Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
በቅዱስ ስሙ ሲበድሉና ሲረከሱ የሚያውቅ ከሆነ አንዴት የሰዎችን ከፋት ዝም ይላል። አዋቂስ አድርጎ የፈጠረኝ ማነው። ነገር ግን ከአባቶቻቸው ሰምተው ያምናሉ እነዚያስ የፊተኞቹ ገንዘብና ከብር ለማግኝት ካልሆነ በቀር ስለምን ዋሹ። ይዕይም ሪቻሃ ታ ወ። ይህንንና የሚመስለውን በሙሉ በልቤ ቀንና ሌሊት እፀልይ ነበር ስለፀሎት ስጋዊና መንፈሳዊ ሥራ ጠዋትና ማታ የምፀልየው ፀሎትም እንዲህ ነበር ፈሟሪያ ጠቋዖ ሯፀ ታ። ታታ ያፖባረስዕው ፌሪየሃ ይፖሃሄሳና ሐም ይምግናሃ ፊ ዓምርሰች ልባችን ዘወትር በአግዚያብሔር እጅ እንደሆነ አወቅኩ በበሽታና በድህነት በችግርም መካከል ብንኖር ጎስቋሎች ሊያደርገን ይችላል ስለዚህም ድሆችና ችግረኞች በልባቸው ደስታ ሁልጊዜ ሲጫወቱ እናያለን ሀብታሞችና ነገስታትም በምኞታቸው ብዛት በሀብታቸው መካከል ሲያዝኑና ሲጎሳቆሉ እናያለን እኛ ሳናውቀውና ሳንፈልገው የመነሻ ምክንያቱን ሳናውቅ ሀዘን በልባችን ውስጥ ይመጣል በምድር ብፁኣን እንዲያድርገንና ፍስሃና ደስታ እንዲሰማን ወደ አግዚያብሔር ልንፀልይ ይገባናል እግዚያብሔር ለፃድቃን ብርሃን ልባቸው ለቀና ደስታን ይሰጣቸዋል እርሱ ያውቃልና የልባችንንም መንገድ ሁሉ ይዝዘል እርሱ በቸግራችን ደስተኞች በድሎታችንም ሀዘንተኞች ሊያደርገን ይቸላል እግዚያብሔር እሚሰማን እንጂ ለሰዎች እንደሚመስላቸው በደስታና ሀዘን አይደርሰንም አንተ ፈጣሪየና ጌታየ በምድር እስካለህ ድረስ ብፁዕ አድርገኝ ደስታና ትፍስህትንም አሰማኝ ከሞቴ በኋላም ወደ አንተ ወስደህ ከአንተ አስጠጋኝ አልኩ እንዲህ ብየ ቀንና ለሊት እየፀልይኩ እግዚያብሔርን ስነ ፍጥረትን አንስሳትን የበርሃ አራዊትን በየስርዓታቸው እያደነቅሁ ነበር እነሱ ግን ሕይወታቸውን ለመጠበቅና ዘራቸውን ለማራባት በፀባየ ተፈጥሯቸው ይሳባሉ አንደገናም የበረሃ አንጨትና ሣር በትልቅ ጥበብ የተፈጠሩ ይበቅላሉ ይለመልማሉ ያብባሉ በየወገኖቻቸውም የዘራቸውን ፍሬ አለ ስህተት ያወጣሉና ነፍስ ያላቸው ይመስላሉ እንደገናም ተራሮችና ኮረብቶች ወንዞችና የውሃ ምንጮች ሥራ ሁሉ ስምህን ያመሰግነዋልጌታየ ሆይ ስምህን በሁሉ በሰማይ እና በምድር እጅግ ተመስግኗል ይህ የእጅህ ስራ ፀሀይ የብርሀንና የዓለም ህይወት ምንጭ እጅግ ትልቅ ነው አንተ የሰራሃቸውን የመሰረትካቸውን ጨረቃና ከዋከብትን አንተ ከሰራህላቸው መንገድ ሌላ አለመዛነፋቸው በጣም ያስደንቃሉ በመራቃቸው ደቃቃዎች የሚመስሉ ከዋከብትን ቁጥራቸውን እርቀታቸውን ታላቅነታቸውንስ የሚያውቅ ማነው። ደመናዎችም ልምላሜን ለማብቀል ውሃዎች ያፈሳሉ ይህ ሁሉ ታላቅና እጅግ የሚያስደንቅ ጥበብ በጥበብ የተፈጠረ ነው አንደዛም ብየ ፈጣሪየን እያደነኩና ፈጣሪየን እያመሰገንኩ ሁለት ዓመት ተቀመጥኩ እንደገናም የአግዚያብሔር ስራ አጅግ መልካም ነው ሀሳቡም ትልቅና የማይነበብ ነው ብየ አሰብኩ እንግዲያስ ትንሹና ምስኪኑ ሰው ለሰው ጥበቡንና አውነቱን እንደገለፀለት ከአግዚያብሔር ዘንድ ተልኬ መጣሁ እያለ ስለምን ይዋሻል።
ሕተታ ዘርዓ ያሰቅብ እግዚያብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ለነፍስ ያደረጋችሁትን መናገር እጀምራለሁና ኑ ስሙኝ ሁሉን በፈጠረ መጀመሪያና መጨረሻ በሆነ ሁሉን በያዘና የህይወትና የጥበብ ሁሉ ምንጭ በሆነ አግዚያብሔር በሰጠኝ ረዥም እድሜየ ትንሽ እፅፋለው ነፍሴ በአግዚያብሔር ዘንድ የተከበረች ትሁን ጆሮዎችም ሰምተው ይደሰቱ እኔ እግዚያብሔርን ፈለኩት መለሰልኝ አሁንም እናንተ ወደ አርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል ፊታችሁንም አያሳፍርም አግዚያብሔርን ከኔ ጋር ከፍ ከፍ አድርጉት አብረን ስሙን እናንሳ እኔ የተወለድኩት በአከሱም በካህናት ሀገር ነው ነግር ግን እኔ በአከሱም አውራጃ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በነገሰ በሶስተኛው ዓመት በ ዓም ከ አንድ ገበሬ ቤተሰብ ተወለድሁ በከርስትና ጥምቀት ረን ታፆ ተብየ ተሰየምኩ ሰወች ግን ወረይሉኛል ካደኩ በኋላ ትምህርት እንድማር አባቴ ወደ ትምህርት ቤት ላከኝ ዳዊትም ከደገምኩ በኋላ መምህሬ አባቴን ይህ ህፃን ልጅህ ልቦናው የበራ በትምህርት ታጋሽ ነውና ወደ ትምህርት ቤት ብትልከው ሊቅና መምህር ይሆናል አለው አባቴም ይህን ሰምቶ ዜማ አንድማር ላከኝ ሆኖም ድም ሸካራ ሆኖ አላምር አለኝ በዚህ ምከንያት ጓደኞቼ መሳቂያና መዘባበቻ አደረጉኝ እዛም ሶስት ወር ያህል ቆየው ስላልተሳካልኝ ከልቤ አዘንኩ ተነስቼ ሰዋሰውና ቅኔ ለመማር ወደ ሌላ አስተማሪ ሄድኩ ከጓደኞቹ ፈጥፔ እንድማርም እግዚያብሔር ጥበቡን ሰጠኝ ይህም የመጀመሪያ ሃዘኔን አስረሳኝ በጣም ተደሰትኩ አዛም አራት አመት ቆየሁ በነዚያ ቀኖች አግዚያብሔር ከሞት አዳነኝ ከጓደኞቼ ጋር ስጫወት ወደገደል ወደኩ እግዚያብሔር በታምራቱ አዳነኝ እነጅ ፈፅሞ ልድን አልችልም ነበር ከዳንኩ በኋላ ገደሉን በረዥም ገመድ ለካሁት አስራ ሶስት ሜትር ሆኖ ተገኝ እኔም ድፔ ያዳነኝን እግዚያብሔርን እያመሰገንኩ ወደ መምህሬ ቤት ሄድኩ ከዚያም ተነስቼ የቅዱሳት መፅሃፍትን ትርጉዋሜ ለመማር ሄድኩ በዚያም አስር ዓመት ቆየሁ መፅሃፍትን ፈረንጆች አንዴት አነደሚተረጉሟቸው የኛም ምሁራን አንዴት አነደሚተረጉሟቸው ተማረኩ ትርጉዋሜያቸው ግን ከኔ ልቦና ጋር የሚስማማ አልነበረም ሆኖም ይህን ስሜቴን ሃሳቤን ለማንም ሳልገልፅ በልቤ ይዥው ቆየሁ ከዚያም ወደሃገሬ ወደ አከሱም ተመለስኩ በአከሱም ለ አራት አመት መፅሃፍ አስተማረኩ ይህ ዘመን ከፉ ዘመን ሆነ አፄ ሱስንዮስ በነገሰ በ ኛው ዓመት የፈረንጆች ተወላጅ አቡነ አልፎንዝ መጣ ከ ዓመት በኋላም ንጉሱ የፈረንጆቹን ሃይማኖት ስለተቀበለ በኢትዮጵያ ትልቅ ስደት ሆነ ይህን ሃይማኖት ያልተቀበለ በሙሉ ግን እጣው ስደት ሆነ አፄ ሱስንዮስ አልፎንዝና ጠላቴ ወልደ ዩሃንስ እኔ በሃገሬ መፅሃፍት ሳስተምር ብዙዎቹ ጓደኞቸ ጠሉኝ በዚህ ዘመን የባልንጀራ ፍቅር ጠፍቶ ነበርና ቅናት ያዛቸው በትምህርትና ጓደኛን በመውደድ ከነርሱ እበልጣለው ከሁሉ ሰው ከፈረንጆቹና ከግብፃዊያን ጋር አስማማለሁ መፅሃፍትን ሳስተምርና ስተረጉም እንዲህ እንዲህ ይላሉ ግብፃዊያኖች ደግሞ ኦርቶዶክሶች እንዲህ አንዲህ ይላሉ እላለው እኛም ብንመረምር ይህን ሁሉ እናውቃለን እላለሁ እንጅ ይህ መልካም ነው ይህ ደግሞ ከፉ ነው አልልም ግብፃቹ የፈረንጅ ፈረንጆቹ ደግሞ የግብፃዊያኖቹ አመስላቸዋለው ስለዚህ ሁሉም ጠሉኘ ብዙ ጊዜም ወደንጉሱ ከሰሱኝ እግዚያብሔር ግን አዳነኝ ከዚህም በኋላ ከአከሱም ካህናት አንድ ወልደ ዮሃንስ የተባለ ጠላቱ የንጉስ ወዳጅ ስለነበረ የነገስታት ፍቅር በሽንገላ ምላስ ስለሚያገኝ ወደ ንጉሱ ሄደ ወደ ንጉሱም ገብቶ አንደዚህ አለው ወያፅው ሆያይዕሳሳ ዕሯይማሯፎታፖፇ ዳኦታና ራ ዳርው ፈሪጀሯም ዳና ባራምው ይሰ እያለ ይሄንና ይሄን በመሰለ ውሸት ከሰሰኝ እኔም ይህን አውቄ ገና ለገና ይገድለኛል ብዮ ፈርቼ የነበረኝን ሶስት ወቄት ወርቅና የምፀልይበትን መዝሙረ ዳዊት ይዝ በሌሊት ሸሸሁ ወዴት አነደምሄድ ለማንም አልተናገርኩም ወደተከዜ በረሀ ገባሁ በነጋታውም ራበኝ ከሀብታሞች ገበሬዎች አንጀራ ለመለምን እየፈራሁ ወጣሁ ሰጡኝና በልቼ እየሮጥኩ ሄድኩ እንዲህ እያልኩ ብዙ ቀን ቆየሁ በኋላ ወደ ሽዋ ግድም ስሄድ ሰው የለለበት በርሃ አገኝሁ ከገደሉ በታች መልካም ዋሻ ነበርና ሰው ሳያየኝ በዚህ ዋሻ አኖራለሁ ብየ ወሰንኩ ሱስንዮስ እስኪሞትም ድረስ በዚያ ዓመት ቆየሁ አንዳድንዴ ወደገበያ እየወጣው ወይም ወደ አማሮች ሀገር እሄድ ነበር ለአማራ ሰዎች የምበላው እንዲሰጡኝ የምለምን ባህታዊ መነኩሴ አመስላቸው ነበር ነገር ግን ሰዎች ከየት አንደምወጣና ወዴት አነደምገባ አያውቁም ከዋሻየ ለብቻየ በሆንኩ ጊዜም በመንግስተ ሰማያት የምኖር መሰለኝ ቁጥር የሴለው ከፋታቸውን አውቄ ከሰዎች ጋር መኖር ጠላሁ ሌሊት መጥተው የበርሃ አራዊት እንዳይበሉኝም በድንጋይና በአሸዋ አጥር ዋሻየን አጠረኩ እሚፈልጉኝ ሰዎች ወደኔ ቢመጡ የማመልጥበት መውጫ አዘጋጀሁ እዛ በሰላም ኖርኩ በሚሰማኝ በእግዚያብሔር ተስፋ አድርጌ በሙሉ ልቤ በመዝሙረ ዳዊት ፀለይኩ ስለአምላክ መኖርና የሐይማኖት መለያየት ከፀሎት በኋላም ስራ ስለሌለኝ ሁልጊዜ ስለሰዎች ከፋትና ሰዎች በእርሱ ስም ሲበድሉ ወንድሞቻቸውን ጉዋደኖቻቸውን ሲያባርሩ እና ሲገድሉ ዝም በማለቱ ስለፈጣሪ ጥበብ አስብ ነበር በዚህም ጊዜ ፈረንጆቹ አየሉ ነገር ግን ያገሩ ሰዎችም ከነሱ የባሰ ከፋት ሰሩ እንጅ ፈረንጆቹ ብቻቸውን አልነበረም የከፉት የካቶሊከ ሃይማኖት የተቀበሉት ኦርቶዶከሶች የመንበረ ጴጥሮስን አውነተኛዋን ሃይማኖት ከደዋልና የአግዚያብሔር ጠላቶች ናቸው አሉ ስለዚህም አሳደዱአቸው ኦርቶዶክሶችም ለሃይማኖታቸው እንዲሁ አደረጉ እግዚያብሔር የሰዎች ጠባቂ ከሆነ ለምን ፍጥረታቸው እንዲህ ከፋ ብየ አሰብኩ በአርያም የሚያውቅ አለን ። ነገር ግን እኔ በተፈጠርኩ ጊዜ አልኖርኩም አባት አናቴ ፈጠሩኝ ብልም እንደገና ወላጆችና የወላጆችን ወላጅወላጅ የሌላቸው በሌላ መንገድ ወደዚህ ዓለም የመጡትን እንደኛ ያልተወለዱትን የፊተኞቹ ድረስ ፈጣሪያቸውን አፈልጋለሁ አነርሱም ቢወለዱ የፈጠራቸው አንድ ህላዌ አለ ከማለት በቀር የጥንት መወለጃቸውን አላውቅም ያለና በሁሉም የሚኖር የሁሉ ጌታ ሁሉን የያዘ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዓመቱ አማይቆጠር አማይለወጥ ያልተፈጠረ ፈጣሪ አለ አልኩ ፈጣሪስ አለ ፈጣሪ ባይኖር ፍጥረት ባልተገኘ አልኩ እኛ ብንኖር ፍጡራን እንጅ ፈጣሪዎች አይደለንም የፈጠረ ፈጣሪ አለ አንል ዘንድ ይገባናል ይህም የፈጠረን ፈጣሪ አዋቂና ተናጋሪ ካልሆነ በቀር ከዕውቀቱ በተረፈ አዋቆዎችና ተናጋሪዎች አድርጎ ፈጥሮናል ሁሉን ፈጥሯል ሁሉን ይይዛልና እርሱ ሁሉን ያውቃል ፈጣሪየ ወደ አርሱ ስፀልይ ይሰማኛል ብየ ሳስብ ትልቅ ደስታ ተደሰትኩ በትልቅ ተስፋም እየፀለይኩ ፈጣሪየን በሙሉ ልቤ ወደድኩት ጌታየ ሆይ አንተ ሃሳቤን ሁሉ ከሩቅ ታውቃለህ አልኩት አንተ የመጀመሪያየ ነህ የመጨረሻየን ሁሉን አወቅህ መንገዴንም ሁሉ አንተ አስቀድመህ አወቅህ ስለዚህም ከሩቅ ታውቃለህ ይሉሃል እኔ ሳልፈጠር ሀሳቤን ያውቃልና ፈጣሪየ ሆይ እውቀትን ስጠኝ አልኩ ስለ ሃይማኖት ምርመራና ፀሎት በኋላም ይህ በቅዱስ መፅሃፍት የተፃፈ ሁሉ እውነት ይሆን። ብየ አሰብኩ በጣም አላወኩምና የተማሩና ተመራማሪ ሰዎች እውነቱን እንዲነግሩኝ ሄጄ ልጠይቃቸው ብዮ ብዙ አሰብኩ እንደገናም ሰዎች በየልባቸው ያለውን ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ይመልሱልኛል ብየ አሰብኩ ሰው ሁሉ የኔ ሃይማኖት እውነተኛ ናት ይላል በሌላ ሃይማኖት የሚያምኑ ሐሰተኞች የእግዚያብሔር ጠላቶች ናቸው ዛሬም ቢሆን ፈረንጆች ሃይማኖታችን መልካም ናት ሃይማኖታችሁ ግን መጥፎ ናት ይሉናል አኛም መልሰን እንዲዚህ አይደለም የናንተ ሃይማኖት መጥፎ የኛ ሃይማኖት ግን መልካም ናት እንላቸዋለን እንደገናም የእስልምና የአይሁድ አማኞችን ብንጠይቃቸው እንዲሁ ይሉናል በዚህም ከርክር ፈራጅ ማን ይሆናል ሰዎች ሁሉ እርስ በአርሳቸው ወቃሾችና ተወቃሾች ሆነዋል አንድ አንኳን ከሰው ልጅ የሚፈርድ አይገኝም እኔ መጀመሪያ ስለብዙ ሃይማኖቶች ጉዳይ አንድ የፈረንጅ መምህር ጠየኩ እሱ ግን ሁሉን አንደራሱ ሀይማኖት አድርጎ ፈታው ኋላም አንድ ትልቅ የኢትዮጵያ መምህር ጠየኩ እርሱም ሁሉን እነደ ሃይማኖቱ አድርጎ ተረጎመው አስልምና እና አይሁድንም ብንጠይቅ እንዲሁ እንደ ሃይማኖታቸው ይተረጉማሉ ታዲያ እውነት የሚፈርድ የት አገኛለሁ። ብየ አሰብኩ የሚዋሹም መሰለኝ የሚያወቁ እየመሰላቸው ምንም አያውቁምና የሚያውቁ ይመስላቸዋል ስለዚህ እውነትን ለማግኝት ብለው አይመረምሩም ዳዊት እንዳለው ልባችን እንደወተት ረካ ከአባቶቻቸው በሰሙት ልባቸው ረከቷል እውነት ወይም ሀሰት ሊሆን ይቸላል ብለው አልመረመሩም እኔም ጌታ ሆይ ፈርድህን አንዳውቅ ያሳመንከኝ ይገባኛል አልኩ አንተ በእውነት ቅጣኝ በምህረትህም ገስፀኝ አንተ አዋቂ አድርገህ የፈጠርከኝ ጥበበኛ አድርገኝ እንጅ የዋሾ መምህራንና የሐጢያት ቅባት እራሴን አልቀባም እኔ አዋቂ ብሆን ምን አውቃለው ብየ አሰብኩ ከፍጥረት ሁሉ የሚልቅ ፈጣሪ እንዳለ አውቃለሁ ከታላቅነቱ የተረፈ ታላላቅን ፈጥሯልና ሁሉንም የሚያውቅ ነውና ከአዋቂነቱ በተረፈ አዋቂዎች አድርጎ ፈጥሮናልና ለርሱ ልንሰግድለት ይገባል እርሱ የሁሉ ጌታና ሁሉንም የያዘ ነውና ወደርሱ በፀለይን ጊዜ ይሰማናል አግዚያብሄር አዋቂ አድርጎ የፈጠረኝ በከንቱ አይደለም አንዲህ አድርጎ የፈጠረኝ እንድፈልገውና አርሱ በጥበቡ በፈጠረኝ መንገድ እንዳውቀው እስካለሁም ድረስ እንዳመሰግነው ነው ብየ አሰብኩ ሰዎች ሁሉ ሀሰት ካልሆነ በስተቀር ስለምን እውነት አይናገሩም ብየ አሰብኩ የሰው ፍጥረት ታካችና ደካማ መሰለኝ ሰው ግን ፍቅርን ቢወዳትና በጣም ቢያፈቅራት የተሸሸገውንም ፍጥረትን ቢያውቅ ይወዳል ይህም ነገር አጅግ ጥልቅ ነውና በትልቅ ድካምና ትዕግስት ካልሆነ በስተቀር አይገኝም ጠቢቡ ሰለሞን ይፊፀ ዕሥሦ ፅሰተርደረሃውፖ ቻታ ጥ ሐመረሰሐግኖ ሥሐመመርመርሮ ሰፊ ጠሥ። እንዲሁም መሐመድ የማዛችሁ ከእግዚያብሔር የተቀበልኩትን ነው ይላል መሐመድን መቀበል የሚያስረዱ ተዓምራት ፀሐፊዎች አልጠፉምና ከሱም አመኑ አኛ ግን የመሐመድ ትምህርት ከአግዚያብሔር ሊሆን እንደማይችል አናውቃኃለን የሚወለዱ ሰዎች ወንድና ሴት ቁጥራቸው ትከክል ነው በአንድ ሰፊ ቦታ የሚኖሩ ወንድ ሴት ብንቆጥር ለእያንዳንዱ ወንድ አንዲት ሴት ትገኛለች እንጂ ለአንድ ወንድ ስምንት ወይም አስር ሴቶች አይገኙም የተፈጥሮ ህግም አንዱ ከአንዲት ጋር እንዲጋቡ አዚል አንድ ወንድ አስር ሴት ቢያገባ ግን ዘጠኝ ወንዶች ሴት የሌላቸው ይቀራሉ ይህም የፈጣሪን ስርዓትና ሕገ ተፈጥሮን የጋብቻንም ጥቅም ያጠፋል አንድ ወንድ ብዙ ሴቶች ሲያገባ ይገባዋል ብሎ በእግዚያብሔር ስም ያስተማረ መሐመድ ግን ትከከል ነው አልልም ከእግዚያብሔር ዘንድ አልተላከም ጥቂት ስለጋብቻ ሕግ መረመርኩ የቀረውን ብመረምርም በሀገ ኦሪትና በከርስትና በአስልምና ሕግ ፈጣሪ በልቦናችን ከሚገልፅልን እውነት እና እምነት አይስማማም ብዙ አይገኝበትም አልኩ ፈጣሪ ለሰው ልጅ ከፉና መልካም የሚለይበት ልቦና ሰጥቶታል በብርሀን ብርሀን እናያለን እንደተባለውም የሚገባውን የማይገባውን ሊያውቅ እውነትን ከሐሰት እንዲለይ ነው ስለዚህ የልቦናችን ብርሀን እንደሚገባ በእርሱ ብናይበት ሊታይልን አይችልም ፈጣሪያችን ይሄን ብርሃን የሰጠን በርሱ አንድንድን ነው አንጅ እንድንጠፋ አይደለምየልቦናችን ብርሀን የሚያሳየን ሁሉም ከእውነት ምንጭ ነው ሰዎች ከሐሰት ምንጭ ነው ቢሱን ግን ሁሉን የሰራ ፈጣሪ ቅን እንደሆነ ልቦናችን ያስረዳናል ፈጣሪ በመልካም ጥበቡ ከሴት ልጅ ማህፀን በየወሩ ደም አንዲፈስ አዚል ሙሴና ከርስቲኖች ግን ይህን የፈጣሪ ጥበብ አርኩስ አደረጉት እንደገና ሙሴ እንዲህ ያለቸውን ሴት የተገናኛት ያረከሳል ይህም የሙሴ ህግ የሴትን ኑሮ በሙሉና ጋብቻዋን ከባድ አድርጎታል የመራባትንም ህግ አጥፍቷል ልጆችንም ከማሳደግ ከልከሎ ፍቅርንም ያፈርሳል ስለዚህ ይህ የሙሴ ሕግ ሴትን ከፈጠረ ሊሆን አይችልም አንደገናም የሞቱትን ወንድሞቻችንን ልንቀብራቸው ተገቢ መሆኑን ልቦናችን ይነግረናል በድኖቻቸውም በሙሴ ጥበብ ካልሆነ በስተቀር ከመሬት የተፈጠርንበት ወደመሬትም ልንገባባዘዘን በፈጣሪያችን ጥበብ እርኩሳን አይደሉም ነገር ግን ለፍጥረት ሁሉ እንደሚገባ በትልቅ ጥበብ የሰራ እግዚያብሔር ስርዓቱን አያረከሳውም ሰው ግን የሐሰትን ቃል እንዲያከብር ብሎ ሊያረከሰው ይፈልጋል እንደገና ወንጌል አባት እና አናቱን ምሽቱን እና ልጁን ያልተወ ለእግዚያብሔር የተገባ አይሆንም ይላል ይህ መተው የሰውን ፍጥረት ሁሉ ያጠፋል እግዚያብሔር ግን ፍጥረቱን በማጥፋት አይደሰትም አባትና እናትም በሽምግልናቸው ጊዜ እረዳት አተው አንዲሞቱ መተው ትልቅ አበሳ መሆኑን ልቦናችን ያሳየናል እግዚያብሔርም አመፃን የሚወድ አምላክከ አይደለም ልጆችን መተው ግን ከበረሃ አራዊት ይብሳሉ ምሽቱ ስታመነዝር የሚፈታት ሁሉ የፈጣሪን ስርዓትና የተፈጥሮን ሕግ አፍርሷል ስለዚህም ወንጌል በዚህ ስፍራ የሚለው ከእግዚያብሔር ሲሆን አይችልም እንደገና በእስልምና ሰው እንደ እንስሳ ሊሸጥና ሊገዛ ይገባል ይላሉ ፈጣሪያችን እንደ ወንድሞች አስተካከሎ ከፈጠረን ከሰዎች ፈጣሪ ይህ የአስልምና ህግ ሊወጣ አይቸልም ልቦናችን ያውቃል እነሱ ግን ደካማን ሰው የሐይለኛ ሰው ንብረት አደረጉት አዋቂው ፍጥረትንም ካላዋቂው እንስሳ ጋር አስተካከሎት ይህ ከእግዚያብሔር ዘንድ ሊወጣ ይችላልን ። ፍጡር አለ ፈጣሪ ሊገኝ እንደማይችል ስለዚህም ፈጣሪ እንዳለ እውነት ነውና ነው ይህ የምናየው ሁሉ ፍጡር እንደሆነ የሰው ሁሉ ልቦና ያውቃል ሰዎች ሁሉ በዚህ ይስማማሉ ነገር ግን ሰዎች ያስተማሩትን ሃይማኖት በመረመርን ጊዜ በውስጡ ሐሰት ከእውነት ጋር ተቀላቅሎበታል ስለዚህ እርስ በርሱ አይስማማም ሰዎች እርስ በርሳቸው አንዱ ይህ እውነት ነው ሲል ሁለተኛው አይደለም ሐሰት ነው ሲል ይጣላሉ ሁሉም የእግዚያብሔርን ቃል የሰው ቃል እያደረጉ ይዋሻሉ እንደገናም የሰው ሃይማኖት ከአግዚያብሔር ብትሆን ከፉዎችን ከፉ እንዲያደርጉ እያስፈራራች መልካም አንዳያደርጉ ትፈቅድላቸው ነበር ደጎችንም በትዕግስታቸው ታፀናቸው ነበር ለኔም እንዲህ ያለው ሃይማኖት ባሏ ሳያውቅ በምንዝርና የወለደች ሴትን ትመስለኛለች ባሏ ግን ስለመሰለው በሕፃኑ ይደሰታል እናቲቱንም ይወዳታል በዝሙት እንደወለደችው ባወቀ ጊዜ ግን ያዝናል ሚስቱንም ልጅዋንም ያባርራል እንዲሁም እኔም ሀይማኖቴን አመንዝራና ዋሾ መሆኑዋን ካወኩ በኋላ ስለርሷ በዝሙት ስለተወለዱ ልጆቿ አዘንኩ እነሱ በጠብ በማሳደድ በመማታት በማሰር በመግደል ወደዚህ ዋሻ ያባረሩኝ ናቸው ነገር ግን የከርስቲያን ሃይማኖት አውነት ናት አንዳልል በዘመነ ወንጌል አንደተሰራ ከፉ አልሆነችም የምህረትን ሥራ በሙሉ እርስ በርስ መፋቀርን ታዛለች በዚህ ዘመን ግን የሀገራችን ሰዎች የወንጌልን ፍቅር ወደ ጠብና ሃይል ወደ ምድራዊ መርዝ ለወጡት ሃይማኖታቸውን ከመሰረቱ አመፃ እየሰሩ ከንቱ ያስተምራሉ በሐሰትም ከርስቲያኖች ይባላሉ ስለ አምላክ ህግና ስለ ሰው ህግ እግዚያብሔር የገዛ ህዝቡን እንዲያስቷቸው ስለምን ዋሾ ሰዎችን ይተዋል ብዮ አሰብኩ አግዚያብሔር ግን ለሁሉም ለእያንዳንዱ እውነትንና ሐሰትን እንዲያውቅ ልቦና ሰጥቶናል እውነት ወይም ሐሰት እንደፈቃዱ የሚመርጥበት መምረጫም ሰጠው እውነትን ብንወድ ለፍጥረት ሁሉ አስፈላጊና ተገቢ የሆነውን አርሱም እንድናይበት አግዚያብሔር በሰጠን ልቦናችን ውስጥ እንፈልጋት ሰው ሁሉ ዋሾ ነውና አውነትንም በሰዎች ትምህርት አታገጂትም ከእውነት ይልቅ ሐሰትን ብንመርጥ ስለዚህ እኛ በስህተታችን እንጠፋለን እንጂ ለፍጥረት ሁሉ የተሰራው የፈጣሪ ስርዓትና ሕግ አይጠፋም እግዚያብሔር ማንንም በሠራው ሥራ ይጠብቀዋል ከሰው ስራ ግን የእግዚያብሔር ስራ ይፀናል የሰው ስራ ሊያጠፋው አይችልም ስለዚህም ከጋብቻ ይልቅ ምንኩስናን ይበልጣል ብለው የሚያምኑ እነርሱ በፈጣሪ ስራ ፅናት ወደ ጋብቻ ይሳባሉ ፆም ነፍስ እንደሚያፀድቅ የሚያምኑ እነርሱ ደግሞ እረሃብ በበዛባቸው ጊዜ ይበላሉ ገንዘቡን የተወ ፍፁም እንዲሆን የሚያምኑ በገንዘብ ለሚያገኙት ጥቅም ወደ ገንዘብ መፈለግ ይሳባሉ ብዙዎች የሀገራችን መነኩሴዎችም እንደሚደርጉት ከተውት በኋላ እንደገና ይፈልጉታል እንደዚሁ ዋሾዎች ሁላቸው የተፈጥሮን ሥራ ሊያፈርሱ ይፈልጋሉ ነገር ግን ደካማነታቸውን ያሳያሉ እንጂ አይቸሉም ፈጣሪም ይስቅባቸዋል የፍጥረት ጌታም በላያቸው ይሳለቅባቸዋል እግዚያብሔር የእግዚያብሔርን ፍርድ ማድረግ ያውቃልና ሃጥአንም በእጁ ሥራ ወጥመድ ተጠመደ ስለዚህም የጋብቻን ሥርዓት የሚያስነውር መነኩሴ በከፉ በሽታና ፍጥረቱ ባልሆነ በሌላ የሴት አበሳ በዝሙት ተፅኖ ይጠመዳል ገንዘባቸውን የሚንቁ ገንዘብ እንዲያገኙ በሀብታሞችና በነገስታት ዘንድ ግብዞች ይሆናሉ ለእግዚያብሔር ብለው ዘመዶቻቸውንም በሽምግልናቸው በችግራቸው እረዳት ባጡ ጊዜ የተው በነሱ ሽምግልና ጊዜ ሰውና እግዚያብሔርን ወደ ማማት መሳደብ ይደርሳሉ እንደዚሁም የፈጣሪን ሥርዓት የሚያፈርሱ ሁሉ በእጃቸው በሰሩት ወጥመድ ይወድቃሉ እንደገናም እግዚያብሔር ከፋትን ስህተትን በሰው መካከል ይተዋል ነፍሶቻችን በዚህ ዓለም የአግዚያብሔር ጥበብ የፈጠረውን የፈተና ቀን ይኖራሉ ጠቢቡ ሰለሞን ግጂቦጩሴር ደድቃጋ። ፉ ቲደርርረሦሰያ ደይምያፈሰሃው ዲሮርረግምውታ ይላል የሰንበትን ማከበር የሚለው ካልሆነ በቀር አስሩ የአሪት ትዕዛዛት የፈጣሪ ናቸው ሰንበትን ለማከበር ግን ልቦናችን ዝም ይላል ልንገድልና ልንሰርቅ ልንዋሸና የሰው ሚስት ልንሰርቅ ይህን የሚመስለውን ልናደርግ እንደማይገባን ልቦናችን ይነግረናል አንዲሁ ስድስቱ የወንጌል ቃላት የፈጣሪ ፈቃዶች ናቸው እኛ ይህን የምህረት ስራ ሊያደርጉልን አንፈልጋለን በሚቻለን ለሌሎች ልናደርግላቸው ይገባናል ደግሞም በዚህ ዓለም ሕይወታችን ንብረታችን አንድንጠብቅ የፈጣሪ ፈቃድ ነው ከፈጣሪ ፈቃድ ወጥተን በዚህ ሕይወት እንኖራለን በተቀደሰ ፈቃዱ ካልሆነ በቀር ልንተወው አይገባንም እርሱ ፈጣሪያችን ለሁሉ ልቦናና ችሎታ ስለሰጠ ኑሯችንን በዕውቀትና በሥራ እንድናሳምረው ይፈቅድልናል ይህ ካልሆነ በቀር የሕይወታችን ፍላጎት አይገኝም እንዲሁ አንዱ ካንዷ ጋር መጋባትና ልጆች ማሳደግን ፈቅዷል ደግሞም ከልቦናችን ጋር የሚስማማ ለህይወታችንም ለሁሉም የሰው ልጆች ኑሮ የሚያስፈልጉ ሴሎች ብዙ ሥራዎች አሉና የፈጣሪ ፈቃድም አንዲሁ ስለሆነ ልንጠብቀው ይገባናል እግዚያብሔር ፍፁማን አድርጎ አንዳልፈጠረን ልናውቅ ይገባናል ለመፈፀማችን የተዘጋጀን አዋቂዎችና በዚህም ዓለም አስካለን ድረስ እንድንፈፅምና ፈጣሪያችን በጥበቡ ላዘጋጀልን ዋጋ የተዘጋጀን እንድንሆን አድርጎ ፈጠረን በዚህ ምድር ፍፁማንና ብፁዓን አድርጎ ሊፈጥረን ለእግዚያብሔር ይቻለው ነበር ነገር ግን ለመፈፀማችን አምንዘጋጅ አድርጎ ፈጠረን እንጅ እንዲሁ ሊፈጥረን አልፈቀደም ከሞታችን በኋላ ፈጣሪያችን ለሚሰጠን ዋጋ የተዘጋጀን ፍፁማን እንድንሆን በዚህ የፈተና ዓለም መካከል አኖረን በዚህ ዓለም አስካለንም ወደ አርሱ እስኪወስደን ድረስ እየታገስን ፈቃዱን አየፈፀምን ፈጣሪያችን ልናመሰግነው ይገባል የፈተናችንንም ጊዜያቶች እንዲያቀልልን ባለማወቃችን ሠራነውን የእብደት አበሳ እንዲተውልን የተፈጥሮ ሕግጋትን አውቀን እንድንጠብቃቸው ልቦና አንዲሰጠን ወደቸርነቱ እንለምን ፀሎት ደግሞ ላዋቂ ነፍስ አስፈላጊ ነውና ዘወትር ልንፀልይ ይገባናል አዋቂ ነፍስ ሁሉን የሚያውቅና ሁሉን የሚጠብቅ ሁሉን የሚገዛ እግዚያብሔር እንዳለ ታውቃለች ወደ እርሱ እንድትፀልይም ከአርሱ መልካም አንድትለምን ከከፉ እንድትድንና ሁሉን ወደ ሚቸል እጅ እንድትማፀን ወደ እርሱ ትሳባለች አግዚያብሔር ምሁርና ትልቅ ነው የሚሳነውም የለም ከበታቹ ያለውን ያያል ሁሉንም ይይዛል ሁሉን ያውቃል ሁሉን ይመራል ሁሉን ያስተምራል አባታችን ፈጣሪያችን ጠባቂያችን ነው የነፍሳችን ዋጋ ቸርና ይቅር ባይ ችግራችንን ሁሉ የሚያውቅ ነው ለሕይወት እንጂ ለጥፋት አልፈጠረንም በትዕግስታችን ይደሰታል ጠቢቡ ሰለሞን ሄታ ፖይ ሦ ዕታታ ያቂፀኖፖ ኖ ታታ ታሪፖምሯሰያ ዎሥቻ ዕታደቦምሃያ ጪጢደሥምውንም ለጋምደደሪሃው ታታ ምም ይምንፇው ፅሐሜዕናሂ ታሥታን ሦመቆ ዕሥታ ፍፖሪም ቂይም ፇራሪሰይረ ፖሐፖይላል የእግዚያብሔርም ታላቅነቱን እንድናስብ ለስጋችንና ለነፍሳችን አሚያስፈልገንን ለማግኝት ወደ እርሱ እንድንፀልይና እንድናመሰግነው አዋቂዎች አድርጎ ፈጠረን ይህም ሁሉ በሰው ልብ ያገባ ፈጣሪያችን ዕውቀት ያስተምራልና አንዴትስ ሀሰት ሊሆን ይትላል በሸ ር አ መክ እኔም እነደገና በሙሉ ልባችን በፍቅርና በዕምነት በትዕግስትም ወደ እርሱ በፀለይን ጊዜ እግዚያብሔርም ፀሎታችንን እነደሚሰማ በሌላ መንገድ አወኩ እኔ በልጅነት ጊዜየ ስለ እግዚያብሔር ሥራ ምንም ሳላስብ ወደ አርሱ ስፀልይ ሃጢያተኛ ነበርኩ ለአዋቂ ፍጥረት የማይገባ ብዙ በደል በደልኩ ስለሃጢያቴም ሰው ከእርሱ ሊያመልጥ ወደማይቸለው ወጥመድም ወደኩ ፈፅሜ ልጠፋም ቀረብኩ የሞት ፍርሃትም መጣብኝ የዚያን ጊዜ ወደ እግዚያብሔር ተመልሼ እርሱ የማዳንን መንገድ ያውቃልና አንዲድነኝ ብየ ወደ እርሱ መፀለይ ጀመረኩ እግዚያብሔር ጌታ ሆይ ለሃጢያቴ እፀፀታለሁ ፈቃድህንም ለማድረግ አፈልጋለሁ አልኩበሙሉ ልቤም ብዙ ጊዜ ፀለይኩ እግዚያብሔር ሰማኝና ፈፅሞ አዳነኝ ወደ አርሱ ተመልሼም በፍፁም ልቤ አመሰገንኩት በመዝሙረ ዳዊት ኃግሂቦቤሴረ በኋመናሃ ቃ ዕምረ መሮርሮታም የሚለውንም ዘመርኩ ደገምኩት ይህም መዝሙር ስለኔ የተፃፈ መሰለኝ አንደገናም ልድን ካልሆነ በስተቀር አልሞትም የእግዚያብሔርንም ሥራ አነግራለሁ አልኩ ነገር ግን ዘወትር ወደ ንጉስ የሚያሳጡኝ ነበሩ ይህ ሰው ጠላትህ ነው ለፈረንጆቹም ጠላታቸው ነው ይሉታል የንጉሱም ቁጣ በላየ አንደተቃጠለ አወኩ አንድ ቀንም የንጉሱ መላከተኛ መጥቶ ንጉሱ ፈጥነህ ወደ እኔ ና ይልሃል አለኝ አኔም እጅግ ፈራሁ የንጉስ ሰዎች ስለሚጠብቁኝም ልሸሽ አልቻልኩም ባዘነ ልቤም ሌሊት በሙሉ ፀለይኩ ሲነጋም ተነስቼ ሄጄ ወደ ንጉሱ ገባሁ አግዚያብሔርም የንጉሱን ልብ ስላራራው በፍቅር ተቀበለኝ ስለፈራሁት ነገርም ምንም አላለኝ ነገር ግን ስለትምህርትና የመፅሃፍት ነገር ጠየቀኝ አንተ የተማርከ ሰው ነህ እነርሱም በጣም የተማሩ ናቸው ፈረንጆቹን ትወዳቸው ዘንድ ይገባሀል አለኝ ስለፈራሁትም እሺ ፈረንጆቹ በእውነት የተማሩ ናቸው አልኩት ከዚህም በኋላ ንጉሱ አምስት ወቄት ወርቅ ሰጥቶ በሰላም ሰደደኝ ከንጉሱ ወጥቼ አተደነቅኩ ለኔ መልካም ስላደረገልኝ እግዚያብሔርን አመሰገንኩት አነደገናም ወልደ ዩሃንስ ባሳጣኝ ጊዜ ልሸሸው ስለተቻለኝ አንደፊተኛው እንዲያድነኝ ሳልፀልይ ሸሸሁ ሰው እግዚያብሔርን በከንቱ ሳይፈታተነው የሚቻለውን ሁሉ ሊያደርግ ይገባል አሁን ግን ስለሸሸሁና በዋሻየም ስለሁንኩ ቀድሞ ያላሰብኩትን እንዳስብና ለነፍሴም ትልቅ ደስታ አሚያስደስታት እውነትን እንዳወኩ ወደ ፈጣሪየ የመመለስ ፍፁምነት ምከንያት ስላገኝሁ ፈጣሪየን አመሰገንኩ ፍርድህን እንዳውቅ ያሳመምከኝ ይገባኛል ከመምህራን ጋር በነበረኩ ጊዜ ካስተዋለኩት ይልቅ ብቻየን በዋሻየ ሆኞ በጣም አስተውያለሁና ይህም የፃፍኩት እጅግ ትንሽ ነው ይህን የመሳሰሉትን ብዙ እያሰብኩ በዋሻየ ቆየሁ እግዚያብሔርም የፍጥረታቱን ምስጢር ለማወቅ ጥበብ ስለሰጠኝ አመሰገንኩት ነፍሴም የእግዚያብሔርን ጥበብ ሥራ ከማሰብ በቀር ሁሉን እየናቀች ወደ እርሱ ትሳብ ነበር በሰፊው ልቤም በዳዊት መዝሙር ሁልጊዜ እፀልይ ነበር ይህ ፀሎት በጣም ይጠቅመኛልና ሕሊናየንም ወደ እግዚያብሔር ያነሳሳልኛል በመዝሙረ ዳዊት ከሕሊናየ ጋር የማይስማማ ባገኝሁ ጊዜ እኔ ተርጉሜ በዕውቀቴ አስማማዋለሁ ሁሉም ያምርልኝ ነበር እንደዚህ እያልኩ በፀለይኩም ጊዜ በእግዚያብሔር መታመኔ ይጨምር ነበር ሁልጊዜም አንደዚህ እል ነበር ታ ፖይ ፅቀተ ፅማች ሰሐመናየም ያነ። ፈጣሪ ታላቅነቱን እንድናውቅ ከሰጠን ህሊና ይልቅ አጅግ ዝቅ ያለና የተናቀ ግዑዝ ባህሉን ካልሆነ በቀር ሊገልፅልን አይችልም ጌታ ሆይ እኔ በፊትህ ደህና ምስኪን ነኝ ስላንተ የማይገናኝን አንዳውቅና ታላቅነትህን አንዳደንቅ አዲስ ምስጋና ሁልጊዜ እንዳመሰግንህ ልቦና ስጠኝ የዘርዓ ያዕቆብ ወደ እንፍራንዝ መግባት በ ዓም ሱስንዮስ ሞቶ ልጁ ፋሲለደስ ነገሰ እርሱም በመጀመሪያ ፈረንጆቹን ወደደ ግብፃዊያንንም አላባረራቸውም በዚህ ምከንያት በኢትዮጵያ ሁሉ ሰላም ሆነ የዚያን ጊዜ ከዋሻየ ወጥቼ መጀመሪያ ወደ አማራ አገሮች ሄድኩ ኋላም ወደ በጌምድር ተመለስኩ ለሁሉም በፈረንጆች ጠላትነት በሱስንዮስ ዘመን ከተባረሩት መነኮሳት አንዱ መሰልኳቸው ስለዚህም ወደዱኝና ምግብና ልብስም ሰጡኝ በዚህ ሁኔታ ከአገር ወደ አገር ስመላለስ የካህናቶቿን ከፋት አውቃለሁና ወደ አከሱም መመለስን አልወደድኩም ሰው የሚሄድበት ከእግዚያብሔር እንደሚታዘዝ አሰብኩ ጌታ ሆይ የምሄድበትን መንገድና የምኖርበትን ነገር ምራኝ አልኩት ወደጎጃም ምድር ተሻግሬም ለመኖር አሰብኩ ነገር ግን እግዚያብሔር ወደአላሰብኩት መራኝ አንድ ቀን ወደ እንፍራንዝ አገር ወደ አንድ ጌታ ሰው የእግዚያብሔር ሀብት ነውና ሀብቱ ወደ ተባለ ደረስኩ በዚያውም አንድ ቀን አደርኩ በማግስቱም አከሱም ወዳሉት ዘመዶቹ ደብዳቤ እንድልከ ከእርሱ ቀለምና ወረቀት ለመንኩት ይህ ሰውም ሦ ሠሪ ወፀፖአለኝ ዎሪ ፉምአልኩት አ ጋር ፓፖ ፇ ሦፇምጠያ ይፃሯም መሃሆመሂን ያፍኝና ዎጋጋ ዳታፖዕሥብሎ ተናገረኝ ጂአልኩት የድካሜንም ፍሬ የምመገብበትን መንገድ ስላሳየኝ እግዚያብሔርን በልቤ አመሰገንኩት እውነት ባስተምር ሰዎች ሲጠሉኝና ሊከሱኝ ሊያባርሩኝ ካልሆነ አይሰሙኝምና ወደ ቀድሞ ሊቅነቴ ተመልሼ ሐሰትን ማስተማር ጠላሁ እኔ ግን ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅርና በሰላም መኖርን ወደድኩ በሃጥአን ቤት ከብሬ ከምኖር ግን ከሰው ተለይቼ የድካሜን ፍሬ እየተመገብኩ እግዚያብሔር በሰጠኝ ጥበብ ተሸሸጌ አልባሌ መስየ መኖርን መረጥኩ በጥቂት ጊዜም ቀለምና ብራና አዘጋጅቼ አንድ የዳዊት መዝሙር ፃፍኩ ፅህፈቴም ያማረች ናትና ጌታዮ ሀብቱና ሁሉም አይተዋት ተደነቁ ጌታዮ ሀብቱም ደሞዜን አንድ መልካም ልብስ ሰጠኝ ደግሞም ወልደ ሚካኤል የተባለ የጌታየ ሀብቱ ልጅ ላባቴ እንደፃፍከው ለእኔም ፃፍልኝ አለኝና ፃፍኩለት አንድ በሬና ሁለት ፍየሎችም ሰጠኝ ከዚህ በኋላ ብዙዎች ወደ እኔ ዘንድ መጥተው ዳዊትና ሌሎች መፅሐፍትን ደብዳቤዎችን አፃፉ በዚያ አገር ካለ እኔ በቀር ሌላ ፀሐፊ አልነበረምና ልብስ ፍየሎች እህል ጨውና ሌላም እነርሱን የመሳሰሉ ሰጡኝ ለጌታየ ሀብቱም አንድ ወልደ ገብርኤል ተሰማ የተባለና ሁለተኛ ወልደ ህይወት ምትኩ የተባሉ ሁለት ልጆች ነበሩት አባታቸው ሀብቱም የሚበቃህን ምግብ አሰጥሃለሁና በአጅህ ፅፈህ የምታፈራውን ላንተ ይሆናልና የዳዊትን ንባብ አስተምራቸው አለኝ አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ አልኩት ነገር ግን ካንተ በቀር ዘመድ የለኝምና በአባቴና በእናቴ ዘመዶችም ፋንታ ዘመድ ሁነኝ አልኩት ስለ ሕጋዊ የፈቃድ ጋብቻ ይህ መንገድ ወደ አበሳ ይስባልና ሴት የሌላቸው ወንድ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንደማይገባው አወኩ ለፊተኞቹ ሴት ታስፈልጋቸዋለች እንጅ ወንድ ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም እንደተባለው በሰሩት ወጥመዳቸው እንዳይጠመዱ ሰዎች ተፈጥሯቸውን ከደው ሊኖሩ አይገባቸውም ጌታየ ሀብቱም የዘመኑን ከፋት ፈርቼ መሰልኩ አንጂ መነኩሴ አይደለሁም አልኩት ለጌታየም ሂሩት የተባለች አንዲት ቤተሰብ ነበረች ምግባረ መልካምና ልባም ትዕግስተኛ እንጂ ደም ግባታም አይደለችም ጌታየ ሀብቱም ይሆቻ ፈቻ ሟዕም ድፖንች ሰጠኝ አልኩት ጓደ ዕዳ ሬባ ባፈ ዲይርተ።