Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ፀ ጠፀሂ ውስጥ ያሉት ገጸባህሪያት ሁሉ ኣዋቲቂምች ዓቸጡ አሷ ብቻ ናት ልጅ እና ይህን የእኛን የአዋቂዎች አለም አራዳ ነቁ ቆቅ ዛዚ አእያየተው ስትጫወትበት ስትማርበት እንዴ ነው።
ብሎ አሰበ ጋብሪዬል እየተበሳጨ ማመኑ ያስቸግራል ታጥበው አያውቁም ጋዜጣ ላይ ሲነግሩን በፓሪስ ከተሰሩት አፓርትመንቶች ባኞ ቤት ያላቸው ከመቶ አስራ አንድ እንኳ አይሞሉም ይፄ አያስገርመኝም ግን ያለባኞ ቤት መታጠብ ይቻላል እነዚህ የከበቡኝ ተሳፋሪዎች ምንም ያህል የሞከሩ አይመስሉም በሌላ በኩል ደግሞ ከፓሪስ ህዝብ በሙሉ ከሁሉ የባሰ የቆሰሰውን ሰው መምረጥ የሚያስመኝ አይደለም ምንም ምክንያት የለም ባጋጣሚ ነው እነዚህ የተሰበሰቡት በኦስተርሊትዝ ባቡር ጣቢያ ለመሳፈር የሚጠብቁ ሰዎች በሊዮን ጣብያ ከሚጠብቁት ሰዎች የባለ ይቆንሳሉ ብሎ ማሰብ የማይሆን ነገር ነው እንደ እውነቱ ከሆነ ምንም ምክንያት የለም ለማንኛውም ግን እንዴት ያለ ቁናስ ነው ጋብሪዬል ከአእጅጌው ውስጥ ወይን ጠጅ የመሰለች የሀር መሀረብ አውጥቶ አፍንጫውን አበሰ ይህን ያህል የሚገማው ማን ነው እሱ አሉ አንዲት ወይዘሮ ከማዶ ጮክ ብለው ይህን ያሉት ስለራሳቸው እያሰቡ አልነበረም ራስ ወዳድ አልነበሩምና የተናገሩት ከዚያ ከለውዬ ስለመጣው ሽቶ ነው ጋብሪዬል በቃላት ጨዋታ ተረብ ፈጣን በመሆኑ ይፄማ እምዬ ሆይ በልዩ ስሙ ባርቡዝ የሚባለው በታላቁ የሽቶ አምራች በፊዮር ቤት የተመረተው ሽቶ ነው አላቸው እሱም ቢሆን አገሩን እንደዚህ እንዲመርዝ ሊፈቀድለት አይገባም ሲሉ ቀጠሉ ወይዘሮዋ መብቱ የራሳቸው መሆኑን እርግጠኛ ስለነበሩ የምትይው በደምብ ገብቶኝ ከሆነ እምዬዋ ያንቺ የተፈጥሮ ጠረን ከፅጌረዳዎቹ ያስንቃል እረ ተሳስተሻል እምየዋ ተሳስተሻል ለማኸው። ባለፈው እንደዚያ ሲሆን ልክ በጊዜ ደረስሽኮ የሆነ ሆኖ አለች ዣን ላሎሼር እንደገና እንዲደገም አልፈልግም አታስቢ አለ ጋብሪዬል ጥሩ እንግዲያው ተነገወዲያ በአስራ ሁለት ከስድሳ በሚነሳው ባቡር እንድንሄድ እዚሁ እንገናኝ የሚወስዳችሁ ባቡር በሚቆምበት በኩል እንክት አለች ዣን ላሉሼር በጀርመንኛ ጀርመናቹ ሲገዙዋት በተማረችው በነገራችን ላይ ሚስትህ ደህና ናትን ደህና ናት መጥተሽ አታይንምንዴን ጊዜ አላገኝም ውሽማ ሲኖራት ሁልጊዜ እንደዚህ ናት አለች ዛዚ ቤተሰብ የሚባል ነገር ለሷ የለም ደህና ሁፒ የኔ ፍቅር ደህና ሁን ጋቢ ይህን ብላ ሄደች ዛዚ ሁኔታዎችን ትዘግባለች ተይዛለች ጋብሪዬል ትከሻውን ከፍ ዝቅ አደረገ ምንም አላለም የዛዚን ሻንጣ አነላሳ እንሂድ አለ እና ወደፊት የመሮጥ ያህል ሲራመድ መንገዱ ላይ ያገኘውን ሁሉ ወደቀኝና ወደ ግራ እየገፋ ነበር ዛዚ ከቷላ ኋላው ጋለበች አጎቴ አለች በሜትሮ ነው ምንፄደው። ጮኸ ጋብሪዬል ሜትሮ። አየኸው ማን እኮ ፓንቴዮን ላይሆንም ይችላል አለ ሻርል ግትር ስለሆነ ሮ ዞሮ አንዱን መንገደኛ እንጠይቅ ሀሳብ አቀረበ ጋብሪዬል መንገደኞቹ ሁሉም ጆል ናቸው አለ ሻርል በጣም እውነት ነው አለች ዛዚ በሰላማዊ ድምፅ ጋብሪዬል መለስ አለ በጋለ ስሜት የሚናገርበት አዲስ ርዕስ አገኘ ይሄሳ። አለ ሻርል በምፀት ቤቴጋ ያለው ማዞሪያ ነዋ አለ ጋብሪዬል በየዋህነት እንግዲያው እሱ አይደለም አለ ሻርል እንዴት አለ ጋብሪዬል ያ እሱ አይደለም እያልክ ነው። ኤዲያ አለች ዛዚ እንደገና ልትጀምሩ እንዳይሆን እሱ አይደለም አለው ሻርል ጋብሪዬልን ግን እውነቴን ነው ኮ አለ ጋብሪዬል በሱቁ አጠገብ ሲያልፉ እዚህኛው ውስጥ ገብቼ አላውቅም እኔ ምልህ አጐቴ አለች ዛዚ እንደዚህ የምትጃጃለው አውቀህ ነው ወይስ ሳትፈልግ ነው አንቺን ለማሳቅ ብዬ ነው ልጄዋ አለ ጋብሪዬል አታስቢ አላት ሻርል ሆን ብሉ አይደለም የሚያረገው ብልጠት አይደለም አለች ዛዚ እውነቱን ልንገርሽ አለ ሻርል አንዳንዴ ሆን ብሎ ያረገዋል አንዳንዴ ሳያውቅ ነው እውነቱን ጮኸ ጋብሪዬል ሰውነቱን እያወራጨ ልክ አንተ የምታውቀው ይመስል እዚህ አለም ላይ ግን ማንኛውም ሰው የማያውቀው ይመስል ይፄ ሁሉ ቅጥፈት ነው። ሁስት እዚህ ነው አለ ጋብሪዬል ዛዚ ቤቱን አስተዋለችው የተሰማትን ግን አትገልፅም ታዲያስ ጠየቀ ጋብሪዬል ይስማማል። ጠየቀ ቱራንዶ ትክክል መለሰ ሻርል እንደዚህ ትልቅ አልመሰለችኝም ነበር እና። ሁለቱም ማሰብ ጀመሩ እንቅልፍ መድሃኒት ብናስውጣትስ አለ ጋብሪዬል እስከ እኩለ ቀን እንድያስተኛት እንዲያውም እስከ አስር ሰአት በፊንጢጣ የሚገባ መድሃኒት አለ አሉ ይህን ውጤት የሚያስገኝልን ካ አለ በሩ በቀስታ ቱራንዶ ነው ማቡ አለ ጋብሪዬል ቱራንዶ ከላቨርድዩር ጋር ገባ ማንም ኖር ሳይለው ተቀመጠና ግረናዲነን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ ላቨርዲዩር የግረናዲን ጠርሙሱን በማይረሳ መጐምጽቫት ተመለከተች ማርሰሊን ወደመጠጫዋ ትንሽ ቀዳችላት ጋብሪዬል የመሀል ጣቱን ጥፍር ጨርሶ የአመልካች ጣቱን ጀመረ ይሄ ሁሉ ሲሆን ማንም አልተናገረም ላቨርዲዩር ግረናዲዋን በአንድ አፍታ መጠጠችው ማንቆሪያዋን መቆሚያዋ እንጨት ላይ አበሰች ከዚያ በሚከተለው ስልት ተናገረች ታወራለህ ታጦራለህ ይሄን ብቻ ነው ማድረግ ምታውቀው ማውራት የቂጤን አበሳ ይስጠው ብሎ መለሰ ቱራንዶ በንይት። ጠየቀ ጋብሪዬል ቁልጭ ባለ ማስፈራራት ስትናገር በፀያፍ ቃላት መሆን ጀመረ አለች ማርሰሊን ሊያበሳጨኝ ስለጀመረኮ ነው አለ ጋብሪዬል አትብሸቅ አለች ማርሰሊን በለስላሳ ድምፅ እንዲህ ያለች ወራዳ ልጅ እቤቴ ውስጥ አልፈልግም አለ ቱራንዶ በሚያሳዝን ቅላ ጻደበርኩህ። አለ ጋብሪዬል እኔ አይደለሁምኮ አለ ቱራንዶ እሷ ናት ያሳብቃል አለች ዛዚ ብሽቅ ነው አሁን ንግዲህ ይብቃን አለ ጋብሪዬል መፄጃዬ ደረሰ ደስ ሚል አይመስልም የሌሊት ዘበኛ መሆን አለች ዛዚ ማንኛውም ሙያ በጣም ደስ አይልም አሁን ሂጂና ተፒ ቱራንዶ የወፍ ጎጆውን እያነሳ እንዲህ አለ በዚህ ርዕስ ውይይታችንን እንቀጥላለን እና የብልህ ሰው ገፅታ እያሳየ ውይይት የቂጤን አበሳ ይስጠው። አለች ዛዚ ወፏን እየተመለከተች ሂጂ ንጂ ተፒ አለ ጋብሪዬል ዛዚ በአንድ በር ወጣች የማታው ጐብፒዎች በሌላ በር ወጡ ጋብሪዬል ሁሉ ነገር ሰላም እስኪሆን ቆይቶ በተራው ወብጣ ደረጃውን ድምፅ ሳያሰማ ወረደ እንደ ጨዋ ተከራይ ማርሰሊን ግን ኮመዲኖ ላይ አንድ ነገር አየችና አንስታ በሩን ለመክፈት ሮጠች እና በደረጃው ጐምበስ ብላ በለስላሳ ድምፅ ተጣራች ጋብሪዬል ጋብሪዬል ምነው ምን መጣን የከንፈር ቀለምህን ረሳህ ሶስት በመኝታ ቤቱ በአንዱ ማእዘን ማርሰሊን አንድ መፀዳጃ ቤት ብጤ ለርታለች አንድ ጠረጴዛ መታጠብያ ሰሀን ማንቆርቆርያ ጭልጥ ያለ ገጠር ውስጥ ያለች እስኪመስል እንዲህ ቢሆን ዛዚ ቤቷ አይናፍቃትም በማለት ዛዚ ግን ግራ ተጋብታለች ወለሉ ሳይ በሚስማር የተጣበቀውን ሽንት ቤት ተጠቀመችበት ሌላውንም ድንቅ ፅዳት መጠበቅያ ቁሳቁስ አስተዋለች ይሄ ፋራነት አስጠላት ፊቷን ውሀ አስነካች ማበጠርያውን በፀጉሯ ላይ አንድ ጊዜ ብቻ አስኬደች ወደ አጥር ግቢው አየች ጭር ብሏል ያው ነው ምንም ነገር ያለ አይመስልም ጆሮዋን ወደ በሩ ብታቀርበውም ምንም ድምፅ አልተሰማት በፀጥታ ከመኝታ ክፍሉ ወጣች እንግዳናምግብቤቱ ጨልሞ ፀጥ ብሏል በዝግታ እግሮቿ ባንድ መስመር ሲራመዱ እየተነካኩ ግድግዳውንም አቃዎቹንም በጥንቃቄ እየነካካች ለበለጠ ደስታ ደሞ አይኗን ጨፍና ነው ሌላኛው በር ጋ ደረሰች እና በስንትና ስንት ጥንቃቄ ከፈተችው ይሄኛው ክፍልም ጭለማና ፀጥታ ውጦታል የሆነ ሰው ተኝቶ በሰላም ይተነናሳል ዛዚ በሩን መልሳ ዘጋች በመጣችበት አኳጊሏጊን የኋሊት መሄድ መረች ሁሌ ደስ ሚል አካፄድ ነው መቸስ እና በጣም ረዥም ጊዜ ካለፈ በኋላ ሌላ እና ሶስተኛ በርጋ ደርሳ ከቅድመ ባላነሰ ጥንቃቂ ከፈፌተችው የደረሰችበት መግቢያ በቀይና በሰማያዊ መስተዋት ባጌጠ መስኮት የገባ ጭላንጭል ያበራዋል አንያ መጨረሻ በር ከፈተችና የጉዞዋን አላማ ደረሰችበት ሽንት ቤት ዘመናሞ በመሆነ ስለተስማማት ሩብ ሰአት ሙሉ አዚያዐኑ አሳለፈች ቦታው ጠቃሚ ብቻ ሳይሆን የደስ ደስ አለው ንዑህ ነው ጻ ት ስጥ ሲንኮሻኮሽ ደስ ይላል በራል ሀር አይነት። እንደ ቱራንዶ። ቱራንዶ ትከጓውን ከፍ ዝቅ አደረገ አንተም ራስህ አለ በንቀት ድምዕ ታጠራለህ ታወራለህ ይሄን ብቻ ነው ማድረግ የምታውቀው እንግዲያው ሂዳ አለች ማርሰሊን በዝግታ ለጋብሪዬል ሁለታችሁም ደበራችሁኝ አጉተመተመ ጋብሪዬል ወደ ክባሉ ገባ በስልት ለበሰ ለመላጨት ጊዜ ያላገኘለትን አገጩን በሀዘን ደባበሰ በረዥሙ ተነፈሰ ተመልሶ ብቅ አለ ቱራንዶና ማርሰሊን ስለልብስ ማጠብያ ማሺኖች ጠንካራና ደካማ ሥን አየተወያዩ ናቸው ጋብሪዬል ጐምበስ ብሎ የማርሰሊንን ግምባር ሳመ የህና ሁፒ አላት በቁም ነገር ተግባሬን ልፈፅም እየመረሽኩ ነው የቱራንዶን እጅ በበቅ አርጎ ጨበጠው ሲለያቸው የሚሰማቸው ዞዘን ልቡን አየጨመቀው ተግባሬን ልፈፅም እየወጣሁ ነው ከሜሉት የተለዩ ታሪካዊ ቃላት ለመናገር አላስቻለውም አስተያየቱ ግን የሚሄዱ በተን ስባራ ላቅ ተግባር በሚጠብቃቸው ግለሰቦች ሀዘን አይነት ተጋርዶ ሃዘር ሌሉ ሀሳባቸውን ሰባሰቡ አየ ሠባ ነቡ ዐጣ ሲወጣ አየሩን ሳበው የሚስተው የተለመዱ ጠረኖች ነበሩ በተለይ ላ ዛዘ የሚወቡጡትቶ ወደ ሰሜን ወይስ ወደ ደቡብ መ እንደሚኖርበት ማወቅ አልቻለም ምክንያቱም የመንገዱ አቅጣጫ እንደዛ በመሆኑ ደግነቱ አንድ ጥሪ ማመንታቱን ቆረጠለት ግሪዱ ጫማ ሰፊው ነው ከተለጣፊ ሱቁ የሚጠራው ጋብሪዬል ወደሱ ሄደ እርግጠኛ ነኝ ትንጂን ልጅ ነው የሚፈልጉት አዎን አለ ጋብሪዬል ቅዝቅዝ ባለ ስሜት የት እንደፄደች አውቃለሁ እርሶ ሁልጊዜ ሁሉን ነገር ያውቃሉ አለ ጋብሪዬል እየበሸቀ ይፄ ደሞ አለ ለራሱ በሚጢጢዋ የውስጥ ድምፁ ከሱ ጋር ባወራሁ ቁጥር የበታችነት ስሜቴን ያባርርልኛል አይመለከቶትምንዴ ጠየቀ ግሪዱ እሱማ በግድ ይመሰከተኛል እንግዲያው ልናገር። ጫማ ሰሪዎችኮ ያስቃሉ አለ ጋብሪዬል አንድ ጊዜም ስራቸውን አያቋርጡም ይወዱታል ያሰኛል እና በፍፁም እንደማያቋርጡ ለማሳየት መስታወት ጐጆ ውስጥ ይቀመጣሉ ሰው እንዲያደንቃቸው የተቀደደ የሀር እግር ሹራብ እንደሚሰፉ ሴቶች እርሶስ መለሰ ግሪዱ ሰው እንዲያደንቆት ምን ውስጥ ነው ሚቀመጡት ጋብሪዬል ጭንቅላቱን አከከ ምንም አለ በልፍስፍስ ድምፅ እኔ አርቲስት ነኝ ምንም ቀሽም ነገር አልሰራም አሁን ይሄን የምናወራበት ሰዓት አይደለም የልጅቷ ጉዳይ ያስቸኩላል ስለሷ ማውራት ደስ ስለሚለኝ ነው መለሰ ግሪዱ በእርጋታ ከስራው ቀና አለ ታዲያስ። ጃንጥላዬን እዛ ቡና ቤት ረሳሁት አለ ለራሱ ነበር የሚያወራው በትንሽ ድምፅ ዛዚ ግን ከተናገረው ቃላት አንድ ነገር ለማወቅ ጊዜ አልወሰደባትም ሰውየው የውሸት ፖሊስ የሚመስል ወጠጤ አይደለም እውነኛ ፖሊስ የሚመስል ወጠጤ ለመምሰል የሚሞክር ፖሊስ ነው ምክንያቱም ጃንጥላውን ረሳ ይህ የሀሳቦቿ ቅደም ተከተል ምንም እንከን የሌለው መስሎ ተሰማት ዛዚ አጎቷን ከእውነተኛ ፖሊስ ጋር ግምባር ለግምባር ማገናኘት ደስ ሚል ረቂቅ ብልሀት ሳይሆን አይቀርም የሚል ሀሳብ መጣባት ይህን ጉዳይ ከተወያዩበት በኋላ ሰውየው ይፄን ሁሉ አይደለሁም አላትና የት እንደምትኖር ጠየቃት ሳታምታታ አድራሻዋን ነገረችው አንዳለችውም ብልህቷ ደስ ሚል ሆነ ጋብሪዬዩል በሩን ከፍቶ ዚ ብሉ ሲጮህ ዛዚ ደስ በተሰኘ ድምፅ አጐቴ ይኸውልህ ሊያናግርህ የሚፈልግ ፖሊስ ስትለው ግድግዳውን እየተደገፈ ፊቱ በድንጋጤ አረንጓዴ መሰለ እውነት ነው በመብራቱ ሊሆን ይችላል እዚህ መግቢያ ላይ ጨለማ በመሆኑ ይፄ ሲሆን ሳለ ሰውየው ምንም ያላስተዋለ መሰለ ጋብሪዬል ይግበንጂ አለው ስልቱን በሳተ ድምፅ እና ወደ ምግብ ቤት ሲገቡ ማርሰሊን በደስታ ዘላ ዛዚን አቀፈቻት ጋብሪዬል ለመስየ ሚጠጣ ቅድላቸው አላት ሰውየው ምንም አንደማይጠጣ ምልክት አሳየ። ጠየቀ ጋብሪዬል ልጅቱ አንድ ጅንስ ሱሪ ሰርቃኛለች ማለቴ ነው ባጭሩ ይሄ ብቻ ከሆነ አለ ጋብሪዬል ትመልስሉታለች ይሄ ቆሻሻ አለች ዛዚ መልሶ ነጥቆኛል እንግዲያው አለ ጋብሪዬል የርስዎ ቅሬታ ምንድነው። ደሞ ጥያቄዎች ሊያቀርቡልኝ ይቅርታ አለ ሰውየው እኔ አይደለሁም የጠየቅኩት ኣርሶ ነዎት እሱ እውነት ነው አመነ ጋብሪዬል በአመዛዛኝነት ይኸዋ አለች ዛዚ እያወቀ ሊታለልለት ነው አሁን መጠየቅ ምናልባት የኔ ተራ ይሆናል አለ ሰውየው ጠበቃ ሳትይዝ መልስ እንዳትሰጠው አለች ዛቪ ሰላም ስጪኝ አለ ጋብሪዬል ማድረግ ያለብኝን እኔ አውቃለሁ እንድትነግረው የሚፈልገውን ሁሉ ያውጣጣሀል ሞኝ እመስላታለሁ አለ ጋብሪዬለ ሰውየውን በወዳጅነት እያናገረው የዛሬ ልጆች እንዲህ ናቸው ድሮ ቀረ ለጥንታውያኑ ከበሬታ አሰ ሰውየው እንዲህ ያለውን ጅልነት መስማት ቂል ያስብላል አለች የራሷ አስተሳሰብ ያላት ዛዚ ከዚህ መሄድ ይሻላል እንዲያ ነው። ጠየቀች ዛዚ ጂንስ ሱሪ የሚለብስ ወንድ ነው አለች ማርሰሊን እየቀለድሽብበኝ ነው አለች ዛዚ ጋብሪዬል ሲያስወጣው ይገባል አለች ማርሰሲን አሪፍ ሀሳብ አለች ዛዚ ከዚያ እየተጠራጠረች እስቲ። ጮሽች ዛዚ ምንም ምክንያት አይኖርም የራሴ ነው እኔ አርግጠኛ አይደለሁም አለ ጋብሪዬል በመሰላቸት አዎን አለ ሰውየው በፍጥነት አውልቂ አስወጣው ንጂ አለች ዛቢ ሰጋብሪዬል ፖሊስ ነው ብለሽ ታስጠነቅቂኝና ከዚያ ደሞ ደብድበው ትይኛለሽ። አዎን አሉ ቱራንዶና ማዶፕቲፒዬ በቁጥብነት እኔ ከዚያ በሏላ ነው የመጣሁት አለ ሻርል እና አለ ጋብሪዬል ሰውየውን ተመልሶ ሲያልፍ አላያችሁትማ እየውልህ አለ ቱራንዶ ሲያልፍ በሚገባ ለማስተዋል ጊዜ አልነበረኝም ስለዚህ ባየው እንደማውቀው እርግጠኛ አይደለሁም ግን ምናልባት ከቷላህ እዛ ጥግ የተቀመጠው ሰውዬ ሊሆን ይችላል ጋብሪዬል ዞረ ሰውየው ወንበር ላይ ተቀምጦ ያዘዘውን የሚያነቃ መጠጥ በትዕግስት እየጠበቀ ነው ኽረ በዝንር ያለህ። ጥሩ ነው ካሉኝ እሺ ይህን ጊዜ ጋብሪዬል ፊቱ እየተለዋወጠ ልፍስፍስ ብሎ ወለሉ ላይ ተጋደመ ፈርኒጥብራንካውን ሁለት አርገው አለ ሻርል ጓደኛውን እያነሳ ሁለት ፈርኒጥብራንካ ሁለት አለ ቱራንዶ ሳያስብ ሁኔታዎች ጭንቀት ስለቀሰቀሱበት ብርጭቆዎቹን መሙላት አቅቶት እጁ ይንቀጠቀጣል ቡኒው መጠጥ እየፈሰሰበት ፈሳሹ አጫጭር ቅርንጫፎች እየበቀለ በጠላት ወረራ ጊዜ ከእንጨት የተሰራውን ባንኮኒ ያጎድፈዋል አሱን ወዲህ በሉ አለች ማዶ ፕቲፒዬ ጠርሙሱን ስሜት ካፈዘዘው አለቃዋ እጅ እየነጠቀች ቱራንዶ ግምባሩን አበሰ ሰውየው ዘግይቶ የመጣለትን የሚያነቃቃ መጠጥ በሰላም ፉት ይላል ሻርል የጋብሪዬልን አፍንጫ አፍኖ መጠጡን ወደ አፉ ሲያንቆረቁርለት በከንፈሩ መጋጠሚያ ትንሽ ትንሽ ተንጠባጠበ ጋብሪዬልን ጭንቅላቱን በሀይል ነቀነቀ የሞትክ ጅል አለው ሻርል በጓደኛ ፍቅር ደካማ ሰው። ጠየቀ ቱራንዶ ወደነዚህ ምርጥ ሰዎች በአይናፋር አድናቆት እየተጠጋ አንተ ደሞ አንዳንዴ ደደብ ትሆናለህ አለ ሻርል ጋብሪዬል ምንም አይነት ሞኝነት ቢሰማ ምኑም ሳይገባው እንደሚደጋግመው ታውቅ የለም ንዴ። እንግዲህ ስለሙያዬ ሲጠይቁኝ መልሱን የማልሰጦት ምክንያት እምቢ ለማለት በመፈለጌ አይደለም አዎንንጂ ሲል አመነ ግሪዱ እየተጨነቀ ፍዝዝ ያለ የሞተር ድምፅ ሰምቶ ሰውየው ተገላመጠ አንድ አሮጌ ታክሲ ጋብሪዬልና ዛዚን ይዞ አለፈ ተመኘ ሸሽርሸር መሄዳቸው ነው አለ ሰውየው ግሪዱ ምንም አልተናገረም ሰውየው ራሱ ሽርሽር ቢሄድለት የቀረኝ እርስዎን ማመስገን ብቻ ነው ሲል ቀጠለ ሰውየው ምንም አይደል አለ ግሪዱ ሜትሮውሳ በዚህ በኩል ነው ሚገኘው። አበክሮ ጠየቀ ጋብሪዬል ይህን ጊዜ አገኘሁት ብሎ ጮኸ ሻርል ይሄፄ እንትንየው ሌዜንቫሊድ አይደለም ሳክሬከር ነው አንተ ደሞ አለ ጋብሪዬል እየተደሰተ ምናልባት ባጋጣሚ ሳክሬ ደደብ ሳትሆን ትቀራለህገ። በናንተ እድሜ ኮሚክ ህፃናት መሆናችሁ ድብርት ይለቅብኛሉ አለች ዛዚ ይህን ጊዜ ዙርያውን የተንጣለለውን ከተማ በዝምታ ተመስከቴ ከዚያ ዛዚ ሶስት መቶ ሜትር ከበታቻቸው ያሰውን ሁኔታ አስተዋለችና ያን ያህልም ከፍታ የሰውም አሰች ኺሆንም አለ ሻርል ሰዎችን ለይቶ ማወቅ ሊያስቸግር ምንም አይቀረው አዎን አለ ጋብሪዬል አየሩን እያሸተተ ምንም ያህል አይታዩም ግን ይሸታሉ ሜትሮ ውስጥ ከሚሸተው ግን ያንሳል አለ ሻርል አንተ በሜትሮ አትሄድምኮ እኔም ይህን አሰቃቂ ርእስ ለመሸሽ ፈልጋ ዛዚ አጎቷን አታይምንዴ አለችው ጎምበስ ብለህ እይስቲ ደስ ይላል ጋብሪዬል ቁልቁል ወደ ጥልቀቶቹ አይኑን ጣል ሊያረግ ሞከረ ሜርድ። አጎቴ ጋብሪዬል አለች ዛዚ በሰላማዊ ሁኔታ አንተ ሶዶማዊ ነህ ወይስ አይደለህም። አለ ጋብሪዬል መሀረቡን ወደ ኪሱ እየመለሰ የወንድ ሽቶ ይፄ አውነት ነው አሉ ባላቸው የሞተባቸው ወይዘሮ ዛዚን ደሞ እንድያው በፍፁም አንቺ የገመትሽው አይደለም ዛዚ ክፉኛ በሽቃ ወደ ጋብሪዩዬል ዞረች እንግድያው ሰውየው ለምን በዚህ ጉዳይ ወነጀለህ። ጮኸ ጋብሪዬል ሉዋት ጠችው በግማሽ አታብዥውንጂ አንቺዬ አሉ ወይዘሮዋ ለይስሙላ እያቀማክ የርሶ ምክር አልተፈለገም ብላ ዛዚ ጋብሪዬልን እንደገና ቆነበ ልጆችኮ በአውነት ደስ የሚሉ ናቸው አጉረመረመ ጋብሪዩል ልቦና ሰማእትነቱን በፀጋ እየተቀበለ እርስዎ ግን ይኸውና እንዲህ እስክትረግጥዎት ድረስ እያስጨነ ቁዋት ነው ልጆችን የማይወዱ ከሆነ አሉ ባለፀጋዋ ወይዘሮ የማስተማር ሀላፊነቱን ለምን እንደወሰዱ ግር ያሰኛል እሱ አለ ጋብሪዬል ራሱን የቻለ ሌላ ታሪክ ነው ይንገሩኝ እስቲ አሉ ወይዘሮዋ አመሰግናለሁ አለች ዛዚ ታሪኩን አቀዋለሁ እኔ አላውቀውማ አሉ መበለትዋ እሱ ስሜት አይሰጠንም ታድያስ አጎቴ መልሱሳገ አይደለሁም አልኩሽኮ አይደለሁም እንደገናም አይደለሁም አንድ ሀሳብ ከያዘች አትለቅም ሲሉ ወይዘሮዋ አዲስ ያመነጩት የመሰላቸውን አስተያየት ሰነዘሩ ሚጢጢዬዩ የለየላት ቄብ በቅሎ አለ ጋብሪዬል በርህራፄ ቀጥለው ወይዘሮዋ ቅድም ከሰጡት አስተያየት ያላነሰ ብልህነት ያለው ቁም ነገር ተናገሩ ይችን ልጅ በሚገባ የሚያውቁዋት አይመስሉም የተለያዩ ተሰጥዎቿን ገና ቀስ በቀስ እያስተዋሉ ነው ያሰኛል አኖሩበት ተሰጥዎዎች የሚለውን ቃል በድምዓቸው የጥቅስ ምልክነት ተሰጥዎ የቂጤን አበሳ ይስጠው አጉተመተመች ዛዚ እርስዎስ ነቂ ኖት አለ ጋብሪዬል ደርሰውበታል። አለች ዛዚ እንዴ። ጠየቀች ዛዚ ሰዶማዊ ነው ንዴ። አለች