Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
የነገረ ሃይማኖት መሰረቱ ሀልዎተ እግዚአብሔር ነውፅ እግዚአብሔር ከሌለ ፍጥረት የለም ፍጥረት ከሌለ ሃይማኖት ነገረ ፃይማኖት ምንጭ ነው። ከነዚህ በተረፈ መጻህፍት እና ሊቃውንት የነገረ ዛይማኖት ምንጮች ናቸው መጻሕፍትንና የአግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁሀማቴ ኛ ነገረ እግዚአብሔር በሰው አንደበት ተነግሮ በሰው ብዕር ቀለም ተጽፎ የማያልቅ ከውቅያኖስ የጠለቀ ከሰማይ እና ከምድር ሁሉ የራቀ ረቂቃን ከምንላቸው ሁሉ የረቀቀ ነው ነገረ አግዚአብሔር ማለት ሰው ሆነ ማለት ነው ።
እግዚአብሔርም የሰው ልጆችን ከተማ ለማየት ወረደ ዘፍ እግዚአብሔርም አብራምን አለው ከዘመዶችህ ተለይ ከሀገርህ ውጣ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ ዘፍ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራፅይ መጽሐፍ ቅዱስን ብናየው ለአበው ለክፉውም ለደጉም እግዚአብሔር መኖሩን በሰፊው ገልጧል እግዚአብሔር ለፍጡራኑ ራሱን ከገለጠባቸው አንዱ መኖሩን የሚያሳይ ነውአነ ውእቱ አምላከ አብርፃም ወአምላከ ይስሐቅ ወአምላከ ያዕቆብ እኔ የአባቶችህ የአብርፃም አምላክ የይስሐቅ አምላክ የያዕቆብ አምላክ እኔ ነኝ ዘጸ ሙሴም ወደ አግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቷል እና ፊቱን ሸፈነ ግርማውን አይቷል እና ሙሴም እግዚአብሔርን እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ ባልኩ ጊዜ የአባቶቻችህ አምላክ ስሙ ማን ነው ባሉኝ ጊዜ ምን እላቸዋለሁ አለው እግዚአብሔርም ሙሴን ያለ እና የሚኖር ወደ እናንተ ላከኝ በላቸው አለው ዘጸ በእብራይስጥ አኽያ ሸራኽያ በግፅዝ ዘሀሎ ወይሄሉ በአማርኛ ያለ እና የሚኖር ይህን ለሙሴ የገለጠ ራሱ እግዚአብሔር እኔ አለሁ እያለ መስማትና ማየት ሲቻል የለም የለህም ማለት ስንፍና ነው ይብል አብድ በልቡ አልቦ አግዚአብሔር ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል ብእሲ አብድ ኢየአምር ወዘ አልቦ ልብ ኢይሌብዎ ለዝንቱ ሰነፍ ሰው አያውቅም ልብ የሌለውም ይህንን አያስተውለውም መዝ ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ ያለህ እና የነበርክ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ትልቁን ኃይልህን ስለያዝክ ስለ ነገሥክም እናመሰግንፃለን ራዕ የውሃውም መልአክ ያለህ እና የነበርክ ጌታ ሆይ ቅዱስ ሆይ እንዲህ ስለፈረድክ ጻድቅ ነህ ራዕ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የነበረ እና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ይሰግዱ ነበር ራዕ ያለው እና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አልፋ እና ኦሜጋ እኔ ነኝ ራዕ እነዚህ ከላይ የተመለከትናቸው የመጻሕፍት ክፍሎች በሙሉ የእግዚአብሔርን ህልውና የሚመሰክሩ ናቸው አግዚአብሔር መኖሩን የገለጠባቸው ዘላለማዊነቱን ያሳየባቸው ናቸው እነዚህን መሰል ብዙ አሉ ብንጠቅሳቸው የሰማእያን ጆሮአቸው ይፈዝዛል አእምሮአቸው ይደነዝዛል የሚሻለን ህልውናውን አምነን መቀበል ነው የሰው ልጆች ስለ ፈጣሪ መኖር ሰምተው ብቻ ሳይሆን አይተው የተናገሩ ሰዎች ብዙ ናቸው ከደጋጎቹ አብርሐም ገጽ ፈጣሪውን አይቷል አብርፃም ብቻም ሳይሆን የሣራ አገልጋይ አጋርም ፈጣሪዋን አይታ መስክራለች አርሷም ያናግራት የነበረውን የእግዚአብሔር ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን እዚህ ደግሞ አየሁት ብላለችና ዘፍ በዓለም ጥበብ የተራቀቁት አወቅን ያሉት ሁሉ የዕውቀት ደረጃ ከአጋር በታች ነው እነርሱ ያላዩትን እርሷ አይታለችና እነርሱ ያልመሰከሩትን እውነት መስክራለችና ማየት ሁሉ የሚያከትምበትን ፈጣሪዋን አይታ መስክራለችና ዘበ ኀሀቤከ የአርፍ ነጽሮተ ኩሎሙ ነባቢያን ማየት የሚችሉ የሰዎች እይታ ሁሉ ባንተ ያልቃል አረጋዊ መንፈሳዊ ሰው አዲስ ነገር ማየት ይወዳል ሲያየው ያረጅበታል ሌላ ይፈልጋል እግዚአብሔርን ከማየት በላ ግን ሌላ አዲስ አይታ የለም የማያረጅ የማይጠገብ ልዩ እይታ ነው ዝያፈትዎሙ ለመላዕክት ከመ የሐውፅዎ ያዩት ዘንድ መላዕክትን የሚያስመኛቸው ጴጥ ያዩታል አይሰለቹትም መጽሐፈ ኪዳንያዩት መላዕክት ይመሰክራሉ አጋርም ለዚህ ምስክርነት የበቃች ናት ወእምዝ በዓመተ ሞተ ኦዝያን ንጉሥ ርኢክዎ ለአግዚአብሔር ዲበ መንበሩ ነዋህ ወብሩህ ንጉሥ ኦዝያን በሞተበት ዓመት አግዚአብሔርን ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ አየሁት የልብሱም ጫፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር ኢሳ ኢሳይያስ የመሰከረው አይቶ ነው እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጥለት ለወደደው ሰው ሁሉ ገልጧል ጌታን በመሰዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት አሞ ዳዊትም ስለ እርሱ እንዲህ ይላል ጌታን ሁል ጊዜ በፊቴ አየዋለሁ በቀ ነውና አልታወክም መዝ ነቢያት በልዩ ልዩ ህብረ አምሳል አይተውት መስክረዋል ሙሴ በአምሳለ ነበልባል ዳንኤል በአምሳለ አንበሳ ሌሎቹም ነቢያት አይተው መስክረውለታል። ከእመቤታችንም