Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚጠይቁ ታክስ ከፋዮች ከተሞላው የተመሳሽ ቅጽ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው ታክስ የተከፈለበት ግብዓት በምርት ሂደት ጥቅም ሳይ መሆኑን የሚያስረዳ የምርት ጥምርታ ማስረጃ ዘበቦ።
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ስለሚደረግበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር መጋቢት አዲስ አበባ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ስለሚደረግበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከተመዘገበ ሰው ለሚቀርብ የታክስ ተመሳሽ ጥያቄ የስጋት ደረጃን መሰረት ያደረገ የታክስ ተመላሽ አገልግሎት መስጠት በማስፈለጉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መብት ያለው ሰው ታክሱን በግብይቱ ላይ ከከፈለ በኋላ በተመላሽ ስርዓት ስለሚስተናገድበት ሁኔታ መደንገግ በማስፈለጉ የገቢዎች ሚኒስቴር በተጨማሪ እሴት ታክስ ደንብ ቁጥር አንቀጽ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህን የአፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌ አጭር ርዕስ ይህ መመሪያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ስለሚደረግበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር ተብሉሎ ሊጠቀስ ይችላል ትርጉም የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር ለዚህ መመሪያ አፈፃሀም ህ መደበኛ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ማለት ለታክሱ የተመዘገበ ሰው የሚያቀርበው ጥያቄ ተከትሎ በአዋጅ ቁጥር በአንተፅ እና ድንጋጌዎች መሠረት ተመላሽ እንዲሆን የሚፈቀድለት ታክስ ነው ጥተመዘገበ ሰው ማለት ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ እና ሰርተፍኬት ያለው ሰው ነሃው ለታክስ ተመላሽ የሚቀርብ ማስረጃ ማለት ስለ ታክስ ማቀናነስ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በግብአት ላይ ወይም በካፒታል ዕቃዎች እና በንግድ ስራ ሀብቶች እንዲሁም በባለ ልዩ መብቶች ወይም በተመላሽ ሰርዓት እንዲስተናገዱ በተፈቀደላቸው ሰዎች የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ለማድረግ ለታክስ ባለስልጣኑ መቅረብ ያለበት ማሰረጃ ነው አነስተኛ የስጋት ደረጃ ማለት በስጋት ምደባ መስፈርቶች መሰረት ታክስ ከፋዩ የሚገኝበት ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ነው መካከለኛ የስጋት ደረጃ ማለት በስጋት ምደባ መስፈርቶች መሰረት ታክስ ከፋዩ የሚገኝበት መካከለኛ የስጋት ደረጃ ነው ፍተኛ የስጋት ደረጃ ማለት በስጋት ምደባ መስፈርቶች መሰረት ታክስ ከፋዩ የሚገኝበት ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ነው ክክስ ማቀናነስ ማለት ታክስ ከፋዩ ዕቃ ወይም አገልግሎት ሲገዛ የከፈለውን ተጨማሪ እሴት ታክስ እቃውን በሜሸጥበት ጊዜ ከሚሰበሰበው ተጨማሪ እሴት ታክስ በመቀነስ ቀሪውን ለታክስ ባለስልጣኑ ገቢ የሚያደርግበት ወይም በአብላጫ የተከፈለ የተጨማሪ እሴት ታክስ ለሌሎች የታክስ ወይም የቀረጥ ዕዳዎች ማካካሻ እንዲውል ማድረግ ነው ዕቃ ማለት ማንኛውም ታክስ ከፋዩ የሚገዛው ዕቃ ሲሆን የንግድ ወይም የካፒታል እቃ ወይም የንግድ ስራ ሀብትን ይጨምራል ጥካፒታል ፅቃ ማለት ለሽያጭ የሚውሉ ምርቶችን ወይም አገልግሉሎቶችን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ለማምረት ጥቅም ላይ የሚውል ሀብት ሲሆን መሬትን ህንፃን ማሽነሪን መሣሪያዎችን ኮምፒዩተር እና አነዚህን የመሳሰሉ ግዙፋዊህልወት ያላቸው ቋሚ ሃብቶችና ንብረቶችን እንዲሁም ሌሎች የንግድ ፃብቶችን ይጨምራል ጥንግድ ሥራ ፃብት ማለት ከአንድ ዓመት በላይ የአገልግሎት ጊዜ ያለውና ለሸያጭ የማይውል በታክስ ከፋዩ ስም የተመዘገበ ወይም የተገዛ ግዙፋዊ ህልዎት ያለው ወይም የሌለው የታክስ ከፋዩ ቋሚ ንብረት ወይም ዛብት ሲሆን ህንፃን ተሸሽከርካሪን የአገልግሎት መስጫ ወይም የንሣድ መሣሪያዎሥችን የኢንቨስትመንት ንብረቶችን የድርጅት መልካም ስምና ዝናን የንግድ ስምን የንግድ ምልክትን እንዲሁም አዕምሯዊ ንብረቶችን ይጨምራል ከፍተኛ ደረጃ ኦዲት ማለት ለመደበኛ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ሥርዓት የሚቀርቡ ደረሰኞችን ሙሉ በሙሉ የማጣራት ዛደት ነው አነስተኛ ደረጃ ኦዲት ማለት ለመደበኛ የተጨማሪ አሴት ታክስ ተመላሽ ሥርዓት ከሚቀርቡ ደረሰኞች ውስጥ ስጋት መሠረት ባደረገው የተጨማሪእሴት ታክስ ተመላሽ አሰራር ማንዋል በተቀመጠው ልክ በከፊል የማጣራትዛደት ነው ቃ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ወጪ ያለው ፕሮጀክት ማለት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ፕሮጀክት ሆኖ ማምረት ወይም አገልግሎት መስጠት እስኪጀመር ደረስ ከሶሰት ዓመት በላይ የሚፈጅበት ሆኖ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ እንዲውል አንድ መቶ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና ከዚያ በላይ ወጪ የሚደረግበት መሆኑ የተረጋገጠለት ፕሮጀክት ነው ዋበጎ አድራጎት ድርጅት ማለት በሰብዓዊ ዕርዳታ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት የተቋቋሙ ሆነው በበጎ አድራጎት ምዝገባና ፈቃድ ኤጀንሲ ተመዝግበው የዕውቅና ሰርተፈኬት የተሰጣቸው ተቋማት ናቸው ባለልዩ መብት ድርጅቶች ማለት ኤምባሲዎች የቆንጽላ ጽቤቶች አለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች እንዲሁም የውጭ አገር መንግስት የዕርዳታ ድርጅቶች ናቸው ስራ ማስፈጸሚያ ማለት የባለ ልዩ መብት ድርጅቶች የተቋቋሙበትን ተግባር ለማሳካት የሚያገለግል ማለት ሲሆን ለሰራተኞቻቸው የግል መጠቀሚያ የሚያውሉትን አይጨምርም ቅይጥ አቅርቦት ስሌት ማለት የተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለበት ግብዓት ከታክስ ነፃ ለሆነ እና ታክስ ለሚከፈልበት አቅርቦት የዋለ በሚሆንበት ጊዜ ታክሱን ለመመለስ ታክስ ለማይከፈልበት ገቢ የዋለውን መጠን ለይቶ ለማስላት የምንጠቀምበት ዘዴ ነው ጉገዥው ተይዞ የሚከፈል ታክስ ማለት ታክስ የሚከፈልበት ግብዓት ሲከናወን ሊከፈል የሚገባው ታክስ ለታክሱ ባልተመዘገበ ወኪል ተይዞ ለታክስ ባለስልጣኑ ገቢ የሚደረግ የተጨማሪ አሴት ታክስ ነው ወኪል ማለት ታክስ ከሚከፈልበት ግብይት ሳይ የተጨማሪ አሴት ታክስን ተንሶ በመያዝ ለታክስ ባለስልጣኑ ገቢ እንዲያደርግ ውክልና የተሰጠው አካል ነው የተፋጠነ የተመላሽ ስርዓት ማለት በስርአቱ ተጠቃሚ እንዲሆን የተመረጠ ለታክሱ የተመዘገበ ላኪ ወደ ዉጭ ለሜልከዉ ምርት ግብዓት ከሀገር ዉሰጥ ሲገዛ የከፈለው ታክስ ምርቱ ወደ ዉጭ ከመላኩ በፊት ተመላሽ የሚደረግበት ስርዓት ነዉ ሰው ማለት የተፈጥሮና የህግ ሰውነት የተሰጠው አዋጅ ማለት የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ነው ታክስ ማለት ተጨማሪ እሴት ታክስ ነው የታክስ ባለሥልጣን ማለት የገቢዎች ሚኒስቱር የክልል ገቢዎች ባለስልጣን የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ማለት ሲሆን ቅርንጫፍ ቤቶቻቸውንም ይጨምራል ሚኒስቴር ማለት የገቢዎች ሚኒስቴር ነው በቢህ መመሪያ በወንድ ጾታ የተገለፀው ለሴት ጾታም ተፈጻሚ ይሆናል በዚህ መመሪያ ውስጥ ትርጉም ያልተሰጣቸው ቃላት በሌሎች የታክስና ተዛማጅ ህጎች የተሰጣቸውን ትርጉም ይይዛሉ የተፈጻሚነት ወሰን ይህ መመሪያ የተከፈለ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ተመላሽ በሜደረግለት ሰው ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ክፍል ሁለት የታክስ ተመላሽ የሚፈቀድባቸው ግብይቶች በአዋጁ አንቀፅ ድንጋጌ መሰረት በአንድ የሂሳብ ጊዜ በተመዘገበ ሰው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ተፈፃሚ የጫሆነው በሚከተሉት ግብይቶች ላይ ነው ሀ ታክስ ከሚከፈልበት ግብይት ዋጋ ውስጥ ቢያንስ ሃያ አምስት በመቶ በዜሮ የማስከፈያ ልክ ታክስ በተከፈለበት ግብይት ላይ በብልጫ የተከፈለ ታክስ ጥያቄው በቀረበ በአርባ አምስት ቀናት ውስጥ ተመላሽ የሚደረገው ለሚከተሉት ግብይቶች ነው ወደ ውጭ የሚላኩ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በዓለም አቀፍ በረራ እና ተያያዥ አገልግሎቶች እንዲሁም ለፍጆታ የሚውሉ የቅባት ዘይቶችና ሌሎች አላቂ ቴክኒክ ዕቃዎች ግብይት በአገር ውስጥ አምራቾች ለብሔራዊ ባንክ የሚቀርብ ወርቅ ግብይት ለ በካፒታል ዕቃዎች ላይ በተደረጉ ግብይቶች እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀንሰው በሚያስቀሩ አካላት ተቀናሽ የሚደረግ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽን ሳይጨምር ተመላሽ መደረግ ያለበት ታክስ በታክስ ጊዜው ውስጥ ያልተቀናነሰ አንደሆነ በሚቀጥሉት አምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ከሜከፈለው ታክስ ላይ የሚቀናነስ ሆኖ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያልተቀናነሰ ቀሪ ሂሳብ ያለ እንደሆነ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በአርባ አምስት ቀናት ውስጥ ተመላሸ ይደረጋል ሐ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀንሶ በሚያስቀር ሰው ታክስ ተቀንሶ የተከፈለበት ደረሰኝ የተሰጠው ታክስ ከፋይ በተቀበለው ደረሰኝ ላይ የተገለፀውን የታክስ መጠን በግብዓት ላይ ከተከፈለው ታክስ ጋር እንዲያካክስ በማድረግ ቀሪው ሂሳብ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በአርባ አምስት ቀናት ጊዜ ውስጥ ተመላሸ ይደረጋል መ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ የተደነገገው ቢኖርም በ ታክስ ከፋዩ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከተመዘገበት ቀን በፊት ባሌት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ በቋሚ የንግድ ስራ ፅቃ ላይ የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲቀናነስ የተፈቀደ እንደሆነ በሂሳብ ጊዜው በግብአት ላይ ከተከፈለው ታክስ ላይ አንዲቀናነስ ተደርጎ ቀሪው ሂሳብ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተመላሸ ይደረጋል አንድ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ ሰው የንግድ ስራውን በማስፋፋት ሂደት ግንባታው ባልተጠናቀቀ ህንጻ ላይ የተከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ህንጻው ተጠናቆ ታክስ ለሚከፈልበት የንግድ ተግባር መዋሉ ሲረጋገጥ በግብዓቱ ላይ የተከፈለው ታክስ በግብይት ላይ ከተከፈለው ታክስ ላይ በሂሳብ ጊዜው ውስጥ እንዲቀናነስ ተደርጎ ቀሪው ሂሳብ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በአርባ አምስት ቀናት ጊዜ ውስጥ ተመላሸ ይደረጋል ሠ በዚህ መመሪያ የተደነገገው ቢኖርም ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ወጪ ያለው ፕሮጀክት ለፕሮጀክቱ ግብዓት በዋለ ግዥ ላይ የተከፈለ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲመለስለት ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ ግዥው ከተከናወነበት ቀን ቀጥሎ ባለው ፎዴ የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተመሳሽ ይደረግለታል ጩ ረ በማዕድንና ነዳጅ ፍለጋ የተሰማራ ኩባንያ የማዕድንና ነዳጅ ፍለጋው ሳይሳካለት የቀረ እንደሆነ ከማዕድን ሚኒስቴር የተረጋገጠ ማስረጃ ሲያቀርብ በግብዓት ግዥ ላይ ለከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ በማያያዝ የታክስ ተመላሽ ጥያቄ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተመላሽ መደረግ ያለበት ታክስ ያለ መሆኑ ተረጋግጦ ጥያቄው