Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ዮሐ የጌታ ሥጋና ደም እን ደሚለወጥ አምነው እንዲቀበሉት አብቅቷቸዋል ማለት ነውን።ኬ ያስተምረናል አሁን ለንስሐ ሰላዘናችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ስላዘኖችሁ አዕ ደለም በምንም ከእኛ የተነሣ እንዳትጐዱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ፀፀት የሌለበትን ወደ መዳን ም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመ ጣል ኛቆሮ እንግዲህ እውነተኛውን ኀዘን ከእንባው ጋር አድርጉ በንጹሕ ልቡናና ጸሎት ለእግዚአብሔር በማቅረብ ተነሳሒው እንደገና ላለመበደል መወሰን ይኖርበታል ውሳኔውንም ለመፈጸም የሚያስችለውን የመንፈስ ቅዱስን ረድኤት ለማግኘት ተነሳሒው ሁልጊዜ ተግቶ መጸለይ አለ በት ታ ከዚህ ቀጥሎ ተነሳሒው ኃጢኣቱን ሥልጣነ ክህነት ላለው ካህን ይናዘዛል ኑዛዜ ማድረግ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘ ነው ከነዚህም ነገ ሮች በአንዲቱ በደለኛ ሲሆን የሠራውን ኃጢአት ይናዘዛል ሰለ ሠራው ኃጢኣት ለእግዚአብሔር የበደል መሥዋዕት ያመጣል ካህኑም ስለ ኃጢአእ ቱ ያስተሠርይለታል እርሱም ይቅር ይባላል ዘሌ እና ከዚህ ጥቅስ የኃጢአት ሥርየት ለማግኘት ለካህን መናዘዝ እንደሚገባን እን ማራለን ሰለዚህ ኃጢአታችንን ለአናዛ ካህን ከበደሉ ዓይነትና ሁኔታ ጋር መናገርና ማስረዳት ይገባል ስንናዘዝም ከእንባና ከፀፀት ጋር ሆነን ከካህኑ ጋር እግዚአብሔር አብሮ እንደሚሰማን አምነን በእውነት መናገር ያስፈልጋል በሸታውን የሰወረ መድኃኒት አያገኝም ተብሏልና ለነፍስ ቁሰል ሐኪም ለሆነው ለካህኑ ኃጢአታችንን ከሰወርን ለነፍስ የሚሆነውን ፈውስ ለማግኘት ኣንችልም ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል ተብሎ ተጽፏልና ምሳ የጌታ ወንድም ያዕቆብ የተባለውም ይኸንኑ ያስተምረናል እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ያዕ እርስ በእርሳችን በቂም በቀል ሳንያያዝ የበደልነውን እየካሥን የበደለንንም ይቅር እያልን ብንናዘዝና የሰማዩ አባታችንንም በጸሎት ብን ጠይቀው ምሕረትንና ፈውሰን ይሰጠናል ነገር ግን እኛ ማንንም አልበደልን ም ኃጢአትም የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን እውነትም በእኛ ውስጥ የለም በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
ትምህርተ ዛፀይማናትና ክርስተያናዊ ሕፀወት ምዕራፍ ሁለት ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ሕይወታችን ልደት እድገትና ሌሎችም ነገሮች እንዳሉት መን ፈሳዊ ሕይወታችንም እንደዚሁ ይኸንኑ የሚመስሉ ሁኔታዎች አሉት በዚህ መሠረት አንድ ሰው መንፈሳዊ ልደትን የሚያገኘው በእምነትና በምሥጢረ ጥምቀት እንደሆነ እንረዳለን ከዚህም ቀጥሎ ምሥጢረ ሜሮንና ምሥጢረ ቁርባን በተከታታይ ይፈጸማሉ እነርሱም መንፈሳዊ ልደታችንንና እድገታችንን ከፍጹምና ያደርሱታል ስለዚህ እነዚህ ሦስቱ አዲስ ሕይወትን የሚያሰጡ ክርስቲያናዊ ሕይወትን የሚያስገኙ ምሥጢራት ይባላሉ እነርሱንም በአንድ ወገን መድበን በመጀመሪያ እንመለከታቸዋለን በሁለተኛው ምድብ የአገልግሎትና የአንድነት ጸጋ የሚገኝባቸውን ምሥጢረ ክህነትንና ምሥጢረ ተክሊልን በአንድ ወገን አድርገን እናያቸዋለን ክፋት በነገሥበት መከራና ችግር በበዛበት ደስታና ኀዘን በሚፈራረቁበት በዚህ ዓለም ውስጥ ሰንኖር ለልዩ ልዩ ፈተና መጋለጥ አይ ቀርምና ነፍስ በኃጢአት ሥጋም በደዌ በተያዙ ጊዜ ለሁለቱም ፈውስ ያስፈልጋቸዋል ለነዚህም ችግሮች መንፈሳዊና ሥጋዊ መፍትሔ እንዲሆኑ ምሥጢረ ንስሐ ለፈውሰ ነፍስ ምሥጢረ ቀንዲል ለፈውሰ ሥጋ እንዲያገለግሉ ተዘጋጅተዋል ስለዚህ እነርሱን በምድብ ሦስት የፈውስ ጸጋ የሚገኝባቸው ምሥጢራት በማለት እንደ ዓይነታቸው በመለየት ከሙሉ በከፊሉ እናጠናቸዋለን እንግዲህ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን በተገለጸው አመ ዳደብና ቅደም ተከተል ከብዙው በጥቂቱ እንደሚከተለው ለመግለጽ እን ሞክራለን ሀ አዲስ ሕይወትን የሚያስገኙ ምሥጢራት ከላይ እንደ ገለጽነው ሦስቱ ምሥጢራት ማለት ጥምቀት ሜሮንና ቅዱስ ቁርባን በክርስቶስ ጸጋ ለተገኘው አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት ክርስቲያናዊ ሕይወት መሠረት ስለሆኑ ከሌሎቹ ምሥጢራት ሁሉ በማስቀደም መጀመሪያ መማር ይገባናል ከሦስቱ ደግሞ የሚቀድመው ጥምቀት ነው ምክንያቱም እምነት ከሁሉ ነገር እንደሚቀድም ጥምቀት ደግሞ እንደዚሁ በክርስቶስ ያለንን አንድነትና እምነት የሚመሰክርልን የእምነት ምሥጢር ስለሆ ነ በመጀመሪያ መፈጸም ይኖርበታል ስለዚህ ጥምቀት የምሥጢራት ሁሉ መጀመሪያ ወደመንፈሳዊ ነገር ሁሉ መግቢያ በር ነው ምሥጢረ ጥምቀት ያጀሇምፖ ሦርሃምኛ ምሥሪፖ ጥምቀት ማለት ከአዳም የወረስነውን ኃጢአትና እኛም የፈጸምነውን በደል ሁሉ ደምስሶ በመንፈስ ቅዱስ እንደገና እንድንወለድ የሚያደርገን የመጀመሪያው የጸጋና የእምነት ምሥጢር ነው ይህም የሚፈጸመው ካህኑ በጸሎተ ክርስትና መሠረት በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃ በአ ጠመዋ ጊዜ ነው ባለዛር ወዐርዐ ትምህርተ ዛፀማናትና ከክርስቲያናዊ ሕፀወት ከላይ እንደ ገለጽነው ከምሥጢራት ሁሉ ጥምቀት ይቀድማል ምክን ያቱም ማናቸውም መንፈሳዊ ሥራዎች ሁሉ በመንፈሳዊ ልደት መጀመር ስላለባቸው ነው የእግዚአብሔር ልጅነት የቤተ ክርስቲያን አባልነትና የመን ፈስ ቅዱስ ሱታፌ የሚገኘው በምሥጢረ ጥምቀት ነው ሥጋዊ ልደት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ እንዲሁም መንፈሳዊ ልደት አንድ ጊዜ ብቻ ነው ስለዚህ ምሥጢረ ጥምቀት አንድ ጊዜ ብቻ ይፈጸማል እንጂ አይደገምም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም አንዲት ጥምቀት ብቻ እንዳለች ጽፏል ኤፌ ጥምቀትን ጌታ መሥርቷል በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ተጠምቆ እንድንጠመቅ በተግባር አስተምሮናል ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በስተቀር መንግሥተ ሰማያት እንደማይገባ ተደንግጓል ዮሐ ወደ ዓለም ሁሉ ሄደው እንዲያስተምሩና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲያጠምቁ ክርስቶስ ሐዋርያትን አዝዚቸዋል ማቴ ያፇጥምፇም ምሪሴሐ ያሇሑሪይ ጴያ ለምሥጢረ ጥምቀት ምሳሌ ሆነው የሚነገሩ ከብሉይ ኪዳን የሚገኙ ታሪኮች አሉ ከነዚህም አንዱ የኖኅ መርከብ እንደሆነ ቅዱስ ጴጥሮስ ያስተምረናል ጴጥ ሊቃውንት አባቶቻችን እንደሚተረጉሙልን ኖኅና ቤተሰቡ የምእመናን ምሳሌ መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ውኃው የጥምቀት ምሳሌ እንደሆነ ተገልዷል ክርስቶስ በሠራት መርከብ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጥምቀት የጸጋ በር ያልገባ ሁሉ ቨውጭ ስለሚቀር መዳንን አያገኝም ከሐዋርያው ጳውሎስም ከብሉይ ኪዳን የተወሰዱ ሌሎች ሁለት ምሳሌዎችን እንማራለን አንደኛው ምሳሌ ግዝረት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከላይ እንደ ተጠቀሰው እሥራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ ይመራቸው በነበረው ደመና ሥር መሆናቸውና እንዲሁም በቀይ ባሕር ውስጥ ማለፋቸውን የሚመለከት ታሪክና ምሳሌ ነው ይህም የምሥጢረ ጥምቀት ምሳሌ እንደሆ ነ ከላይ ተመልክተናል ቆላ ቆሮ ከዚህም ሌላ የኢ ዮብና የንዕማን በዮርዳኖስ ተጠምቀው መዳናቸው እንደ ምሳሌ ተቆጥሯል ኛ ነገ ስለ ጥምቀት ታሪክና ምሳሌ ብቻ ሳይሆን ትንቢትም ተነግሯል መዝ ሕዝ ተመልከት ያሟፖዖው ሥራሄሦ ኖጥምፇዎት ያሜዕታፖያዖው ዴ። ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን ሮሜ ከውኃው ውስጥ ሦሰት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ማለቱ ጌታ በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀንና ሌሊት መቆየቱን ያስረዳል በሦስተኛው ከውኃ መውጣቱ ጌታ በሦስተኛው ቀን ከመቃብር ለመውጣቱ ማስረጃ ነው እንደዚሁም ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር ይነሣሉ በመጀመሪያ የነፍስ ትንሣኤን ያገኛሉ በመጨረሻ ደግሞ ነፍስና ሥጋቸው ተዋሕደው ይነሣሉ የነፍስ ትንሣኤ የተባለው በእምነትና በጥምቀት የምናገኘው የትንሣኤ ልቡና ጸጋ ነው በነፍስ ገነት መግባትን ያመለክታል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጥምቀትን ከጌታ ሞትና መቃብር ጋር አወዳድ ሮ ክርስቲያኖች ጌታን በሞቱ ከመሰሉት በትንሣኤውም እንደሚመሰሉት አስ ረድቶናል ሮሜ የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ከአኛ ሕይወት ጋር እንዴት እን ደሚዛመድና እንዴትስ በተግባር ልንገልጸው እንደምንችል መማር አለብን በመጀመሪያ በኃጢአታችን የመጣውን የሞት ፍርድ በአኛ ምትክ ስለ እኛ ሆኖ መሞቱን እናምናለን እንግዲህ ይህንን ካመንን ከአዳኛችን ጋር የጠበቀ አንድነት አለን ማለት ነው በክርስቶስ ሞት አንድ መሆናችን የሚገለጸው ከኃጢአት ሥራ መሞታችን ከክፉ ነገር መለየታችን ለመሆኑ ዝነገነገርህኽ ትምህርተ ዛይደማናትና ክርስቲደዖናዊ ሕይዉት ከቅዱስ ጳውሎስ እንማራለን የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ ገሏ የተባለው ቃል ኃጢኣትን እንደ ሞተ እንደ ተቀበረ እንድንቆጥረው ያመለክተናል ከክርስቶስ ጋር መሞትና መቀበር ማለት ፈቃደ ሥጋንና ፈቃደ ሰይጣንን መዋጋትና መጋደል ከዓ ለማዊም ደስታ ራሳችንን መለየት መሆኑን የጥምቀት እውነተኛ ትርጓሜ ያስረዳናል እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አ ይንገሥ ሮሜ በጥምቀት ከጌታ ሞት ጋር አንድ የመሆናችንና በትንሣኤውም የመተባበራችን ትርጉም ምን እንደሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ያስረዳናል ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትን ሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከአርሱ ጋር እንደተሰቀለ እናውቃለን የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን ሮሜ እንግዲህ የተጠመቅን ክርስቲያኖች አሮጌውን ሰው ማለት የድሮውን ክፉ ጠባያችንንና የኃጢአት ሥራችንን ከክርስቶስ ጋር ሰቅለን ማለት እንደ ሞተ ሰው ያህል ተለያይተን በክርስቶስ እንደ አዲስ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ተወልደን አዲስ የጸጋ ሕይወትን መኖር እንዳለብን እንማራለን ስለዚህም እን ደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ከክርስቶስ ጋር የጠበቀ የመንፈስ ቅዱስ ግንኙነት ይኑረን እያንዳንዱ ክርስቲያንም በመንፈስ ከእርሱ ጋር እንዲህ ይበል ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ እኔም አሁን ሕያው ሆፔ አልኖርም ክር ስቶስ ግን በእኔ ይኖራል አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው ገላ ናም ወቅሄ ማኖምመፇና ያ ምህረ ዕሰ ማሷደሃ እኔ የተጠመቅሁት በሕፃንነቴ ስለሆነ ይኸንን ሁሉ አላውቅም ማለት በቂ አይደለም ይልቅስ ተምሮ የተማሩትን በሥራ ላይ ማዋል ትልቅ ቁም ነገር ነው በጥንተ አብሶ የተላለፈው ፍዳና መርገም ሕፃናትን ሁሉ ስለሚመለከት በወቅቱ መጠመቅ ይኖርባቸዋል በወላጆች ወይም በካህናት ቸልተኝነት ሕፃኑ ሳይጠመቅ ቢሞት በቤተ ክርስቲያን ሕግ መሠረት ይቀጣሉ ፍትነጊአንቀጽ በጥንት ጊዜ መላው ቤተሰብ ማለት አዋቂዎችም ሕፃናትም እንደሚጠመቁ በታሪክም በቅዱሳት መጻሕፍትም ይገኛል የሐዋሥራ ኛቆሮ በኦሪት የቃል ኪዳን ምልክት የሆነው ግዝረት ሕፃናት በተወለዱ በስምንተኛው ቀን ይፈጸም ነበር ዘፍ ስለ ቃል ኪዳን ምንም በማያውቁ ሕፃናት እንደዚህ የግዝረት ሥርዓት የሚፈጸም ከሆነ የጥምቀትንም ሥርዓት ለሕፃናት መፈጸም ተገቢ ነው ግዝረት ለጥምቀት ምሳሌ ነውና ቆላ ሕፃናት ሳያውቁ በሥጋ እንደ ተወለዱ እንደዚሁም ሳያውቁ መንፈሳዊ ልደትን በጥምቀት ያገኛሉ አለማወቅ የጸጋን ምሥጢር አይገድበውም በእናታቸው ማኅፀን እንኳ ጸጋ መንፈስ ቅዱሰን የተቀበሉ እንዳሉ ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ ኤር ሉቃ ከዚህም ሌላ ሕፃናት ወደ ክርስቶስ እንዳይመጡ መከልከል አይገባም ማቴ ይልቅሰ ሕፃኑን ባለዛር ወዐርዐ ትምህርተ ዛፀማናትና ክርስተያናዊ ሕወት በክርስቶስ ጸጋና እውቀት ማሳደግ ታላቅ ቁም ነገር ነው ስለዚህ ወላጆች በተለይም የክርስትና አባቶችና እናቶች ክርስትና ያነሙአቸውን ሕፃናት በሃይማኖት ትምህርት እንዲያሳድጓቸው በመልካም ምግባር እንዲያንዷቸው ያስፈልጋል ካህናትም ምእመናን ሁሉ ምሥጢረ ጥምቀትን እንዲያውቁ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲማሩ ማድረግ ከቅዱሳን ሐዋርያት የተረከቡት ሥልጣንና ሥራ መሆኑን ተገንዝበው ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንዲተጉና ይህም ሐዋርያዊ ተልእካቸው ታላቅ ኃላፊነትና አደራ ያለበት መሆኑን መዘንጋት አይገባቸውም የክርስትና አባትና እናት የሚሆኑትን ምእመናን በቅድሚያ አውቆ አስ ፈላጊውን ምክርና ትምህርት በመስጠት ጸሉተ ሃይማኖትን በቃል እንዲያጠኑ ትርጉሙንም እንዲያውቁ የቤተ ክርስቲያንንም ምሥጢራት በትክክል እን ዲረዱ ማድረግ የካህናት ሁሉ ኃላፊነት ነው የክርስትና ልጆችንም በሃይማኖትና በሞራል ትምህርት የማሳደግ ኃላፊነት የተጣለው በክርስትና አባ ትና እናት ላይ መሆኑ ሁሉም እንዲያውቁት ያስፈልጋል የሥጋ ወላጆችም ልጆቻቸው የሃይማኖት ፍቅር እንዲያድርባቸውና የቤተ ክርስቲያንንም ሥርዓት እየተለማመዱ እንዲያድጉ ማድረግ የዘወትር ጥረታቸው መሆን ይገባዋል እያንዳንዱ ቤተሰብ እንደ ቤተ ክርስቲያን ስለሚቆጠር የጠዋትና የማታ ጸሎት በግልም ሆነ በአንድነት ማድረግ ከዚህም ጋር የማእድ ጸሎትን ማድረስ ለቤተ ሰቡ አባላት ሁሉ ጸጋና በረከትን ያስገኛል ሕፃናትንም አብረው እንዲጸልዩ ማበረታታትና ከክፉ ነገርም እንዲቆጠቡ በፍቅርና በጥበብ መክሮና አስተም ሮ ማሳደግ የወደፊት ኑሯቸው እንዲቃና ከማድረጉም በላይ ወላጆቻቸውን በነፍ ስም በሥጋም ይጠቅግቸዋል ምሥጢረ ሜሮን ፖታሮሥጉሙኛ ለመሥራሪያ ሜሮን ማለት ከጥምቀት ጋር ከጥምቀት ቀጥሎ የሚፈጸም መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጠን በመንፈስ ቅዱስ መጠመቃችንን ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለዳችንን የሚያረጋግጥልን ታላቅ ምሥጢር ነው ጌታችን ከዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ሲወጣ መንፈስ ቅድስ እንደ ወረደና የባሕርይ ልጅ ነቱ እንደ ታወቀ እንዲሁም ተጠማቂዎች በምሥጢረ ሜሮን የጸጋ ልጅነትን ማግኘታቸው ይረጋገጣል ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ መወለዳቸው ይታወቃል በዚህም የክርስቶስን አርአያ ይከተላሉ እንግዲህ በምሥጢረ ጥምቀትና በምሥጢረ ሜሮን አማካኝነት አማኞች ከክርስቶስ ጋር አንድ ይሆናሉአዲስ የመንፈስ ቅዱስ ሕይወትንም ይጀምራሉ ምሥጢረ ሜሮንን ማን መሠረተ። ፇ ከላይ እንደ ተመለከትነው መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት አማካኝነት በአን ብሮተ እድ ይሰጥ ነበር ዛሬ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቀሳውስት አማካ ይነት በቅብዐ ሜሮን ይፈጸማል ሜሮን የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ቅብዐት ማለት ነው በተቀደሰው ቅብዐት የመቀባት ሥርዓት በኦሪት ሕግ የተደነገገ ነው ካህናቱና የመቅደሱ ንዋያተ ቅድሳት በተቀደሰው ቅባት እን ደሚቀቡና በዚህም ምክንያት እነርሱም የተከበሩና የተለዩ የተቀደሱም እንደሚሆ ኑት ተጽፏል ዘፀጋ ይህም ለሐዲስ ከኪዳኑ ሥርዓት ለምሥጢረ ሜሮንና ለቅብዐ ቅዱስ ሁሉ ምሳሌ ሆጳል የብሉይ ኪዳኑ ቅብዓት ሰዎችን ለእግዚአብሔር የተለዩና ለአገልግሎቱም የተመረጡና የተቀደሱ ብቻ ለማድ ረግ ሳይሆን ሁሉን የሚቀድሰው መንፈስ ቅዱስ በሐዲስ ኪዳን ለመሰጠቱም ጭምር ምሳሌነት አለው ሰለዚህ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ ቅባት ሲል አማኞችን የሚቀድሰውና ለአማኞችም የተሰጠውን መንፈስ ቅዱስን ያሳ ያል እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል ሁሉንም ታውቃላችሁ እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በአናንተ ይኖራል ማንም ሊያስተምራችሁ አያስ ፈልጋችሁም ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ እውነተኛም እንደሆነ ውሸትም እንዳልሆነ እናንተንም እንዳስተማራችሁ በእርሱ ኑሩ ኛዮሐ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ስለዚሁ ጽፏል በክርስቶስ ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው ኛቆሮ ዝነገነገርህኽ ትምህርተ ዛፎማናትና ክርስቲያናዊ ሕደዉወት ያምሥጢጪሪ ሟሮዖ ጸጺ መፈፅዕ ፇራያ ያ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚደረገውና በሚታየው የቅብዐ ሜሮን ሥርዓት አማካይነት የማይታየው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ይሰጣል ቅዱሱንም ቅባት ለተቀበሉት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ገለጸው መንፈስ ቅዱስ ስለ ሁሉ ነገር ያስተምራቸዋል ኛዮሐ መንፈሰ ጽድቅ አድሮባቸዋልና ፀደ ትክክለኛው ነገር ሁሉ ይመራቸዋል ዮሐ የክርስቶስን መስቀል ተሸክመው እንዲከተሉት ያበቃቸዋል እስከ መጨረሻው በትዕግሥት እንዲጸኑ ያደርጋቸዋል እንግዲህ መንፈስ ቅዱስ በጥምቀት ጊዜ በመንፈስ እንድንወለድ ከግድረግ ጀምሮ በክርስቶስ ጸጋ እንድናድግና የሃይማኖት ፍሬ እንድናፈራ የግያበቃን እርሱ ነው መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ ምእመን የመንፈስ ቅዱስ ሀብታት ያድሩበታል የእግዚአብሔር መንፈስ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ የምክርና የኃይል መንፈሰ የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል ኢሳ በእነዚህ ሀብታት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምናው ፃጎበት የሃይማኖትን ምሥጢራት የምናስተውልበት መልካሙንና የሚሜበል በውን መንገድ ለመምረጥ ምክርን የምናገኝበት ክፉውን ለማስወገድ ኃይል የሚሆኑንና መልካሙንም ሥራ እንድናከናውን የሚያበቁን መሆናቸውን እን ረዳለን ስለዚህ ክርስቲያኖች ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ሰጦታዎች እየተመሩ ወዉልካም ሥራቸው የሰማይ አባታቸውን በሰዎች ዘንድ እንዲመሰገን በማድረጋ ቸው ክርስቲያናዊ ሕይወታቸው በዘልማድ ሳይሆን በእውነትና በመንፈስ ቅዱስ ሪይል መሆኑን ያረጋግጣሉ መንፈስ ቅዱስን መቀበል ቀላል ነገር አይደለም ምክንያቱም እኛን በግዳን ክርስቶስ በተቀበለው ሕማምና ሞት የተገኘ ታላቅ ጸጋ ነው እንጂ እን የው በከንቱ ወይም በአጋጣሚ የመጣ አይደለምና እንዲህማ ካሰብን አግዚአብሔርን ፍቅርና ውለታ ረሳን ማለት ነው የእውነት መንፈስ የለብንም ግስት ነው እግዚአብሔር እኮ እኛ ሳናውቀውና ሳንወደው እርሱ በመጀመሪያ እአገዲሁ ወደደን ልጁን ወደ ዓለም ልኮ በእርሱ ሕማምና ሞት እንድንድን አ ሀፅን ከዚያም በሰጠን ሃይማኖት ሳንፈራ በትዕግሥት እንድንኖር የሚያጸናን በመከራችንና በችግራችን የሚያጽናናን በጨለማው ዓለም በምንኖርበት ጊዜ ከቋለፋው ሀገር እስክንገባ ድረስ በእውነተኛው መንገድ የሚመራን መንፈስ ቅዱስን ላከልን ይህን ሁሉ ያደረገ እግዚአብሔር እኛ ከእርሱ ጋር ሆነን ያዘጋጀልንን የዘለዓለሙን ደስታና ተድላ ተካፋይ እንድንሆንለት ብቻ አስቦ ጸመው ነው ስለዚህ ይኽን ሁሉ በመገንዘብ እንደዚህ የወደደንን እግዚአ ሴር እኛም በሙሉ ልባችን በደስታ መንፈስ መውደድና ማመስገን ይየርብናል እንግዲህ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሉስ እንደ መከረን በመንፈስ ብንኖር ወንፈስ ደግሞ እንመሳለሰ ገላ የሥጋን ምኞት የዚህን ዓለም አም ርቦት ወደ ጐን ትተን ከእግዚአብሔር ጋር ሆነን ልባችንን ክርስቶስ ወደ ኣለበት ሥፍራ ከፍ ከፍ አድርገን የተስፋይቱን ሀገር እየተመኘን በመንፈስ ቅዱስ ቦዕት ወደፊት እንገሥግሥ እንግዲህ አላስፈላጊ የሆኑትን ባሕላዊና ለግዳኛ አኗኗራችንን ትተን በፈቃደ ሥጋ ሳይሆን በፈቃደ መንፈስ ቅዱስ ርስቶስ የማዳን ሥራ ያገኘነውን ጽድቅና ደኅንነት ጠብቀን መኖር ይበናል በዚህም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ወደተባሉት እንደርሳለን እነርሱም ር ደስታ ሰላም ትዕግሥት ቸርነት በነጎነት እምነት የውሃት መግዛትናቸው ገላ ዝነገነገርህኽ ትምህርተ ዛይማናትዓ ክርስቲያዓዊ ሕይጠት ምሥጢረ ቄርባን ፖረ ጉም ምሥጢረ ቁርባን ማለት ክርስቶስ ስለ እኛ ኃጢአት በመሰቀልዌቹ መሥዋዕት ሆኖ በሥጋው በመሞቱ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደባት የዘዛ ሕይወትን ያስገኘበት የመዳናችን መሠረት የጸጋችን ሁሉ ምንጭ የሆ የቅዱስ ሥጋውንና የክቡር ደሙን የማዳን ጸጋ የሚያመለክት ታላቅ የክር ሃይማኖት ምሥጢር ነው ክርስቶስ እንደ መሥዋዕትም እንደ ዐቢይ ለቀ ህናትም በመሆን ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ፈጽሟል ዕብ ዐቢይ ሊቀ ካህናትነቱ በመስቀል ላይ የተቆረሰው ሥጋውን የፈሰሰው ደ የኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር በማቅረቡ ሰውን ከራሱና ከእ ብሔር ጋር አስታረቀ የጥልንም ግድግዳ አፈረሰ የተራራቀውን አቀራረበ ይህም ነገር የቁርባንን የምሥጢር ትርጉም ያስረዳኖል ቁ ማለት በአንድ» በኩል ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕት በሊላ ደግሞ እኛ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበትን የምንቀራረብበ የምንዋሐድበትን ሁኔታ ያሳየናል ልንቀርብና የመለኮታዊውንም ጸጋ ተሳታፅ ልንሆን የምንችለው በምሥጢረ ቁርባን አማካኝነት ኅብስቱና ወይኑ ሀደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ተለውጦ ስንቀበለው ነውና ምሥጢር መሆኑን ከዚህ ላይ እናስተውሳላለን ነ ና ቁርባን የሚለው ቃል መሠረቱ ከዕብራይስጥ ቋንቋ የመጣ ሲሆነ የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም ስጦታ ማለት ነው ይህም ማለት እንደ ኦሪ ቁርባን ሰው ለእግዚአብሔር ያቀረበውን ሰጦታ ብቻ የሚያመለክት ሳይሆነ እግዚአብሔርም በተለየ ሁኔታ ለሰዎች ደዓንነት ለዓለም ሁሉ የሰጠውን በሥጋና በደም የመጣውን የልጁን ስጦታ ያስገነዝባል ስለዚህም ለዓለም መድኃኒት ሆኖ የተሰጠው በጸሉተ ኀሙስ ማታ ወደ ጌታ ሥጋና ደም የተለወጠው ኅብስትና ወይን ዛሬም በጸሎተ ቅዳሴ የጌታን ሥጋና ደም ሆኖ የሚቀርበው ቅዱስ ቁርባን ይባላል እርሱም ከእግዚአብሔር የተሰጠ የተቀደሰ ስጦታና መሥዋዕት ነው እንግዲህ ለኃጢአታችን መሥዋዕት ሆኖ ከእግዚአብሔር የተ ሰጠንን እኛ ደግሞ ከምስጋና ጋር መልሰን ለእርሱ እናቀርባለን ነ ስለዚህ ነው በጸሉተ ቅዳሴ ካህኑ አምላኪየ እግዚአብሔር ሆይ። ደስ የሚያሰኝህ መሥዋዕት የልጆህ ሥጋ እነሆ በዚህም ኃጢአቴን ሁሉ አቃልልኝ ስለ እኔ አንድ ልጅህ ሙቷልና ስለ እኔ በቀራንዮ የፈሰሰ ንጹሕ የሚሆን የመ ሲሕም ደም እነሆ ስለ እኔ ይጮኻል ይህ የሚናገር ደም የእኔን የባርያሀን ኃጢአት የሚያሰተሠርይ ይሁን በማለት የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ለእግዚአ ብሔር ያቀርባል የሐዋርያት ቅዳሴ ቁጥር ፇቀፉዕ ወረያ ያምኃታና በብሉይ ኪዳን ታሪክ ውስጥ ለሥጋውና ለደሙ ማለት ለምሥጢረ ቁርባን የተመሰሉ ምሳሌዎች አሉ በጠቅላላ የኦሪት መሥዋዕት ሁሉ ለወንጌሉ መሥዋዕት ምሳሌነት ቢኖራቸውም ዋና ዋናዎቹን ብቻ እንጠቅሳለን መጀመሪያው የልዑል እግዘአብሔር ካህንና የሳሌም ንጉሥ ያቀረበው