Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ደጃዝማቹም አዲሱ ባሪያም ትልቅ ሰው መሆኑን ያ የገዛው አረመኔ ዐወቀና መቼም ሥራው ካልጠቀመኝ ብሉ ገንዘብ ያተርፍበት ዘንድ ፈለገ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ይህ ነገር ከሆነ እርግጡን ከእርሱ ከጦቢያ ጠይቄ አባቱንም እርሱንም አንድነት ተፊቴ አርቃለሁ መቅጣት ግን ገና ካገኘሏቸው ዕለት ጀምሮ ብልኅቱን ሳያስታውቅ ትልቅ ዓመት በዓል አለብኝ እያለ ያሳላ ጠጁን ያስጥል ጠላውን ያስጠምቅ ናሪዳውን ያሰበስብ ሁለንተናውን ያሰናዳ ጀመር ደግሞ ሌት ሌቱን በስውር ትልቅ የገዳም መምህር እየመጣ የዛፃይማኖትን ነገር የጌታችን መውረድና መወለድ መሞቱንም ያስተምረው ጀመር የአጎቱንም ልጅ በጦቢያ አስመስሎ ከዋሕድ ለማጋባት የወደድሽውን ጦቢያን እንዳጋባሽ ክርስቲያን ሁፒ እኔም የክርስቲያን ወገን ለማግባት ክርስቲያን መሆኔ ነው ብሎ ነግሮአት አብራው ትማራለች ንጉሥም ያቺም ያጎቱ ልጅ የክርስቶስ ዛሃይማኖትትምህርት ገባቸው ከዚህ ወዲያ ንጉሥሙ ውስጥ ለውስጥ በየመሣሪያው ሁሉ ላይ መስቀል ያለበት ሰንደቅ ዓላማ አስተከለና የጥንቱን ከእሳት አስጨመረው ወዲያው ጎሕ እንደቀደደ ወፍ ጭው ጭው ማለት ሲጀምር ከአደባባዩ ላይ የአዋጅ ነጋሪት ወጣና በግራና በቀኝ መስቀል የተለጠፈበት ዓላማ በንፋስ ሲውለበለብ ነጋሪቱ ይደበደብ ጀመር።ጸ አሁን ግን ክርስቶስ ልብ ሰጠኝ ከድንቁርና አወጣኝ የእውነተኛውን ፈጣሪ እንዳውቅ አደረገኝ የእውነተኛው ሃይማኖት የክርስቶስ ወገን መሆን ነውና የእኔ ህይማኖት ነው ዕወቀው። አረቄው ቀረበ ፍሪዳው ሙክቱ ተጣለ ብርሌው ብርጭቆው ተለቀለቀና ተደረደረ ሁለንተናው ግጥም ብሎ ተሳላ። ነገር ግን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በሰይፍ ሥራ ገብቷል ኢምንት የሌለ እህልገብ በአህል ፈንታ የሚበላ ቅጠላቅጠል ወይም የሣር ፍሬ ሊሆን ይችላል ከ ከለቻ እንደ ቡሽ ባርኔጣ ያለ የቀድሞ ወታደሮች የራስ ቁር ኩራቢ መደረቢያ ያንገት ልብስ ካፊር ባረብኛ ከሐዲ ማለት ነው ክስል እንደከሰል ጥቁር ኮለኮለ ርካብ ረግጦ ፈረስን ወይም በቅሎን መኮርኮር ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር።
አሁንም ወደ ዘመዶችህ ላክና አልፍ ወቄት ወርቅ አስመጥተህ ስጠኝና አገርህ እንድትሄድ እአለቅሃለሁ ብሎ ነገረውፅ ያ ደጃዝማች ግን እንኳን አገሩ ጠፍቶ ንጉጮ ሙቶ ከብቱ ተዘርፎ በሬው ላሙ ተነድቶ ይቅርና ይኽም ባይሆን ታገሩ በጌትነቱ ሳለ ለጀግና መስጠት ለድኃ መርጠብ ለተራበ ማብላት ለታረዘ ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር ማልበስ እንጂ ገንዘቡን ወደ ኋላ ማድረግ ለነገ ማለት አያውቅም ነበርና የምከፍለውም የለኝ ድኃ ነኝ እንደ ወደድህ አድርገኝ ብሎ መለሰለት የዚሁ ደጃዝማች ሎሌዎች ሁሉ አብረውት ሲዋጉ ከዚያው ከፊቱ አልቀዋል ንጉሥም ሙቷል አንድ ደጋፊ አንድ ተስፋ ታገሩ አልነበረም ብቻ ተቤቱ ሚስቱና መንታ የተወለዱ አንድ ወንድን አንድ ሴት ልጆች ነበሩትፊ እነዚሁ ልጆች በዚያን ጊዜ አስራ ስድስት ዓመት ሆኗቸው ነበርሖ ታለባበሳቸው በቀር ወንዱም ገና ጢም አላቀነቀነም ነበርና ምንም የሚለያዩበት ነገር አልነበረም ለልጆቹና ለሚስቱ ፊት አርሱን ሞተ ብለው አረድዋቸው አርሱ ግን ምርኮኛ ነው የነበር ኋላም ታንዱ ወዳንዱ ሲል ይኸው አባታቸው ተሸጦ ኖሮ ያው የገዛው አረመኔ እልፍ ወቄት ወርቅ አምጣና ልልቀቅህ አለው ሲባል ወሬው ደረሰላቸው ምንም ባለመሞቱ ደስ ቢላቸው ወዲህም እንደባሪያ በመሸጡ ወዲህም ሰጥተው የሚያስለቅቁበት ገንዘብ በማጣታቸው እንደገና ይላቀሱ ጀመር ንጉሥ ሙቶ አገር ጠፍቶ እነርሱ ለራሳቸው ደኽይተው ከወዴት ገንዘብ ይገኝ። ዋሕድ ግን ያላሰበውን ሲሳይ ድንገት በማግኘቱ አጅግ ደስ አለውና እንኳን የዚያን የለጋስ ስምና አገር ለመጠየቅ እግዚአብሔር ይስጥህ ለማለት አላደረሰውም አንዲያው ወደ ቤቱ ከነፈ ነገር ግን ከዚያ ለጋሥ ሰው ፊት የተቀበለውን ለማየትና ለመቁጠር አፍሮ አላየውም ነበርና ወዲያው እንደተለያዩ አንድ የሚሸሸግበት ቁጥቋጦ መሳይ ባየ ጊዜ ዋሕድ የከረጢቱን ወርቅ ቶሎ ከሸማው ላይ ዘረገፈና ቢቆጥር ጓጣ ወቄት አገኘበትጹ በዚህ ጊዜ ይልቁንም በደስታው ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር ላይ ደስታ ተጨመረለትና እየፈነደቀ ሲሮጥ ከቤቱ ገባና ለናቱና ለአኅቱ ወርቁን ሆጭ አደረገላቸው ነገሩንም ነገራቸው አናቱም እኅቱም ነገሩን ሰምተው የነጋዴውን ደግነትና የተሸጠውን ሰዋቸውንም መለቀቅ ባሰቡ ጊዜ በደስታም ይሁን በሀዘን በንባ ይታነቁ ጀመር ሀብታሙ ነጋዴ ጥንቱንም ዋሕድን በቅሎዬን ጫንልኝና ተከተለኝ ማለቱ ድንገት የሚረጥቡት ሰው እንደሆነ ለመርጠብ ምክንያት እንዲሆነው ለተቀባዩም ሳያገለግል አለሰበብ መቀበሉ ውርደት እንዳይሆንበት ብሎ ነበር ሁሉም ይኸው የተገኘው ገንዘብ ያ አረመኔ ለመልቀቂያ አምጣ ታለው ወርቅ አይደርስምና በጎደለው ለመሙላት እናቲቱም ጦቢያም ዋሕድም እንደፊተኛው እያሳባቸው ገቡ። ምን ያድርግ ዋሕድ ፍርዱ ነው ደግሞም ገና ጮርቃ ልጅ ነው ዋሕድ ይኸ ሁሉ ሲሆን ያንን መደብር ያየበትን አንጣር ይዞ ቀስ በቀስ አያለ መጓዙን አልተወምፈ አንድ ጊዜ ግን በጨለማው አሻግሮ አንድ ቁጥቋጦ አየና አራት አግር ያለው የውነተኛው አንበሳ መሰለውና ነፍስና ስጋው ተለያየበት ጉልበቱ እየተብረከረከ ትክ ብሎ ሲያየው ጊዜ ያው በፍርሀት የተፈጠረ አንበሳ የሚንቀሳቀስ ዘሎም ሊይዘው ልበልን ልተው የሜል መሰለው በዚህን ጊዜ ዋሕድ ብልኅት ያገኘ መስሉሎት ለዚያ አንበሳ ብዙ ሰው ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር የመጣበት እንዲመስለው ብሎ ድምጡን ባስራ አምስት አይነት እያረገ አንድ ጊዜ ቀጭን አንድ ጊዜ ጎርናና እያደረገ አንዳንድ መንጋ ሰው እየጮኸ ክበብ አያምልጥህ አይኮዞህ በዚያ አለፍ እያለ ድምጡን አንዱን በአንዱ ላይ እያነባበረ ይጪሟህ ገባ ዋሕድ ግን ብቻውን አንድ ፍጥሩን ነበር ከጨለማው ጋር እየተደባለቀ ይሳከር ተነበረው ተገዛ ጥላው በቀር የዚያን ጊዜ ምንም ባልንጀራ አብሮት አልነበረም ያ በከንቱ የታማ ቁጥቋጦ ምንም ባልንጀራ በአንበሳ ስም ቢጠራ ነፍስ የለውምና አልሸሽለት ሲል ጊዜ ዋሕድ መንገድ ሰብሮ ይሄድ ጀመር ዙሮ ባየው ጊዜ ግን ያው በገዛ ፍርሀቱ የፈጠረው የቁጥቋጦ አንበሳ የሚከተለው መሰለው ዋሕድ ሆዬ ጉልበቱም በፍርሀት እየተብረከረከበት መፄድ ተሣነው ከዛፍ ላይ ወጥቶም እንዳያመልጥ ከዚያ ምድረ በዳ እንዳጋጣሚ ሁሉ እንኳን ትልቅ ዛፍ የምጣድ መሰቅሰቂያ የሚሆን እንጨትም አልነበረም ተዚህማ ወዲያ ዋሕድ ተጨነቀ ፍርሀቱም እያደረ ነገሠበት የሚያየውም ጥቁር ነገር ሁሉ አውሬ ብቻ መሰለው ከፍና ዝቅ እያለ በዳባቱ እያየ መንገዱን እየለወጠ ሲፄድ በግራው አንድ ትንሽ ዋሻ መሳይ ደርሶ ገች አለበትና የዋሕድ መብረክረክ ባሰ በድንጋጤ ቀጭን ላብ መጣና በገላውም በፊቱም ተሰራጨበት ታንዱ አንበሳ ባመልጥ ከሁለተኛው ደግሜ ደረስሁ አሁንስ ቁርጥ ነው አላመልጥም እያለ ዋሕድ ይጨነቅ ጀመር ቁሞ እንደ ቄጠማ እያረገረገ ድምጡን እንደፊተኛው በያይነቱ ከፍና ዝቅ እያደረገ በውኃ ጥማት የከረረው ጉሮሮው አስቲነቃና እስቲሰነጠቅ ድረስ ክበብ አያምልጥህ እያለ ይጮህ ጀመር። ነገር ግን ሲያየው ጊዜ ምንም አይሸሽለትምፁ የናቀው መሰለውና እንደገና አጥብቆ ተንጠራርቶ ሲጮህ ጊዜ ያው ነው ኋላ ግን ድምጡም ሰለለበት ጉሮሮውም የባሰውን ተዘጋበትፅ ከዚያ ታስራ አምስት ዓይነት ድምጡ አንዱንም ዓይነት ለመጮህ ቸገረው ያው የውሸት አንበሳም ንቆት ዝም ያለው መሰለው ዋሕድ ከዚህ በኋላ መጠርጠር ጀመረ ድንገት ሌላ ነፍስ የሌለው ጥቁር ነገር ይሆናል ማለት ጀመረፁ ቀጥሎም በውል ለማስተዋል በጉልበቱ ተንበረከከና ትክ ብሎ ከአሁን አሁን ይንቀሳቀስ ይሆን እያለ ሲመለከት እንደገናም ጥቂት ጥቂት የሚንቀሳቀስ ይሆን እያለ ሲመለከት ጥቂት ጥቂት የሚንቀሳቀስ መሰለው ዓይኑን ሳያጥፍ አተኩሮ እንደገና ባስተዋለ ጊዜ ይልቁንም ከመንቀሳቀሱ ወደ አርሱ መራመድ የጀመረ መሰለው አተኩሮ ከማየቱ የተነሳ በዓይኑ እንባ ሞላበት ዋሕድ ግን ጊዜ ያጠፋሁ መስሎት አንባውን መጥመቅ ትቶ ባየ ጊዜ ይልቁንም ያው እንባው እያደናገረው የዚያን አውሬ ርምጃ ወደ አርሱ የተፋጠነ አስመሰለው በመጨረሻ ግን ዋሕድ ዓይኑን ከዚያው አውሬ ላይ እንደተከለ ባባና ተተንበረከከበት ጠጠር ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር አፍሶ ወደፊቱ ብትን አደረገ ለመከራ አጋዥ አይታጣምና ዋሕድ ላደረገው ሁሉ ነገር ምስክር ሆና ተሸሸጋ ስታይ የነበረች አንድ ድርጭት ተተሸሸግሁበት ተገለጥሁ ብላም እንደሆነ አይታወቅ ሳር ቅጠሉን በክንፏ አስሸብራ ተነስታ በረረች ዋሕድም ያው አውሬ ደርሶ አነቀኝ መስሎት ትንፋሹን አቋርጦ እንደሞተ ታለበት ተንዘራጋና መንቀሳቀሱም ቀረቆ ቆይቶ ቆይቶ ግን ነፍሴ አለች ወይስ ሙቻለሁ ብሎ አሰበ ቀጥሉም በአውሬው መነከሱንና አለመነከሱን ለማወቅና ለመረዳት በጆሮው ቢያንቋቋም ምንም አልሰማህ አለውኙ ዓይኑን ግን አውሬ ሲነክሰው ጨክኖ ማየቱን ቢፈራ ጨፍኖት ነበርና ሲፈራ ሲቸገር ገርበብ አድርጎ ቢያይ ተፊቱ አንኳን አንበሳ ምንም ጥንቸል አልነበረም ዋሕድ ከዚያ ወዲያ ነፍስ አጋባና ጫን ተንፍሶ ተነሳ አሻግሮ ባየ ጊዜ ያ አውሬ ጥንት ተነበረበቱ አይንቀሳቀስ ምን አይል ዝም ብሎ አየው ዋሕድ ከዚያ ወዲህ ትልቅ አሳብ ገባውና ወይስ ምንም አውሬ አልመጣም ኑሯራል ወይስ አውሬም አይደል ኑራል። ሳልደርስ አልቀርም ብሏልና ከፎከረበት የነጋዴ ሠፈር ለመድረስ በዚያ ጥቅጥቅ ድንጉር ጨለማ ቁልቁለቱን በእጅና በእግሩ እየተተማተመ በቅምጡ ሲንኳተት በንብርኩም ሲድህ አንዳንድ ጊዜም አልሆንለት ሲል ፊቱን ወደመጣበት አዙሮ አግሩን ወደሚሄድበት አስረዝሞ ማጭድ አረስቶ እንደመጣ ለጓሚ በጁ ሣር ቅጠሉን አእየጨበጠና አየሟጠጠ አየጓጠጠም እሾም አይቀረው እንደ ሐር ጎፍላ እአየጨባበጠ በደረቱ ሲሳብ ሲጋፍና ሲጎተት ተወራጁ ወንዝ ደረሰ ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር ያ ወራጅ ውኃ ለዋሕድ ጥሩም ይሁን ድፍርስ አልታወቀውም ገና በጥማት ልሳኑ ታስሮ ነበርና ተጎንብሶ እንደ ገልዳ ጠጅና አንደ ገፈታማ ጠላ ለስም ያህል ተላይ ያሰፈፈውን አረንጓዴና ስልባቦት እፍ አፍ እያለ በትንፋሹ ገፈፈና የተቻለውን ያህል አንስቶ ጥማቱ እንዳለፈ ተመስገን ጌታዬ አለና ተሹል ደንጊያ ላይ ቁጭ ብሉ የመሻገሪያውን መልካ ያይ ጀመር ቢመለከት ሁሉም ጥልቅ መሰለውፁ ቋሚ ይሁን ጠሊቅ ውኃው አልታወቅ አለው መሻገሪያውም በላይ ይሁን በታች አልታወቅህ አለው ዝም ብሎ እንዳይገባ ዋሕድ የዋና ነገር አያውቅም ነበረና ፈራ ይልቁንም ያ ወንዝ ፏፏቴ አልነበረውም ዝም ያለ ወራጅ ውኃ ሙሉ ነው ሲሉት ሰምቶ ነበርና ፈራ ምን ላድርግ እያለ ገና በልቡ ሲያመናምን እንዳጋጣሚ አንደእርሱ ውኃ ጥም የተባሰች በቅሎ ከመደብር ችካሏን ነቅላ አምልጣ ደረሰች ዋሕድ አውሬን ይሆን ብሎ ሲደናገጥ አፍንጫዋንና ከንፈራን ስታማታ በቅሎነቷን አውቆ ሲረጋጋ ያችው በቅሎ ገስግሳ ከውኃው እስተንቢያዋ ገብታ ተነክራ ተዚያ ውኃ ትግፍለት ጀመር በዚህ ጊዜ ዋሕድ በዚያች በቅሎ ምክንያት የውኃውን ግልብነትና ቁምነት አውቆ አስረገጠና ቶሎ በቅሎዩቱ ጠጥታ የጠገበች እንደሆነ አትያዘኝም ታመልጠኛለ ሲል ወደ በቅሎዩቱ አንጣር አድርጎ ውኃውን በዘንጉ እየለካ ተሻገረና ተማዶው ደረሰ የዚያን ጊዜ በቅሎዩቱ አንድ አፍታ ተዚያው ውኃ ግፋለት አንገቷን አቅንታ ጆሮዋን እያርገበገበች ለሁለተኛው ገና ልበልን ልተው ይብቃኝ አይብቃኝ ስትል ዋሕድ ቶሎ ብሎ አንቺ እንቺ አያለ እያባባለ ቀረበና ያዛት እርሷም ገራም ነበረች ትራገጥ መስሎት አስቀድሞ በአጁ ይዳስሳት ጀመር በቅሎዩዬቱ ግን መድከሙን አውቃ ይረፍብኝ ብላ ያዘነች መስላ ዝም አለችው መገረሟን አስረገጠና ዋሕድ ወደ ትልቅ ደንጊያ ስቦ አቀረበና ተቀመጠባት ቀጥሎም ወደ መጣችበትም ወገን አቃንቶ እንግዲህ ወደ ሠፈርሽ ውሰጅኝ አለና አሳቡን እርስዋ ላይ ጣለው በቅሎዩቱም ዋሕድ የሚለው ነገር እንደገባት ሁሉ የመደብሩን መንገድ ይዛ ሳትነቀንቅ ይዛው ትጓዝ ጀመር ብቻ አንዳንድ ጊዜ ለምለም ሣር ባየች ጊዜ ቆማ ትነቻቸፍና አርሷ በጠዳት ጊዜ እንደገና ተባልንጀሮቿ ለመደባለቅ መንገዱን ትይዛለችር ዋሕድ ግን ቀስ አድርጎ እንዳይወድቅ ብቻ ጋማዋን ተመጨበጥ በቀር አልኩለኩላትም ሂጂ መጭ አላላትም እንዲያው እርስዋ አንዳለች ተዋት ስለምን አርሷ በፈቃዲ ነውና የተያዘችለት መጭ እያለ በግሩ መጎሳሰም ወረታዋን ማጥፋት መሰለው አሁንስ ቢሆን የማን እንግዳ በተቀባይ ቤት ገብቶ ያዝዛል። ያን እያዩ አባትና ልጁ እንደገና አዘንና ድንጋጤ ገባባቸው ተስፋቸው እንደገና ተባነነ እንደገና ወደ አምላክ ይማለሉ ይሳሉ ጀመር አጀቡ ግን አያደር ይቀርብ ጀመር ነጋሪቱና ቀንደ መለኸቱ ከነፋሱ ጋር እየተሳከረ ይሰማቸው ጀመር በውል ወጀቡ በቀረበ ጊዜ የፈረሱ የበቅሎ መጣምር በነቻው የሰውም ጌጥ ከለቻው ራስ ወርቁ ወርቅ ኩፍታ አቁዳማ ቢተዋው አንፋሮው ወርቅ ለምዱ ጫሜው ጣፋው አንዲህ እንዲህ ያለው ጌጥ ከፀሐዩ ጋር እየተሳደበ ላይን ይገለምጥ ጀመር ከእዚያ ከሁለት ከተከፈለው አጀብ መካከል ጥቂት ፈንጠር ብሉ ጥቂት ሰው ይታይ ጀመር ንጉሥ ግራና ቀኝ ባለወርቅ ዝምዝም ባለወርቅ ጉብጉብ አጫዋች ሀር ጥላ ተይዞለት ከእርሱ አካል ይልቅ ወርቁ በከበዳት በቅሎ ተቀምጦ ከጥቂት ባለሟሎቹ ጋር እየተጫወተ ይጓዝ ነበር በዚህ መካከል ፀሐይ እንደ መቆልቆል ብላ ነበርና ያ እአየተቸነነ ይመጣ የነበረ አጀብ አንደተቆጡት ባንድ ጊዜ ቀጥ አለና ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር ቆመ ያ ይጎሰም የነበረ ነጋሪትና ይክላላ የነበረ መለኸት የጉዞውን ድምጥ ትቶ የሠፈሩን ምልክት ይመታ ጀመር ቀጥሎም ከፍ ታለው ሥፍራ ንጣቱ ከበረዶ የበለጠ አንድ አጅባር ድንኳን ፍንትው አለና ተተከለ ከዚያ እየተከታተለ ሌላውም ሁሉ ይተከል ጀመር። ይሉ ጀመር ወደ ቀትሩ ሠፈር ተጀመረፊፅ እንደ ልማዱ ከፍ ታለ ዲብ ላይ የንጉሥ ድንኳን ፊጥ ባለ ጊዜ ከመቅፅበተ ዓይን ዙሪያውን ሁሉ ድንኳን ብቻ ሆነ ወራሪውም ተግራ ተቀኙ የገደለ የማረከውን እየማረከ እያቅራራ እየዘፈነ እየተጅመለመለ ሆ ሆ እያለ የደም ሸማውን በፈረሱ አንገት እያሰረ ያመጣ ጀመር ንጉሠ በዚህ ጊዜ ካደባባዩ አፋፍ ላይ ባለ ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጦ ዙሪያውን ትልልቅ ሹማምንት ተቀምጠው በግራና በቀኝ ዐምድ ዐምድ የሚያካክል ሰይፈ ጃግሬ ሻንቅላ የዝፕን አንገት አንደዝፃ የሚቆርጥ የመሰለ ሰይፉን አየመለጠ ቁሞ ነበር ከዚህ ቀደም ሲል ባለ ጫሜ ባለቢተዋ ባለአንበሳ ባለግስላ ሽልሜ ሁሉ ተገርግር ቀኝ ቀኝ አጁን ተመክዱ ታውራሪሱ ላይ ጣል እያደረገ ቆሞ ነበር ከዚህ ቀጥሎ ግራና ቀኝ በውቅ የተመረጠ ደንደሳም ደንደሳም በገዛ ጡጫው ዝዣፕን ተመሬት የሚደባልቅ የመሳሰለ አምስት ሺ ዘበኛ ተገጥግጦ ቆሟል ከዚህ ሁሉ ሰው አንድ ትንፋሽ አይሰማምጵኹ ንጉ ሳይቀር ዝም ብሎ ግዳይ ጣን ይጠብቃል ያ ሁሉ ሽልሜ ያ ሁሉ ጀግና ዝምታ ታክሎበት እንደሳት የሚገላምጥ ስጋጃና ወላንሳ በፊቱ ተለጥልጦበት ግራና ቀኙ ኑግ ልጥልጥ የመሳሰለ ሻንቅላ የተሳለ ሰይፍን አየመዘዘ ቆሞበት በመካከሉ ከጠይምነቱ በቀር ቅዱስ ሚካኤልን የመሰለ ወዘላ ህፃን ንጉሥ በረጅም ወርቅ ወንበር ተደላድሎ ተቀምጦ ጦቢያና አባቷ ይህን ግርማ ይኽን ዝምታ ባዩ ጊዜ አመ ይመጽእን እንጂ ሌላም አልመሰላቸውም ነበር ሁሉ እንዲህ አምሮ ተተሰናዳ በኋላ ግዳይ ጣይ ተጠራና በየተራው እየደነፋና እየፎከረ ግዳይ ይጥል ጀመርዙኹ ንጉሥም ደስ ደስ እያለውና ጥርሱን ፍግግ ፍግግ እያደረገ ይቀበል ጀመር ጦቢያ ግን ይኽን ሁሉ ዓለም ይኽን ሁሉ ደስታ ባየች ጊዜ የሰውን ማለቅ ያገሩን መጥፋት የክርሰቲያኑን ዘር መጠቃት ያረመኔውን ዘር መልማት እያሰበች አንገቷን ወደ አባቷ ጎን ሸሸግ አድርጋ አዩኝ አላዩኝ እያለች ታለቅሳለችፎ ንጉሥ በሩቁ ሐዘኗን ዐወቀባትጵ ያንዱ መከራ ላንዱ ደስታ መሆኑን አሰበና ወዲያ ምንም ነገሩን ባያስታውቅ ግዳይ ጣዩን አቋርጦ ትቶ ወደ ድንኳኑ ገባ የንጉሥ ድንኳኖች ዋኖቹ አምስት ነበሩ የንጉሥ አባቱም እናቱም ልጅ ሳለ ስለሞቱበት አንዳባትና እንደ እናት ሆኖ ያሳደገው አጎቱ ነው አጎቱ አንድ ልጅ ነበረችው ለንጉሥ እኅት ይሉ ወንድም አልነበረውምና ይህችን ያጎቱን ልጅ እጅግ አድርጎ ይወዳታል። ብሎ ጠየቃቸው መቼም የጨዋ ልጅ ንግግር አይጠፋውምና የጦቢያ አባት ቶሉ ብሎ ጌታዬ ከአርስዎ ፊት በቀር የሌላ ንጉሥ ፊት ልናይ አንፈልግም አለና መለሰ ንጉሥም እንዳወቁት ገባውና አንግዲያውስ ከእኔ በስተቀር ሌላ ሰው ካልወደዳችሁ አፄም አልጥላችሁም እመኑኝ አለና ወደ ግብር ሄደ የእርሱ ንጉሥነት ላባትና ልጁ ተተገለጠላቸው ዘግይቷል ለንጉሠ ግን የጦቢያ ሴትነት ይገለጥለት ዘንድ ገና ነበረ በማግሥቱ ከወሬሳ የደከመው ሰው ከብቱም አንዲያርፍ ውሎ ሆነ ንጉሥም በማግሥቱ የሚያደርገውን ሲያስብ ዋለ ተሁሉም የሚታሰበው ትላንትናውን ተቀምጦ ግዳይ ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር ሲቀበል ጦቢያ የሰውን እልቂትና የአገሩን ጥፋት እያሰበች ያለቀሰችበት ጉዳይ ነው ከዚህም ነገር የተነሣ ሰዉ በከንቱ አእንዳያልቅና አገሩ በከንቱ እንዳይጠፋ አዋጅ ሊነገር አሰበ ሀ የአዋጁ አነጋገር እንደሚከተለው ነው በፊት አዋጅ ነጋሪው ካደባባይ ወጥቶ ከፍ ታለ ደንጊያ ላይ ቆሞ እንዲህ እያለ ሦስት ጊዜ ይጮፃል። ጉዞውም ከዚህ እለት ጀምሮ ቀረ ከዚያው ከተሠፈረበት ላይ ዋና ትልቅ ከተማ ተቆረቆረፁ አንድ ላይ ተመቀመጥ የተነሣ በግድም በውድም ንጉሥ ጧትና ማታ ጦቢያን እስታባቷ ያያቸው ነበርና ከቀን ብዛት ውቃቢው ጦቢያን እጅግ ወደዳት እርሷም ጉዞው ቀርቶ የቀን ፀሀይ የሌት አመዳይ ሲቀርላት ጊዜ በእንባ የታረሰው መልታሕትዋ እያማረ በርኅብና በጥም የተጎዳው ገላዋ እየተመለሰ ሄደ ምንም አርሷ እያፈረች ሴትነቷ እንዳይታወቅባት ራቅ ብትል ንጉሥ ይልቁንም ያፈቅራትና ያቀርባት ጀመር አባትየው ግን ንጉሥ እያደር ሲያቀርባት ባየ ጊዜ የልጁ የጦቢያው ሴትነት አእንዳይገለጥባት ተጨነቀ አይዞሽ እንዳይገለጥብሽ አረማመድሽንም አነጋገርሽንም እንደ ወንድ አድርጊ እያለ ይመክራት ነበር ነገር ግን ልብስዋ ፈፅሞ እንደ ወንድ ነበርና የሴትነቷን ነገር ማንም አልጠረጠረም ብቻ እንኳን ንጉሥ ሌላው ያያት ሰው ሁሉ በመልኳ ይወዳት ጀመር አውነትም ጦቢያ እጅግ የተዋበች እጅግ የተደነቀች ላያት ሁሉ የምታነሆልልና የምታዘነጋ ነበረች ዓይንዋ አስቀድሞ የብር አሎሎ መስሎ ካጥቢያ ኮከብ ጋር የተፎካከሩ ነበር። እኔ ከዚህ ልጄ ጋር ከቤቴ ተወጣሁ ብዙ ጊዜዬ ነውጺ አንዱ ልጄ አንድ ትልቅ ውለታ የዋለልን ሰው ያለበትን ስፍራ ለመፈለግ ከቤቱ ከወጣ ይኸው ዓመት ሆነው አኛም ወሬውን ብንጠይቅና ብናስጠይቅ የደረሰበቱን ደብዛውን አጣነው አሁን የምናደርገውን ብናጣ አገር ለአገር እየዞርን እርሱን ለመፈለግ ሁለታችን ወጣን በመፈለግ ላይ ሳለን የእርሶ ሠራዊት አገር እያጠፋ መጣ ደረሰ ሲሉ በሰማን ጊዜ መጀመሪያ ወደኋላችን ለመሸሽ አሰብን ቀጥለንም እንዳላደረሰን ብናይ ፈረስ ተማይመታው ኮረብታ መውጣት ይሻለናል ብለን ወጣን ነገር ግን መቼም ያጋጣሚ ነገር አይታወቅምና ንጉሥ ራስዎ አገኙን ከዚህ የደረስንበት ጉዳይ ይኽ ነው አለና ሲጨርስ የጦቢያን ሴትነት ገልጦ ሊናገር ይቺ ብሎ ገና እንደጀመረ ጦቢያ አፍዋን በእጅዋ እየተመተመች እንዳይናገር ተቆጣችውና ንግግሩን ለውጦ ይህች ዓለም ላልታደላት ሰው ከንቱ ናት እኛም ይኽው በልጄ መጥፋት ማልቀስ ከጀመርን አንድ ዓመት ሆነን ስለዚህ ይኽ ልጄ ወዲህም ከእናቱ ተለይቶ ወዲህም የሚወደው ወንድሙ ጠፍቶበት በሐዘን ሳለ ከዚህ ቤተ መንግሥት ገና ደስ ይለኛል ብሎ ለራሱ አድልቶ ይቀመጥ ዘንድ ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር አይቻለውም አለና ተናገረ ጦቢያ ግን ሴትነቷን ገልጦ እንዳይናገር መከልከሏ አሕዛቦች ሴት አይተው አይለቁም ሲሉ ሰምታለችና ለዘለዓለሙ ከዚያው ይዞ እንዳያስቀራት ፈርታ ነው ባንድ ወገንም ሁሉን ቢናገሩ ሆድ ባዶውን ይቀራል እንደሚሉት ምስጥሩን ሁሉ ጨርሶ አንዳይዘረግና ብላ ነው አትናገር ያለችው ንጉሥ የጦቢያን ወንድም መጥፋት በሰማ ጊዜ ምን ጊዜ ነው የጠፋው። ብሎ ጠየቀ እነርሱም እሺ ንጉሥ እንዳሉን እንሆናለን አሉ ንጉሥ እንዳመኑት ባየ ጊዜ ደስ አለውና ወዲያው አባትና ልጅ እንዳይለያዩ አድርጎ የሚበቃቸውን ድንኳን የሚጭኑትን ፈረስና በቅሎ የሚያዝዙትን አሽከሩን ባሪያውን ለጓሚውን ጫኙን ወጥ ቤቱን የሚለግሥትን ብሩን ወርቁን አድርጎ በአንድ ጊዜ ንብረታቸውን አሟልቶ ሰጠና ከእርሱ አጠገብ ከሸማው አጥር ውስጥ ድንኳናቸው እንዲተከል አደረገ ከዚህ ቀጥሉ ፊት እንደተናገረው ጦቢያን እንደ ባለሟሎቹ ሸልሞ ወደ እልፍኝ አስገባ አባትዬውንም እንደ መኳንንቱ አንቆጥቁጦ ሸልሞ በጨዋ ልጅ ሥፍራ አስቀመጠ ይኽን ባደረገ በበነጋው ከአንድ ዓመት ወዲህ ወንድ ባሪያ የገዛህ አንድ የጠፋኝ ሰው አለና ሰብስበህ ወደ እኔ አምጣ ይኽን ቃል በሰማህ ጊዜ አለቱን ይዘህ ወደ እኔ ተነሣቆ ያን የምፈልገውን ሰው ይዘህ የመጣህ ሰው ይዘህ የመጣህበትን ዋጋ አሥር እአጣፍ አድርጌ ሰጥቼ ወዲያው ሸልሜ አሰድፃለሁ አለና በያገሩ በያደባባዩ በየሸንጎው በየጣቢያው ሁሉ አዋጁን ለቀቀ ከዚህ አዋጅ ወዲያ የሚገዛው አገር እጅግ ሰፊ ስለሆነ አንድ አምስት ስድስት ወራት ያህል አንድም ባሪያ ይዞ የመጣ ሰው አልነበረም ይኽን ሁሉ ቀን ጦቢያና አባቷ ዝም ብለው ከንጉሥ ጋር ተቀመጡ ከቀን ብዛት የተነሣ ንጉሥ ጦቢያን አጥብቆ ወደዳት እንደብርቅ ያያት ጀመር ከጥንት ባለሟሎቹ አንድም እንደእርሷ አድርጎ የሚያቀርበው የለውም ነበርፁ ደግሞም ተመልኳ ጠባይዋ ከንግግራ ውበቷ እየተባበረ ጦቢያ የሰው ልብ ታዘናጋ ነበር እንኳን ንጉሥ የንጉሥ አጎት አስተ ልጁ ከንጉሥ እልፍኝ አይለዩምና እያይዋት እጅግ ወደዲት አጅግም አቀረቧትፅ ይልቁንም ያች የንጉሥ አጎት ልጅ ሥራዋ አይኗን ከጦቢያ ላይ መሰካት ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር ብቻ ሆነ ወሬዋ ሁሉ የጦቢያ ነገር ብቻ ሆነ በዚህ ጊዜ ጦቢያን ያየችው የንጉሥ የአጎት ልጅ በጦቢያ ልቧ እንደተሰቀለና ፍቅር እንዳደረባት ዐወቀው ከዚህም ወዲያ ለአጎት ልጅ ገናው ባልሽ እንደዚህ እንደ ጦቢያው ቢያምር ትወጃለሽ። ብቻ ሆነ የባለሟል ሁሉ ንግግርሱ በቢሁ ብቻ ጧትም ማታም ተጉተምታሚውና ተጉረምራሚው በዛ ነገሩም አልቀረ ለንጉሥ አጎት ነገሩን አሳቅለው ነግረው ጦቢያ በመከራ ላይ እንድትወድቅ ወይም ከእልፍኝ እንዳትገባ ለማድረግ አሰቡ ፊት እንዳልሁት ሁሉ ከዚያው ቤተ መንግሥት እንደ ጥንግ የተንከበከበ አንገቱና ወገቡ በሥፍራ የተጣሉበት ድንክ ነበርና ከእርሱ ጋር እንዲህ ብለው መሰጠሩ ንጉ ከምሳ በላ ጥቂት እንቅልፍ ያሸልብ ነበርና እንደልማዱ እንቅልፍ ሲያሸልበው ያው ድንክ ጦቢያን የንጉሥ አጎት ልጅ ትጠራዛፃዛለች ብሎ ሊነግር በዚህን ጊዜ ጦቢያ አሺ ብላ ያች የንጉሠ አጎት ልጅ ካለችበት ድንኳን ስትገባ ላባትዬውና ለንጉሠ አጎት ፄዶ ጦቢያ የሚሉት ካፊር ከልጅቱ ድንኳን አለጊዜው ገብቶ ተቀምጧል የሚያደርገውን ነገር አናውቅም ብሉ ሊያሲዙ መከሩ በዚሁ ምክር ያ ድንክ አንዱን ቀን ንጉሥ እንደተኛ አይቶ ተፋጠነና የንጉሥ ዘመድ ቶሎ ና ትልፃለች አለና ለጦቢያ ነገራትር ጦቢያም በቅንነት እሺ ብላ ቶሎ ፄደች ደግሞም ይህን ሁላ ነገር አዙራ አላየችም ነበርፁ ነገር ግን ገና ከተጠራችበት ድንኳን ጥልቅ እንዳለች ያው የንጉሠ አጎት ነገሩን ሰምቶ ደረሰና ጦቢያ ተያዘች ወዲያውም ባለሟል የተባለ ሁሉ ወሬውን በቶሎ ለሁሉ አደረሰው ድሮ ያ ጦቢያ የሚባል አዲሱ ባለሟል ላቀንና የንጉሥን ዘመድ ብቻዋን ካለችበት ደፈራት ጭር ባለበትም ጊዜ አይቶ አደጋ ጣለባት ተባለ ንጉሥም ወዲያው ነገሩን ሰምቶ እውነት አልመስልህ አለው። ሰው ባልዋለበት ይሞት ዘንድ ዛሬ ብቻም አልተጀመረ አርስዎም ምንም ብልኅ ምንም መሐሪ ንጉሥ ቢሆኑ እንደ ሁሉ ሥጋ ለብሰዋልና በሰው ልብ ገብተው እውነቱንና ሐሰቱን ይለዩ ዘንድ አይቻለዎም ሰው የነገረዎትን እንደሚያምኑ የታወቀ ነው አሁንም ነገሩን ሁሉ ገልጩ ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር አነግርዎ ዘንድ ምሥጢሩ ከእኛ አንዳይወጣ ቃልዎን ይስጡኝ አለ ንጉሙም አሺ ብሎ ቃል ሰጠው ከዚህ ወዲያ የጦቢያ አባት ከመጀመሪያው አስከ መጨረሻው ምሥጢሩን ሁሉ ለነገ ሳይል የጦቢያንም ሴትነት ገልጦ ነገረው ንጉሥ ይህን በሰማ ጊዜ አጅግ አዘነ አጅግም ነገሩ ደነቀውፅ የጦቢያ ነገር ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አሳዘነው ወዲህም በወንድ ተመስላ መከራዋን እያየች ወንድሟን አገር ላገር መፈለጓ ወዲህም እነዚያ ባለሟሎቹ በምቀኝነት ባሏለችበት ነገር አሻኩረው ሊያስቀጧት እንደነበር ስታውቀው አለማሳጣቷ ገረመው ይኸው ንጉሥ ነገሩ ምንም ቢያሳዝነው ባንድ ወገን አጅግ በጦቢያ ሴትነት ደስ አለው ፍቅሩ ጥንት በውቃቢ ብቻ ሴትነቷን ሳያውቅ ነበር አሁን ግን ያው ፍቅሩ ወደ አውነተኛው ፍቅር ተለወጠና ተስፋው ሌላ ሆነ ድሮ በእርሷ ፍቅር ልቡ ተሸወጠና ደረቱን ይገምሰው ጀመር ፍቅር እንደ ቀጭን ብርድ በሁለንተናው ገባበትና ያንከፈክፈው ጀመር ነገር ግን አባትና ልጁ እንዳያውቁበት ተጠንቅቆ ይናገር ነበር እነዚያን ቅናተኞች ባለሟሎቹን ለመቅጣት ይወድድ ነበር ነገር ግን ምሥጢራቸው እንዳይወጣ ተነጋግረዋልና የማይሆን ሆነ ኋላ ግን ንጉሠ አሰበ አሰበና ለሰው ይምሰል ለቅጣት አስመስሎ ጦቢያ ዕለቱን የባለሟልነቷን ልብስ ለውጣ እንደ ጥንቷ ለብሳ ከእልፍኝ ልትወጣና ካባቷ ጋር በድንኳን ርቃ ልትሠፍር ወደደ ላባትና ልጁ ይኽን አሳብ ነገረና በምሥጢር አድርጎ ብዙ ወርቅ ብዙ ከብት ሰጠና ድንኳኑን ቤተሰቡን ጨምር ሂዱ በሩቁ ስፍራ ተቀመጠ አለና ስፍራውን አሳይቶ ጦቢያ ከድንኳን እአንዳትወጣና ሰው አንዳያያት አባትዬው ግን ከአደባባይ ተቀን አንድ ጊዜ ብቻ አንዲወጣ አድርጎ መካከረና ሰደዳቸው