በቀረበ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተመላሽ ይደረግለታል ሰ በውጭ ንግድ ማበረታቻ አዋጅ ቁጥር አንቀፅ በተደነገገው መሰረት በተፋጠነ የተመላሽ ስርዓት እንዲስተናገድ የተፈቀደለት ላኪ ምርቱን ወደ ውጭ ከመላኩ በፊትም ቢሆን በሀገር ውስጥ ባከናወነው የግብዓት ግዥ ላይ ለከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ ግብይቱ ከተከናወነበት ቀን ቀጥሎ ባለው ወር ውስጥ የተመላሽ ጥያቄውን ካቀረበ በሰባት ቀናት ጊዜ ውስጥ ተመሳሽ ይደረግለታል ሸ የባለ ልዩ መብት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት በሚውል ዕቃ ላይ የከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ በዚህ መመሪያ በተመለከተው መሠረት ተመላሽ ይደረግለታል ቀ የበነ አድራጎት ድርጅት ለተረጂዎች ጥቅም በሚውል ፅቃ ወይም አገልግሎት ላይ የከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ በዚህ መመሪያ መሠረት ተመላሽ ይደረግለታል በ ለኮንዲሚኒየም ቤቶችና ለመከላከያ ፋውንዴሽን ግንባታ ጥቅም ላይ በዋለ ግብዓት ላይ የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ በዚህ መመሪያ መሠረት ተመላሽ ይደረጋል ተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በመውሰድ የካፒታል ዕቃዎች የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለማቅረብ ከአገር ውስጥ አምራቾችና አስመጪዎች የካፒታል ዕቃውን ሲገዙ የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ በዚህ መመሪያ መሠረት ተመላሽ ይደረጋል በከፊል ታክስ ለሚከፈልበት እና በከፊል ከታክስ ነጻ ለሆነ ግብይት በዋለ ዕቃ እና አገልግሎት ላይ የተከፈለ ታክስ ሀ ለታክሱ የተመዘገበ ሰው በሂሳብ ጊዜው ውስጥ ያከናወነው ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ዋጋ ለጠቅላላ ግብይት ዋጋ ሲካፈል ውጤቱ ከዘጠና በመቶ በላይ ከሆነ በግብዓቱ ላይ የተከፈለውን ታክስ ሙሉ በሙሉ በማቀናነስ ቀሪ ሂሳብ መኖሩ ሲረጋገጥ ተመላሽ ይደረጋል ለ ለታክሱ የተመዘገበ ሰው በሂሳብ ጊዜው ውስጥ ያከናወነው ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ዋጋ ለጠቅላላ የግብይቱ ዋጋ ሲካፈል ውጤቱ ከዘጠና በመቶ በታች ከሆነ በግብዓቱ ላይ የተከፈለው ታክስ ተመላሽ አይደረግሯ በሚኒስቴሩ የሚሰጥ መደበኛ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ አገልግሎት እና የሚከናወን የቁጥጥር ስርዓት በመረጃ በተደገፈ የስጋት መምረጫ መስፈርት የታክስ ከፋዩን የሰጋት ደረጃን በመለየት የሚከናወን ይሆናል ስጋትን መሰረት ያደረገ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ አገልግሎት ተግባራዊ የሚደረገው በመደበኛ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ስርዓት ይሆናል ሚኒስቴሩ መደበኛ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽን በሚመለከት የስጋት ደረጃን የሚወስን የአሰራር ማኑዋል ያወጣል ታክስ ከፋዩ የተመዘገበው በግብር ዘመኑ በመሆኑ ምክንያት መረጃ ማግኘት ባልተቻለ ጊዜ በዚህ መመሪያ አንቀጽ የተጠቀሰውን የታክስ ተመላሽ አገልግሎት የሚጠይቅ ታክስ ከፋይ ሀ ለአቅራቢው በባንክ በኩል ክፍያ የፈጸመበትን ማስረጃ ካቀረበ ወይም ለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቀንሶ የሚያስቀረው ሰው ክፍያ የፈፀመለት በባንክ በኩል መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ካቀረበ የተመላሸ ጥያቄው በአነስተኛ ኦዲት ተጣርቶ ተመላሸ ይደረጋል በዚህ መመሪያ አንቀጽ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ለግብይቱ ክፍያ የተፈፀመው በባንክ በኩል ካልሆነ ታክስ ከፋዩ የሚያቀርበው የታክስ ተመላሸ ጥያቄ በከፍተኛ ኦዲት ተጣርቶ ተመላሽ ይደረጋል በአንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ለ ሐዛቫመሥረ እናሰ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሀ በአነስተኛ የስጋት ደረጃ የሚመደብ እና ኦዲት ሳይደረግ ተመላሽ የሚደረግለት ታክስ ከፋይ የተመላሽ ጥያቄ ባቀረበ በሰባት ቀን ውስጥ ተመላሽ ይደረግለታል ለ በአነስተኛ የስጋት ደረጃ የሚመደብ እና ኦዲት ከተደረገ በኋላ ተመላሽ የሚፈፀምለት ታክስ ከፋይ የተመላሽ ጥያቄውን ባቀረበ በሰላሳ ቀን ውስጥ ተመላሽ ይደረግለታል ዐ በህግ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ በተደረገ ሰው ላይ የሚፈፀም የታክስ ተመላሽ ሥርዓት የተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መብት ያለው ሰው በአገር ውስጥ ግብይት ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ሲያከናውን ታክሱን ከፍሎ በተመላሽ እንዲስተናገድ ይደረጋል የታክስ ነጻ ባለመብቱ ለአቅራቢው ክፍያ የፈጸመው በባንክ በኩል መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ካቀረበ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በሰባት ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል የታክስ ነጻ ባለመብቱ ለአቅራቢው ክፍያ የፈጸመው በባንክ በኩል ካልሆነ በአነስተኛ ኦዲት ተጣርቶ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል ክፍል ሶስት የታክስ ተመላሽ ጥያቄ የሚያቀርብ ሰው ማሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታ የተመላሽ መጠየቂያ ቅጽ ስለመሙላት እና ማስረጃ ስለማቅረብ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ እንዲደረግለት የሚጠይቅ ማንኛውም ሰው የተመላሸ ጥያቄውን በሜያቀርብበት ጊዜ በዚህ መመሪያ የተመለከተውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ጥያቄውን የታክስ ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የተመላሽ መጠየቂያ ቅጽ ሞልቶ ማቅረብ አለበት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ እንዲደረግለት የሚጠይቅ ማንኛውም ታክስ ከፋይ የሚከተሉትን ማስረጃዎች ከተሞላው ቅጽ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት ሀ በአንድ የሂሳብ ጊዜ ውስጥ ከተከናወነው ግብይት መካከል ቢያንስ ሃያ አምስት በመቶ የሜሆነው ግብይት ዕቃን ወደ ውጭ በመላክ የተከናወነ ግብይት ከሆነ ወደ ውጭ የተላከውን ዕቃ መጠን እና ዕፅቃው ለውጭ ገበያ የተላከ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ለ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሀ መሠረት የሚቀርበው ማስረጃ የሚከተሉትን የሚጨምር ይሆናል ለማስጫኛ ወይም ለትራንስፖርት ክፍያ የተፈፀመበት ሰነድ ጉ በዐልቫ ጺሃ ዕቃው ወደ ውጭ የተላከበት የጉምሩክ ዲክላራሲዮን የባንክ ፈቃድ በ ኮፅፀጠ ሽያጩ የውጭ ምንዛሪ ያስገኘ መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ በ« ርሼፀዚ ልዉርፀ ወዶ ውጪ ለተላከው ዕቃ ግብዓት የተከፈለውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚያሳይ የድርሻ ስሌት ሰንጠረዥ ዕቃው ከተላከለት ገዢ ጋር የተደረገውን የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ውል መ በዓለም አቀፍ የትራንስፖርት አገልግሉት የተሰማራ ሰው ከሆነ በሂሳብ ጊዜው ከትራንሰፖርት አገልግሎቱ ጋር በቀጥታ ለተያያዙ ግብዓቶች የተከፈለ ታክስ መኖሩን የሚያሳይ ህጋዊ ደረሰኝ እና ማስረጃ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወርቅ የሚያቀርብ የአገር ወስጥ ወርቅ አቅራቢ በተጠቀሰው የሂሳብ ጊዜ ሳከናወነው አቅርቦት ከብሔራዊ ባንክ የተሰጠ ማስረጃ እና ወርቁን ለማቅረብ የተከፈለ የግብዓት ታክሰ ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ደረሰኝ እና ሌሎች ማስረጃ ረ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሀ እና ለ የተገለጸው ቢኖርም በተፋጠነ የተመሳሽ ስርዓት የሚስተናገድ ታክስ ከፋይ ምርቱን ወደ ውጭ ከመላኩ በፊትም ቢሆን በግብዓት ላይ የከፈለው ታክስ ተመላሽ እንዲደረግለት የተፈቀደበትን ማስረጃ እና በአገር ውስጥ የግብዓት ግዥ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለበትን ደረሰኝ ሰ በመደበኛ በመቶ የማስከፈያ ልክ የተጨማሪ እሴት ታክስ በሚከፈልባቸዉ ግብይቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚጠይቁ ታክስ ከፋዮች ከተሞላው የተመሳሽ ቅጽ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው ታክስ የተከፈለበት ግብዓት በምርት ሂደት ጥቅም ሳይ መሆኑን የሚያስረዳ የምርት ጥምርታ ማስረጃ ዘበቦ። ርቨርበክ የተሸጠ ምርት ወይም ዕቃ እና ያልተሸጠ ወይም በመጋዘን የሚገኝ የስቶክ ማረጋገጫ ማስረጃ በገዢው ተይዞ የሚከፈል ተጨማሪ እሴት ታክስን በተመለከተ በሂሳብ ጊዜው ውስጥ ከወኪሎች ጋር የተደረገውን የግብይት መጠን የሚያሳይ ማስረጃ እና ከወኪሉ የተቀበለውን ኦርጂናል ደረሰኝ ለታክስ ባለስልጣኑ ያስረከበ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ በማዕድንና ነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማራ ኩባንያን በተመለከተ ድርጅቱ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚጽፈው የታክስ ተመላሽ ተጠቃሚዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተተ መሆኑን የሚያሳይ ማሰረጃ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የተሰማራ ባለሀብትን በተመለከተ ከአንድ መቶ ሜሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡ መሆኑን የሚገልጽ ከብሔራዊ ባንክ የተሰጠ ማረጋገጫ ወይም የፕሮጀክቱ ወጪ ከአንድ መቶ ሜሊዬን የአሜሪካን ዶላር በላይ ስለመሆኑ የሚያረጋገጥ የኦዲት ሪፖርት እንዲሁም ፕሮጀክቱ ማምረት ወይም አገልግሎት መሰጠት እስኪጀምር ሶስት አመት እና ከዚያ በላይ የሚወስድበት መሆኑን የሚያሰረዳ ማስረጃ ሸ ከህንጻ ውጪ ባለ ቋሚ ዕቃ ግዢ ላይ የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ እንዲደረግ ጥያቄ የሚያቀርብ ታክስ ከፋይ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከመመዝገቡ በፊት ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ወይም በሂሳብ ጊዜው ለተገዛ ዕቃ ለተከፈለ የተጨማሪ አሴት ታክስ ደረሰኝ እና በሂሳብ ጊዜው ውስጥ ታክስ ለሚከፈልበት ግብይት የዋለ መሆኑን እና በድርጅቱ የተመዘገበ ቋሚ ዕቃ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ተ በአዲስ ህንጻ ግንባታ ወይም በማስፋፊያ ግንባታ ጊዜ የተከፈለ ተጨማሪ አሴት ታክስ ተመላሽ እንዲደረግ የሚጠይቅ ታክስ ከፋይ ለታክሱ ከተመዘገበ በኋላ ለአዲስ ህንጻ ግንባታ ወይም ማስፋፊያ በዋለ ዕቃ ወይም አገልግሎት ግዢ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለበትን ደረሰኝ ሀንጻው የተሰራው በህንጻ ተቋራጭ ከሆነ የህንጻ ተቋራር በሚያቀርበው የግብዓት ዋጋ ዝርዝር መሠረት የተከፈለውን ተጨማሪ እሴት ታክስ መጠን የሚያሳይ ደረሰኝ ሀንጻው የተጠናቀቀ እና ሰራ መጀመር የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰልጣን ከተሰጠው የመንግስት ተቋም የተሰጠ ማስረጃ የባለ ልይፀ መብት ተጠቃሚ ድርጅት የታክስ ተመላሽ እንዲደረግለት ሲጠይቅ የሚከተሉትን ማስረጃዎች አያይዞ ማቅረብ አለበት ሀ ባለ ልዩ መብቱ የገዛው ዕቃ ወይም አገልግሉት ለተቋሙ ስራ ማስፈፀሚያ ቨ ህ የዋለ መሆኑን የማረጋገጥ ኃሳፊነት በተሰጠው የተቋሙ የስራ ሃላፊ ማረጋገጫ ለ በሚመለከተው ኃላፊ ፊርማ የተረጋገጠ የዕቃ ወይም የአገልግሎት ግዢ ደረሰኝ ሐ ባለ ልዩ መብቱ ክፍያ የፈፀመው በባንክ ከሆነ ክፍያው የተፈፀመበትን የባንክ አካውንት መ ባለ ልዩ መብቱ ያቀረበው የተመሳሽ ጥያቄ ከግንባታ ጋር የተያያዘ ከሆነ የግንባታ ስራ ውሉንና ለስራ ተቋራጩ የታክስ ክፍያ የፈፀመበትን