕይታ ነው ይህም አንድን የታወቀ አውነታ በግልጽ ማየት መቻል ነው»ኾ በሌላ አገላለጽ ለአውግስጢኖስ በእውቀትና በማመን « መካከል ልዩነት አለ እውቀት በዐኣርዐዉ ማለት ለአውግስጢኖስ አንድን ነገር በምንጨታዊ ወይንም ሀህቬ መንገድ በሚደረስ ድምዳሜ ላይ በመደገፍ የሚጨበጥ ነገር ሳይሆን በቀጥታ አንድን ነገር ማወቅ ነው ማመን ግን ሰዎች ወይም የመረጃ ምንጮች በሚሰጡን መሠረት ላይ በመቆም የምንወስደው ወይም ስለ አንድ ነገር ምንነት የምናገኘው ግንዛቤ ነው የአውግስጢኖስ እውቀ ትንና ማመንን በምን ዓይነት መንገድ እንደተረዳቸው ለማወቅ መረዳት ያለብን ነገር አለ ይኸውም አውቀት ለአውግስጢኖስ ያለማንም ዕገዛ ሊታወቅ ያለን ነገር ማወቅ ነው ለምሳሌ አንድ ሰው የራሱን መኖር ለማረጋገጥ የሌላ ሰው ምስክርነት አያስፈልገው ይሆናል የራሱን በዚህ ምድር መኖር በሕይወት እስካለ ድረስ በቀጥታ ያውቀዋል በርግጥ ይህን ምሳሌ የሚቃወሙ ሰዎች ቢኖሩም የራስ መኖር በትምሕርት የሚረጋገጥ ሳይሆን በቀጥታ የሚታወቅ ሐቅ ነው የአስራ ሰባተኛው ዘመን ፈረንሳዊው ፈላስፋ የዲካርት ምሳሌ ጠቃሚ ነው ከ ከርፎጪር ጸጠ ስለማስብ ስለዚህ አለሁ አንድ ሰው መኖሩን የሚጠራጠር ከሆነ ለዚያው ለጥርጣሬውም እንኳ መኖር መቻሉ የግድ ይሷል በመሆኑም የራሱን መኖር የሚጠራጠር ሰው ቢያንስ ለመጠራጠር መኖር ስለሚኖርበት የራስን መኖር ለማወቅ ከራሳችን ውጭ በቀዳሚነት አሳማኝ የሆነ መረጃ አይኖርም በማለት መቋጨት የሚቻል ይመስለኛል ማመን ግን ለአውግስጢኖስ ከእውቀት ለየት ባለ መልኩ በተለያዩ መረጃዎች ላይ በመደገፍ የሜወሰድ የግንዛቤ ርምጃ ነው ለምሳሌ አየለ የበቀለ ልጅ መሆኑን በቀጥታ አናውቅም በተለያዩ መረጃዎች ላይ በመደገፍ አየለ የበቀለ ልጅ መሆኑን ግን እናምናለን ይህም የአየለን የልደት ሰርተፊኬት በማየት አብሮ በማደግ አየለ በአቶ በቀለ ቤት መኖሩን በማየትና አቶ በቀለ ለአየለ የሚያደርጉለትን እንክብካቤ በማየት ሌሎች ሰዎች አየለ የአቶ በቀለ ልጅ መሆኑን በሚሰጡን ምስክርነትና ወዘተ ማረጋገጥ እንችሳላለን ከዚህ ባሻገር አውግስጢኖስ ማሰብን ያላካተተ ማመን ሊኖር እንደማይችል ሲናገር «ማንም ቢሆን ሊታመን ስላለው ስለዚያ ነገር በቅድሚያ ሳያስብ ምንም ነገር አያምንም» ብሎአል በመቀጠል አውግስጢኖስ የማመንና የማስብን ትስስር ጠበቅ አድርጎ ያስቀምጠዋል «የሚያስብ ሰው ሁሉ የሚያምን አይደለም ሰበቡም ብዙ ሰዎች ላለማመን ሊያስቡ ስለሚችሉ ነው ነገር ግን የሚያምን ሁሉ ያስባል በማመን ያስባል በማሰብ ያምናል አውግስጢኖስ በአመክንዮ ላይ ያለው ጠንካራ አቋም ግልጽ የሆነበት ዐረፍተ ነገር እንዲህ ይነበባል አግዚአብሔር ራሱ ከሌሉች ፍጥረታት አስበልጦ የሠራልንን በአኛ ውስጥ ያለውን ያን የአመክንዮን ክፍፍል መጥላትን ይከለክሳል ስለዚህ ለምናምንበት ነገር ምክንያት ሳንቀበል ወይም ሳንፈልግ ለማመን እምቢተኞች መሆን ይገባናል አመክንዮአዊ ነፍስ ባይኖረን ኖሮ ፈጽሞ ማመን አይቻለንም የሰውን የሕይወት መርሕ በተመለከተ «አግዚአብሔር በአመክንዮአዊ መንገድ የማመዛዘንና የማሰብን ችሎታ በሰው ውጡስጥ አኑሮአል አስከአሁን በጥቂቱ ካነበብነውና ከተደረገው አጠር ካለ ውይይት በመነሣት መረዳት እንደምንችለው ከሆነ አውግስጢኖስ አመክንዮንና እምነትን የሚያየው አፋትቶ ሳይሆን ኖርማን ጋይዝለር እንደ ደመደመው «ለአውግስጢኖስ የአመክንዮ አገዛው ሰው በወንጌል እንዲያምን ከማመኑ በፊት ሲያምንና ካመነም በኋላ በጥቅም ላይ መዋሉ ነበር ቶማስ አኪውነስ ከ ላቧህበ ዓም በጪኛው ክፍለ ዘመን ተነስተው ከነበሩ ስመጥር ፈላስፎችና ነገረፈመለኮታዊያን መካከል አንዱ ነው የአሪስጣጣሊስን የስነ አመክንዮ ሕጎች ከክርስትና አምነት ጋር በማገናኘት ትልቅ ሚና የተ ጫወተ ሰው ነበር አኪውነስ እምነትና አመክንዮ የተጣመሩ መሆናቸውን ያምናል ሁለቱ እንደማይነጣጠሉ ሲያመላክትም«አምነት አመክንዮን ይጠቀማል አመክንዮም አውነትን ያለ እምነት ፈልጎ ሊያገኘው አይችልም አመክንዮ የራሱ የሆኑ የሚገድቡት ባሕርያት ቢኖሩትም አንኳ ከጠቀሜታው አኳያ በአኪውነስ እይታ አዎንታዊ የሆነ ስፍራ አለው በተ ለይም አኪውነስ የአመክንዮና የአምነት ግንኙነት ሁለቱም ነገሮች በየራሳቸው መንገድ ለዛፃይማኖት አምነት አስተዋጽኦ አበርካች አንደ ሆኑ በማሳየት ረገድ የላቀ ሥራ ሠርቶአልፎ ለምሳሌ ለአኪውነስ አምነት ተገቢ ያልሆነ ነገር አይደለም እምነት ከስምምነት ጋር የሚደረግ አመክንዮአዊ ሂደት እንጂ አኪውነስ አክሎ እምነትን በተሻለ መልኩ ሲተነትን «አምነት ከሳይንስ የሚለየው ባለቤቱ የማይታይ በመሆኑ ነው በተጨማሪም እምነት ካለማመን ከጥርጣሬ እና ከግምታዊ አመለካከት የሚለየው አምነትን ለመደገፍ መረጃ በመኖሩ ነውፃ በአኪውነስ ግንዛቤ አምነት ባዶ በሆነ መሠ ረት የለሽ ነገር ላይ የሚደገፍ እንዳልሆነ ለማስተዋል አይቸግርም ስለዚህ እምነት ፊት ለፊት በሚታይ ነገር ላይ የሚደረግ ተስፋ አንኳ ባይሆንም «አመክንዮአዊ አውነት ከክርስቲያን ፃሣይማኖት አውነት ጋር የሚቃረን አይደለም» አኪውነስም ልክ እንደ አውግስጢኖስ የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣንነት አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል የነዚህ የቅዱሳት መጻሕፍት የአግዚአብሔር መገለጥ መሆናቸወ የተመሠረተወ በተፈጸሙ ትንቢቶችና ተኣምራቶች ላይ ነው የሚል ሃሳብም ነበረው ስለቪህ በአመክንዮ ብቻ ሊፈቱ የማይችሉ ነገሮች በቅዱሳት መጻሕፍት ሥልጣንነት ሥር በእምነት ተቀባይነት ሊያገኙ ይችላሉ» ይህ ደግሞ አንደ ሥላሴ ተሠግዎ በበርቿክበሀዐበ የመሳሰሉትን አስተምህሮዎን ያጠቃልላል እነዚህ አስተምህሮዎች አመክንዮን በመጠቀም የምንረዳቸው ገጽታዎች ቢኖሩዋቸውም አመክንዮን የሚያልፉ ገጽታዎች ደግሞ አሉዋቸው አኪውነስ አመክንዮን የእምነት ጠላት ሳይሆን አጋዥ አንደ ሆነ ነው የሚረዳው በአመክንዮ ብቻ የማንረዳቸው ነገሮች ስላሉ እምነት ደግሞ አስፈላጊ ነው ይህም አኪውነስ ከጽንፈኝነት የፀዳ አቋምና አካፄድ እንዳለው እንድንገነዘብ ይረዳናል በሌላ አነጋገር አምነት ከሌለ አመክንዮ ብቻ ሊጠቅመን አይትልም አመክንዮም ከሌለ አምነት ብቻ በራሱ የአመክንዮን ሚና ሊጫወት አይችልም ይህ አውነት ከሆነ ደግሞ አኪውነስ እንደተናገረው « መለኮታዊ ኑባሬን ከ በተ መለከተ ሁለት እውነቶች አሉ አንዱ በአመክንዮ የሚደረስበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከስው አመክንዮአዊ ችሉታ የሚያልፍ ነው ሁለቱም መንገዶች በመለኮታዊ መንገድ ሰው አንዲያምን ሊቀርቡለት የሚችሉ ናቸው» ሆኖም ነገሮችን ያለ አምነት ተሳትፎ በሰው አመክንዮ ብቻ በመጠየቅ ለመ ረዳት መሞከር የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽአኖ አንዳለው አኪውነስ በሦስት ምክንያቶች አስደግፎ ይገልጻል ፒ ጥቂት ሰዎች ብቻ ስለ አግዚአብሔር ይረዳሉ ከብዙ ጊዜ ልፋት በኋላ እንኳ ሰዎች የአግዚአብሔርን እውነት በጣም በጥቂቱ ሊያገኙ ይችላሉ የሰው አመክንዮ ከስሕተት የጸዳ አይደለም ይህም ነገሮችን አመዛዝኖ የመፍረድ ዕውቀት ብቃት ማነስና የብዙ ነገርች መቀላቀል ነው» ይህን የምናውቅበት መንገድ ቅዱሳት መጻሕፍት የሰው ልድ በኀጢአት ከመውደቁ የተነሣ አመክንዮው እንደተበከለ ስለሚነግሩን ነው «እምነት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው ያለ እምነት ደግሞ ማንም ቢሆን ሊያምን አይችልም ይህም ሆኖ ግን በአኪውነስ ግንዛቤ እምነት የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑ «የሚያምነውን ሰው ግንዛቤ በአመክንዮአዊ አስተሳሰብ ያመናቸውን ነገሮች እንዳያስተያይ ወይም ነገሮችን ማመዛዘን እንዳይችል አያደርገውም ከዚህ አቋም የተነሣ አኪውነስ ሲናገር እንዲህ ይላል የቅዱሳት መጻሕፍት ሥልጣንነተ ተቀባይነት ካገኘ አመክንዮን ተጠቅመን ስለ አምነት የምንለው ሊኖረን ይችላል ከአይሁዶች ጋር ለመከራከር ብሉይ ኪዳንን ልንጠቀም እንችላለን ከመናፍቃን ጋር ለመከራከር ደግሞ አዲስ ኪዳን ልንጠቀም እንችላለን ነገር ግን አሕዛብና መሐመዳውያን ብሉይ ኪዳንንም ሆነ አዲስ ኪዳንን አይቀበሉም ስለዚህ ሰዎች ሁሉ ስምምነታቸውን ሊሰጡት ወደሚገደዱት ወደ ተፈጥሮ አመክንዮ እከዘኗ የ መመለስ ይገባናል ይህ ተፈጥሮአዊ አመክንዮ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በሙሉ የሰጣቸው የማሰብና ከዚህም የተነሳ ነገሮችን የመገምገም የማመዛዘን በመጨ ረሻም አንድ ዓይነት ድምዳሜ ላይ የመድረስ ብቃት ችሎታ ነው ይህም ችሎታ የሰው ልጆች የጋራ የሆነ መለያቸው ነው አስከ አሁን አጠር ባለ መልኩ ካነበብነው መመልከት አንደሚቻለው ከሆነ አኪውነስ እምነትና አመክንዮን በሚመለከት ያለው አቋም ሚዛኑን የጠበቀ ነው ሁሉ ነገር በአመክንዮ ብቻ የሚፈታ አንኳ ባይሆን በእምነት ለምንቀበላቸው አመክንዮን ለሚያልፉ እውነቶች ትርጉምና ተቀባይነት አመክንዮ አስፈላጊ እንደ ሆነ ያስገነዝበናል ማርቲን ሉተር ከ ፀክርቪ ዓም የኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያን የተ ሐድሶ መሪ የሆነው ጀርመናዊው ማርቲን ሉተር በአመክንዮ ላይ ያለው አመለካከት ጠንከር የሚልበት አቅጣጫ አለው ሉተር እምነት ለድነት ከ በቂ መሆኑን ያለ ምንም ቅድሚያ ሁኔታ የሚያምን ሰው ነው «ጽድቅ በእምነት ብቻ» የሚለውም ሐረግ የሉተር ቁልፍ መታወቂያው ነው ሰው ከአግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት መመሥረት ያለበት በአምነት ላይ ነው እንደ ሉተር አባባል ያለ እምነት የአግዚአብሔር ወጠዳጅ መሆን አይቻልም ሉተር በእምነት ላይ ካለው አመለካከት ይልቅ ስለ አመክንዮ ያለውን አመለካከት ብዙዎች በተሳሳተ መልኩ እንዲረዱት በር ከፍቶአል ለምሳሌ በአብዛኛዎቹ በጸጻፋቸው ጽሑፎቹ አመክንዮን «ሥጋዊ» «ደደብ» «አውሬ የአግዚአብሔር «ጠላት» አና «የአታላይነት» ምንጭ እንደ ሆነ ይናገራል» ሉተር በአመክንዮ ላይ ያለው አመለካከት በይበልጥ በአሉታዊ መልኩ እንዲታይ አስተዋጽኦ ያደ ረገው ተጨማሪ ምክንያት አመክንዮን ንጹሕ ሰውን የሚዳራ «ሴተኛ አዳሪ» ብሎ መጥራቱ ብቻ ሳይሆን ግሪካዊወውን ፈላስፋ አርስጣ ጣሊስን ላዘሀ በቃላት መወረፉም ጭምር ነው ይኸውም በሉተር ዐይኖች ፊት አርስጣጣሊስ «የቅዱስ አስተምህሮ አውዳሚ ጥራዝ ነጠቅ «ዐዋቂና ጫሪ «የተረት ተረት ፈጣሪ» «ቅድስና የጐደለው የአደባባይ የአውነት ጠላት «የሚገማ ፈላስፋ «የመለስተኛና ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትርኢት ሰው» «አታላይ» «ባለጌ «ቀጣፊና ታማኝነት የጐደለው» «የአሕዛብ አውሬ» በሚል መገለጹ ነው ማንም ሰው ቀደም ሲል ከላይ የተቀመጡትን አሳቦች ያነበበ ሰው ሉተር በአመክንዮ ላይ ባለው አመለካከት ላይ ጽንፍ መያዙ አይቀርም ምን አልባትም ሉተር በጣም ጠንከር ያሉ ቃላቶችን መጠቀሙ አርስጣጣሊስን የነቀፈውን ያህል እሱኑ መልሶ ሊያስነቅፈው አንደሚችል ሊያሳስብ ይችላል ይህን ያህል በአርስጣጣሊስ ላይ ነቀፋ የሰነዘረው አርስጣጣሊስ እምነትና አመክንዮ እንዲጣመሩ የሚያስችላቸውን የሥነ አመክንዮን መዋቅር የዘረጋ ፈላስፋ በመሆኑ ነው የአርስጣጣሊስን የሥነአመክንዮ መዋቅር በተመለከተ አጠር ያለ መግለጫ በግርጌ ማስታወሻ ቁጥር ይመልከቱ ለምሳሌ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ፍልስፍናና ክርስትና የተጣመሩበት ዘመን ነበር እምነትና ክርስትና መጣመራቸው አመክንዮን የእምነት የበላይ አንዲሆን በር ስለከፈተ ማርቲን ሉተር ይህንን አጥብቆ ይቃወም ስለነበረ አርስጣጣሊስንም ጨምሮ ሊቃወም ችሏል ይህ በመካከለኛው ዘመን እምነትና የግሪክ ፍልስፍና የተጣመሩበት ሂደት ተምህሮነት ከከርክ ይባላል ለበለጠ ማብራሪያ የግርጌን እ ማስታወሻ ቁጥር ይመልከቱ ሉተር እጅግ በጣም በእምነት ላይ የሚያተኩር ሰው በመሆኑ አመክንዮ በክርስቲያናዊ አምነት ላይ ጫና ማሳደር የለበትም የሚል ጠንካራ አቋም የነበረው ሰው ነው በመሆኑም የክርስትና አምነት የግሪካውያንን ፍልስፍና ጥምረት ተቃወመ በሌላ በኩል በዚህ የጥምረት ሥራ ቶማስ አኪውነስና አውግስጢኖስ የተሳተፉበት ነበር ለምሳሌ ቶማስ የአርስጣጣሊስን ፍልስፍና በመጠቀም ከክርስትና እምነት ጋር አገናኝቶ በርካታ አስተምህሮን ገልጾአል እንደዚሁም ደግሞ አውግስጢኖስ የአፍላጦንን ፍልስፍና በመጠቀም ስለ ክርስቲያናዊ እምነት ምንነት ግንዛቤ ውን አካፍሏል በሉተር አጽንኦት መሠረት ግን ድነት ኩክ የእምነት ውጤት በመሆነ ስፍራ ሊሰጠው የሚገባው ከስነ አመክንዮ በላይ የአግዚአብሔር ቃል ነው በተምህሮነት መንገድ ከተ ሄደ ግን እንደ ሉተር ግንዛቤ የእምነትን ዋጋ የሚያሳጣው በመሆኑ የአርስጣጣሊስ አመክንዮ ደግሞ ይህን የሚደግፍ እንደሆነ ስላሰበ ተቃወመው እንግዲህ ወደ የትኛውም ድምዳሜ ከመድ ረሳችን በፊት ሉተር በአመክንዮ ላይ ያለውን አቋም በተለያዩ ደረጃዎች ማየት የተሻለ ስለሚሆን በሉተር ነገረ መለኮት ከር ላይ ጠለቅ ያለ ጥናት ያደ ረገው ሰው ቢኤ ጌሬሽ ዉጺለ ሉተር