ዳግማይ አዳም የሚባል ጌታ ተወልዷልና በጠቅላላው በስድስቱ ቀን ከተፈጠሩት ሥነ ፍጥረታት ምስጢረ ሥላሴን ምስጢረ ሥጋዌን ምስጢረ ጥምቀትን ምስጢረ ቁርባንን ምስጢረ ትንሣኤ ሙታንን እንማርባቸዋለን ይህንን ሥነ ፍጥረት አስገሂው እግዚአብሔር መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዳሉ አንዳንዱ መጻሕፍት በጅምላና በዝርዝር አልያም እንደሸማ ጠቅልሎ እንደወርቅ አንከብልሎ ሁሉን የፈጠረ በሚል አገላለጥ የሁሉ ፈጣሪ መሆኑን ያስረዳሉ ነቢያት ሐዋርያት ሊቃውንት በሰፊው ከገለጡት ጥቂቶቹን ለማስረጃነት አንመልከት በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ በመጀመሪያ አግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ዘፍ ሰማይ በማለት በሰማይ ያሉትን ምድር በማለት በምድር ያሉትን አንድ ላይ ጠቅልሉ ተናግሯል ነቢዩ ሙሴ ገጽ እግዚአብሔር ሁሉን ለርሱ ለራሱ ፈጠረ ኀጥአንን ደግሞ ለክፉ ቀን ምሣ ለማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም ምድርንና በውስጧ ያለውን ያጸና ኢሳ ምድርን በኃይሉ የፈጠረ ሰማያትንም በጥበቡ ያጸና የመሰረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው ኤር እነሆ ተራሮችን የሰራ ንፋስንም የፈጠረ አሞጽ ከዚህ ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባህርንም በርሷም ያለውን ሁሉ ወደፈጠረ ወደ እግዚአብሔር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን ሐዋ ጠቅላላውን መጻሕፍቱ የሚነግሩን ይህን መሰል ነገር ሰፊ ነውና መጻሕፍቱን አገላብጠን ማንበብ ለዚህ ጠቃሚ ነው ስህትክሙ በኢያእምሮ መጻሕፍት ወኢ ኃይለ እግዚአብሔር የነገረ ፃይማኖት ትምህርት ምንጮች ኛ ሀህልዎተ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር መኖር ዋናው የዛይማኖት ምንጭ ነው እግዚአብሔር ራሱን ለልዩ ልዩ ሰዎች መግለጡ ድንቅ ሥራዎችን ሰርቶ ሰዎችን በሀብት መሳቡ በረድኤት ማቅረቡ ሰዎች እንዲያምኑበት የሃይማኖትን መንፈስ በውስጣቸው ማሳደሩ ወብነ መንፈስ ዘፃይማኖት የፃይማኖት መንፈስ አለን እንዲል መጽሐፍ ማመን መቀበል የሚችል ልብ ሰጥቶ በውስጣችን እምነት ሲጎድል እየሞላ ነገረ ሃይማኖትን የገለጠ ራሱ ባለቤቱ ነው ምክንያትም ዛፃይማኖትን ለቅዱሳን አበው የሰጠ ትምህርቱንም ለአበው የገለጠ ነቢያትን በትንቢት ያጸና ልቡናችንን በሃይማኖት ያቀና እርሱ ነው በዚህም መሰረት የነገረ ሃይማኖት መሰረቱ ሀልዎተ እግዚአብሔር ነውፅ እግዚአብሔር ከሌለ ፍጥረት የለም ፍጥረት ከሌለ ሃይማኖት ነገረ ፃይማኖት አይኖርም ምክንያቱም ሃይማኖት ሰው እና እግዚአብሔር የሚገናኙበት ነውና ነቢያት ለተልእኮ ከመላካቸው መጻሕፍትንም ከመጻፋቸው በፊት ሰዉን በሕገ ልቡና ፈጥሮ አምነት በልቡናው አሳድሮ መስዋየሚዕት አእንዲሰዋለት ምሥጋና እንዲያቀርብለት ያደረገው እርሱ ነው በተአምኖ ሀየሰ መሥዋዕተ አቤል እአምዘቃየን አቤል በእምነት ከቃየን የሚበልጥ መሥዋዕት አቀረበ ፅብ ይህ የሚያሳየን ነቢያት ሳያስተምሩት ሕግ ሳይሰራለት መጻሕፍት ሳይጻፉለት እግዚአብሔርን አምኖ መሥዋዕት ማቅረቡ የዛይማኖት ምንጩ ሀልዎተ አግዚአብሔር መሆኑን ያስረዳል ኛ ስብከተ ነቢያትነቢያት ከእግዚአብሔር ተልከው በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ከፈጣሪያቸው ጋር ቃል በቃል ተነጋግረው ሰውን ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እንዲመለስ ከሕገ ጣኦት እንዲፈልስ አስተምረዋል የነገራቸውም መነሻ አግዚአብሔር እንዲህ ይላል የሚል ነበር ሕዝቡ እግዚአብሔርን አንዲያውቅ እንዲያመልክ የሚያደርግ ነበር የነቢያት ዋና ተግባር የእግዚአብሔርን መኖር ለሕዝቡ መግለጥ እና ድንቅ ሥራውን መመስከር ቀድሞ ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች መመስከር ቀድሞ ያደረጋቸውን ወደፊትም የሚያደርጋቸውን መናገር ነበር አግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ ነቢያት ሳይገልጠው የቀረ ምሥጢር የለም እስመ አልቦ ምንትኒ ነገረ ዘይገብር እግዚአብሔር ዘኢከሠተ ወዘኢነበበ ለአግብርቲሁ ነቢያት ጌታ ገጽ አግዚአብሔር ምስጢሩን ለባርያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም አሞጽ በዚህ መንገድ አግዚአብሔር ምስጢሩን ጥበቡን የገለጸላቸው ነቢያት እግዚአብሔር ይወርዳል ይወለዳል ዓለምን ያድናል አያሉ ማዳነን ሰብከዋል ይህ የነቢያት ስብከት የነገረ ፃይማኖት ምንጭ ነው እስመ ተሀነጽክመሙ ዲበ መሠረተ ነቢያት በነቢያት መሠረት ታንጻችቷል ኤፌ ኛ የአምላክ ሰው መሆን ነቢያት በተናገሩት ትንቢት ባስተማሩት ትምህርት መሰረት አምላክ ሰውን ለማዳን በሰጠው ጽኑ ቀጠሮ ሰው ሆኖ መገለጡ የነገረ ዛሄይማኖት ምንጭ ነው። አንሰ ሶበ እቤ እግዚአብሔር እብል በአንተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እኔ እግዚአብሔር ባልኩ ጊዜ ስለ አብ ስለ ወልድ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማለቴ ነው እግዚአብሔር ማለት ሀያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረት የፈጠረ ማለት ነው በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ዘፍ እግዚአብሔር ገባሬ ኩሉ ወጣኔ ኩሉ ወፈጻሜ ኩሉ አሀዜ ኩሎ እግዚአብሔር ሁሉን የፈጠረ ሁሉን የጀመረ ሁሉንም የጨረሰ ሁሉንም የያበዘ ቅዳሴ ማርያም መገለጫዎቹ ኛ ቅዱስ ነው እግዚአብሔር ቅዱስ ነው ብለን ስንጠራው ቅድስናው እንደ ፍጡራን በገድል በመከራ የተገኘ ከሌላ የተቀበለው አይደለም ቅዱስነት የባህርይው ነው ቅድስናን ለሌሎች የሚሰጥ ከፍጡራን ቅድስና የተለየ ቅድስና ያለው ነውል የፍጡራን ቅድስና በርኩሰት ይለወጣል እርሱ ሁል ጊዜ የተቀደሰ ነው ኩኑ ቅዱሳነ እስመ አነሂ ቅዱስ አነ እኔ ቅዱስ ነኝ እና እናንተም በሥራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ዘሌ ኩኑ ቅዱሳነ በኩሉ ግዕዝክሙ እስመ አነሂ ቅዱስ አነ እኔ ቅዱስ ነኝ እና እናንተም በሥራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁነ ጴጥ እኔ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና ለእኔ ትሆኑ ዘንድ ከአሕዛብ ለይቻችቷለሁና ቅዱሳን ትሆኑልኛላችሁ ዘሌ ምስጋና እና ውበት በፊቱ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው መዝ አስመ ግሩም ወቅዱስ ውእቱ ግሩምና ቅዱስ ነውና መዝ ኢሳ ኛ እንደርሱ ያለ ሌላ ማንም የለም እግዚአብሔር በአምላክነቱ ብቸኛ የሚመስለው የሌለ ተወዳዳሪ የማይገኝለት አምላክ ነው አቤቱ በአማልክት በካህናት በነገሥታት መካከል እንዳንተ ያለ ማን ነው። መንገዱ ጠፍቷቸው እንጂዙ ስለዚህ ፈቃዱን መጠየቅ ይገባል ምዕራፍ ሁለት አምስቱ አዕማደ ምሥጢር የምስጢር ፍቺ በቤተ ክርስቲያን ምሥጢር በቤተ ክርስቲያን ራሱን የቻለ ትርጉም አለው ቤተ ክርስቲያን የምሥጢር ባለቤት እንደመሆንዋ ብዙ ምሥጢራትን ትፈጽማለች አነዚህን ምሥጢራት ስትፈጽም ዝም ብላ አይደለም ትርጉማቸውን አውቃና ጠንቅቃ ነው ምሥጢር የሚለው ቃል አመስጠረ አራቀቀ ከሚል የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም እንደሚከተለው ነው ኛ ስውር ድብቅ ኛ ጥልቅ ኛ ረቂቅ ገጽ ኛ በልብ ውስጥ የሚኖር ኛ ለማይገባው ሰው የማይነገር ኛ ለሚገባው የሚገለጥ ኛ በእጅ የማይጨበጥ ኛ በዓይን የማይታይ ኛ በተግባር የሚገለጥ በጠቅላላው ምሥጢር ማለት ለዓይን የራቀ ለልቡና የረቀቀ አይተው የሚያምኑት ብቻ ሳይሆን አምነው የሚቀበሉት የሚረዱት የሚፈጽሙት በልቡና የሚያኖሩት የሚያስረዱት ተረድተው የሚያስረዱት በእግዚአብሔር አጋዥነት የሚገለጥ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ የገለጠው የሚገልጠው ከማያምኑት የሰወረው የሚሰውረው ምሥጢር ይባላል በቤተ ክርስቲያን ምሥጢር የሚባሉት አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ናቸው በሌላ አነጋገር ምሥጢር ማለት ፃይማኖት ነው ኛ ምሥጢረ ሥላሴ ምሥጢር ይባላል በአካል በስም በግብር በኩነት ሦስት በባሕርይ በህልውና በአገዛዝ በሥልጣን በመለኮት አንድ ናቸው ብለው ለሰው ይነግሩታል አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ አንደምን ይቻላል ብሎ ልብ ሊመረምረው አንደበት ሊናገረው አይቻልምና ምሥጢር ይባላል ኛ ምሥጢረ ሥጋዌ ምሥጢር ይባላል ከሦስቱ አካላት አንዱ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ያለወንድ ዘር ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በህቱም ድንግልና ተጸንሶ በህቱም ድንግልና ተወለደ ብለው ለሰው ነግሩታል ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ ልብ ሊመረምረው አንደበት ሊናገረው አይችልምና ምሥጢር ይባላል ኛ ምሥጢረ ጥምቀት ምሥጢር ይባላል ካህኑ ውዛውን በብርት አድርጎ አሀዱ አብ ቅዱስ አሀዱ ወልድ ቅዱስ አሀዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ በባረከው ጊዜ ውሃው ተለውጦ በእለት ዓርብ ከጌታ ቀኝ ጎን የፈሰሰ ማየ ገቦ ይሆናል ብለው ለሰው ነግሩታል ይህ አንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ ልብ ሊመረምረው አንደበት ሊናገረው አይችልምና ምሥጢር ይባላል ኛ ምሥጠረ ቁርባን ምሥጢር ይባላል ካህኑ ህብስቱን በጻህል ወይኑን በጽዋ አድርጎ አሀዱ አብ ቅዱስ አሀዱ ወልድ ቅዱስ አሀዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ በባረከው ጊዜ ህብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል ብለው ለሰው ነግሩታል ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ ልብ ሊመረምረው አንደበት ሊናገረው አይችልምና ምሥጢር ይባላል ኛ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ምሥጢር ይባላል ሰው ከሞተ ከፈረሰ ከበሰበሰ በኋላ አካል ገዝቶ ኃይል አግኝቶ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልን ሳይል ነፍስና ሥጋው ተዋሕደው ይነሳል ብለው ለሰው ገጽ ይነግሩታል ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ ልብ ሊመረምረው አንደበት ሊናገረው አይችልምና ምሥጢር ይባላል ምሥጢር የተባለበትም ለሚያምኑ የሚገለጥ ለማያምኑ የተሰወረ በመሆኑ ነው ወለእመኒ ክዱን ትምህርትነ ክዱን ውእቱ ለህርቱማን ወለንፉቃን ወተነብዮሰ ለዘየአምን ወአኮ ለዘኢየአምንትንቢት መናግር ለሚያምኑት ነው እንጂ ለማያምኑት አይደለም ወንጌላችን የተከደነ ቢሆንም ለማያምኑት ነውቆሮ ለአዋቂዎች የተሰወረ አውቀት ለሌላቸው የተገለጠ ነው አስመ ሀባእአኮ ለዝንቱ እም ጠቢባን ወአማአምራን ወከሰትኮ ለህጻናት ከአዋቂዎች ሰውረህ ለህጻናት ገልጠኸዋልናማቴ ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስ ባዕለጠግነት ለአሕዛብ አሰብክ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር የተሰወረው የሥርዓት ምሥጢር ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ለማንስ ለእኔ ተገለጠ ቆቁሮ በዚህ መሰረት ለቅዱሳን አበው የተገለጠ ምሥጢር ሃይማኖት ነው ይህን ከልቡና ከመጻሕፍት ከመምህራን መርምሮ መቀበል ነው ምሥጢረ ሥላሴ ምሥጢረ ሥላሴ የሚባለው በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት አንዱ ነው ይህም የቤተ ክርስቲያን መሰሶዎች ተብለው ከሚጠሩት የመጀመርያው ነው አፈቅድ እንግር አምስተ ቃላተ አፅማዲዛፃ ለቤተ ክርስቲያን ለቤተ ክርስቲያን መሰሶዎች የሆኑ አምስት ቃላትን ልናገር እወዳለሁ ቆሮ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር በአንድነት በሦስትነት ጸንቶ የሚኖር በአንድነቱ ምንታዌ በአንድነቱ መንታነት በሦስትነቱ ርባኤ በሦስትነቱ አራትነት ሳይኖርበት የኖረ ያለ የሚኖር እግዚአብሔርን የምናውቅበት ትምህርት የመጀመሪያው ምሥጢረ ሥላሴ ይባላልኹ ይህን ምሥጢር ዓለም እና አለቆቹ ሊያውቁት አልቻሉም ረቂቅ ነውና ጥበበ እግዚአብሔር ነውና ጥበበ ንነግሮሙ ለጠቢባን ወአኮ ጥበበዝ ዓለም ወኢጥበበ መላዕክተ ዝንቱ ዓለም ዘሀለዎሙ ይሰአሩጥበብን ለጥበበኞች እንነግራቸዋለን ጥበቡም የዚህ ዓለም ጥበብ አይደለም ይሻሩ ዘንድ ያላቸው የዚህ ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም ቆሮ በቤተ ክርስቲያን አዕማደ ምሥጢር የሚባለው ትምህርት የሁለት ቃላት ውጤት ነው አዕማድ እና ምሥጢር ከሚሉ አፅማድ ማለት መሰሶዎች ማለት ነው ምሥጢር ማለት ደግሞ ከላይ እንደተመለከትነው ነው መሰሶ ቤቱን ተሸክሞ አጽንቶ እንዲኖር እነዚህም የሰውን ቤተ ልቡና በሃይማኖት አጽንተው ተሸክመው የክህደት ነፋስ እንዳይጥለው ደግፈው የሚኖሩ ስለሆነ አዕማድ ይባላሉ በዚህ መሰረት የመጀመሪያው አምድ ምሥጢረ ሥላሴ ነው ምሥጢረ ሥላሴ ማለት የአግዚአብሔርን አንድነት ሦስትነት የምንማርበት የትምህርት ክፍል ነው አግዚአብሔር አንድም ሦስትም ነው ሥላሴ ማለትም ልዩ ሦስትነት ማለት ነው። ልዩ ሦስትነት ማለትም አንድ ሲሆን ሦስትነት ያለው ሦስት ሲሆን አንድነት ያለው ማለት ነውር ይህ ትምህርት ምሥጢረ ሥላሴ ተብሎ ይጠራልፎ በቅደም ተከተል አቅማችን በፈቀደ መጠን ይህንን ትምህርት መማር ለክርስቲያኖች የግድ ያስፈልጋል ገጽ ምሥጢረ ሥላሴ የሦስትነት ምሥጢር የማይመረመር መለኮት ቅድመ ዓለም የነበረ ወደፊትም የሚኖር አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ የተባሉ አካላትን በማዋሐድ እግዚአብሔር በአካል በስም በገጽ በግብር በኩነትሁኔታ ሦስት በባሕርይ በሕልውና በመለኮት አንድ መሆኑን የምናምንበት የምንማርበት የምናስተምርበት ክፍል ነው አግዚአብሔር ወይም ሥላሴ አንድ ሲሆን ሦስት ሦስት ሲሆን አንድ መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት አበው ሊቃውንት ያስረዳሉ አነጋገራቸው እግዚአብሔር በአካል ሦስት ሲሆን በባሕርይ አንድ ነውና ባለቤቱን አንድ አድርገው ይናገራሉ ይኸውም እንደሚከተለው ነው ወይቤ እግዚአብሔር ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበ አምሳሊነእግዚአብሔር አለ ሰውን በመልካችን እንደ ምሣሌያችን እንፍጠር አለዝፍ ወይቤ እግዚአብሔር አዳም ኮነ ከመ አሀዱ እምኔነአዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ አለ እግዚአብሔር ዘፍ እያለ ባለቤቱን አንድ አንቀጹን አንድ ሃሳቡን ዝርዝሩን የብዙ እያደረገ እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት ሦ ስት ሲሆን አንድ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ወይቤ እግዚአብሔር ንዑ ንረድ ወንከአው ነገሮሙ ለከለዳውያን ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር አንዳይሰማው ቋንቋቸውን እንደባልቀው አለ እግዚአብሔር ብሉ ከላይ ያየነውን ምስክርነት የፀናዋል ዘፍ ስለዚህ እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት ሦስት ሲሆን አንድ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በየሥርዓቱ በየአይነቱ ያስረዳልና ማንበብ ነው የአካል ሦስትነት እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው በአካሉ በገጽ መጠቅለል መቀላቀል መፋለስ የሌለበት ልዩ ሦስት ነው በባሕርይ አንድ ሲሆን በአካል በገጽ ሦስት መሆኑን ራሱን በራሱ መሰወር ራሱን በራሱ መግለጥ የሚችል አምላክ ገልጧል መጀመሪያ ለአበው በአብርሃም በዘመነ ሥጋዌ ለዓለም በሙሉ ራሱን ገልጦ አስረድቷል ምንም እንኳን የሰው ልጅ ባጠፋው ጥፋት በበደለው በደል የእግዚአብሔርን ፊት ሊያይ ባይችልም ሃይማኖቱ ለቀና ምግባሩ ለጸና ለአብርሃም ያየው ዘንድ ራሱን ወድዶ እአና ፈቅዶ ገለጠለት አንድም ሦስትም መሆኑ ይታወቅ ዘንድ በቀትር ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት ዓይኑንም አነሳና እነሆ ሦስት ሰዎችን አየዘፍ ከላይ ባለቤቱን እግዚአብሔር እያለ አሳቡን የብዙ እያደረገ መጥቶ መጽሐፍ ጭብጡን አይለቅምና ። ግን አካል አለው አካሉም ምሉዕ ስፉህ ረቂቅ ኢህማሚ የማይደክም የማይዝል የማያረጅ ዘላለማዊ ነው የአካል ወይም የገፅ ሦስትነት የምንለው ለአብ ፍጹም አካል አለው ለወልድ ፍጹም አካል አለው ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል አለው በዚህ አካል መጠቅለል መቀላቀል ሳይኖርበት ጸንተው የነበሩ ያሉ ናቸው ይህ የአካል ሦስትነት በአብርሃም ቤት ለአብርሃም በዘመኑ ለኢሳይያስ አምላክ ሰው በሆነበት ዘመን ለሁሉ ተገልጧል ለምሳሌ ወተጠሚቆ እግዚእ ኢየሱስ ሶቤሃ ወጽአ እማይ ወናሁ ተርህወ ሎቱ ሰማይ ወርዕየ መንፈሰ አግዚአብሔር እንዘ ይወርድ እም ሰማይ በአምሳለ ርግብ ወይነብር በዲበ ርዕሱ ለእግዚእ ኢየሱስ ወመጽአ ቃል እም ሰማይ ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውዛ ወጣ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ ሲወርድ በራሱም ላይ ሲቀመጥ አየ እነሆም ድምጽ ከሰማይ መጥቶ በአርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ማቴ ሲል መሰከረ በዚህ አንድነት ሦስትነት ተገልጧል አንዱ አካል ወልድ ሲጠመቅ ታይቷል መንፈስ ቅዱስ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አብ ሲናገር ተሰምቷል ይህን እንዴት ሊሆን ይቻላል ሳንል አምነን መቀበል ነው አካላዊ መሆኑን መጻሕፍት ያስረዳሉ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው ጆሮዎቹም ወደ ልመናዎቻቸው መዝ ሰማይኒ መንበርየ ወምድርኒ መከየደ አገርየ እዴየ ሳረረታ ለምድር የማንየ አጽንአቶ ለሰማይ አኮኑ አደውየ ገብራ ዘኩሎ እነሆ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችምኢሳ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የአግሬ መረገጫ ናት እነዚህን ሁሉ አጄ ሰርታለች እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር ኢሳ እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር አኔ ነኝ ባይ አካል ያለው ዓይን ገፅ እጅ አግር ሙሉ አካል ያለው መሆኑን ገላጭ ናቸው ሀሰስኩ ገጸከ ገጸዚአከ አሀሥሥ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ ፊትህን ፈለግኩ አቤቱ ፊትህን እሻለሁ ፊትህን ከአኔ አትመልስመዝ ይህም ሦስት ጊዜ ፊትህ ፊትህን ፊትህ የሚለው የገጽ ሦስትነቱን ሲያሳይ ፊትህን ከእኔ አትመልስ የሚለው አንድነቱን ያሳያል ገጽ የስም ሦስትነት የአካል ሦስትነት አንዳለው ሁሉ አግዚአብሔር የስም ሦስትነት አለው ይህም ስም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ብለን የምንጠራው ሃይማኖትን የምንገልጽበት አምነን የምንጠመቅበት ሰይጣንን የምናሸንፍበት ስም ነው ሁሩ ወመሀሩ ኩሎ አሕዛበ ወእንዘ ታጠምቅዎሙ በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስወደ ዓለም ሁሉ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ እያስተማራችሁ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አያጠመቃችሁ ደቀመዛሙርት አድርጉ ማቴ ቀድሞ ለአብርፃም በመምሬ የአድባር ዛፍ በቀትር ጊዜ የተገለጠለት ኋላም ለዮሐንስ በዮርዳኖስ የተገለጠለት አካላት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው በዚህ ስም ከመጠራቱ በፊት እግዚአብሔር በባህርይ ስሙ ሦ ስቱም በሚጠሩበት ስም እግዚአብሔር አምላክ እየተባለ ይጠራ ነበር አልፎ አልፎ በብሉይ ኪዳን ስማቸው ለየብቻ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እየተባለ ቢጠራም በብዛት እግዚአብሔር በሚለው ስሙ ይጠራ ነበር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የሚለውን አንድ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ገለጠውበዚህ ስም እንጠራው ዘንድ ስማእ አስራኤል አሀዱ ውዕቱ አምላክከ እስራኤል ሆይ ስማ ፈጣሪህ እግዚአብሔር አንድ ነው ዘዳ አካላት በሦስትነት ቢገለጡም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ብሎሉ መጥራት አልተለመደም ምክንያቱም በብዛት አልተገለጠም ነበርና በጥቂቱ ግን ተነግሯል አኮኑ ዝንቱ አብ ፈጠረከ የፈጠረህ አርሱ አብ አይደለምን። ዝዳ ወራብኡሰ ይመስል ወልደ እግዚአብሔር አራተኛውስ የእግዚአብሔር ልጅ ይመስላልዳን ስለ እግዚአብሔር አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስ በርብቃ አፍ ላይ ወረደ ኩፋሌ ይህን በብሉይ ኪዳን በተለያየ መልኩ የተገለጠው የስም ሦስትነት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድ ላይ ሰብስቦ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አያጠመቃችቷኋቸው