የኅኀብስትና የወይን መሥዋዕት ለክርስቶስ ዘላለማዊ ሊቀ ካህናትነትና ለሥጋው ወደሙ ዓይ ነተኛ ምሳሌ ሆኖ ይነገራል ዘፍ ዕብ እና ፅ ሁለተኛው ከቀሳፊ የሞት መልአክ አድኖ ከግብፅ ባርነት ነፃ ያወጣቸው የፋሲካ ዝነገነገርህኽ ትምህርተ ዛደመናትና ክርስቲይናዊ ሕይፎወት በግ ደም መረጨትና ሥጋውም ተጠብሶ መበላቱ የእግዚአብሔር በግ ለተባለው ለክርስቶስ አዳኝነትና ለምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ ሆኗል ዘዐ ኛ ቆ ሮ ሥስተኛው እሥራኤላውያን በምድረ በዳ ይመገቡት የነበረው ከሰማይ የወረደው መና ዛሬ ምእመናን ለነፍሳቸው ምግብ የሚቀበሉት የሥጋውና ያደሙ ምሳሌ ነው ዘፀ ዮሐ አራተኛው ጥበብ ያዘጋጀችው ማዕድ ያረደችው ፍሪዳ የጠመቀችው የወይን ጠጅ የላከቻቸው ኣገልጋዮቿ የተጠሩት ሰዎች ሁሉ ምሳሌነት እንዳላቸው ይነገራል ጥበብ የክርስቶስ ማዕድ የሥጋው የደሙ አገልጋዮች የካህናት ተጋባች የምእመናን ምሳሌ ናቸው ተብሉ ይተረጉማል ምሳ ይህን የመሳሰሉ ሴሎች ምሳሌዎችም አሉ ዘሌዋ ሲራክ ትንቢትም ስለ እውነተኛው ቁርባን ተነግሯል ከፀሐይ መውጫ ጀም ሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና በየሥፍራውም ለስሜ እጣን ያጥናሉ ንጹሕም ቁርባን ያቀርባሉ ሚል ይህ ሰለ ወንጌል መሥዋዕት የተነገረ እንጂ ስለ ሶሪ መሥዋዕት አይደለም ምክንያቱም የኦሪት መሥዋዕት በኢየሩሳሌም ከተማ በቤተ መቅደስ ብቻ እንጂ በሌላ ቦታ እንዳይፈጸም በሕግ የተከለከለ ነው እንግዲህ ነቢዩ ሚልክያስ ንጹሕ ቁርባን ያለው እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ለአሕዛብ ወንጌል በተሰበከበት ሥፍራ ቤተ ክርስቲያን በተቋቋመበት ቦታ ሁሉ የሥጋውና የደሙ ንጹሕ መሥዋዕት መቅረቡን የሚያመለክት ነው ሌላው ደግሞ የኢሳይያስ ትንቢት ነው እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውኃ ኑ ገንዘብም የሌላችሁ ኑኖ ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ በረከትንም ብሉ ኢዲ ይህ የነቢይ ቃል በመብልና በመጠጥ ስለሚመሠጣው ስለ ምሥጢረ ቁርባን በትንቢትና በምሳሌ እንደ ተነገረ ይታመናል ያፖረሥዉጠሪ ወሮያዕ ዲመሥሪሪም ምሥጢረ ቁርባንን ጌታችን ከሕማማቱና ከሞቱ በፊት በዋዜማው ኀሙስ ማታ መሥርቶቷል ይህም ሰዓት በአይሁድ የቀን አቆጣጠር ወደ ዓርብ ይታሰባል በዚያም ወቅት የኦሪት የፋሲካ በግ የሚሠዋበት ጊዜ በመሆኑ ጌታችን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የኦሪትን መሥዋዕት አሳልፎ መሥዋዕተ ወን ጌልን መሥርቷል በዚያች ምሽት የኦሪቱ በግ መሥዋዕትነት አበቃ ከእን ግዲህ ወዲህ እውነተኛው የእግዚአብሔር በግ ይሠዋል እርሱም የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው ስለዚህ በማዕዱ ዙሪያ ለተሰበሰቡት ሐዋርያቱ በብሉይ ኪዳን ምሳሌ የተመሰለለትን ትንቢት የተነገረለትን አዲሱን ቃል ከኪዳን ጌታ በራሱ ሥጋና ደም መሠረተ የአውነተኛው መሥዋዕት ምሳሌ የሆነው የኦሪቱን ማዕ ድ እየበሉ ሳለ ኢየሱስ እንጀራን ኅብስትን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ ብሹ ይህ ሥጋዬ ነው አለ ጽዋንም አን ሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው በማለት ምሥጢረ ቁርባንን መሠረተ ማቴ ኪዳን ማለት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባውን ቃል ኪዳን የሚያመለክት ነው በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ከቤተ እሥራኤል ጋር ቃል ኪዳን የገባው በእንስሳት ደም ነበር ዘፀ ያን ጊዜ ቤተ አሥራኤል ቃል የገቡት ሕገ ኦሪትን ሊፈጽሙ አሠርቱ ትእዛዛትን ሊጠብቁ ሥርዓቱን ሊያከብሩ ነበርጉ እግዚአብሔር ደግሞ በበኩሉ አምላካቸውና ባለዛር ወዐርዐ ትምህርተ ዛደማናትና ክርስቲያናዊ ሕይወት ጠባቂያቸው ሊሆን ምድረ ርስትንም ሊያወርሳቸው ተስፋ ሰጣቸው ዕኔ ገባላቸው በወንጌል ግን እግዚአብሔር ቃል ኪዳን የገባው በልጁ ደም ነው እግዚአብሔርም የፈጸመልን አዲሱ ኪዳን ከብሉይ ኪዳን እጅግ የ ነው ምክንያቱም በክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን ደም ኃጢአታችን ተወግዶልናል ከእግዚአብሔር ታርቀናል የእግዚአብሔርን ልጅነት አግኝተናል እግ ለ ብሔርም አባት ሆኖን የመንግሥቱ ወራሾች እንድንሆን አብቅቶናል ስለ ይህን ወሰን የሌለው እስከ ሞት ድረስ የወደደንን የክርስቶስን ፍቅር እያሰብን እግዚአብሔርን በልጁ ሰም ዘወትር ለማመስገን ወንድሞቻችንንም ለማፍቀርየ ችግረኞችንም ለመርዳት የወንጌልንም ትእዛዝ ለመፈጸም እኛም በበኩላችን ቃል መግባት ይኖርብናል ቃል ኪዳን ከገባንበት ዋናው ነገር በቆረብንና ቅዳሴ ባስቀደስን ቁጥር የበደላችንንና የኃጢአታችንን ሥርየት ያገኘንበትን ከእግዚአብሔር የታረቅ በትን የክርስቶስን ሕማምና ሞት ማሰብና ማስታወስ ነው ስለዚህ ነው ጌታችነ ኅብስቱን አንሥቶ ባርኮና ቆርሶ ለሐዋርያቱ ከሰጣቸው በኋላ ስለ እናንተ የሚ ሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት ብሎ ያላቸው ሉቃኾ መታሰቢያዬ የተባለው ስለ ሕማምና ሞቱ መሆኑንና ይህንን ም የሞቱን ዜና የመስቀሉን ነገር ጌታ እስኪመጣ ድረሰ በምሥጢረ ቁርባን ከ ማካኝነት እንደሚነገር ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንማራለን ኛቆሮ ዛሬም በጸሎተ ቅዳሴ ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ የተባለውን እያዜምን እናሰታውሰዋለን በምንቆርብበት ጊዜ የምናየው የተፈጥሮ ኅብስትና ወይን ብቻ መሰሎን እንዳንሳሳት የማይታየው መለኮት የተዋሐደው የጌታ ሥጋና ደም መሆኑን አምነን መቀበል አለብን አለበለዚያ በራሳችን ላይ ፍርድን እናመጣለን ሳይገባው ራሱን ሳይፈትንና ሳይመረምር የሚቆርብ የጌታን ሥጋ ሰለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና በማለት ይኸው ሐዋርያ ያስጠነቅቀናል ስለዚህ ሳይገባው ይህን እንጀራ ኅብስት የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ፅዳ አለበት ሰው ግን ራሱን ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ከኅብስቱ ይብሳ ከጽዋውም ይጠጣ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና ይጠጣልምና ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል ራሳችንን ብን መረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኩነን በጌታ እንገሠጻለን ኛቆሮ ያምሥጪሪ ዌረያ ዖሟጀ ዲጋ የሚታየው ኅብስትና ወይን በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ በክርስቶስ ቃል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በካህኑ ጸሎት ወደ ጌታ ሥጋና ደም መለወጣቸውን በሙሉ ልብ አምነውና በንስሐ ተዘጋጅተው ለማቀበሉ ሁሉ በወንጌል የተጻፈውን የማይታየውን ጸጋ ለማግኘት ይችላሉ የሚከተሉትን የእግዚአ ብሔር ጸጋ ማግኘት ለአማኞች ሁሉ ከፍተኛ ጥቅምና እድል ነው የመጀመሪያው ጸጋ ሰውና እግዚአብሔርን ያራራቀውን ኃጢአትን ማስወገድ ነው ስለዚህ ነው የቁርባን ምሥጢር ሲመሠረት ጌታችን ይህ ደሜ ነው ለብዙዎች የኃጢአት ሥርየት የሚፈሰው በማለት የጸጋውን ስጦታ የጀመረው ማቴ የኃጢአት ሥርየት ከተገኘ ከእግዚአብሔር ጋር እርቅና ሰሳም ይወርዳል እርቅ ከተገኘ ደግሞ ሌሎቹ ሰጦታዎች ደግሞ ይጨመራሉ ኃጢአታቸው የተተወላቸው ብፁዓን ናቸውና መዝ ዝነገነገርህኽ ትምህርተ ዛዘመናትና ክርስቲያናዊ ሕይዉት ከዚህ ቀጥሎ በምሥጢረ ቁርባን የምናገኘው ጸጋ ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነን በኀግብረት መኖር ነው ይህም ማለት እኛ በእርሱ እርሱ በእኛ ይኖራል ማለት ነው ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእር ሱ እኖራለሁ በማለት ጌታ አረጋግጦልናል ዮሐ ነገር ግን ከቁርባን እርቀን ሥጋውና ደሙን ሳንቀበል