Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ስትል ጠየቀችው ቁርጥ አድርጋ አልመጣም አላሰችኝም እርግጥ ሚስተር ፓተርሰንን እየተመላለሰች ለማየት ከምትለያቸው በስተቀር አፍ ለአፍ ገጥመው እንዳወሩ ነበር የዋሉት ዣዛሬም እንደትናንቱ ስናወራ ካደርን ነገ መነሳታችንንም እንች ስትል ሂላሪ አረጋጋቻት። ብርቅርቅታ ማርጋሬት የሂላሪን እጅ በፍቅር ጭብጥ አድርጋ ያዘችና ለ ባሏ ስለ ሄነሪ ያነሳችብሽ ነገር ነበር ስትል ጠየቀቻት ብርቅርቅታ በመብቃቴ በጣም ዕድለኛ ነኝ ከገመትኩት በላይ ነው ደስታ የተሰማኝ አለችና ማረጋሬትን አቅፋ ብዚህም ደስታዬ ወቅት ከእኔ ባለመለየትሽ ደስታዬን እጥፍ እጥፍ ያደርገዋል አለች አሌክሳንድራ ከዚያም ከማርጋሬት መኝታ ክፍል ገብተው ባለፉት ሁለት ቀናት ከአህቶቿ ጋር ስላሳለፈችው ሕይወት አንድ በአድ ስታጫውታት ቆየች ቃ ኺ ብጣም ነው ደስ ያለኝ እማማ ሁለቱንም እህቾቼን ለማግኘት ብርቅርቅታ ምዕራፍ ሰላሳ ሁለት በኒውዮርክ ውስጥ ያሳለምኞት የመጨረሻ ምሽት ድሎት ያልተጓደለውም ቢሆን በሌላ መልኩ ደግሞ ሐዘንና ትካዜ ማስከተሉ አልቀረም እራት የበሉት በኮት ባስከ ሆቴል ሲሆን ሄነሪና አሌክሳንድራ ሕፃናቱንም ይዘዋቸው መጥተው ነበረ ማርጋሬት ከፄነሪ ጋር ማምሸቱ ደስ ባይላትም በአሌክሳንድራ ጉጐትጓችነት ተገኝታለች ሂላሪ ደግሞ ቀደም ሲል ከሌላ እንግዳ ጋር እንደምትመጣ ለእህቷ ገልፃላታለች ስለ እንግዳው ማንነት ግን ሂላሪ አልነገረቻትም አሌክሳንድራም ለማወቅ ብትፈልግም ደፍራ አልጠየቀቻትም ከሂላሪ ጋር የመጣው ሰው ጆን ቻፕማን መሆኑን ስታይ ግን አሌክሳንድራ ውስጥ ውስጡን ፈንጥዛ ነበረ።
ብርቅርቅታ ቀኑን በስልክ ትገልጪልኛለሽሦ ቆይ እስቲ አለችና ለጥቂት ጊዜ ዝም አለች በአእምሮዋ የምታሰላው ነገር ነበረ ቀጠል አድርጋም ከመስከረም አንድ ቀን ጀምሮ የአንድ ሳምንት ዕረፍት ስለሚኖረኝ ለምን በዚያን ጊዜ አናደርገውም አለችው ጥሩ። አለ እንዳቀረቀረ እንዳልከው ለእኔም ቢሆን ለማመን ከብዶኝ ነበረ ታሪኩ ቢለማ ስትል ስላደረብህ ጥርጣሬ ግን እኛ ሆነ ብለን ካላወራን ሌላ አንድም ሰው ሊያውቀው አይችልም እኔና እህቶቼ የምንገናኘው በምስጢር ነው ልጆቻችንም ቢሆኑ ወደ ኒውዮርክ የሚሄዱት ለሽርሽር ነው የመሰላቸው አኔም ወደ ኮንክቲከት ስፄድ ከአያታቸው ጋር ኒውዮርክ ይጠብቁኛል ለምን ሕፃናቱን ይዘሻቸው ለመሄድ እንደ ፈለግሽ አልገባኝም ምን ያደርጋሉ የእነርሱ ከአጠገቤ አለመለየት ብርታት ይለጠኛል ብላ ትንሽ አሰብ አደረገችና እሺ አትለኝም እንጂ አንተማ ፈቃድህ ሆኖ አብረን ብንፄድ ደስታውን አልችለውም ነበረ ለሰላሳ ዓመት የተለያየቷቸውን እህቶቼን ለመጀመሪያ ጊዜ መገናኘት ማለት ቀላል ነገር አይደለም ኦህ ድሮ በጣም አወዳቸው ነበረ ስትል ያልተጠበቀ ጥያቄ አቀረበችለት አብሬሽ ልፄድ ቀርቶ አንቺም አንድትፄሄፄጂ አልፈልግም አሁንም ቢሆን አእንዳትሄጂ አስጠነቅቅሻለሁ እህቶቼ አህቶቹ የምትያቸው ሴቶች እንዳንቺ የተከበሩ እመቤቶች አይደሉም ስለዚህ ልመና ጭምር አትሂጂ ነው የምልሽ ሯጄ ብርቅርቅ ታ ጅ ሜጭኗሟሂ ከዚህ በላይ አሌክሳንድሪ ልትሰማመጠው አልፈስገችም ወደ ኒውዮርክ በመሄዲ ቆርጣለች እነኛንም እህቶቿን አግኝታ ለማየት ብቻ ሳይሆን ልትነካቸው ልታቅፋቸው ልታፈቅራቸውም ትችል ይሆናል ዝናስሁ ሄነሪ በመፄዴ ቆርጫለሁ ይህ ደግሞ በትዳራችን ላይ ችግር ያስከትላል ብዬ አልገምትም አለችና ወደ ተቀመጠበት ሄደት በማሰት አንገቱን ልታቅፈው ሞከረች ቴ አላስቀረባትም ነበረ በሩቁ እጆቿን በአጁ ገፈተረና ከዛሬ ጀምሮ የእኔና ያንቺ ነገር አከተመለት አላት ብጣም ነው የማዝነው ፄነሪ የእኔ እህቶቼን ማግኘት ስዚህ የሚያደርሰን ከሆነ በድጋሚ ሐዘኔታዬን እገልፅልፃሃለሁ እኔ ግን ነገ ወደ ፓሪስ ከተመለስኩ በኋላ ተነገ ወዲያ ወደ ኒውዮርክ በራሪ ነች አለችው ከርሱ ጋር መቆራረጧ እየታያት ለቅሶ ጀምራ በመነፋረቅ ላይ ለነበረችው አሌክሳንድራ ሌላ ተጨማሪ ቃል ሳይናገራት ከተቀመጠበት ተነስቶ በሩን ከፍቶ ወጣ ብርቅርቅታ ምዕራፍ ፃያ ስድስት የመስከረም አንዱ ቀጠሮ ከመድረሱ ከሶስት ቀናት በፊት ነበረ ቻፕማን ሂላሪን ለማነጋገር ወደ ቢሮዋ የፄደው አንደ በፊቱም በልዩ ዘዴ ያገኘውን