Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
መብቱ የደራሲዋ ነው ሬ ሩብ ፍ ሸኩ ፍሺቃ ቆ ብው ቁ ብሙ ቀ ፍዕ ቀርጅ ጅ ቀ ዊ» ቀ ቤ ር ታ ፍዋ ዛፍሠ ቁ ፍው ቀ ውሃ ከልሶ ሲፈላ የሽ ንብራውን ዱቄት ነፍቶ ማገንፋት ነው። ከዚህ በኋላ የፉርኖ ዱቄት የስንዴም ይሆናል ለብ ባለ ውሃ አሽቶ ሳይቀጥን ማቡካትና መዳ መጫውን አጥቦ አድርቆ ዘይት ቀብቶ የታሸውን ሊጥ በስሱ መዳ መጥ የተገነፋውን የሽንብራ ዱቄት የተፈጨ ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ በዕንቁላል ቅርጽ ማድበልበልና በተዳመጠው ሊጥ መጠቅለልና ዘይት በመጥበሻ አፍልቶ መጥበስ ነው። ማቁላላትና አንድ የሾርባ ማንኪያ መከለሻ ቅመም ጨምሮ ከሩብ ሰዓት በኋላ የተጠበሰውን የጾም ዕንቁላል ጨምሮ ማውጣት ነው። ስለ ጓያና ስንዴ እንጀራ አገጋገር ስንዴውን ለቅሞ አጥቦ ማስጣት ጓያውን ለቅሞ አንፍሶ ማስ ጣትና በጣም ሲደርቅ አራት እጅ ስንዴ አንድ እጅ ጓያ ለክቶ አደባልቆ በጣም አልሞ ማስፈጨት ነው። አንድ ጊዜ ኩፍ ማልት ሲጀምር ምጣዱን አስምቶ መጋገር ነው። ስላ ሕፃናት ምግብ አሠራር ላዋቂም ይሆናል በቆልት የሚሆኑ እህሎች የማይበቅሉ እህሎች ጤፍ ጹ በቆሎ ስንዴ ሽንብራ ጅ ባቄላ ኮጅ ማሽላ አተር አጃ ጁ ምስር ገብስ ጁ ዳጉሣ ጂ ጠመዥ ዘንጋዳ አሠራር ጤፉን ምስሩን ጠዋት በቀዝቃዛ ውሃ በጥብጦ ከፈላው ውሃ ላይ ጨምሮ ማንተክተክና ትንሽ ጨው ማብሰል ነው። ሱፍ በቀይ ቆልቶ ሳይደቅ ይወቀጥና ይነፋል ገለባው ይጣ ላል የደቀቀው ከተደባለቀው ተልባና ሱፍ ላይ መጨመር ነው ።
ስለ ለምለም ዝግን ወጥ አሠራር ቀይ ሽንኩርት ልጦ ከትፎ ለቅለቅ አድርጎ ማቁላላት ከበሰለ በኋላ ለማቁላያ ከተዘጋጀ አብሽ መሀሉን ገለጥለጥ አድርጎ በሻይ ማንኪያ አንድ ጨምሮ ማቁላላት ተስማምቶ ከበሰለ በኋላ ውሃ ጣል ማድረግ መጠነኛ ድስት ከሆነ በሾርባ ማንኪያ ሁለት የጐ ንደሬ ድልህ መጨመርየሸዋ ድልህ አንድ የሾርባ ማንኪያ መጨ መርውሃ ጣል እያደረጉ ማቁላላት ግማሽ ጭልፋ ጠጅ ጨምሮ አብሮ ማቁላላት በሻይ ማንኪያ አንድ መከለሻ ቅመም መጨመር ከተቁላላ በኋላ አንድ ጭልፋ ቅቤ መጨመር ትንሽ የሞቀ ውሀ ጣል እያደረጉ ጥሩ አድርጎ ማቁላላት የበግ ሥጋ የሆነ እንደ ሆነ የጐድን ሥጋ ባጭር ባጭሩ ቆራርጦ አብሮ ማቁላላት የበሬ ሥጋ ከሆነ ሥጋውን ባጭር ባጭሩ ቆርጦ አብሮ ማቁላላት ከተቁላላም በኋላ ብሩንዶውን ሥጋ ድቅቅ አድርጎ መክተፍ ከከተፉ በኋላ የማስተካኪያ ቅመም መጨመር መውጫው ሲደርስ ሊበላ ሲቀ ርብ የተከተፈውን ሥጋ በቅቤ ለውሶ ወጡ የሚተርፍ የሆነ እንደ ሆነ በጐኑ በኩል የተከተፈውን ሥጋ ጨምሮ በጐኑ በኩል በማንኪያ አደባልቆ አውጥቶ መብላት ለምለም ዝግን ሥጋው ከተጨመረ በኋላ አይቆይም ወዲያውኑ ወጥቶ ወዲያውኑ ይበላል ። ስለ አልጫ ምንቸት አብሽ አሠራር ቀይ ቀዩን ሥጋ መርጦ ቆራርጦ መቀቀል የተቀቀለውን ሥጋ ድቅቅ አድርጎ መክተፍ ከተከተፈ በኋላ ቀይ ሽንኩርት አድቅቆ መክተፍ ከዚያም ድስቱን ጥሩ አድርጎ አጥቦ ጥዶ ሽንኩርቱንም አጥቦ ጨምሮ ለጋ ቅቤ ጨምሮ ከሽንኩርቱ ጋር ማብሰል ከዚህ በኋላ ድቅቅ ብሎ የተከተፈውን ሥጋ ጨምሮ ነጭ ማለፊያ ትንሽ ሽሮ ጨምሮ የፈላ ውሃ ትንሽ ትንሹን እያደረጉ ማብሰል ነጭ ሽን ኩርት ተልጦ ዝንጅብል ተፍቆ እርድ ተጨምሮበት በእርጥቡም ሆነ በደረቁ ተልሞ ከተቀመጠው ቅመም ግምቱን ለክቶ መጨመር ተስማምቶም ከበሰለ በኋላ ቃሪያውን ሰንጠቅ ሰንጠቅ አድርጎ ጨምሮ ማውጣት ። ስለ አልጫ ሥጋ መረቅ አሠራር ጮማ የሆነውን የፍርምባና የዳሌ ሥጋ ቆራርጦና አጥቦ ድስ ቴን ሙልጭ አድርጎ አጥቦ ጨምሮ መጣድ ከዚያም እያማሰሉ ማብሰል ከበሰለ በኋላ ቀይ ሽንኩርት ድቅቅ አድርጎ ከትፎ ድስት ጥዶ አጥቦ ሽንኩርትና ቅቤ ጨምሮ ለብቻ ማብሰል ከዚያም በኋላ ሥጋውን ጨምሮ የሥጋውን ውሃ እያቀረሩ እየጨመሩ ደግሞ የተ ላመ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል አድርጎ እርድም ጨምሮ ሊወጣ ሲል እርጥብ በሶብላና ቃሪያውን ሰንጠቅ ሰንጠቅ አድርጎ አስተካ ክሎ አብስሎ ማውጣት ። ከዚያም በጭድም ሆነ በወረቀት መለብለብ ከለበለቡም በኋላ በሽሮ ትንሽ ውሃ ጠብ እያ ደረጉ ሰውነቷን ማሸት ካሹም በኋላ ቆዳውንና ሥጋውን ሙልጭ አድርጎ ማጠብ ከዚህ በኋላ ቆዳውን ከሥጋው መለየት ከዚህ በኋላ ብልቱን መለያየት ከዚያም በኋላ ማጠብ እንደገና በሎሚ በጨው መዘፍዘፍ ከዚያም አጠብ አጠብ አድርጎ የተዘፈዘፈበትን አፍሶ እንደገና ጥሩ አድርጎ ማጠብ ቀይ ሽንኩርት በርከት አድርጎ ድቅቅ አድርጎ መክተፍ ከዚያም በኋላ ዘርጋ ያለ ድስት አጥቦ መጣድ ሽንኩርቱን ለቅለቅ አድርጎ አጥቦ መጨመር ከዚያም ሽንኩርቱ ብስል እስከሚል ማቁላላት ከበሰለም በኋላ ለማቁላያ ከተዘጋጀው አብሽ በሾርባ ማንኪያ ግማሽ መጨመር እርሱም ከተስማማ በኋላ የሞቀ ውሃ መጨመር ። ከዚህ በኋላ ግን ቀይ ሽንኩርት ልጦ ድቅቅ አድርጎ ከትፎ ድስት አጥቦ ጥዶ ጨምሮ ማቁላላት ክዚያም መሐሉን ገለጥለጥ ኣድርጎ ለማቁላያ ከተዘጋጀ አብሽ በሻይ ማንኪያ አንድ ማድረግ ትንሽ አቁላልቶ የሞቀ ውሃ ትንሽ ጣል ማድረግ ከዚያም በኋላ በደኅና ሰታቴ አንድ ጭልፋ የጐንደር ድልህ ግማሽ ጭልፋ የሸዋ ድልህ አሁንም መከለስ ቅመም በሾርባ ማንኪያ አንድ ጨምሮ የሞቀ ውሃ ጣል እያደረጉ ማቁላላት ከዚያም በኋላ ሦስት ጭልፋ ቅቤ አድርጎ የጐድን አጥንት አጠር አጠር አድርጎ ቆራርጦ ጨምሮ አብሮ ማቁላላት ከዚህ በኋላ በያይነቱ ከተዘጋጁ ቅመሞች በትንሽ በትንሹ እንዳይከብድ ተጨምሮበት ጥሩ ሁኖ ከበሰለ በኋላ መው ጫው ሲደርስ ተጠብሶ የተቀመጠውን ሥጋ ጨምሮ ወዲያውኑ ማውጣት ከወጣም በኋላ የተፈጨ ቁንዶ በርበሬ ይጨመርበታል። ስለ ጨጓራ ወጥ አሠራር ጨጓራውን አጥቦ በብረት ምጣድ ጥዶ ውሃው ሲፈላ ጨጓራ ውን እየቆራረጡ ከፈላው ውሃ ላይ ጣል እያደረጉ እያወጡ መክ ተፊያና ቢላዋ አቅርቦ ትኩሱን ቶሎ ቶሎ መፋቅ ነው ከተፋቀም በኋላ እንደገና አጥቦ መቀቀል ከበሰለም በኋላ ቀይ ሽንኩርት ልጦ ከትፎ ማቁላላት ከተቁላላም በኋላ እንደሰታቴው ማነስና መተለቅ አይቶ አንድ እጅ የሸዋ ድልህ ሁለት እጅ የጐንደር ድልህ ሁለት ማንኪያ አዋዜ አንድ ማንኪያ መከለሻ ቅመም አድርጎ ማቁላላት ከተቁላላ በኋላ የተቀቀለውን ጨጓራ በትንንሹ ሰንጠቅ ሰንጠቅ አድርጎ እየቆራረጡ ቅቤ በርከት አድርጎ ጨምሮ ግማሽ ጭልፋ ጥሩ ጠጅ ጨምሮ ሙቅ ውሃ ትንሽ ትንሽ ጠብ እያደረጉጥሩ አድ ርጎ መጥበስና ከዚያው በያይነቱ ቅመሞች ትንሽ ትንሽ ሳይበዛ መጨመርከዚያም ጥሩ አድርጎ አብስሎ ማውጣት ነው። ስለ ጦም የክክ ወጥ አሠራር በመጀመሪያ ዐተሩን ለቅሞና አንፍሶ በሰል አድርጎ ማመስ ምስሩን ለቅሞና አንፍሶ አጥቦ ማመስ የታመሰውን ዐተርና ምስር ለየራሱ መከካት ሁሉንም አንፍሶ መልቀም ለየራሱ አጥቦ በን ጹሕ ማስጫ ማስጣት ከደረቀም በኋላ ለየራሱ አስቀምጦ ከዚያም ወጥ በሚሠራ ጊዜ ድስቱን አጥቦ የዐተሩን ክክ በፊት አጥቦ ጨምሮ ትንሽበሰል አድርጎ ማቆየት ከዚያም በኋላ የምስሩን ክክ አጥቦ መጨመር በሰል ሲል አውጥቶ ከምጣድ አነስ ጐድጐድ ብሎ በተ ሠራ ሰታቴ ጥሩ አድርጎ አጥቦ ለማቁላያ የተዘጋጀውን አብሽ ሁለት በሾርባ ማንኪያ ጨምሮ ትንሽ አቁላልቶ የሞቀ ውሃ ጣል ማድ ረግ ከዚያም በኋላ ማለፊያ ሆኖ የተመጠነ ድልህ አንድ ጭልፋ የጐንደሬ ድልህ አንድ ጭልፋ የሸዋ ድልህ ጨምሮ ሙቅ ውሃ ጣል እያደረጉ ማቁላላት ከዚያም ቢገኝ ቅባኑግ ባይገኝ ዘይት ሦስት ጭልፋ መጨመር ውሃም እየጨመሩ አቁላልቶ የተቀቀለ ውን የዐተር ክክና ምስር ላም አድርጎ ደቁሶ መጨመር ከዚያም በኋላ የማስተካከያ ቅመም ነጭ አዝሙድ በሶብላ ዝንጅብል ነጭ ሽንኩርትና ቀይ ሽንኩርት እነዚህን ቅመሞች አልሞ ከአንድ ቦታ አስቀምጦ ግማሽ ጭልፋ መጨመር ይህ ዓይነት ወጥ ሲሠራ በት ንሹ አምስት ሰዓት ያስፈልገዋል ። ስለ እሽክንፍር ወጥ አሠራር ድልህና ሽንኩርት ማቁላላት ጥሩ ሆኖ ከተቁላላ በኋላ ውሃ ጣል ማድረግ ውሃ ጣል ካደረጉ በኋላ ማለፊያ ድልህ መጨመር ከዚያም በኋላ ግማሽ ጭልፋ ማለፊያ ጠጅ ጨምሮ ማቁላላት ከተ ቁላላሳ በኋላ የበግ ሥጋ ጐድኑን ባጭሩ ቆራርጦ ወርቹን ቆራርጦ ሥጋወን ዘልዘል አድርጎ ማጠብ ከታጠበ በኋላ ከማጣሪያ ላይ ማድረግ ጨምሮ ማቁላላት ተቁላልቶ ውሃውን መጠጥ ሲያደርግ ሁለት ጭልፋ ቅቤ መጨመር ጥሩ ሆኖ ሲቁላላ ጮማ ሥጋ ድቅቅ አድርጎ መክተፍ የተጣደውን ሥጋ ውሃ ጣል እያደረጉ ማብሰል የበግ ጨጓራ በብረት ምጣድ ላይ ውሃ አፍልቶ የበግ ጐን ጨጓራ ከፈላው ውሃ ላይ ቁርጥ እያደረጉ ጣል ማድረግ ቶሎ ወጣ ኦድ ርጎ ከመክተፊያ ላይ መፋቅ ከዚያም በኋላ የተፋቀውን ሙልጭ አድርጎ ማጠብ የተከተፈውን ሥጋ ቅቤ ጨምሮ ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ እዋዜ በትንሹ አንድ የሾርባ ማንኪያ ጨምሮ የተከተፈ ን ሥጋ መለወስ ቅቤ መጨመር የተለወሰውን ሥጋ በተፋቀው ዐኃራ ላይ እያደረጉ ከዚያም ከተሠራው ወጥ ላይ መጨመር ጨምሮ ደኅና አድርጎ ማብሰል ከበሰለ በኋላ በየዓይነቱ ቅመም በሻሂ ማንኪያ እየለኩ መጨመር አስማምቶ ማውጣት ከዚ ያም ሲበላ በቢላዋ ቆረጥ እያደረጉ መብላት ። ስለ ጾም የክክ ኣልጫ ወጥ አሠራር ዐተሩን አንፍሶ ለቅሞ ሞቅ ሞቅ አድርጎ ማስጣት ከደረ ተም በኋላ መከካት የተከካውን ዐተር አጥቦ ማስጣት ከደረቀ በኋላ በንጹሕ ዕቃ ገጥሞ ማስቀመጥ በሚሠራቦት ጊዜ ብረት ድስትም ሆነ ድስት አጥቦ መጣድ ክኩን አጥቦ መጩመር ከዚ ያም ውሃ እንዳያንሰው ደኅና አድርጎ ጨምሮ ማብሰል ከበሰለም በኋላ ሌላ ድስት አጥቦ መጣድ ከዘያም ሽንከርት ድቅቅ አድ ርጎ ከትፎ መጨመር ከዚያም መሰልሰል አድርጎ ዘይት መጨ መር ከዚያም ጨው ጨምሮ በዘይቱ እያቁላሉ ሽንኩርቱን ማብ ሰል ከበሰጳ በኋላ ውሃ ጣል አድርጎ የተቀቀለወን ክክ ደቁሶ መጨመር ለዳቦ ከተፈጨ ነጭ አብሽ ቀዝቃዛውን ውሃ ጣድ አድ አብሹን መጨመር ለክክ አልጫ አብሽ አይቁላላም። ጥሩ አድርጎ ማብሰል ነጭ ሽንኩርት ከትፎ መጨመር ከዚያም ዝን ጅብል አጥቦ ፍቆ ከትፎ ነጭ ሽንኩርት ሁለት ፍሬዎች አብሮ ከዝንጅብሉ ጋር አብሮ መጨመር ከዚያም ኣብስሎ በሶብላ ነከር አድርጎ ማውጣት ከዚያም በኋላ አውጥቶ ቃሪያ ሶንጠቅ ሰንጠቅ አድርጎ መጨመር ድስቱን ማውጣት ። ስለ ጦም አልጫ መረቅ አሠራር ጥሩ ነጭ ዐተር አንፍሶ ለቅሞ መንከር ውሃውን አጠንፍፎ መብቀል እስከሚሞክር ማቆየት ቀይ ሽንኩርት ድቅቅ አድርጎ ጉፎ በድስት ማቁላላት ከተቁላላ በኋላ ዐተሩን አጥቦ መጨመር እንዲሁም የነጭ ዐተር ክክ ቀቅሎ ድቅቅ አድርጎ ደቁሶ በጥብጦ አቅርሮ በትንሹ መጨመር ነጭ ሽንኩርት ልጦ ድቅቅ አድርጎ ከትፎ መጨመር ከዚያም ቃሪያ ሰንጠቅ አድርጎ በሶብላ አጥቦ መጨመር ተስማምቶም ሲበስል ማውጣት ። ስለ ምስር አዚፋ አሠራር ምስሩን ለቅሞና አንፍሶ ደጋግሞ አጥቦ መቀቀል ጥሩ ሆኖ አስከሚበስል ድረስ ማቆየት ከበሰለም በኋላ ሱፍ ለቅሞና አን ፍሶ አጥቦ መቀቀል የተቀቀለውንም ሱፍ ደጋግሞ አጥቦ ማላም ከተላመም በኋላ በውሃ በጥብጦ በወፍራሙ ማጣራት ከዚያም ስናፍጭ አጥቦ አድርቆ መፍጨት እንደገና የተቀቀለውን ምስር ማላም ከዚያም በኋላ ቀይ ሽንኩርት አድርጎ ልጦ ድቅቅ አድርጎ መክተት ሎሚ አጥቦ መጭመቅ የተፈጨውን ስናፍጭ በወፍ ራሙ በተጨመቀው የሱፍ ወሃ መበጥበጥ ትንሽ ቃሪያ አጥቦ ሰንጠቅ አድርጎ ፍሬውን አራግፎ መክተፍ ከዚያ በኋላ ተቀቅሎ የተላመውን ምስር የተከተፈውን ቀይ ሽንኩርት በሱፍ ውሃ የተ በጠበጠውን ስናፍጭ አንድ ላይ አድርጎ ጨውና የተነጠረ ዘይት ትንሽ ጨምሮ ይኸን ሁሉ ከአንድ ላይ አድርጎ የሎሚውን ውሃ ጨምሮ በማንኪያ ማደባለቅ ነው ። ስለስቅስቆ ወጥ አሠራር ሥጋውን ቆራርጦ አጥቦ መቀቀል በኋላ ሽንኩርቱን ልጦ ከትፎ በውሃ አለቅልቆ ማቁላላት ሽንኩርቱን አቁላልቶ የተቁላ ላውን ሽንኩርት ገለጥለጥ አድርጎ ለማቁላልያ ከተዘጋጀው አብሽ በሾርባ ማንኪያ እንደ ሰታቴው መጠን ከመሐል መጨመር አብ ሹና ሽንኩርቱ ጥሩ ሆኖ ከተቁላላ በኋላ ወሃ መጨመር ከዚያም በኋላ ድልሁን ጨምሮ በሰል አድርጎ ማቁላላት እንደገና ደግሞ መከለሻ ቅመም ጨምሮ ማቁላላት ከዚያ በኋላ የተቀቀለውን ሥጋ ድቅቅ አድርጎ መክተፍ የተከተፈውን ሥጋና ቅቤ ጨምሮ ከተቁላላው ሽንኩርት ላይ ጨምሮ የሞቀ ውሀ ጣል እያደረጉ ማብ ሰል ከዚያም አንደኛውን ከተከለሰ በኋላ ማስተካከያውን ጨምሮ ከ ደቂቃ በኋላ ማውጣት ከወጣ በኋላ ቁንዶ በርበሬ ነስነስ ማድረግ ነው ። ስለ ቅቅል ጠላ አሠራር ፍሬውን ገብስ አንፍሶ ለቅሞ መቀቀል ተቀቅሎ ከበሰለ በኋላ ውሃውን አንጠፍጥፎ ማሳደር ከአሳደሩም በኋላ ጧት በንጹሕ ማስጫ ይሰጣል ከዚያም ከደረቀ በኋላ በጣም ሳይገባው አስተካ ክሎ መቁላት ከዚያም ሸክሽኮ ማንፈስ ከተነፈሰ በኋላ ቢቻል በቤት ወፍጮ ባይሆንም በመኪና ወፍጮ ማስፈጨት ከዚያም በኋላ ዘርዘር ባለ ወንፊት መንፋት እንደገና ጥሩ ሆኖ የበቀለ ገብስ ብቅል ያልበቀለ ምንም ያልተቀየጠበት ወቅጦ መፍጨት ከተፈ ጨም በኋላ ይነፋል የጌሾ ቅጠል እንጨት የሌለውን አንፍሶና ለቅሞ መውቀጥ ከላመ በኋላ ጌሾውን ነፍቶ ከብቅሉ ጋር አደባ ልቆ ዕቃውን ደጋግሞ አጥቦና ጥሩ አድርጎ አጥኖ መጠንሰስ ከዚ ያም በኋላ በነጩ ታምሶ የተፈጨ የገብስ ዱቄት ዕቃውን አጥቦ አጥኖ እርሾ ሳይጨምሩ ማቡካት በአምስተኛው ቀንም ጥቁር ስንዴ ሳይገባው አመስ አመስ አድርጎ ጥቁር ጤፍ አስፈጭቶ ተቦክቶ የሰ ነበተውን ሊጥ አውጥቶ በሙቅ ውሃ አደባልቆ ማሸት ከታሸም በኋላ ብድግ ማለት ሲጀምር ጥሩ አድርጎ በሸክላ ምጣድ መጋገር ከዚያም በረድ ሲል ከተጠነሰሰው ጥንስስ እየቆራረሱ መጨመር ከዚህ በኋላ በማግሥቱ መፍላት ሲጀምር መደፍደፊያውን በደንብ አጥቦና አጥኖ የብቅልና የጌሾውን ዱቄት ከደረቆቱ ዱቄት የቁና ግማሽ ዝቅ አድርጎ ከፅቃው ከመደፍደፊያው ዕቃ ሥር አድርጎ ከዚያም በኋላ ሁለት እጅ ጥንስስ አንድ እጅ ውሃ አድርጎ የደረቆ ቱን ዱቄት በወፍራሙ እየለወሱ ከመደፍደፊያው ዕቃ ውስጥ መጨ መርከዚያም በኋላ አንድ ቀን አሳድሮ መምረግ የደረቆቱ ዱቄት አሥር ቁና የሆነ እንደሆነ ሁለት ቁና የብቅል አንድ የጌሾ ዱቄት ነው የሚበቃው አጠማመቁ ግን ድፍድፉን ቢገኝ በወንጠፍት ባይገኝ በወንፊት ይጠመቃል ይህም ማታ ተጠምቆ ጧት ሊጠጣ ይችላል ። ስለ ገብስ እንጀራ አሠራር ነጩን ገብስ አንፍሶና ለቅሞ ማስጣት ከዚያም እያሰጡ ደጋ ግሞ መውቀጥየተወቀጠውን አንፍሶ የሞቀ ውሃ እርከፍከፍ አድ ርጎ እፍን አድርጎ ከድኖ ማሳደር ጡት በንጹሕ ማስጫ ማስጣት ከደረቀ በኋላ አሁንም ደጋግሞ መውቀጥ ከዚያም ጥሩ አድርጎ አንፍሶና አበጥሮ ማስፈጨት ከተፈጨ በኋላ በቀዝቃዛ ውሃ ጥቅ ልል አድርጎ ትንሽ እርሾ ጨምሮ ማቡካት ከተቦካ በኋላ በሦስተ ኛው ቀን በሞቀ ውሃ ትንሽ ጤፍ ዱቄት ጨምሮ በፈላ ውሃ ማሸት ከዚያም አቅጥኖ ማቆየት ከቆየም በኋላ ኩፍ ኩፍ ብሎ መለስ ሲል መጋገር ይህም እንደጤፍ እንጀራ ሊሆን ይችላል። ከዚያም በኋላ የሞቀ ውሃ ጨምሮ ማብሰል ቀይና ነጭ ሽንኩርት አንድ ላይ ከትፎ አብሮ ማብሰል ከዚያም ብስል ሲል አውጥቶ እንደገና ሽንኩርት ዘይት ማቁላላት ከዚያም የተቀቀለውን እን ዶድና ሽንኩርት ላም አድርጎ መደቆስ ደቁሶ ከተቁላላው ዘይት ሽንኩርት ላይ መጨመር ጥሩ ሆኖ እስኪበስል ድረስ ውሃ ሳያ በዙ እየጨመሩ ማማሰል ውፍር ብሎ ሲቦስል ቃሪያ ጣል አድርጎ ማውጣት ለእንይድ ወጥ ቢገኝ ቅባኑግ ካልተገኘም ዘይት ነገር ግን ቅቤ አይጨመርበትም አውጥቶ አስቀምጦ ቀዝቀዝ ሲል መብ ላት ነው ። ስለ ሦስተኛው ተልባ ጐመን አሠራር ጐመኑን አጥቦና ቀንጥሶ በድስትም ሆነ በብረት ድስት ውሃ መጣድ ከዚያም ውሃ ከፈላ በኋላ ጐመኑን መጨመር ከዚያም ሽንኩርቱን ልጦና ከትፎ መጨመር ከዚያም በኋላ በጣም ሳያር በጣም ጥሬ ሳይሆን የተቆላ ተልባ ጥሩ ሆኖ ተደቁሶ እንደገና ሌላ ድስት ጥዶ ቀይ ሽንኩርት ደቀቅ አድርጎ ከትፎ ማቁላላት ሽን ኩርቱም ከተቁላላ በኋላ ግማሽ ጭልፋ ዘይት ጨምሮ ማቁላላት ሽንኩርቱም ከበሰለ በኋላ ትንሽ ውሃ ጨምሮ ተደቁሶ የተቀመጠ ውን ተልባ መጨመር የተቀቀለውንም ጐመን አንጠፍጥፎ ከተ ቁላላው ድስት መጨመርና ማብሰል ከዚያም ተስማምቶ ሲበስል ቃሪያ ጐረድ ጐረድ አድርጎ መጨመር ከዚያም ከበሰለ በኋላ ማውጣት ለጤንነት ተስማሚና ቢበሉት ጣፋጭና አስደሳች ምግብ ይሆናል ። ስለ ዱባ ቋንጣ ወጥ አሠራር ዱባውን ፍቆ አጥቦ ማስጣት ከዚያም ሳሳ ያለ ሻሽ በላዩ ጣል ማድረግ በደንብ ሲደርቅ ማስቀመጥ ከዚያም እንዲሠራ ሲፈ ለግ ሰተተ ያለች ድስት ጥዶ ቀይ ሽንኩርት ከትፎ ማቁላላት ከዚ ያም ባዶ ውሃ ጣል አድርጎ ድልህ መጨመር ከዚያም በኋላ ጥሩ አድርጎ ማቁላላት ከዚያም ደርቆ የተቀመጠውን ደረቁን ዱባ ሙቅ ውሃ ከሣንን ላይ ጨምሮ ማቆየት ከዚያም በኋላ ለቅለቅ አድርጎ መጨመርየተፈጨ ኮረሪማ አንድ በሻሂ ማንኪያ መጨመር ቁንዶ በርበሬ ነስነስ አድርጎ ማውጣት ከዚያም በኋላ ሲቀዘቅዝ መብ ላት እርጥቡ ከሚሠራው የበለጠ ምግብ ይሆናል ። መ ቋሾ ስለ ግፍልፍል አሠራር ለቁርስ የሚሆን ሥጋውን ቆራርጦ ገንፈል ማድረግ በኋላ ቀይ ሽንኩርት ድቅቅ አድርጎ መክተፍ ድስቱን ጥሩ አድርጎ እጠብ ሽንኩርቱን ለቅለቅ አድርጎ መጣድ ሽንኩርቱን ደኅና አድርጎ አቁላልቶ ሲበስል መሐ ሉን ገለጥለጥ አድርጎ በሻይ ማንኪያ የማቁላያ አብሽ መጨመር ሲስተካከል የሞቀ ውሀ ጣል አድርጎ ድልህ መጨመር የመከለሻ ቅመም ትንሽ በሻይ ማንኪያ መጨመርውሃ የሞቀ ጣል እያደረጉ ጥሩ አድርጎ ማቁላላት ከዚያ የተገነፈለውን ሥጋ ጥሩ አድርጎ ከትፎ ለጋ ቅቤ ጨምሮ ጥሩ አድርጎ ማቁላላት ወይም ባጭሩ ቀጠን ቀጠን አድርጎ ዘልዝሎ መጨመርከዚያ ውሃውን ሳያበዙ በመጠኑ አንደኛውን መከለስ የማስተካከያ ቅመም እንዲሁ በሻይ ማንኪያ መጨመር ተስተካክሎ ጥሩ ሆኖ ከበሰለ ያደረውን እንጀራ እየቆ ራረሱ ባይን ባይኑ ጣል ጣል ማድረግ ከዚያም በጣም ድርቅ እ ዳይል በማንኪያ ገልበጥ ገልበጥ አድርጎ ቶሎ ማውጣት ለቁርስ ያገለግላል ።