በአመክንዮ ላይ ያለውን አመለካከት ለመረዳት ከሦስት አቅጣጫዎች አመክንዮን ማየት እንደሚኖርብን ይጠቁመናል ሉተር አመክንዮን የሚጠቀመው በተለያዩ መንገዶች ነው የተፈጥሮ በተገቢው ክልል ሲንቀላሳቀስ አመክንዮ አመክንዮ የተፈጥሮ ወሰን ሲጥስ ከመንፈሳዊ ጉዳዮች ጋር የተገናኘ ዳግም የተወለደ አመክንዮ ነገር ግን ዘወትር ለቃሉ የሚገዛ ሉተር አመክንዮን የጠላው በሁለተኛው ዐይነት መንገድ አመክንዮ ጥቅም ላይ በመዋሉ ነውይህም ማለት ሉተር አመክንዮ የተፈጥሮን ወሰን ጥ በእምነት ላይ መሰልጠኑ አይዋጥለትም የተቀሩት የአመክንዮ መንገዶች ግን ይቀበላል ስለዚህ ሎ ርን የአመክንዮ አጠቃቀም በሚገባ ለማወቅ ኩ ጠቀሱት በየትኛው መንገድ አሳቡን እየገለጸ እንዳ መረዳት የግድ ይላል ይህ ካልሆነ ግን ትችታን ተገቢ አይሆንም በተጨማሪ ደግሞ ሙግታን የተፋለሰ ይሆናል በጥቅሉ ሉተር በእምነት ይ ያለው አቋም በጣም ጥብቅ በመሆኑ በአመክንዮ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበትን ቲስ ሲሰነዝር ይስተዋላል ይህ አውነት አንዳለ ሆኖ ግን ሉተር የአመክንዮ ተጻራሪ አለመሆኑ ዕውቁ ፈላስፋ ዊሊያም ክሬግ ባስቀመጠው እጥርጥር ህጠጠጴጺ ግልጽ ሆኖ እናገኘዋለን «ማርቲን ሉተር በትክክል አለቃዊና አገልጋያዊ የአመክንዮ ጥቅም በማለት ለይቶአል በዚህም አለቃዊው አመክንዮ ጥቅም ላይ የሚውለው አመክንዮ በወንጌል ላይና አልፎ ተርፎም ልክ እንደ አለቃ ቆሞ ወንጌልን በሙግትና በመረጃ መሠረት ላይ ሲፈርድ ነው አገልጋያዊ አመክንዮ ጥቅም ላይ የሚውለው ደግሞ አመክንዮ ለወንጌል ሲገዛና ሲያገለግለው ነው ብሎ ያምናል ስለዚህ ሉተር በደፈናው የአመክንዮ ተጻ ራሪ ተደርጎ ከመወሰዱ በፊት ሉተር የአመክንዮ ተገቢ ባልሆነ መንገድ በሥራ ላይ መዋል ተቃዋሚ ወይስ በጭፍን አመክንዮን የሚጠላ ነው ነው። የሚል ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ኖርበታል ሉተር የመጀመሪያውን አሳብ ማለት ካመክንዮን ያለ አግባብ በሥራ ላይ መዋል ይቀበልም አመክንዮ ለእምነት የአገልጋይነት ሶልግሎት የሚሰጠው ክሆነ በሉተር እይታ አምነትና አመክንዮ የእጅና የጓንት ወዳጅነት ይኖራቸዋል ማለት ነው ጃን ካልቪን ከ ክ ዓም ካልቪን በኛው ክፍለ ዘመን ተነስቶ የነበ ረውን የፕሮቴስታንት ተሐድሶ ካስፋፉ አንቱ የተባሉ ቁልፍ ሰዎች አንዱ ነው ካልቪን በአምነትና በአመክንዮ ላይ ያለውን አመለካከት ለመረዳት መሠረታዊ ከሆኑ የቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮዎች መነሣት የግድ ነውይሁን እንጂ ሁሉም ነገር በዚህ ስፍራ ሊዳሰስ ስለማይችል አንኳር የሆኑ ጥቂት አሳቦችን ብቻ አንቃኛለን ካልቪን አጽንኦት ሰጥቶ ከሚያነሣቸው አሳቦች ውስጥ የ«እግዚአብሔር ዕውቀት አስተ ምህሮ» ከ በርከዝክ ዐያ የከፍ ቪከበኳዐ ር አንዱና መሠረታዊ የካልቪን ትምህርት አካል ነው ካልቪን ሰው ፈጣሪውን እንዲያውቅ ተደርጎ መፈጠሩን ይናገራል እንዲያውም «በሰው አእምሮ በተፈጥሮ መለኮታዊ ኃይልን ማወቅ አሰለ ይላልእንደዚህ ሰው አባባል ለሰው ልጅ የፈጣሪን መኖር እንዲያስተውል ሌላው አጋዥ ነገር ቢኖር ፍጥረት ነው ይህን ነገር ካልቪን እንዲህ በማለት ይገልጸዋል «እግዚአብሔር ራሱን በፈጠረው ዓለም ገልጦአል ቀን በቀን ደግሞ ራሱን ያሳያል በመሆኑም ሰዎች በሠራው ሥራ እርሱን ሳያዩ ዓይናቸውን መግለጥ አይችለም» ከቢህ አሳብ መረዳት እንደሚቻለው ለካልቪን ስለ ፈጣሪ ለማወቅ የመጀመሪያ ደረጃ የፈጣሪን የእጆቹን ሥራ ማየት መሆኑን ነው ይህም ከመዝሙረኛው አሳብ ጋር መጣጣመን ልብ ይሳል ሰማያትም የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች ሌሊትም እውቀትን ትናገራለች መዝ ይህ እውነት እንደ ተጠበቀ ሆኖ ግን ሰው በተ ፈጥሮ ዕውቀት ብቻ ሊድን እንደማይችል ካልቪን ሳይጠቅስ አላለፈም የተፈጥሮ ዕውቀት ጥቅም ለሰው ልጅ የፈጣሪውን መኖር ጠቋሚ እንደ መሆኑ ስው ላለማመን የሚያመካኝበት ነገር እንዲያጣ የሚያደርገው ነው ስለዚህ ሰው ወደ ሙሉና ወደሚያድነው ዕውቀት እስካልመጣ ድረስ ድነት አያገኝም ካልቪን ስለ ድነት ዕውቀት ሲናገር ጠበብ አድርጎ የሚያሳየን ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት አስፈላጊነት ነው «ምንም እንኳ ላለማመን የምናመካኝበትን ነገር አንድናጣ የአግዚአብሔር የክብሩ ግርማ በፍጥረቱ የተገለጠ ቢሆንም ፈጣሪ ያችንን በሚገባ ለማወቅ ተጨማሪና የተሻለ ረዳት ያስፈልገናል ከዚህ የተነሣ ራሱን በቅርበት ለገለጠላቸው ሰዎች የቃሉን ብርፃን በላያቸው ላይ አንደ ልዩ ዕድል አብርቱላቸዋል ቅዱሳት መጻሕፍት የተምታታውን በአአምሮአችን ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ፅውቀት ግልጽ ያደርጉልናል እርሱንም እግዚአብሔርን በተለየ መልኩ ይገልጠልናል ከተፈጠሩ ነገሮች ስለ አግዚአብሔር ልናገኝ የምንችለው ዕውቀት እውነት ሆኖ እያለ ግን ካልቪን አንደ ገና ሲመክረን «ሰው ስለፈጣሪው በማወቅ ጥሩ ርምጃ ወደ ፊት መጓዝ ከፈለገ ጆሮዎቹን ለአግዚአብሔር ቃል መስጠት አለበት ማንም ሰው ቢሆን የቅዱሳት መጻሕ ፍት ተማሪ ካልሆነ በጣም አናሳ ዝቅተኝ የሚባልለትን የትክክለኛና የጤናማ አስተምህሮ ጣዕም እንኳ ሊያገኝ አይችልም ካልቪን ለቅዱሳት መጻሕፍት የላቀ ስፍራ የሚሰጥ ቢሆንም አንኳ ተአማኒነታቸውን ግን ለማረጋገጥ የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን ወይም የሰውን አመክንዮ ሳይሆን የሚያነሣው የመንፈስ ቅዱስን ውስጣዊ ምስክርነትን ያስቀድማል ቃል በቃልም አንዲህ ይላል «ቅዱሳት መጻሕፍት ለእግዚአብሔር የድነት ዕውቀት በቂ ናቸው ይህም እውን ሊሆን የሚችለው ውስጣዊ በሆነ በሚያሳምን በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ላይ የተመሠረተ ሲሆን ብቻ ነው አንግዲህ ካልቪን ስለ እግዚአብሔር ለማወቅ ፍጥረት አስፈላጊ መሆኑን ቢያምንም ለድነት ዕውቀት ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያስፈልጉት ያሰምርበታል ስለዚህ በካልቪን አካሄድ የአነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ተአማኒነት የሚረጋገጠው በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ብቻ ከሆነ ስለ አምነትና አመክንዮ ምን ዐይነት አመለካከት እንዳለው አሁን መጠየቅ እንችላለን እስቲ ቀድመን አንደኛውን ገጽታ እንመልከት እምነትን ካልቪን አምነት ምን እንደ ሆነ ሲናገር «አምነት ጽኑና ተአማኒነት ያለው ለእኛ የሆነ የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ዕውቀት ነው ይህም ፅውቀት የተመሠረተው ለግንዛቤአችን ይሆን ዘንድ በክርስቶስ በኩል በተገለጠው በጸጋው ተስፋ እውነት ላይ ነው እውነቱም በልባችን ላይ በመንፈስ ቅዱስ ታትሞአል ለካልቪን የአምነት መሠረት አመክንዮ ወይም የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ሳይሆን የአግዚአብሔር ቃል ነው «አምነት በጥቂቱ እንኳ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ከተፋታ ከተላለፈ ተፈ ጥሮውን ያጣዋል ውጤቱም ግልብ እምነትና ስሕተት ይሆናል ቃሉ የእምነት መሠረት ነጡ ቃሉ በሌለበት እምነት አይኖርም አምነት ትርጉም እንዳለው ካልቪን ያምናል ሆኖም ግን ለእርሱ የአምነታችን መሠረት የእግዚአብ ሔር ቃል ነው የእምነትን ይዘት ልናገኝ የምንችለው ከቃሉ ይሆናል ስለዚህ እምነት ከአግዚአብሔር ከራሱ ዘንድ የሚሆንልን ነገር እንደ ሆነ መረዳት እንችላለን በመሆኑም ፌ ትክክለኛ አምነት በራሳችን ጥረት ማግኘት አንችልም ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ስለ ልጅነታችን መብት በሚመሰክርልን ጸጋ ነው በካልቪን እይታ የአምነት ምንጭ አግዚአብሔር ይሁን እንጂ «የአምነት መገለጫወ ስንፍና ሳይሆን የአግዚአብሔር ዕውቀትና ፈቃዱ ነው» ሁለተኛው ገጽታ አመክንዮ ነው የካልቪን እምነት ሙሉ በሙሉ የተያያዘው ከእግዚአብሔር ጋር ነው የሚለው አተያይ ሰው የራሱን አመክንዮ በመጠቀም ሊያከናውናቸው የሚችላቸው ነገሮች የሉም ማለት ነው። የሚል ጥያቄ ሊፈጥር ይችላል ካልቪን የሰው አመክንዮ ከአምነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የበኩሉን ሚና ሊጫወት አንደሚችል የሚረዳው ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ነው ይህ በመሆኑ ካልቪን ሲናገር «ሰው ደግና ክፉ ነገርን የሚለይበት ነገሮችን የሚረዳበትና የሚፈርድበት የአመክንዮ ኀይል የተፈጥሮ ስጦታ ነው ስለዚህ አመክንዮ ሙሉ ለሙሉ የተደመሰሰ አይደለም ካልቪን የሰው አአምሮ ከኀጢአት የተነሣ ስለተ በላሸ አመክንዮ በራሱ የአግዚአብሔርን እውነት አንድንረዳ የሚያግዘን ዋና መንገድ አይደለም የሚል አቋም አለው ይህ ማለት ግን አመክንዮ ሙሉ ለሙሉ ፋይዳ ቢስ ነው ማለት አይደለም በአርግጥ ለማያምኑ ሰዎች ቅዱሳት መጻሕፍት የአግዚአብሔር ቃል መሆናቸውን ለማረጋገጥ መሞከር ትርጉም የለሽ ነው ይህም በእምነት ብቻ የሚታወቅ በመሆኑ ነው «ምንም እንኳን አንድ ሰው ውጤታማ በሆነ መልኩ የእግዚአብሔርን ቃል ከተቃዋሚዎች ጥቃት ሊታደግ ቢሞክር ያ ሰው በተ ቃዋሚዎች ልብ ውስጥ ከአግዚአብሔር የሆነ ትክክለኛ እምነት ሊመሠርት አይችልም በዚህ ረገድ ካልቪን የአመክንቶ ተቃዋሚ ሳይሆን የአመክንዮን የእምነት ነገር በመረዳት ረገድ ያለውን ብቃትና ውሱንነት ገላጭ ነው «በራሳቸው መረጃ ዎች ጽኑ እምነት ሊያመጡ አይችሉም ይህም የሰማዩ አባት ግርማውን በዚያ ቦታ እአስኪገልጥ ለቅዱሳት መጻሕፍት ከክርክር ያለፈ አክብሮት እስኪያመጣ ድረስ ነው በአጭሩ የካልቪን አካፄድ የሰው አመክንዮ በእምነት ጉዳይ ላይ የቅዱሳት መጻሕፍትና የመንፈስ ቅዱስ ውስጣዊ ምስክርነት ያህል ሰውን የማሳመንም ይሁን የመለወጥ ኃይል የለውም ሆኖም ግን አመክንዮ ከእምነት ጋር የተፋታ ነገር አይደለም ለማንኛውም ካልቪን ስለ ራሱ በተናገረው ሀሳቡን አእንቋጭ በራሴ በኩል ታላቅ ክህሎት ወይም አንደበተ ርቱፅነትን ባልጎናጸፍም አንኳ እግዚአብሔርን የሚንቁትን የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣን በብል ጠታቸውና በቀልዳቸው ሲያብጠለጥሉ የሚፈልጉትን ሰዎች ክርክር መግጠም ካለብኝ ልቅ አፋቸውን በቀላሉ ጸጥ ለማሰኘት ወኔው አለኝ ብሌዝ ፓስካል ዓም በው ክፍለ ዘመን በፈረንሳይ አገር ተወ ልዶ የነበረ የሂሳብ ሊቅ ፈላስፋና የፈጠራ ሰው ነው ፓስካል ስለ አመክንዮና እምነት ያለው አመለካከት ከዚህ ቀደም ካየናቸው ሰዎች ጋር የሚመሳሰል ነው እናም እንደዚህ ሊቅ ኦባባል ሰው ትልቅ ነው ሰው ከኃጢአት የተነሣ ደግሞ የትልቅነቱን ማፅረግ ሊያጣ የበቃ ፍጡር ነው የሆነ ሆኖ ግን የሰው ተፈጥሮ የሚያስደንቅ ገጽታ አለው ሰው ስለ ራሱ የሚኖረው አይታ ሚዛናዊ የሚሆነው የኃይለኛነቱን ያህል ደካማ ማንነቱን ዐውቆ ሲኖር ነው ፓስካል በይፋ እንደ ተናገረው «እኛ በትዕ ቢት በምኞት በፍትወት በድካም በችግር እና ፍትሕን በማጓደል አንደ ተሞላን ካላወቅን ዕውራን ነን ይህ ብቻ አይደለም ፓስካል ስለ ሰው ኃጢአተኛነት ሲናገር ሰው በራሱ ችሎታ ከገባበት ችግር ነጻ ሊወጣ አይችልም ይላል ለዚህም ነጻ የሚያወጣውን ፈጣሪውን በአምነት ሊገናኘው የግድ እንደ ሆነም አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል ቀጥሎም ከዚህ የተነሣ ሰው ችግር ውስጥ እንዳለ ዘንግቶ ስለ አግዚአብሔር የሚኖረው ዕፅውቀት ትዕቢት ያስከትላል ፓስካል ወደ መፍትሔ ሲመጣም እንዲህ ይላል ሰው ያለ እግዚአብሔር ደግሞ ስለ ራሱ ችግርና ደካም ማወቁ ተስፋ መቁረጥን ያመጣል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማወቁ ሚዛኑን የጠበቀ ዕውቀት እንዲኖረው ያደርጋል ምክንያቱም በአርሱ ክክርስቶስ በኩል እግዚአብሔርንም ድካሙንም ማግኘትና ማወቅ ስለሚችል ነው» በሌላ አነጋገር ክርስቶስን ባወቅን መጠን ስለ ራሳችን ትክክለኛ ግንዛቤ እንጨብጣለን ከዚያም ባሻገር ስለ እግዚአብሔር ያለን ዕውቀት ያለ ክርስቶስ የተሟላ አይሆንም ማለት ነው ስለዚህ ለሰው ልጅ ክርስቶስን ማወቅ ወሳኝ ነው ፓስካል ስለ ሰው ያለው አመለካከት ሰው ከኃጢአተኝነቱ የተነሣ ባሕርይው እክል እንደገጠመው ያመለክታል ይህ ደግሞ በሰው አምነትና አመክንቶ ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ መኖሩ አይቀሬ ነው እምነት ለፓስካል «ከማመን ርምጃ ወይም ወደ ክርስቶስ ለድነት ከሚደረግ ጥሪ ይበልጣል ይልቁንስ እምነት ሕያው ሂደት ረጅምና በሥርዐት የተካነ የሕይወት ዘመን ፍቅር ለውጥ እና የተሰጠ የክርስቲያን ባሕርይ ነው ከዚህም ባሻገር እምነት ለፓስካል «ከማ ረጋገጫ ክር ይለያል አንዱ ምድራዊ ሰዋዊ ነው ሌላው እምነት የአግዚአብሔር ስጦታ ነው ይህ በሰው ልብ ውስጥ አግዚአብሔር