ብሎ የእምነታችን መገለጫ በአንድነት ስሙ ላይ ጨመረልን ገለጠልን ማለት ነው በኦሪት ላይ ወንጌልን በመንፈሰ ረድኤት ላይ መንፈሰ ልደትን እንደሰጠን እግዚአብሔር ብለን የምንጠራው በተጨማሪ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ብለን አንድንጠራ ስሙን አስተማረን እግዚአብሔር የሚለው የሦስቱም ስም ነው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይጠሩበታል አንሰ ሶበ አቤ እግዚአብሔር አብል በእንተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እፄ እግዚአብሔር ባልኩኝ ጊዜ ስለ አብ ስለ ወልድ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማለቴ ነው ቅዱስ ባስልዮስ ዘአንጾኪያ ሃይማኖተ አበው ምዕ ወሶበሂ ንብል አሀዱ እግዚአብሔር ወአሀዱ መለኮት ንብል በእንተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሐር አንድ መለኮት ስንል ስለ አብ ስለ ወልድ ስለ መንፈስ ቅዱስ መናገራችን ነው ዛአ ዮሐንስ ዘአንጾኪያ ምዕ ክፍል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የሚለው ስም ግን ተፋልሶ የለበትም አብ የሚለውስም አብ ብቻ ይጠራበታል ወልድ የሚለው ስም ወልድ ብቻ ይጠራበታል መንፈስ ቅዱስ የሚለው ስም መንፈስ ቅዱስ ብቻ ይጠራበታል ገጽ ኢይፈልስ ስመ አብ እምከዊነ ስመ አብ ሀበከዊነ ስመ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወስመ ወልድኒ ኢይፈልስ አእምከዊነ ስመ ወልድ ሀበከዊነ ስመ አብ ወመንፈስ ቅዱስ ወስመ መንፈስ ቅዱስኒ ኢይፈልስ እምከዊነ ስመ መንፈስ ቅዱስ ሀበ ከዊነ ስመ አብ ወወልድ የአብ ስም አብ ከመባል ወልድ መንፈስ ቅዱስ ወደመባል የወልድም ስም ወልድ ከመባል አብ መንፈስ ቅዱስ ወደ መባል የመንፈስ ቅዱስ ስም መንፈስ ቅዱስ ከመባል አብ ወልድ ወደ መባል አይፋለስም አይለወጥም ፃአ አብኒ አብ ውእቱ ወልድኒ ወልድ ውእቱ መንፈስ ቅዱስኒ መንፈስ ቅዱስ ውእቱ አብኒ ኢኮነ ወልደ ወኢ መንፈስ ቅዱሰ ወልድኒ ኢኮነ አበ ወኢመንፈስ ቅዱሰ ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢኮነ አብ ወኢ ወልደ አብ አብ ነው ወልድ መንፈስ ቅዱስ አይባልም ወልድም ወልድ ነው አብ መንፈስ ቅዱስ አይባልም መንፈስ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ነው አብ ወልድ አይባልም አብም ወልድን መንፈስ ቅዱስን አይደለም አብ ነው ወልድም ወልድ ነው እንጂ አብ መንፈስ ቅዱስ አይደለም መንፈስ ቅዱስ አብ ወልድ አይደለም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ ዛይ አበ የግብር ሦስትነት እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ የስም ሦስትነት አንዳለው ሁሉ የግብር ሦስትነት አለው ግብር በሁለት ይከፈላል የአካል ግብር እና ሥልጣናዊ ግብር ተብሎ ። መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ አየተባሉ ይኖራሉ አብ ወላዲ እንጂ ተወላዲ ሰራጺ አይባልም ወልድም ተወላዲ እንጂ ወልድ አሰራጺ አይባልም መንፈስ ቅዱስም ሰራጺ ይባላል እንጂ ወላዲ ተወላዲ አይባልም በየራሳቸው ስም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ተብለው ይጠራሉ በየራሳቸው የአካል ግብር ወላዲ ተወላዲ ሠራጺ ተብለው ፀንተው ይኖራሉ በስም በግብር በአካል ሦስት ማለት ይህ ነው ይህ የአካል ግብራቸው በመጻሕፍት ተገልጧል ማንበብ ነው የአብ አባትነት ወይም ወላጅነት የወልድ ልጅነት ተወላዲነት ወትሰምዩዬዮ ስሞ ኢየሱስ ውእቱ አቢይ ወይሰመይ ወልደ እግዚአብሔር ልዑል ስሙን ኢየሱስ ትለዋለች አርሱ ታላቅ ነው የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይባላል ሉቃ እግዚአብሔር አንድ ልጁን እስከመስጠት ደርሶ ዓለሙን እንዲህ ወዲልና ዮሐ ገጽ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክቡር የሆነውን ክብሩን አየን ዮሐ አቡየኒ እስከ ይዕዜ ይገብር ወአነሂ እገብር አባቴ እስከ ዛሬ ይሰራል እኔም እሰራለሁ ዮሐ ወመልአ መንፈስ ቅዱስ ላአለ ኤልሳቤጥ መንፈስ ቅዱስ በኤልሳቤጥ ሞላ ሉቃ ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችል ዮሐ ከአብ የወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል ዮሐ በዚህ መልክ በራሳቸው የአካል ግብር ጸንተው ይኖራሉ ሥልጣናዊ ግብር የሚለውን በስልጣን ያላቸውን አንድነት ስናይ እናየዋለን የኩነት የትኔታ ሦስትነት ኩነታት በተፈልጦ በተከፍሎ ያለመጠቅለል ያለመቀላቀል በራሳቸው ጸንተው የሚኖሩ አካላትን በሕልውና የሚያገናዝቡ ናቸው አነርሱም ልብነት ቃልነት እስትንፋስነት ተብለው ይጠራሉ ወይም ልብ መሆን ቃል መሆን እስትንፋስ መሆን ማለት ነው ልብነት በአብ መሰረትነት ለራሱ ልባዊ ሆኖ ለወልድ እአና ለመንፈስ ቅዱስ ልብ እውቀት መሆን ነው። ቃልነት በወልድ መሠረትነት ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ንባብ መሆን ነውእስትንፋስነት በመንፈስ ቅዱስ መሰረትነት አራሱ ሕያው ሆኖ ለአብ እና ለወልድ ሕይወት መሆን ነው ይህ ኩነታት ይባላል በዚህ መሰረት ምሥጢረ ሥላሴ የሚያስተምሩ ሊቃውንት አብ በልብ ወልድ በቃል መንፈስ ቅዱስን በአስትንፋስ መስለው ያስተምራሉ በአብ ልብነት ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስቡበታል በወልድ ቃልነት አብ መንፈስ ቅዱስ ይናገሩበታል በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት አብ ወልድ ሕልዋን ናቸው ይኖሩበታል አብኒ ልቡናዎሙ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ ወልድኒ ቃሎሙ ለአብ ወለመንፈስ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስኒ አእስትንፋሶሙ ለአብ ወወልድ ዛይ አበ አብ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ ልባቸው እስትንፋሳቸው ነው ወልድ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው መንፈስ ቅዱስ ለአብና ለወልድ እስትንፋሳቸው ሕይወታቸው ነው በአብ ልብነት ያስባሉ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ይኖራሉ ማለት ነው ይህን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሚከተሉት ምሣሌዎች መስለው ያስተምራሉ በነፍስ በፀሐይ በእሳት በነፍስ ነፍስ አካሏ አንድ ሲሆን ሦስት ከዊን አላት ልብ ቃል እስትንፋስ ገጽ ልብ ቃል እስትንፋስ ያላት ነፍስ የሦስትነቷ ከዊን አንድነቷን እንደማይከፍል የአንድነቷ ከዊን ሦስትነቷን አእንደማይጠቀልለው ሥላሴም በአካል በስም በግብር በከዊን ሦስትነታቸው አንድነታቸውን ሳይከፋፍለው አንድነታቸውም ሦስትነታቸውን ሳይጠቀልለው ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አንላቸዋለን ነፍሳችን ልብ ቃል እስትንፋስ ስላላት ሦስት ነፍስ እንደማትባል ሥላሴም በአካል በሥም በግብር ሦስት ብንልም ሦስት አምላክ አይባልም አንድ አምላክ እንጂ ዛይ አበ ወኢይትበሀሉ ሠለስተ አማልክተ አላ አሀዱ አምላክ ሦስት አምላክ አይባሉም አንድ አምላክ እንጂ በፀሐይ ፀሐይ ሦስት ከዊንሁኔታዎች አሏት ክበብ ብርሃን ሙቀት ክበቡ በክበብነቱ ሙቀትን ብርፃንን ያስገኛል ብርሃንም በክበቡ መሰረትነት ከክበብ ተገኝቶ ለዓለም ያበራል የጨለማን ሥልጣን ይሽራል ሙቀትንም በክበብ መሠረትነት ተገኝቶ እርጥቡን ያደርቃል ቅዝቃዜን ያስለቅቃል በክበቡ አብ በብርሀኑ ወልድ በሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላል። በነበልባሉ አብ በብርሀኑ ወልድ በዋዕዩ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላልፁኹ ይህ አንድ እሳት ይባላል እንጂ ሦስት አሳት እንዳይባል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል በስም በግብር በኩነት ሦስት ቢሆንም አንድ አምላክ ይባላሉ እንጂ ሦስት አምላክ አይባሉም ከላይ የተመለከትናቸው ሦስትነቶች በህልውና ተገናዝቦ አንዱ በአንዱ ሕልው ሆኖ አንዲት ስግደት ተሰግዶላቸው አንድ አምልኮት ተሰጥቷቸው ይኖራሉ አንድ አምላክ ተብለው ይመለካሉ። ዘዳ ረ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ዕብ ላ ሁሉ በአርሱ ሆነ ዮሐ የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ ኢዮ ሦስቱን አንድ እግዚአብሔር አንድ ፈጣሪ ብለን እናምናለን በአካል በስም በግብር በኩነት ሦስት በባህርይ በህልውና በሥልጣን አንድ አምላክ ብለን እናምናለን አነ ወአብ አሀዱ ንህነ እኔና አብ አንድ ነን ዮሐ ላ ርእየ ኪየ ርእዮ ለአቡየ እኔን ያየ አብን አየ ዮሐ ወበዝሁ ሕዝብ በትምህርተ መንፈስ ቅዱስ ሐዋ ይህ የምትሰሙት ቃል የእኔ አይደለም ዮሐ ገጽ ትምህርቴ ከእኔ አይደለም ዮሐ የአውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ሁሉን ከእኔ ወስዶ ያስተምራችል የሚሉት የሕልውናን አንድነት የሚያሳዩ እኩል እሩያን አንደ ሆኑ የምንማርባቸው ናቸው ይህ ምሥጢረ ሥላሴ ይባላል አብ አባት ነው ከወልድ አይቀድምም አይበልጥም ከመንፈስ ቅዱስም አይበልጥም አይቀድምም ወልድ ልጅ ነው ከአብ አያንስም ከመንፈስ ቅዱስ አይበልጥም መንፈስ ቅዱስ ከአብ ከወልድ አያንስም ምሥጢር ያሰኘውም ይህ ነው ሦስት ናቸው አንድ አምላክ አባቱ ነው አይበልጠውም መቅደም መቀዳደም መብለጥ መበላለጥ የለም አሀቲ ቅድምናሆሙ ለሥላሴ ወእሩያን እሙንቱ በቅድምና ለሥላሴሰ አልቦ ቅጽበት ከመ ቅጽበተ ዓይን ለሥላሴ ቅድምናቸው አንዲት ናት ቅድመ ዓለም በመኖር የአይን ጥቅሻ ያህል አይቀዳደሙም ዛይ አበ ኤራቅሊስ ይህን ተቀብሎ መኖር ምሥጢር ነው። መሞትን ኣንድ ጊዜ ፈፅሞ ለኋጥያት ሞቷልና በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚኣብሔር ይኖራል ሮሜ እነዚህ ሁሉ ዳግም ሞት ኣለባቸው እንዳልን ዳግም ትንሣኤ ዘጉባኤን ይጠብቃሉ እርሱ ግን ፈጥኖ ተነስቷል ወአህፀረ እድሜ ለርዕሱ ትንሣኤውን አድሜ ነበተ ጥሪኣን መጽሐ በአዚህ መሠረታዊ ጉዳዮቸ የክርስቶስ ትንሣኤ ልዩ ነው የሰው ልጆች ትንሣኤ የሰው ልጆች ትንሣኤ ዘጉባኤን ጠብቀው ለሚነሱት ትንሣኤ መሪው ወይም መሠረቱ የክርስቶስ ትንሣኤ ነው ክርስቶስ ሞትን ድል ኣድርጎ ትንሣኤያችንን ካበሠረ ጀምሮ የሰው ልጆች ሞትን መፍራት ትተዋል ይልቁም ወደ አርሱ ፄደው ከእግዚኣብሔር ጋር መኖርን መርጠዋል ገጽ እምኒ ሐየውነ ለአግዚኣብሔር ነሐዩ ወዕመኒ ሞትነ ለአግዚኣብሔርን መውት ዕመኒ ሐየወነ ወአመኒ ሞትነ ለእግዚኣብሔር ጉደጋነ ብንኖርም ለእግዚኣብሔር እንኖራለን ብንሞትም ለእግዚኣብሔር እንሞታለን ብንሞትም ብንኖርም ለአግዚኣብሔር ነንሮሜ ልፄድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ ከሁሉም ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና ፊል የሰው ልጅ እንዲህ ከሞት ላይ ድፍረት ያገኘው ክርስቶስ በትንሣኤው ሌላ ሕይወት አንዳለ በማረጋገጡ ሞት በመሻሩ ነው ስለዚህ ሰው ይህን የክርስቶስን ትንሣኤ በኩር ኣድርጎ ከሙታን ተለይቶ ይነሣል ጻድቁም ኋጥዑም ይነሣ ዘንድ የግድ ነው የሰው ልጆችን ተስፋ ትንሣኤን የሚያሳዩ ትንቢቶችም ነበሩ የሰው ልጅ ሆይ እነዚህ ኣጥንቶች በሕይወት ይኖራሉንኣለኝ እኔም ጌታ ሆይ ኣንተ ታውቃለህ ኣልሁ አርሱም እንዲህ ኣለኝ በእነዚህ ኣጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው እናንተ የደረቃችሁ ኣጥንቶች ሆይ የእግዚኣብሔርን ቃል ስሙ ጌታ አግዚኣብሔር ለአነዚህ ኣጥንቶች እንዲህ ይላል እነሆ ትንፋስን ኣለብሳችሁኣለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ ኣመትም እሰጣችኋለሁ ሥጋንም ኣወጣባችጊለሁ በእናንተም ላይ ቁርበትን እዘረጋለሁ ትንፋሽንም ኣነበላችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ እኔም እግዚኣብሔር እንደሆንኩ ታውቃላችሁ እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ ስናገርም ድምፅ ሆነ እነሆም መናወጥ ሆነ ኣጥንቶችም ኣጥንት ከኣጥንት ጋር ተቀራረቡ እኔም ኣየሁ እነሆም ጅማት ነበረባቸው ሥጋም ወጣ ቁርበትም በላያቸው ተዘረጋ ትንፋሽ ግን ኣልነበረባቸውም እርሱም የሰው ልጅ ሆይ ትንቢት ተናገር ለነፋስም ትንቢት ተናገር ጌታ እግዚኣብሔር እንዲህ ይላል ነፋስ ሆይ ና ከኣራቱ ነፋሳት ዘንድ ና በተገደሉትም እነዚህ የተገደሉትም በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው በል ኣለኝ እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ ትንፋሽምነፍስገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ እጅግ ትልቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ ሕዝ ሕዝቤ ሆይ መቃብራችሁን አከፍታለሁ ከመቃብራችሁም ኣወጣችሁ ኣለሁ ሕዝቤ ሆይ መቃብራችሁን በከፈትኩ ጊዜ ከመቃብራችሁም ባወጣቷችሁ ጊዜ እግዚኣብሔር እንደሆንኩ ታውቃላችሁ በሕይወትም ትኖራላችሁሕዝ ኣሁን ከላይ ያየነው የነብዩ የሕዝቅኤል ትንቢት በቀጥታ የሚያስረዳን የሰው ልጆች ሞተው ፈርሰው በስብሰው አንደማይቀሩ ትንሣኤ እንዳላቸው ነው ቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ ሙታንን የምታስተምረው የነቢያት ትንቢት የሐዋርያትን ትምህርትን መሠረት ኣድርጋ ነውና ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል በምድር ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ እኩሌቶቹ እኩሌቶቹ ወደ ዘለዓለም ሕይወት እኩሌቶቹ ወደ እፍረት ወደ ዘለዓለም ጉስቁልና ጥበበኞችም እንድ ሰማይ ፀዳል ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘለዓለም ይደምቃሉ ዳን ቤተ ክርስቲያን ይህን ተስፋ ትንሣኤ ከነብያት አና ከሐዋርያት ኣግኝታ በሊቃውንት ታስተምራለች ገጽ ይህ ትንሣኤ ዘጉባኤ በሚሆንበት ጊዜ ንቃህ መዋቲ ዘትነው ወያበርህ ለከ ክርስቶስ ኣንተ የተኛህ ንቃ ክርስቶስ ያበራልሃል እንደተባለው ቅዲስ እግዚኣብሔር ዘያነቅሆሙ ለሙታን ሙታንን የሚያስነሳቸው እግዚኣብሔር ልዩ ነው የሚለው ኣዋጅ ሲታወጅ ኣውሬ የበላው ውዛ የወሰደው የፈረሰ የበሰበሰው የሥጋ ቅሪት ሁሉ ይሰበሰባል በቀዳሚ ነፍሐተ ቀን ሣትግ በዕኩሉ ፀበለ ሥጋ ዘተዘርው ውስተ ኩሉ ኣጽናፈ ዓለም ዘበልየ ወዘማሰነ በዘዚኣሁ ኣሪያ ወኣምሳል ወበዳግም ንፍሐተ ቀን ይሰፈያ አዕጽምት ምስለ ሥጋ ወሣከውን ንፍሐተ ቀን ይትነሰኡ ሙታን ጻድቃን ወጥኣን እንዘ ይፀውሩ ምግባራቲሆሙ እማሂ ሰናየ ወእመሂ እኩይ ዘተለዎሙ እምዲበምድር በመጀመሪያ የነጋሪት ድምፅ በዓለም ዳርቻ በተነ ኣጥንት ሁሉ ውፃ የወሰደው በኣራዊት ሆድ ውስጥ ያለው በልዩ ልዩ መልኩ የጠፋው ኣጥንት ይሰበሰባል በሁለተኛ የነጋሪት ድምፅ ያለመንቀሳቀስ ትኩለ በድን ይሆናል በሦስተኛው የነጋሪት ድምፅ ጻድቃንም ጊጥኣንም ከምድር የተከተላቸውን ሥራቸውን ይዘው እንደ ዓይን ጥቅሻ ይነሳሉ ያዕ ጻድቁም ሥራውን ይዞ ይነሣል ዋጋውን የሚቀበልበት ነውና ኋጥኡም ሥራውን ይዞ ይነሣል ፍዳውን የሚቀበልበት ነውና ገበሬ ጤፍ ዘርቶ ኑግ ኑግ ዘርቶ ጤፍ ማጨድ እንደማይችል ሁሉ ጻድቁ ጊጥአእ ጊጥሁ ጻድቅ ሆኖ ኣይነሳም ቅዱስ ጳውሎስ ትንሣኤ ሲያስተምር አአበድ አንተ ዘትዘርእ ኢየሐዩ ለእመ ኢሞተ አንተ ሠነፍ አንተ የዚሁኸው ዘር ካልፈረሰ ካልበሰበሰ አይበቅልም ብሎ ያስተማረው ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዎች ስለነበሩ ነው ኛ ቆሮ ጌታችንም የሙታንን ትንሣኤ እንዲህ በማለት ነግሮናል ኣማን እብለክ ይበድህ ጊዜ ከመምውታን ይስምዕዎ ቋሉ ለወልደ እግዚአብሔር ወይዕዜ ውእቱ ወይወጽኡ አለሰናየ ገብሩ ውሰተ ትንሣኤ ዘለህይወት ወአለሰ እኩየ ገብሩ ውስተ ትንሣኤ ዘለጸይን እውነት እላችኋለሁ ሙትን የእግዚአብሔርን ልጅ ቃል የሚሰሙበት ግዜ ይመጣል እርሱም አሁን ነው ።