የሚሰፍሩበት ስፍራ ግን ከንጉሥ ድንኳን ፊት ለፊት ነበር ንጉሥ ባይሆን አንኳ በመነጠር ጧትና ማታ ጦቢያን ማየት ተስፋ መሰለው። ሦስቱም እየራሳቸው የናፍቆት ስስትና የደስታ ድንጋጤ ያዛቸውና ተፋዘዙ ንግግርም ተሳናቸው ሁሉም ዲዳ መሰሉ ይህ ሁሉ ሲሆን ዋሕድ ጦቢያን አላስተዋለም ነበር ጠጉርዋን ተቆርጣ እንደ ወንድ ለብሳ ለምዲን አጥልቃ ባያት ጊዜ ሌላ ሰው መስላው ነበር ኋላ ግን ነፍሳቸው ጥቂት እንደተመለሰ እየተላቀሱ መጠያየቅ ሲጀምሩ ነፍሳቸው ጥቂት እንደተመለሰ እየተላቀሱ መጠያየቅ ሲጀምሩ መቼም ንጉሥ ሁሉንም በመነጥሩ ይመለከት ነበርና ያ የጠፋው ሰው መገኘቱን አወቀ ወዲያውም ያው የተገኘው ልጅና እርሱኑ ያመጣው ሰው ወደ አርሱ እንዲመጡ አዘዘኮ ንጉሥሙ ዋሕድን ባየ ጊዜ ደስታ ፈነቀለው አውነትም የጦቢያን ቁርበት ገፎ የለበሰውን እንጂ ሌላም አይመስል ነበር ጦቢያን ባለሟል ሳለች ያወቃት ሁሉ እንደገና ንጉሥሙ ምራት አርሷው ራሷ የመጣች መሰለው እንጂ ሌላም አይመስል ነበር ጥቂት ዋሕድና ጦቢያ የሚለያዩበት በአተያይ በአነጋገርና በንቃት ብቻ ነበር ጦቢያ ምንም ልሸሽግ ብትለው ነገሯ ሁሉ ወደ ሴትነቷ ያደላባት ነበር ንጉሥ ለሰው ባያስታውቅ ነው እንጂ ደስ ብሎት አንግዲህ ለአህቴ ባል አገኘሁላት መቼም እርሷ ሌላ መሆኑን አትለየውም ያው የወደድሁት ጦቢያ ተመለሰልኝ ብላ ነው ደስ የሚላት እያለ በሆዱ ያሰናዳ ነበር ወዲያው ንጉሠ ዋሕድን ላመጣው ነጋዴ እስታነሳው ድረስ ወርቅና ብር ሰጥቶ ሸልሞ አሰናበተ ዋሕድን ግን አሳድግፃለሁ አስመችቼ አኖርዛለሁ ከእኔ ጋር ኑር አለው ዋሕድም በበኩሉ ተጨንቆ ንጉሥ ሆይ አንድ ትልቅ ውለታ የዋለልኝ ነጋዴ ጠፍቶኝ አርሱን ካላገኘሁ አርፌ አእንዳልቀመጥ ምዬ ከቤቴ ወጣሁ ይኸውና አርሱን ስፈልግ ብዙ መከራ አገኘኝ ቀጥሉም ባሪያ ሆጌ ተሸጥሁ አሁን እርስዎ ባያወጡኝ ከዚያው እንደሌሎቹ መቅረቴ ነበር አንግዲህ ለዚህ ካበቁኝ እርሱን ስፈልግ እሞታለሁ እንጂ ራሴን ወድጄ ደስ ካለኝ ብዬ ከዚህ መቀመጥ አይቻለኝም አይዘነኑብኝ እኔ ጌትነት ይቀርብኛል እንጂ ለእርስዎ አሽከር አይታጣም አለና ነገረው ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር ንጉሥ አስተውሎ ሰምቶ ቁም ነገረኛነቱን አድንቆ ሲያቆም በዚህስ ከሆነ አታስብ አንዳገኘሁ አርሱንም በየትም አስፈልጌ አስገኝልሃለሁ አንተ ብቻ ከእኔ ጋር እንድትቀመጥ አሺ በለኝ አለው ዋሕድም ንጉሥ ሆይ ይኸንማ ታደረጉልኝ እንኳን በደስታ እኖራለሁ ሲሉኝ ባሪያ ቋሚ አድርገው ቢገዙኝም ደስ እያለኝ አገዛልምታለሁ ምን ከፍቶኝ አለና መለሰ ንጉሥ ለዋሕድ እንዳደረገው ሁሉ ወዲያው አለቱን ነጋዴ የሆንህ ወረታህንም የዘረፋው ጊዜ የተገፈፍህ ወረትህን እንዳስመልስልህ ወረትህንም ያልተቀማህ ለእንግዲሁ በየፄድክበት ሁሉ አንዳትነካ ድብዳቤ እሰጥሃለሁና ክተት አዋጁን እንደሰማህ ገስግሰህ ድረስ አለና በያገሩ አስነገረ ዋሕድም በማግሥቱ ጦቢያ በነበረችበት ቦታ የባለሟል ጌጥ ተሸልሞ እልፍኝ ገባ ንጉሥም እጅግ አቀረበው ባለሟል የተባለ ሁሉ እንደልማዱ በቅናት ይፈጠረቅ እርስ በርሱ ይመሳጠር ጀመር ንጉሥ ግን የጦቢያ ነገር እንዳይደርስበት ፈርቶ ከፊቱ እንዳይለይ ከእሱ በቀር ማንም ቢጠራው እንዳይሰማ ከትእዛዝ ጋር መከረው ከዚህ ወዲህ ንጉ እናዳለው ተጠንቅቆ ቀን ቀኑን ከእልፍኝ ከንጉሥ ጋር እየዋለ ማታ ማታውን ወደ አባቱና ወደ እኅቱ አየሄደ ያድራል የንጉጮ ዘመድ ግን በጦቢያ ነገር ተታማች ወዲያ አባቷ ባለሟሎች ከሚገቡበት ከንጉሥ እልፍኝ እንዳትገባ ለብቻዋ ከድንኳኗ እንድትቀመጥ አድርጎ ከልክሏል ስለዚህ የዋሕድን አልፍኝ መግባት አታውቅም ነበርኹ ንጉሥ ግን አንድ ቀን መቼም በጦቢያ መሄድ እንዳዘነች እንዳለቀሰች ያውቃልና ለዚያችው ለዘመዱ በምሥጥር አድርጎ አይዞሽ እህቴ ጦቢያ ሄደ ብለሽ አትዘኝ ተወደድሽው ተመልሶ እንዲመጣ አደርጋለሁ አለና ነገራት እርሷ ግን ይህን በሰማች ጊዜ ደስታና የጦቢያ ናፍቆት ይዚት ነበርና ዝም ብላ እንባዋን ታዝረከርክ ጀመር ቀጥላም ጌታዬ ወንድሜ ይህንማ ታደረግህልኝ ይህ ሁሉ ጌትነቴ ማዕረጌ ቀርቶብኝ ወጠ ሰሪ ገንቦ ተሸካሚ ሆኝ ወረታህን እከፍልዛፃለሁ እውነት ነው ያንተ ወገን ሆሼ ምን የሚጎድለኝ ምን የሚቸግረኝ ነገር ይገኛል ይኽ ሁሉ ማዕረግ የተመኙት ነገር ካልሆነ በዚህ ዓለም ምንም ደስታ የለውም። እያለ ይጠያይቀው ጀመር ምንም ያው ነጋዴ በሐዘንና በመከራ መልኩ ቢለዋወጥና ቢጎሳቆል የዋለለቱ ደግ ስራ አላስረሳውም አላስናቀውም እርሱ ግን ዋሕድን ተሸልሞ አብቦ ባየው ጊዜ ያየበት ስፍራ ጠፍቶት ተጨነቀ ኋላ ግን ነገሩን ሁሉ ዋሕድ በነገረው ጊዜ ጥንቱንም ስጦታው በዚህ ዓለም ቢታወቅበት አልወደደም ነበርና እንደ ክፉ አድራጊ ዐፈረ ደነገጠ ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር ንጉሥ የእዚህን ነጋዴ መገኘት እንዳወቀ ወዲያው አስጠራና አርሱ በገዛ አፉ ይኽን ያህል ከብት ይኽን ያህል ወርቅና ብር ጠፍቶብኛል ብሎ በተናገረው መሰረት ሁለት አጥፍ አድርጎ በሚገዛው አገር ነጋድራስ አሰኝቶ ሹሞ ለቀቀው የሰው ውለታ ክፉም ቢሆን በጎ በወዲያኛው ዓለም ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜም በዚህ ዓለም ፍዳው ወይም ካሣው ባድራጊው ላይ ይደርሳል ይኸን ሁሉ ነገር አሣምሮ ከጨረሰ ወዲያ ንጉሥ ዋሕድንና አባትዬውን ለብቻቸው አድርጎ በምሥጢር የምትወደው ልጆህ ጠፍቶብህ ስታለቅስ ፈልጌ አግኝቼ ይኽው አንተን ደስ አሰኘሁህ እንባህንም አደረቅሁልህ ደግሞ ወደ ዋሕድ ዙሮ ስትፈልግ ከመሸጥ የደረስህበትን ሰው በአዋጅ አስፈልጌ አስገኝቼ አንተንም ደስ አሰኘሁህል ስለዚህ ሁለታችሁም ወረታ መመለስ ይገባችሏልና ወረታዬን መልሱልኝ አላቸው ይኽን ቃል በሰሙ ጊዜ ሁለቱም ተጨነቁ ቀጥሎም ንጉሥ ሆይ። አሉና በአክብሮት መለሱለት ንጉሥም አስተውሎ ሁሉንም ሰማና አውነታችሁ ነው ሁሉ ይቻለኛል ንጉሥ ነኝ መንግሥቴም እጅግ ሰፊ ነው እኔ ምንም ልጅ ብሆንና እናት አባትም ደጋፊም ባይኖረኝ የእኔ አምላክ ሁሉን አሟልቶና አሳክቶ ሰጥቶኛል ነገር ግን ጨርሶ ደስ ይለኝ ዘንድ አንድ ነገር ብቻ ይቀረኛል ይኸውም ነገር ከእናንተ ዘንድ በቀር ከሌላ አይገኝምፅ ደፃግሞም ንጉሥና ሀብታም ብቻ አይደሉም ወረታ ማድረግ የሜቻላቸው ንጉሥም ከድኃው ደገፋ ካላገኘ ከቶ በሰላማዊ ኑሮ ሊመራ አይቻለውም መንግሥቱም መንግሥት ትዳሩም ትዳር አይሆንምሱ አሁንም የማይቻላችሁን ነገር አልለምናችሁምና እሺ በሉኝ አላቸው እነአርሱም ቸገራቸውና ነገሩን እስኪ አእንወቀው ከሆነልን ለንጉሥ እንቢ የምንለው ነገር የለንም አሉ በዚህ ጊዜ ንጉሥ እንዲህስ ታላችሁ ከበግና ከፍየል መካከል ከሚኖር ቀበሮ ከሚስቱ ጋር ጭሮ የሚኖር ዶሮ ይበልጣል እኔም ምንም ሁለንተናው ተዘጋጅቶልኝ ብታዩት ጨርሶ ደስ አላለኝም ጭራሽ ደስ ብሎት ይኑር ብላችሁ ታዘናችሁልኝ አንተ ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር አባትዬው ጦቢያን በሚስትነት መርቅልኝ አጅግ ወድጃታለሁ ሞቴም ሕይወቴም በአርሷ ይሁን አንተም ዋሕድ የምወዳትን የአጎቴን ልጅ መርቄ እሰጥፃለሁና አግባ አርሷንም ታገባህ ወዲያ ከአንተ በላይ ሹም እንዳልሾም ቃሌ ነው አለና ጨረሰ አባትዮው በሃይማኖት ነገር ጦቢያ አጅግ ብርቱ ነበረችና ፈርቶ ተጨነቀ ጊላ ግን ቀን ይስጡኝ መክሬ እነግርዎታለሁ አለና ተለያዩ ዋሕድም ፊት የአኅቱን መጨረሻ ነገር ለማወቅ ዝም ብሉ ቀየ ጦቢያ ነገሩን በሰማች ጊዜ ደነገጠች ነገሩም ደነቃት ጦቢያ ከልጅነቷ ጀምራ የኩራትና የጌትነት ነገር አታስብም ነበርና ቶሉ እሺ አላለችም። ፅ ንጉሥ ይኽን በሰማ ጊዜ ስሙ ዋሕድ ይሁን ብያለሁና የባልሽ ስም እንደተለወጠ ዕወቂው ዋሕድ ማለት አረመኔና አማራ አንድ ሆነ ማለት ነውና ስለዚህ ተለወጠ የእርሱንም ስም ለአኔ ሚስት አድርጌዋለሁ ብሉ ነገራት እርሷ አሺ መልካም ስም ነው መልካም ትርጉም አለው ብላ ደስ ብሏት ተቀበለች ሠርጉም ተሠረገ ጋብቻቸው እስከልጅ ልጅ የደስታ ግቢ ሆነ መንግሥቱም የጠና ሃይማኖቱም የበረታ ሆነ ዋሕድ ከዚህ በኋላ ነጋዴ ደብድቦ ጥሎት የሄደ ጊዜ አስታመው ያዳኑትን ሰዎች ልጅ ከተሸጠበት አስመጥቶ ስለ እናት አባቱ ወረታ የእርሱ እንደራሴ አድርጎ ሾመው ንጉሥ ከዚህ ወዲያ ጦቢያን አገባና አንዲህ ብሎ ገጠመላት ፐዩፀፀበ ልጠከር በበፎኋበገከር እንዲች ያለች ጽጌ ከወዴት በቀለች እንዲያው መላክ ኑራ ከላይን ወረደች አላመል ተፈጥራ ሰውን አስጨነቀች እንኳን ወንዱንና ሴቱን አዘነጋች ይኽም ሁሉ ሆኖ መኩራት አላሰበች ሳዱላዋን ትታ ጠጉሯን ተሸለተች ጠልሰሟን አውልቃ አጎዛ ደረበች ሥጋጃዋን ንቃ አቃቅማ ረገጠች ከዙፋኗ ወርዳ ተኮረብታ ወጣች እንኳን ለመዋረድ ለሞት ያልተገባች ዓለም ሲሰግድላት በድንክ ተከሠሠች።