የሚያስቀምጠው አምነት ነው ማረጋገጫ ግን ሁል ጊዜ መሣሪያ ርዐ ነው። ሰው ወደ መለኮታዊ መገለጥ መምጣት እንዳለበት ግልጽ ቢሆንም እንኳ የአምነትና የአመክንዮ ሚዛን መጠበቅ አለበት «ሁሉን ነገር ለአመክንዮ በናስገዛ ሃይማኖታችን ያለ ምንም ምስጢራዊና ተአምራታዊ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ክሥተቶች ይቀራል የአመክንዮንም መርሖች ብንጥስ ደግሞ ሃይማኖታችን ትርጉም የለሽና እርባና ቢስ ይሆናል በሌላ አገላለጽ ለፓስካል አመክንዮና እምነት በየራሳቸው መንገድ ጠቃሚ ናቸው በመሆኑም አመክንዮና እምነት የየራሳቸውን አስተዋ ጽኦ እንዲያበረክቱ ከተፈለገ ጥቅማቸው ሊታወቅ ይገባል አንዱ የሚሰጠው ጥቅም በሌላኛው ወገን ስለማይተካ ከሁለቱም ሊገኝ የሚችል ጥቅም ለሃይማኖታዊ አምነት የተሟላ ገጽታ ይሰጠዋል ፓስካል እምነትና አመክንዮ በየራሳቸው አቅጣጫ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ እንደ ሆኑ ይናገራል ሆኖም ግን «አመክንዮ የእምነትን ያህል ስለ አግዚአብሔርና ስለ ሕይወት ምንነት አንድናውቅ አያስችለንም ይህም በእምነት ሊገኝ የሚችል ዕውቀት በመሆኑ ነው እግዚአብሔርን ሊለማመድ የሚችለው ልብ በመሆኑ ልብን ደግሞ በአመክንዮ መድረስ አንችልም በፓስካል እይታ የአመክንዮን ገደብ መረዳት ከሰው ከራሱ ማንነት ውሱንነት ጋር የተገናኘ እንደሆነ ማየት እንችላለን ይህ ደግሞ የፓስካልን የአመክንዮ ተጻራሪ መሆኑን ሳይሆን ልኩን ገደቡን ያወቀ አንደ ሆነ ያሳያል የሰው አመክንዮ አንደ ፓስካል አመለካከት ሁል ጊዜ ውሱን ነው ይህም የሆነው ሰዎች ስለ ታላላቅ መንፈሳዊ ጉዳዮች ለማወቅ በእግዚአብሔር መገለጥ እስካልተደገፉ ድረስ በዕውቀታቸው ውሱን በመሆናቸው ነው»ፓስካል ሰው በራሱ ጥበብ ብቻ በመታገዝ የእግዚአብሔርን እውነት ማወቅ አዳጋች እንደሆነ በማመን የእግዚአብሔርን ዕርዳታ አማራጭ የሌለው ነገር አድርጎ ያቀርባል አንግዲህ ስናጠቃልል ፓስካል እምነትን ላቅ አድርጎ ይመለከተዋል አመክንዮን በሚመለከት ደግሞ እንዲህ ይላል «ክርስትና የሚያስተምረው ትሕትና አመክንዮን ለመለኮታዊ መገለጥ መገዛትን ሀከፎጠዘዚ ማድረግን ያካትታል «መገዛትና አመክንዮን መጠቀም ልክ የሆነውን ክርስትና ይፈጥራልኖ አመክንዮ ትክክለኛ ተግባሩን ሊፈጽም የሚችለውለእምነት ተገቢውን ሥፍራ በመስጠት ጥቅም ላይ ሲውል ነው ይህም የአመክንዮን ለእምነት መዝት የተባለውን ሃሳብ ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ያደርገዋል ፓስካል የአግዚአብሔርን ታላቅነት ከመረዳቱ የተነሳ ሰው ውሱን እንደሆነ ያምናል ያለ እምነት ደግሞ በአመክንዮ ብቻ ስለ አግዚአብሔር ለመረዳት ሰው መልፋት እንደሌለበት ያስገነዝባል የታሪካዊ ዳራ ግምገማ ከአውግስጢኖስ እስክ ብሌዝ ፓስካል ያለው ጊዜ ሲታይ እምነትና አመክንዮ የተጣመሩ እርስ በአርሳቸው የማይጣረሱ መሆናቸውን ልብ ይላል የእነሺህ ታላላቅ የቤተክርስቲያን ታሪክ የጀርባ አጥንት የሆኑ ሰዎች እምነትና አመክንዮን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መረዳታቸው ለክርስቲያናዊ ሥነመለኮት መጎልበት ከፍተኛ መሠረት ጥሎ አልፎአል ለቅዱስ አውግስጢኖስ እምነትና አመክንዮ የተፋቱ ሳይሆኑ ተጣምረው የየራሳቸውን ሚና የሚጫወቱና ለቅዱሳት መጻሕፍት ተገዥ መሆን ያለባቸው ነገሮች ናቸው ይህ ደግሞ አውግ ስጢኖስን ለእምነት ያለውን ላቅ ያለ ስፍራ አመልካች ነውር ቶማስ አኪውነስ ደግሞ ከአውግ ስጢኖስ ጋር ሲስተያይ በእምነትና በአመክንዮ አቋሙ የሚያመሳስለው ሁለቱንም ነገሮች በሥራ ላይ ሊውሉና ላይውሉ የሚችሉበትን መንገዶች በማሳየት ረገድ ነው እምነት ከአመክንዮ ለሚያልፉ ነገሮች ረጂነቱ ከፍ ያለ መሆኑና አመክንዮ ደግሞ የእምነትን ፅርዳታ ሳንሻ ልንረዳቸው ለምንችላቸው ነገሮች የበኩሉን አስተ ዋፅኦ ማድረጉ መታመኑ ነው የሉተርን አቋም ስንቃኝ ስለ እምነት ያለው አመለካከቱ ለአመክንዮ ካለው አመለካከቱ ላቅ ያለ ቢሆንም አመክንዮን በተመለከተ ደግሞ ከአጠቃቀም የተነሣ የአምነትን መሠረት ሊያናጋ ስለሚችል አመክንዮ ተቀባይነት ማግኘት የሚኖርበት ማጣሪያ ውስጥ ገብቶ ጤናማነቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው ይህም አመክንዮ በእግዚአብሔር ቃል ሥር ያለ በመሆኑ ነው ከዚህ የተነሣ ደግሞ አመክንዮ የእምነት አገልጋይ ሊሆን ይገባል ይህም በሉተር አካፄድ አመክንዮ ከእምነት ጋር ቁርኝት የለውም ለማለት ሳይሆን ከእምነት ጋር ያለውን ዝምድና ጠብቆ ሊዘልቅ የሚችለው ውሱን መሆኑ ታውቆ ያለቦታው በሥራ ላይ በማይውልበት ሁኔታ ብቻ ነው ወደ ካልቪን አቋም መለስ ስንል ደግሞ አመክንዮ ከሰው ኃጢአተኛነት የተነሣ ለጤናማነት ማጣት የተጋለጠ በመሆኑ ያለ እምነት ጠቀሜታ አይኖረውም የኃጢአት ውጤት በአመክንዮ ላይ ያመጣው ጠባሳ በእምነት በኩል ሊቀረፍ ሲችል ትልቁን ሚና ሊጫወት የሚችለው ግን አሁንም እምነት ነው አመክንዮ ሰካልቪን ውሱን ነው የብሌዝ ፓስካል አቋም የእስከ አሁኖቹን አቀራረብ የተከተለ ነው በመሆኑም ፓስካል አመክንዮ አምነትን ተከታይ አንጂ ቀዳሚ ሊሆን እንደማ ይገባው ይናገራል ሰው በኃጢአት የወደቀ በመሆኑ ስለ እግዚአብሔር ስለ ራሱና ስለ ፍጥረት በንጹሕ መንገድ ማሰብ የሚችለው አመክንዮው በእምነት ተገርቶ ከፈጣሪ ጋር ሰው በሚያደርገው የግል ግንኙነት ነው ስለዚህ ፓስካል አመክንዮ ውሱን ቢሆንም ከእምነት ጋር ተስማምቶ ሊያገለግል እንደሚችል ያምናል ስለዚህ በአውግስጢኖስ በአኪውነስ በሉተር በካልቪንና በፓስካል መካከል ያለው የጋራ አቋምየአመክንዮና የአምነት ጥምረት እንደተጠበቀ ሆኖ የእምነት የበላይ መሆንና የአመክንዮ ውሱንነት ነው እነሂህሦሁ ሰዎች የአመክንዮን ውሱንነት ያጎሉት የሰው ልጅ በተፈጥሮው ውሱን ከመሆኑ የተነሳ ነውበፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለው ግንኙነት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ባለመሆኑ ፍጡር ሁልጊዜ ፈጣሪው በሁሉ ነገር ኢውሱን በሆነ መልኩ የላቀ እንደሆነ መረዳት ይኖርበታል ስለዚህ እምነት አመክንዮን ሳይጻረር በአመክንዮ ቁጥጥር ሥር ደግሞ ሳይሆን አልፎት ሊሄድ አንደሚችል ግልጽ ሊሆን ይገባል በተለይም የአምነትና የአመክንዮ መደጋገፍ በክርስትና አምነት ውስጥ ኮኛ ክፍለ ዘመን በፊትና በኋላ አንድ ዐይነት ገጽታ የለውም በ እና ከስፒኖዛ እስከ ጀርመናዊው ለዘብተኛ የፕሮቴስታንት ነገረ መሰኮት ጀማሪ ሽየርማከር ባለው ጊዜ ውስጥ አመክንዮአዊ የክርስቲያና እምነት መሠረት ተለወጠ ከዚያ በፊት አመክንዮና አምነት አብረው መሥራት አይቸግራቸውም ነበር አመክንዮ ለአምነት መረጃ ያቀርብ ነበር ነገር ግን ከስፒኖዛ አስከ ሽየርማከር ባለው ጊዜ ውስጥ መረጃ አመክንዮአዊ በሆነ መንገድ ክርስቲያናዊ አምነት ሊረዳ ይችላል የሚለው አሳብ ራሱ ተተወ ይህም ከመሆኑ የተነሣ በአምነትና በአመክንዮ ላይ የአመለካከት ልዩነቶች እየሰፋ መጡ። ይሁን እንጂ አንዳንድ በአመክንዮ ብቻ የሚያምኑ ሰዎች በተወሰነ ደረጃ ብቻ ለእምነት ስፍራ ሰጥተዋል ይሁን እንጂ እምነት አሁንም አመክንዮን እስካገለገለ ብቻ ነው በዚህ አመለካከት ሥር የኛው ክፍለ ዘመን ዕውቁ ፈላስፋ ኢማኑኤል ካንት በተወሰነ ደረጃ አምነት አመክንዮን ካገለገለ ተቀባይነት ሊኖረው እንደሚችል ቢያምንም ሌላኛው የኛው ክፍለ ዘመን ፈላስፋ ስፒኖዛ ግን ሥር ነቀል የሆነ የአመክንዮአዊነት ብቻ ተቀባይ ነው በዚህ በአመክንዮ ብቻ አመለካክት ሥር ኢማኑኤል ካንትና ቤኒዲክት ስፒኖዛ ይገኙ ብታል አመክንዮ በመገለጥ ላይ መገለጥ ጪዕ አስፈላጊ ነው ሆኖም ግን አመክንዮ ከመገለጥ ይልቅ ተቀባይነት ያለው ነገር ነው መገለጥ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ አመክንዮ የሚያስገኘው ጥቅም የበለጠ ነው ከአመክንዮ ጋር ለሚጻረር ነገር ብዙ ስፍራ መስጠት አስፈላጊ አይሆንም መገለጥ ጥቅሙ ባይካድም ጐልቶ መውጣት ያለበት አመክንዮ ነው በዚህ አመለካከት ሥር የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን አበው መካከል ዮስጦስ ሰማዕትና ቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያ ይገኙበታል በተጨማሪ የዚህ አመለካከት ሁነኛ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉት ለዘብተኛ አቋም ያላቸው የነገረ መለኮት ሊቃውንት ናቸው ይህ ጎራ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ውስጥ ጣልቃ አይገባም ብለው የሚያምኑትን አምላከኛ ውያንን ጭምር ያካትታል ስለ ለዘበተኛነት በ በግርጌ በቁጥር ሥር አጠር ያለ ማብራሪያ ተሰጥቷል ሟሰ በአመክንዮ ላይ መገለጥ በአመክንዮ ላይ የበላይነት አለው አመክንዮ በመገለጥ ሥር አንጂ መገለጥ በአመክንዮ ሥር ሊሆን አይገባም አመክንዮ ስፍራ ሊኖረው የሚችለው መገለጥን ሲከተል እንጂ ሲያስከትለው አይደለም አመክንዮ በመገለጥ ላይ የተደገፈ እንጂ የአለቅነት ሚና አይጫወትም በዚህ አመለካከት ሥር ጠርጡሊያኖስና ኮርነሊየስ ቫንቲል ይገኙበታል ፎገለጥና አመክንዮፁ እምነት ሰውን ወደ መረዳት ይመራዋል ግንዛቤ ካእምነት የሚገኝ የአመክንዮ የጥረት ውጤት ነው አመክንዮ የእግዚአብሔርን መኖር እንድናውቅ ያግዘናል ሆኖም በርካታ ከአመክንዮ ችሉታ ዐልፈው የሚሄፄዱ አውነቶች አሉ እነሺሂህን አመክንዮን የሚያልፉ እውነቶች ደግሞ ልንረዳቸው ልናውቃቸው የምንችለው በእምነት ነው አመክንዮ ግን ስለምና ምናቸው እውነቶች ተገቢነት ግንዛቤ እንድንጨብጥ ያግዘናል በዚህ በእምነትና አመክንዮ የጥምረት አገልግሎት አመለካከት ሥር ቅዱስ አውግስጢኖስና ቶማስ አኪውነስ ይገኙበታል በእነሺፒህ በአምስቱም አመለካከቶች ሥር የተጠቀሱ ሰዎች ማንነት አጠር ባለ መልኩ በዚህ መጽሐፍና መጨረሻ ላይ ተብራርቷል ግፎገማ ከላይ በታሪካዊ ዳራ ሥር ከተዘረዘሩት ከአምስቱ አመለካከቶች ውስጥ በአራቱ ላይ ብቻ እንነጋገራለን አምስተኛው አመክንዮና መገለጥ የሚለው አመለካከት ከላይ ከአውግስጢኖስ እስክ ብሌዝ ፓስካል ድረስ ካለው የእምነትና የአመክንዮ ድምዳሜ ጋር አንድ ዐይነት በመሆኑ ነው ይህም አቋም እምነትና አመክንዮ የተፋቱ ነገሮች ሳይሆኑ የተጣመሩ ናቸው የሚል አቋም ነው እንግዲህ መገሰጥ ብቻ አመክንዮ ብቻ አመክንዮ በመገለጥ ላይና መገለጥ በአመክንዮ ላይ የሚሉትን አቋሞች ስናጠቃልል እያንዳንዱ አቋም በራሱ መንገድ በተ ወሰነ ደረጃ ሊያስፄድ የሚችል አውነት ቢኖረውም ደካማ ጐኖችም እንዳሉት ልብ ይሏል ሀ መዝጥ ብቻ መገለጥ ብቻ የሚለው የኪርክጋርድ የባርትና የቡልትማን አመለካከት የአመክንዮን ከመገለጥ ጋር ያለውን ዝምድና የሚክድና መገለጥን የመጀመሪያም የመጨረሻም የእውነት ማወቂያ መንገድ አድርጎ የሚያስቀምጥ አካፄድ አለው በርግጥ በአንድ ጐኑ መለኮታዊ እውነት በመገለጥ መታወቁ እውን ቢሆንም ይህንኑ ለመረዳት ሥራ ላይ የዋለ አመክንዮ እርባና ቢስ እንደ ሆነ መታሰቡ አመለካከቱን ኢሙሉዕ ያደርገዋል ለምሳሌ አመክንዮ ጥቅም ላይ ሳይውል ይህን አቋም እንኳ መግለጽ አይቻልም ለ አመክንዮ ብቻ አመክንዮን ብቻ የአውነት ተቀባይ መስፈርት በማድረግ የተነሣው የአማኑኤል ካንትና ቤኒዲክት ስፒኖዛ አመለካከት የመገለጥን አስፈላጊነት ከመካዱ ባሻገር ለአመክንዮ የማይገባውን የብቃት ማረጋገጫ ያስጨበጠ ነውሱ የአመክንዮ ጥቅም ግልጽ ቢሆንም ሁሉ ነገር በአመክንዮ ብቻ ይፈታል ብሎ ማሰብ ከአውነት ውጭ ሊሆን የሚችል በመሆኑ መገለጥ ብቻ ካሉት ክነ ባርት ኪርክጋርድና ቡልትማን አካፄድ ጋር በጽንፈኝነቱ የሚመሳሰል ሆኖ የአመክንዮን ውሱንነት ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው አመክንዮ ደግሞ ሊገልጻቸው ለማይችላቸው ነገሮች ደግሞ ምላሽ ሲሰጥ ብቃት ያንሰዋል ለምሳሌ እግዚአብሔር በባሕርይው አንድ ነው በአካል ሦስት ነው ሆኖም እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል ከዚህም የተነሣ ይህን እውነት ለማመን የመገለጥን አስፈላጊነት ለመቀበል የማይፈልግ ግትር አቋም ነው አመክንዮ በመገለጥ ላይ የሚል የዮስጦስ ሰማዕትና የቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያ አቋም አመክንዮን ከመገለጥ ገንጣይ ባይሆንም ሚዛኑን የጠበቀ አይደለም ይህም የሆነው መገለጥን በአመክንዮ ሥር በማድረግ ይገዛዋል በርግጥ በማወቅ ሥርዐት ውስጥ ኗበክበ አብየ አመክንዮ መገለጥን ሊቀድመው ይችላል ስለ እግዚአብሔር ለማወቅ አመክንዮን መጠቀም የግድ ነውና በሥነ ኑባሬ ሥርዐት በጩር ጪሮ ግን መገለጥ አመክንዮን ስለሚቀድመው አመክንዮ የመገለጥ የበላይ ሆኖ የሚቀር ከሆነ ውስንነቱ ተዘንግቶ በመገለጥ የሚታወቁ ነገሮች ተቀባይነት ያጣሉ በመሆኑም የአመክንዮ በመገለጥ ላይ መሠልጠነ ለመገለጥ ተቀባይነት ደንቃራ የሚሆንበት ሁኔታ የሚፈጥር ይሆናል ለምሳሌ የተአምራት የልፅለ ተፈጥሮአዊነትን ምስጢር በመገለጥ እንጂ በአመክንዮ ብቻ የሚፈታ አይደለም እንዲያው በደፈና ግን አመክንዮ በመገለጥ ላይ ይሠልጥን ከተባለ ልፅላ ተፈጥ ሮአዌነት ትርጉም የለሽ መሆን አለበት መ መገለጥ በአመክንዮ ላይ መገለጥ በአመክንዮ ላይ የሚለው በጠርጡሊ ያኖስና በቫንቲል የተወከለው አቋም የመገለጥን የበላይነት የሚያጐላ ነው በርግጥ ከሥነ ኑባሬ ሥርዐት ርበር ር አኳያ መገለጥ አመክንዮን መቅደሙ ልክ ነው። ይህም ፃይማኖታዊ እምነቶች ለአመክንዮአዊ ግምገማ የተጋለጡ ሊሆኑ አይችሉም የሚሉ ናቸው እነሺህን ጽንፎች ማስወገድ የራሱ የሆነ ጠቀሜታ አለው አሜሪካዊው ክርስቲያን ፈላስፋ ስቴፈን ኢቫንስ እንዳስቀመጠው «አንድ ሰው በእምነትና በአመክንዮ ላይ ያለው አመለካከት ፍልስፍናና ሃይማኖት አንዱ ለሴላኛው ጠላት ሳይገናኙ በሰላም አብረው መኖራቸውን ወይም የሚተባበሩ እንደ ሆነ አድርጐ እንዲወስን ሊያደርግ ይችላል ይህም ብቻ ሳይሆን የእምነትና የአመክንዮ ዝምድና ችግር እንደ ኢቫንስ እምነት በፍልስፍና ሃይማኖት እና በነገረ መለኮት ውስጥ ማዕከላዊ ጥያቄ ነው አመክንዮና አምነት ከተነጣጠሉ ከሚፈጠሩት ችግሮች አንዱ ለየብቻቸው መጓዝ የማይችሉ መሆናቸው ነው በሌላ አነጋገር አመክንዮ ለእምነት አምነትም ለአመክንዮ የሚያስፈልግበት ጊዜ አለ አንዱ ያለ ሌላኛው ትርጉም ሊያጣ የሚችልበት ሁኔታም ሊኖር ይችላል ይህም ሆኖ ግን እምነትም ሆነ አመክንዮ አንዱ በሌላው ላይ አላስፈላጊ በሆነ መንገድ መሠልጠን የለበትም ሁለቱ ክርስቲያን ፈላስፎች ክሬፍትና ታሲሊ አንዳሉት «አመክንዮ የአምነትን የተስፋንና የፍቅርን ቀዳሚነት መጋፋት አንዳለበት አናምንም በአግባቡ ከተጠቀምንበት አመክንዮም ሆነ አምነት ጠቀሜታቸው የጐላ ነው ለምሳሌ የሥላሴ አስተምህሮ ሊጠቀሱ ከሚችሉ ነገሮች መካከል አንዱ ሊሆን ይችላል አመክንዮን በመጠቀም እግዚአብሔር በባሕሪዩ አንድ መሆኑንና ያን የመለኮት ባሕርይ ተካፋይ የሆኑ ሦስት አካላት አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ እንዳሉ ከሐሳብ ግጭት ነጻ በሆነ መንገድ ማሳየት ይቻላል ነገር ግን አግዚአብሔር አንድ አንጂ ሦስት አለመሆኑን በአመክንዮ ማረጋገጥ ደግሞ የሚቻል አይሆንም አዚህ ቦታ አመክንዮ ከእምነት ጋር ሳይቃረን ስፍራውን ለእምነት ይለቃል ማለት ነው ብዙ ምሳሌ ዎችን መጥቀስ ይቻላል የክርስቶስ ውልደት የክርስቶስ ሁለት ባሕርያት መለኮትና ትስብዕት ወይም ሰብአዊ በአንድ አካል መኖራቸው ታምራታዊ አሠራሮችና ሌሎችም ይገኘበታል ሁሉም ነገር በአመክንዮ እንደማይፈታ ሁሉ በእምነትም አይፈታም «አመክንዮን በአምነት ላይ መጨመር ዕድገት ነው ነገር ግን ከእምነት በፊት አመክንዮ ምክንያት መጠየቅ ግን አይደለም ይህ የሚያስረዳን «እምነትና አመክንዮ ባላንጣዎች አለመሆናቸውን ነው ነገር ግን በኢምክኑአዊ ጥርጣሬ ፍላጐት ፕሮፓጋንዳ ፍርፃት ስንፍና ሐሳብና ተፋልሶ ላይ በኅብረት የሚዘምቱ ናቸው» እምነትና እመክንዮ ተስማምተው ሲሠሩ በሁለቱም ጥምረት የማይስማማው ሰው ነው ይህም የሚሆነው ከየሰው ርዕዮተ ዓለም ንጽሮተ ዓለምና የሃይማኖት ታሪካዊ ዳራ ልዩነት የተነሣ ነው ይሁን እንጂ የእምነትና የአመክንዮን ዝምድና ከእግዚአብሔርና ከሰው ማንነት አኳያ ብናየው የተ ሻለ ነው እግዚአብሔር በማንነቱ በዕውቀቱ በችሎታውና በሌሎች ባሕርያቱ ኢውሱን ነው ሰው ደግሞ ውሱን ነው በሁሉም አቅጣጫ ውሱን የሆነው የሰው ልጅ ስለ ራሱ ስለ ፍጥረት ስለሌ ሎች ሰዎች ስለ አውነታ ቭዜ የሚያውቃቸው ነገሮች የሚደገፉት በአመክንዮው አስቦ በሚደርስባቸው የማሰብ ውጤቶች አሊያም የቱንም ያህል ቢጥር ከአእምሮው ችሎታ የሚያልፉ ነገሮችን በአግዚአብሔር ኢውሱኑነትና ሉዓላዊነት በማመን በአምነት መቀበል በመቻሉ ላይ ነው ነገሮችን ለመረዳት በአመክንዮ ብቻ ከተደገፍን አምነት በአስተሳሰብ ሥርዐታችን ውስጥ ስፍራ አይኖረውም ማለት ነው ይህም ከአመክንዮ ችሉታ የሚያልፍ ማንኛውም ነገር ትርጉም ስለሌለው አምነት መፍትሔ ሊሆን አይችልም ለምሳሌ ሣራ በዘጠና ዓመት መውለዷ በአመክንዮ መንገድ ብቻ ሊፈታ አይችልም ይህን ለመቀበል ማመን አማራጭ የሌለው መንገድ ነው ይህ ደግሞ አምነትን ይጠይቃል ምክንያቱም እግዚአብሔር በችሎታው ያደረገው ከኛ አእምሮ መረዳት የሚያልፍ ነገር በመሆኑ ነው ይህ ሲባል ግን በሌላ ጐኑ ነገሮችን ለመረዳት ሁሌ አምነት ያስፈልገናል ማለት አይደለም ለምሳሌ መሆኑን ለማወቅ እምነት አያስፈልገን ይሆናል ምክንያቱም ዬ መሆኑ በራሱ ግልጽ በመሆኑ ነው ሌላ ምሳሴ ልስጥ አማኝ ያልሆነ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ ይጋጫል ብሎ ተአማኒነቱን አልቀበልም ቢል ቅዱሳት መጻሕፍት እንደማይጋጩ በአምነት እንዲቀበል መናገር ሳይሆን መፍትሔው አመክንዮአዊ መንገድ በመጠቀም ቅዱሳት መጻሕፍት እርስ በርስ እንደማይጋጩ ለማሳመን መጣርና ለዚህም ማረጋገጫ በመስጠት እውነትን ማሳየት ነው ግራ ለተጋባው ሰው መፍትሔ ሊሆንለት የሚችለው ስለዚህም የአመክንዮና የእምነት ዝምድና መታየት የሚኖርበት አንዱ ለሌላው ከሚያመጣው ዕገዛ አንጻር ነው ፒተርና ታሲሊ የሚባሉ ሁለት ክርስቲያን ፈላስፎች በጋራ በጻፉት መጽሐፋቸው እንደተናገሩት «መኪና ወደ ባሕር አጠገብ ሊያመጣህ እንደሚችል ሁሉ ሙግቶች ጳዌክክክ ወደ እምነት ሊያመጡህ ይችላሉ መኪና ሊዋኝ አይችልምፅ ባሕር ውስጥ በመዝለል ያን ማድረግ ያለብህ አንተ ነህ ሆኖም ግን በብዙ ርቀት ላይ ሆነህ ወደ ባሕር መዝለል አትችልም በመጀመሪያ በአምነት ወደ ባሕሩ የምትዘልበትን ቦታ እንዲያደርስህ መኪና ያስፈልግፃል እምነት መዝለል ነው ነገር ግን የሚዘለለው በብርፃን እንጂ በጨለማ ውስጥ አይደለም የብሌዝ ፓስካል ሀሳብ ደግሞ የበለጠውን በጠነከረ መንገድ የአመክንዮንና የእምነትን ትስስር አመላካች ነው ፓስካል ለምሳሌ ሐሳቡን ሲሰነዝር በመጀመሪያ ደረጃ በአመክንቶ መታመን ራሱ በአመክንዮአዊ መንገድ የሚረጋገጥ ነገር ሳይሆን በእምነት የሚወሰድ ርምጃ ነው» ይላል በአኔ አመለካከት እምነትንና አመክንዮን በማፋታትና በማጣመር ስለ ነገሮች የሚኖረን ግንዛቤ በእኩል ደረጃ ሚዛኑን የጠበቀ አይሆንም ነገሮችን ለአመክንዮ ብቻ መስጠት የዐቅማችንን ልክ እንዳናውቀው ያደርገናል ይህም በትዕቢት እንድንሞላ ያደርገናል ምክንያቱም ከአመክንዮ ጋር ሳይቃረን አመክንዮን ዐልፎ የሚሄድ እውነት አለና እምነት ብቻም ካልን መጠቀም እስከምንችለው ድረስ አእምሮአችንን እንዳንጠቀም የስንፍና እና የጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ባለቤቶች ያደርገናል አመክንዮንና አምነትን አጣምረን ከያዝን ብቻ ጥሩ ተጠቃሚዎች እንሆናለን አመክንዮና አምነት ባላቸው ግንኙነት አምነት የበላይ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም አመክንዮ ከተጠቃሚው ውሱንነት የተነሣ ውሱን አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ነው እምነት ግን ኢውሱን በሆነው አምላክ ላይ የሚደረግ አለኝታ በመሆኑ አመክንዮን ባይጻረርም የበላይነት ይኖረዋል። ይህ ማለት አመክንዮና እምነት አብረው ሲጓዙ እንደ ዊሊያም ክሬግ አባባል «መንፈስ ቅዱስ ስለ መሠ ረታዊ የክርስቲያን እምነት እውነት በሚሰጠው ምስክርነት በሙግትና በመረጃ ላይ በተደገፈው እምነት መካከል ግጭት ቢፈጠር ሥፍራውን መልቀቅ ያለበት የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ለሙግት ሳይሆን ሙግትና መረጃ የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ማስቀደም ይኖርባቸዋል በክርስትና እምነት ውስጥ የአመክንዮ ጠቀሜታ ግምት ውስጥ ቢገባም የእምነት የበሳይነት ደግሞ ለድርድር የሚቀርብ አይሆንም እንግዲህ እምነትና አመክንዮ መጣመራቸው ስለ ነገሮች አጥጋቢ ዕውቀት ኖሮን ተጠቃሚዎች እንድንሆን ያደርገናል ክዚህ ባሻገር ለእኛ ለክርስቲያኖች አምነት እጅጉኑ ጠቃሚ ነው «የእምነትና የአመክንዮ ጋብቻ በዐቃቤ እምነት ላዞ ውስጥ በጣም ጠቃሚ የሆነ ጥያቄ ነው እምነትና አመክንዮ የተጋቡ ወዳጆች መሆናቸው ቀርቶ የተፋቱ ከሆኑ ወይም ደግሞ እንደ ድመቶችና ወፎች የማይስማሙ ከሆኑ እምነትን መከላከል አዳጋች ነው እምነትን መከላክል አመክንዮን ከእምነት ጋር ለማገናኘት የሚደረግ ጥረት ነው በሌላ አገላለጽ እምነትን በአመክንዮ መሣሪያ እንደ መጠበቅ ነውጆ ምዕራፍ አምስት መሠረቶች የእምነትና የአመክንዮ ጥምረት ፋይዳ ሊታይ የሚገባው በተለያዩ ጊዜያት ተነሥተው ከነበሩ የታሪክ ክስተቶች አኳያ ብቻ ሳይሆን መሠ ረታዊ ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል ጭምር ነው ሀ እምነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእምነት መሠረት እግዚአብሔር ነው እምነት ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ የሚያበቃው የመግቢያ በር ነው ይሁን እንጂ በባሕርይው አምነት ጭፍን አይደለም የእግዚአብሔር ቃል ግልጽ አድርጎ እንዳስቀመጠው እምነት አማኙን ወደ ረጂውና ወደ በላዩ አካል የሚያስጠጋ ኃይል ነው የዚህን ሙሉ ገጽታ ለመረዳት የብሉይና አዲስ ኪዳንን የእምነት እይታ ማጤን ጠቃሚ ነው በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት የገለጹት ከጠሳቶቻቸው እጆ ለመዳን ከተፈጥሮ አደጋዎች ለማምለጥ ምሕረት ለማግኘት ለተስፋ ቃል መፈጸም ለዕለት ተዕለት ትሮ ፍላጎቶችና ሌሎችም ነገሮች ነበር ከዚህ የተነሣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት አቅጣጫ የለሽ እንዳልሆነ እንረዳለንሉ ሰዎች ሲያምኑ የእምነታቸውን ባለቤት ያውቃሉ ይህም ብቻ ሳይሆን የእምነታቸው ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር የሰጣቸውን እውነት በአምነት ተቀብለው ዘወትር ሊኖሩበት የሚለማመዱት ሕይወት ነው ጄ አይ ፓክር የተባለ ስመ ጥር የነገር መለኮት ምሁር በበኩሉ ስለ አዲስ ኪዳን አምነት ምንነት ጠቃሚ አሳብ ሰንዝሯል «እምነት በተቀበሉት እውነት መኖር ነው በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ የተመሠ ረተ እምነት ለእግዚብሔር ክብር እየሠራ ለእግዚአብሔር ጸጋ ምስጋና ይሰጣል። ምዕራፍ ሰባት ማጠቃለያ አምነት ከአለኝታ ከማመንና ከመታዘዝ አንጻር ሊታይ ይገባል እምነትና አመክንዮ ሲጣመሩ ለምሉዕ የነገሮች ግንዛቤ ዕድል ይኖረናል እምነት ብቻ የሚል ጽንፍ መያዝ ወደ እምነታዊነት ጠ ይወስደናል «አመክንዮ ብቻ» የሚለው ጽንፍ ደግሞ ወደ አመክንዮአዊነት ጽንፍ ይወስደናል ሚዛኑን የጠበቀ የአምነትና የአመክንዮ ግንዛቤ ከሁለቱም ትስስር አኳያ ይሆናል በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጐልቶ የወጣው የአምነት በላይነትና የአመክንዮ አገልጋይነት ነው ለዚህ ደግሞ አውግስጢኖስ ቶማስ አኩዊናስ ማርቲን ሉተር ጆን ካልቪን ብሌዝ ፓስካልና ሌሎችም ሰዎች ምስክሮች ናቸው እምነትና አመክንዮን ሊያፋቱ የሞከሩ ሰዎች አካፄድ ለብዙ ነገሮች አጥጋቢ የሆነ ገለጻ የመስጠት ዐቅም ሲያንሰው ይታያል በዚህ ረገድ ካንት ስፒኖዛ ኪርክጋርድ ባርትና ሌሎችም ሰዎች ተጠቃሽ ዓቸው የእምነትና የአመክንዮ ጥምረት አቋም ሚዛናዊነቱ ከአስከአሁኑ ውይይት ግልጽ ሊሆን የሚችል ነው ሲ ኤስ ሉዌስ እንደተናገረው ሖሐ እምነት አመክንዮ አንዴውኑ የተቀበላቸውን ነገሮች የመያዝ ጥበብ ነው አመክንዮንና አምነትን የማፋታቱ ግንዛቤ በዳንኤል ቴይለር እንደ ተባለው «አመክንዮ በእግዚአብሔር ማመን ኢአመክንዮአዊ ዝ እንደ ሆነ ያሳያል ብሎ ከማሰብ የበለጠ ጥራዝ ነጠቅ የአመክንዮ አጠቃቀም የለም» ይህ ልክ አይደለም ማንም ሰው ቢሆን በዚህ መልክ ሙግቱን ላጳጩከበ ቢገነባ የአመክንዮ ሆነ የእምነት ምንነት አልገባውም» የእምነትና የአመክንዮ ትስስር እንዲገባን ዊሊያም ክሬግ እንዳስቀመጠው ማመን ያለብን ነገር ቢኖር «ምንም እንኳ ሙግቶች እና መረጃዎች የአማኝን አምነት ለመደገፍ ጥቅም ላይ ሊውሉ ቢችሉም የእምነት መሠረት ግን አይደሉም ለአማኝ እግዚአብሔር የክርክር ማጠቃለያ አይደለም ነገር ግን የአብርፃዛምየይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ በውስጣችን የሚኖር ሕያው አምላክ ነው» አምነት እንደማያስፈልገን ማሰብ ከዐመጸኛው ባሕርያችን ሊመነጭ የሚችል አስተሳሰብ ነው ለአምነት ስፍራ ስንሰጥ ለእምነታችን ባለቤት የምንሰጠው የከበረ ስፍራ አለ በአመክንዮ ብቻ ስንደገፍ ራሳችንን በራሳችንና በሌሎች ነገሮች ላይ ጭምር መሾማችን ነው ይህ ሲሆን ደግሞ አመክንዮ የትዕቢት በር ይሆናል እምነት ግን የጸጋና የመለኮታዊ ጎይል መለማመጃ መንገድ ነው ከትፅ ቢት ማምለጫ መንገድ የአመክንዮ ለእምነት መገዛትና የእምነት በአመክንዮ ላይ መመሥረት ነው እምነት ትርጉም የለሽ ነገር እንዳይሆን አመክንዮአዊ መሠ ረት ያስፈልገዋል ሆኖም ግን እምነት ከአመክንዮ የበለጠ የመለኮታዊ አውነቶች ምንነት ገላጭ ነው ይህም ደግሞ አመክንዮን በመሣሪያነት በመጠቀም ነው ስለዚህ እምነትና አመክንዮ የተጣመሩ ወይስ የተፋቱ።