Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ስለ መስቀል ታሪክ መናገር ማለት ነው መስቀሉን ከተቀበልን በኋላ ከነ ወርቅ ሣጥኑ የዕንቁ ሣጥን መስቀለኛ አድርገን አሠርተን ከዚያ ውስጥ አስቀመጥነው ከለሜዳውን አክሊለ ሦኩን ሰፍነጉን ጅራፉን ገመዱን ከነሙዳዩ እኛ ባሠራነው በወርቅ ሣጥን ውስጥ አስቀመጥናቸው ከዚኸውም ውስጥ እንደ ሥዕለ ስቅለት የተሠራ የዕጅ የወርቅ መስቀል አለበት ዘወርቅ ወሙዳያትሂ ብዙን ቦቱ ወመክድናሂ ለሣፁን ዘወርቅ ወየዓፅውዎ በቅፍሎ ዘወርቅ ወለሣፁንሰ ዘወርቅ ዘአግበርኖ ንሕነ ጉል ወርቁ ወወወዛ ዲናር ወለሣፁንሂ ዘዕፅ ዘሥርግው በወርቅ ጉልቱ ለሥርጋዌ ዕፅ ወ ጅወ ዲናር ዘንተ ኩሎ ወሀብነ ሰእግዚአብሔር አብ። ይኸውም ለረጅም ዘመናት በቃል ሲተላለፍ የቆየውን መጽሐፈ ቅዳሴ ነጠላ ንባቡን ከነትርጓሜው እንዲያዘጋጁ ነበር ።
ኛቆሮ ብሏል ይህ የሚያሳየው ምንም እንኳ አይሁድ መስቀሉን ቢቀብሩትም በላዩም ቆሻሻ ቢደፉበትም ሐዋርያት ስለ መስቀሉ ክብርና በመስቀሉ ስለተገኘው ድኅነት መመስከር ማስተማር አለማቋረጣቸውን የመስቀሉ ፍቅር ከውስጣቸው የማይወጣ ከደማቸውና ከሥጋቸው የተዋሐደ በቆዳቸው ሳይ በማይፋቅ ቀለም የተቀረጸ መሆኑን ነው አይሁድ በክፋታቸው አሕዛብ በሥጋዊ ኃይላቸው ሲመኩ ለክርስቲያኖች ግን ትምክህታቸው መስቀሉ ነበር ነገር ግን ዓለም ለእኔ ከተሰቀለበት እኔም ለዓለም ከተሰቀልኩበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ ገላ እንዳሰለ በዚህ ሁኔታ መስቀሉ አይሁድ እንደቀበሩት አሕዛብ በላዩ ላይ የጣዖት ቤት እንዳነጹበት ክርስቲያኖች ግን ሳይረሱት ለሦስት መቶ ዓመታት ተቀብሮ ቆይቷል ሄ በኋላ ግን አሁንም የነፃነት ምልክትና መገኛ የሆነው ቅዱስ መስቀል ለክርስቲያኖች ዘመነ ሰቆቃ ፍጻሜም ምክንያትና ኃይል ሆነ ከሦስት መቶ ዓመት በኋላ ንጉሥቆስጠንጢኖስ በሮምና በግሪክ ነግሠው ዓለምን አስጨንቀው ፍትሕ አጥፍተውክርስቲያኖችን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ታትረው ይሠሩ የነበሩ ዲዮቅልጥያኖስንና መክስምያኖስን ለመግጠም ተነሣ በዚህ አስፈሪና እጅግ ከባድ በሆነ ጦርነት ውስጥ ደግሞ መጽናኛና ኃይል የሚሆን ሕልምን አየ ሕልሙም የመስቀል ምክልት የያዘ መልአክ መስቀሉን ለንጉሠ እያሳየበዚህ ምልክት ጠላቶችህን ድል ንሣ የሚል ነበር ከዚህ ቀደም ንጉሥ ይህንን ምልክት አያውቀውምነበር አሱ የሚያውቀው ከሱ በፊት የነበሩ የሮም ነገሥታት መስቀሉን ወንጀለኛ ይሰቅሉበት ስለነበር የሞት ምልክት መሆኑን ነው እንጅ ሞት ድል ተነሥቶበት የሕይወት ምልክት መሆኑን አያውቅም ነበር እናቱ እሌኒ ስለ ክርስትና ትምህርት እያስተማረች ያሳደገችው ቢሆንም የክርስትናን ምሥጢር ተቀብሎ አልተጠመቀም ነበር እግዚአብሔርም እርሱ የሚድንበትንና ሌሎቹንም የሚያድንበትን ምልክት ሰጠው ቅዱስ ዳዊት ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠኻቸው እንዳለ በመቀጠልም ንጉሥ በተሰጠው ምልከት ጠላቶቹን ሁሉ ድል ነሣ በ ዓም በሚላን ሆኖ የነፃነት አዋጅ አወጀ መስቀሉ የፍትሕ ምንጭ ሆነ ከአሁን በኋላ ክርስቲያኖች እንዳይሰደዱ ሃይማኖታቸውንም በግልጽና በነፃነት እንዲያስተምሩ በነፃነት እንዲያመልኩ አወጀ አብያተ ክርስቲያናት ታነፁ አብያተ ጣዖታት ተዘጉ ይህን ውለታ ለመክፈል ንግሥት እሌኔ ከቀድሞ ጀምሮ በነበራት ስእለት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ በጎለጎታ የተሠራን ቤተ ጣዖት አፈረሰች ቤተ ክርስቲያንም አሠራች በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያን ሊቃውንትን ሊቀ ጳጳሱን መቃርዮስንና አረጋዊው ኪራኮስን በመጠየቅ መስቀሉን ከተቆፈረበት አወጣች እንደ ታሪኩ አቀራረብ ንግሥት እሌኒ መስከረም ቀን ቁፋሮውን ጀምራ መጋቢት ቀን ዓም መስቀሉን አወጣችበኋላም ለመሰቀሉ መታሰቢያ ቤተክርስቲያን ተሠርቶ ቅዳሴ ቤቱ መስከረም ቀን ዓም ተከበረ እነዚህ በዓላት በመላው ዓለም ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይከበራሉ ንግሥት እሌኒም ቅዱስ መስቀሉን ሊቀ ጳጳሱ መቃርዮስ በኢየሩሳሌም ባሠራችው ቤተ መቅደስ እንዲያስቀመጥ አድርጋ ወደ ሀገረ መንግሥቷ ቆስጥንጥንያ ተመለሰች ከዚያም መስቀሉ በኢየሩሳሌም ተቀመጠ ብዙ ዓመታትንምኖረ በርካታክርስቲያኖች ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ወደ ኢየሩሳሌም ከሚፄዱባቸው ምክንያቶችም አንዱ መስቀሉን ለማክበር ነበር እስከ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ በሰላም ቆቀየ በ ዓም የፋርሱ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን ወረረ ብዙ ጥፋትም አደረሰ መስቀሉንም ማርኮ ወደ ፋርስ ወሰደው በ ዓም ክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል በክርስቲያኖች ጥያቄ ፋርስን ወግቶ መስቀሉን ወደ ኢየሩሳሌም መለሰው ቆይቶም ኢየሩሳሌም በዓረቦች እጅ ስትወድቅ ክርስቲያኖች መስቀሉን ደበቁት ይሁን እንጅ መላው ኢየሩሳሌም ፍልስጥኤም ምሥራቃዊው ሮም ሰሜን አፍሪቃ ሁሉ በዓረቦች ቁጥጥር ሥር ስለሆኑ መስቀሉን ደብቀው ማስቀመጥ አልቻሉምና ወደ እስክንድርያ አመጡት ከእስክንድርያም በዚህ መጽሐፍ እንደተጻፈው በእግዚአብሔር ፈቃድና በነገሥታቱ ጥረት ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ መጣ የጌታችንና የመድንሂኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል የተቀመጠባት የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ ከደሴ ከተማ ኪሜ ርቃ ከፍ ብሎ በሚታይ መስቀለኛ ተራራ ላይ ትገኛለች በአቅራቢያዋም ከሚገኙ በርካታ ታሪካውያንና ጥንታውያን መካናት መካከልም ጥንታዊው የደብረ ሐይቅ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም የድጓ ምስክር የነበረው ደብረ እግዚአብሔር የቅኔ ትምህርት ምንጭ የሆነው ዋድላደላንታየኛው ክፍለ ዘመን የሃይማኖት ውሳኔ የተደረገበት የቦሩ ሜዳ ሥላሴ የውጫሌ ውል የተፈረመበት የውጫሌ ከተማ የመቅደላ አምባ የበሽሎ ወንዝ ሸለቆና ሌሎችም ናቸው የግሸን ደብረ ተራራ ከላይ ወደታ ሲታይ ግሸን ደብረ ከርቤ የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት በልዩ ልዩ ታሪካዊና ምሥጢራዊ ምክንያቶች ደብረ ነገሥት ደብረ ነጐድጓድ ደብረ እግዚአብሔር በሚባሉ ስሞች ትጠራ ነበር ግሸን ደብረ ከርቤ መጀመሪያ የተመሠረተችው በዘመነ አክሱም በዐዔ ካሌብ ዘመነ መንግሥት ነበር ዐፄ ካሌብ በየመን የነበሩ ክርስቲያኖች በአይሁድ መሪ ዱን አናሚስ እየደረሰባቸው ከነበረው መከራ ለመታደግ ወደ ናግራን ዘምተው ድል አድርገው መንግሥት አጽንተው ሲመለሱ በዚያ ይኖሩ የነበሩ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የሚባሉት መነኩስ አብረው ተመልሰዋል አባ ፈቃደ ክርስቶስም ከናግራን ሲመለሱ ሁለት ጽላቶችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት የበሸሎ ወንዝን ተሻግረው ወደ ግሸን ተራራ ጫፍ ለመውጣት የአምባውን ዙሪያ ሲመለከቱ በገደሉ ላይ ንብ ሰፎ ማሩ ሲንጠባጠብ አይተው የአምላክን ስጦታ ለማድነቅ በጥንታዉያን ግእዝና ዓረብኛ ቋንቋዎች ቦታውን አምባ አሰል አምባሰል ብለው ጠሩት ትርጉሙም የማር አምባ ማለትነው እስከ አሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል አባ ፈቃደ ክርስቶስም ይዘዋቸው የመጡትን ሁለት ጽላቶች ወደ አምባው በማስገባት ሁለት ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ደብሩን መሥርተዋል ይኽንኑ ታሪክ በመከተልም ይመስላል በጉዲት ጦርነት የስደት ዘመን የአክሱሙ ንጉሥ ድል ነዓድ በዘጠነኛው ከፍል ዘመን ከአምባሰል ባሻገር ከሐይቅ ባሕር አጠገብ ባለው ተራራ ላይ ደብረ እግዚአብሔርን መሥርቶ ኖሯል ከዚህም በኋላ መንግሥት ከደብረ እግዚአብሔር በመራ ተክለሃይማኖት አማካኝነት ወደ ሳስታ ሲሻገር የደብረ ከርቤ ክብር በላስታ ዘመንም አልተቋረጠም በቅዱስ ላሊበላ ዘመን እንደተፈለሰፈሉ የሚነገርላቸው ጅምር ዋሻዎች አሁንም በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም ይገኛሉ በዚህ ዘመን ደብረ ከርቤ የነገሥታት መናኸሪያ የሊቃውንት መገኛ የቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ሥርዓት መፈጸሚያ ቅድስት ቦታ ነበረች በመጨረሻም በዐፄ ዘርዓ ያፅቆብ ዘመነ መንግሥት የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል መቀመጫ ሆናለች በግሸን ደብረ ከርቤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ያረፈበት የእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ፎ። አንን ንኑ ብለው ዳዊት ሆነው ከኢትዮጵያው ወሶበ ንጉሠ ኢትዮጵያ መፍቀሬ እግዚአብሔር ዳግማዊ ዳዊት ሰምዓ ተከዘ ወኃዘነ ብዙኃ ወቀንዓ መንፈሳዊተ ቀንዓተ ወተንሥአ ይሑር ብሔረ ግብፅ ክመ ይጽብዖ ለንጉሠ ምስር ወለመኳንንቲሁ ወበእንተ ዘአሠሮ ለሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ አባ ሜካኤል የእግዚአብሔር ወጠዳጅ የሆኑ ዓፄ ዳዊትም ይህን በሰሙ ጊዜ የአሕዛብ ንጉሥ በአኔ ዘመን ይህን ያህል ይታበያልን ብለው ፈጽመው አዘኑ ከዚህ በኋላ መንፈሳዊ ቅንዓት አድሮባቸው እእ ከአባቴ ብበልጥ እንጂ አንሳለሁን ብለው ከምስሩ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ግብፅ ሊዘምቱ ተነሠ የአስክንድርያውን ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤልን ስለአሠራቸው ወበእንተ ዘኀደገ ኪዳነ ዘተካየደ ምስለ አቡሁ ሰይፈ አርዓድ ወኮኑ ሠራዊቱ እለ ወረዱ ምስሌሁ ብሔረ ግብፅ አፍራሰ ወ አብቅልተ ወ አግማለ ወሶበ በጽሐ ኀበ ካርቱም ወጠነ ከመ ይሚጦ ለፈለገ ዓባይ ከመ ይክልኦሙ ማየ ፈለገ ዓባይ ዘይሰመይ ግዮን ለሰብአ ግብፅ መጀመሪያ ከአባታቸው ከዓፄ ሰይፈ አርዓድ ጋር ሁለተኛ በክርስቲያን ላይ ከፍቅር በቀር ጸብ ላያነሣ ተማምለው የነበረውን መሐላ በማፍረሱ ከሳቸውም ጋር ግብፅ የወረደው የሠራዊታቸው ብዛት ዐሥር እልፍ ፈረሰኛ ዐሥር እልፍ ባለበቅሎ ዐሥር እልፍ ባለግመል ሆኑ ከሀገረ መንግሥታቸው ተነሥተው ካርቱም ሲደርሱ ግዮን የሚባለውን የዓባይን ውሀ መልሰው ወደ ካርቱም በረሐ ሰደዱት እስመ አልቦሙ ማይ ወኢክረምት ክእንበለ ፈለገ ኢትዮጵያ ዘውእቱ ዓባይ ወሶበ ሰምዑ ንጉሠ ምስር አህመድ ወልደ መርዋን እልጋዲን ወመኳንንቲሁ ተንባላት አእመሩ ከመ ዝንቱ ኩሉ ዘኮነ በእንተ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ደንገጸ ወፈትሖ እመ ዋቅሕቲሁ ወአክበሮ ክብረ ዓቢየ ወከማሁ ለኩሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን የግብፅ ሰዎች ዓባይ ከተባለው ከኢትዮጵያ ወንዝ በቀር ወሀ የላቸውምና የምስሩ ንጉሥ የመርዋን እልጋዲን ልጅ አህመድ እና መኳንንቱም ይህን በሰሙ ጊዜ ይህ የሆነው ሊቀ ጳጳሳቱን አባ ሚካኤልን በማሠራቸው እንደሆነ ዐወቁ ተረዱት ደንግጦም አባ ሚካኤልን ከአእሥራታቸው ፈታቸው ፍጹም ክብር አከበራቸው ከሞት የተረፉትን ምእመናንም ከግዞት ነፃ አወጣቸው ወእምዝ ሰአሎ ንጉሠ ምስር ለዝንቱ አብ ክቡር አባ ሚካኤል ወለኩሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን ዘኢየሩሳሌም ወሶርያ ወአርማንያ ወሮም ወቀስጥንጥንያ ከመ ይፈንው መልእክተ ኅበ ንጉሠ ኢትዮጵያ መፍቀሬ እግዚአብሔር ዳግማዊ ዳዊት ወከመ ይስአልዎ ይትመየጥ ብሔሮ በስላም ዓዔ ዳዊት የፈጸሙትን የቆራጥነት ሥራ ከሰማ በኋላ የምስሩ ንጉሥ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤልን ይለመናቸው ጀመር በኢየሩሳሌም በሶርያ በአርማንያ በሮም በቀዮስጥንጥንያ ያሉ ምእመናንንም ይለምን ጀመር ይአግዚአብሔር ወዳጅ ወደሚሆኑ ወደ ዓፄ ዳዊት ዘንድ ላኩልኝ ለምኑልኝ ብሎ መልእክት ይልኩ ዘንድ በፍቅር በሰላም ሆኖ ወደ ሀገሩ ይመለስ ዘንድ ለምኑልኝ ብሎ ይለምናቸው ጀመር ጩ ወመሐለ ሎሙኒ ከመ ኢይሥዓር ሃይማኖቶሙ ወከመ ኢይወልጥ ሥርዓታቲሆውጮ ወከመ ኢያንስእ ጸብዓ ላዕሲሆሙ ዳግፃመ ወሰሚዖሙ እሙንቱ ተፈሥሑ ወሰብሕዎ ለእግዚአብሔር በእንተ ዘአድጎኖሙ እምኩነኔ ተንባላት ወለአኩ ወፈነውዎ ለዝንቱ አብ ክቡር ከባ ሚካኤል ምስለ ብዙኃን መኳንንተ ግብፅ ወምስሌሆሙ ወ ዲናረ ወርቅ አምኃሁ ለንጉሠ ኢትዮጵያ እኔም ሃይማኖታችሁን ለውጡ የፈጣሪአችሁን ስም አትጥሩ ሕጋችሁን ሥርዓታችሁን ለውጡ ብየ አልጣላችሁም ዳግመኛም ከፍቅር በቀር ጸብ ክርክር አላነሣም ብሎ በሃይማኖቱ ማለላቸው እነዚህም ምእመናኑ ይህን መሐላ በሰሙ ጊዜ በዓፄ ዳዊት አድሮ ከአሕዛብ አገዛዝ ነዓ ስለአወጣቸው እግዚአብሔርን ፈጽመው አመሰገኑት ምእመናኑም መክረው ደብዳቤ ጽፈው ሊቀ ጳጳሳቱን አባ ሚካኤልን መኳንንቱም ዐሥራ ሁለት አልፍ ወቄት ወርቅ እጅ መንሻ አስይዘው ወደ ዓፄ ዳዊት ላኩ ምስለ መጽሐፈ መልእክት ዘይብል እግዚአብሔር ይባርክ ላዕሌከ ወላዕለ መኳንንቲከ ወላዕለ ሠራዊትከ ወመሳፍንቲከ እስመ ናሁ አድኃነነ እግዚአብሔር እማዕሠረ መዋቅሕት ወእምኩነኔ ተንባላት በእንቲአከ ወይአዜኒ ተመየጥ ኀበ ብሔርከ በዳህና ወበሰላም ወእግዚአብሔር ይዕሚከ በመንግሥተ ስማያት ህየንተ ዘፃመውከ በእንቲአነ ወሶበ ሰምዓ ንጉሠ ኢትዮጵያ ዳግማዊ ዳዊት እግዚአብሔር በአንተ አድሮ ከአሕዛብ አገዛዝና ከግዞት ነዓ አውጥቶናልና እግዚአብሔርመገሥትህን ያስፋ ሠራዊትህን ያብዛ መኳንንትህንና መሳፍንትህን ይጠብቅ የሚል የምርቃን ደብዳቤ ጭምር ላኩ አሁንም ወደ ሀገርህ በፍቅር በደስታ ተመለስ ለእኛ ብለህ ስለ ደከምከውም ድካም ሁሉ ዋጋህን እግዚአብሔር በመንግሥተ ሰማያት ፅጽፍ ድርብ አድርጐ ይክፈልህ ዓ ዳዊትም ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ሜካኤል ምጽአቶ ለሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ወረደ ምስለ ኀዳጣን ሠራዊቱ እስከ ምድረ እስዋን ዘውእቱ ወስን ማዕከለ ኢትዮጵያ ወግብፅ ወተራከበ በህየ ምስለ ሊቀ ጳጳሳት ወምስለ መኳንንተ ግብፅ ወወሀብዎ መጽሐፈ መልእክቶሙ ለእሉ ዘተናገርነ ቀዳሚ ወአቅረቡ ሎቱ አምኃ ወ ዲናረ ወርቅ ዛዌ ከእሥራታቸው ተፈትተው ወደሳቸው እንደመጡ በሰሙ ጊቤ ምርጥ የሆኑ ጥቂት የጦር አበጋዞቻቸውን ይዘው እሰዋን ድረስ ወረዱ ይኸ እስዋን የተባለው የኢትዮጵያና የግብፅ ወስን ድካ የነበረው ነው ከዚህም ቦታ ሲደርሱ ሰኔ ቀን ከሊቀ ጳጳሳቱ እና ከመኳንንቱ ጋር ተገናኙ አስቀድመን የተናገርናቸው ምእመናን የጻፉላቸውን ደብዳቤ ሰጧቸው ያመጡትን ዐሥራ ሁለት እልፍ ወቄት ወርቅ እጅ መንሻ አቀረቡላቸው ውእቱኒ ሰብሖ ለእግዚአብሔር በእንተ ዘአድኃኖሙ ለክርስቲያን እምኩነኔ ተንባላት በእንቲአሁ ወለአከ ኀበ ንጉሠ ምስር ወመኳንንተ ተንባላት እንዘ ይብል ሠናየ ገበርክሙ በእንተ ዘገበርክሙ ዕርቀ ምስለ ክርስቲያን አኃዊክሙ ወእምይአዜሰ አጽንዑ መሐላክሙ ወኢታንሥኡ ጸብዓ ምስለ ክርስቲያን ዓፄ ዳዊትም ይህን አይተው እግዚአብሔር በእሳቸው አድሮ ወዳጆቹ ምእመናንን ከአሕዛብ አገዛዝ ነዓ ስለአወጣቸው ፈጣሪያቸው አመሰ። እናንተን ለማጥፋት ያለኝን ሐሳብ አልለውጥም ነበር ከዚህ በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱንና መካንንቱ የዓባይን ወሀ መልሰው እንዲሰዱላቸው ለመኑአቸው ዓፄ ዳዊትም ውሀውን አልመልስም ይህንም እጅ መንሻ ወርቅ አልቀበልም ብለው መለሱት እንዲህ ብለው ወርቅና ብር የእኛን ነፍስ ለማዳን አይረባም አይጠቅምም አያድንም አላ ለአከ ንበ ኩሎሙ ክርስቲያን ዘኢየሩሳሌም ወሮም ወሶርያ ወአርማንያ እንዘ ይብል አንሰ ኢይትዌከፍ አምኃክሙ ወርቀ ወብሩረ አላ መዩጥየ ፈኖኩ ለከሙ እስመ ኢያድኃነነ እግዚአብሔር በወርቅ ወበሩር አላ አድኃነነ በደመ መስቀሉ ወእንሰ እፈቅድ ከመ ትፈጽሙ ፈቃደ ልብየ ኢየሩሳሌም ሶርያና አርማንያ አሉ ክርስቲያኖች ላኩ እንጂ ሮም ወደ እንዲህ ብለው እኔ የላካችሁትን እጅ መንሻ ወርቅና ብር አልቀበልም መልሼ ሰድጀላችሁአለሁ እንጅ እግዚአብሔር በመስቀል ተሰቅሎ በከበረ ደሙ ፈሳሽነት አዳነን እንጂ በወርቅበብርአላዳነንምና እኔ ግን በልቤ ያሰብኩትን ሐሳብ ትፈጽሙልኝ ዘንድ ነው እንጂ ወከመ ተሀቡኒ መስቀሎ ለክርስቶስ ዘተክዕወ ደሙ ቅዱስ ላዕሌሁ ዘሀሎ በኀበ እዴሁ ለሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ ወሶበ ሰምዑ መልእክቶ ለንጉሠ ኢትዮጵያ መፍቀሬ እግዚአብሔር ዳዊት ኩሎሙ ክርስቲያን መከሩ ምክረ ዓቢየ ምስለ ሊቀ ጳጳሳት ዘአእስክንድርያ ከመ ይፈንው ሎቱ መስቀሎ ለክርስቶስ ክቡር እንዘ ይብሉ ይደልዎ ከመ ንፈኑ ሎቱ እስመ ውእቱ ኢኃሠሠ ደሙ ፈሳሽነት የክበረየጌታችን የክርስቶስ መስቀል በእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት እጅ ያለውን ትሰጡኝ ዘንድ ነው እንጂ በከበረ እነሱም እግዚአብሔርን የሚወድ የኢትዮጵያ ንጉሥ የዓፄ ዳዊትን መልእክት በስሙ ጊዜ ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ጋር ታላቅ ምክርን መክከሩ ክቡር የሚሆን የጌታችን የክርስቶስን መስቀል ይሰዱላቸው ዘንድ መከሩ እንዲህ ብለው መንፈሳዊ ንጉሥ እንደ መሆኑ መጠን ወርቅ ወርቀ ወብሩረ አላ ቀንዓ ቅንዓተ መንፈሳዊተ ለሀገረ መንግሥቱ ኢትዮጵያ በዘይድኅኑ ሰብአ ኢትዮጵያ በዝንቱ መስቀል ክቡር ዘእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አባር ወእምኃጢአ ዝናም ወእምኩሉ ደዌ ወመቅሠፍት ሕማም ወመንሱት ወነጉሠ ምስርሰ አህመድ ወመኳንንተ ተንባላት ተሐውኩ ብዙኃ በምክንያተ ዝንቱ ወመፍቀሬ እግዚአብሔር ዳዊት ለአክ ኀቤሆሙ ብር አይሻምና ልንሰድለት ይገባዋል ብለው መከሩ እሱም መንፈሳዊ ቅንዓቱ የሀገሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለሚድኑበት እንጂ የኢትዮጵያ ሰዎች በዚሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ክኮረኃብ ከድርቅ ከዝናብ እጦት ከመዓት ልዩ ልዩ ከሆነ ከፍጹም ጥፋት ይድኑበት ዘንድ ነውና ይገባዋል አሉ በዚህ ምክንያት የአሕዛቡ ንጉሥ አህመድንና መኳንንቱ ፈጽመው ታወኩ ዓፄ ዳዊት ግን ወደ እነሱ መልእክት ላኩባቸው እንዘ ይብል አንሰ ኢይመይጥ ማየ ዓባይ ፈለግ ዘብሔርየ አላ አኃድጋ ለሀገርክሙ ትትመዝበር በኃጢአ ማይ ወሰሚዖሙ እሙንቱ ቃሎ መከሩ ምክረ ሠናየ በዘመከሩ ክርስቲያን ወእምዝ ኀቢሮሙ ፈነው ሎቱ ክርስቲያን ወተንባላት መስቀሎ ለክርስቶስ ወሥዕላተ እግዝእትነ ማርያም ሰብዑ ዘሠዓሎን ሉቃስ ወንጌላዊ እንዲህ ብለው መስቀሉን ካልሰጣችሁኝ ሀገራችሁ በድርቅ ፈጽማ ትጥፋ እንጂ የሀገሬን ወሀ አልመልስም ብለው ላኩ እነሱም ዓፄ ዳዊት የላኩትን ቁርጥ ሐሳብ ሰምተው ምእመናኑ እንደ መከሩት ይውሰድ ብለው በጐ ምክርን መከሩ ከዚህ በኋላ አሕዛብም ክርስቲያኖቹም አንድ ሆነው ተስማምተው ከነሱ ዘንድ የነበረው የጌታችንን መስቀል ሰደዱላቸው መስቀሉን ብቻ ሳይሆን ሉቃስ የሣላቸውን ሰባቱን የእመቤታችንን ሥዕሎች። ወሥዕለ ኩርዓተ ርእሱ ለእግዚአነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘሠዓሎ ዮሐንስ ወንጌላዊ ህየንተ ዘሜጠ ሎሙ ወጅ ዲናረ ወርቅ ዘአምጽኡ ሎቱ ወወሀብዎእሎንተንዋያተ ክቡራት አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ ወመኳንንተ ግብፅ ውእቱኒ መፍቀሬ እግዚአብሔር ዳግማዊ ዳዊት ተንሥአ በክብር ዓቢይ ወሰገደ ለመስቀለ እግዚአነ ወለሥዕላተ እግዝእትነ ወለኩርዓተ ርእስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የሣለውን የጌታችንን የኩርዓተ ርእሱን ሥዕል እጅ መንሻ ብለው የላኩለትን ዐሥራ ሁለት ወቄት ወርቅ መልሶ ስለሰደደላቸው እነሱም ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ሚካኤልና መኳንንቱ ሆነው ይህን መስቀሉንና ሥዕላቱን እጅ መንሻ አድርገው ሰጧቸው እግዚአብሔርን የሚወዱ ዳግማዊ ዓፄ ዳዊትም በፍጹም ደስታና ክብር ተነሥተው ለጌታችን መስቀል ለእመቤታችንና ኩርዓተ ርእሱ ሥዕፅሎች ሰገዱላቸው ወእምዝ ተመጠዎሙ በእዴሁ እምድኅረ ፈጸመ አምጥቶሙ ዝንቱ ኩሉ ኮነ አመ ለመስከረም ወኮነ ብርሃን በኢትዮጵያ ወበኩሉ አድያሚፃ ወተፈሥሑ ዓቢየ ፍሥሐ ሕዝብ ወአሕዛብ ፅድ ወአንስት አዕሩግ ወሕፃናት በዓለ ዕለት ዓቢየ አመ ወገብሩ በይእቲ ለመስክረም ንጉሥ ወሠራዊቱ ወሕዝቡ እጅ ነሥተው ካበቁ በኋላ በእጃቸው ተቀበሏቸው ይህ ሁሉ ተፈጽሞ የተቀበሉበት መስከረም ቀን ነው መስቀሉን በተቀበሉበት ጊዜ በኢትዮጵያና በአውራጃዎችዋ ሁሉ ብርሃን ሆነ በዚህም ምክንያት ታላቁም ታናሹም ወንዱም ሴቱም ሕዝቡም አሕዛቡም በፍጹም ደስ ተሰስኙ መስቀሉን በተቀበሉበት መስከረም ቀን ዓፄ ዳዊት ከሠራዊቶቻቸው ጋር ፈጽመው ደስ ተሰኙ በዓሉንም አከበሩ እንዘ ያሌዕሉ ቃላቲሆሙ ወይጠፍሑ በአደዊሆሙ ወያጽሕሱ በእገሪሆሙ ወገብረ ንጉሥ ምሳሐ ዓቢየ ዘአልቦ ጉልተሩ ወእስከ ይእዜ ያብዕልዎ ነገሥታተ ኢትዮጵያ ለዝንቱ በዓል ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰምተው እየጮሁ በአጃቸው እያጨበጨቡ በዕልልታ በእግራቸው እየረገጡ በሆታ ካህናቱ በዝማሬ መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ እያሉ ከፍ ባለ ደስታ በዓሉን አከበሩ ዓፄ ዳዊትም ከደስታቸው ብዛት የተነሣ ሥፍር ተጐተዜጥር የሌለው ግብዣ አድርገው ይህንም ልማድ ምክንያት አድርገው እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያ ነገሥታት በዓሉን ያከብሩታል ወሰመይዎ በዓለ ዓፄ መስቀል በከመ ተጽሕፈ በመጽሐፈ ስንክሣር ወእምዝ ጎደገ ሎሙ ፈለገ ዓባይ ዘውእቱ ግዮን ይሑር በቀዳሚ ሥርዓቱ ወይስተዩ ሰብአ ግብፅ እምኔሁ። ምክንያት እንናገራለን ወአንበሮ ውስተ ደብረ ነገሥት እንተ ይእቲ ደብረ ከርቤ በወ ወ ዓመት እምፍጥረተ ዓለም በወ ወጃጁ ዓመት እምልደተ መድኃኒነ በ ወ ወጁ ዓመተ ስማዕታት ነግሠ ዘርዓ ያዕቆብ ርቱዓ ሃይማኖት ወልደ ዳዊት ዳግማዊ » አምላክ ደብረ ነጐድጓድ ነገሥት ከዓፄ ዘርዓ የቪህች ቦታ ስመ ተፋልሶ ጊዜ ነው ከዓዔ ደብረ ክርቤ እየተባለች በምትጠራው በደብረ ነገሥት አስገብተው እንደ አስቀመጡት እንናገራለን ዓለም በተፈጠረ በስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ፃያ ሰባት ዓመት ጌታ በተወለደ በሺህ አራት መቶ ፃያ ሰባት ዓመት በሺህ አንድ መቶ ፃያ ስባት ዓመተ ሰማዕታት ፃይማኖታቸው የቀና የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ነገሠ ወተቀብዓ ቅብዓ መንግሥት እምዘተርፈ እምይኩኖ አምላክ አበአቡሁ። ቦታዋም በመስቀል አምሳል የተቀረፀች ተራራ ናት እኔም ታቿን ዙሪዋን ሦስት ጊዜ ዞርኳት ወረከብክዋ ከመ ትእምርተ መስቀል ይእቲ ወእቤ ዝንቱ መካን ዘይቤለኒ አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል ዘንተኒ ዜነውክዎሙ ለጳጳሳት እለ ሀለው ምስሌየ ወለካህናት ወለመኳንንት ወእሉኒ ይቤሉኒ በአማን ይደሉ ዝንቱ መካን ለዝንቱ መስቀል ክቡር ከመ ይንበር ውሴቴቱ በትእምርተ መስቀል አምሳል ተቀርጻ በፈቃደ እግዚአብሔር ታንጻ አገኘሏት እኔም መስቀሌን በሥስቆል ላይ አስቀምጥ ያለኝ ይህ ቦታ ነውን አልኩ ይህንኑም አብረውኝ ላሉት ለጳጳሳቱ ሰነ አባ ሚካኤል ለሊቃውንቱ ካህናት ለመኳንንቱ ነገርኳቸው አማከርኳቸው ጳጳሳቱም መኳንንቱም አይተው በእውነት ለዚህ ክቡር መስቀል መቀመጫ የተገባ ቦታ ነው አሉኝ ወእምዝ ስዕነ በዊኦታ ለአንቀጽ እስመ ኢኮነ ርቱዓ ፍኖተ ሙባሁ ወበእንተዝ ኃደርነ ታሕቴፃ መንገለ ምሥራቅ ወበሌሊት አስተርአየኒ መልአክ ዘይዜንወኒ ወይቤለኒ ከዚህም በኋላ ገደል ከመሆኑ የተነሣ ወደ አምባው ለመግባት አቃተን ብዙ የነገሥታት ሀብት ስለነበረበት ማንም ገብቶ እንዳይዘርፈው በማለት የመግቢያው በር ጭንቀኛ በመሆኑ ንጉሥ ሊገባበት በትንሽ ጊዜ አይችልምና ስለዚህም ከእግረ ደብሩ በምሥራቅ በኩል ካለው ሜዳ ሠፍረን አደርን ከዚህ በኋላ የሚመራኝና የሚከተለኝ መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ሌሊት በራዕይ ተገለጸልኝ ተገልጾም እንዲህ አለኝ ናት ማነ ላገስናጣጋ ስ ኩ መጻኤ ዛቲ ይእቲ ደብር ዓባይ ዘትሰመይ ደብረ ነጐድጓድ ወእምይእዜሰ ትሰመይ ደብረ ከርቤ ወይእቲ ሀገረ መንግሥት ወክህነት ኢየዐርግ ኅቤሃ አዕጋረ ዕቡያን ወአማጽያን ትሄይስ ወትከብር እምኩሎን አድባራት ቀደም ሲል ደብረ ነጐድጓድ ኋላም ደብረ ነገሥት እየተባለች የምትጠራው ታላቋ ቦታ ይህች ናት ከዛሬ ጀምሮ ወደፊት ግን ደብረ ከርቤ ትባላለች ደብረ ነጐድጓድ የተባለችው የካህናትና የነገሥታት መኖሪያ ስለሆነች ነው የትዕቢተኞች የመናፍቃን እግር አይረግጣትም ከሀዲያን ማለት አንድነቱን ሦስትነቱን የሚክዱ ሊኖሩባት አይችሉም ከአድባራት ሁሉ ከፍ ያለች የከበረች ናት ። ኢይሴሰል እምኔፃ መንፈስ ቅዱስ ኩሎ ጊዜ ለሐውዖፆዖታ ወዕርግ ህየ አንቀጸ እንተ ምሥራቂፃ ወበህየ ትረክብ ተ አብያተ ክርስቲያን ንዑሳተ ድ ይህችውም ደብረ ከርቤ ለአግዚአብሔር አብ እንደ ጽርሐ አርያም የሚሠለስባት የሚቀደስባት ቦታ ናት ለእመቤታችንም አመ አምላክ እየተባለች የምትመስሰገንባት ቦታ ናት የተጸለየውን ጸሎት የተሠዋውን መሥዋዕት በነጋ በነጋ በየጊዜው ለመቀበል መንፈስ ቅዱስ ከሷ አይለይምና ይህን ብሎ ከነገረኝ በኋላ በምሥራቅ በኩል ባለው በር ግባ አለኝ ከገባህም በኋላ ትንንሽ ሁለት አብያተ ክርስቲያን ተሠርተው ታገኛለህ አሐቲ በስመ እግዚአብሔር አብ ወአሐቲ በስማ ለቅድስት ማርያም ወእሉሂ ዘአምጽኦሙ ፈቃደ ክርስቶስ ባሕታዊ እምሀገረ ናግራን በወበወ ዓመት አእምልደተ መድኃኒነ በመዋዕለ ካሌብ ንጉሠ ኢትዮጵያ ወምክንያተ ምጽአቶሙሰስ ለታቦተ እግዚአብሔር አብ ወታቦተ ማርያም ድንግል ከሁለቱም አንዲቱ በእግዚአብሔር አብ ስም የተሠራች ናት አንዲቱም በእመቤታችን ቅድስት ማርያም ስም የታነጸች ናት እነዚህም ዐሥራ አራት ዓመተ ምሕረት በዓፄ ካሌብ ዘመን ፈቃደ ክርስቶስ የሚባል ባሕታዊ ከሀገረ ናግራን ያመጣቸው ናቸው የእግዚአብሔር አብና የእመቤታችን ድንግል ማርያም ታቦቶችም የመጡበት ምክንያት ግን በሁለቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉት ታቦቶች በአምስት መቶ እንዘ ሀሎ ፈቃደ ክርስቶስ ባሕታዊ ውስተ ሀገረ ናግራን ተተክለ ዓምደ ብርሃን ዓቢይ ዘሥዑል ውስቴቱ ሥዕለእግዝእትነ ማርያም ውስተ ይእቲ ሀገር ወቀፀቦ እንዘ ያበርህ ከመ ፀሐይ ወዕንዘ ያስምዕ ድምፀ ከመ ነጐድጓድ ወበዕለተ አስተርአዮ ዝንቱ ዓምደ ብርሃን አስተርአየቶ እግዝእትነ ማርያም ወትቤሉ ፈቃደ ክርስቶስ የሚባል ባሕታዊ ሀገረ ናግራን ተቀምጦ ሳለ ከዚህች ቦታ ላይ በመካከሉ የእመቤታችን ማርያም ሥዕል የተቀረጸበት ዓምደ ብርሃን ተተክሎ እንደ ፀሐይ እያአበራ እንደነጐድጓድ ድምፅ እያሰማ ሲጠቅሰው በጸጋ ያይ ነበር ይህችም ቦታ የቀራንዮ አምሳል እንደ መሆኗ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ድምፅ እያሰማ ይጠቅሰው ነበር የብርፃን ዓምዱ በተገለጸለት ቀን እመቤታችን ድንግል ማርያም ተገልጻ ታየችው እንዲህ አለችው ተንሥእ ወንሣእ ታቦተ እግዚአብሔር አብ ወታቦተ ዚአየ ወሑር ኅበ አስተርአየከ ዓምደ ብርፃን ወሀሎ ህየ እስከ ይከውን ፈቃዱ ለእግዚአብሔር እስመ ዛቲ ህገር ዓባይ ይእቲ ወወሀበኒ ወልድየ ሶበ ሖርኩ ኢትዮጵያ ጊዜ ስደትየ ትኩነኒ ርስተ ለትውልደ ትውልድ አ ዱረዜ ዱዊጻዲዝዜ ዱን ንሴ ሴሌሴኔሴሌኤሴሴ ሌሴ ኢሲ የአኔና የአግዚአብሔር አብንታቦት ይዘህ ተነሥ ተነሥተህም ይህ የብርፃን ዓምድ ተተክሎ ከጠቀስህ ቦታ ፈጥነህ ሂደ የእግዚአብሔር ፈቃዱ እስኪሆን ከዚያው ተቀመጥ የእግዚአብሔር አለችው ፈቃድ እስኪሆን አለች ታቦቶቹ በክብር የሚገለጹት በመስቀሉ ምክንያት ነውና ይህችም ቦታ ከአድባራቱ ሁሉ ተለይታ የከበረች ናትና በርጉም ሄሮድስ ዘመን ተሰድጄ ኢትዮጵያ በፄድኩበት ጊዜ ለልጅ ልጅ መታስቢያ ርስት ትሁንሽ ብሎ ወይሰባሕ ስምየ ውስቴታ እስክ ለዓለም ወባረካ በበረከተ መንፈስ ቅዱስ ወአልዓለ ክብራ እምክብረ ኩሎን አድባራት ወእምድኅረ ዜነወቶ ዘንተ ተሠወረት እምኔሁ ወበእንተዝ መጽአ በፈቃዱ ለካሌብ ንጉሥ እንዘ ይመርሖ መልአከ እግዚአብሔር ቅዱስ ዑራኤል ስሜም እስከ ዕለተ ምጽአት ያለማቋረጥ ሲመሰገን ይኖርባት ዘንድ ሰጥቶኛልና ሂደህ ተቀመጥ አለችው አንድነቱ ሦስትነቱ ሲነገርባት እንዲኖር በመንፈስ ቅዱስ ባረካት አከበራት ስሟም ከአድባራቱ ሁሉ በላይ ሆኖ በክብር እንዲታወቅ አደረጋት ይህን ቃል ተናግራ ካስረዳቸው በኋላ ከርሱ ተሠወረችው በዚህምክንያትበዓዒካሌብ ፈቃድ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ዑራኤል እየመራው ታቦቶቹን ይዞ ወምስሌሁ ወ መነኩሳት ወቦአ ኅበ ዛቲ ደብር ወነበረ ውስቴታ ብዙኃ መዋዕለ ወአዕረፈ በሰላም ወትረክብ አዕፅምቲሁ መትሕተ ቤተ ክርስቲያን ክእግዚአብሔር አብ ወበገቦ ይእቲ ቤተ ክርስቲያን ሀሎ ዓቢይ ነቅዕ ከሱ ጋር ዐሥራ ሁለት መነኮሳት አስከትሎ ነበር ከዚህች ቦታ ገባ እመቤታችን እንዳዘዘችው ታቦቶቹን አክበሮ ቤተ ክርስቲያን ተክሎ ብዙ ዘመን ኖረ። ችም ቦታ ከጌታ በተሰጣት ሥጋውን ደመሙን ተቀብለው የሚማፀ ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቃ አንድነትን አሰጥታ ገነት መንግሥተ ደብረ ከርቤም ማለት መካነ መስቀል ማለት ነው ሰሎሞን ቀደም ብሎ ምእመናን ወደዚህ መጥተው እጅ መንላት እንዲገባቸው ለማጠየቅ ኑ ወደ ደብረ ከርቤ እንሂድ ብሎ በመኀልዩ ተናግሯልና ደብረ ከርቤ አለ መልአኩ ብለው ሰየሟት ቀድሞ ግን ደብረ ነጐድጓድ ትባል ነበር ሰማያት ታገባቸዋለችና ስለዚህ ደብረ ከርቤ አለ አስቀድሞ ደብረ ከርቤ ትባል ብሎ እንደተናገረ ደብረ ከርቤ ለዝ ነገር ሠራዕኖ ለትውልደ ትውልድ ወካዕበ አዘዝክዋ ለእኅትየ ፅሌኒ ንግሥት ወለተ ዳግማዊ ዳዊት ከመ ተሐድስ ሕንፃፃ ለቤተ ክርስቲያን ዘእግዚአእትነ ማርያም ውስተ ይእቲ ደብር እንተ ርኅቅት መጠነ ሙጋረ ዕብን ይህን ሥርዓት ከዘልጅ ልጅ እንዲተላለፍ ብለን አዘናል ጽፈናል ሠርተናል ቀደም ብሎ ፈቃደ ክርስቶስ ተአምራት እያደረገችለት እየተማፀነባት የአመጣትን የእመቤታችንን ታቦት ዓፄ ይኩኖ አምላክ ለነገሥታቱ ሴቶች ልጆች መማፀኛ ሲሉ ለይተው ቤተ ክርስቲያኗን አሠርተው ቦታይቷን ደብረ ነገሥት ብለው ሰይመው ስትኖር በጊዜ ብዛት የተነሣ ቤተ ክርስቲያት አርጅቶ ነበርና የዳንማዊ ዳዊት ልጅ እኅቴ ንግሥት ዕሌኒን መንፈሳዊ ቅንዓት አትቀኝምን እኔ ምን ስሠራ ታያለሽ አንችስ በእመቤታችን ስም የታነጸችውን ቤተ ክርስቲያን አታሳድሽምን ብየ አዘዝኳት የቦታውም ርቀት እኔ ከሠራሁበት ቦታ አንሥቶ ጐልማሳ ድንጋይ ወርውሮ እንደሚያደርስበት ነው ወይእቲኒ ሐደሰት ወሐነጸት አሠርጊዋ በወርቅ ወበዕንሩ ወበብሩር ወአመ ቅዳሴ ቤቱ ለእግዚአብሔር አብ ወ ዓጓወሀ ዓመት እምልደተ መድኃኒነ አመ ወ ለመስከረም መጽአ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዘ ሀሎ በሥላሴሁ ዲበ ዘባነ ኪሩቤል። ወእምድጎኀረዝ ዓርገ ውስተ ሰማያት በዓቢይ ስብሐት ወእምዝ በራብዕ ወርኀ እም አመ ኮነዝ አመ ወ ለጥር ኮነ ቅዳሴፃ ለቤተ ክርስቲያን ዘእግዝእትነ ማርያም ዘሐነፃታ እሌኒ ንግሥት ወመጽአ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና ሰማይ ምስለ እሙ ቅድስት ድንግል ወአዕላፍ መላእክት ይቀውሙ ዓውደ ከዚህ በኋላ በክብር በሥልጣን እንደመጣ በክብር በሥልጣን ወደሰማይ ዓረገ ከዚህ በኋላ ቃል ኪዳን በሰጠን በአራተኛው ወር ጥር ፃያ አንድ ቀን እኅቴ ንግሥት ዕሌኒ በእመቤታችን ስም አድሳ የአሠራቻት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቷ ሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባህርየ ክብሩ እንዳለ ሁኖ ንዕድ ክብርት ከምትሆን ከእናቱ ጋር አእላፍ መላእክት ዙሪያውን ሁነው እያመሰገኑት መጣ ወአስተርአየነ ከመ ቀዳሜ ወይቤለነ ዛቲ መካነ ምዕራፍየ ይእቲ እስከ ሰዓለም ወእለሂ ይነብሩ ውስቴታ እንዘ ይሰፈው ዐሥራተ እምየ ይከውኑ ከመ መላእክተ እግዚአብሔር ወእለሂ ተመጠው ሥጋየ ወደምየ ውስተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን ይከውኑ ከመ ሕፃናት ዘቤተልሔም ዘተቀትሉ በአንተ ስምየ መስከረም ፃያ አንድ ቀን ያ የእግዚአብሔር አብን ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱን ባከበርንበት ቀን አንደ ተገለጸልን ሁኖ ታየን ይህች ቦታ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ የስሜ መመስገኛ በረድኤት መገለጫየ ናት አለን የእናቴን አማላጅነቷን አምነው ከዚህች ቦታ ውስጥ የሚኖሩትም እንደ መላእክት አደርጋቸዋለሁ በዚህችም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሥጋዬን ደሜን የተቀበሉትን በእኔ ስም ደማቸውን እንደ አፈሰሱ የቤተልሔም ሕፃናት ይሆናሉ ወለዛቲ ቤተ ክርስቲያን ረሰይክዋ ትኩን ከመ ጌቴሴማን መቃብረ እምየ። ባየ ጊዜ ከደረቅ ዕንጨት ወአመ ለመስከረም ግብሩ በዓለ መስቀል በዘወጽአ መስቀል በመዋዕለ አቡየ ዳዊት በከመ ነገርነ ቀዳሚ ወአመ ወሄ ለመስከረም ግበሩ በዓለ መስቀል በከመ ሥሩዕ አምትካት ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑ ለመስቀል ወይእዜኒ ያጽንዓነ ያጽንዕክሙእግዚአብሔር በርትዕት ሃፃይማኖት ዳግመኛም በመስከረም ቀን የመስቀሉን በዓል አክብሩ አስቀድመን እንደ ተናገርነው አባቴ ዓፄ ዳዊት መስቀሉን የተቀበሉበት ቀን ነውና መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን በዓሉን አክብሩ ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉን ያገኘችበት ቤተ ክርስቲያኑን ያሳነጸችበት ሁለተኛም አባ አውደኪስ ይስሐቅ ሣምራዊን በመስቀል ተአምራት ያሳመነበት ነውና አሁንም እግዚአብሔር በጸናች በቀናች በተዋሕዶ ፃይማኖት ያጽናችሁ ያወ በእንተ ሥጋሁ ወደሙ ለክርስቶስ መጣዌ ኦሪት ወነቢያት ወሀቤ ወንጌል ወሐዋርያት ለዓለመ ዓለም አሜን ወአሜን ለይኩን ለይኩን በእንተ ሥጋሁ ወደሙ ለክርስቶስ ለይኩን ለይኩን ያጽናን ሥጋውን ደሙን ስለተቀበላችሁ ኦሪትን ሠርቶ የሚያስተምሩ ነቢያትን የሰጠ ወንጌልን ሠርቶ ያኑ የሚያስተምሩ ሐዋርያትን የሰጠ ለዘለዓለሙ እስከ ትውልድ ድረስ በተዋሕዶ ሃይማኖት ያጽናችሁ አሜን ይሁን ይደረግልን የክርስቶስ አካል ማኅበር ቤተሰብ ስለተባላችሁ ይሁን ይደረግልን ፌሚ ሚሙ ሙች ችኝ ምዕራፍ ወካዕበ አምጻእነ ለክሙ ከመ ትትአምኅዎሙ ወታከብርዎሙ ወትግበሩ ተዝካሮሙ ዘሀለው አፅፅምቲሆሙ በውሣጤሁ ለሣፁን ዘዕፅ ዘሥርግው በወርቅ ወውእቱ ይጸውሮሙ ለኩሉሎሙ ህየ ሀለው ዓፅመ ሐና እመ ማርያም ወላዲተ አምላክ ምዕራፍ ዳግመኛም በዓላቸውን ታከብሩ ዝክራቸውን ትዘክሩ ትማፀኑባቸው ዘንድ በወርቅ ከተለበጠው ከዕንጨቱ ሣጥን በውስጥ አፅማቸው ያለ አሁን የሚቁጥራቸውን ሁሉ የቅዱሳንን ዓፅም ከመስቀሉ ጋር አንድ አድርጎ የሚይዛቸው እሱ ነውና ከዚህ ቀጥሎ የመጣውን የቅዱሳንን ዓፅም ተርትሮ ይቂቄጥሯል ከዚያውም ካለው መጀመሪያ አምላክን የወለደች የአመቤታችን ድንግል ማርያም እናት የሐናዓፅም ያ ወአፅመ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ ወዓፅመ ጊዮርጊስ ዘልዳ ወዓፅመ ገላውዴዎስ ሰማዕት ዘአንዖኪያ ወዓፅመ ሳዊሮስ ወዲዮስቆሮስ ሊቃነ ጳጳሳት ወአፅመ ሕዛናት ዘቤተልሔም አሉ ቱ ሀለው ውስተ ሣፁን ዘዕፅ ዘሥርግው በወርቅ ወታቦተ ማርያም ድንግል በኤ አምጻእነ ለክሙ የ ሐ ዋ ር ያ ው የበርተሎሜዎስን ዓፅም የቅዱስ ጊዮርጊስ ዘልዳን ዓፅም የአንያኪያ ሰማዕት የሆነ የገላውዴዎስን ዓፅም የሊቃነ ጳጳሳቱ የሳዊሮስን የዲዮስቆሮስን ዓፅም ፄሮድስ በቤተልሔም ያስፈጃቸው ሕፃናት ዓፅም እህ የቄጠርናቸው ሰባቱ ሁሉ ካጌጠው በወርቅ ከተለበጠው የእንጨት ሣጥን ውስጥ አሉ ከ ዚያውም ላይ አምላክን በወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ በጸናች ከመ ይሠራዕ ወይትቀደስ ባቲ ፉርባን አንቢረክሙ ዲበ ታቦት ወትረ እስከ ለዓለም ወይእቲ ታቦት ዓባይ ይእቲ ወባቲ ቃላት ወኩሉ ታቦት ዘቦ ቃላት ዓቢይ ውእቱ ። ወካህናተ ደብተራ ዘመርጡል መኳንንት ዳግመኛ የቀና ቂስጠንጢኖስ የተባሉ ንጉሣችን ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ እንዲህ አሉ እስራኤል የተባላችሁ ምእመናን ሁሉ በዚህ በአግዚአብሔር አብና በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ተሠርታችሁ የምታገለግሉ ካህናት ደጃዝማቹ ቀኛዝማቹ ግራዝማቹ ሃይማኖታቸው ወአቃምባ ምስለ ሥዩማን ፅድ ወአንስት አንስወሀብኩለሊቀካህናት ይስሐቅ ዘእግዚአብሔር አብ ኩስኩሰ ዘወርቅ ዘቦ ሥዕል ዘወርቅ ወፈቃር ዘወርቅ ወክዳነ ዘወርቅ ወመነግሣግንስ ዘሐር የክፍሉ ምስለኔ አቦ አስተዳዳሪው በውስጡ የምትገኙ ሹማምንት ወንዶችም ሴቶችም ብትሆኑ ስሙ ለግሸን አለቃ ሆኖ ቦታውን ይጠብቅ ካህናቱን ያስተዳድር ዘንድ የማዕርግ ስሙን ሊቀካህናት ብየ ለሾምኩት ለሊቀ ካህናት ይስሐቅ የወርቅ ሥዕል ያለበት የአንገት ሀብል በወርቅ የተጠለፈ የወርቅ ቀሚስ ከወርቅ የተሠራ ካባ ከነጭሐርየተሠራጭራ ወድባበ ዘወርቅ ወመስቀለ ዘወርቅ ዘዕድ ዘቦ ሥዕል ላዕሌሁ ወብርተ ዘወርቅ ወምስለ ንብቲራ ዘብሩር ዘንተ ኩሎ ወሀብነ ከመ ይኩን ሞገሰ ደብርነ ወሞገሶሙ ለዕብራውያን አበዊነ ወአኃዊነ የወርቅ የየድባብ በላዩ ሥዕል የተቀረፀበት የወርቅ የፅጅ መስቀል የወርቅ ሰን ከብር የተሠራ ብርት ማለት መታጠቢያ ይህን ሁሉ የደብራችን የሹመቱ ማዕርግ መታወቂያ ይሆን ዘንድ ሰጠን ቀደሞ በዚህ ሥልጣነ ክህነት ለነበሩ አባቶቻችን ወደፊትም በዚህ ሥልጣን ለሚተኩ ወንድሞቻችን የሹመታቸው መታወቂያ የሥልጣናቸው መከበሪያ እንዲሆን ያ በከመ ነገረ ቀዳሚ ሕግ ዘሌዋውያን ዘንተ ሠራዕፅነ ለትውልደ ትውልድ ዘለዓለም ወካዕበ ወሀብነ ለጃንጠራረ መኩንንነ አምባሰል ዳታነ ዘወርቅ ወአራዘ ዘወርቅ ወክዳነ አዝራር ዘወርቀ በዓለ ወፀምረ ለይ ዘወርቅ ዘይቀንቶ ቀይሕ ቀደም ብሎ የካህናትን ክብር ለማጠየቅ ሲል ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ ተብሎ እንደ ተናገረ ይህን ሥርዓት ለዘለዓለም እስከ ልጅ ልጅ ይተላለፍ ብለን ሠራን የአምባሰል ገዥ አስተዳዳሪ አድርገን ለሾምነው ለጃንጠራሩ የአጁ መታጠቢያ የሚሆን የወርቅ ዳታን የወርቅ ቀሚስ አዝራር ያለው የወርቅ ለምድ የሚታጠቀው የወርቅ ቀይ ግምጃ ሱሪ ወቅናተ ዘወርቅ ወዓዲ ወሀብኖ ሥልጣኖ ይስተይ በጽዋዓ ንጉሥ ወይጸዓን በቅለ ዘሥርጉት በወርቅ ወያንፍሕ ቀርኖ እስከ ውሣጤ ጽርሐ ንጉሥ ወይንበር በፀጋመ ንጉሥ የወርቅ ቀሸመሪ ዝናር ሰጠን ዳግመኛም በንጉሥ የወርቅ ዋንጫ እንዲጠጣ በወርቅ መረሻት ባጌጠች በቅሎ እንዲቀመጥ ከንጉሥ እልፍኝ ደጃፍ ድረስ ነጋሪቱን እያስመታ እንዲገባ ገብቶም በንጉሥ ግራ ተካክሎ እንዲቀመጥ ወይንብር ካህን በየማነ ንጉሥ እንዲል ቀኙ የሊቀ ጳጳሱ መቀመጫ ነውና ወይትለዓል ክብሩ እምክብረ መሳፍንት ወመኳንንት እስመ ጃንጥር ብሂል ኃራዬ ወጸዋዒ ወአቅራቢ ንጉሥ እምወ ውሉደ ነገሥት እለ ይነብሩ ውስተ ዛቲ መካን ወለፍትሐ ሊቀ ካህናት ክደብረ ከርቤ አልቦ ዘይሰምዕ ዘእንበለ ሊቀ ጳጳስ ወንጉሥ ክብሩም ከመሳፍንቱ ከመኳንንቱ በላይ እንዲሆን ሥልጣን ሰጠን ጃንጠራር ማለት ከዚህች ቦታ ውስጥ ተቀምጠው ከሚማሩት አምስት መቶ ዘጠና የነገሥታት ልጆች ኑ ሃይማኖት ሰፊ አእምሮ ያለውን ጠርቶ መርጦ ለንጉሥነት የሚቀርብ ማለት ነው መርጦ አቅራቢው እሱ ነውና የግሽን ደብረ ከርቤ አለቃ ሊቀ ካህናቱ የፈረደውን ፍርድ ግን ያለ ሊቀ ጳጳሱና ንጉሥ በቀር የሚሰማ የለም ወአብያተ ክርስቲያናት ዘሀገረ አምባሰል ይጎኅድራ በታሕተ ሊቀ ካህናት ዘደብረ ከርቤ እስከ ለዓለም እስመ አልቦን ዘእንበሌሁ ዘይቀንዮን ወይሜሕርሮን ኢይምሰልክሙ ዝንቱ ደብርነ ቀሊለ ወዝንቱ መቅደስን ወለዝ ደብር ዘይትማሰሎ ኢረከብነ እምቅድመዝ ወኢይትረከብ እምድኀረዝ በአምባሰል ያሉ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ዘለዓለሙ ድረስ በግሸን ደብረ ከርቤ አለቃ ሥልጣን ውስጥ ይተዳደሩ ያለእሱ የሚያስተዳድሯቸውና የሚያስተምሯቸው የላቸውምና ይህ ደብራችን ግሸን ደብረ ከርቤ በእግዚአብሔር አብና በእመቤታችን ስም የሠራናቸውመቅደሶቻችን ቀላል አይምሰሏችሁ ከአሁን በፊት ይህን ደብር የመሰለ በክብር የሚተካከል አላገኘንም ወደፊትም አይገኝምና ወዘንተ ዘአጽርዓ ሥርዓተ እመሂ ነገሥት ወእመሂ ጳጳሳት አውገዝነ ወአሠርነ በቃልነ ዘኢይትፈታሕ እስክ ለዓለመ ዓለም አሜን ወአሜን ለይኩን ለይኩን ይህን ሥርዓት የአፈረሰውን ነገሥታቱም ቢሆኑ ጳጳሳቱም አስተምረን ይህን አናስፈጽምም ቢሉ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ በማይፈታ ቃላችን አውግዘናቸዋል አሥረናቸዋል አሉ አባ ሚካኤል አባ ገብርኤል ናቸው በውነት ይሁንባቸው ይደረግባቸው ጋር ጮጮ ውጪውም ጀምአ መው ምዕራፍ ዓፀደ እግዚአብሔር አብሂ ወዓፀደ እግዝእትነ ማርያም ይርእዩ ወይሕሥሥሠ ስለአውራንኀ አዘዝነ መኳንንተ ዘተሠይሙ ለሀገረ አምባሰል ወአኮ ዘንተ ባሕቲቶ አላ ዓውደ መርህባ ሉዓላዊ እስመ ቀጸርነ ሎቱ ቅጽረ ወአውጻእነ ፀተ አንቀጸ ከመ ይኩን ቅዱሰ ወባሕረ ዘአምጻእነ ዮርዳኖስ እምፈለገ ምዕራፍ የእግዚአብሔር አብንና የእመቤታችንን ድንግል ማርያምን ክበብ የአምባሰል ጃንጠራሮች በውስጣቸው የተሾሙት ባላምባራሱን ቀኝ አዝማቹን አዘው በየወሩ መጥተው ያጸዱ ያስጠርጉ ዘንድ አዘናቸዋል ይህም ብቻ አይደለም ላይኛውን ሜዳውን ጭምር ነው እንጂ ቦታው የተለየ ይሆን ዘንድ ዙሪያውን አስቀጽረን በአራቱ ማዕዘን በር አውጥተን አክብረነዋልና ጌታችን በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት ከዮርዳኖስ ዮርዳኖስ በቱ አግማል ወወደይነ ውስቲቱ በከመ አሰፈወነ እግዚእነ ወሠራዕነለአሠነዮ ቅጽር ወጀጐል ወለኩስትሮ ነኪረ ኩሉ ኩስሐአራዊትወአዕዋፍ ወብዙኅ ዕሚቶሙ በከመ አሰፈወነ እግዚእነ ወለእመሰ ተሐክዩ ወኢገብሩ ዘአዘዝኖሙ ፃ ውሀ በአራት ግመሎች አስጭነን አምጥተን የቀላቀልንበትን ዮርዳኖስ ብለን የሰየምነውን የጠበሉን ዙሪያ ጭምር እንዲያጸዱ አዘናቸዋል የፈረሰውን ቅጽር ለማሠራት የዙሪያውን የአጥር ዕንጨት እንዲያሳድሱ ከዚህ ጋር አራዊቱ አዕዋፉ የኩሱበትን አዘው ያስጠርጉ ያጸዱ ዘንድ አዘናቸዋል ጌታ በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት ይህን ስለ ሠሩ ዋጋቸው ብዙ ነውና ነገር ግን ባለሥልጣኖቹ ጃንጠራሮቹ አናዝም እግዚአብሔር ያውርድ ላዕሌሆሙ መቅሠፍተ አሳተ መዓቱ እንበለ ስሣሌ ወያማስን ነፍሶሙ ወሥጋሆሙ ለዓለም ዓለም አሜን ወአሜን ለይኩን ለይኩን ባላምባራሱ ቀኝ አዝማቹም አንታዘዝም ከፍ ያለ ሥልጣን ይዘን ዕንጨት ድንጋይ ጭቃ ልናሸክም ነው ኩስሐ አራዊት ልናስጠርግ ነውን ብለው ትእዛዛችንን ንቀው ግዝቱን አፍርሰው አናሠራም የሚሉ ቢሆን እግዚአብሔር ያለማቋረጥ በላያቸው እሳተ መዓቱን ያዝንምባቸው በዚህ ዓለም በሥጋቸው በወዲያኛው ዓለም በነፍሳቸው መከራ ይታዘዝባቸው ይሁን ይደረግ ወካዕበ አውገዙ አባ ሜካኤል ወአባ ገብርኤል ወአነሂ ምስሌሆሙ ከመ ኢይባዓ አንስት ውስተ ቤተ እግዚአብሔር አብ በእንተ ዘኢኮና አንስት ድልዋተ ለፀዊረ ታቦት ወገሚሶቱ ታቦትሂቲ ዘንቤ ዘሀለው ውስቴቱ መስቀል ወከለሜዳ ወአፅፅምቲሆሙ ለቅዱላን እስመ ሐነጽነ ሎን በስመ እግዝእትነ ማርያም ከመ ይጸልያ ወይትመሐፀና ባቲ በከመ ትቤ ኦሪት ምቅዋሞን ለአንስት ወምጽላዮን ለባሕቲቶን ዳግመኛም አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል ሴቶች ከእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አይግቡ አሉ እኔም እንደአነሱ ከለከልኩ ሴቶች ታቦት ሊዳስሱ ሊይዙአግባብአይደለምና ታቦትም ያልናቸው በእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉት መስቀሉ ከለሜዳው እና የቅዱሳን አፅም ናቸው ኦሪት ለሴቶች እንደሚገባ ባዘዘችው መሠረት ይጸልዩባት ይማጸኑባት ዘንድ በሕአመቤታችን ድንግል ማርያምስምቤተክርስቲያን ሠርተንላቸዋልና ወኢይሂዳ ዘንተ ትእዛዝ ከመ ኢይረድ መቅሠፍተ እግዚአብሔር ሳላዕሆን በከመ ወረደ በመዋዕሊነ ላዕለ አሐቲ ብእሲት ምስለ ቲ አዕማቲሣዝ ወይእቲኒ ለብስት ልብሰ ዕደው ምስለ አዕማቲፃዛ ወቦአት በድፍረት ውስተ ቤተ እግዚአብሔር አብ ወወጽአት እምዐፀድ ወትቤ።