Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ለዚህም ዋንኛው መንስኤ በምድራዊ ሰማያትና በሰማያተ ሰማያት እና በምድራዊ ሰማያት መካከል ግንኙነት የሚፈጠርባቸው ታላቅ መንፈሳዊ ሃይል ያላት ጽላት ታበተ ጽን እንደሆነች ነው ይሁን እንጂ ለምድራችን የመጀመርያዋ ጽላት አዳም ከገነት እንደተመለሰ ቅዱሳን መልአክት ያስተማሩትን የሰማየ ሰማያት ብሎም የምድራዊ ሰማያት ምስጢራትና ጥበባት ለልጆቹ ኢትዮጵያውያን ማስተማርያ ይሆን ዘንድ በእግዚብሔር ፈቃድ በድንጋይ ላይ በግዕዝ ቋንቋ ጽፎ አስቀመጠላቸው ይህም የህይወት መጽሀፍ ወይም መጽሀፈ ራዚኤል ብለን የምንጠራው ነው። ጥንታውያን ኢትዮጵያውያንም ይህን መጽሀፍ አንብበው በመረዳት ዘመናት የማይሽራቸውን ቅርሶች ትተውልን አልፈዋል ይህ መጽሀፍ ሰድስተኛ ከሆነው ጥበብ ከተሰኘው ምስጢረ ጥበብ በዘመናችን ቴክኖሎጂ የምንለው ነው። እነዚህ ስድስቱ ምስጢረ ጥበባት እና ስድስቱ የክብር እቃዎች ከምድራችን ብቻ ሳይሆን ከዓለማችን እንዲሰወሩ የተደረጉት ለሰባት መቶ ዓመታት በርሃብ በጦርነት በመከፋፈል ያሳለፍነው እኛው ራሳችን የአባቶቻችንን መንገድ አንከተልም ብለን ጠላቶቻችን ባዘጋጁልን ወጥመድ ውስጥ በመውይደቃችን ነው።
ከነዚህ ቦታዎች አራቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ቀሪዎችም ቢሆን ከሰባት መቶ ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ግዛት በነበሩት የመን ሲና በርሃ እና ኢየሩሳሌም ግዛቶች ውስጥ ይገኛሉ በዚህም የተነሳ አባቶቻችን ሰማያዊና ምድራዊ የሆነውን ጥበብ እና ምስጢራት ከቅዱሳኑ ማግኘት ችለዋል ይህም ዛሬም ድረስ ለዓለም እንቆቅልሽ የሆኑ የጥበብ ስራዎችን ሰርተውልን እንዲያልፉ አስችሏቸዋል ለአብነትም በሶስት የተለያዩ ቀለማት የተገነቡትንና በራሳቸው በአባቶቻችን የተሰወሩትን ከግብጽ ፒራሚዶች በመጠናቸው የሚበልጡትን ፒራሚዶች በርካታ ከቋጥኝ ድንጋይ የተፈለፈሉ አብያተ ክርስትያናትን በርካታ የተሰወሩ ከተሞች እንዲሁም በርካታ የኣለማችንን ምድራዊ እና ሰማያዊ ጥበቦችን ያስቀመጡበትን ጥንታዊ መጻህፍትን መጥቀስ ይቻላል ቅዱሳን መላእክት አባታችን አዳምን የምድራዊ ሰማያትን እና የሰማያተ ሰማያትን ምስጢራት እና ጥበባትን አስተምረውታል ታዲያ አባታችን አዳም ርስት ተደርጋ በተሰጠችው ኢትዮጵያ እና የምድር ማእከላዊ ስፍራ በሆነው የረር በሚገኘው ተራራ ላይ ለኢትዮጵያውያን ልጆቹ ያገኘውን የረቀቀ የሰማያተ ሰማያትና የምድራዊ ሰማያትን ጥበቦች ስላስተማራቸው በዘመናቸው ሃያል እና ገናና ህዝቦች ሆነው አልፈዋል ኢትዮጵያውያን እስከ ሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ድረስ ሀያላን ሆነው የዘለቁበት ምክንያት ለዚህ ትውልድ እና ለተቀረው ዓለም የተሰወሩትን ስድስቱን ምስጢራትን ተረድተው በመጠበቃቸው ነው። በመሆኑም የአባቶቻችን የሃይል ሚዛን ስለነበሩት ስድስቱ ምስጢረ ጥበባት ብሎም ስለሰባቱ የምድራችን የክብር ቦታዎች ከማንሳታችን አስቀድመን የአባቶቻችን አስተምህሮት የሆነውን አምሳላዊ ንድፈ ሀሳብ መሰረት በማድረግ ስለ አስራ ሁለቱ ሰማየ ሰማያት እና ምድራዊ ሰማያት እና ከየረር ተራራና ከሌሎቹ ስድስት የክብር ቦታዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንመለከታለን በተምሳሌታዊ እውቀት ትንታኔ መሰረት ማንኛውም ፍጥረት የተፈጠረበት በፍጻሜ ላይ የሚገኝ አሳብ አለው በዚህ መሰረትም ምድራዊ ሰማያት የሰማያተ ሰማያት አምሳል ናት በመሆኑም በሰማያተ ሰማያት የሚገኙ ስፍራዎች የፈጣሪያችን መገኛ የሆነውን ማእከላዊ ስፍራ በአራት አቅጣጫ ከበውት እንደሚገኙ እንዲሁ የምድራዊ ሰማያት ክፍል የሆኑት አስራሁለት ስፍራዎች በአራት አቅጣጫ የፈጣሪ ማደሪያ አምሳል በሆነችው ጸሀይ ዙሪያ ይገኛሉ ይህን በተምሳሌታዊ ንድፈ ሃሳብ መሰረት ድርሳነ ዑራኤልን ጨምሮ በተለያዩ በተለያዩ ቅዱሳን አዋልድ መጻህፍት እና አባቶች የምድር እምብርት ተብሎ የተጠቀሰው በየረር ተራሮች መሃከል የሚገኘውን ምስጢራዊ ተራራ መሀከል አድርገን ስናጠና ቦታውን በአራት አቅጣጫ የሚከቡትን የምድራዊ ሰማያት አቀማመጥ እንረዳለን ። እኛ ኢትዮጵያውያን የቀን አቆጣጠራችንም መሰረቱም ይህ የጊዜ አቆጣጠር ሲሆን አባታችን አዳም ወደ እዚህ ምድር ከገነት ተመልሶ ከመጣበት ጊዜ አንስቶ የተቆጠረ ነው ይህም በእኛ ስሌት ስድስት ሺ ዓመታትን ሰባት ሺ ዓመታት ውስጥ ይገኛል ይህ በሰማየ ሰማያት ስድስተኛው ቀን አልቆ ሰባተኛው ቀን ላይ መሆኑ ነው አዳም ወደዚህ ምድር ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት በርካታ ጊዜያትን ይህች ምድራዊ ሰማያት አሳልፋለች ለዚህም ማስረጃችን አቡሻህር የተሰኘው መጽሃፋችን ነው አባታችን አዳም አትብላ የተባለውን እጽ በልቶ ከገነት በተባረረበት ወቅት ቅዱሳን መላእክት በምድራዊ ሰማያት በሁለተኛው ምድብ ከሚገኘው ስፋራ ወደአንደኛው ምድብ ወደምትገኘው ወደዚች ምድር በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አማካይነት ሲመጣ መጀመርያ ያረፈውና መጽናኛ ትሆነው ዘንድ ርስት ተደርጋ የተሰጠችው ስፍራ በየረር ተራሮች መካከል በምትገኘው እና የምድር እምብርት በሆነችው ተራራ ላይ ነው ይህን ተራራ መሀከል አድርገን በስተሰሜን ስንመለከት የበርካታ ቅዱሳን አባቶች መገኛ የሆነው ደን እና ዋሻዎች እናገኛለን እነዚህ የበቁ የተሰወሩ አባቶች የሚገኙበት ስፍራ በሁለተኛው የምድራዊ ሰማያት ምድብ በሆነው ክፍል ብሄረህያውን የሚገኝበት ቦታ እንደሆነ ልብ ይበሉ በተጨማሪ ሰባቱ ምድራዊ ሰማያት የበርካታ አእዋፋት መኖርያ ሲሆን በዚሁ አቅጣጫ በርካታ አሞሮችና አእዋፋት ወደየረር ማእከላዊ ቦታ ይመጣሉ ይህም አዳም ገነት በነበረበት ወቅት ከሌሎቹ ሰማያት ሊጠይቁት እንደሚመጡት ማለት ነው ይህን አንድምታ ስንፈታው በዚህ ተራራ ስር ከሚገኙት ዋሻዎች በአንዱ የሚገኘውን የበቃ ባለትንቢቱን አባት ለመጠየቅ እና ለመመልክት ከቅዱሳን ስፍራ አእዋፋት እና ቅዱሳን ይመጣሉ። የምድር እምብርትየረርነ እና የኢትዮጵያ ትንሳኤ የተለያዩ ከብሔረ ህያዋን የሚመጡ ቅዱሳን አባቶችን ጨምሮ ቅዱሳን መላእክት ለመልእክት ወደምድር ሲመጡ የሚያርፉባቸው ሰባት የተመረጡ ቦታዎች አሉ እነዚህ የክብር ቦታዎች በሰማያተ ሰማያት እና በምድራዊ ሰማያት መካከል ግንኙነት የሚፈጠርባቸው ታላቅ መንፈሳዊ ቦታዎች ናቸው ከእነዚህ ሰባት የክብር ቦታዎች መካከል አራቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አንደኛው የመን ውስጥ ሌላው በሲና በርሃ የተቀረው ደግሞ በእስራኤል ምድር ውስጥ ይገኛል እነዚህ የተቀሩት ቦታዎች ቀድሞ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ይገኛሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት የክብር ቦታዎች ዋንኛውና አንደኛው በየረር ተራሮች መካከል የሚገኘውና በበርካታ ቅዱሳን መጽሃፍት የምድር እምብርት በተጨማሪም የአዳም ርስት ሃገር ብለን የምንጠራው ስፋራ ነው። ልብ ይበሉ ጊዜው ደርሷል ኢትዮጵያ ትንሳኤ ቀርቧል ስድስቱ ምስጢራተ ጥበባትና ስድስቱ የክብር እቃዎች መገለጫ ምልክቱም ይህ ነው እኔ እና እናንተ ይህን መነጋገር መጀመራችን ስድስቱ ምስጢረ ጥበባት እና የዓለማችን የሃይል ሚዛን አባታችን አዳም አትብላ የተባለውን እጽ በልቶ ከገነት በወጣ ወቅት የአዳም የቅርብ ወዳጅ የሆነው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልና ሌሎች መላእክት ከገነት ይዘውት እንደተመለሱ ሀዘኑን እና ትካዜውን ያስረሳለታል ብለው ያሰቡት ቦታ ማለትም አዳም ርስት ብለው የጠቀስነውን በየረር በሚገኘው እምብርት ቦታ አስቀምጠውታል ታዲያ የአዳምን የአላዋቂነት እና የየዋህነት ባህሪውን ተረድቶ ሳጥናኤል በቀላሉ እንደረታው ቅዱሳን መላእክት ስለተረዱ ድል የሚነሳበትን የምድራዊ ሰማያና የሰማያተ ሰማያትን ጥበቦች አስተምረውታል አዳምም ይህን ከቅዱሳን መላእክት የተማረውን ትምህርት በድንጋይ ላይ ጽፎ በርስት ቦታው ላይ አስቀምጦታል የአዳም ልጆች የሆኑት ኢትዮጵያውያንም መንግስታቸውን እንዴት ስድስቱን ምስጢረ ጥበባትን ተጠቅመው መግዛት እንዳለባቸው ከአዳም አባታቸው የተማሩትን ምስጢራቶች ጠብቀው በመኖራቸው በዘመናቸው ሃያላን ሆነው አልፈዋል። የኃላ ኃላ ግን እንደራሳችን ሃሳብ እና እንደምእራባውያን ጠባብ ፍልስፍና መመራት ጀምረን እነዚህ ምስጢራት ችላ ስንል የገዥነት ክብራችን አጣን ስድስቱ ምስጢረ ጥበባት እኛ በምንኖርባት ምድርም ሆነ በሌሎች ምድራዊ ሰማያት ላይ የገዥነት ክብራችንን የምናገኝበት ሰማያዊ ጥበብ ነው ስደስቱ ምስጢረ ጥበባት ብለን የምንጠራቸውም ስም በረከት ሃይል ስልጣን ህብረት ጥበብ ናቸው። ሃይል አባታችን አዳም በድሎ ወደዚች ምድር ዳግም ከመመለሱ አስቀድሞ በአራት ምድብ የተከፈሉት አስራሁለቱ ምድራዊ ሰማያት ገዢ እና አስተዳዳሪ ስለነበር የገዥነት ሃይል አብሮ ተሰጥቶት ነበር ቢሆንም የኃላ እግዚአብሐየርን አሳዝኖ የገዥነት ክብሩን አጥቶ ወደምድር ሲመለስ ቅዱሳን መላእክት በምድር ላይ ለሚኖሮ ልጆቹ ይጠቅመው ዘንድ ለምድር ፍጥረታት የሚያገለገል የሃይልን ጥበብ አስተምረውታል ይህ ጥበብ በምድር ላይ የሚገኙ ማንኛውንም አይነት ፍጡራን ክፉ መናፍስትን ጨምሮ ለማንበርከክ የሚያስችል ሃይል ነው ሰው ከእርሱ በላይ ለሆነ ሃይል እንደሚገዛ እንዲሁም ሃገራትም የላቀ ሃይል ላለው መንግስት ይንበረከካሉ የጥንቷ ኢትዮጵያ የገዥነት ሃይልም ከዚህ የመነጨ ነው ይህ የሃይል ጥበብ በዚህ በኛ ጊዜ መከላከያ ወይም ሚሊተሪ የምንለው ነው በዚህ ዘመን የሚኖረው ትውልድ በኃይል የበላይነቱን ለመያዝ እጅግ የረቀቀ የጦር መሳሪያዎችን የሚጠቀም ሲሆን ጥንት የነበሩት አባቶቻችን ደግሞ በዘመናቸው የበላይነትን መያዝ የቻሉት በምድራዊ ሰማይትና በሰማየ ሰማያት ከሚገኙ ቅዱሳን መላእክት ጋር ህብረት በመፍጠራቸው ነው ከጠላት ጋር ውጊያ በገጠሙ ወቅት ቅዱሳን መላእክት በግልጽም ሆነ በስውር አብረዋቸው በመሰለፍ ጠላትን ድል ይነሱላቸው ነበር ስልጣን አባታችን አዳም የገዥነት ክብሩን ይዞ የተወለደ ሲሆን በምድራዊ ሰማያት የሚገኙትን አስራሁለቱን ሰማያት እና በውስጣቸው የሚገኙትን ፍጥረታት ይገዛና ያስተዳድር ነበር ታዲያ በነዚህ ሰማያት የሚገኙ ፍጥረታት ተገዥነታቸውን ለማሳየት አዳም በነበረበት ገነት በመመላለስ ይሰግዱለት ነበር ኃላ ግን አዳም የገዥነት ክብሩን ከምድራዊ ሰማያት ላይ ቢነፈግም ቅዱሳን መላእክት የገዥነት ክብሩን የሚያገኝበትን ምስጢር አስተምረውታል አዳምም ይህን ጥበብ ርስት ተደርጋ ለተሰጠችው ምድር ህዝቦች አስተምሮዋቸዋል እነዚህ ህዝቦች የቀደሙት ኢትዮጵያውያን ናቸው ኢትዮጵያውን በነዚህ ምስጢራተ ጥበባት ጸንተው በመቆየታቸው የገዥነት ክብራቸውን እስከሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ አስጠብቀው ቢቆዩም ከዛ በኃላ የመጣው ትውልድ ግን እነዚህን ጥበባት ንቀው ምእራባውያን የስማዝያ ወገኖች ባሳዯቸው መንገድ በመጓዛቸው የውርደትን ካባ ተከናንበን የድህነት ጭራ ስር ተገኝተናል ህብረት አዳም ከተፈጠረ ጊዜ አንስቶ ከቅዱሳን መላእክት ጋር መልካም የሆነ የወንድማማችነት ህብረት ነበረው በዚህም የተነሳ የቅርብ ወዳጁ በሆነው በመልአኩ በቅዱሳ ገብርኤል አማካይነት ወደገነት ተሸጋግሮ ምድራዊ ሰማያትን ይገዛ ነበር በኃላም አምላክን በድሎ ወደምድር በመጣ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት አልተለዬቱም ይልቁንስ የምድራዊና የሰማያ ሰማይትን ጥበባት አስተምረው የኢትዮጵያን ምድር መጽናኛ እንድትሆነው ሰጥተውታል ከዚህም በኃላ ቢሆን ስድስቱን ምስጢረ ጥበባትና ስድስቱን የክብር እቃዎች ሰጥተውት የገዥነት ክብሩን መልሰውለታል። ይህ ጥበብ ተብሎ የተጠቀሰው በዚህ ዘመን ቴክኖሎጂ የምንለው ነው እነዚህን ስድስት ምስጢረ ጥበባት የምንጠቀምባቸው ሌሎች ስድስት የአዳም የክብር እቃዎች ይገኛሉ ስድስቱ ምስጢረ ጥበባትና ስድስቱ የክብር እቃዎች በአንድ ሲዋሃዱ ዳግም የዚች ምድር ትንሳኤ ይሆናል የገዥነት ክብሯም ይመለሳል ስድስቱ የክብር እቃዎች እና ባለትንቢቱ ንጉስ ቶዎድሮስ አባታችን አዳም ከገነት በተባረረበት ወቅት በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እና በሌሎችም ቅዱሳን መልአክት አማካይነት የገዥነት ክብሩን የሚመልስበትን ስድስቱን ምስጢረ ጥበባትን የተማረ ሲሆን እነዚህን ጥበባት የሚያዋህድበት ወይም የሚያሰራበት ስድስት የክብር እቃዎችን ይዞ መጥቷል እነዚህ ስድስት የክብር እቃዎች የአዳም ርስት ቦታ ብለን ከላይ በገለጽነው እና የምድር እምብርት በሆነው የየረር ተራራ ውስጥ ተሰውሮ ይገኛል እነዚህ ስድስት የክብር እቃዎች በዚህ ጽሁፍ ላይ ለማብራራት ባልፈቅድም በአጭሩ ግን ግንዛቤ ለመስጠት እሞክራለሁ እጽ ይህ እጽ የተባለ የክብር እቃ አባታችን አዳም ከገነት ይዞት የመጣው የመጀመርያው የክብር እቃ ሲሆን ባለትንቢቱ ንጉስ ቶዎድሮስ የሚይዝው እጽ በትረ ሙሴን የተሰራበት ነው ይህ የንጉሱ በትረ ሙሴ አንደኛው የሃይሉ ምንጭ ይሆናል ይህ እጽ በቀጥታ ስም ካልነው ምስጢረ ጥበባት ጋር ይያያዛል ይኀውም ፖለቲካ ያልነው ነው።