Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ሰዎች ይህንን እናስተውል የኛ ልጆችና የልጅ ልጆቻችን በያሉበት ቀርተው አገራችን የሚሉትን የባእድ አገር እየሠሩ በማሳደግ ላይ ስለሚቆዩ የአለም ማሕበራዊ ኢኮኖሚና የፖለቲካ ሁኔታ ይሻሻላል እኛ ተሰደን በተሰደድንበት ሌላውን አገር ማሳደጋችን የአለም ስደተኞች ሁሉ ይህንን ማድረጋቸው አጠቃላይ ሉላዊ ግንባታ አገራችን ኢትዮጵያ ምን አተረፈች። የምድርን ለምድር የሰማይን ለሰማይ ከፋፍሎ በመመልከት ብቻ ይህቺን አድሎአዊ ምድር ሰማያዊ ማስመሰል አያቅተንም ደግ ደጉን በሚያሳስብ ሃሳብ ይበርዝልን መጨረሻው የት ነው። ምድር ከመፈጠሯ በፊት ጀምሮ እንዴት እንደነበረ ከየት ተነስተን እዚህ እንደደረስን በማውሳት በቅደም ተከተል ባጭር ባጭሩ አድርጎ ያቀርባልር ይህም አንዳንድ ጥያቄዎቻችን ለመመለስ እንዲረዳን ነው እንጂ ይህ ነው እውነተኛው በማለት አይደለም ከጥንት ጀምሮ አንድ ብቻ የሆነውን እና በሁሉም ሃይማኖት ውስጥ የሚገኘውን እውነት ለገዛ ሃይማኖት ማጠናከሪያ ማድረግ ይጠቅማል የክፍል ሦስትም ዋነኛ አላማ ይኸው ነው።
እያለ ከምድራዊነታችን ጀምሮ እስከ ባሻገሩ መንፈሳዊነታችን ድረስ ያለውን ይመረምራል አንድ ግለሰብ ምንም ቢደርስበት እድል ፈንታው በምድር ሲፈጸም ከሰማይ የሚደነገግለትን እንደማያጣ የሚበልጠውም ከምድራዊነታችን ባሻገር መኖሩን ይጠቃቅሳል ክፍል አንድ እና ክፍል ሁለት ከአንድ ግለሰብ የተጀመረውን ታሪክ ሁለንተናዊ በማስመሰል ስንገባበት ያላገናዘብነውን ስንሰነብትበት የተደናበርንበትን ስንወጣለትም የማናውቀውን አጭር ምድራዊ ሕይወት የሙጥኝ ከማለት ይልቅ የመጣንበትንና የምንሄድበትን አለም በአይነ ሕሊና መመልከቱ የተሻለ ነው የሚያሰኝ መንፈሳዊ ስሜት ለማስተጋባት ይሞክራል መግቢያ ክፍል ሦስት የምድራዊ መንፈሶች ተጽንኦ በኑሮአችን ላይ በምድራዊ መንፈሶች ወይም እኛ ከምድራዊነታችን በወረስነው ጠባያችን ተጽንኦ በዚህ አለም ኑሮአችን አስከፊ ሲሆን የሰው የመንፈሱ ጥሩነት ለዚህ አለም እንግዳነቱን ሲያሳውቀው የት ላይ ነው የምድራዊ ሕይወታችን ተስፋ ያለው። የሰዎች ስሜት መንፈሳዊ ሲሆን በጋርዮሽም ሲተሳሰር ደስታም ሆነ ሃዘን የጋራ ይሆናል ሃዘኑም ቢሆን ተስፋና ደስታ አዘል ይሆናል እንጂ ፍጹማዊ ሃዘን አይሆንም በማንኛውም ጊዜ ለክፉም ሆነ ለደግ ሰዎች እርስ በርስ ሃሳብ ለሃሳብ ሲለዋወጡ ትንሽ ትንሽ አንዱ ሌላውን ይመስሳል በዚህን ጊዜ ክፋቶችና ደግነቶች ሁሉ ካንዱ ወደ ሌላው ይዛመቱና ሁለት አቢይት ማዕበሉች ይፈጠራሉ የክፋት ማዕበሎች ሲደማመሩ ሰው እርስ በርሱ ይጨራረሳል የደግነትም ማዕበሎች ሲደማመሩ ማሕበራዊ ግንባታ ይሆናል ሁለቱ ተቃራኒ ማዕበሎች ሲደነቃቀፉ ደግሞ ምንም ሳይሠራ እድሜ መፍጀት ብቻ ይሆናል በተመሳሳይ መንገድ አንድ ግለሰብም የተጠቀሱት ሁለት ማዕበሎች በውስጡ ከምድራዊነታችን ባሻገር አሉበት ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ሰው ይሆናል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ መጥፎ ሰው ይሆናል አንድ ግለሰብ በማሕበር ከሌሎች ጋር በሕብረት ሲኖር የክፋት ማዕበሎች በሰልፍ ሆነው በውስጡ እንዳይደማመሩበትና እንዳያድጉበት ወደጥፋትም እንዳይከቱት መጠንቀቅ ይኖርበታል ለጊዜው ነው እንጂ ሥጋ አይጠቅምም ምድራዊ ኑሮ ሲያስመርር ብንመለከት መንፈሳዊ ኑሮ ጸጸት ሲሆን አላየንም ከምድራዊነታችን ባሻገር ሰማያዊ እና ዘለአለማዊ አለም ውስጥ የሚከተን ቀድሞ ከእግዚአብሔር የመጣ በኋላም ወደ እርሱው የሚመለሰው ጥሩው መንፈሳችን በምድርም በሰማይም ሕያው ሆኖ ይኖራል ታዲያ እስከዛው ድረስ መመላለሺያ አለማችንን መኖሪያ አገራችንን መሰናበቺያ ጊዜአችንን ሁሉንም በአይነ ሕሊና እየተመለከትን እናውራ በደስታ በዚህ አለም የሚሠራው ሥራ ሁሉ ይህንን እና ያንን የሚመስለውም ሁሉ ከሕብረተሰብ እስከ ግለሰብ የሰውን ሕይወት ሲያተራምስ እንዲሁ ዝም ተብሎ የሚታለፍ አይደለም በደምሳሳውም ቢሆን ውስጠ ጠባዩንና ሂደቱን መመልከት ያስፈልጋል እንጂ ቋንቋ የሚያሰለጥን አንደበት የሚከፍት የሚያሳውቅ የሚያዝናና የሚያጫውት የሚያቀራርብ የሚያፋቅር ደስታን ከቤት ወደ ቤት ከአድማስ ወደ አድማስ የሚያዛመት በአለማችን የሚታየው ሁሉ የሰው ጥሩነቱ ሲከፈት የደስታን ስሜት ለመስረጽ ብልሃቱ ምንድነው። ይህቺን አለም ጥሩ መኖሪያ ሥፍራ የሚያደርገው ምዕራፍ ሁለት በአንድ አለም ሁለት አለም ምድራዊ ክንውኖች ከኃጢአት ጋር ይሠራሉ አንዳንድ የተዳፈኑ ኃጢአቶች ሲቆሰቆሱ ሌሎችም ከሥር ሲያቆጠቁጡ ይታያሉ ዘረኛነት እና የሃይማኖት አክራሪነት በመሠረታዊ ጠባያቸው ይመሳሰላሉ ሁለቱም ከአድሎአዊነት ጠባይ ይመነጫሉ የሰው ልጅ የሚፈልገውን ሃይማኖት በራሱ መርጦ እንዳይከተል ሰብአዊ ዲሞክራሲያዊ መብቱን የሚነፍግ የሃይማኖት አክራሪ የፖለቲካ አክራሪም ቢሆን ከምድራዊ አድሎአዊ የዘረኛነቱም ጠባይ የሚያላቅቀው ሰማያዊ ግንዛቤ አይኖረውም እግዚአብሔር ሰውን በአምሳሉ ፈጠረ ከዛም በኋላ ይህንን መልካም ሥራ ለማበላሸት ሰይጣን በሰዎች አይምሮ ይጫወታል ሰዎች ኃጢአትን እንዲሠሩ ይታገላል እግዚአብሔር ግን ፈጥሮ አልተወንም። በአንድ ዘር ውስጥ ግለሰቦች እኛ ብቻ ነን ለአለም ሕብረተሰብ ሁሉ እድገት ያመጣን ሲሉ ዘረኛነት ተቀሰቀሰ ማለት ነው እንዲህ አይነት ጠባብ አመለካከት ያለው ሰው ተመጻዳቂ በዘሩ የሚመካና የሚሜኮራ የዘረኛነትም ዝንባሌ የሚያድርበት ነው ይህች አለም አንድ ወጥ እንዳትሆን እግዚአብሔር ሆነ ብሎ ለምክንያት ፍጥረታትን ዥንጉርጉር አድርጎ በመፍጠሩ የሰው ዘር የተለያየ መልክ አወጣ ይህ ተፈጥሮአዊ ቁንጅና መደሰቻ የእግዚአብሔርን ሥራ ማወደሻ እንጂ ሰውን ከሰው የሚያጣላ መሆን አልነበረትም የሰው ዘር እንደ አበቦች ቀለም መለያየት እንደ አንዱ የተፈጥሮ ቁንጅና መቆጠር ሲገባው የቆዳው ቀለም የጠቆረ ጸጉሩም የከረደደ ከአንድ ነጭ ባለ ጸጉረ ብዥት ወይንም ቢጫማ ቀይ ሰው በአንድ አለም ሁለት አለም የጎላ ልዩነት ቢታይበት ይህንን ልዩነት መካድ የተፈጥሮን ቁንጅና እንደ መካድ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንደ ማቃለል ይቆጠራል የእግዚአብሔር ፍጡር የሆነችዋን ጥቁር ኢትዮጵያዊት ለምን ሙሴ አገባት ብላ የሙሴ እህት ስለተናገረች ብቻ እግዚአብሔር ተቆጥቶ ለምጻም እንደ አደረጋት ኦሪት ዘጉልቁ በአፈጣጠር እገሌ ከገሌ ይበልጣል ብሎ መናገር በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ መግባት እርሱንም ማስቆጣት መሆኑን ያመለክታል ትዳር ይፔአለሁና ስለውጪው አለም ሳልጨነቅ ከራሴ ቤተሰብ ጋር ብቻ ደስ ብሎኝ እንድኖር የሚያደርገኝን እያሰብኩ እኖራለሁ ማለት አልተቻለም ባጠቃላይ ይህች ምድርና በውስጧ የሚሠራው ሁሉ የሚያስጠላ ነው ባይባልም አልፎ አልፎ የሚታየው ዘረኛነት በጣም ያሳዝናል ያስፈራልም እኛም አዎንታውያን ስለሆንን የበጋ ክረምት በልግና ጸደይን መለዋወጥ እየተመለከትን የምድር ክፋቶችና ደግነቶችም እንዲሁ የሚፈራረቁ ናቸውና ምንም ይሁን ምንም እንኑርበት በማለት ቆይተናል ሆኖም በዘር ልዩነት ሳቢያ በየጊዜው ከመካከላችን ስነአይምሮአዊ ድንጋጤ ውስጥ የሚገቡ ወንዶችና ሴቶች ወገኖቻችን ብዙዎች መሆናቸውን ስንገነዘብ መንፈሳችን ይታወካል የሰውን ልጅ እንስሳዊ ጠባይ መንፈሳዊነቱ እየሸፈነለት ነው እንጂ ያ መንፈሳዊነቱ ባይኖር ቢሰወር ቢጠፋ ቢዳከም እንስሳዊ ጠባዩ ቁልጭ ብሎ በግልጽና በጉልህ መታየቱ አይቀርም መከራና ጭንቀት የደረሰበት ጠባየ ለስላሳና የዋህ ሰው የሰዎችን እንስሳዊ ጠባይ ከገጽታቸው ቢመለከት ሊደነግጥ ስነአይምሮአዊ ድንጋጤ ውስጥ ሊገባ ይችላል የዚህም መዘዙ ብዙ ነው ሰው ካገሩ ከወጣ ሆድ የሚብሰው ለመኖር አስፈላጊ ከሆኑት ከመብልና ከመጠጥ ሌላ የጎደለበት ስለሚኖር ነው ከጎናችሁ ያለ ሰው መንፈሱ ሲደነግጥ ዝም አትበሉ አይዞህ አይዞሽ እያሉ ማደፋፈር ያስፈልጋል ከብዙ ዓመታት ጀምሮ የተገፉ ወገኖቻችንን እያሰብን የምድር ክፋቷን መናገሩ ጥሩውን መርሳት መደበቅ አይደለም ግን በሄድንበት ዘርፈጥ ብለን ከመቀመጣችን በፊት አስቀድሞ ዙሪያችንን መመልከቱ ይበጃል አድሎአዊነትን የዘረኞች ተንኮልና ግፈኝነትን በጥሩነት ለውጦ ይህቺን ምድር ሰማያዊ ማድረግ ወይም ማስመሰል የሚቻለው እንዴት ነው ማለትም ተገቢ ነው ሰውን ሁሉ ምንጊዜም በአዎንታዊነት ብቻ መመልከቱ ብዙ ችግሮችን ይከላከላል እኛ እንደ ንስር አሞራ ከላይ ሆነን በከፍታ የምንመለከት ብንሆን ጥቃቅን ችግሮች አያስጨንቁንም ሆኖም ዘረኞች የሰውን እኩልነት እንዲማሩና እንዲያውቁ የማድረግ ኃላፊነት አለብን ከምድራዊነታችን ባሻገር ክፋትና ጥላቻዎችን ሁሉ ችለን አብረናቸው ሰነብትን ለመቆየታችንም ዋጋ እየከፈልን ኑሮን ለማሸነፍ ከሁለት ከሦስት ቦታ ሠርተን ከተራ የቀን ሠራተኛነት እስከ ሳይንቲስትነት ደረጃ ተሠማርተን ከነጭ በልጠን እንዳንታይ እየተኮረኮምን ሥጋችንን አይምሮአችንንም አድክመን ግን ምንድነው ዋስትናው ይህ ኑሮአችን ምንጊዜም እንግዳ ባይተዋር መሆናችን በገዛ ኃጢአታችን አልጠቆርንም እግዚአብሔር እኛን ከነጭ በታች አድርጎ አልፈጠረንም በሰው ዘር ውስጥ ሁሉ ያለ የሰብእነት ምልክት እንዲህ ሲዋረድ በዝቅተኛ አመለካከት የአለም ሕዝብ ተጎድቷል በዚህ ወገናዊ ኃጢአት ግን በመጎዳታችን እንድንነቃበት በድካማችን እንድንከብርበት ካለማቋረጥ በመበርታት ከፍ ብሎ በልጦ ለመታየት ጥረት ይህ ብቻ ነው የኛ ምርጫ በእውነት ሰው በሃይማኖታዊ ፍልስፍና የተራቀቀው በተፈጥሮውና በኑሮው የራሱ እውነት ሲርቀው የአካላዊነት ሥጋ ጠባዩ አይኑን ሲያሳውረው እርስ በርሱ መተዋወቅ እንኳን ሲያቅተው ግላዊና ማሕበርዊ አስተሳሰቡ ሃይማኖቱ እምነቱም ተለያይተው ቀለም ዘር ሌሎችም ክፋቶች ተደማምረው ተስፋ በመቁረጥ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ሲተወው ከጤንነት እብደት ሲሻለው ልዩነቶች ጥላቻን ሲፈጥሩ እጅግ በጣም ተካረው ጠብና ጭቅጭቅ ወደ ሞት ሲመራው ይህን ሁሉ ማሰብ ያስጠላል ከመታየት መደበቅን ያስመኛል አንዱን ካንዱ ማበላለጥ በልብስ በሃብት በመልክ በውጫዊነት የተውነው መስሉን ነበር ካገር ቤት ዝቅ ብሎ በመታየት መጠላት እዚህም ቢሆን ፈረንጅ አገር ሰው ሰርቶ በድካሙና በወዙ ከሚኖርበት ተጠናክሯል ልዩነት በዘረኛነት ዘመኑ የፈጠረውን ኮትኩቶ ያሳደገውን በአንድ አለም ሁለት አለም ይህንን ጠባይ ልዝብ ሰይጣናዊነት ማነው የሚያጠፋው። ይህ የአሁኑ የሰው ዘር ጠፍቶ ሌላ አዲስ የሰው ዘር እስኪተካ ድረስ ለዚህ አንድ የሰው ዘር ሕብረትና አንድነት ያልተቋረጠ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል በሁሉም ሰው ዘንድ ያለውን ጥሩነት እያየን እንጂ መጥፎነቱን ብቻ ከተመለከትነው ኑሮአችን በከንቱ አሉታዊነት ይበረዛል የተጨቆኑትን ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔር ብድግ ሲያደረጋቸው ሰብአዊነትም በአንድ ሰማያዊ መልክ ሲካተት መጨረሻው መጥፎ አይሆንምና መጥፎ መጥፎውን በመመልከት ብዛት ኑሮ እንዳይበላሽ ከእግዚአብሔር መንፈስ አንራቅ በአለም ሁሉ እግዚአብሔር አለ በጠፈርም ሁሉ እግዚአብሔር አለ በቤት ውስጥ እግዚአብሔር አለ ከውጪ እግዚአብሔር አለ በሁሉ ሥፍራ እግዚአብሔር አለ ዘረኞች ቢያሳንሱህሽ በሥራ ቦታ ጥቃት ቢደርስብህሸሽ በጾታ ልዩነት ውርደት ቢደርስብህሸሽ በሃይማኖት ልዩነት በሃብት በእውቀት መበላለጥ በቋንቋ በባሕል ልዩነት ጥቃት ቢደርስብህሸ ብቸኝነት ቢሰማህሽ ምንም ሃዘን ቢገባህሽ ምንም ቢከፋህሽ አጽናኝ መንፈስን የሚልክልህሽ እግዚአብሔር አለልህሽ አምላክ አለልህሽ ለወደፊት ልዩነት በመንፈሳዊ ፍቅር ሲካተት ሰው ሁሉ በአንድነት ለፈጣሪው ሲሰግድ በታላቅ እምነት ከምድራዊነታችን ባሻገር እውነትም ወገግ ብሎ ሲታይ በእምነት ኦ ሰላም። አይምሮ የሚታየውንም የማይታየውንም መመዝገብ የሚችል ስለመሆኑ በስነአይምሮ ተመራማሪዎች ዘንድ ታዋቂ ሆኗል አይምሮ ይህንን ያህል ችሎታ ባይኖረው ኖሮ ካለ አንዳችም አካላዊ ሞገድ ከምድራዊነታችን ባሻገር የሚከሰት በእርግጥ እንደ አካል ቁልጭ የሚል የመንፈስ ነገር ሊታወቅ አይችልም ነበር በአይምሮ ውስጥ የሚመዘገበው ስዕል ባለ ቅርጽ ሆኖ ወደ አይምሮ የሚሰርጽ ከብርሃን ሞገድ ብቻ የሚመጣ አይደለም እንዲህማ ቢሆን ኖሮ ከልጅነታቸው ጀምሮ አይነ ስውር የሆኑ በአይምሮአቸው የሚቀረጽ ስዕል አይኖርም ነበር ይገደል ይወገድ ይጥፋ በአንድ አለም ሁለት አለም ሳናውቀው ባለብዙ ስሜቶች በመሆናችን ነው ከአካላዊ ትርጉም ፈቀቅ እያልን የመንፈስን ሥራ ለመመርመር የምንሞክር ስለሰው ስናወራ በቶሎ የሜታየን ሥጋዊነቱ ነው መንፈሳዊውን ሰው ስለማናየው እንደሌለ አድርገን ነው የምንቆጥረው ለምሳሌ የመንፈስ ልጅነት ከሥጋ ልጅነት ጋር አብሮ ማደግ እንዳለበት በሥጋ የወለዱን እናትና አባታችን ስለሜያምኑ ገና ሶስት ወር ሳይሞላን በአርባ ቀን ለወንድ እና በሰማንያ ቀን ለሴት ያጠምቁናል ይህም ታላቅ ምሥጢርን ያዘለ ስለሆነ በተለይ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ያውቁታል ፍጥረታችን በመንፈስና በሥጋ በመሆኑ ድርጊታችን ሁሉ የሚያንጸባርቀው ሁለቱንም ነው ስለዚህ አንድ ሕጻን ሲወለድ በሥጋ ሦስት ወር ባይሞላውም እንኳን በመንፈስ ከተወለደ በክርስቶስ ክርስቲያን ከሆነ ቆይቷልና ያንን ክርስቲያናዊ እሱነቱን ከአካላዊነቱ ጋር ለማዛመድ ሲባል ይጠመቃል ክርስቲያንነቱም ጸንቶ እንዲቆይ ለማድረግ የክርስትና አባት ለወንድ የክርስትና እናት ለሴት ይመደባል በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ መንፈስና ምድራዊነት እየተሟገቱ ሰዎች እርስበርሳቸው በጦርነት ሲጨራረሱ ይህ ታሪክ የኛ የሰብአዊነት ብቻ ላይሆን ይችላልና በታሪካችን ውስጥ የመናፍስትም ትግል አለበት በሜል አንጻር እንመልከተው በእርግጥ በሃይማኖት መጻሕፍት ስለ ሥጋዊነት የተገለጸውን ያህል ስለመንፈሳዊነትም የተገለጸ ይኖራል ሆኖም እኛ ምንጊዜም አስተሳሰባችን ወደ ሥጋዊነት ስለሚያዘነብል ይኸው ሥጋዊነታችን ማወቅ የሚገባንን ሁሉ ሸፍኖብናል አብዛኛው የአለም ሕዝብ ፍዝዝ ያለ ኑሮ ይኖራል በሕዝቦችም መካከል አልፎ አልፎ ነቃ ነቃ ያሉ ሰዎች ይወለዳሉ ለጥሩም ሆነ ለመጥፎ ታሪክ ሠሪዎቹ እነርሱ ነቃ ነቃ ያሉት ይሆኑና ሰብአዊነት በአካሉ መልክ አውጥቶ ደምቆ እንዲታይ ያደርጉታል ጥንት የነበረ ለወደፊትም የሚኖር በሕይወታችን ውስጥ ዋና ተዋንያን መንፈሳችን እየሆነ የማንወደውን የሚያሠራ የምንወደውንም ቢሆን ለጥፋት ሲሆን የሚያፋጥን ለበጎ ሲሆንም የሚያጓትት ሰውም እንደ መንፈስ መንፈስም እንደሰው ሲሆን አስተውለናል በዚህ አለም ላይ ብዙ ነገር ይሠራል የግለሰብም ሕይወት በዚህ አለም ላይ ከሚሠራው ሥራ ጋር ሁሉ ይያያዛል በዚህ አለም ላይ ብዙ ነገር ብዙ ነገርን ይመስላል የግለሰብም ሕይወት በዚህ አለም ላይ ከሚመስለው ሥራ ጋር ሁሉ ይያያዛል የግለሰብ መፍጨርጨር ብቻውን ምድራዊ ሕይወትን አያሻሽለውም ከምድራዊነታችን ባሻገር ለዚህ ነው ሕይወታችን የዙሪያችንን የሚሠራውንም ሁሉ የሚመስለውን እና የማይመስለውን ሁሉ ከማጥናት ጋር አብሮ መሄድ ያለበት የሰይጣን በጠፈር ውስጥ ሁሉ መኖር በጠፈር ሁሉ የቅራኔን መኖር ያመለክታል በጠፈር ሁሉ ከሚኖር ቅራኔ የማናመልጥ ነውና የኛም የቅራኔአችን ታሪክ በሰማይ ከመላእክት አለቆች መካከል ሉሲፈር ከተባለ መልአክ ታሪክ የቀጠለ መሆን አለበት ሉሲፈር ፈጣሪውን እግዚአብሔርን ፈልጎ ሲያጣው ጊዜ ከኔ በላይ ማንም የለም ብሎ አወጀ እራሱን ከመላእክት ሁሉ በላይ በማድረግ ለኔ ስገዱ አለ እግዚአብሔርም ብቅ ሲልበት በጥፋቱ ተጸጽቶ ይቅርታ በመጠየቅ ፋንታ በጥፋቱ ቀጠለ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከጭፍሮቹ ጋር ሆኖ ከሰማይ ተባረረ አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ ሉሲፈር እንዴት ከሰማይ ወደቅህ። ል ምድራዊና መንፈሳዊ ኑሮን በማጣመር የሚኖሩ ሰዎች ባንድ በኩል ሰማያዊ መንፈሳዊነታቸው በሌላ በኩል ደግሞ ምድራዊ ሰብአዊነታቸው ሲነካባቸው የሕልውና ጥያቄ ይሆንባቸዋል በዚህን ጊዜ ነው አክራሪዎች የሚያይሉት እንደ ባሕር ጥልቅ ከሆነው እውቀታቸው ጋር የሰዎችን ልዩነት የሚያጋንን ፍልስፍና እያናፈሱ እንደ ጨለማ ከጠቆረው ድንቁርናቸው ጋር በምድር ላይ ኃይለኞች የሚሆኑት እነርሱ ናቸው የዛሬ ዘመን ሰው ሰላምን ፈላጊ ቢሆንም የእርኩሳን መናፍስት ቅስቀሳ በተፋፋመበት ወቅት ውስጥ ነው ያለነው ፍርኃት በሰዎች ዘንድ ብዙ ጊዜ ሲቆይ ጠባያቸው ሆኖ ቶሎ ቶሎ የሚናደዱ ሰዎች ትእግስት አጥተው አለም አቀፍ አደጋ ይፈጥራሉ በሌላ በኩል ደግሞ እጅግ አደገኞች የሆኑ ቶርቶራዎች ስለመጡባችሁ ችላ ብላችሁ አትቀመጡ ወሳኝ ለሆነው ጦርነት ተዘጋጁ የሜል ወሬ ይነፍሳል ሁለት አይነት ወሬ አለ አንደኛው ሰሙ ቶርቶራዎች አደገኞች ስለሆኑ እነርሱን በጋራ እናጥፋቸው የሚለው ነው ሁለተኛውና የተደበቀው ወሬ ወርቁ ግን ለወሳኝ ጦርነት እንዘጋጅ ነው ማንም ሰው እየፈራ ላለመኖር ሲል አንድ ነገር ማድረጉ ስለማይቀር ይህ ከፍርኃት የሚመነጭ ዝግጅት ከፍተኛ እጅግ በጣም ከፍተኛ ሆኗል ኃያላን መንግሥታት ወሳኝ ለሆነው ጦርነት ተዘጋጅተዋል ለአለም ጦርነት መቀስቀሻ ተዘጋጅተው ከተቀመጡት ከፓለስታይን እና እስራኤል መካከል በእግዚአብሔር የማያምን በሌለበት በአሁኑ ወቅት ሁሉም ለአንድ አምላክ እየሰገደ በፍቅር መኖር እንደሚቻል አላወቁም በሕዝቦች መካከል ለረጅም ዘመን የቆየ ጦርነት ሲቀጥል ለዛ ሥፍራና ለዚያ ሕዝብ እንዲሁ እርስ በርስ ከማገዳደል በስተቀር ሌላ መፍትሔ ያለ መስሎ አልታያቸውም እርኩሳን መናፍስት በመልካም መንፈስ እንደሚቸነፉ አልገባቸውም እስራኤሎችና ፍልስጤሞች የዘር ግንዳቸው ከአብርሃም የሆኑ የአጎት ልጆች ናቸው ሁለቱም የሴም ዘሮች ለየወገኖቻቸው የሚሜቆረቆሩ ከፍተኛ የሕብረተሰብና የቤተ ሰብ ፍቅር ያላቸው ናቸውና ከመካከላቸው ሰው ሲገደል ፍልስጤም ከምድራዊነታችን ባሻገር ከመገደል የተረፈው ዘመድ የብቸኝነት ኑሮ ያቅተዋል ያለው ምርጫ ገድሎ መሞት ወይም ማበድ ይሆናል ሰው በተገደለ ቁጥር የተገደሉ ሰዎች የመንፈስ ኃይል ይጨምራል በሁለቱም ወገን ያሉ መንፈሶች ቀሪ ዘመዶቻቸው የሥጋን ከንቱነትና ውሸታምነት ይረዱ ዘንድ ሰማያዊ ትምህርት እየተማሩ ሰማያዊ ሰላም እንዲያገኙ የሚጠሯቸው የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው ። ስለዚህ እርስ በርስ መገዳደሉ ካለማቋረጥ ይቀጥላል ይህ ነው የማይታይ መንፈሳዊ ክስተት በሰይጣናዊ ልባምነት የሚኖሩ ሰዎች ሰላም እንዳይኖር ሲከላከሉ በቅዱስ መንፈስ ልባዊነት የሚኖሩ ሰዎችም ለሰላም ሲሉ የሚደክሙበት እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር ከወጡ ጀምሮ እግዚአብሔር የሚነግራቸውን ሁሉ እንዳይገባቸው ሰይጣን ነገር እያጣመመ ከሰው ሁሉ ጋር ካለ ጦርነት ተስማምቶ መኖር የሚቻልበትን መንገድ ሁሉ እያጠረባቸው ቆይቷል ጥንትም ቢሆን እግዚአብሔር በርሱ የማያምኑትን ጠሳ እንጂ በርሱ የሚያምኑትን ሁሉ የግድ እስራኤላውያን ካልሆናችሁ ብሉ አይጠሳም በአናንተም መካከል ልጆችን ለሚወልዱ መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ትከፋፈላላችሁ እነርሱም በእስራኤል ልጆች መካከል እንዳሉ የአገር ልጆች ይሆኑላችኋል በእስራኤል ነገዶችም መካከል ከእናንተ ጋር ርስትን ይወርሳሉ መጸጻተኛውም በማንኛውም ነገድ መካከል ቢቀመጥ በዚያ ርስቱን ትሰጡታላችሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ሕዝ እግዚአብሔር ምድሪቱን አንዴ ፈጥሯታልና ለእስራኤላውያን ብሎ ሌላ አዲስ መሬት እንደማይፈጥርላቸው ሁሉ ካለ ጦርነት ተስማምቶ መኖር የሚቻልበትን ይህንን መንገድ ነገራቸው እነርሱ ግን እስካሁን ድረስ ይህ አልገባቸውም እግዚአብሔር ሰውን በሰው አይለውጥም አገር የለሽ የነበሩ እነርሱ በተሰደዱበት ሥፍራ ሁሉ ሲያለቅሱ እንዳልነበሩ ሁሉ አሁን እነርሱ ፍልስጤሞችን ማስለቀሳቸውን የአለም ሕዝቦች አይተው አዝነውባቸዋል እውነት እየቆየ ሲሄድ እየደመቀ ሰዎችን በመልካም መንፈስ ያነቃል ስለዚህ ለወደፊት ክፉ ሥራ የሚሠራውን ሁሉ የአለም ሕዝብ ያወግዛል እነርሱ ከፍልስጤሞች በጉልበታቸው የነጠቁትን መሬት መልሰው በየአገሩ የተሰደዱትን ፍልስጤማውያን ሁሉ ተመልሰው በነፃነት እንዲኖሩ ካላደረጉ በስተቀር በክፉ አድራጊነት የሚታወቁ ይሆናሉ የሰላም ጠንቆች ከመባልም አያመልጡም ሰውን የሚያስለቅስ ሁሉ በያለበት የኋላ ኋላ ልቅሶ በርሱ ሳይ እንደሚጸናበት ልብ ይበል ሰው ሁሉ የምድራዊነት መሟጠጫ ጊዜ እስኪቃረብ ድረስ እያለቀሰ በእንግሊዝኛውም ጠ ነፀቨዐበ ሂካፀ ዓቭሕበዐፎበሜ ከካ ዓፎዐሀጠ ቋገዐበዐ ሃህ ይለዋል በአንድ አለም ሁለት አለም እንዳይኖር መልካሙን አማራጭ ይፈልግ በማልቀስ ላይ ያሉትን ወንድሞቻችንን በያሉበት ቀርበን ማነጋገር እና በሰላም አብሮ ስለመኖር ጉዳይ መምከር ይገባል ምንም ቢሆን ሰውን ሰው መጥላት የለበትም በጥላቻ መቆየት ሰውን ይጎዳል ፓለስታይን ነፃነቷን ተቀዳጅታ ሕዝቦቿም ሲፈልጉ ከፓለስታይን ሲፈልጉም ከእስራኤሎች ጋር በሰላም መኖር እንዲችሉ ለማድረግ ያለው ምርጫ የፓለስታይኖች ወይንም የእስራኤሎች በጎ መንፈስ ብቻ ሳይሆን በሰው ልጅ በጠቅላላ በውስጡ ያለው በጎ መንፈስ ሲቀሰቀስ መሆኑ ነው በሰው ልጅ በጠቅላላ በውስጡ ያለው በጎ መንፈስ ሲቀሰቀስ የሰውን ልጅ በእኩልነት ማየት የሚበጀውን ማሰብ ያሰቡትንም በተግባር መፈጸም ይጀመራል ይህንን በጎ መንፈስ የሚከላከል መጥፎ መንፈስ ረግቶ አልተቀመጠም የሚያሰራጨውን የክፋት አይነት ዘርዝሮ መጨረስ ካቅም በሳይ ነው ከሁለተኛው አለም ቀጥሎ እስራኤሎች እና ፍልስጤሞች የአለም ጦርነትን መቀስቀሺያ እሳቶች እንዲሆኑ ተዳፍነው ተቀምጠዋል በተለይም ከጠባዮቻችን አንዱ ዘረኛነታችን የሦስተኛው አለም ጦርነትን ሲቀስቀስ ሁኔታዎች ሁሉ ይህንን ሂደት ሲጠቁሙ እያየን ዝም ማለት አንችልም እግዚአብሔር ከሰዎች መካከል እስራኤላውያንን ለይቶ እናንተ የምወዳችሁ ሕዝቦቼ ናችሁ ቢል ጠቅላላ የሰው ዘር እንዳይጠፋበት አስቦ ያደረገው የመከላከያ ዘዴው ነው እንጂ የምድራዊነት ጠባይ የሌለበት እግዚአብሔር አንዱን የሰው ዘር ከሌላው አብልጦ የሚመለከት ሊሆን አይችልም ሻሉሎም ሻሎም ሻሉም ሻሉም አሌኩም ከአራቱም ማዕዘን የምትመጡ ሁላችሁም ጀሩ የሩ የርሱ የርሷ ሳሌም ጥላቻ በፍቅር ሲቀየር ቆንጆ እንዳንቺ የለም አንቺ እስራኤል የአራት ባሕሮች አገር የምድርና የሰማይ መጋጠሚያ ድንበር ቤተልሔም ናዝሬት ቢታንያ የሁለት አለም መንደር አንቺ አለም የአብርሃም ተስፋ አንቺ የሩሳሌም የኢሳያስ ራእይ የዮሐንስ ምስጢር አንቺ ቆንጆ ለምለም አዲስ እርስት ሰማያዊት ምድር የገሊላ ባሕር የሙት ባሕር የቀይ ባሕር የሜዲተራንያ ባሕር ዘፍ ኢሳ መጨረሻ ዮሐ ራዕ ከምድራዊነታችን ባሻገር መንግሥታት ሲገባቸው ሲያቆሙልሽ የአለም ወታደር ያለማወቅ ጨለማ እንዲገፈፍ ድንቁርና እንዲሰበር ውበትሽ እንዲገለጥ ነፃነትሽ እንዲከበር አንቺ ሥፍራ የሰው ዘር ሁሉ የረገጠሽ ክርስቶስ የተመላለሰብሽ ከሰማይ መላእክት የወረዱብሽ በእውነት ለሁሉም የሁሉም መሆንሽ ሲታወቅልሽ ፍጹም ሰላም ይሰርጻል ከውስጥሽ አዲሲቷ እስራኤል በጣም ደስ ይበልሽ የምድር ነገዶች ሁሉ ባንቺ ተባረኩልሽ በክርስቶሳዊነት ሰው ሁሉ አንድ ሆነልሽ በዘመናችን የምዕራቡ አለም በሦስተኛው አለም ላይ አምባገነን መሆንን አውቆበታል። እነዚህ ይህ አስተያየት አጠቃላይ የሰብአዊነትን እድገት ከመመልከት አንጻር የተሰነዘረ ከምድራዊ ፖለቲካም ውጪ ስለሆነ ወገናዊ ሊሆን አይችልም በአንድ አለም ሁለት አለም እርስ በርስ የሚጨራረሱ ኃይሎች የማይፈለጉ ምድራዊ እውነታዎች መሆናቸውን ልብ ይሏል ሰምና ወርቅ የአለም ሕብረተሰብ ከሁላችን በላይ በሆነ የመንፈስ ኃይል መናወጥ አለበት ካልተናወጠ በስተቀር መስተካከል አይመጣምና የአለም ሕብረተሰብ ሲናወጥ ድሃው ሃብታም ሃብታሙም ድሃ እየሆነ የሰው ዘር ሁሉ በጊዜ ውስጥ ከዚህች ምድር የሚኖረው ድርሻ እኩል ሲሆን የዚያን ጊዜ ነው ሰላምና ጸጥታ የሚኖር የዚያን ጊዜ ነው አብሮ መሥራትና አብሮ ማደግ ተፈጥሮአዊ ግዴታ የሚሆን የዚህ ትውልድ መጨረሻው በተለያዩ መንገዶች ይፋጠናል በየወቅቱ የሚቀሰቀሱ ጦርነቶች መንፈሳዊ ግንዛቤን ያፋጥናሉ ካለ ጦርነት መቆየትም ከሥልጣኔ ጋር የሕብረተሰብ እድገትንና መንፈሳዊ ግንዛቤን ስለሚያፋጥን መጨረሻውን ያቀርበዋል ከሁለተኛው የአለም ጦርነት መጨራረስ የተረፉት ለመጪው አለም የተሻለ ሁኔታ ፈጠሩ ከእንግዲህስ ሕዝቦች በሰላም እንጂ በጦርነት የሚያምኑ እንዳይሆኑ አንጋፋ መሪዎች እየመከሩና እያስጠነቀቁ ቆይተዋል እነርሱ የሁለተኛውን የአለም ጦርነት እንዳሳለፉ የነርሱ ትውልድ ሦስተኛውን የአለም ጦርነት እንዳያይ ይመክራሉ ነገር ግን እነኛ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት የተረፉ አዛውንት አርጅተው እየሞቱ ማለቃቸው ነው ተተኪው ትውልድ የሰላምን ምንነት እንደ አባቶቻችን በደንብ አላወቀውም ይህች ምድራችን መጨረሻዋ እየተፋጠነ ነው የመጣው በምድር ላይ ያለው ምግብ የተወሰነ ነው በላተኛ እየበዛ ሲመጣ ከምድሪቱም የሚመረተው ሰብል ለሰዎች ሁሉ አልዳረስ ሲል ይህ የመጨረሻውን መፋጠን ነው የሚያመለክተው ግን ምድር እራሷን መሆን እስኪያቅታት ድረስ ጊዜው ረዥም ነው ከእንግዲህስ የሰው ቁጥር እየበዛ ሲሄድ የምድርም ሃብት ወደ ተወሰኑ ሥፍራዎችና ሰዎች ዘንድ ብቻ ሲቆይ በደኸዩ አገሮችም ከመሬት የሚመረተው ሰብል በማንኛውም አይነት መንገድ ቢከፋፈል የማይበቃ ሲሆን ሰዎችም ሆዳቸውን ለመሙላት የሚያባክኑት ኃይል ከምግብ ከሚያገኙት ኃይል ሲበልጥ መደህየት መቸገር መጨነቅም ሲከታተል ይባስ ብሎ በነኛው በተዳከሙቱ ላይ የተፈጥሮ ጉዳት ሲጸና ከትንቢቶች ሁሉ ባሻገር ለሰው ልጅ የሚበጀው በመንፈስ መጠናከር መሆኑ የማይገባው አይኖርም እኛም ካሁኑ ገብቶናል አለም አቀፋዊ ጦርነት እንደገና ሲቀሰቀስ ይህም ጦርነት የተካረረ ሲሆን የዚያን ጊዜ አዲስ ነገር ይታያል ከቋሚው ሟቹ ይበዛል ከሚታየው አካል የማይታየው መንፈስ ያመዝናል ሰው ከመኖር አለመኖርን ይመርጣል የዛን ጊዜ ኑሮ ማለት ከምድራዊነታችን ባሻገር መሆኑ በደንብ ይታወቃል ከምድራዊነታችን ባሻገር ለወደፊት የእድገት መመዘኛው ምድራዊ አለማዊ ስልጣኔ ብቻ ስለማይሆን የአለም ሕዝቦች ሁሉ በአንድ በኩል ለአንድ ምድራዊ ኢኮኖሚ እና የጋራ ብልጽግና ባንድነት ይሠራሉ በሌላ በኩል ደግሞ መንፈሳዊ አንድነታቸውን ያጠናክራሉ የሰው እምቢተኛነት የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ፈቃዳዊ ነፃነትና ፍላጎት አያሳጣውም አያዳክመውም ስለዚህ የርሱ ፈቃድ በዚህች በምናውቃት ምድር ላይ በምሥራቅ በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ ሁሉ ይሰፍናል የዚያን ጊዜ የዚህች የምናውቃት አለም መጨረሻ ይሆናል ይህም ማለት የእግዚአብሔር መንግሥት ይመጣል ማለት ነው የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት ነፃነት አለ ኛ ቆሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ይመጣል ማለት ሰይጣን በዚህች በምድር እንደነገሠባት እንዲሁ ለዘለአለም አይቀጥልም ማለት ነው አዲሱ ትውልድ ከሰይጣን ቁራኛነት ነፃ ይወጣል ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሕይወቱ ሲያልፍ ቀኑ ጨለመ በዚያው እንደጨለመ ሊያስቀረው ይችል ነበር አላደረገውም የሚሆነውን እና የማይሆነውን ለይቶ የማያውቅ ሰው ስለወደፊቱ እድሉ ማወቅ ስለሚፈልግ በሰው አንጎል የሚታሰብ ሁሉ እንደ ትንቢት ሆኖ ሲነገረው በጉጉት እየሰማ እንደቆየጨለማው ብርሃን ሆኖልን ከክርስቶስ በኋላ አዲስ ትውልድ ተተካ በቅርቡ ወደፊትም ሌላ አዲስ ትውልድ ይተካል በዘመናችን እና ለወደፊትም የሰው ዘር ሁሉ አብሮ በመኖሩ እየተቀራረበ ሲመጣ ሰውን ሁሉ እንደ አንድ የሰው ዘር መቁጠርና መንከባከብ ይገባል ይህም እናትና አባት ለልጆቻቸው ከሚያደርጉት እንክብካቤ ተለይቶ አይታይም እግዚአብሔር የሕዝቦችን ጩኸት ያዳምጣል ጉልበተኛው ሲያይል እጅግ ሲበዛ በደል ማነው ልክ። አንዱን ከፍ አድርጎ ሌላውን ዝቅ ሳያደርግ ካለ ምንም አድልኦ የሚያስተዳድር መንግሥት ይመጣል የዛን ጊዜ ኢትዮጵያ ኤርትራንም ጨምሮ በቀናው ጎዳና እስከ አለም መጨረሻ ድረስ ወደ ፊት ትጓዛለች ይህ ወሳኝ ጊዜ መሆኑን አንባቢ ያስተውል ከእንግዲህ መጪው ጊዜ በጣም አስፈሪና አስከፊ ቢሆንም በግራና በቀኝ ከሚታየው የሰዎች እልቂት በስተጀርባ ሰብአዊነት በማያቋርጥ ጉዞ ወደፊት ይገሰግሳል መጨረሻው ጥሩ መሆኑ አይቀርም ውሸት በያለበት ሲረግፍ እውነት በምትኩ ሲያብብ እያየ የማያምን አይኖርም በምዕራቡ አለም ውስጥ አለማዊ ድርጊቶች ሕዝቦችን ከመንፈሳዊነት አርቀዋቸዋል ነገር ግን በመንግሥታዊ አስተዳደር በኩል ከፍተኛውን የሥልጣኔ እድገት የሚያንጸባርቁት እነርሱ ናቸው ሦስተኛው አለም ከምዕራቡ አለም የመንግሥት አስተዳደር እየተማረ ከአምባገነን መንግሥታዊ አስተዳደር ለመላቀቅ በራሱ የሚያደርገው ጥረት መከራ ጭንቅ እና የሕዝቦች እልቂት እያስከተለ በመምጣቱ ጊዜው ጩኸትን በጠመንጃ አፈሙዝ ከማሰማት ይልቅ በአፍ እና በወረቀት እንዲሁም በኮምፔተር ማሰማቱ የተሻለ ውጤት የሜገኝበት እየመሰለ ነው እንዲሁም ጊዜው መንፈሳዊነትን የትግል መሳሪያ ማድረግን ይጠይቃል ከምድራዊነታችን ባሻገር ሥጋዊና መንፈሳዊ ሆኖ ለተፈጠረ ሕዝብ የሚበጀው እስላም ክርስቲያን ሳይል ሁሉንም በእኩልነት የሚመለከት የጠቅላላ የሕዝቦችን ሁሉ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሕይወት የሚንከባከብ መንግሥታዊ አስተዳደር ነው ይህቺ አለም ውሸቶችን ታቅፋ ለዘለአለም ተደላድላ አትቀመጥም በምክንያት ትናወጣለች እግዚአብሔርም ኢትዮጵያን እያየ ዝም ብሎ አይተዋትም ስለዚህ ስለ አገራችን ድምጻችንን ከማሰማት ከመጮህ እና ከመጸለይ አናቋርጥ ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም የበለጠ ወደፊት እንድትራመድ የሚያስችላትን መንፈሳዊ አንድነትን እግዚአብሔር እንዲሰጠን ለአገሪቷ ልማትና የጋራ ብልጽግና ለሕዝቦቿም ሰላምና ፍቅር እንዲሰጣት በሕብረትና በአንድነት ሆነን እንለምነው ሁላችንንም እያቀራረበ አንድ የሚያደርገንን ሁሉ በማጠናከር ፋንታ ሊከፋፍለን በሚችል ላይ ጊዜ ካጠፋን ሁሉም ይጠፋል የተያያዝነው ተራማጅ የመሰለ ፖለቲካችን ከፋፍሉና አራርቆ እስከ መጣላት እንዳያደርሰን በተለይ በዘረኛነታዊነት ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ማክተም አለበት ካሁን በኋላ በታላቅ ፍጥነት የሚማር መንፈስ ቅዱስም የተጠጋው የሕብረት እና የአንድነት መንገድ መንገዱን የሚቀይስ መንግሥት ካልመጣ በስተቀር ኢትዮጵያችን አገራችን የምንላት እንዳትሆንብን ያሰጋል መጥፎ መንግሥት እንዳይመጣ ከሰሜን ከኤርትራ ሕዝብ ጀምሮ በክልል በክልል ተከፋፍሎ የሚኖረውን ሕዝብ ለመምራት የሚታገሉ አክራሪ ዘረኞች እነርሱና ተከታዮቻቸው በኢትዮጵያ ላይ ታላቅ ውድቀት እንዳያመጡ ተከላካይ መንፈስ በኢትዮጵያ እንዲኖር እንጸልያለን አገራችን ለረጅም ዓመታት በአለም ታውቃና ተከብራ የቆየችው በሰላም ወዳድ ሕዝቦቿ ባይሆን ኖሮ ይህ ዛሬ በዘር የተከፋፈለ ክልል ሁሉ አገር ይሆን ነበረ ዞሮ ዞሮ ጥሩ መንግሥት የማምጣት ጫና ያለው ከሕዝቡ ላይ ስለሆነ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከፍ ከፍ እያለ ለሕብረት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆን ዘንድ የጊዜው ሁኔታ ያስገድደዋል የጥንት ኢትዮጵያውያኖችንኤርትራውያኖችን ሕብረተሰብአዊ አንድነት በሚመለከት የውጪ ጸሐፊዎች እንደሚከተለው አቅርበውታልጠዩከ ሀከሺፎፀ ኩሃ በከ ዘቨበሺቪሃ ዐ ከፀፄ ህከርከ አዐሀ ርዐሀበ። ጤነኛው የሚያገኘውን ምድራዊ ተሳትፎ ለማግኘት ያልበቁ ሕመምተኞች ገና ከምድር አልተሰናበቱም በልዩ ልዩ ምክንያት አካለ ጎዶሎ የሆኑ ሁሉ እንደማንኛችንም ምድራዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ይሻሉ እንግዲያውስ ሁላችንም የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን ለመጨረሻው መንፈሳዊ አንድነት ብለን ልዩነቶቻችንን አናጉላ ከምድራዊ ወጣ ገብ ልዩነቶች ባሻገር እርስ በርሳችን በመንፈሳዊ እይታ እየተያየን እንከባበር እንቀራረብ እንዋደድ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ ኤፌሶን ማንም ሰው ከጎኑ ካለ ሰው ጋር በትእግስት መነጋገርና ሃሳብ ለሃሳብ ግንኙነት ማድረግ ይገባዋል ባልና ሚስት በአካልና በመንፈስ አንድ በመሆን ይጓዙ እንጂ ለየብቻ አይሁኑ በሃሳብ ላለመታመም ሁልጊዜ ማውራት ያስፈልጋል ሰዎች በሃሳቦቻቸው ሁሉ አንዱ ከሌላው እየተማረ ለሁሉም ሰው የሜስማማ ሃሳብ ማቅረብ ሲቻል ከሰው ሁሉ የተለየ መሆን ማፈንገጥና ተለይቶ ለብቻ መሆን አይጠቅምም ማንም ሰው በኑሮው ቀለል ብሎት በሰላምና በፍቅር ሊኖር የሚችለው ከጎኑ ወዳለው ሰው እየተጠጋ አብዛኛውን ሰው እየመሰለ ነው እንጂ ገለል ፈንጠር ካለ ጉዳት ላይ ይወድቃል ይጠቃል አንድ ሰው በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ ሲገባ አትተውት አብራችሁ ዝለቁ ክርስቶስም መሄጃው በተቃረበ ጊዜ ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም ዮሐ አላቸው ብዙ ከመከራቸው በኋላ ተነሱ ከዚህ እንሂድ ዮሐ አላቸው ከእንግዲህ መጥፎ ጊዜ በተናጠል ለግለሰብ ወይንም በጋራ ለሰው ሁሉ ሲመጣ አስፈላጊ ሲሆን ተነሱ ከዚህ እንሂድ ማለት ነው እንጂ የገዛ ነፍስን ለማዳን ከጎን ያለውን ሰው ጥሎ መሄድ አይገባም ብዙውን ጊዜ እናቶች ከእናታዊ ፍቅራቸው ጋር ግንዛቤአዊነታቸውም የተፈጥሮ ጠባያቸው ስለሆነ ከነርሱ መማር ያስፈልጋል አስታማሚዎች ብርቱዎች ታጋሾች ሆደ ሰፊዎችና በቶሎ ተስፋ የማይቆርጡ መሆናቸው በሽተኛውን ያጠናዋል ያክመዋል ያድነዋልምሖ በሆስፒታልም ሆነ በቤት አስታማሚሜዎች ከምድራዊነታችን ባሻገር እነርሱ ባለመታመማቸውና ለማስታመምም በመብቃታቸው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በሙሉ ተስፋና በእምነት ለበሽተኛ የሚያደርጉት እንክብካቤ ነው ፈዋሽ መድኃኒት የሚሆን የግንዛቤአዊነት አስፈላጊነት በየሥራ ቦታዎች ሁሉ በትምህርት ቤት በሆስፒታልወዘተ በአንክሮ ሲታወቅ የሰዎች የቀን ተቀን ግንኙነት ይሻሻላል ጸብና ጭቅጭቅም ይጠፋል ለወደፊት ማንም ሰው የሚሠራውን ሥራ እየሠራ ብቻ በሰላም እንዳይኖር እስከዛሬና ለወደፊት ከአይምሮው የሚሜሰረጹ ሃሳቦች ያስጨንቁታል የከፋ ቀን ሲመጣ የግለሰቦችም ጠባይ ቅይር ማለቱ አይቀርምና የሰውን ውስጠ መንፈሱን መርምራችሁ ውደዱት እንጂ በአፋዊ የቃል ምልልስ ልባችሁ አይቀየም ለመውደድ የፈጠናችሁ ለመጥላት የዘገያችሁ ሁኑ ሰው ለሰው መድኃኒት ነው የሚባለው በግንዛቤአዊነት መደማመጥ ሲኖር ነው አንድ ግለሰብ እንዲህና እንዲያ ቢያስብና በሕብረተሰብ ዝቅተኛ ደረጃ ቢሰጠውም ምን ጊዜም በውስጡ ስለሚኖረው ፍጹም እውነት እያሰባችሁ አክብሩት አንዱ ሌላውን ያክብር እንጂ አይስደበው ሰውን ድሃ ብላችሁ አታንቋሹ ሞኝ አትበሉት በሞኝነቱ ውስጥም ቢሆን ደግነቱን እዩለት እግዚአብሔር የሚፈልገው ከሁሉ ነገር ጥሩ ጥሩውን መሆኑን አስተውሉ ማንም ሰው የአይምሮ መታወክ የደረሰበትም ቢሆን እሱነቱን እያወቁለት ሁኔታውን ሁሉ ከእሱነቱ አንጻር እየተገነዘቡለት ሲረዱት ይረዳል አለበለዚያ እሱነቱን እያጠፉበት ቢረዱት አይጠቅመውም። የማንኛውም ሰው ሕልውና የተጠበቀለት መሆኑ ሲረጋግጥለት ያ ሰው መጽናናትን ያገኛል የገዛ ራሱን ሕልውና የሚያሳጣ ምድራዊ እውነታ ውስጥ በግድ እንዲገባ ሲገፋፉት ግን ያ ሰው ካልታሰበ ጉዳት ላይ ሊወድቅ ይችላል በእግዚአብሔር ግንዛቤአዊነት ምክንያት ነው ያልጠፋነው እግዚአብሔር በኛ ላይ ግንዛቤአዊነት ባይኖረው ኖሮ ኃጢአተኞችን ሁሉ አጥፍቶ ይህችን ምድር ለጻድቃን ብቻ ያደርጋት ነበር ከነኃጢአታችን ታግሶን ያቆየን መዳኛችንንም ያዘጋጀልን አምላካችን የእያንዳንዳችንን ድክመት ስለሚገነዘብ ነው በዳበሳ እንዳንኖር ነቃ እንበል የሰውን ታሪክ መንፈሳዊነቱንም ባንድላይ ሆነን እንመልከትለት የተሰጠንን ምድራዊ ኑሮአችንን ከመንፈሳዊነት አንጻር ባንድነት ሆነን እንገምግም ምግቧን ያገኘች መስሏት በእሳት ዙሪያ እንደምትዞር በረሮ እኛም ሳናውቅ የእሳት እራት እንዳንሆን የራሳችንን ግንዛቤአዊነት እንመርምረው ግንዛቤአዊነታችን ለራሳችን ለኢትዮጵያችን ለምድራችንም ሁሉ ይሁን ግንዛቤአዊነታችን ምድራችን ግንዛቤአዊነትን ከመንፈሳዊነት የሚያዋህድ የሌላውን ጉድለት ከራሱ እያሟላ እያካካሰ ከሰው ሁሉ ጋር ተቻችሎ የሚኖር ሰላማዊ ሰው ያስፈልጋታል ስለዚህ የመጨረሻ አላማችን የሆነውን የወደፊቱን ሰው ለመሆን እንጣር ከሰብአዊ ግንዛቤ በላይ ካቅም በላይ የሆኑ ብዙ ችግሮች አሉብን ለወደፊትም ይጠብቀናል ግን ሃዘን እንዳይበዛብን ደስታም እንዳይሸሸን መሆን ያለበትን መቀበል ያስፈልጋል ምድር ምንም ብትከፋ ይህ ይመጣል ብለን የምናስበው የአለም ችግር ዘለአለማዊ በሆነውና እስካሁን በተነጋገርነው የማያቋርጥ ክስተት መሠረት እንደ ሌትና ቀን መቀያየር እንደ መሞትና መወለድ ያለ መሆኑን ተገንዝበን ለሰው ሁሉ ከማሰብና ከመሥራት አናቋርጥ ሕይወት አጭር ናት ሁሉም ይሆን ዘንድ የጌታ ቃል መፈጸሙ አይቀርም የሚራዱ መንፈሶች ይመጣሉ ጠላት ሰይጣን እና በምድር ላይ የሚታየው እርኩስ ሥራ ሁሉ በእግዚአብሔር ኃይል ውድም ብሉ መጥፋቱ አይቀርም መጥፎ ሆኔታ ውስጥ ስንዘፈቅ አንፍራ ለእግዚአብሔርም እድል እንስጠው እርሱ የያንዳንዱን ሰው ብርታቱንና ድክመቱን ችሎታውንና ጉድለቱን መጠኑን ወሰን ድንበሩን ሁሉ ያውቃልና እግዚአብሔር ሰውን አንድ ጊዜ ብቻ ፈጥሮ አልተወውም እስከ መጨረሻ ሞቱ ድረስ ይመለከተዋል ስለዚህ ሁላችንንም እንደየአመለካከታችን እየመዘነ እየመጠነ ይመራናል ጠብቆ እዚህ ላደረሰን የርሱን ፈቃድ ለመፈጸም ላበቃን አምላካችን ይክበር ይመስገን ሰው ሁሉ ከሥጋዊ ተጽንኦ በላይ በመሆን መጪውን የመከራ ጊዜ ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት እንዲያገኝ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁንልን አሜን እንድናውቅ የተደረግን እውነት በውስጣችን እንዳይከፋው መንፈሳችን ይቅር መባባል ይሁን ልማዳችን ደግ መሥራት ዕዳችን እንዳይጠፋ ከአይምሮአችን አንድነት እና ፍቅር ሳይለየን በጋራ ችግር ተረዳድተን እርስ በርስ ተግባብተን በመንፈስ ተቀራርበን እጅ ለጅ ተያይዘን ከምድራዊነታችን ባሻገር ቁራሽ እንጀራ ተቆራርሰን በምድራችን ቆይታችን እየሠራን በጎውን እንድንፈጽም የእግዚአብሔር ፈቃዱን እስኪያልፍ ድረስ ሕይወታችን ተፈጸመ ቅጽ ሁለት ይቀጥላል በእውነት ፈጣሪ አምላካችን እግዚአብሔር ፍጹምና ኃያል ስሙ ክቡር ለዘለአለምም የተመሰነጎነ ነው አባሪዎች አባሪ አንድ ተክልዬ የመንፈስ ጸሐይ አባሪ ሁለት ጸሎታት አባሪ አንድ ተክልዬ የመንፈስ ጸሐይ ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እራሱን ዝቅ ያደርጋል ቀሳውስት ጳጳሳትና ዲያቆናት የጻዲቁ የአባታችን የተክለ ሃይማኖትን ታሪክ መርምረው ከኛስ የጎደለው ምንድነው ብለው ይጠይቃሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ካጠገባቸው ምሳሌ የሚሆንላቸው ሰው ቢያጡ የጻዲቁን ታሪክ ተመልክተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን እምነት ያመሳስሉበታል የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮችም ሕዝቦችን በጋራ የሚያስተሳስር የእግዚአብሔር ፍቅር ብቻ መሆኑን እንደሚገነዘቡ ሁሉ ይህም የእግዚአብሔር ፍቅር በኢትዮጵያ እንደነበረ አሁንም መኖሩን ያስተውላሉ የመንፈስ ጸሐይ ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ላይ እያበራ ነው እነሆ። በወጣትነት ዘመናችሁ ለአገራችሁ የተጋደላችሁ ብትኖሩ የእናንተ አካላዊ ሰውነት ቢደክም ብታረጁም ከምድራዊነታችን ባሻገር በማያረጀው መንፈሳዊ ጤንነታችሁ ለኢትዮጵያ መጸለያችሁን እንዳታቋርጡ ለማደፋፈር ይህ ጽሑፍ አስፈለገ በዚህ መጽሐፍ ተክልዬ እያልንም የምንጠራቸው ታላቅ የመንፈስ አባታችን የሆኑት አቡነ ተክለ ተክለ ሃይማኖት በእርግጥ እንደ ጴጥሮስና እንደ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ሐዋርያ የነበሩ ናቸው እርሳቸው በኢትዮጵያ ያከናወኑትን መንፈሳዊ ተግባራት ኢትዮጵያውያን ቢያውቁ ምናልባት የርሳቸው መልካም መንፈስ የበለጠ ያፋቅረን ይሆናል ከዚህ ከዘመኑ ሰው መካከል አንድ መልካም ተአምራታዊ ሥራ የሠራ ሰው ቢኖር ያ ሰው በሚኖርበት አካባቢ ከተቻለም በአለም ዙሪያ የሠራው ሥራ እንዲነገርለት እንዲታወቅለትና እንዲከበርበት አድናቆትን አትርፎ ከሰው ሁሉ በላይ ሆኖ መታየትን ይመኛል ነገር ግን ተአምር የሚሠራ እግዚአብሔር ነው እንጂ ሰው አይደለምና እግዚአብሔር በሰዎች መከበር ሲገባው ሰዎች ሊከበሩበት አይገባም ስለዚህ በእግዚአብሔር ፈቃድ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት በኩል የተሠራ ተአምር ከአንድ አካባቢ ተወርቶ በሰዎች ዘንድ ሰብአዊ ክብር ወደ አባታችን ሲመጣ እርሳቸው ታላቅ ሃዘን እየተሰማቸው ሊኖሩበት የፈቀዱትን ሥፍራ እየለቀቁ ወደ ሌላ ሥፍራ ይሄዱ ነበር ታዲያ ስለርሳቸው ታሪክ እና በርሳቸው በኩል ስለተሠራ ተአምር ሁሉ እንዴት በምድር ይታወቅ። በማለት ካለ ፍርሃት መለሱለት በመጨረሻም ለአጋንንት የሚሰዋበትን ሥፍራ በማፈራረስ ተአምራቶችን ሁሉ በማሳየትና በማስተማር የአካባቢው ሰው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ አድርገዋል በዳሞት አውራጃ ዝባፈተን ከሚባል ተራራ ጣኦታትን በማፈራረስ ሕዝቡን ማስተማር ጀመሩ በዚያን ጊዜ ሽማግሌዎችና መኳንንቶች ተናደዱ አባታችንን ይዘው ለአገረ ገዢው ለክፍለ አገር አስተዳዳሪው አስረከቡ ይህንን ሰው ከንጉሥ እስክናደርሰው ድረስ ጠብቅ ብለው አገረ ገዢውን በኋላ አባታችን ስላጠመቁት ገብረ ዋህድ የተባለውን አስጠነቀቁት ገብረ ዋህድ ግን ልጁን ከሚጥል በሽታ አባታችን አድነውለት ስለነበር ከቤቱ አስቀመጣቸው እርሳቸውም በዳሞት አካባቢ የታመሙትን እየፈወሱ የክርስትና ሃይማኖትን እያስተማሩ ለሦስት ወራት ያህል ተቀመጡ በዚህን ጊዜ ያገር ሽማግሌዎችና መኳንንቶች እንደገና ተናደዱ ከገብረ ዋህድ ቤት በመምጣት ጠብቅ ያልንህን ሰው ከንጉሥ ስለምናቀርበው አሁን አምጣ ብለው ጠየቁት ገበረ ዋህድም አብሬ ከርሳቸው ከአባቴ ጋር እሞታለሁ እንጂ አልሰጣችሁም አላቸው ያገር ሽማግሌዎችና መኳንንቶች አጅግ ተቆጡ ይህንንም ጉዳይ ፈጥነው ለንጉሥ ነገሩት ንጉጮም ሁለቱንም አስራችሁ አምጡልኝ ብሎ አዘዘ ሁለቱም ታስረው ወደ ንጉሥ በሚሄዱበት ወቅት ገብረ ዋህድ ለአባታችን ስለ ንጉሥ ታሪክ እንዲህ እያለ ያጫውታቸው ጀመር ይህ ሞተለሚ የተባለ ንጉሥ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት አንዲት የተዋበች ሴት ወዶ ነበር እርሷንም ለማግባት የሠርግ ስነ ስርዓት በማከናወን ላይ እንዳለ ድንገት ባልታወቀ ኃይል ካጠገቡ ጠፋችበት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አእምሮውን አጣ ምናልባት እርስዎ ከዚህ በሽታው ቢያላቅቁት በነጻ ይለቀን ይሆናል አለበለዚያ ግን ሁለታችንንም እንደሚገድለን አልጠራጠርም ገበረ ዋህድና አባታችን እንዲህ እያወሩ ከቤተ መንግሥቱ ደረሱ ንጉጮዶም ባያቸው ጊዜ በንዴት አስር ሰዎች መረጠና በሉ እነፒህን ሁለት ባለጌዎች ተክልዬ የመንፈስ ጸሐይ ፈጥናችሁ ከሁለት ቀፎ ክተቱና ቀፎውን በደንብ ዘግታችሁ በእርጥብ ቁርበት ጠቅልላችሁ ጦመ ግራር ከተባለው ገደል ወርውራችሁ ጣሉልኝ ብሎ አዘዘ በትእዛዙም መሠረት ተፈጸመ ዳሩ ግን አባታችንና ገብረ ዋህድ ከጣሉአቸው ሰዎች አስቀድመው ከንጉሥ ፊት ለፊት ቆመው ተገኙ የጣሉአቸው ሰዎች ሲመለሱ ባዩአቸው ጊዜ ለጊዜው ተደናገጡና እኛ ከአንግዲህ ወዲያ በነፒህ ሰዎች አምላክ ለማመን ወስነናል አሉ ንጉሥም ሳይጥሉ ጥለናል ብለው የዋሹት መስሉሎት በንዴት ጣሉ ከተባሉት ጭምር አስራ ሁለት ቀፎ ተዘጋጅቶ ሁሉንም ብዙ ሰው በምስክርነት በሜገኝበት ወደ ገደል እንዲከቷቸው ትእዛዝ አስተላለፈ በትእዛዙም መሠረት ተፈጸመ ነገር ግን ከጣሉአቸው ሰዎች አስቀድመው አስራ ሁለቱም ሰዎች ከንጉሥ ፊት ለፊት ቆመው ተገኙ በዚህን ጊዜ ሞተለሚ እጅግ ከመናደዱ የተነሳ በያዘው ጦር አባታችንን ለመውጋት ሲወረውር ጦሩ ከእጁ ላይ እንደ ሰም ተጣብቆ ቀረ ሞተለሚ አባታችንን ለማስገደልና ለመግደል ያደረገው ጥረት ሁሉ ከሸፈበት እሱው ራሱ ከጦሩ ጋር ተጣብቆ በሽተኛ ሆኖ ተሰቃየ በዚህን ጊዜ ገብረ ዋህድ አስታራቂ ሃሳብ ይዞ በመቅረብ እንዲህ አለ ንጉጮ የሚያምንባቸው አዋቂዎችና ጠንቋዮች ማርያኖች ሁሉም ይምጡና ንጉሥን ለማዳን የሚቻላቸውን ያድርጉ ከተክለ ሃይማኖትና ከማርያኖች ንጉሥን ለማዳን የተቻለው እንዳይሞት ለማዳን ያልተቻለው እንዲሞት ይሁን ንጉሥ በገብርዋህድ ሃሳብ ስለተስማማ ማርያኖች ተጠርተው እንዲመጡ አደረገ ንጉሥን የማዳን ሙከራ በማርያኖች ተጀመረፁ ማርያኖች የተቻላቸውን ሁሉ አደረጉ ግን ንጉጮን ማዳን አቃታቸውፅ ቀጥሎም አባታችን ተጠሩ እርሳቸውም በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከደዌህ ዳን ብለው የሞተለሚን እጅ መዳሰስ ሲጀምሩ ወዲያው ጦሩ ከጁ እየተላቀቀ የሰለለ ክንዱም እየዳነ አይምሮውም እየተስተካከለ መጣና ፈጽሞ ጤነኛ ለመሆን በቃ ሞተለሚሜ አይምሮው ሲመለስለት ካሁን በፊት የነበረበትን ሁኔታ እያገናዘበ ስለ አባታችንም በማጠያየቅ ማንነታቸውንም ከተረዳ በኋላ አባታችንን እባክህ እናትና አባትህ ያወጡልህን ተስፋ ዮን የተሰኘውን ስምህን ለኔ ስጠኝ እኔ ደግሞ በምትኩ ሺህ ወርቅ ልስጥህ ብሎ ጠየቃቸው እርሳቸውም የመንግሥትህን እኩሌታ እንኳን ብትሰጠኝ የቀድሞ ስሜን በፈቃዴ አልሰጥህም ነገር ግን በፈጣሪዬ ስም አምነህ ብትጠመቅ ካለ ዋጋ እሰጥሃለሁ ብለው መለሱለት ከምድራዊነታችን ባሻገር ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ማርያኖች ውሸታሞች አባታችን ግን እውነተኛ እንደሆኑ የሚገልጹ አያሌ ተአምራቶች ተፈጽመዋል ይህን ሁሉ በማየት ሞተለሚ ከልቡ በእግዚአብሔር ለማመን ውሳኔ አደረገ አዋጅ አስነግሮም ለጣኦት የሰገደ ሁሉ የሚቀጣ መሆኑን ሕዝቡም በተክለ ሃይማኖት ፈጣሪ እንዲያምን እንጂ ማርያኖችን እንዳይከተል በትእዛዝ መልክ አስጠነቀቀሖ ከዚህ በኋላ ሞተለሚ ጭፍሮቹንና ሠራዊቱን ይዞ አባታችን እንዲያጠምቁት ጠየቃቸው እርሳቸውም ውሃውን ባርከው በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቁት እስከ ነገ ጧት ምንም እንዳትቀምስ ብለው አስጠነቀቁት ቅዱስ ቁርባን አድርገውም ለሞተለሚ እና ለሠራዊቱ ሥጋ ወደሙ አቀበሏቸው ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት ቅዱስ ሚካኤል እና የመላእክት አለቆች አብረዋቸው በመሆን ይራዷቸው ነበር ሞተለሚ ከዚህ ቀን ጀምሮ ሞተለሚ መባሉ ቀርቶ ፍሥሐ ጽዮን ተባለ እንዲህ ሁኔታዎች ተቀያይረው ፍሥሐ ጽዮን የቀድሞው ሞተለሚ ልዩ አለም ውስጥ ገባ ከደስታው የተነሳ ለአባታችን ብዙ ወርቅና ገንዘብ ሰጣቸው አባታችንም ይህንን ገንዘብ ተቀብለው ለድሆችና ለችግረኞች አከፋፈሉ ከዚህ በኋላ በአባታችን ትእዛዝ ፍሥሐ ጽዮን በመንግሥቱ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን አሠራ በተለይ በዳሞት አውራጃ ብዙ ቤተ ክርስቲያን ተሠራ ጣኦት ማምለክ ዛርና ጠንቋይ መጠየቅ ሁሉ ጠፋ አባታችን ወዲያ ወዲህ የማያወላውሉ እውነትን ብቻ የሚያስተውሉ ይህንንም እውነት በተግባር ለመፈጸም ቀጥ ብለው ወደፊት ብቻ የሚጓዙ ስለነበሩ ያንን እርኩስ አረመኔ የተባለ ሞተለሚ ክርስቲያን አድርገው ማቁረባቸው ክፉውን በበጎ ለመለወጥ ያላቸውን ችሉታ ያሳያል ቅዱስ ቁርባን ለማንም ሰው መዳኛ ይሆን ዘንድ የተሰጠ መድኃኒት መሆኑን በተግባር አሳውቀውናል ሞተለሚን ክርስቲያን ስላደረጉት ከአረመኔነት ተለውጦ ጣኦት በማምለክ ዛርና ጠንቋይ በመጠየቅ ፋንታ ቤተ ክርስቲያን በማሠራት ይተባበራቸው ጀመር ክፉውን በደግ የሚቀይር ይህ የጻዲቁ አባታችን መንፈስ ሕያው ሆኖ በኢትዮጵያችን እንዲሁም በምድራችን ይኑርልን እኛም እንደርሳቸው ክፉውን በደግ ለመመለስ ያብቃን አንዳንድ አድርባይ ቄሶች በሞተለሚ ግፊት ቅስናቸውን አፍርሰው ለጣኦታት ሰግደው ነበረ መጥፎውን ወደጥሩ በመመለስ ችሎታቸው አባታችን ቄሶቹን እንደገና አስተምረውና መክረው ወደቀድሞው ክርስቲያናዊ ተግባራቸው ትኩረታችን ከዚህ ታሪክ በምንቀስመው መንፈሳዊ ትምህርት ላይ ይሁን እንጂ በተአምራቶቹ ላይ አይሁን ተክልዬ የመንፈስ ጸሐይ እንዲመለሱ አደረጉ ከሃዲ የሆኑትን ቄሶች ዳግመኛ ቅስና ሰጧቸው ለዲያቆኖችም እንዲሁ አደረጉ ጻዲቁ አባታችን ቄሶች ሃይማኖታቸውን ለሥጋዊ ኑሮአቸው መጠቀሚያ ብቻ እንዳያደርጉት የፈተና ጊዜ ሲመጣም ጸንተው እንዲቆዩ አስተማሩ እንጂ እነርሱን ወንጅለው አላባረሯቸውም አልገዘቷቸውም ሰው ሆኖ በሰው ላይ መፍረድ የማይገባ ስላልሆነ ቄሶቹን እና ያካባቢውን ሁኔታ በግንዛቤአዊነት ተመልክተው ጻዲቁ አባታችን ለቄሶቹ ራሩላቸው የቅስና ማዕረጋቸውን መልሰው አብረዋቸው እንዲሠሩ ስለ ፈቃዳዊ ነፃነታቸው ተማጸኑ እንጂ እነሱን አገልለው ለብቻቸው አልቀሩም እንዲህ አብሮ ለመሥራት የሚያስችል ሁኔታን የሚያስተካከል የጻዲቁ አባታችን መንፈስ ሕያው ሆኖ በኢትዮጵያችን እንዲሁም በምድራችን ይኑርልን እኛም እንደርሳቸው ከነልዩነቶቻችን በግንዛቤአዊነት አብሮ ለመሥራት ያብቃን አባታችን በዳሞት አውራጃ ዓመታት ከኖሩ በኋላ በምትካቸው ገብረ ዋህድን እና ካህናቱን እንዲያስተምሩና እንዲንከባከቡ በሃላፊነት አስረክበው ተለዩአቸው ወደ ሰሜን በመጓዝ እግረ መንገዳቸውን ብዙ በሽተኞችን ከፈወሱ በኋላ ወደ አንድ ገዳም ደረሱ የዚህም ገዳም አበ ምኔት አባ በጸሎተ ሚካኤል ይባላሉ አባታችን እዚህ ገዳም ውስጥ ለስድስት ዓመታት በመኖር እራሳቸውን ዝቅ አድርገው በወፍጮ ሥራና በሌላም ሥራ ያገለግሉ ጀመር የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም ማቴ የሚለውን ጥቅስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን በማስታወስ አባታችን ከገዳም በሚኖሩበት ወቅት በውስጣቸው ያለው የመንፈስ ኃይል ባካባቢያቸው የሚገኙትን በሽተኞች ሳይረዱ እንዳይቀመጡ አደረጋቸው በዚህም ምክንያት ብዙ በሽተኞችን አዳኑ በዚህም ሥራቸው በመደነቅና በመከበር በአማራው አውራጃ ሁሉ ታወቁ አበ ምኔቱም የአባታችንን የተደበቀ ታሪካቸውን በመስማታቸው በልዩ ክብር ይንከባከቧቸው ጀመር የሰው ልጅ በመልካም ሥራው ቢመሰገን መልካም ነው ግን የመንፈስን ወሮታ ለሥጋ ለውጦ ለራስ ክብርን መቀዳጀት ውዳሴ ከንቱ የሚጠላ እንጂ የሚወደድ ስላልሆነ አባታችን ይህንን ውዳሴ ከንቱ በመሸሸ በወሎ ክፍለ ሀገር ሐይቅ ወደምትባል ሥፍራ ለመሄድ ቆረጡ። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ የኢትዮጵያ ታሪክ ኛ መጽሐፍ ተስፋ ገብረ ሥላሴ አዘጋጅ መዝሙረ ዳዊት ወጸሎታት ዘነቢያት ወመልየ ዘሰለሞን ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት አዲስ አበባ ተስፋ ገብረ ሥላሴ አዘጋጅ ገድለ አቡነ አረጋዊ ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት አዲስ አበባ ተስፋ ገብረ ሥላሴ አዘጋጅ መልክአ ሚካኤል በአማርኛ ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት አዲስ አበባ ህኪት ሉላዊ መካነ አራዊት መንፈሳዊ ቅንአት መዝት ምድር ምድራዊነት ምድራዊ እውነታ ሩሐማ አዎንታዊነት አሉታዊነት አልባ ንድፈ ሃሳብ ቶርቶራ የቃላት ትርጉም እንቅፋት ደንቃራ ክፋት ተንኮል ክፉ ሥራ አለም አቀፋዊ የተለያዩ አራዊቶች ከተፈጥሮአዊ ተወስደው የሚኖሩበት ውሱን ሥፍራ መኖሪያቸው የመንፈሳዊነት ዝንባሌ ማገድ ማሰር በምንኖርበት አለም መሬቱ አፈርና ድንጋዩ ውሃውና አየሩ በውስጡ የሚገኙ ሕይወት ያላቸውና የሌላቸው በጠቅላላ አዳም የሰው ልጅ ከገነት ከወጣ ጀምሮ ከምድር የተረከበው ሁሉ በምድር ለመኖር ሲባል የግዴታ መሆን ያለበት ሁሉ ምድራዊዋነት ዘለአለማዊ ደግነትን ፍቅርን እና ሰላምን በሰው ልጅ እድሜ ብቻ ይወስናል ምድራዊነት ከጊዜያዊ ጥቅም ጋር ስለሚሄድ በጎም ሆነ ክፉ ግልጋሎቱ ለምድራዊ ኑሮ ማደላደሊያ ለሥጋ ምቾት ለአካላዊ እንቅስቃሴና አድገት ከመሆን አያልፍም ምሕረት የሚገባውት ሁሉን ነገር በጥሩ ጎኑ መመልከት ሀከበከ ሁሉን ነገር በመጥፎ ጎኑ መመልከት ህ ባዶ የሌለው በማስረጃ የሚረጋገጥ ሃሳብ በከዩስ አክራሪ እንዲሁም ነፍስ አጥፊ ክርስቶሳዊነት ክስተት ኪርያት ቂርያት ንቃተ ሕሊና ቀኖና ቅዱስ ቁርባን ቅድምአየሁ ስነ አመክንዮ ሰብእነት ሰብአዊነት ከምድራዊነታችን ባሻገር እንደ ክርስቶስ መሆን የክርስቶስን ትምህርት ይቅር ማለት መጥፎን በጥሩ መተካት ቂም በቀል የሌለው የፍቅር ኑሮ መከተልና በሥራ መተርጎም መልካም መሥራት የሚጎዳው መጥፎዎችን ብቻ ስለሆነ አንድ ግለሰብ መጥፎ ነገር ቢደርስበትም ክርስቶሳዊ አመለካከት ካለው ጥሩ ከመሥራት አያቋርጥም ክርስቶሳዊነት የሰው ዘር የሆነ ሁሉ ሊኖረው የሚችል የፍጹም ሰውነት ጠባይ ነው አሁን ክርስቶሳውያን ያልሆኑ ሂንዱዎች እስላሞች አይሁዶች እና ሌሎችም በተፈጥሮአቸው ክርስቶሳዊ ሊሆኑ ይችላሉ በመጨረሻ ሰው ሁሉ ክርስቶሳዊ ይሆናል የሁኔታዎች መከታተል ሂደት ፀከዩበዐዘዩበዐበ ከተማ ኪርያተ ሰማይ የሰማይ ከተማ የሕሊና ንቃት ርዐበከርዐህከ በመንፈስ ነቃ ማለትም ሊሆን ይችላል የቤተ ክርስቲያን ደንብ ሕግ። ከክርስቶስ ጋር አንድነትን የሚመሠርት ሥጋ ወደሙ መቀበል ሀርከበቨ ዘቨ ር ዐበበበበሀበዐበ ቅዱስ ቁርባን ከክርስቶስ የተሰጠ የምህረት መንፈሳዊ ምልክት ነው ሰው ከኃጢአት እስካልተለየ ድረስ ቅዱስ ቁርባን እየተቀበለ ራሱን ከመጥፎ ተግባር ለማራቅ እንደሚረዳ የሚቆርቡ ሁሉ ያውቁታል ለወደፊት የሚሆነው አስቀድሞ በግልጽ ሲታይ ሃበ ቀጥተኛ አስተሳሰብ ከህበበ ትክክል የሚመስል የአስተሳሰብ ዘገባ ቀጥ ያለ አስተሳሰብ ሰው መሆን ከእንስሳት የተለየው የሰው ልጅ በሰውእነት ፍጥረቱ ጠበከ ክዘዐበበከ የሰው ዘር በጠቅላላ ከሀጠበከ የቃላት ትርጉም የእውቀት መለኪያ የሰው ልጅ የግለሰብ ግድያ የአያድርስ በሽታ የሰው ሁለትነት ይቀተል ውስጣዊ ድርድር ዶግማ ድምጽ አልባ በእውቀት መለኪያ ሚዛን ሀፎጠሃ ፍልስፍና መሠረት እውቀት ማለት የሚታመንና እውነት የሆነ ነው ከአዳም ጀምሮ ከፍጥረታት ሁሉ ተለይቶ ሰው የተባለውና የሰብአዊነትን ቅጥልጥል ሕይወት የሚገልጽ አብዮታዊ ያልሆነ ወደ መሠረታዊ ለውጥ የማያመራ ግድያ ሀህከበ በሰውነት ውስጥ የበሸታ ተከላካዮችን የሚቀንስ በሽታ ል በዓለም ውስጥ ከሰላሳ ሚሊዎን በላይ በዚህ በሽታ የተያዙ ሲሆን እስካሁን ከሦስት ሚሊዎን በላይ በዚሁ በሽታ ሞተዋል አንድ ሰው በአካሉ እና በምድራዊ አመለካከቱ አንድ ቢባልም ከምድራዊነቱ ባሻገር በሚኖረው ሰማያዊ አመለካከቱ ምክንያት ውስጣዊ መንፈሳዊ ጠባይም ስለሚኖረው ሁለትነቱን ይረጋገጣል በአጠቃላይ ከአንዱ ሰው የሚመነጨው የራስ ወዳድነቱ ጠባይ ከምድራዊነቱ በተቃራኒውም ለአጠቃላይ ሰብአዊ ደህንነት የማሰብ ጠባዩም ከሰማያዊነቱ የሚመነጭ ሳይሆን አይቀርም አንድ ሰው ከምድራዊነቱ ሌሳ መንፈሳዊ ጠባይ ባይኖረው ኖሮ ምናልባት የሚያሳዝን ነገር እጅግ ያሳዝነው የሚያስደስት ነገርም እጅግ ያስደስተው ነበር ይገደል ይወገድ ይጥፋ ተጻራሪ ሃሳቦችን ከራስ ጋራ በሚዛናዊነት ለማስታረቅ መሞከር በሲኖዶስ የጸደቀ መሠረታዊ የእምነት መግለጫ ጸሎተ ሃይማኖት እምነታችንን የምንገልጥበት ዶግማችን ነው ድምጽ የሌለው ድኅነት ግንዛቤአዊነት ከምድራዊነታችን ባሻገር መዳን ከኃጢአት መንጻት ደህንነት ቢባል ከሥጋ ደዌ መዳን ይመስላል ከአካባቢ ጋር ነፍስ ያለውም የሌለውም ስምም ሆኖ በሰላምና በፍቅር ለመኖር የሚያበቃ በሁኔታዎች ውስጥ እራስን በሌላው እግር ሆኖ ነገሮችን በከፍታ በመመልከት የሜገኝ አስተዋይነት ነው ነፎበፎ የቅጽ ሁለት ይዘት የቅጽ ሁለት ይዘት በሚቀጥለው መጽሐፍ ቅጽ ሁለት የተጠቃለሉ የሦስት ክፍሎች ይዘት እንደሚከተለው ነው ክፍል አንድ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ በጠፈር ሁሉ ክፍል አንድ አካላዊ ተፈጥሮ ከመጀመሩ በፊትም ሌላ አካላዊ ያልሆነ አለም ነበረ በማለት ይነሳና አካላዊ ተፈጥሮ ከየት ተጀመረ። በማለት የወደፊቱን የሰብዓዊነትን መንፈሳዊ ጉዞ ለመገምገም ሲል በተለይ የመካከለኛው ምሥራቅን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ ይጀምራል ቀጥሎም ስለ ኢትዮጵያውያኖች የመንፈሳዊነታቸው ታሪካዊ ሂደት ከብዙው በጥቂቱ ይጠቃቅሳል ሃይማኖተኛነትን እንደ ኋላቀርነት የሚመለከቱ ሰዎች የሃይማኖትን ጉዳይ በሳይንሳዊ ስነአመክኖአዊ አመለካከት ቢገመግሙት ወይንም ከምድራዊ አካላዊ ስነአመክኖአዊ አመለካከት ውጪ በመንፈሳዊ ተመስጦ ቢመለከቱት አንዳንድ ሃይማኖታዊ ምሥጢሮች ይገለጡላቸው ይሆናልና በውስጣችን በመንፈሳችን ያለውን የዛሬውን እና የወደፊቱን ብሩህ ተስፋችንን እንመለከተው በማለት አንዳንድ መንፈሳዊ ጉዳዮች በክፍል ሦስት እና በአባሪዎች ተካተዋል የሃይማኖት ትምህርት እንደ ሳይንስ አንድ ወጥ ሆኖ ለሰው ሁሉ በአንድ አይነት መልክ ብቻ አይደለም የሚሜዳረሰው ተናጋሪዎቹ ሰባኪዎቹ አስተማሪዎቹም ምንጊዜም የሃይማኖት ሊቃውንት ብቻ አይደሉም እግዚአብሔር የሰው ልጅ በጠቅላላ እንዲጠፋ ስለማይፈልግ ግለሰቦችን በተለያየ መንገድ ያስተምራቸዋል ይህንኑ በመንፈሳዊ ቅንአት ለሌሎች ለማካፈል የሚሹ ብዙዎች ናቸው በነባር ሃይማኖታዊ ጽሑፎች የተደገፈ ከተራ ሰዎችም የሚፈልቁ መንፈሳዊ ሃተታዎችን በጥሞና ማስተዋል አንድም የሰው ልጅ በተፈጥሮአዊ ጠባዩ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን መንፈሳዊ የአመለካከት ጸጋ በገዛ ራሱ ያጎላው ዘንድ ይጠቅመዋል በመጥፎ አድራጊዎች ያልተጠለፈ ሃይማኖት የሰውን ልጅ ምድራዊ ኑሮም እን ዳሻሻለው እንደተመለከትን ሁሉ በዚህ ክፍል የተካተቱ ሃይማኖታዊ ፍሬ ሃሳቦችም አላማ ከምድራዊነታችን ባሻገር የሚኖረን አመለካከት ከሞትን በኋላ ለሰማያዊ ኑሮ ብቻ ሳይሆን ለምድራዊ ኑሮአችንም ለሰላማችን ለማሕበራዊ ኑሮአችን እና ለአንድነታችን ስለሚጠቅመን የመንፈሳዊነታችንን ነገር ችላ እንዳንል ለማስታወስ ለማደፋፈርም ነው ከምድራዊነታችን ባሻገር በዚህ ክፍል ውስጥ ዋናዋናዎቹ የሰብአዊነታችን ሃይማኖቶች ጠቅለል ባለ መልክ ቀርበዋል አንባቢያን ከአንዱ ሃይማኖት ዘለው ወደሌላ ሲሄዱ በሁሉም ሃይማኖት ውስጥ ጊዜ የማይሽረው እውነት መኖሩን ያስተውላሉ በሰብአዊነታችን ታሪክ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ አንድ ብቻ የሆነውን እና በሁሉም ሃይማኖት ውስጥ የሚገኘውን እውነት ለገዛ ሃይማኖት ማጠናከሪያ ማድረግ ይጠቅማል የክፍል ሦስትም ዋነኛ አላማ ይኸው ነው።