ዛዚ ሜርድ። አዎን መስየ ጋብሪዬል ስልኩን ዘጋችው እንዲህ ቀላል አልነበረም እንደ እውነቱ አንድ ደምበኛ ነበረ ደሞ ትታው ልትሔድም ትችል ነበር ሰውየው ሻርል ስለነበረቴ ሻርል ደሞ ትንሽ ገንዘብ ለመውሰድ ብሎ ካዝና ውስጥ የሚያነፈንፍ አይነት አይደለም ሀቀኛ ሰው ነው ሻርል። እኔ በበኩሌ ግድ የለኝም አለ ሻርል ዛሬስ እኔ ነኝ የማቀራርብልሽ አለ ቱራንዶ በጨዋነት ቂጧን መታ እያደረገ እንዲህ የማድረግ ልማድ አልነበረውም በስራ ሰአታት ካልሆነ በስተቀር ያውም የቤቱን ድባብ ሞቅ ለማድረግ ብቻ ሻርል አንድ ፈርኒጥብራንካ ለመውሰድ ይችላል አለች ማድሌን እሱስ ሰው የሚፈልገው መጠጥ አይደለም አለ ሻርል ቢሆንም በስድስት ሰአት አንዱን በሚገባ ጨልጠሀል ቱራንዶ አስተያየቱን ሰነዘረ እውነት ነው ደሞ እንግድያው ለኔ ቦዥሌ ወይን ይሁንልኝ ብርጭቆዋቸውን አጋጩ ዛሬ ህጋዊ ለሆነው የጨለማ መደባዊ ትግላችሁ አለ ቱራንዶ እናመሰግናለን መለሰ ሻርል አፉን በኮፍያው እየጠረገ እሱ ብቻም አይደል ሲል ቀጠለ ፄጄ ለማርሰሊን መንገር ይኖርብኛል አትድከም ጋሽዬዋ አለች ማድሌን እኔ ፄዳለሁ አገባህ አላገባህ ለማርሰሊን ምን ስሜት ይሰጣታል። አለች ዛዚ እንዲህማ ጉድ አታረገንም አለ ቱራንዶ ታወራለህ ታወራለህ አለች ላቬርድዩር ይህን ብቻ ነው ማድረግ ምታቀው እቺ አራዊትኮ እምትናገረውን ታውቃለች አለ አንዱ ሶዶማዋ አስተናጋጅ ክጉዳይ አትቁጠራቸው ጋቢ አለ ቱራንዶ እኛም እንደሌሎቹ ሰዎች ነን ብለህ አስብ አለች ዛዚ እኔን ደስ እንዲለኝ አሉ ባልቴትዋ ሙዋክ እየተቅለሰለሱ እርሶንማ አለ ጋብሪዬል እደብሮታሰሁ አይደለምገዷ ወዳጆቼ። ላያቸው አልፈልግም በህይወታችን ውስጥ ለሰዎች ከዚህ የበለጠ ሰብአዊነት ማሳየት ይገባናል ዛፓ ቢሆንምኮ አሉ ባልቴትዋ ሙዋክ ሁሉንም ሰምተው ስለነበረ ኮሮ ዞሮ ሰው ነው አንድ ዙር መጠጥ በኔ ይሁን አለ ትሩስካዮን እንደማፈር አያለ በጭራሽ አይሆንም አለ ጋብሪዬል ዛሬ ማታ አኔ ነኝ ማምበሸብሻችሁ አንዲት ትንሽ ዙር ብቻ አለ ትሩስካዮን በሚማፀን ድምፅ ሙስካዴ ወይን ለምሳሌ አቅሜ የሚፈቅደውን ያህል ጥሎሽህን አታባክን አለ ጋብሪዬል የኔ ጉዳይ ሌላ ነው ክዚህም ጋር አለ ቱራንዶ አንተ ምንም አትጋብዘንም። ታወራለህ ታወራለህ አለች ላቬርድዩር ይህን ብቻ ነው ማድረግ ምታውቀው ይሄ አለ ግሪዱ አዎን ማለት ነው እሷ ምትናገረውን ለማወቅ ምታስተምረኝ አንተ አይደለህም አለ ቱራንዶ በኩራት ያን ያህልስ አልንጠራራም አለ ግሪዱ መንጠራራቱ አልቀረም አሉ ባልቴትዋ ሙዋክ ነገሩን አታባብሱትንጂ አለ ጋብሪዬል ይገባሀል።