መታወቂያ ደብተር ስዘብተኞች በማሳየት ያለ ችግር ወደ ሕንፃው ገባ። » ከእነኛ ሁለት ህፃናት መካከል አንዷ ለዚህ ማዕረግ ትበቃለች ብሎ መገመቱ አዳጋች ሆነባት ሚጋን ናት ግሩም ልጅ ወጥቷታል አሌክሳንድራም ብትሆን በእመቤትነቷ ሳትኩራራ በጣም ሩህሩህ የደስ ደስ ያላት ሴት ናት ብህፃንነቷም ጊዜ እንደዚሁ ነበረች ስትል ድምዷን ዝቅ በማድረግ ተናገረችና ሳይታሰብ ፊቷን በሁለት እጆቿ ሸፍና አቀረቀረች ራሷንም ጅ ኤኤ ርኤ ብርቅርቅታ እያወዛወዘች እነኛን ከሲኦል የከፋ አስር የመከራ ዓመታት ለመግፋት የቻልኩት እህቶቼን አገኛቸዋለሁ በማ ላው ተሰፋ በመፅናናቴ ነበረ ከአክስቴም አስር ሺህ ብር የሰረቅሁት ወደ ኒውዮርክ መጥቼ እህቶቼን አሳድግበታለሁ ብዬ በማቀዴ ነበረ አለችና እጆቿን ከፊቷ ላይ ሳታነላ ለረጅም ጊዜ ከት ከት ብላ ሳቀች ቻፕማን ግን የሚያየው በጣቶቿ መሐል እየተንከባሰሉ ከጠረጴዛው ላይ የሚንጠባጠቡትን የዕንባ ዘለላዎች ነበረ የሚተናነቃትን ሲቃ እንደ ምንም እየዋጠች ን ግን ያ ሰው ያ አረመኔ ሰው የት እንደደረሱ አላውቅም አለኝ እኔም አፈላልጌ አፈላልጌ አጣኋቸው አለችና ማንባት ባላቋረጡት ዓይኖቿ ቻፕማንን ያለ ሀፍረት አየችው ታዲያ ሚስተር ቻፕማገ። ሆኖም መልካም ጉዞ አመኝልሻለሁ የመጨረሻዎቹ ቃላት የምፀት ጭምርም ነበሩ የምቆየው ግፋ ቢል እስከ መስከረም እስር ቀን ብቻ ነው የማርፈውም በፒየር ሆቴል ስለሆነ ስልክ ልትደውልልኝ ትችላለህ አኔም ደውዬ አነጋግርሀለሁ የሚያስፈልግ አይመሰለኝም ብትደውይም ስራ ስለሚበዛብኝ እታገሺኝም አላትና ወደ ኋላው ዞር ብሎ ከቤት በመውጣት ጀርባውን ሰጥቷት ከበረንዳው ላይ ቆመ አሌክሳንራም ወደሚጠብቃት መኪና ለመሄድ ደረጃውን መውረድ ስትጀምር ለመጨረሻ ጊዜ የታያት ያው የሄነሪ ጀርባ ነበረ መኪናው ተንቀሳቅሶ ከግቢው በመውጣት ላይ እንዳለ ግን የፄነሪ ዓይኖች ከፊቱ በተንጣለለው ባህር ላይ ተሰክተው በእንባ ይዋኙ ነበረ ሆኖም ይህን አሌክሳንድራ አላየችውም ለይምሰል ይኮሳተርባት እንጂ ፄነሪ ከልቡ ነበረ የሚያፈቅራት እሁን ግን ለዘለዓለም ብርቅርቅታ እንዳጣት ያህል ሆዱን ባር ባር አለው ለብዙ ዓመታት ተሳስበው እንዳልኖሩ የጠየቃትን ሁሉ በደስታ እንዳልፈፀመችለት ሁሉ በጥቂት ቀናት ውስጥ ያ የሞቀ ትዳር ያ የፍቅር ቤት የንትርክ ቤት ሆነ አሌክሳንድራ የኮምት ዴቦርን ልጅ አልነበረችም ሌላው ቀርቶ ማርጋሬት እንኳንስ እናቷ ልትሆን ቀርቶ የስጋ ዝምድናም አልነበራቸውም አሌክሳንድራ ክተለየቻቸው ሰላሳ ዓመት የሆነውን የረሳቻቸውን እሀቶቿን ለማየት ከሄነሪ ትፅዛዝ ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሷ ወሰነች ያ በነ አክሌልና ማሪ ሳቅና ጨዋታ በአሌክሳንድራ ውበትና ደግነት ሕይወት የነበረው ቤት ከበረዶ ቀዘቀዘ በአሌክሳንድራና በሄነሪ ትዳር ላይ ጥቁር ጥላ አንዣበበበት በአውሮፕላን ውስጥ የተያዘላቸው መቀመጫ እንደኛ ማዕረግ ነበረ በዚያ ክፍል ውስጥ ሌላ ተሳፋሪ ባለመኖሩ አሌክሳንድራና ማርጋሬት እንደልብ ለመወያየት ችለው ነበረ ስለ ሄነሪም ሁኔታ አንስተው ብዙ ተነጋገሩ በመጨረሻም ላይ አሌክሳንድራ ቁርጥ አድርጐ ባይነግረኝም የሁለታችን ነገር አክትሟል ስመለስ መግቢያ ቤት እንደማላገኝና የፍርድ ቤት መጥሪያ እንደሚጠብቀኝ አርግጠኛ ነች አሰቻት ለእናቷ ለምን እኔ እንዳስቸገርኩሽና ወደ ኒውዮርክም አብረሺኝ እንድትሄጂ እንዳደረግሁ አስመስለሽ ኣትነግሪውም ነበረ አለች ማርጋሬት ሞክሬ ነበረ ዌን የምፄደው ለሌላ ጉዳይ እንደሆነ ሊነቃብኝ ቻለ ውጥር አድርጎ ስለያዘኝም እውነቱን አፍረጥርጨ ነገርኩት አሌክሳንድራ ከዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ብዙ ነገሮችን አመዛዝና ነው በዚሁ ሳቢያ ከባሏ ልትለያይ ትችላለች ያም ሆኖ ትክክለኛውን ምርጫ ማድረጓ ይሰማታል ከህሊና ፀፀት አሁን ነፃ ናት ትልቅ ስህተት ነው የፈፀምሽው አለቻት እናቷ አፍ አውጥታ ለአሌክሳንድራ ባትነግራትም ከእንግዲህ ትዳራቸው ስለመፍረሱ እርግጠኛ ነበረች ልጆቹንም ይቀማታል የሚል ስጋት እድሮባታል ሁለቱም ቢሆኑ በዚህ አርእስት ላይ ቀጥለው ለመወያየት አልፈለትም ማርጋሬት ከህፃናቱ ጋር መጫወቱን ስትመርጥ አሌክሳንድራ ግን ወደ ሐሳቡ ዓለም አመራች ስለወላጆቿ ስለ እህቶቿ ብዙ ነገሮች በአአምርዋ አመላለሰች ሂሊን ሚጋንን ለሰላሳ ዓመታት የተለዩዋትን እህቶቿን ልታያቸው ነው የጋደፊቱ አየታለባት ከውስጥ የተለማት ደስታ ፊቷን እንደ አበባ አፈካው ። ዛሬ ልክ እኔን ነው የምትመስይው ኣለች ማርጋሬትም ብትሆን በአሌክሳንድራ ልዩ ውበት ከመደሰቷም የጥንቱን ትዝታ ቀስቅሶባት ሳብ አድርጋ እንደ ህፃን ልጅ ከደረቷ አስጠጋቻችና አክሲ እወድሻለሁ አለቻት አሌክሳንድራም በተመሳሳዩ ነበር ለአናቷ ያላትን ፍቅር የገለፀቸው ምሳ ከበሉ በኋላ በልዩ ልዩ ሱቆች እየተዘዋወሩ አንዳንድ የመታሰቢያ ዕቃዎችና ለህፃናቱም አሻንጉሊቶች ሲገዙ ቆዩ አስር ለዓት ከመድረሱም በፊት ወደ ሆቴላቸው ተመለሱ አሌክሳንድራም ለኮኔክቲከቱ ጉዞዋ መዘገጃጀት ጀመረች ለመንገድ የሚያስፈልጋት አንድ ሻንጣ ብቻ ነበር ቀጠሮ የያዘችው አስር ሰዓት እንደ ሞላም እናቷንና ልጆቿን ተራ በተራ ከሳመች በኋላ ማታ ላይ ስልክ እንደምትደውልላቸው ቃል ገባች ከዚያም ወደ ኮኔክቲከት ሊወስዳት ከሆቴሉ ፊት ለፊት ይጠብቃት ከነበረው የፓተርሰን ካዲላክ መኪና ውስጥ ገባች ያን ጊዜ ብቻ ነው አሌክሳንድራ ፍርሐት ፍርዛት ያላት ሰላሳ ዓመት ያህል ጊዜ ወደ ኋላ ተጉዞ ከአህቶቿ ጋር መገና ኘት ቀላል ነገር አልነበረም በተጨማሪም የዛሬው ግንኙነታቸው በወደፊት ሕይወታቸው ላይ ለውጥ ማስከተሉም አይቀርም ብርቅርቅታ ምዕራፍ ፃያ ስምንት በኮኔክቲከት ግዛት ከባህር ዳርቻ ይገኝ ከነበረው የፓተርሰን ቤት ለመድረስ ከሁለት ሰዓት በላይ ይፈጅ ነበረ አሌክሳንድራ ከአውቶሞቢሉ የቷላ መቀመጫ ላይ እንደልቧ ተዝናንታ ብትቀመጥም በሌላ በኩል ከሐሳብ ባህር ውስጥ ተዘፍቃለች ዓይኖቿን በመስታወቱ ውስጥ አስርጋ ውጪ ውጪውን እያየች በቅድሚያ ስለ እናቷ ስለ ማርጋሬት ታሰላስል ጀመረ አንድም የእናትነት ርህራፄ ሳይጐድልባት አሳድጋ ለወግ ለማዕረግ አብቅታታለች ለሰላሳ ዓመታት ሙሉ ገደብ የለሽ ፍቅሯን እንዳሳየቻት ነበረ ለማርጋሬትም ቢሆን ያለቻት አለኝታ እርሷ ብቻ ነበረች ማርጋሬት ግን አሁን ፈርታለች አሌክሳንድራ አህቶቿን ካገኘች ትቀየርብኝ ይሆናል ስትል ሰግታለች። ስትል ቻፕማንን ጠየቀችው አጅግ ቢዘገይም እህትማማቾቹን መልሶ ለማገናኘ ት ስላደረገው ጥረት ሚስተር ፓተርሰንን ልታመሰግነው ፈልጋ ነበረ ቁ ላይ በሚገኘው መኝታ ቤታቸው ፅሪረፍት በማድረግ ላይ ናቸው አላት ቻፕማን ሚስተር ፓተርሰንን የሚረዱ ሁሰት ቋሚ አስታማሚዎች ተቀጥረው ነበረ እንደ እውነቱ ለዚህን ያህል ጊዜ በሕይወት መቆየቱ የተአምር ነው ለማሰት ይቻላል የዛሬውን ዕለት ለመጠበቅ ሲል ነፍሱን ታግሎ ያቆያት እንጂ እንደ አያያዙስ ከሆነ ገና ዱሮ አፈር ትቢያ በሆነ ነበረ አሁኑኑ ልታያቸው ትፈልጊያለሽ አላት ቻፕማን አዎኙ አለችና ቀና ስትል ዓይን ሰዓይን ተጋጩ ፈገገሳት ፈገገችለት የቻፕማን አለባበስ በመካከለኛው ዕድሜ እንዳለ ሰው ተጠንቅቆ ሳይሆን ካኪ ሱሪና ከደረቱ የተከፈተ ሰማያዊ ሸሚዝ ነበረ የለበሰው ገፅታው ለምሁርነቱ ምስክር ቢሆንም መልኩና ሁኔታው ግን የጐረምሳ ነበረ የሚመስሰው አሌክሳንድራ ከፊት ሰፊቷ የቆመውን የደስ ደስ ያለውን ቻፕማንንና ኮስታራውን ባሏን ሄነሪን በሐሳቧ አወዳደረቻቸው የሄነሪ ፊት አለመፈታት ትእዛዛዊ አነጋገሩ በኩራት የተጠነነው አረማመዱ አመለካከቱ ሁለንተናው ወዲያውኑ ነበረ በሰው ላይ የዝቅተኝነት ስሜት የሚያሳድረው ቻፕማን ግን በተቃራኒው ፍልቅልቅና ቦርቧራ የልብ ልብ የሚሰጥ ዓይነት ሰው ነበረ ብርቅርቅ ታ ዴዴ ሞፎዱቨዱዱዱ ወደ ደረጃው ሲቃረቡ ሲሉ ከበስተላይ የኮቴ ድምፅ ስለሰሙ ቆም አሉ። አሁን ግን ከፊት ለፊቷ የቆመችውን ሴት እያየች ቁርጥ እኔን አይደለም አንዴ የምትመስይውኑ አለቻት ታላቅ እህቷን አሌክሳንድራ በእንባዋ ውስጥ ፈገግ አለችና እንደገና ስባ በደረቷ አቅፋት ቁርጥ አንቺን እንዳልመስል በአንድ ነገር እንለያያለን በአለባበስ አለችና እነ ቻፕማንን ጭምር አሳቀቻቸው አሌክሳንድራ እውነቷን ነበረ የእርሷ አለባበስና ጌጣጌጦች እንደ አውሮፓውያን መሳፍንት ሚስቶች ሁሉ እጅግ ያማረና በጥንቃቄ የተመረጠ ነበረ ሚጋን ግን የምታዘወትረውን ጂንስ ሱሪና አጅጌ ጉርድ ሸሚዝ ብቻ ነበረ የለበሰችው የተጫማችውም