ብንቀር በራሳችን ሕይወት አይኖረንም ምክንያቱም አንዲት የወይን ሐረግ ከወይኑ ግንድ ተለይታ ለመኖር አት ችልምና ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው እውነት እውነት እላችኋለሁ የወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስን ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም ዮሐ እንግዲህ የመጨረሻውን ጸጋ የዘላለም ሕይወትን የምናገኘው ለትንሣኤውም የምንበቃው በሥጋና በደሙ ነው ሥጋዩን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻው ቀን አሥ ነሣዋለሁ ዮሐ ከላይ ከተጠቀሱት ጸጋዎች ሌላ ምሥጢረ ቁርባንን በንስሐና በጸሎት ሆኖ በሚገባ ተዘጋጅቶ የሚቀበል ሁሉ ነፍሱን ከመራብና ከመጠማት ያድናታል ምክንያቁም ሥጋውና ደሙ እውነተኛ መንፈሳዊ ምግብ ስለሆ ነ ነው ኢየሱስም እንዲህ አላቸው የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚግመጣ ከቶ አይራብም በእ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠ ማም ዮሐዐ ምሥጢረ ቁርባን የሚያስገኘው ጸጋ ሰውን ከእግዚአብሔር ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ሰውንና ሰውንም ያቀራርባል ስለዚህ የክርስቶስን ሥጋና ደም የተቀበሉ ሁሉ እርስ በርሳቸው በፍቅር የተሳሠረ ኀብረትና አንድነት አላቸው ምክንያቱም በቁርባኑ ሁሳችንም የክርስቶስ አካልና አባል ሆነናልና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ሁላችንም ከአንዱ ኅብስትና ጽዋ ተሳትፎ ስላለን ነው የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደ ለምን። ሐዋርያው ጳውሉስም የክህነት ሹመት ከመሰጠቱ በፊት በጥንቃቄ እንዲሆን በማሰብ መልካም ጠባያቸውና አኗኗራቸውን በማስመልከት መመረጥና መሾም ስለሚገባቸው ካህናት መመሪያ አዘጋጅቷል ኛጢሞ ቲቶ በዚህም ምክንያት ፈጥኖ እጆቹን በመጫን ካህናትን እንዳይሾም ጢሞቴዎስን አስጠንቅቆታል ኛጢሞ ዛሬም በቤተ ክርስቲያናችን ይህ መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን ተደንግጓል ዲቁና ለመቀበል የሚፈልግ ሁሉ ከቃል ትምህርቱ ጋር ትምህርተ ሃይማኖትን ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን እና ትእዛዛትን ሁሉ በመጠኑም ቢሆን ማወቅ ይኖርበታል ከዚህም ጋር በመልካም ጠባዩና በታዛዥ ነቱ የተመሰከረለት ካልሆነ ክህነት ባይቀበል የተሻለ ነው እንደዚሁም የቅስና ማዕረግ ለማግኘት የሚመጣ ሁሉ ስለ ሃይማኖትና ስለ ምሥጢራት ጠንቅቆ ማወቅ አለበት በተለይም ሕገ እግዚአብሔርንና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አውቆ የሚያሳውቅ ሕዝብን የሚያስተምርና የሚመክር የሚገሥፅም እንዲሆን ያስፈልጋል ከዚህም ጋር የብሉያትና የሐዲሳት መጻሕፍትን ያወቀ በተለይም ቅዱስ ወንጌልንና መልእክታትን ያጠና በተጨማሪም ስለ መልካም ጠባዩና አኗኗሩ የተመሰከረለት ከሆነ ለሥልጣነ ክህ ነት ብቁ ይሆናል ነገር ግን ይህንን የትምህርት ችሎታና የጠባይ ሁኔታ ሳ ያሟሉ በግድ ክህነት ይሰጠን ማለት ለተቀባዩም ሆነ ለሰጪውም በእግዚአብሔር እና በሰው ዘንድ ከማስወቀሱም በላይ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ያልተጠበቀ ቾግርን ያስከትላል እውነተኛ ካህን ከእምነት በአፍአ ማለት ከእምነት ውጭ ያሉትን ሰዎች አስተምሮ የሚያሳምን መናፍቃንን ተከራክሮ የሚረታ ወሆን አለበት ያሃፇ ጋይሪም ሃያራምት ሥጋም ናሦው ካህናት ሁሉ በጥንቃቄ ተመርጠው እንዲሾሙ የተባለበት ምክንያት ሥራቸውና ኃላፊነታቸው ከፍተኛ በመሆኑና የክርስቶስም አደራና ትእዛዝ ያለበት ስለሆነ ነው ክርስቶስ ሐዋርያትን መርጦ የሾማቸው ሦስቱን ከበይት ተግባራት እንዲፈጽሙ ነው ሂዱና አስተምሩ የሚለው ትእዛዝ ትምህርተ ፀንጌኣ ለሰው ልጆች ከሁሉ በፊት የሚያስፈልግ መሠረታዊ ነገር መሆኑን ያስረዳናል ማቴ ባለዛር ወዐርዐ ትምህርተ ዛደማናትና ክርስቲያናዊ ሕይዉት ስለዚህ የካህን የመጀመሪያ ተግባሩ ጸሎትና ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማር መትጋት ነው ስለዚህ ነው ሐዋርያት ሌላውን ሥራ ለሌላ ሰጥተው እኛ ግን በጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን ያሉት የሐዋሥራ ሁለተኛው ተግባር የሕዝቡን ኃጢአት ማስተሥረይና የቅድስናን ጐዳና ማስተማር ነው ዮሐ ኛጴጥኑዙ ይህም ማለት ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን መፈጸምና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለምእመናን ሁሉ እንዲዳረስ ማድረግ ነው ሦስተኛው የካህን ተግባር በጐን ጠብቅ ግልገሎቼን አሠማራ የተባለው ትእዛዝ ነው ዮሐኑ መንጋውን የመጠበቅና የማስተዳደር ሥልጣን ለጳጳሱ ብቻ የተተወ ሳይሆን እያንዳንዱ ካህን በየአጥቢያው የሚገኙትን ምእመናን ከነጣቂ ተኩላዎች ከመናፍቃንና ከከሐዲዎች እንዲሁም ዲያብሎስ ካጠመደው ከኃጢአት ወጥመድ እንዲድኑ በየጊዜው ሳይሰለቹ ማስተማርና መምከር መገሠዕና መሠሯሠሰከር ያስፈልጋል ካህናት ሐዋርያዊ ተግባራቸውንና ተልእኳቸውን ለመፈጸም መን ፈሳዊ አገልግሉታቸውን ለማከናወን የምእመናንን ትብብር ይጠይቃሉ ስለዚህ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ለሁላችንም ስለሆነና ትእዛዙንም መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ስለሆነ ምእመናን ሁሉ በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን እንዲተዳደሩና እን ዲመሩ ቤተ ክርስቲያን አደራ ትሳላለች ያያዕታ ማሪርም ፖሥዕንም ናቻው ሐዋርያዊ ትውፊት ያላቸው አብያተ ክርሰቲያናት ሦስት የክህነት ማዕ ርጋት አሏቸው በመጀመሪያ ደረጃ የኤሏስ ቆጸጳሱ ማዕርገ ክህነት ነው ኤ ሏስ ቆልሱ ጳጳሱ በሐዋርያት ወንበር ላይ የተቀመጠ ስለሆነ ሥልጣነ ክህነቱ ምሉዕ ነው አይከፈልበትም ሐዋርያዊ ትውፊት ያለው ሐዋርያትን መስሎ ሐዋርያትን አክሉ የሚሠራ የክርስቶስ እንደራሴና ባለ ሙሉ ሥልጣን ስለሆ ነ በቤተ ክርስቲያን ከፍተኛውን ማዕርግ ይይዛል ሥልጣነ ክህነት በምልዓት ከእርሱ ብቻ ስለሚገኝ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን በአንብሮተ እድ የመሾም መብትና ኃላፊነት የእርሱ ብቻ ነው ሜሮን የመባረክ አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንንና ንዋያተ ቅድሳትን የመባረክ ሥልጣን የኤኢስ ቆጸሱ ነው በክህነት ማዕረግ ሁለተኛውን ቦታ የሚይዘው ቄሱ ነው ከኤሏስ ቆጸሱ ቀጥሎ የሚገኘው ደረጃ የቄሱ ስለሆነ ክህነት ከመሰጠት በስተቀር ስድስቱንም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ይፈጽማል ሌሎቹንም መንፈሳዊ አገልግሎቶች ያከናውናል ለምእመናንም የወንጌል ትምህርትና ምክር መስጠት መብቱና ግዴታው ነው ለምእመናንም አበ ነፍስ በመሆን በመንፈሳዊ አባትነቱ መን ፈሳዊ ልጆቹን ይጠብቃል የችግራቸውም የኀዘናቸውም ተካፋይ ይሆናል በሦስተኛ ማዕርገ ክህነት ተመድቦ የሚገኘው ዲያቆኑ ነው እርሱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ለመፈጸም መብት ባይኖረውም ቄሱና ኤሊስ ቆጸጳ ሱ ምሥጢራቱን በሚፈጽመበት ጊዜ በመርዳት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሥርዓትን መጠበቅ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ማስተማርና መስበክ ሌሎችንም መንፈሳዊ አገልግሎት መፈጸምና ለጳጳሱና ለቄሱ መታዘዝ የዲያቆኑ የሥራ ድርሻ ይሆናል ሐዋርያት ሰባቱን ዲያቆናት የሾሙበት ዋና ምክንያት በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ለሚያስፈልገው መንፈሳዊና ባለዛር ወዐርዐ ትምህርቱ ሃይማኛቶሃ አርሳተያናዊ ሕደቋት ግኅበራዊ አገልግሎት እንዲረዱዋቸው መሆኑን እናስታውሳለን የሐዋ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተጨማሪ የሴት አገልጋዮች ዲያቆናውያት የተባሉ እንደነበሩ ተጽፏል ቲቶ ዲድስቅልያ እነር ሱም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተወሰነ ሥራ ነበራቸው ለሴቶች ክርስቲያኖች ለምእመናት አገልግሎት በመስጠት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሴቶች መቆሚያ በኩል ተገኝተው ሥርዓትን በመጠበቅና በማስተናበር በመምከርና በመርዳት ጉዳይ ያላቸውንም ሴቶች ወደ ቄሱና ጳጳሱ በማቅረብና ለችግራቸውም መፍትሔ ግስገኘትና ሌሎችም የመሳሰሉትን መንፈሳዊ ተግባራት ይፈጽማሉ ከዚህም በላይ ሴቶች በሚጠመቁ ጊዜ ቅዱስ ሜሮንን በመቀባት ይረዱ ነበር ሐዋርያው ጳውሎስ እድሜያቸው ከስድሳ ዓመት ያላነሰ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን እንዲመዘገቡ የፈቀደው ስለ ዲያቆናውያትም ጭምር እንደሆነ ይታመናል በኛጢሞ ምሏመሂናሃ ዳዷዴሥሰጳ ቋ ዖሦዕጠው ዱዴ ፖሥጎም ሪው ምሥጢረ ክህነት ሲፈጸም የሚታየውና የሚደረገው ነገር የጳጳሱ አንብ ሮተ እድና የጸሎቱ ሥነ ሥርዓት ነው በዚህ ሥርዓት ማለት በጳጳሱ አማካኝ ነት ደግሞ እግዚአብሔር የማይታየውን ጸጋ ለካህኑ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይ ሰጠዋል ሐዋርያው ጳውሎሰ ስለ አንብሮተ እድ የጻፈው ነገር የእግዚአብሔርን የጸጋ ስጠታ ያሳስበናል እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ ኣሳ ሰብለሁ ኛጢሞ ኛጢሞኑ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ የግይታይ ጸጋ ሲሆን የካህኑን ሥልጣንና ተግባር የሚያስፈጽምለት ለምእመናን የሚያበረክተውን አገልግሎት የሚያሠምርለት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ረድኤት ታላቅ ነው በዚህ ምሥጢር አማካኝነት ክርስቶስን ወክለው እንደ ሐዋርያት ሥልጣን አግኝተው ሦስቱን ምግባራት ለማከናወን የሚያስችል ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ይቀበላሉ እንደ ክርስቶሰ ነቢይ ካህንና ንጉሥ ሆነው የእርሱን ቤተ ክርስቲያን እንዲያገለግሉ ጸጋ ተሰጥቷቸዋል ማለት ነው እንደ ነቢይ ወንጌልን የግስተማር እንደ ካህን ኃጢአትን የማስተሥረይ እንደ ንጉሥ መንጋውን የመጠበቅና የማስተዳደር ሥልጣን አላቸው ስለዚህም ክርስቶሰን የሚያስመስላቸው ታላቅ የጸጋ ስጦታን እንዳገኙ እናምናለን የክህነት ሥርዓት ለካህናት መጠቀሚያ የሚመስላቸው ቢኖሩ ተሳ ስተዋል እግዚአብሔር ሥራውን ለመሥራትና ሰዎችን ለማዳን ሲፈልግ በ ሰፆች አማካኝነት ይሠራል በጥንት ጊዜ እግዚአብሔር ነቢያትን በመሳክ ፈቃዱን ይገልጻል ትእዛዛቱን ሰከብራል በኋለኛውም ዘመን ክርስቶስ ሰው በመሆን ሰለ ሰዎች መዳን ሲል ራሱን ካህን ራሱን መሥዋዕት አድርጐ ዓለ ምን አድናል ሥራውንም ፈጽሞ ከሰማያዊ ስፍራው ተመልሷል ይህንን የማን ሥራውንየምሥራቹን ዜና ለሕዝብ የሚያደርሱ መልእክተኞች በግድ ያስፈልጋሉ ያለ መልእክተኛ መልእክቱ ከግቡ አይደርስምና ሐዋርያት ግለትም ልዑካን መልእክተኞች ማለት ነው ስለዚህ የመዳኑን መልእክት ለሕዝቡ ለማድረስ የምእመናኑንም ኃጢአት ለማስተሥረይ ሐዋርያትንና አርድእትን ካህናት አንዲሆኑ ማለት እንዲያገለግሉ መርጦ የሾማቸው ራሱ ክርስቶስ ነው ይህንንም ያደረገው ለምእመናን መጠቀሚያ ለኃጢአታቸው ማስተሥረያና ከእግዚአብሔር መታረቂያ እንዲሆን በግዕብ ነው በተሰጣቸውም የአገልግሎት ጸጋ ሰውን ከእግዚአብሔር ያስታርቃሉ ኛቆሮ ስለዚህ የዛሬዎቹ ካህናትም ሐዋርያትን ኤ ባለዛር ወዐርዐ ትምህርተ ዛሄማናትና ክርስቲያናዊ ሕይወት «ሓሙ በጻ መ ዘጩ በመተካት በተሰጣቸው ሐዋርያዊ ጸጋ ምእመናንን እንዲያገለግሉ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ረድኤት እንደማይለያቸው የቤተ ክርስቲያን መሥራች የሆነው ክርስቶስ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ ያለው ቃል ሕያው ምስክር ሆኖ ለዘላለም ይኖራል ማቴ ምሥጢረ ተክሊል ፓረዮኙሙናኖ ለመሠሥራሪረቋ ምሥጢረ ተክሊል ማለት የሙሽራውና የሙሽራይቱን የጋብቻ ቃል ኪዳን በሃይማኖት የሚያጸና የጋብቻ ግዴታን ለመወጣት የሚያሰችል በፍቅር የሚያስተሣሥር ዘላቂ አንድነትን የሚያስገኝ ከቅዱስ ቁርባን ጋር የሚሰጥ የጸጋ ምሥጢር ነው ቅዱስ ጋብቻ ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ፍቅርና አን ድነት ምሳሌ ስለሆነ ታላቅ ምሥጢር መሆኑን ያስረዳናል ኤፌ ጌታችንም በቃና ዘገሊሳ ሠርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን ለውጦ ለሙሸሮቹና ለሠርገኞቹ ሁሉ መስጠቱ በደመ የዋጃትን የሙሽራይቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ሆኖ ይተረጉማል ዮሐ በተአምር የተገኘው ወይን በጸሎተ ኀሙስ ማታ ጌታ የባረከውን ጽዋ ያመሰክተናል ስለዚህ የተክሊል ወይም የእውነተኛ ጋብቻ ምሥጢር ከቅዱስ ቁርባን ጋር የተያያዘ ስለሆ ነ ያለቁርባን የሚፈጸም ተክሊል መንፈሳዊ ትርጉም የለውም ከላይ እንደ ተጠቀሰው ጌታችን ከቅድስት እናቱ ከድንግል ማርያምና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በሠርግ ቤት በመገኘት በእመቤታችን አማላጅነት ተአ ምራቱን በመግለጽ ሠርጉን በመሳተፍ የታደሉትን ሙሽራና ሙሽሪት በመባ ረክ የቅዱስ ጋብቻን ምሥጢር ከሁሉ በሚቀድመው ተአምራቱ መሥርቶታል ይህም በኋላ ጊዜ ጌታ በአዲስ ኪዳን በደሙ ለሚመሠርታት ቤተ ክርስቲያን ለእውነተኛው ቃል ኪዳንና አንድነት ማስረጃ እንዲሆነው በሠርጉ ሥነ ሥርዓት ተገኝቶ የደሙ ምልክት የሆነውን መልካሙን ወይን አስገኝቶላቸዋል ስለዚህም በቅዱስ ጋብቻ ተመሥርተው የሚኖሩ ሙሽሮች የተቀደሱ አባትና እናት ይሆናሉ ከተቀደሱ ወላጆችም የሚያምኑና የተጠመቁ ልጆች የቤተሰብ አባሎች ይፈጠራሉ የሚያምኑ ቤተሰቦችም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አካላትና አባላት ይሆናሉ ሰለዚህ ቅዱስ ጋብቻ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያለው ግንኙነት ምሳ ሌያዊ ብቻ ሳይሆን እውነተኛና መሠረታዊ ሁኔታ እንዳለው እንገነዘባለን ይህም ማለት ቅዱስ ጋብቻ ለእውነተኞቹ የቤተ ክርስቲያን አባላት ብዛትና ጥራት እድገትና መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ማለት ነው ከሥነ ፍጥረት ጆምሮ ቅዱስ ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት ብቻ ተመሥርቶ የሜፈጸም መሆኑን ጌታችን አስተምሯል ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል በማለት አስረድቷል ማቴ የፍቺውን ደብ ዳቤ ከሰጣት በኋላ ባል ሚሰቱን ለመፍታት ይችላል በማለት ሙሴ የፈቀደበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጌታ ተጠይቆ መልስ ሲሰጥ ሙሴ ይህን ያደረገው ለለ ልባቸው ክፋት እንደሆነ ገልጸ አስረድቷቸዋል ከጥንት ግን አንድ ወንድና አን ዲት ሴት ብቻ ነበሩ እነርሱም አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለ ዝነገነገርህኽ ትምህርተ ዛክማናትና ክርስቲያናዊ ሕፀወት የውም ማቴ ዘፍ ዘዳ ስለዚህ ጋብቻ በአን ድ ወንድና በአንዲት ሴት ብቻ የተመሠረተና መፋታትም የተከለከለ መሆኑን ከቅዱስ ወንጌል ተምረናል ልዩ ስጦታ ካላቸው ጥቂት ሰዎች በስተቀር ማንኛውም ክርስቲያን የቅዱስ ጋብቻን ሥርዓት መፈጸም ይኖርበታል ጋብቻ አያስፈልገኝም ብሎ ለብቻ በንጽሕና በድንግልፍ መኖር ለሁሉም ሰው እንደማይቻል በወንጌል ተጽፏል ባልና ሚስት ሳይፋቱ መኖር እንዳለባቸው ጌታ ስለ አስተማረ ደቀ መዛሙርቱ የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምም አ ፅት እርሱ ግን ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም በእናት ግኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው ማቴ እንግዲህ ከዚህ እንደ ተገለጸው ከጥቂቶች ማለት ከሕፅዋን ከደናግልና ከመነኮሳት በስተቀር ሁሉም በጋብቻ ሕግ መኖር እንዳለበት