የታክስ ደረሰኝ የበጎ አድራጎት ድርጅት የታክስ ተመላሽ ሲጠይቅ የሚከተሉትን ማስረጃዎች አያይዞ ማቅረብ አለበት ሀ በበጎ አድራጎት ድርጅትና ማህበራት ኤጀንሲ የተመዘገበ ሰለመሆኑ የሚያስረዳ ማስረጃ ለ የዘመኑ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ሐ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ለተረጂዎች የዋለ ስለመሆኑ በኤጀንሲው የተረጋገጠ ማስረጃ መ በውጭ ኦዲተር የተመረመረ የሂሳብ ሪፖርት ሠ ለእርዳታ የሚውል ፕሮጀክት ለማከናወን የተከፈለ የተጨማሪ እሴት ታክስ ለማስመለስ ከሆነ ታክስ የተከፈለበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ ጥቅም ላይ የዋለ ስለመሆኑ በኤጀንሲው የተረጋገጠ ማስረጃ ረ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ የውጭ አገር ድርጅት ከሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዕውቅና ያገኘበትን ማስረጃ ለኮንዶሚንየም ቤቶች እና ለመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ግንባታ በዋለ ግብዓት ላይ የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚደረገው እንደሁኔታው የክልሉ ወይም የከተማ አስተዳደሩ ወይም የመከላከያ ሚኒስቴር የሚከተለውን ማስረጃ አሟልተው ሲቀርቡ ይሆናል ሀ የክልል መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የመከላከያ ፋውንዴሽን ለሚያስገነቧቸው የኮንዶሜኒየም ቤቶች በአገር ውስጥ በተፈፅመ የግብዓት ግዥ ላይ የከፈሉት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ እንዲደረግላቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ በእያንዳንዱ ወር ግብይት ላይ ለተከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ የተጠቃለለ የታክስ ደረሰኝ ከኦሪጅናሉ ጋር በማገናዘብ እና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አሕለባቸው ለ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሀ የተመለከተው የተመላሽ ጥያቄው በተመላሽ መጠየቂያ ቅጽ ላይ ተሞልቶ እንደሁኔታው የክልሉ እና የከተማ አስተዳደሩ የቤቶች ልማት ኤጀንሲ እንዲሁም የመከላከያ ፋውንዴሽን የበላይ ኃላፊ ወይም እነዚሁ በሜወክሏቸው የሥራ ኃላፊዎች ተፈርሞ ሙቅረብ አለበት የካፒታል ዕቃ ኪራይ አገልግሎት የሜያቀርብ የፋይናንስ ድርጅት በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት የሚቀርቡ የካፒታል እቃዎች ከአገር ውስጥ አምራቾች ወይም አስመጪዎች ሲገዙ የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚደረገው የሚከተለው ማስረጃ ተሟልቶ ሲቀርብ ነው ሀ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለበት ደረሰኝ ለ ከኢትዬጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ፈቃድ ሐ የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ሰጪው ከተከራዮች ጋር ያደረገውን ውል ክፍል አራት የተመላሽ አፈጻፀም ሥርዓት ስለታክስ ተመላሽ አፈጻፀም ከ ጄ ማንኛውም ታክስ ከፋይ የንግድ ፈቃዱ ከተሰረዘ በኋላ በሚያከናውነው ግገር ላይ ለከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመላሽ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም ለህንፃ ግንባታ በሚውል ግብዓት ላይ የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚደረገው የህንፃው ግንባታ ተጠናቆ ገቢ ማመንጨት በተጀመረበት የመጀመሪያው የሂሳብ ጊዜ ከሰበሰበው ታክስ ላይ እንዲቀናነስ ከተደረገ በኋላ ቀሪ ሂሳብ ካለ ታክስ ከፋዩ ገቢ ማመንጨት ከጀመረበት ወር ቀጥሎ ባለው ወር ውሰጥ ይሆናል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ የተደነገገው ቢኖርም ለህንፃው ግንባታ በዋለ ግብዓት ላይ የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ግንባታው ተጠናቆ ታክስ የሚከፈልበት ገቢ ማመንጨት ከመጀመሩ በፊት በተደረጉ ሌሎች ታክስ የሚከፈልባቸው ግብይቶች ላይ ከተሰበሰበ ታክስ ጋር ሊቀናነስ አይችልም ማንኛውም የተመዘገበ ታክስ ከፋይ በግብዓት ላይ የከፈለው ታክስ የካፒታሉ አካል ሆኖ ከተመዘገበ እና የእርጅና ቅናሽ ወጪ እንዲታሰብለት ከተደረገ ታክሱ ተመላሽ አይደረግም በዚህ መመሪያ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ለነ የተመለከተው ቢኖርም የልዩ መብት ተጠቃሟ የታክስ ተመላሽ ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዜ የልዩ መብት ተጠቃሚው የፊርማ ናሙና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ለታክስ ባለስልጣኑ መላክ አለበት ባለ ልዩ መብቶች ለገዙት ዕቃ ወይም አገልግሎት ክፍያ የፈፀሙት ከከፐ ወይም ከአከክ አካውንት ላይ ከሆነ ታክሱ ተመላሽ የሚደረገው ገንዘቡ ወጪ በተደረገበት አካውንት መልሶ በማስገባት ነው ማንኛውም ባለ ልዩ መብት በዕቃ ወይም በአገልግሎት ግዢ ላይ የከፈለው ታክስ ተመላሽ የሚደረገው የተመላሽ ጥያቄውን ባቀረበ በአንድ ወር ጊዜ ውሰጥ ሲሆን በማንኛውም ሁኔታ ለግብይቱ ክፍያ ከተፈፀመ ከአንድ አመት በኋላ የሚቀርብ የታክስ ተመላሽ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም ዐፀጊጊ ጊ የልዩ ባለመብቶች በሚከፍሉት የህንፃ ኪራይ እና የቴሌኮሚኑኬሽን አገልግሎት ክፍያ ላይ ታክሱን መክፈል የሌለባቸው ስለመሆኑ በዚህ መመሪያ የተደነገገው ቢኖርም የልዩ መብት ተጠቃሚዎች በሚከፍሌት የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ክፍያ እና የህንፃ ኪራይ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል የለባቸውም የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ቢኖርም የልዩ መብት ተጠቃሚው የህንፃ ኪራይ በሚከፍልበት ጊዜ ከታክስ ባለሰልጣኑ የተሰጠውን የታክስ ነጻ መብት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኮፒ በማድረግ እና በማህተም በማረጋገጥ ለአከራዩ መስጠት አለበት ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች የሚኒስቴሩ ኃላፊነት የተፋጠነ ቀረጥ ተመላሽ ስርዓት ተጠቃሚዎች ያቀረቡትን ሪፖርት በማጠናቀር በየስድስት ወሩ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ለገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት ያቀርባል ስለተሻሩ መመሪያዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መመሪያዎች በዚህ መመሪያ ተሸረዋል ሀ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ አፈጻፀም መመሪያ ቁጥር ለ ቅይጥ አቅርቦት እንዲሁም የካፒታል ግንባታ ሲከናወን የተከፈለን የተጨማሪ እሴት ታክስ ስለማቀናነስ የወጣ መመሪያ ቁጥር ሐ ለሰብዓዊ እርዳታ ስለሚውሉ እቃዎች እና አገልግሎቶች የታክስ ነጻ መብት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር መ ለባለ ልዩ መብት ድርጅቶች ስራ ማስፈፀሚያ እንዲውል በሜከናወን የዕቃ እና የአገልግሎት ግዢ ላይ የተከፈለ የተጨማሪ አሴት ታክስ ተመላሽ የሚደረግበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር ይሀን መመሪያ የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ ወይም አሰራር በመመሪያው በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት ተጀምረው ውሳኔ ያሳገኙ ጉዳዮች በነባሩ መመሪያና አሰራር መሠረት ውሳኔ ያገኛሉ መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ ይህ መመሪያ በገቢዎች ሚኒስቴር ሜኒስትር ተፈርሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል መ ዓም አዳነች አበቤ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር።