Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
እነሱ ነ የጻፉትስ መጽሐፍ የትኛው ነው ። መጽሐፍ ቅዱስም ብርፃዛኑን ጨለማ ጨለማውን ብርፃን ጣፋጩን መራራ መራራውን ጣፋጭ ለሚሉ ወዮላቸው እንዳለው እንዲሁ እንዳይሆንብን ክፉውን ከበጎው ጻድቁን ከኃጥኡ ቅዱሱን ከረከሰው ለይተን ማዎቅ ይገባናል እአንዳመጸኛይቱ ዓለም ሰላም በሌለበት ሰላምን አውነት በሌለበት እውነትን አግዚአብሔር በሌለበት እግዚአብሔርን ልንሰብክ አይገባንም እንደ ብርሃን ልጆች ግን ጨለማውን ጨለማ ብርዛኑን ብርዛን አውነቱን እውነት በማለት የጨለማን ሥራ ልንገፍ ይገባናል አዘጋጁ ኣ ፃሃይማኖተአበው ቀደምት ተጽሕፈ በኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተጻፈ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስምከክመሠረቱ ንጹሕ የሆነውን የዓለቱን የፃይማኖት ጽናት በብርሃን ሰሌዳ መጻፍን እንጀምራለን በጧት አንደበትም እንናገራለን ዓለት የተባለውም ክርስቶስ ነው በቅዱሳን አበው ገድልና በሌላ ታሪክም ስለ እርሱ የተጻፈ አለ መራ ተክለ ሃይማኖት የሚባል ነው እርሱም በሐዋርያው ስም የተጠራ ፅጩጌው ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያ ፀሐይ ዘኢትዮጵያ ይህ ደግሞ ማለትም ተክለ ዛይማኖት የተባለው በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሣው ታላቅ አባት ነው ። ተክለፃይማኖት የሰዎች ሁለንተና ምዕ ሩ ይህ መድኃኒታችን ይህ አለኝታችን ይህ ነጻ አድራጊያችን ይህ የመንግሥተ ሰማያት ፈለማችን ይህ በታረዝን ጊዜ ልብሳችን ይህ በተራብን ጊዜ አውነተኛ ምግባችን ይህ በተጠማን ጊዜ የሕይወት መጠጣችን ጽምዓ ምዕመናንን የሚያረካ ስታየ ጽሙዓን የሆነ ጌታ አነ ውአቱ ስቴ ሕይወት ዘበአማን እያለ የሚያስተምር የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል» ሲል አሰምቶ ተናገረ ዮሐፕቶ በትንቢትም ነቢዩ ኢሳይያስ «አናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውኃ ኑ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም ያለገንዘብም ያለዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ» አለ ኢሳ ቡሩክ የሆነው ጌታችን እናንተ ደካሞች ወደ እኔ ኑ አኔም አሳርፋችኋለሁ ሲለን ለመስማት አልታደልንም ባለመታደላችንም ድጋፍና ምርኩዝ ሊሆኑ የማይችሉትን ራሳቸውም ምርኩዝ ፈላጊ የሆኑትን ፍጡራን አእንደገፍባቸው ዘንድ ተማጽነናል ሆኖም ጌታችን ደግሞ ለደካሞች ምርኩዝ እስከ ሽምግልናና አስከ ሽበት የሚሸከም አርሱ ብቻ ነው ። አናቲቱ ትናገረውም ወይም ደራሲው ይፍጠረው ሰአኛ የሚገባንና የምንረዳው ግን ፍጡር የሆነ ሰው ሁሉ አንደ ፈጣሪ መሆን የማይችል መሆኑን ነው እግዚአብሔር ብቻውን ሁሉን የሚችል ተወዳዳሪ የማይገኝለት ታላቅ አምላክ ነው ። እግዚአብሔር አምላክ ሰዎችን እጅግ አብዝቶ የባረከበት ታላቅ በረከት «ብዙ ተባዙ» የሚል ሲሆን ጋብቻም ቅዱስ ምኝታውም ርኩሰት የሌለበት ሊሆን ሲገባው ለዓይናቸው እንቅፋት እስክትሆን ድረስ የጠሉበት ምክንያት ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ እንደሆነ ያስረዳል ሐዋርያው ስላገቡትና ስላላገቡት የተናገረው አለው ሆኖም የተክለዛይማኖት የትዳር ሕይወት ግን በእጅጉ ሲጤን ይገባዋል ካገቡ እንደ እግዚአብሔር ቃል ሚስትን እንደራስ አድርጎ መቀበል ግዴታ ነው ።
ሁለተኛውም ቅዱስ አባት ለሀገራችን ፍቅርና ለነጻነታችን ሰላሟ አንዲሁም የወንጌልን ብርፃን ገላጭ የሆነው ፍሬ ምናጦስ ነው የአነርሱ ሦስተኛ የሆነው ደግሞ ብርቱና ጠንካራ የተባለው የሊባኖስ ተራራ ተክል ወይም መልካም መዓዛ ከቅዱሳንም ወገን የሆነ ቅዱስ የፅጣን ዛፍ ከርቤም የወይራ እንጨትም የአረግ እሬሳም በእርሱ ላይ በጊዜ ፅጣን አግዚአብሔር ያረገበት አምላካችንም በአልልታ ከፍ ከፍ ያለበት ነው ያቺ ቀን ምን ያህል ታስደንቅ ምን ያህልስ ታስገርም ምክንያቱም በርሱ ላይ መንፈስ ቅዱስ ይወርድበታልና የከንፈሩንም የምስጋና መሥዋዕት ከእርሱ ዘንድ አብረን እንቀደስ ዘንድ እንመገባለን ለዚህ አባት አፋችን ክፍት ነው ጉረሮዋችንም የተለቀቀ ነው አንደበታችንም በሙሴ ኮልታፋ አንደበት ላይ አእንደሰለጠነችው እንደ አሮን አፍ የእግዚአብሔርን ቃል በቅንነት እንደሚገልጥ ነው ተክለ ፃይማኖት ሐዋርያዊ ናሁ ንዜኑ በኅጹር ንባብ ህላዌሁ ለዝንቱ አብ ተክለ ዛይማኖት ርግብ ዘሀሎ እምቅድም በሳብዓይ ምዕት እምቅድመ ዛጌ ወጉጐዲት በዘመነ አርማኅ ዳዊት አርማኅስ ጠቢብ ወፍልሱፍ ብሩሀ አዕይንት ዘተለአከ ጦማረ ጐኅሉት ምስለ መሐመድ ነቢየ ፉንባላት ወጦማሩሂ ሀሎ ጽሑፈ አስከ ዮም በመጽሐፈ ቀፉሩርርዓን ውስተ ሐምስ አንቀጽ በሰማንያ ወስድስቱ ገጽ ወበከዊነ በመዋዕለ ሕርቃል ነጉሥ ወብንያሚ ሊቀ ጳጳስ አመ አሐዝዋ ተንባላት ለአስክንድርያ ወግብጽ ወአመ አውዐዩ ባቲ ሠራዊተ ዑመር ዐፅ ኀምሳ አልፈ መጻሕፍቲናኛ መጻሕፍተ ትምህርት ወገጽ ወአሜዛ ተሠይመ ዲያቆነ ዝንቱ ኣብ ቅዱስ እአምአባ ቄርሎስ እንዘ ብንያሚ ሊቀ ጳጳስ በከመ ጽሑፍ ውከተ ቬና ገድሉ ስመ ልደቱሰ ፍስሐ ጽዮን በአፈ አቡሁ ወአሙ ወስመ ጥምቀቱ ዘርዓ ዮሐንስ በአፈ ቀሲስ ጊዜ ልደተ ነፍስ በከመ ጽሑፍ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ዝኬ ውእቱ ቀዳማዊ ወበኩር ተክለ ዛይማኖት ዘአዕበዮ እግዚአብሔር ጥቀ አምዕለ ከማሁ ዐበይት ወጸገም ዘንተ ስመ ዐቢየ ወሐዲሰ ዘኢተጸውዐ ቦቱ ካልእአምቅድሜሁዘእንበለ አምድኅሬሁ ዘውእቱ ተክለ ሃይማኖት ከመ በስሙ ይትመራሕ ኀበ ግብረ አበው ቀደምት ነቢያት ወሐዋርያት አስመ ውእቱ ንሥር ሠራሪ ልዑለ ስብከት ወሐዋርያ ስሙይ በሥነ አምልኮት ጸዋዔ አሕዛብ ቀርን በቃለ ብሥራት ውስተ ቤተ ከብካብ ሰማያዊት ወቃለ ዐዋዲ መጥምቅ ጸያሔ ልቡና ፍኖት ወሰባኬ ሐዲስ ጥምቀት አበ አዕላፍ ወትዕፅልፊትምዕመናንወምዕመናት ወላዴ ብዙኃን ፍኖት ወሊቃውንት ደናግል ወመነኮሳት በዘርዐ ትምህርት ወአኮ በዘርዐ ፍትወት ውአቱኬ ዐቢይ ወውርዝው አበ አበው ተክለ ሃይማኖት ነጌ ዘወረደ ስሙ ሐዲስ በኢኑታጌ ኀበ ካልእ ንጉሠ ዛጌ ወኀበ ሣልስ ሐገ ሐዋርያው ተክለ ሃይማኖት በንጉሥ ዳዊት አርማህ ዘመን በሰባተኛው መቶ ክዘመን ከጉዲትና ከዛእ አስቀድሞ የነበረውን አባት የተክለ ዛይማኖትን ታሪክ እነሆ በአጭሩ እንናገራለን አርማህም ጥበበኛና ፈላስፋ ዓይነ ልቡናው የበራለት የሽንገላ ደብዳቤዎችን ከመሐመድ ጋር የተላላከ ነበር የተላላከውም ደብዳቤ እስከ ዛሬ ድረስ በመጽሐፈ ዮርዓን ውስጥ በአምስተኛው አንቀጽ በሰማንያ ስድስተኛው ገጽ ላይ ይገኛል ሕርቃል ንጉሥ በነበረበት ወቅት ብንያሚም ሊቀ ጳጳስ ሳለ ሙስሊሞችም ግብጽንና እስክንድርያን በወረሩ ጊዜ የዑመር ሠራዊቶችም አምሳ ሽህ መጻሕፍቶቿን ባቃጠሉ ጊዜ ይህ ተክለ ሃይማኖት ብንያሚ ሊቀ ጳጳስ ሳለ ከአባ ቄርሎስ ዘንድ ዲቁና ተቀበለ በመጽሐፈገድሉ እንደተጻፈው ከወላጆቹ ፍሥሐ ዮን በጥምቀቱ ወቅትም ከካህናቱ ዘርዓ ዮሐንስ ተብሏል ገድለ ተክለ ፃይማኖት ቀዳማዊና በኩሩ ተክለ ዛይማኖት እንደ እርሱ ካሉት ይልቅ አብልጦ አግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው ከእርሱ በኋላ ካልሆነ በስተቀር ከእርሱ በፊት ማንም ያልተጠራበትን ታላቅና አዲስ ስም የሰጠው ይኸው ተክለ ዛይማኖት ስሙ እንደሚያመለክተው ከእርሱ በፊት በነበሩት ነቢያትና ሐዋርያት ፈለግ የተጓዘ ነው ። አርሱ እንደ ንሥር በራሪ ስብከቱ ታላቅ በአምልኮ ውበትም የተጠራ አሕዛብን የሚጠራ ለምሥራች ቃል ለሰማያዊት ሠርግም መለከት አዋጅ ነጋሪ የልቡናን መንገድ ጠራጊ አዲስ ጥምቀትንም ሰባኪ የአልፍ አዕላፋት የምዕመናንና የምዕመናት አባት በፍትወት ዘር ሳይሆን በትምህርት ዘር ብዙዎችን የወለደ ነው ይህም ታላቅ ብርቱ የአባቶች አባት ተክለ ዛይማኖት አዲሱ ስሙ ያለመከልከል ወደ መራ ተክለ ዛይማኖትና ወደ ዕጩጌው ተክለ ዛይማኖት የወረደው እርሱ ነው ዝኬ ውእቱ ተክለ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወሠርፀ ፃይማኖት ቅዱስ ዘኢይጸመሂ ወኢይኤብስ ዕፀ ጥበቡሂ ትምህርት ዕፀ ሕይወት ወፅፀ መድኃኒት እንተ ታሌቡ ሠናየ ወአኩየ አስመ ልቡ ለባሕታዊ ገነተ ተድላ ዘኢይበሩልዎ ሦክ ወአሜከላ በከመ ጽሑፍ ዝኬ ውአቱ ጳውሎስ ሐዲስ መስተጽዕነ ወንጌል ፈረስ ረዋጺ እስከ አድማስ ክዘተጸውዐ ወተፈልጠ አእምንጉሠ ዛጌ ቀዲሙ ወእምሐፄጌ ዳግሙ እስመ አሉ ጸወርተ ስሙ ዝኬ ሐዋርያ ዓለም ወሰማዕተ ገዳም ገባሬ ተአምር ወመንክር ኃያል ወመስተጋድል መነኮስ ታስዓየ እንጦንስ አንጦኒ መቃሪ ጳኩሚስ ቴዎድሮስ አረጋዊ ክርስቶስ ቤዛነ መስቀል ሞአ ዮሐን ተክለፃይማኖት ወፅረፍቱኒ በሳምናይ ምፅት ዘመነ ሐዲስ ዘውአቱ በሳብዓይ ምዕት ወዐሠርቱ ዓመት እአምልደተ ክርስቶስ ቅድመ ከማሁ ጽሑፍ በዜና ቅዱሳን አበው ወበካልዕኒ ታሪከ ዘመን ግጽው ዘተጽሕፈ ቅድመ እምኀበ ጸሊማን ወጸዐድውሩ መራ ተክለ ሃይማኖት አስመ ቀዳሚሆሙ ለነገሥተ ዛጌ ዘነግሠ በአሥራይ ምዕት ኮነ ይሰመይ መሪተክለዛይማኖት በስመ ዝንቱ ጻድቅ ያዕቆባዊ ዘበአማን ወአሥራኤላዊ ዘአልቦ ጽልሑት ሐፄጌ ተክለ ሃይማኖት ወሐፄጌኒ ቀዳሚሆሙ ለሐፄጌያት ዘቀብዖ ወአንገሦ ለይኩኖ አምላክ ወልደ አኅተ እሙ በዐሥር ወሣልሳይ ምዕት ውእቱ ተክለ ሃይማኖት ዘብሔረ ሳይንት ወእመ አኮ ዘዳውንት ወቦ መጽሐፈ ገድል ዘበአንቲአሁ ይነግር ወይብል ከመ ውእቱ ሕጋዊ ካህን ወመዐስብ ባዕል ወአኮ እምንእሱ መነኮስ ድንግል ብእሲሁሰ ክቡር ወልዑል ወዝንቱ ገድል ፍሉጠ ዜና ይትረከብ ጽሑፈ ለባሕቲቱ አው ሥርዋጸ ወተውሳከ ማዕከለ ገድል ወተረክቦቱኒ በበአሐዱ ደብር ወበበአሐቲ ገዳም ወፈድፋደስሰ በወይንጌ ዘብሔረ ወግዳ ወዐዲ በግራርያ ዘበጌምድር ሀሎ ጽሑፈ ማዕከለ ገድል ከመስ ኢይርአዮ ሰብእ ወኢያንብቦ ከመ ኢይበል ላዕሌሁ ቃለ መሐደምት ከመ ሰብአ ጎንደር ደኃርት አቦ ብልኀት ዕጩጌነት ከሚስት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተክል ቅዱስ የሆነ የሃይማኖት አወጣጥ የማይጠወልግ የማይደርቅ ዛፍ ዕፀ ጥበቡም የሕይወት ዛፍና የመድኃኒት ዛፍ ነው እርሷም ክፉውንና መልካሙን የምታሳውቅ ናት የአንዲህ አይነቱ ሰው ልቡ የደስታ ገነት ነው እሾህና አሜከላ አይበቅሉበትም እንደተባለለትም ይህ ሰው አዲሱ ጳውሎስ ነው ወንጌልን የተሸከመ ሠጋር ፈረስ አስከ ምድር ዳርቻ የሠገረ የበረረ ከመራ ተክለ ሃይማኖትና ከፅጨጌው ተክለ ሃይማኖት የተለየ ይህ ሐዋርያ ተክለ ዛይማኖት ነው የዓለም ሐዋርያና የበረኃ መሥካሪ ይህ ተክለ ዛይማኖት ነው ድንቆችንና መንክራቶችን ያደረገ ብርቱ ተጋዳይ የእንጦንስ ዘጠነኛ ነው አንጦንስ መቃርስ ጳኩሚስ ቴዎድሮስ አረጋዊ ክርስቶስ ቤዛነ መስቀል ሞዓ ዮሐንስ ተክለ ዛይማኖት የፅረፍቱ ዘመንም በስምንተኛው መቶ ዘመን በዘመነ አዲስ በሰባት መቶ አሥር ዓመተ ምህረት ድኅረ ልደተ ክርስቶስ ነው በቅዱሳን አበው ገድልና በሌላ ታሪክም ስለ እርሱ የተጻፈ አለ መራ ተክለ ሃይማኖት ይህ መራ ተክለ ሃይማኖት ደግሞ በአሥረኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ነግሦ የነበረ የዛዛዎች መንግሥት ጀማሪ የሆነ መራ ተክለ ሃይማኖት የሚባል ነው እርሱም በሐዋርያው ስም የተጠራ ፅጩጌው ተክለ ሃይማኖት ሦስተኛውና ዕጩጌው ተክለ ፃይማኖት ደግሞ የእናቱን የአኅት ልጅ ይኩኖ አምላክን ቀብቶ ያነገሠ ሰው ነው ዘመኑም በአሥራ ሦስተኛ ው መቶ ዘመን ነው የዚህ ሰው አገሩ ሳይንት ወይም ዳውንት ይባላል ስለ አርሱ የተጻፈው ገድል አንደሚተርከው አርሱ ሕጋዊ ካህን ባለ ትዳርም ነው መነኩሴም አይደለም ይሁን አንጂ ሰውየው ግን ታላቅና የተከበረ ነበር የእርሱ የሆነውና ትክክለኛው ገድሉ በገድላቱ መካከል ተሰንቅሮ ለብቻው ይገኛል በሁሉም ቦታ ሳይሆን በአንዳንዱ ደብርና ገዳም ብቻ ይገኛል በተለይም ወግዳ በተባለች አገር ውስጥ በወይንጌና በበጌ ምድር ውስጥ በግራርያ ተደብቆ ይገኛል መደበቁም ማንም ሰው እንዳያነበው አንደ ኋለኞች ጎንደሬዎችም አቦ ብልሐት ዕጨጌነት ከሚስት አያሉ አንደዘበቱበት አሁንም እንዳይዘበትበት ነው ። ር ጽ አስረጅ አማርኛ የግዕዝ ጐራኛ በ እማኝ በኛ ዳኛ የሮማውያን ስንክሳርና በ ዓመተ ምህረት በላስቶች ዘመን ተጥፎ ከደብረ ሊባኖስ ወደ አውሮፓ የሄደው ጥንታዊው ገድለ ተክለ ዛይማኖት ስለ ተክለ ሃይማኖት ሥጋዊና ደኃራዊ ነገር ሳይጨምር መንፈሳዊና ቀዳማዊ ብቻ ይተርካል ጹ ይህንም ገድል አንድ ባለ ታሪክ ዲልማንና አንጧን ዲባዲ የሚባሉ ግዕዝ አዋቂዎች የአውሮፓ ሊቆች በእንግሊዞች አገር አግኝተው አንዳዩትና አንደመረመሩት በመጣፋቸውም አንደጠቀሱት ዛሬም በሎንዶን አንደሚገኝ ተናግሯል ከግራኝ በኋላ በዓፄ ሚናስ ዘመን ዕጨጌው ተክለ ፃይማኖት በሞቱ በ ዓመት የኋላ ሰዎች እነአባ ዮሐንስ ከማ አንደ ቅኔና እንደ ድርሳን ቀምመው አጣፍጠው የጣፉት ገድል ግን የጻድቁን ሥራ ለዕጩጌው ሰጥቶ ጻድቁንና ዕጩጌውን በሙጫ ጸያፍ አጣብቆ ለጥቆ በአንድ ስም ጨፍልቆ አንድ ሰው አድርጎ ያልጠራ ያልበራ ድፍርስ ጨለማ ታሪክ ይተርካል በጻድቁና በዕጩጌው መካከል ሁለቱን የሚለይ ታላቅ ረዥም ገደል ዓመት አለ ሌላም ይህን የመሰለ ብዙ እናገኛለን ከብዙው አንዱ አርድእት የሚባለው የጸሎት መጽሐፍ እነሆ እንዲህ ይላል ቱ አርድእት ወይም ሐዋርያት ሰዶም ገሞራ ገብተው ወንጌልን ሲሰብኩ የሰዶም ሰዎች አናምንም አንቀበልም ቢሏቸው አርድአት ወደ እግዜር ጸልየው አሳትና ዲን አዘነሙባቸው ሉጥ ግን ከነልጆቹ በወንጌል በአርድእት ቃል ስላመነ ከአሳት ዳነ ብሎ ገና ኦሪት ሳትጻፍ በአብርፃም ዘመን የሆነውን ለወንጌልና ለአርድእት ሰጥቶ ይተርካል ጣፊ ለጣፊ ዋሾ ቀጣፊ የሚያሰኝ እንደዚህ ያለው ነው ይህም ታሪክ ፈጽሞ የቱርዓንን ታሪክ ይመስላል አቡዛ ለሐሰት ሙሐመድ አርሱ ይስማዔላዊ ስለሆነ ይስማዔልን ያስከበረ መስሎት ኢብራሂም መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው አላህም የራራለትና በስማያዊ በግ የተቤፔው የእኛን አባት ይስማዔልን እንጂ ይስሐቅን አይደለም ብሏል ሁለተኛም ነቢይ ኢሳን የወለደች ድንግል ማርያም የሙሴና የአሮን እኅት ናት ይላል አስላሞችም ከፊት ቀላጤ የኃላ ቀላጤ እያሉ ከኦሪትና ከነቢያት ይልቅ የተጐርርዓንን ውሼት ያምናሉ አባ ጊዮርጊስም በጣፉት በመጽሐፈ ምሥጢር በሌሎችም ዜና በነቀውስጦስ ገድል የአርድአትን ውሼት የመሰለ ፍሬ ቢስ ወሬ ኦሪት ነቢያት በሰሎሞን ጊዜ ኋላም በየጊዜው ከዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ እንደተመለሱ የሚያወራ ልብ ወለድ ፈጠራ ዋሾ ታሪክ አለ የጳጳሳትንም ታሪክ ስማቸውንና ተራቸውን ሲጥፍ ሰላማ ከሣቴ ብርዛን አንድ ብሎ ሰላማ ከሣቴ ብርዛን ካልእ ብርሃነ አዜብ ሁለት ይላል ። አለቃ ይህን ሁሉ መልክ መልክ ለማስያዝ ብዙ ጥረዋል ብዙም ደክመዋል ተሰፍሮ ተቆጥሮ የማያልቀው የሰነፎችና የክፉዎች ታሪክ ግን በአርሳቸው ብቻ ተዝቆ የሚያልቅ ባለመሆኑ በነበረው ላይ እየተጨመረበትና እየበዛ ከዘመናችን ደርሷል ሊቁ ኪዳነ ወልድ አንደጥናት አድርገው ካቀረቡት መካከል በአንድ ስም ተጣብቀው ታሪካቸው ተደባልቆ ማን ምን አንደሆነ መለየት ተስኖን ያለውን ነገር የሦስቱን ተክለ ሃይማኖቶች ጉዳይ ነው ምንም እንኳ ታሪካቸው ለሊቃውንቱ ብዙ የተሰወረ ባይሆንም አላዋቂው ሕዝባችን ግን ብዙ ስለተሳሳተበት ስለዚህ ጉዳይ በአለቃ ዘንድ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ትኩረቱ እውነት ነውና አኛም ይህንኑ ጥናት ለማየት ሞክረናል አኒህ ታላቅ አባት «ሃይማኖተ አበው ቀደምት» የቀደምት አባቶች ዛይማኖት በማለት ርእስ ይሰጡና መነሻቸውን ከእስክንድርያ አድርገው የኢትዮጵያን ሁኔታ ይቃኛሉ ኢትዮጵያ በታሪክ ከአክስክንድርያ ጋር የተሣሰረችብት ነገር አለና ከዚያው መነሣቱ አግባብ ነው ወንጌልን ለመስበክ የተጠሩ ብዙዎች ሆነው የተመረጡትና አገልግሎታቸውን በመልካም የፈጸሙ ጥቂቶች እንደሆኑ አለቃ ተናግረዋል ከእነዚህም መካከል ሦስቱ አባቶች ናቸው ሲሉ አእውቃታቸውን መረዳታቸውን አሳይተውናል አነርሱም ሐዋርያዊ አትናቴዎስ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ፍሬ ምናጦስ አባ ተክለ ዛይማኖት ቀዳማዊ በኩር ዘብሔረ ሳይንት ዘዳውንት በጌ ምድር በሕየ ምድር ውስጥ የተወለዱ ሰው ናቸው አነዚህ አበው ለቤተ ክርስቲያናችንና ለምድራችን አግዚአብሔር የተጠቀመባቸው አበው አንደሆኑ አውነተኛ ታሪካቸው ምሥክር ነው እነዚህ ሰዎች ለምን አንደተጠቀሱ እንድንቀበለው የሚያስችለንን እውቀት ከታሪካቸው ማየቱ ጠቀሜታ ስላለው ሦስቱንም አበው በጥንቃቄ አንመልከት ኛ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ይህ አባት ከመጀመሪያዎቹ ከሐዋርያት በዘመን ብዙ ያልራቀ በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ገደማ የነበረ ታላቅ ሰው ነው በዘመኑ የስሕተት አስተማሪዎች ቢበዙበትም መከራውንና ስደቱን ታግሶ ወንጌልን እየሰበከ ትእግስቱን አሳይቷል ምንም እንኳ አንገቱ በሰይፍ ባይቆረጥና ደሙን ያፈሰሰ ሰማዕት ባይባልም ቅሉ ሊቁ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ «ሰማፅት እንበለ ደም» ሲሉ አሞግሰውታል በአርግጥም ስለክርስቶስና ስለወንጌል የሚሰደዱ ሁሉ የወንጌል ምሥክሮች ናቸውና ይህ ሰው አትናቴዎስ ይህን ስም ማግኘቱ አግባብነት ያለው ነው አትናቴዎስ በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ በመሆን በተራ ሩጥር ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ አራተኛ ለእአስክንድሮስ ሦስተኛ ሆኖ ሲያገለግል አርዮስ የተባለ መናፍቅ ወልድ በባሕርየ መለኮቱ ፍጡር ነው ስላለ በኒቅያ ጉባዔ በጸሐፊነት በመገኘት «ዘአሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ» በመለኮቱ ከአብ ጋር አኩል ነው የሚለውን አቋም በጽሑፍ አስፍሯል ። ይህም አስከዛሬ ድረስ ለሁሉም ማለትም ለኦርቶዶክሳውያንና ለካቶሊካውያን ለወንጌላውያንም የሃይማኖት መግለጫ ሆኖ ያገለግላል አትናቴዎስ ከአርዮስ ደጋፊዎች በሚደርስበት መከራና ስደት ሁሉ ታግሦ ምዕመናንን በማስተማርና ወንድሞቹን በማጽናት አጅግ ብርቱ ሰው ነበር በአውቀትና በችሎታ ብርቱ የነበረው አትናቴዎስ አርዮሳውያን ከመንግሥት በሚያገኙት ድጋፍ ስቃዩን አብዝተውበት ነበር ዛሬም በዓለም ዓቀፍ ኅብረተ ሰብእ ዘንድ እውቅናና ተቀባይነት ያለው አትናቴዎስ በትምህርቱና በእምነቱ ነቀፌታ ያልነበረበት አባት ነበር በተለይም አርሱ የነበረበት ወቅት እጅግ አደገኛ ስለነበር ዶክትሪናል በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይሰጥ ነበር በዚያን ዘመን አትናቴዎስ ባይኖር ኖሮ አርዮስን ተከራክሮ የሚረታ በእውቀት የበሰለ በሥነ ምግባር የታነጸ አባት አይገኝም ነበር ይባላል «አግዚአብሔር ወልድ በመለኮት ፍጡር ነው» የሚለው ክፉ ትምህርት በአስክንድርያ ብሔራዊ ሃይማኖት እስኪሆን ድረስ በባለሥልጣን የተደገፈው የአርዮስ አንግዳ ትምህርት መላ ሀገሪቱን እንዳይወርስ አንድ ብቻውን በትጋት የተንቀሳቀሰው አትናቴዎስ የአርዮስ ትምህርት ሥር እንዳይሰድ በማድረግ በጊዜው እንዲመክን አድርጎታል ከዚህም የተነሣ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ይህን ታላቅ አባት «ቅዱስ» በሚል ማዕረግ ጠርተዋለች አሁንም በዚሁ ማዕረግ ቅዱስ አትናቴዎስ» ተብሎ ይጠራል በአርግጥ አርሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ እንደሆነ አምነው በቅድስናው ሥር የተጠለሉ ቅዱሳን ሁሉ የቅድስናው ተካፋዮች ናቸው እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ብሏልና አስከቪህ ዘመን ድረስም ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ሳትሆን የምዕመናን ስብስብ እንደሆነች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል በዚህ ሰው ዘመንም ምንኩስና የተባለው ሥርዓት ለጽድቅ ሥጋን መጨቆን ትዳርን መፍታት በብቸኝነት ከሰው ተገልሎ መቀመጥ የሚለውን ክፉ ትምህርት ይዞ በነአባ እንጦንስና በነአባ መቃርስ በነአባ ጳውሊ ይሰበክ ጀመር ። ይህ ሰው በንጉሥ አርማህ ወይም ዳዊት ዘመን የነበረና እውነተኛዋን ወንጌል የስበከ ሐዋርያ ነው አርሱም እንደነ ሰላማ ሆኖ በዚህ ዓለም ነገር ራሱን ሳያጠላልፍ ለወንጌል የተለየ ጃንደረባ አድርጎ ዘመኑን ሁሉ በአገልግሎት የፈጸመ አርበኛ ነው ቀዳማዊና በኩር የተባለው ይህ አባት ከእርሱ በኋላ በተነ ሌሎች ተክለ ሃይማኖቶች ታሪኩ ጠፍቶና ታሪክ አልባ ሆኖ በእርሱ ታሪክ ታሪክ አልባዎቹ እየተሞገሠበት ይገኛል ይህ ሰው ወንጌልን እንበለ ፍርኃት በድፍረት እንበለ ስሕተት በአውነት እንበለ ተወላውሎ በጥብዓት የሰበከና ሐዋርያዊ ተልዕኮውን በፍቅርና በሐዋርያት ፍለጋ የፈጸመ ሰው ነው አለቃ ኪዳነ ወልድ ያገኙት የዚህ ሐዋርያ ተክለ ዛይማኖት ታሪክ አንደሚለው «ዝኬ ሐዋርያ ዓለም ወሰማዕተ ገዳም ገባሬ ተአምር ወመንክር ኃያል ወመስተጋድል መነኮስ ታሥአየ አንጦንስ »እ ማለትም «የዓለም ሐዋርያና የበረኃ መሥካሪ ይህ ተክለ ዛሃይማኖት ነው ድንቆችንና ምልክቶችን ያደረገ ብርቱ ተጋዳይ የአንጦንስ አሥረኛ» ነው ምንኩስና በዘመናችን ብዙ የሚያነጋግርና አሕዛብ ለአማልክቶቻቸው ከገንዘባቸው አልፈው ሕይወታቸውን ለመሠዋት ብቸኛና ቤሳቢስቴ የሌለው ድኃ ሆኖ በመኖር መታዘዛቸውን ይገልጡበት ዘንድ የሚወስኑት ውሳኔ ነው ራስን ወይም ሥጋን በመጨቆን ጽድቅ የሚያስገኝ የሚመስለው ይህ ክፉ ትምህርት በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሰተት ብሎ ገብቶባታል ቢሆንም ታላላቅና ወንጌልን የተረዱ ቅዱሳን አበው ሲገቡበት ግን ለወንጌል አገልግሎት አስፈላጊና ጊዜን ሁሉ ለክርስቶስ እንደመዋጀት ይቆጠራልና እንደበጎ ሊታይ ይችላል ብለን ልንቀበለው እንችላለን የምንኩስና ክፋቱ በክፉዎች ሰዎች ሲያዝ ጽድቅን ከክርስቶስ አውጥቶ በሰው ድካም እንዲፈጸም ማድረጉ ብቻ ነው በተለይ አጅግ በከፋ ሁኔታ ምንኩስና መልኩንና ውበቱን አንዲያጣ ካደረጉት ክፉ ሰዎች መካከል ዕጩጌው ተክለ ዛይማኖትና ከእርሱ በኋላም እርሱን አብነት አድርገው የተነሥውት መነኮሳት ናቸው ። ከነዚህ ጋርም ምንም አንኳ ከነዚህ ተክለ ሃይማኖቶች ጋር የተቀራረበ ታሪክ ባይኖረውም የጎጃሙ ንጉሥ ተክለ ዛይማኖትም አለ ፅጨጌው ተክለ ዛይማናት ይህ ሰው በአሥራ ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሣና የእናቱን የአኅት ልጅ ይኩኖ አምላክን ቀብቶ ያነገሠ ሰው እንደሆነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ያገኙት መረጃ ያረጋግጣል ይህ ተክለ ሃይማኖት የዕጩጌዎች ሁሉ መጀመሪያ እንደሆነም ተገልጧል ይህ ሰው ባለ ትዳርና ሕጋዊ ቄስ እንደነበረም የራሱ ገድል ይናገርለታል የዚህ ሰው ገድል ማንም አንዳያነበው እንዳያገኘው ተደርጎ ተደብቆና ተቀብሮ በወይንጌና በጌምድር ውስጥ በምትገኝ ግራርያ በተባለች አገር ውስጥ ይገኛል ይህም የተደረገበት ዓቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መቀለጃ እንዳይሆንና አንዳይዘበትበት እንዲሁም የታሪክ ተወቃሽ እንዳይሆን ጭምር ነው ውስጥ ያልኖሩ ሰው በመሆናቸው ይልቁንም በዚህ ዓለም ላለቸው ዘማዊትና ምድራዊት ለሆነችው መንግሥት ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡና ከነገሥታቱ ጋርም በማለዳ በማዕድ በመቀመጥ የሕዝብንና የካህናትን ጉዳይም በመፍታት ውሳኔም በመስጠት ቀልጣፋ በመሆናቸው እንደ ባለሥልጣን የነበሩ ሰው ናቸው ። አለቃ ኪዳነ ወልድ ስለዚህ ሰው ሲናገሩ «አኮኬ በዓለ ትሩፋት ወፍጹመ ትምህርት አላ ብሩሃ ልብ ወበሊሐ ንባብ ዘርቱአ ይመትር ነገረ ካህናት ወሕዝብ» ማለትም ይህ ሰው በጎ ምግባር የለውም በቂ ትምህርትም አልነበረውም ነገር ግን አንደበተ ርቱዕና አአምሮው የበራለት አስተዋይ ሰው ነበር የካህናትንና የሕዝብን ጉዳይ በአግባብ በመፍታት ውሳኔም በመስጠት ተወዳጅ ነበር ተብሏል ከዚህ ችሎታውና ለቤተ መንግሥትም ካደረገው ውለታ የተነሣ ሚሦ መንግሥት ተሰጥቶት የመጀመሪያው ዕጩጌ ተክለ ዛይማኖት ተብሎ ተሾመ ተብሏል በ ዓመተ ምሕረት በላስቶች ዘመን ተጥፎ ከደብረ ሊባኖስ ወደ አውሮፓ የተወሰደው የሮማውያን ስንክሣር ሥጋዊና ደኃራዊ ነገር ሳይጨምር የመጀመሪያውን ተክለ ሃይማኖት ታሪክ እንደሚናገር ዲልማንና አንጧን ዲባዲ የተባሉ አውሮፓውያን ግዕዝ አዋቂ ሊቃውንት በእንግሊዝ አገር አግኝተው እንዳዩት ተናግረዋል ይሁንና የሐዋርያውን ታሪክና የዕጩጌውን ታሪክ በአንድ ላይ አደባልቆ አንዱን ባንዱ አጣፍቶ አንድ ተክለ ሃይማኖት ብቻ አድርጎ የጻፈው ከግራኝ መሐመድ ወረራ በኋላ በዓፄ ሚናስ ዘመነ መንግሥት ዮሐንስ ከማ የተባለ ሰው አንደሆነ ሊቁ ገልጠዋል ሊቁ ስለዚህ ሰው የተሰማቸውን ቅሬታ ሲገልጡና የሚጽፍ ሁሉ በጥንቃቄ እንዲጽፍ ሲያስገነዝቡ «ጣፊ ለጣፊ ዋሾ ቀጣፊ የሚያሰኝ እንደዚህ ያለው ነው» ብለዋል ይህ ብቻ ሳይሆን በአባ ጊዮርጊስ ገድልና በመጽሐፈ ምሥጢር በሌሎችም ዜና በነቀውስጦስ ገድልም አንደዚህ ያለ ውሸት አንደሚገኝ አስረግጠው ተናግረዋል ። ወደርና አቻ የማይገኝለትን ይህን ጌታችንን አጥተን በዘላለም ሞትና ኩነኔ እንኖር ክንድ የሰይጣንና የመልእክተኞቹ ዓላማ ስለሆነ ከእንዲህ ዓይነቱ ጠማማና ክፉ ትምህርት ልንርቅ ይገባናል መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለበት መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን የሚያርቅ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን የሚያድል እውነተኛ መድኃኒት ወልደአብ ወልደማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ዮሐንስ ከማ የማይደፈረውን የማይነካውን ሊታሰብ እንኳ የማይገባውን ክፉ ትምህርት በቤተክርስቲያናችን ላይ ጥሎ አልፏል ወይስ በዕፀዋት ቅመማና በልዩ ድግምት ይኩኖ አምላክን በማንገሥ ችሎታው የተሰጠውና የተቸረው ስም ይሆን ግን ምንም ይሁን ምን ከእንግዲህ ግን እንዲህ ዓይነቱን ጠማማ ትምህርት የምንሸከምበት ጀርባችን ጎብጧልና አይሆንልንም ይልቅስ እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ደካሞች ወደኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁና» ወደሚለው ጌፓፖ ተጠግተናል ይህ አለኝታችን ለእኛስ ክብር ሁሉ ለስም አጠራሩ ይሁንና አለኝታ መከታ ጋሻ መተማመኛ የአበው ተስፋ የነቢያት ትንቢት የነገሥታት ዘውድ የሐዋርያት ሞገስ የሆነው ጌታችን ብቻ ነው አለን የምንለው ከአብ የተሰጠ ውድ ሥጦታ መድኃኒታችን ብቻ ነው ለአውነተኛ ክርስቲያን ደካማና ምስኪን ለሆነ ክርስቲያን ከዓለምና ከዓለም ክብር ለራቀ ክርስቲያን ከዘመድ ከወገን ለተለየ ክርስቲያን አለኝታውና ተስፋው መኖሪያውም ክርስቶስ ብቻ ነው ገድላት ድርሳት በጸሐፊዎቻቸው አማካኝነት ከምንፈራውና ከማንደፍረው ቦታ ስለተቀመጡ እስከ አሁን ድረስ ክብር ለእናንተ ይሁን አያልናቸው ቆይተናል አሁን ደግሞ ውርደት ለእናንተ እንላቸዋለን ምክንያቱም አለኝታችን ከሆነው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ለይተውናልና ነው ክርስቶስን ትቶ ፍጡርን አለኝታ ማድረግ ግን በተቀጠቀጠ ሸንበቆ እንደመደገፍ ያህል ነው ይህ ነጻ አድራጊያችን የደራሲው ክፋት ነውና አሁንም በክፋቱ ቀጥሏል ቅዱስ መጽሐፍ ግን በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ» ብሏል ገላ በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ የነበረ ሕዝብ ታላቅ ብርዛን አየ እንደተባለ ከሰይጣን ባርነት ከሞት አገዛዝ ነጻ አውጥቶ በብርፃን ያኖረን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ከዕለታት አንድ ቀን ጌታችን ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ መጽሐፍ ሊያነብ ቆመ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ የሚከተለውን ምንባብ አገኘና ስለራሱ ራሱ እንዲህ ሲል አነበበ «የጌታ መንፈስ በአኔ ላይ ነው ለድዣች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛ ልና ለታሠሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት አስብክ ዘንድ ልኮኛል» ሉቃ ኢሳ ዕብ ይህን ክፍል ካነበበ በኋላ «ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሯችሁ ተፈጸመ» አላቸው አሜን በአርግጥ ተፈጽሟል ለቃሉ ያመጹትና እምቢ ያሉት እነ ዮሐንስ ከማ ግን አሁንም የተጠቁና ነጻ ያልወጡ ሆነው በግዞትና በሞት ጥላ ውስጥ ይኖራሉ ይህ የመንግሥተ ሰማያት ፈለማችን አረቦንመያዣ ይህም በክርስቶስ ድነን ለቤዛ ቀን የታተምንበት የርስታችን መያዣ የተባለው ቅዱስ መንፈስ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ነገር ሲናገር እንዲህ ብሏል «በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው» ቁሮ እንዲሁም «ነገር ግን ለዚሁ የሠራን አግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን» ይላል ቁሮ እንደገናም «በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ አርሱም የርስታችን መያዣ ነው» ተብሏሷል ። «በልቡናው ክርስቶስ አድሮበታልና ይኸውም ለሰው ዕውቀትን የሚገልጥ በምዕመናን አድሮ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ነው» ወደሚለው ክሕደትም እንደርሳለን አግዚአብሔር አብ አግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ሦስት አካላት አለ አብ ተለውጦ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አይሆንም ወልድም ተለውጦ አብ መንፈስ ቅዱስ አይሆንም መንፈስ ቅዱስም ተለውጦ አብ ወልድ አይሆንም አብ አንድያ ልጁን ወደ ምድር በመላክ በልጁ አድኖናል ወልድም በአባቱ ፈቃድ ተልኮ ሥጋችንን ለብሶ አድኖናል ። አርሱ አጽናኝ ሆኖ እንደገና አልተላከም ወይም መንፈስ ቅዱስ ሆኖ አልመጣም ዛሬም በአማኞች ሕይወት ውስጥ አድሮ ምሥጢርን የሚገልጥ የሕይወት መንፈስ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ነው መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ አይደለም ክርስቶስም መንፈስ ቅዱስ አይደለም ይህንም ትምህርት ቅዱስ መጽሐፍ በግልጥ ያስተምረናል ።