ያስገነዝበናል ደይጋቋያፖ ማና ጥፇም ዙ ጋብቻ በእግዚአብሔር የታዘዘ የተፈጥሮ ሕግ ቢሆንም ዋናው ዓላማው ልጆችን ለመተካት የሰው ዘርን ለማብዛት መሆኑ የተጻፈ ነው ዘፍ እግዚአብሔር እንደ መላእክት የመጀመሪያውን ሰው ኣዳምን በዘር በለደት አልፈጠረውም ከአዳምና ከሔዋን በኋላ የተፈጠሩት ሰዎች ግን በዘር በሩካቤ የተገኙ ስለሆነ ወላጆች ልጆችን በማስገኘት የሰው ዘር በምድር ላይ እን ዲበዛ በማድረግ የእግዚአብሔር ሥራ ተባባሪዎች ናቸው ስለዚህም ወሳጆች በጎብረተሰቡ ዘንድ የተከበሩ እንዲሆነ ከኣሠርቱ ትእዛዛት አንዱ ስለ እነርሱ ከብር የታዘዘ ነው ዘፍ። ወላጆችም ከዚህ ክብር የደረሱት ቅዱስ ጋብቻን በማክበራቸው ነው ጋብቻቸውን በምሥጢረ ተክሊል የፈጸሙ እስከ መጨረሻውም በቅዱስ ቁርባን የጸኑ አባትና እናት ክብራቸው አጥፍ ድርብ ነው በምድርም በሰማይም የተመሰገኑ ናቸው ሁለተኛው የጋብቻ ዓላማና ጥቅም እርስ በእርስ መረዳዳት ነው እግዚአብሔር አምላክም አለ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት በማለት ሔዋንን ፈጠረ ሁለቱም እየተረዳዱ እንዲኖሩ ሆነዋል ዘፍ ከአንድ ብርቱ ሁለት መድኃ ኒቱ እንዲሉ ዛሬም ብዙ የክርስቲያን ቤተሰቦች በቅዱስ ጋብቻ በመጽናት የእግዚአብሔርን ረድኤት በማግኘት እርስ በእርሳቸው በመተባበርና በመረዳዳት ኑሯቸውን አቸንፈው የእግዚአብሔርንም ትእዛዝ ፈጽመው መገኘታቸው ሁላችንንም ያስደስተናል እንግዲህ ጋብቻን ያልመሠረቱት ሁሉ የእነዚህ ዓይ ነት ቤተሰቦችን አርአያ እንዲከተሉ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች የጋብቻ ሦስተኛው ዓላማና ጥቅሙ ከአመንዝራነት ለመዳንና የሥጋ ፍትወትን ለመቆጣጠር እንደሆነ ይታመናል ኛቆሮ ማቴ ዚዛ ከዚህም ሌላ በዝሙት ጠንቅ ከሚመጣው የሥጋ ደዌና የመንፈስ ጭን ቀት የቤተሰብ ችግርም የሚዳነው የቅዱስ ጋብቻን ዓላማ በመጠበቅ ነው በተለይም በዘመናችን በተከሠተው ችግር ምክንያት አንድ ወንድ በአንዲት ሴት አንዲት ሴት በአንድ ወንድ እንዲጸኑ ክርስቲያን ያልሆኑት ሁሉ የሚያስተምሩበት ዐቢይ ርእስ ሆኗል እንግዲህ ሁላችንም የጋብቻ ዓላማና ጥቅም ትልቅ መሆኑን አውቀን ማሳወቅ ጠብቀን ማስጠበቅ ለኅብረሰተቡም አ ርአያ መሆን ይገባናል በቅዱስ ጋብቻ መጽናት በእዚአብሔር ዘንድ ዋጋን ባለዛር ወዐርዐ ትምህርተ ዛይማናትና ክርስቲያናዊ ሕፀዉት ያሰጣል በሰውም ዘንድ ያስከብራል ለቤተሰቡ ሁሉ ጤንነትንና ሰላምን ያስገኛል ያዖምሥጢዉሪ ፖቃፈጳ ጸጋ ከላይ እንደ ተጠቀሰው ምሥጢረ ተክሊልን ከቅዱስ ቁርባን ጋር በመፈጸም የማይታየውን ታላቁን የእግዚአብሔር ጸጋ እንቀበላለን ከሥጋዊ አንድነት በላይ የሚሆነውን የመንፈስ አንድነትና ፍቅርን በተጠናከረ ሁኔታ እናገኛለን በተክሊል የምናገኘው ጸጋ ጋብቻችንን የተከበረና መንፈሳ ችንንም የተቀደሰ ያደርገዋል መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ን ጹሕ ይሁን የተባለውን ለመፈጸም ያስችለናል ዕብ እንግዲህ ይህን የተሰጠውን የአንድነት ጸጋ ዘላቂ ለማድረግና የእግዚአብሔርን ረድኤት ለማብዛት በየጊዜው ሁለቱም በአንድነት መቁረብና በአንድነት የኅብረትና የቤተ ሰብ ጸሎት ማድረግ ያስፈልጋል ከዚህም ጋር ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት ለሕይወታቸው የሜያስፈልገውን መንፈሳዊ ምግብ ያገኛሉ የነፍስ አባትንም በማቅረብ ችግር ቢኖርም ባይኖርም ስለ ኑሮ ሁኔታ ተገላልጦ መወያየትና ከመምህረ ንስሰሐቸውም ምክርና ትምህርት ጸሎትና ቡራኬን መቀበል እጅግ ይጠቅማል እንደዚህ የሚያደርጉ ቤተሰቦች መንፈሳዊ ኃይልን ያገኛሉ የጋብቻ ሕይወታቸው ይታደሳል ሥጋዊና መንፈሳዊ አንድ ነታቸው ይጸናል እንግዲህ የጋብቻን ግዴታ ለመወጣት ልጆችን በክርስቲያናዊ ሥርዓ ት አሳድጐና አስተምሮ ለወግ ለማዕረግ ለማብቃት ጊዜያዊ የኑሮ ችግሮችን ለመቋቋም የሚያጋጥመንንም የቤተሰብ ፈተና ለማለፍ ከራስ ጥረት ጋር በእግዚአብሔር ረድኤት መተማመን ነው በተለይም አንዱ የሌላውን ሸክም ተሻክሞ አንዱ የሌላውን ጉድለት ችሎና ተቻችሎ እስከ ሞት ድረስ በትዕ ግሥት በመኖር ፍቅርን እስከ መቃብር ለማድረስ መንፈሳዊ ተጋድሎ የሚያደርጉ ቤተሰቦች ብፁዓን ናቸው ከእግዚአብሔርም የማያልፈውን ተድላና ደስታ ያገኛሉ የምሥጢረ ተክሊልም ዓላማና ፍጻሜ ወላጆች በቅዱስ ቁርባን ጸንተው የዘላለም ሕይወትን ጸጋ እንዲቀዳጁ ለማድረግ ነው ተክሊል ሲፈጽሙ ቤተ ክርስቲያን ያደረገችላቸውን አክሊል አክብረው በመጠበቅ የትዳርንም ውጣ ውረድ በትፅግሥት በመቻል እስከ መጨረሻው ለኑሮ ጓደኛቸውና ለእግዚአ ብሔር ታማኝነታቸውን ካስመሰከሩ የሰማያዊውን የሕይወት ኣክሊል ይቀበላሉ ሐ የነፍስና የሠጋ ፈውስ የሚገኝባቸው ምሥጢራት እስከ አሁን የተመለከትናቸው ሦስቱ ምሥጢራት ጥምቀት ሜሮንና ቁርባን በአንድ ወገን ተቆጥረው ስለ መጀመሪያውና መሠረታዊው የክርስቲያን ሕይወታችን ያስረዱናል ከውኃና ከመንፈስ በመወለድ ኣዲስ ሕይወት እን ድናገኝ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንድንጠናከር መንፈሳዊ ምግብ በመብላት እን ድናድግና ወደ ሙሉ ክርስቲያናዊ ሕይወት እንድንደርስ ያበቁናል ከእነርሱ የሚገኘው ጸጋና ረድኤት መለኮታዊ ባሕርዩን ክብሩን ለመሳተፍ እንድንችል እድል ይሰጡናል የኛን ፈቃድ በማነሣሣትና በማስተባበር የተሰጡን የጸጋ ስጦ ታዎች ራሳችንን ከክፉ ነገር እንድንጠብቅና የተቀደሰውንም ሕይወት እንድንኖር ያስችሉናል ዳሩ ግን በዚህ በክፋትና በበደል በተያዘ ዓለም ውስጥ የምንኖር ስለሆነ የተ ሰጠንን ጸጋ እንድንተውና ከብዙ መከራና ፈተና ውስጥ እንድንወድቅ የሚሆን ባለዛር ወዐርዐ ትምህርተ ዛይመናትና ክርስቲያናዊ ሕፀጠት በት ጊዜ አለ ከሥጋዊ ፈቃዳችንና ከምድራዊ ኑሯችን ውሱንነትና ደካማነት የተነሣ የሚያጋጥሙን የክፋት ኃይሎች መንፈሳዊና ሥጋዊ ሕይወታችንን በማጐሳቆል ለልዩ ልዩ ሕማምና አደጋ ይዳርጉታል የሰው ልጆች ኑሮ ለልዩ ልዩ ኃጢአትና በደል ለሕማምና ደዌ ለጭንቀትና ለሥቃይ የተጋለጠ መሆ ኑን የሚያውቅ ቸርና መሐሪ የሆነው አምላካችንና መድኃኒታችን ለነፍሳችንና ለሥጋችን ቁስል መጠገኛ የሚሆነውን የፈውስና የመዳን ምሥጢራትን በቅድሚያ አዘጋጅቶልናል እነርሱም ለነፍሳችን ቁስል መዳኛ ምሥጢረ ን ስሐ ለሥጋችን ደግሞ ምሥጢረ ቀንዲል ስለሆኑ ስለ እነርሱ እንደሚከተለው ልናውቀው የሚገባንን ያህል በመጠኑ እንገልጻለን ምሥጢረ ንስሐ ደቃጋ ለሪፈያሂሪምኖ ምታ ምሥጢረ ንስሐ ማለት ምን ማለት መሆኑን ለማወቅ በቅድሚያ አስፈላጊ ነቱን ብንመለከት ወደ ፍሬ ነገሩ ለመድረስ ይረዳናል እንደ ታዘብነው ጥቂት ክርስቲያኖች ከተጠመቁና ከቆረቡ በኋላ አውቀውም ይሁን ሳየያውቁ ለቀላልም ሆነ ለከባድ ኃጢአት ተጋልጠው በጨለማ ውስጥ ሲመላለሱ እናያቸዋለን ቁጥራቸው አይብዛ እንጂ አንዳንዶቹማ በሰመ ክርስቲያን ከባድ ወንጀል በመፈጸም በኃጢአት አዘቅት ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ ሁኔታውን በጽሞና ለተመለከተው ሐቀኛ ክርስቲያን ሁሉ ጉዳዩ እጅግ ያሳዝናል ነገር ግን እንዲህ ያለው ሁኔታ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ የነበረ ነው ለምሳሌ በቆሮንቶስ ክርስቲያኖች መካከል ከነበሩት አንዱ ስሙ ያልተጠቀሰ ሰው ከፍተኛ የዝሙት ኃጢአት እንደ ፈጸመና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም እንደገሠፀው እናነባለን ኛቆሮ እንዲሁም ደግሞ ክርስቲያን ከክርስቲያን ወንድሙ ጋር ተጣልቶ ወደ ኢአ ማንያን ፍርድ ቤት ተያይዘው በመሄዳቸው ቅሬታውን ትምህርቱንና ምክሩን ይኸው ሐዋርያ በጻፈው መልእክቱ ገልጸታል ኛቆሮ የሐዋርያው ጳውሎስ ረዳት የነበረ ዴማስ የተባለ ደቀ መዝሙር ይህን ዓለም በመውደዱ ሐዋርያውን ትቶት ሄጳል ኛጢሞ ይህን የመሰለ ታሪክ በብሉይም በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትም ይገኛል ለጌታ ክብር ምስጋና ይግባውና የሰውን መመለሰ እንጂ ጥፋቱን የማይወድ አምላክ የምንመለስበትን የንስሐ መንገድ አዘጋጅቶልናል ከአዳም የወረስነው በኃጢአት የጐሰቆለ ሰውነት ደካማ በመሆኑና በክፉ ምኞቱም እየተ ነዳ ሰውን ወደ ጥፋት ጐዳና የሚጐትተውና የሚጥለው ስለሆነ በጸጋ እግዚአ ብሔር ካልተረዳ በስተቀር ከጥፋት አዘቅት ውስጥ ወድቆ ይቀራል ስለዚህ ለመነሣት የሚረዳውና ለደኅንነቱ የሚያስፈልገው ምሥጢረ ንስሐ በቅድሚያ ተዘጋጅቶለታል እንግዲህ ምሥጢረ ንስሐ ማለት አንድ ሰው ከጥምቀት በኋላ የፈጸመውን ጥፋት አውቆ ሁለተኛ ጥፋትን ላለመድገም ወስኖ በእግዚአብሔርና በካህኑ ፊት ተንበርክኮ በልቡ ተፀፅቶ ኃጢአቱን በመናዘዝ ከኃጢአቱ እሥራት የሚፈታበትና ከእግዚአብሔር ይቅርታን የሚያገኝበት ታላቅ የጸጋ ምሥጢር ነው ከጥምቀት በኋላ የተባለውም በጥምቀቱ ጊዜ ከአዳም የወረሰውን አርሱም የሠራው ኃጢአት ሁሉ የተሠረየለት ስለሆነ ነው ዝነገነገርህኽ ትምህርተ ዛዩማናትና ክርስቲይናዊ ሕፎወት መጪዉሪ ለመራሪ ምሥጢረ ንስሐን የመሠረተ ራሱ ጌታችን ነው ለሰው ልጆች አዛ የሆነው መፍቀሬ ሰብእ ክርስቶስ የኛን ኃጢአት ሁሉ በሰውነቱ ተሸክኞሾ በሕማምና በሞቱ ኣንድ ጊዜ አድኖናል ይህንንም ጸጋ በምሥጢረ ጥምቀት አ ግኝተነዋል ከዚያም በኋላ ለምንፈጽመው በደል ማስተሥረያ እንዲሆነን ለሐዋርያቱና እነርሱንም ለሚተኩት ካህናት ሥልጣንን በመስጠት ምሥጢረ ስሐን መሥርቶልናል ኃጢአትን የማሰስተሥረይ ሥልጣን የእግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ለእኛ ጥቅምና ደኅንነት ሲል ይህን ሥልጣን ለቤተ ክርስቲያን እ ገልጋዮች ለጴጥሮስና ለሐዋርያት ተከታዮች ሰጥቷል ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ እው ነተኛው እምነት ከመሰከረ በኋላ ሥልጣነ ክህነትን ማለት የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ክርስቶስ ሰጥቶታል እንዲህም ብሎታል የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ ይሆናል በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማዴት የተፈታ ይሆናል ማቴ እንደዚሁም ይህን ሥልጣን ለሌሎች ሐዋርያት ሰጥቷቸዋል እውነቅ እላችኋለሁ በምድር የምታሥሩት ሁሉ በሰማይ የታሠረ ይሆናል በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል ማቴ ከትንሣኤው በኋላም የትንሣኤ ዕለት ለሦስተኛ ጊዜ ኃጢአት የማስተሥረይ ሥልጣን ሰጥቶ በመንፈስ ቅዱስ ሰጦታ አረጋግጦላቸዋል አትሞላቸዋል አብ እንደ ላሳከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው ይህንንም ብሎ እፍ አለባቸውና መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል አላቸው ዮሕ እንግዲህ ኃጢአትን የማሰተሥረይ ሥልጣን ለእነርሱ የተሰጠ ሰለሆ ነ በሐዋርያት እግር ለተተኩት ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ለካህናች ኃጢአ ታችንን ከመናዘዝ ቸል አንበል የአንዳንድ ችግረኞች ካህናትንም ሁኔታ በማየት በንቀት ዓይን ማየቱን እንተው ይህ የዓለማዊ ሰዎች አጉል ስሜታዊ አመለካከት ስለሆነ ከዚህ እንራቅ ይልቅስ ሥልጣንን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን አምነን በትኅትና መንፈስ ሆነን ኃጢአታችንን ሥልጣነ ክህነት ላላቸው ቀሳውስት ተናዝዘን የኃጢአትን ሥርየት ማግኘት ታላቅ ጸጋ መሆኑን ተረድተን የምሥጢረ ንሰሐን ሥርዓት መፈጸም ይጠቅመናል ከራሳችን ሐሳ ብና ስሜት ይልቅ ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ ይበልጣል ኃጪልጵሉም ሥረፖ ዳምኛ መፇያምሦ ንስሐ የሚገባ ሰው በቅድሚያ ንስሐ በመግባት ኃጢኣት ሁሉ እን ደሜሠረይና እንደሚደመሰስ ማመን አለበት ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘን ድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም ተብሉ ተጽፏልና የሐዋሥራ እግዚአ ብሔር ንስሐ በሚገቡ ሰዎች ደስ ይለዋል ክርስቶስ ኃጥአንን እንጂ ጻድቃንን ለመጥራት እንዳልመጣ እርሱ ራሱ ተናግሯል ማቴ እውነተኛው ጠባቂያችን እረኛችን ክርስቶስ ዘጠና ዘጠኙን በጐች ትቶ የጠፋችውን አንዲት በግ እንደ ፈለጋትና ባገኛትም ጊዜ በጫንቃው ተሸክሞ ወደ ቤቱ እንዳመጣትና ታላቅ ደስታም እንዳደረገ በምሳሌ አስረድቶናል እንዲህም አለ ንስሐ ከማያሰፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአ ተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል ሉቃ የአንድ ኃጢአተኛ መመለስ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ታላቅ ደስታን ያስከትላል ሉቃ እን ግዲህ እግዚአብሔር ንሰሐ የሚያስፈልገንን እኛን ኃጢአተኞችን ለመቀበልና ይቅር ለማለት ምን ያህል ደስ እንደሚለው መዘንጋት የለብንም አርሱ ባለዛር ወዐርዐ ትምህርተ ዛፎማናትና ክርስቲወናዊ ሕይወት ጌታችን መፍቀሬ ንስሐ ከባቴ አበሳ ተወካፌ ንስሐ ወሠራዬ ኃጢአት መሆ ኑን ማመን ይኖርብናል አንድ ንስሐ የሚያስፈልገው ሰው በደሌ ብዙ ነው ከእግዚአብሔር ይቅርታን አላገኝም በማለት ያለንስሐ ዝም ብሎ መቀመጥ በገዛ ፈቃዱ ከቀቢጸ ተስፋ ጉድጓድ ውስጥ እንደ መውደቅ ስለሚቆጠር በነፍሱ ላይ የሚያስከትለው አደጋ እጅግ ከፍትኛ ነው ለሰው ልጆች የማይሠረይ ኃጢአ ት አንድ ብቻ ነው ሌሎች ኃጢአቶች ሁሉ ምንም ከባድ ወንጀሎች ቢሆኑም እንኳ ይሠረያሉ ስለዚህ እላችኋላሁ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሠረይላቸዋል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሠረይለትም በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሠረይለታል በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አ ይሠረይለትም ማቴይህም ማለት የእግዚአብሔርን ፍቅር ጣቃለል የክርስቶስን የማዳን ሥራ መቃወም የመንፈስ ቅዱስን የምሕረትና የይቅርታ ጸጋ መሳደብ ስለጀነ ዲያብሎስ ከፈጸመው ኃጢአት እጅግ የከፋ መሆኑን መናገር ነው ለእንዲህ ዓይነቱ ኃጢአት ሥርየት የለም ከዚህ ከተጠቀሰው በስተቀር ለማናቸውም በደል ይቅርታ ይደረጋል በሰው ልጅ ላይ እንኳ ቃል የሚናገር ይሠረይለታል ተብሏልና እንግዲህ ኃጢአታችሁ ምንም ከባድ ቢሆን ሥርየትን እንደምታገኙና ከበደላችሁም አእንደምትነጽ አምናችሁ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አ ለባቸሁ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነፃለች እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች ኢሳ ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል ይነሣልም የተባለውን እያስታወስን በቀቢጸ ተስፋ የወደቀውን ስሜታችንን በማነሣሣት በአጉል አስተሳሰብ የፈዘዘውን አእምሮአችንን በማ ነቃቃት በክፉ ልማዳችን የደነዘዘውን ጉልበታችንን በማበረታታት ንስሐ ለመግባት መዘጋጀት ይኖርብናል ምሳሌ ፅብ ያፖዕም ገሮቻ ሪፈሬጸማጳ እንግዲህ ንስሐ ገብተን የኃጢአት ሥርየት አግኝተን ከሰውና ከእግዚአ ብሔር ጋር ታርቀን በጽድቅ ጉዳና ለመራመድና በደኅንነት ጸጋ ለመኖር እን ድንቸል ቢያንስ ሦስት ነገሮችን መፈጸም አለብን በመጀመሪያ የንስሐ ኀዘን ማለት እውነተኛና ልባዊ ጸጸት በቅድሚያ እንዲኖረን ያስፈልጋል ሁለተኛው ኑዛዜ ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ ስለኃጢአታችን የሚሰጠንን የንስሐ ቅጣት የሚመለከት የቀኖናን ሥርዓት መፈጸምና እንደዚሁም በካህኑ በኩል የምናገኘው የፍትሐት ጸጋ ነው ደዕጩ ንስሐ የሚገባ ሰው በመጀመሪያ ኃጢአቱን እያስታወሰ ሰውንና ፈጣሪውን መበደሉን እያሰበ የሚያደርገው ኀዘን ወደ ንስሐ የሚወሰድ እውነተኛ ኀዘን ስለሆነ ኀዘኑን እግዚአብሔር ይቆጥርለታል የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው መጽናናትን ያገኛሉና የተባለው የራሳቸውንና የሌላውን ኃጢአት እያሰቡ የሚያዝኑትን ተነሣሕያን ያመለክታል ማቴ ንሥሐ ማለት ፀፀትን የሚያመለክት ቢሆንም ቁጭትና ቅንዓት የሞላበት የዓለማዊ ፀፀት ሳይሆን እው ነተኛው ኀዘንና መመለስ መሆኑን በቅድሚያ መገንዘብ ይኖርብናል ባለዛር ወዐርዐ ትምህርተ ዛይመሟናትና ክርስቲያናዊ ሕይጠት ስለ እውነተኛው ኀዘን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚከኣ።