Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ፍቅረኛህ ፒዛ አማረኝ ካለችህ ፒያሳ ፒዛ ኮርነር ውሰዳት ከዚያ በኋላ መች ነው የምንጋባው። ትልህ ይሆናል ልብስ ጫማ ከገዛህ ከፒያሳ ግዛ ዝናህ ለጉረቤት ይተርፋል የጨርቆስ ልጅ ከሆንክ ደግሞ ዝናህ በሰፈሩ ይናኛል ኪሎ ስጋ የገዛህ ይመስል ሲኒማ ላ ፒያሳ ስማኝማ። ፒያሳ ነው ቤታቸው ድሮ ሲኒማ ኢትዮጵያ አልሳም ያለችህን ፍቅረኛ ወስደህ በፊልም አሳበህ የከንፈር ዳር ድንበሯን የምትጋፋበት ቤት ነበር ሆኖም እጣህ ሆኖ ሴት ጓደኛህን ይዘህ የገባህ እለት የህንድ ፊልም ከከፈቱብህ አለቀልህ ጓደኛህ ከህንዶቹ እያየች አልሳም ትልኸለች ለማፏጨትም ለመሳምም ያልተመቸ ሲኒማ ምኑን ሲኒማ ነው። የባቅላባ ፍቅር ፒያሳን የምወድበት ሌላው ምክንያት ባቅላባን ስላስተዋወቀችኝ ነውአንዳንዶች ቫቅላባ ነው የሚባለው ይላሉ እኛ ምናገባን ባቅላባውን እንጂ ሆሄያቱን አንበላቸው ትዝታ ገብረትንሳኤ ወመኮንን ባር መኮንን ባር የፒያሳ አድባር ነው ይህ ቤት የየመን ዝርያ ባላቸው ሐበሾች የተያዘ ነው ከፒያሳ ፍቅር እንዲይዝህ ከሚያስችሉ አዚሞች አንዱ ነው ዳላስ እጅግ የቆዩ የሚጣፍጡ ሙዚቃዎችን ዛሬም ድረስ ያስኮመኩማል ከዚህ ቤት የሚደመጡ ሙዚቃዎች ዘፋኞቹ በህይወት የሌሉ ወይም ደግሞ ዘፋኞቹ ራሳቸው የረሷቸው ሙዚቃዎች ሊሆኑ ይችላሉ ኦልዲስበት ጉዲስ አንድ አንባቢዬ ዳላስን እንዴት ገለጸው መሰለህ ፐከ ሀበበኋርዞ ዐየ ኮ ዘላለማዊ የሆኑ ዘመን የማይሽራቸው የሱዳንና የአገረሰብ ሙዚቃዎች በዚህ ቤት ይዘወተራሉ በቲቪ የምታውቀው ጀማሪ ዘፋኝ እዚህ ዳላስ ሙዚቃ ቤት አካባቢ ሲያንዣብብ ካየኸው አንድ ነገር ጠርጥር ሊከትፍ ወይ ሊመነትፍ ነው የፒያሳ ጭንቅላት ማን ነው። ማሰርያ አንቀጽ ፒያሳ እንዲህ ያወጋሁህን ያህል ብቻ አይደለችም።
የፒያሳ ካፌዎች ፒያሳ አንድ ሺህ አንድ መቶ ካፌዎች ያሌባት ቅመም የሆነች ሰፈር ናት አንድ ሺህ አንድ መቶ ቆንጆ ልጃገረዶች ደግሞ በካፌዎቿ ውስጥ ተኮልኩለው ኮካ በስትሮ ይጠጣሉ ስትሮ ምን እንደሆነ ካላወቅክ የፒያሳ ልጅ አይደለህም ማለት ነው ስትሮ በቆንጆ ልጅ ከንፈርና በቆንጆ ብርጭቆ መሀል የተሰራ የላስቲክ ድልድይ ነው ፒያሳ በካፌ ብዛት ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ናት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው እንዲህ ያለው ይባላል እንደ ፒያሳ በካፌ የተጥለቀለቀ ሰፈር ከየት ይገኛል። ከአምፒር እስከ ራስ መኮንን ድልድይ ብቻ በግራና በቀኝ የተሰለፉ ከ በላይ ካፌዎችን ልቆጥርልህ እችላለሁ በእርግጥ ቆንጆ ልጃገረዶችና ወርቅ ቤቶች በመሀል በመሀል እየገቡ ቆጠራዬን አስተጓጉለዉት ይሆናል ሆኖም ቁጥራቸው ከዚህ ቢልቅ እንጂ አያንስም የፒያሳ ካፌዎች ልዩ ገፅታ ሁልጊዜ ሙሉ መሆናቸው ነው አንዳንድ የፒያሳ ምሁራን ይህንን ጉዳይ ከመንግሥት የትምህርት ፖሊሲ ጋር ሊያይዙት ይሞክራሉ እኔ ግን እላለሁ ይህ የፒያሳ ልዩ ከራማ እንጂሌላ ምንም ሊሆን አይችልም በፒያሳ ምርጥ ቡና ጠጥተህ ቀንህን ብሩህ ለማድረግ ካሻህ እነማንኪራ እነ አፍሪካ እነ ቶሞካ ቆንጆ ሻይ ከቆንጆ ልጃገረዶች ጋር ተፋጠህ ፉት ለማለት ካሻህ እነ ናምሩድ እነ ራዜል እነ ኢቪያን እነ ሳሬም እነ ኦስሎ እነ አፕቪው እነ ዲጄስ እነ ሃርድኮር እነ ጉድታይምስ አሌልህ በተለይ በቅርቡ የተከፈተው ጉድ ታይምስ እንደ ደብልፌስ ጃኬት አይነት ተፈጥሮ ነበረው ቀን ላይ ውብ ካፌ ኾኖ ይቆይና ማታ ላይ በፍጥነት ራሱን ቀይሮ ወብ ባር የመሆን ልዩ ጥበብ ነበረው የጨርቆስ ልጆች ያለ ሰፈራቸው መጥተው በቡዳ በሉት መሰለኝ ሰሞኑን ተቃጠለ አሉ ነፍስ ይማር። ክፍል ሁለት በየትያትር ቤቶች እጅህ እስኪቀጥን ያጨበጨብክለት ድርሰት የተፈጠረው ዶሮ ማነቂያ ውስጥ ሊሆን ይችላል የድርሰቱ ቃለ ተውኔት የሚሸመደደውም በእነ መካ ቤት የጫት ጉዝጓዝ ላይ ነው ደግሞ አርቲስት ብቻ አይምሰልህ የዶሮ ማነቂያን መታወቅያ የወሰደው የተማሩና የተመራመሩ ኢትዮጵያ ጨረቃ ላይ ከወጣች መወጣጫ መሰላሉን ያዋቅራሉ የሚባሉ ምሁራን ተራ ሰው መስለው ዶሮ ማነቂያ ይሽሎኮሎካሉ ማን መሆናቸውን የምታውቀው ግን ከእነርሱ ጋር ለማውራት እድሉ ሲገጥምህ ብቻ ነው እውቀታቸው መሬትን ከሰማይ ይደባልቃል እነርሱ ግን ከዶሮ ጋር አባሮሽ ይጫወታሉ ዶሮ ማነቂያ ሺሻና ጫት ቤቶቿ በየጊዜው በዘመቻ ይታሸጉባታል በዚያ ስታልፍ በቤቶቹ በር ላይ በቀይ ቀለም ታሽጓል የሚል ጽሑፍም አንብበህ ይሆናል ግን እውነት የታሸገ እንዳይመስልህ በጀርባ በኩል መስኮት የሚመስል በር አለው የቤቱ ደንበኞቹ ብቻ ናቸው በር መሆኑን የሚያውቁት ቀበሌዎችን ለማዘናጋት ዶሮ ማነቂያዎች የፈጠሯት መላ ናት ዶሮ ማነቂያ በዶሮ ማነቂያ ዶሮ አይታነቅም ሰው ግን ይታነቃልለምሳሌ ኑሮ አልሞላ ሲለው ወይም ዶሮ እጅግ አምሮት መግዣ ሲያጣኑሮን ቀለል አድርገው መኖር የሚሹ ዜጎች ዶሮ ማነቂያን ይመርጣሉ አንተም ኪስህ ቢነጣ መሄጃ ብታጣ ፒያሳ እንደ ቦሌ ሂድ ከዚህ። ኢትዮጵያዊ ጨዋ ፈሪሐ እግዚአብሔር ያደረበት የሰው የማይመኝ ሕዝብ እንደሆነ ለመመስከር ፒያሳ በቂ ናት ፒያሳ የሚገኝን አንድ ቱባ ወርቅ ቤት በህሊናህ አስብ ከጀርባው ያለውን ቤትና ቤተሰቡንም ለማስታወስ ሞክር ትገረማለህ የኋለኛው ቤት ባለቤትና አስራምናምን ልጆቹ ወርቅ ቤቱን ሰርስሮ ስለመግባት አስበው አያውቁመም የሸዋ ዳቦ በልተው ሆዳቸውን እያከኩ ወርቅ ቤቱን ተደግፈው ኅብረትርዒት እያዩ ይተኛሉ ወርቅ ቤቶችን ከተደገፉ ቤቶች በአመዛኙ የሚገኙት በዶሮ ማነቂያ ነው በመሆኑም ለዶሮ ማነቂያ ክብር ስንል ሰፈሩን በዶሮ በረር እንቃኛለን ሂድ ዶሮ ማነቂያ ውስጥ ውስጡን ፒያሳን ፒያሳ ያደረጋት አንዱ ሀብቷ ምን ይመሰልሃል። ሂድ ዶሮ ማነቂያ እነ መካ ቤት እነ ቭመሱ ቤት እነ ኑሪያ ቤት እነ ቦስ ሺሻ ቤት በቴሌቪዥን ተንሰፍስፈህ የምታያቸው አርቲስቶች አንድ ጥግ ይዘው በነጻነት ሲጋራቸውን ሲያቦኑት በርጫቸውን ቦርጫቸው ላይ አስቀምጠው ሲበርጩ ት ትመለከታለህ ከዚህ ስፍራ ማንም ፈርሙልኝ አይላቸውም ማንም አይቁለጨልጭባቸውም እነርሱን ከዶሮ አስበልጦ የሚያያቸው ሰው በድፍን ዶሮ ማነቂያ አታገኝም ስለዚህ ነጻነታቸውን ለመጎናጸፍ ዶሮ ማነቂያን መረጡ እርሷም የነጸነት መሬታቸው ሆነች በየትያትር ቤቶች እጅህ እስኪቀጥን ያጨበጨብክለት ድርሰት የተፈጠረው ዶሮ ማነቂያ ውስጥ ሊሆን ይችላል የድርሰቱ ቃለ ተውኔት የሚሸመደደውም በእነ መካ ቤት የጫት ጉዝጓዝ ላይ ነው ደግሞ አርቲስት ብቻ አይምሰልህ የዶሮ ማነቂያን መታወቅያ የወሰደው የተማሩና የተመራመሩ ኢትዮጵያ ጨረቃ ላይ ከወጣች መወጣጫ መሰላሉን ያዋቅራሉ የሚባሉ ምሁራን ተራ ሰው መስለው ዶሮ ማነቂያ ይሽሎኮሎካሉ ማን መሆናቸውን የምታውቀው ግን ከእነርሱ ጋር ለማውራት እድሉ ሲገጥምህ ብቻ ነው እውቀታቸው መሬትን ከሰማይ ይደባልቃል እነርሱ ግን ከዶሮ ጋር አባሮሽ ይጫወታሉ ዶሮ ማነቂያ ሺሻና ጫት ቤቶቿ በየጊዜው በዘመቻ ይታሸጉባታል በዚያ ስታልፍ በቤቶቹ በር ላይ በቀይ ቀለም ታሽጓል የሚል ጽሑፍም አንብበህ ይሆናል ግን እውነት የታሸገ እንዳይመስልህ በጀርባ በኩል መስኮት የሚመስል በር አለው የቤቱ ደንበኞቹ ብቻ ናቸው በር መሆኑን የሚያውቁት ቀበሌዎችን ለማዘናጋት ዶሮ ማነቂያዎች የፈጠሯት መላ ናት ዶሮ ማነቂያ የራሷ መግባቢያም አላት። የከተማችን ሥጋ በል ሕዝብ የማያባራ የስጋ አምሮቱን ከሚወጣባቸው ሰፈሮች ውስጥ ከልደታ ቀጥሎ ዶሮ ማነቂያ ትጠቀሳለች በጊዮርጊስ በኩል ባለው የዶሮ ማነቂያ የባህር በር ያለውን ትእይንት ስትመለከት አዳም የተሳሳተው በበለስ ሳይሆን በሙዳ ሥጋ ሊመስልህ ይችላል የበግ የበሬ እና የፍየል ስጋ እንደጉድ ይነገዳል የሚገርመው በዶሮ ማነቂያ የዶሮ ሥጋ አለመገኘቱ ነው ገና ወደ ዶሮ ማነቂያ ግዛት አንድ እግርህን እንዳስገባህ ነጭ ጋውን የለበሱ ሥጋ አራጆች ልክ እንደ ጆፌ አሞራ እና ጭልፊት ያንዣብቡኻል ያዋክቡኻል ቢላቸውን እያፋጩ የፒያሳ ልጅ ካልሆንክ አንተኑ አርደው የሚበሉህ ስለሚመስልህ ትፈራለህበነጻ የሚጋብዙህ ይመስል እነርሱ ቤት እንድትገባ ያባብሉኻል ቁራጭ ሥጋ አፍህ ውስጥ ወርውረውልህ ኪስህን ሊያራቁቱት እኮ ነው እነ በቀለ እነ ባንቡ እነ አዱኛ እነ ፋሲካ እነ ቤተልሄም እነ ታደሰ መስኮታቸውን የሥጋ መጋረጃ አሰርተውለት እንቁልልጭ ይሉኻል አይንህ ሥጋዎቹን በደንብ እንዲያይ ስልሳ ሻማ አምፖል በሥጋው ትይዩ ያበሩልኻል የኃይል እጥረት በከተማችን እንዲከሰት ከሚዳርጉ ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ቀጥሎ የሥጋ ቤት አምፖሎች ዋንኛዎቹ ናቸው ብዬ ብጮኸ የሚሰማኝ አጥቻለሁ ለማንኛውም እንደ አብዛኛው የአገርህ ዜጋ ሥጋን ለአውድ ዓመት ብቻ የምታገኝ ከሆነ ወይም እንደ ጨርቆስ ልጆች ሥጋን እንደ ኦሎምፒክ በየአራት ዓመቱ የምትበላ ከሆነ በዶሮ ማነቂያ እየተመላለስክ አምሮትህን ልትወጣ ትችላለህ መብላት ነበር። ፒያሳን ከሌሎች እህት ሰፈሮች ልዩ የሚያደርጋት ለላይኛውም ለታችኛውም የኅብረተሰብ ክፍል የምትመጥን በመሆኗ ነው በቀላሉ እንዲገባህ ወጣት ምሳሌ ልስጥህ አይበለውና ወንድነትህ አስቸገረህና እንደኔ በጨዋ መንገድ እንደ ጨው የምትጣፍጥ ፍቅረኛህን ማሀሙድ ጋ ጠብቂኝ ብለህ ኬክ ጋብዘህ በጁስ ተለማምጠህ በክትፎ ተለማምነህ ከንፈር ላይ ቂብ ማለት የማትችል ከሆነ አልያም ደግሞ የሴት ቢሮክራሲ ከሰፈርህ ቀበሌ ጋር የሚመሳሰልብህ ከሆነ ፒያሳ መፍትሄ አላት እስኪመሽ መታገስ ከቻልክና ኪስህ ድፍን ብሮችን ካቆረ እነ ባካል ፀ እነ ብሉናይልእነ ጊቤ እነ ቼ ጉቬራ ይተባበሩኻል እስኪመሽ መታገስ ካልቻልክ ደግሞ ገሊላ የሚባል ቤት አለልህ ገሊላ ቢራ ሳይሆን ማክያቶ አዘህ ከአስተናጋጆቹ ጋር ለአጭሬ የምትደራደርበት ቤት ነው ስለዚህ እና ሌሎች አራት ተመሳሳይ ድብቅ አገልግሎት ስለሚሰጡ እህት ኩባንያዎች በቅርቡ አጫውትህ ይሆናል በነገርህ ላይ ቼ ኩቬራ ለፒያሳ አዲስ ገብ ነው ገና ከመምጣቱ የጎረምሶች ቡጢ ቤት ሆኗልኸል ይሄ ቤት በጨርቆስ ክፍለከተማ ቢከፈት ይሻል ነበር የፒያሳ ልጅ ይመታሃል እንጂ አይደባደብህም ዋጋ ከተወደደብህ ደግሞ ቀውጢ ሰፈር ልጠቁምህ ከትግራይ ሆቴል እስከ ጣይቱ ሆቴል ያለውን መንገድ ታውቀዋለህ። ይህ አጭር ጎዳና የያዘውን ረዥም ጉድ በዝርዝር ለመግለፅ እንደ መስቀል አደባባይ ሰፊ ብራና ቢገኝም የሚሞከር አይደለም በያዘው የሴት አዳሪዎች ብዛት ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ሳይሆን አይቀርምከአዲሳባ ግን ከቺቺኒያ ቀጥሎ ሁለተኛ እንደሆነ ስነግርህ ያለጥርጥር ነው በዚህ ሰፈር ንጉሳቸውን እንደሚጠብቁ ሜኒስትሮች የመንገዱን ግራና ቀኝ ተሰልፈው የሚቆሙ ልጅእግር ኮማሪቶች በየእለቱ ይወለዳሉ ደግሞም በየምሽቱ ቁጥራቸው ይጨምራል ከየት ነው የሚፈልቁት ልትል ትችላለህ ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳኸው ሴቶቹ አራት ኪሎንአውቶብስ ተራንጣልያን ሰፈርን ከመሰሉ የጎረቤት ቀዬዎች ወደ ፒያሳ ይፈልሳሉ ከነዚህ ጎረቤት ሰፈሮች አታለው የሚያመጧቸው ደግሞ እሳት የላሱ የፒያሳ ደላሎችናቸው እንዲህ ይሏቸዋል ፒያሳ የሚባል አገር አለ ወርቅ የሚታፈስበት ባለፀጋ የሚኮንበትፖስፖርት አውጪና ወደ ፒያሳ ልውሰድሽ ለቤተሰቦችሽ ዶላር ትልኪያለሽ ከየሰፈሩ በዚህ መልኩ በደላሎች ለስደት የተዳረጉ ትኩስ ኃይሎች ጣይቱ አካባቢን የስደት መጠለያቸው ያደርጓታል ሰራተኛ ሰፈርና ዶሮ ማነቅያ ባሉ ቆጥ ቤቶች አዳራቸውን ያደርጋሉ አሁን አሁን እነዚህ የፒያሳ የጎዳና ኮማሪቶች መቆምያ ቦታ እያጡ ስለሆነ ተራ በተራ መተዛዘል ጀምረዋል የፒያሳ ክፍለ ከተማ ለነዚህ የጎዳና ኮማሪቶች ወይ ኮንዶሚንየም ቤት ወይ ሴንሴሽን ኮንዶም ወይ መቆምያ ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል ፒያሳን በቅርቡ በምሽት አይተኻት ከሆነ ሰንሻይን ባር ገብረትንሳይ ኬክ ቤት መብራት ኃይል ህንፃ ሲኒማ ኢትዮጵያ ደጅ ማሀሙድ ጋ ማሀሙድ ቁልቁለቱን አራዳ አቀበቱን አላሙዲን አጥሩን ሁሉም ደጆቻቸው በኮልኮሌዎች ተሞልተዋል ደፈር ብለህ ከጠየቅክ ኮልኮሌዎቹ አውትዶር ሰርቪስ ይሰጡኻል እየመሸ ሲሄድ ደግሞ ይደፍሩኻል ነብሱ ባርዬባሪቾቀዮ እያሉ በነገርህ ላይ አላሙዲን ላለፉት አስር አመታት ያጠረውን የማዘጋጃ ሜዳ ሰሞኑን አምርሮ እየቆፈረው እንደሆነ አይቻለሁ የቁፋሮዎን ጥልቀትና የወሰደውን ጊዜ በማየት የፒያሳ ጀዝቦች ወርቁ ከአዶላ ሳይሆን ከፒያሳ ነው የሚወጣው እያሉ ይቀልዳሉ አሌ ይህ አላሙዲ ያጠረው ህንፃ ድሮ ወርቅ ወርቅ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ያፈራ ነበር አሉ እነ መንግስቱ ወርቁን እነ ወርቁ ኪዳኔን እነ ወርቅነሸ ተስፉን አራጋቢ ናት እነ ወርቅነህ ዘውዴን እነ ወርቁ ድንቁን እነ ፍቅሩ ኪዳኔን የኢትዮጵያን እግር ኳስ የሚገድለውም የሚያነሳውም አላሙዲን ነው የሚል ፒያሳዊ ፍልስፍና በቅርቡ ሰማሁ እንዴት አልኩ እንዲህ አሉኝ እሳት የፒያሳ ልጆች ሼኩ መጫወቻ ሜዳዎችን ለኢንቨስትመንት ይወስድና በምትኩ የውጭ አሰልጣኝ ይቀጥራልከዚያ ቡድናችን ጥሩ ይጫወታል ግን የግብ እድል የለውም ችግሩ ምንድነው ተብሎ ሲጠና ተጫዋቾቹ ጎል በሌለው ሜዳ ትሬይኒንግ እየሰሩ ነው ተባለ ሼክ አላሙዲ አሰልጣኙን ወስደው ሜዳውን ቢመልሱልን መልካም ሳይሆን አይቀርም ባንጫወትም የጎል እድል ይኖረን ነበርሼኩ ቶሎ የፒያሳውን ህንፃ ገንብተው ጥሩ ጥሩ ዣንጥላ መሸጫ ሱቅ በመክፈት የስቴድየምን ህዝብ ይክሱታል ብዬ አስባለሁ ምስኪን የስቴድየም ሕዝብ አሁንም ጎል እየጠበቀ ይዘንብበታል። ፒያሳ ነው ካላመንክ ሂድ ቴዎድሮስ አደባባይ ሰቫስቶፖል አፍንጫውን ወደቀሰረበት አቅጣጫ ተመልከት ሰይጣን ቤትን ወይም ሸይጣን ቤትን ታገኛለህ ካላመንከኝ የታሪክ መጸሕፍትን ፈትሽ እኔ የነገርኩህን ይደግሙልኻል በዚህ ቦታ ዋልታ ረዥም ፎቅ ሊሰራበት ነው ፎቅ ሳይቆምበት ቶሎ እየው ታድያ ስትገባ አማትበህ አልያም ቢስሚላህአኡዙ ቢላህ ብለህ ግባ ሰይጣን ቤት መሆኑን አትርሳ በኢትዮጵያ ውስጥ በጣት የሚቆጠሩ ሲኒማ ቤቶች ይገኛሉ ከነዚህ ውስጥ ከ በመቶ በላይ የሚገኙት በፒያሳ እንደሆነ ማን በነገረህ ፒያሳ የኢትዮጵያ ሆሊውድ ልትላት ትችላለህሰይጣን ቤትሲኒማ ኢትየጵያ ማዘጋጃ ቤት አገር ፍቅርሲኒማ አምፒር እስክስታው ቤት እንዲሁም አገር በቀል የዶሮ ማነቅያ ቪዲዮ ቤቶች ወዘተ ሁሉም ፒያሳ ነው ቤታቸው ድሮ ሲኒማ ኢትዮጵያ አልሳም ያለችህን ፍቅረኛ ወስደህ በፊልም አሳበህ የከንፈር ዳር ድንበሯን የምትጋፋበት ቤት ነበር ሆኖም እጣህ ሆኖ ሴት ጓደኛህን ይዘህ የገባህ እለት የህንድ ፊልም ከከፈቱብህ አለቀልህ ጓደኛህ ከህንዶቹ እያየች አልሳም ትልኸለች ለማፏጨትም ለመሳምም ያልተመቸ ሲኒማ ምኑን ሲኒማ ነው። የፒያሳ ሀብት ወርቅ ቤቶቿ ናቸው የፒያሳ ጆሮ ዳላስ ነው የፒያሳ አይን ሲኒማ አምፒር ነው የፒያሳ መልክ ውብ ሴቶቿ ናቸው የፒያሳ ራስ ቅል ማዘጋጃ ቤት ነው የፒያሳ ጭንቅላት ማን ነው።