እንደ አዘቦቱ ከጉልበቷ የሚደርስ ረጅም ቦት ጫማ ነበረ ከእህቷ ደረት ላይ ቀና አለችና እንዳንቺ ያለች ቆንጆ ሴት አይቼ አላውቅም አለች እየሳቀች ሌሎቹም ተሳላሳቁ ከዚያም አሌክሳንድራ አንድ እጂን ይዛ ሚስተር ፓተርሰን ወደ ተቀመጠበት ወንበር ልታስተዋውቃቸው ወሰደቻት ደህና ነዎት ሚስተር ፓተርሰን። አለና ፓተርሰን ፈገግ እንደማለት ብሎ እህትማማቾቹን ተራ በተራ አያቸው ሁለቱም የመጨነቅ ስሜት አይታይባቸውም የጥላቻም አስተያየት አይነበብባቸውም ፓተርሰን ለሁለቱም የመረጠሳቸው የጉዲፈቻ አባቶች በእንክብካቤ ሊያሳድጓቸው የሚችሉ ስዎች መሆናቸውን ካረጋገጠ በኋላ ነበረ ምስኪኗን ሂላሪ ግን የሚያስጠጋት ጠፋ ቻፕማን ከቢሮዋ ድረስ ፄዶ እንዳነጋገራትና ምን እንደመለሰችለት ለፓተርሰን አጫውቶት ነበረ ምናልባት ብትመጣም ፓተርሰንን በነገር ግርፊያ እንደምትሸነቁጠወ አያጠራጥርም ፓተርስንም ይህንን ፈርቷል ግን ከምትቀር ብትመጣና ብትሰድበው ይመርጣል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊያያት ይቅርታም ሊጠይቃት ምኛቱ ነው እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ ጠበቋት ግን ሂላሪ አልመጣችም ጨክና መቅረቷ ነው ሲሉ ሁሉም ውስጥ ውስጡን መታመስ ከጀመሩ ቆይተዋል ላይ ላዩን ግን ለማስመሰል ያህል አንዳንድ ነገሮችን እያነሱ መጫወታቸው አልቀረም ፓተርሰን ስለ አለፈው የወላጆቻቸው ታሪክ የሚያስታውሰውን ያህል ሊያወጋቸው ሞክሯል ሚጋንና አሌክሳንድራ ስለ ግል ሕይወታቸው አልፎ አልፎ መነጋገራቸው ኣልቀረም አሌክሳንድራ የሁለቱን ልጆቿን የሄነሪን እናቴ የምትላትን የማርጋሬትንና በበጋ በክረምት እየቀያየረች የምትኖርባቸው ሕንፃ ቤቶች ፎቶግራፎች አምጥታ ስለነበረ ተራ በተራ አሳየቻቸው ሚጋንም በፊናዋ ያሳደጓትን የሬቤካንና የዴቪድን የምትለራበትን የኬንታኪውን ሆስፒታል ፎቶግራፍ በመያዚ ከአሌክሳንድራ ፎቶግራፎች ጉን ደረደረቻቸው የሁለቱን ሁኔታ ላጤነው ለሰላሳ ዓመት እንዳልተለያዩ ያህል አሁን በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በማስካካት ውስጠ ሚስጥራቸውን ለመገላለፅ ዕቅድ አንዳላቸው ነበረ የሚመስለው የሚጋንን አትኩሮት በተለይ የሳበው የሄነሪ ፎቶግራፍ ነበረ ከዶሮኙ መኖሪያ ቤታቸው ሕንፃ ፊት ለፊት ለተነሳው ፎቶግራፍ በእርግጥ የነገስታት ዘር ለመሆኑ ይመሰክራል ከሕንፃው መ መ ብርቅርቅታ ውበትና ግዝፈት ሌላ የሄነሪ ግርማ ሞገስ ልዩና የሚያርድ ነበረ ከእንደዚህ ካለ ሰው ጋር አህቷ መጋባቷና እነኛን የመሳሰሉ ልጆች መውለዷ ሚጋንን እጅግ አድርጎ ነው ያስደነቃት እስቲ የአንቺንና የእኔን ሕይወት አወዳድሪው። ያም የቀድሞ ጥላቻዋ ታድሶባት በነገር ልትገርፈው ስትል ዓይኖቿ ከጐኑ ከተቀመጠችው ባለወርቃማ ፀጉር ወጣት ሴት ላይ አረፉ ከርሷም ላይ ዓይኖቿን ነቅላ ሌላኛይቱን ለመፈለግ ዙሪያውን ማተረች ከበስተጐን ካለ ክፍል በር ላይ ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር እንደተያዩ ባለችበት ፈዛ ቀረች አሌክሳንድራ ግን ነፍስ የዘራችው በዚያን ጊዜ ነበረ ብርቅርቅታ አሁን በምትታያት ረጅምና ሙሉ ሴት ምትክ ለአሌክሳንድራ በዓይነ ሕሊናዋ ትመላለሰ የነበረችው የዱሮዋ ሂላሪ ያቺ ከአጠገቧ የማትለያት እንደ እናት የምትንሰፈሰፍላት ፀጉረ ጥቁር ልጅ ነበረች አሌክሳንድራም የለቅዕ ሳግ ጉሮሮዋን እየተናነቃት ልትቆጣጠረው ያልቻለችው እንባዋ የዓይኗን ግድብ ጥሶ በጉንጮቿ ላይ እየወረደ ሚ ሂሊ ሂሊ በማለት ላይ እንዳለች ሂላሪም ሳይታወቃት ከእህቷ አንገት ላይ ተጠምጥማ ፇክሊሲ ክሲ የእኔ ትንጂ አክሲ ስትል እንባዋን ለቀቀችው ፓተርሰን እህቶቿን በጉልበት ነጥቆ ካለያያት ወዲህ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ስታቅፋት ነው የዚያን ጊዜዋ አሌክሳንድራ ያቺ ፎልፏላና ስትስቅ ስትናገር እናቷን ሶላንጅን የምትመስለው አሌክሳንድራ እወድሻለሁ አክሲ እወድሻለሁ የሚሉትን ቃላት ብቻ እየደጋገመች ሁለቱም እንደተቃቀፉ ለረጅም ጊዜ ተላቀሱ ከዚያች ዓይኖቿ በአሌክሳንድራ ትከሻ ላይ አልፈው በሚጋን ላይ ተንገዋለሉ ሚጋንም እንደ እህቶቿ አስታውሳ የምታለቅስበት ያለፈ ትዝታ ባይኖራትም ሁኔታቸው አንጀቷን ስላላወሰው እርሷም አብራቸው ማንባቱን ተያይዛው ነበረፊ ሂላሪ አንዱን እጂን ከአሌክሳንድራ ላይ እንስታ ወደ ሚጋን ዘረጋች ሜጋንም ከመቀመጫዋ ተነስታ ከእህቶቿ ጋር ተቃቀፈች ሚጊ ለመጨረሻ ጊዜ ካየሁሽ እምብዛም አልተቀየርሺብኝም ስትል ሂላሪ ሶስቱም እህትማማቾች ማልቀሳቸውን ትተው ተሳሳቁ እህቶቿን በግራና በቀኝ እጂ ይዛ ወደ ፓተርሰን ቀረብ አለችና አንተን ላለማየት ስል ብቻ ላልመጣ ወስኝጌ ነበረ ይገባሃል አይደል አለችው ሂላሪ ድምዷን ከፍ አድርጋ ፓተርለን ቀና ብሎ ሊያያት አልደፈረም እንዳጐነበሰ ራሱን ዝቅ ብድግ በማድረግ ብቻ የገባው ለመሆኑ አሳየ እንዴት እንደምጠላህ ታውቀው የለም አለችው አሁንም ደገመችና ለምን ሂሊ። ቁ ፓተርስን በረጅሙ ተነፈለ በጣም ተደካክሞም ስለነበረ ዓይኖቹን ከደነ ቻፕማንና አስታማሚዋ ወደ መኝታ ቤቱ ሊወስዱት ደጋግፈው እስነሉት ደረጃውንም ከወጣ በኋላ ዞር ብሎ ቁልቁል እየተመሰከተ ቁርጥ ቁርጥ በሚል ድምፅ ይህ ቤት ከእንግዲህ የእናንተ የእህትማማቾቹ ቤት ብርቅርቅታኾ ጅጅ ዴ ዴጅዴጅቪጅቪጅቪጅች ይሆናል ልጆቻችሁንባሎቻችሁን ይዛችሁ መጥታችሁ መለባለቢያችሁ ይህ የእኔ የመጨረሻ ስጦታዬ የሆነው ቤት እንደሚሆን ተስፋ አለኝ ሊል ሚጋንና አሌክሳንደራ በእንድነት እናመለግናለጉኙ ሲሉ መሰሱለት ሂላሪ ግን ከአንገቷ ጐንበስ በማለት ብቻ ምስጋናዋን በምልክት ገለፀች ሐኪሟ ሜጋን ለሚስተር ፓተርሰን የሚያስፈልገው የሕክምና እርዳታ ቢኖር ሰመከታተል ከእህቶቿ አስፈቅዳ ተለየቻቸው ሂሳሪና አሌክሳንድራ እጅ ሰእጅ ተያይዘው ወደ አሌክሳንድራ መኝታ ክፍል አመሩ ከከፍሉም ውስጥ እንደገቡ ነበረ ሁለቱም ሰመጨረሻ ጊዜ አብረው የኖሩባትን ያቺ አክስታቸው ኢሊን ከልላላቸው የነበረችውን ትንሽ መኝታ ቤት የታወሰቻቸው ሂላሪና አሌክሳንድራ በአንድ አልጋ ላይ ተቃቅፈው ሊተኙ ትንጂ ሚጋን እንዳትወድቅ ከበስተግርግዳው በኩል ተዘርግታላት በነበረች አንካሳ የአራስ አልጋ ላይ ነበረ የምትተኛ ው ኢሲንም ሕፃናቱን እንዳትመታቸው ሂላሪ ታደርገው የነበረው ጥንቃቄ ትዝ ብሏት ሌላ ሐሳብ መጣባትና እስከ አሁን ሳልጠይቅሽቹ ሰመሆኑ ልጆችሽ ማንን ነው የሚመስሉት ስትል ከአሌክሳንድራ ጐን አልጋው ላይ ተቀመጠችና ጠየቀቻትቋ አሌክሳንድራ እህቷ ባቀረበችላት ጥያቄ ፈገግ አለችና ትልቋ ማሪ ቁርጥ አንቺን ነው የምትመሰለው አቋቋሟ ፀጉሯ ሁሉ የአንቺ ትክክል ግልባጭ ነው አከሴል ደግሞ በሕፃንነቴ የተነሳሁትን ፎቶግራፍ ትመስላለች በሁለቱ መካከል የወለድኩት ወንድ ልጅ ግን በአራስነቱ ሞተብች አሰች በዚሁ ትዝታዋ ስውነቷ ስቅጥጥ ብሎ ሂላሪ ከብዙ ዓመታት በፊት ያስወረደችው ፅንስ በዚያን ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ ታወሳት ከዚያን ወዲህ ከሕፃናት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳይኖራት ትጠነቀቅ ነበረ። ስትል የፊት መታመስ እየተነበባት ተናገረች አዎኽ ለማንም እንደማይቀር ሁሉኑ ብላ ሚጋን መለሰችላት ሂላሪ ስለ ፓተርሰን የምታስታውሰውን ሁሉ ለእህቶቿ በማጫወት ላይ እንደነበረች ነው ቻፕማን ሊስናበታቸው በሩን ከፍቶ ከደፉ ላይ የቆመው ከእንግዲህ እህትማማቾቹ ብቻቸውን ሆነው የልባቸውን መጨዋወት አሰባቸው ቻፕማን ግዳጁን በሚገባ ተወጥቷል ዳግመኛ እንደምንገናኝ ተስፋ አለኝ ስትል ቅድሚያ ምኞቷን የገለፀችው አሌከሳንድራ ናት ቻፕማን ግን ተስፋ እንደቆረጠ ሰው ራሉን በመደጋገም አወዛወዘ ከፊቱም ላይ የሚነበበው የቅሬታ ፈገግታ ለወደፊቱ እንደ እናንተ የተጠፋፋ ሰው እን እስካልጠየቃችሁኝ የምንገናኝበት ምክንያት የሚኖር አይሠለለኝም ይህንን የመስለ አጋጣሚ ደግሞ ተደጋግሞ የሚከሰት አይደለም አለና ሶስቱንም ተራ በተራ ከተመለከተ በኋላ ከእናንተ በመሰየቴ የሚለማኝ ሐዘን ከባድ ነው ሲል ተናገረ በእርግጥም ላለፉት ጥቂት ወራት ቀን ከሌሊት በውኑም በእንቅልፉም የሚያስበው ስሰ እነሂሁ ሶስት እህትማማቾች ነበረ ከፊል ሕይወቱም አድርጎ ሊቆጥራቸው በቅቷል በተለይም አሁን ጭንቀት የሆነበት ከሂላሪ የመለየቱ ጉዳይ ነው አንጀቱ ተላውሶላታል መንፈሱ ቆስሎላታል በልቡም አልቅሶላታል ምን እንደሚያደርግላት ግራ ገብቶታል ለሁላችሁም መልካም ዕድል እመኝላችኋለሁ» ብሎ በደመ ነፍሱ ከተናገረ በኋላ ሊወጣ ሲል ሚጋገ ፈጠን ብላ በመራመድ ደርሳበት ብጣም ነው የማመሰግንህ ሚስተር ቻፕማኙ አለችና ጉንጩን ሳም አደረገችው እንደታላቅ ወንድም ያህል ነበረ የወደደችው። ሂሳሪ አለማወቋ እንጂ ቤቷን እንኳን ለሰቻፕማን ቀደም ሲል በውጪውም ቢሆን አይቶታል ከመኪናው አድርስውት በመመለስ ሳይ እንዳሉ ሂሳሪ ከደስታዋ ብዛት የተነሳ እንባዋ እየተናነቃት ነበረ በአንድ ቀን ያውም በአንድ ምሽት በምትወዳቸው እህቶቿ ተከባለች ሌላም የሚወዳት ሰው ስለመኖሩ እርግጠኛ ለመሆን የበቃችው ዛሬ ነው አሌክሳንድራ ከፍል እንደ ገቡም ሂላሪ ከመካከል ሁለቱ እህቶቿ በግራና በቀኛ ተቀምጠው ሲያወሩ አመሹ ለወሬው አቀንኛ ሚጋን ነበረች በተሰይም አሌክሳንድራን የማትጠይቃት ጥያቄ አልነበረም ስለ ባሏ ስለ ቤተሰቦቹ ስለ ፓሪስ ስለ ሪቬዬራ ስለ መኖሪያ ቤቶቻቸው አበዛዝ ስለ አሽክሮቻቸው ስለ ልጆቿ የልጅ ነገር ሲነሳም አሌከሳንድራ በተራዋ ሚጋንን ልጅ የመውሰድ ፍላጐት እንዳላትና እንደሌላት ጠየቀቻት ለሕክምና ሙያዋ እንቅፋት እስካልሆነ መውሰዱን እንደማትጠላ ነገረቻት የሚያወሩት ሁሉ አብሮ እንዳደገ እህትማማች እንጂ ለሰላሳ ዓመት ያህል የተሰያየ ሕይወት እንደመሩ ሁለት የተለያዩ ሴቶች አልነበረም ሂላሪም በእህቶቿ ውይይት መሐል ጣልቃ ገብታ ቁጐኔስ ልጅ የሚባል ነገር ፈልጌ አላውቅም ልጅም ስሰሌለኝ ቅሬታ አይሰማኝም እለች ሂላሪ ውሸቷን ነበረ ያንን ፅንስ በማስወረዲ አሁንም ሆድ ሆዷን ይበላታል ቀጠል አድርጋም ብወጣትነቴ እንኳን ቢሆን መቼም ሌሎቹ ሲወልዱ ሳይ ልጓን እችላለሁ በአሁኑ ወቅት ግን የመውለጃ ጊዜዬ የተላለፈ ይመሰለኛል አለች ፅድሜሽ ስንት ሆነና ስትል ሚጋን ሐኪሟ ግንባሯን ቋጠር አድርጋ ጠየቀቻት ሚጋን የራሷም ሆኖ የእህቶቿ ዕድሜ ይዘነጋት ነበረ ሰሳሳ ዘጠች አለቻት ሂላሪ ብአሁኑ ጊዜ በተለይም በሰሰጠነው ህብረተሰብ አካባቢ በዚሀ ዕድሜ መውለድ የተለመደ ነው አለችና ሚጋን ፈገግ እንደማሰት ብላ እኔ በምሰራበት መንደር ውስጥ ገና የአስራ ሁለትና የአስራ ሶስት ዓመት ልጃገረዶች ናቸው የሚወልዱት በእኛ በእህትማማቾቹ መካከል ዴዴ ብርቅርቅታ ልዩነት እንዳለ ያህል በኮኔክቲከት ተራራ ላይ በሚኖሩ እናቶችና በኒውዮርክ ሴቶች መካከል አኣለ አሌክሳንድራ አንድ ጊዜ በፓሪስ በሌላ ጊዜ በሪቪዬራ የበጋ የክረምት የፀደይ ማሳለፊያ ሕንፃ ቤቶችና ቪላዎች ታማርጣለች እኔ ደግሞ የምኖረው ዓመቱን ሙሉ በአንዲት ጎጆ ውስጥ ነው። ያንን ረጅም የከፋና የበደል ታሪክ ስታወጋቸው ከሁለት ሰዓት በላይ ፈጀባት በሆዷ የቋጠረችውን ሁሉ ለእህቶቿ በመናገሯ እፎይታ ተሰማት ሁለቱም እህቶቿ ከግራና ከቀኝ አቅፈው እንባቸውን አብረዋት አፈለሱ እርሷ በአለፈችበት የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ በዓይነ ሕሊናቸው አብረዋት ተጓዙ ተመላለሱ ወደየመኝታ ክፍላቸውም የሄዱት ሊነጋጋ ሲል ነበረ አስከ እኩለ ቀን ድረስ ሁሉም በእንቅልፍ ላይ ነበሩ ቀድማ የተነሳችው አሌከሳንድራ የእህቶቿን መኝታ ክፍል በር በመቆርቆር ከቀሰቀሰቻቸው በኋላ ስልከ ለመደወል ወደ ምድር ቤቱ ወረደች በቅድሚያ ወደ ኒወዮርክ ደውላ ከእናቷና ከልጆቿ ጋር ስትነጋገር ከግማሽ ለዓት በላይ ቆየች ከሁለት ቀናት በኋላም እንደምትመለስ ለእናቷ ገልፃላት ስልኩን ቨዘጋችር ቀጠለችናም ወደ ሄነሪ ለመደወል የስልኩን መነጋገሪያ አነሳች ግን ፍርሃት ፍርፃት ስላላት መናገሪያውን መልሳ አስቀምጣ ወደ መኝታ ክፍሏ ሄደች ገላዋን ተጣጥባ ወደ ሂላሪ ከፍል ስትገባ ሚጋንን እዛው አገኘቻትፅ እንደ ድሮውም እንደ ሕፃንነት ጊዜያቸው ሂላሪ የሚጋንን ፀጉር አበጥራ እየጐነጐነችላት ነበረ ሚጋን ዛሬም የለበሰችው ጂንስ ሱሪና ሸሚዝ ሲሆን በዚያ ከፀጉሯ አበጣጠር ጋር ላያት የሕክምና ዶክተር ቀርቶ ገና አፍላ ኮረዳ ነበረ የምትመስለው አሌክሳንድራም በእህቷ ሁኔታ ከልብ ነበረ የሳቀችባት ግን ሂሳሪም ሆነች አሌከሳንድራ በዚያን ቀን ሁሉም በልጃገረድ ዕድሜ አካባቢ ያሉ ብርቅርቅታ ነበረ የሚመስለው ከሁሉም ትከሻ ላይ የእርጅና ጫና የወረደ ይመሰላል ሂላሪ እህቶቿን አግኝታለች ቻፕማንንም የምትረሳው አልነበረችም አሌክሳንድራ ስለ ፄነሪ ማሰቡንም ትታዋለች ከእንግዲህ የሚወዷት ልጆቿ እህቶቿ ሂሊና ሚጋን አሏት እናቷም ማርጋሬት ሌላዋ መፅናኛዋ ነበረች ሚጋን በሙያዋ ለማገልገል ሚስተር ፓተርሰንን እየተመላለሰች ለማየት ከምትለያቸው በስተቀር አፍ ለአፍ ገጥመው እንዳወሩ ነበር የዋሉት ዣዛሬም እንደትናንቱ ስናወራ ካደርን ነገ መነሳታችንንም እንች ስትል ሂላሪ እህቶቿን እያየች ፈገግ አለች አሌክሳንድራ ግን ፊቷ ቅዝዝ እያለ ነገ ወደኒውዮርክ ልትመለሺ ነው። ብርቅርቅታ ኒውዮርክ ውስጥ ለጥቂት ቀናት ያህል ስንዘንጥ ለመክረም ዕቅድ እያወጣን ነው እና ትንጂ ሚጋን ከእኔ ጋር አብራ እንድትከርም በዚህ አጋጣሚ ልመናዬን አቀርብላታለሁ አለች ሂላሪ እየሳቀች ለምን። ክእኔ ጋር ነው አብራ የምትቆየው ስትል አሌክሳንድራ ክርክር ከፈተች የሚጋን ውሳኔ ግን ክእህቶቿ ፍላጐት ለየት ያሰ ነበረ ከሁለታችሁም ጋር ተራ በተራ አድር ነበረ ግን የሚስተር ፓተርሰን ቁርጣቸውን እስካላየሁ ድረስ ትቻቸው ለመሄድ አልችልም ከሙያ ግዴታዬም ሌላ የሕሊና ዕረፍት ስለማይሰጠኝ ለጥቂት ቀናት እዚሁ መቆየት ይኖርብኛል ከዚያም ወደ ኒውዮርክ እመጣለሁ አለች ሚጋን በዚያን ምሽት ራት በመብላት ላይ እንዳሉ ጭውውታቸው ከአንዱ እርዕስት ወደ ሌላ ሲንክባለል ቆይቶ በመጨረሻም ላይ የጆን ቻፕማን ወሬ ተነሳ ከቢሮዬ ዘው ብሎ ገብቶ ከፊት ለፊቴ ሲቆም አደጋ ሊጥልብኝ የመጣ ሰው መስሎኝ ደንግጨ ነበረ አለችና ሂላሪ እህቶቿን አሳቀቻቸው እኔ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ሳየው በመልከ መልካም ቁመናው በመማረኬ የሚወደድ እንጂ የሚፈራ ሰው ሆኖ አላገኘሁትም» ስትል አሌክሳንድራ በእህቷ አነጋገር ተሳለቀች ሚጋንም ቀጠል ኣድርጋ እኔም እንደ አሌክሳንድራ የሚፈቀር እንጂ የሚጠላ ሆኖ አልታየኝም ስትል በተራዋ አሾፈች ሶስቱም ውስጥ ውስጡን ተነቃቅተው ነበርና እንደ አፍላ ልጃገረዶች ሲሳሳቁ ቆይተው ቻፕማን ሚስት ይኖረው ይሆን። ማርጋሬት የሆነ ምክንያት ፈጥራ ተለይታቸዋለች ይኸውም ናፍቆታቸውን እንደልባቸው እንዲወጡ በማለቧ ነበረ ሂላሪ አሌክሳንድራንና ሕፃናቱን የምትመራውን የዜና አገልግሎት ድርጅት ቢሮዎች አንድ በአንድ አዘዋውራ አስጉጐበኘቻቸው ክዚያም በከተማው የሚገኙትን የተለያዩ መናፈሻ ሥፍራዎች ዝነኛ የትያትር ቤቶች የንግድ ድርጅቶችና ወዘተ ስታሳያቸው ቆየች ለሕፃናቱ የተለያዩ አሻንጉሊቶች ስትገዛ ለአህቷ ደግሞ መታለቢያ የሚሆን በሉል የተለራ ያንገት ጌጥ አበረከተችላት በመጨረሻም ላይ ያሳየቻቸው ይኖሩበት የነበረውን የዱሮ መኖሪያ ቤታቸውን ነበረ ሂላሪና አሌክሳንድራም ወላጆቻቸውን አስታውሰው አንገት ለአንገት ተቃቅፈው ሲያለቅሉ ምክንያቱ ያልገባቸው ሕፃናት ልጆቻቸውም ሆኑ አላፊ አግዳሚው መንገደኛ እንደጉድ ያዩዋቸው ነበረ ለአሌክሳንድራም ሆነ ለሂላሪ የውቧ እናታቸው የሶላንጅ ትዝታ የዝነኛው አባታቸው የዎከር ሰቀቀን ያንን መኖሪያ ቤት ሲያዩ ሳይታወቅ ተቀስቅሶባቸው ለተመልካች እንቆቅልሽ የሆነውን ለቅሷቸውን የገቱት አረ ሰው ይታዘባችኋል ብላ ትልቋ ሕፃን ማሪ በነገር ስትገጫቸው ነበረ ሂላሪ ማሪ አሌክሳንድራና አክሴል እጅ ለእጅ አንደተያያዙ መንገዱን አቋርጠው ወደ ፒዮር ሆቴል አመሩ ራት አብረው በልተው ሲጨዋወቱ ካመሹ በኋላ ሂላሪ ወደ መኖሪያ ቤቷ ለመመለስ ተነሳች በበነጋታውም ሥራ ቢበዛባት አንኳን ለምሳ ሰዓት እንደማትቀር ከእህቷ ጋር ተቀጣጥረው ተለያዩ ገና ከመኖሪያ ቤቷ ሳሎን ከመግባቷ የስልክ ድምፅ አንቃጨለ ስልክ ደዋዩም ጆን ቻፕማን ነበረ ሚጋን ክሰዓት በኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ ሁሉ እህቶቿን በስልክ ለማግኘት ሳይሳካላት ይቀራል በዚያን ጊዜም ነው ጆን ቻፕማንን ማነጋገሩን አንደ አማራጭ የተጠቀመችበት ብርቅርቅታ የሚስተር ፓተርሰን የቀብር ሥነ ሥርዓት ከሁለት ቀናት በኋላ በኮኔክቲከት እንደሚፈፀም ነግራዋለች የምትሄጂ ከሆነ በእኔ መኪና አብረን እንድንሄድ ላላስብሽ ነበራ አላት ቻፕማን ሂላሪ ጥቂት እንዲታገሳት ጠይቃው ከሁለት ቀናት በኋላ ስላላት ቀጠሮ ማስታወ ደብተሯን ኣገላብጣ አየች የማያንቀሳቅስ ከባድ ጉዳይ ይጠብቃት ስለነበረ ምክንያቶቹን ጭምር በመግለፅ ለመሄድ እንደማትችል አስታውቃው አሌክሳንድራ ግን በቀብሩ ላይ የማትገኝበት ምክንያት ስለማይኖር ደውዬ እነግራትና አብራችሁ እንድትሄዱ አደርጋለሁ አለችው ችግርሽ ይገባኛል ሰሞኑን ደግሞ ከማታምፒው ቢሮሽ ተለይተሽ ነው የከረምሺው ለመሆኑ አሌክሳንድራ እንዴት ናት። አላት ሁሉም ደህና ናቸው ገና አሁን ነው ከነርሱ ተለይቼ ወደ ቤት የተመለስኩት ቀኑን ሙሉ ኣብረን ነው የዋልነው ደስ የሚል ጊዜ አሳልፈሻል ብጣም እንጂ ጆን በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ደሰታ የተሰማኝ እህቶቼን ካገኘሁበት ቀን ጀምሮ ነው በዚህም አጋጣሚ ስለዋልክልን ውለታ በድጋሚ አመለግናለሁ በደረቁ ምስጋና የለም እመቤት አንቺ ባትጋብዥኝም ከኮኔክ ቲከት እንደ ተመለስኩ ቢያንስ እራት አብረን መብላት ይኖርብናል አለና ሳቅ ካለ በኋላ የቱን ያህል መሰለሽ የናፈቅኩሽ ሂሊ አላት በዚያ በገርማማ ድምፁ ሂላሪ ልትቆጣጠረው የማትችለው ስሜት ሰውነቷን ወረራት ለሞኑን በፈንጠዝያ በከረመው የሂላሪ ልብ ውስጥ የቻፕማን ፍቅር ሰተት ብሎ ገብቶበታል አንድም ጊዜ ቢሆን ስለ አንቺ ከማሰብ አላቋረጥኩም አለ ቻፕማን ቀጠል በማድረግ ፊት ለፊት ደፍሮ የማይናገራትን ቃላት ሁሉ አሁን በስልክ ውስጥ አፈሰሳቸው ለምን አለችው ሂላሪ የልቧ ምት ትርታ እየጨመረ ብተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ እንደ አካሌ ቁራጭ አድርጌ ነው የምቆጥርሽ ንክ ነህ አትበይኝ እንጂ ዴ ዴዴ ዴ ፌዴ ዴዴ ዴ። ብቻ በደህና ተመለኩ ብሳው ተሳሳቁ ቻፕማን የሚስተር ፓተርሰን ውርስ ጉዳይ ባይኖርበትና ውርሱም እነ ሂላሪን የሚመለከት ባይሆን ኖሮ ወደ ኮኔከቲከት ባልሄደም ነበረ ብርቅርቅታ ምዕራፍ ሰላሳ አንድ የሚስተር ፓተርሰን የቀብር ሥነ ሥርዓት እንደተፈፀመ ቻፕማን አሌክሳንድራና ሚጋን አብረው ወደ ኒውዮርክ ተመለሱ ሶስቱም እህትማማቾችና ቻፕማን በተገኙበት ሰመጨረሻ ጊዜ በአንድነት ራት ሲበሉ አመሹ ሚጋን በሚስተር ፓተርስን ሕመም የተነሳ ከተስጣት የፈቃድ ቀናት ውጪ በመዘግየቷ እኩሰ ሌሊት ላይ ወደ ኬንታኪ በአውሮፕላን መብረር ነበረባት ከማርጋሬትና ከአሌክሳንድራ ልጆች ጋር ብዙም የመጫወት ዕድል አይግጠማት እንጂ ተዋውቃቸዋለት ፓተርለን በኑዛዜው ስለተወላቸው መኖሪያ ቤትና ሌሎችም ንብረቶች አንስተው መጫወታቸው አልቀረም ዘላቲ ከሆነ የመፍትሔ ሐሳብ ላይ እስቲደርሱም ማናቸውም በውርስ ያገኙትን ንብረት ቻፕማን በኃላፊነት እንዲያስተዳድርላቸው ማድረጉን መረጡ የሚቀጥስውንም የክረምት ጊዜ ሶስቱ እህትማማቾች በኮኔክቲከቱ ቤታቸው ሰማሳለፍ ተስማጮሙ እንዳውም እኮ በየዓመቱ በክረምት ወራት የማንገናኝበት ምክንያት አይኖርም ስለዚህ ይህንን ቋሚ ልምድ ልናደርገው ይገባል ስትል ሐሳቡን ያመነጨችው አሌክሳንድራ ነበረች ሁለቱም እህቶቿ ስምምነታቸውን በፈገግታ ገሰፁላት እንጂ በዚህ ዕቅድ ላይ ቅንጣትም ያህል ቅሬታ አልነበራቸውም። ቻፕማንን ወዳዋለች አሁን ደግሞ የምታየው እንደ ታላቅ ወንድሟ ነበረ መልክ መልካሙ ቻፕማን ለዚያ ላማረ ቁመናው የሚስማማ ጥቁር ሱፍ ለብሷል ቁንኑ ፄነሪ አንኳን ያሳየው አክብሮት ለየት ያለ ነበረ ረጋ ካለ አንደበቱ የሚሰነዘሩት ቃላት አእምሮ ብሩህነቱን ብቻ ሳይሆን ለመልካም አስተዳደጉም ምስክሮች ነበሩ በዚያን ምሽት ሂላሪና ቻፕማን ይህ ጐደላቸው የማይባሉ ጥንድ ሆነው ነው የታዩት ግብዣውም ሞቅ ያለ ነበረ ሌላው ቀርቶ ሕፃናቱ አንኳን ሻምፓኝ እንዲጠጡ አባታቸው ፈቅዶላቸዋል በዚሁ ሁኔታ እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ድረስ ሲጫወቱ አምሽተው ተሰያዩ ሂላሪም ወደ ቀድሞው የብቸኝነነት ዓለሟ አልተመለሰችም ዛሬም ሌሲቱን ያሳለፈችው ከቻፕማን ጋር ነበረ ወደ ፓሪስ ከሚበሩበት ሰዓት በፊት ሁሉም በአውሮፕላን ማረፊያው ተገናኙ ትንጂ አክሴልና ማሪ አክስታቸው የገዛችላቸውን ትልልቅ አሻንጉሊቶች በየብብታቸው ታቅፈው ከፊት ለፊት ይሄዳሉ ፄነሪ የሚስቱንና የማርጋሬትን ሥፍር ቁጥር የሌላቸው የልብስ ሻንጣዎች ለማሳፈር ከወዲያ ወዲህ ይላል ሂላሪና አሌክሳንድራ ደግሞ አፍ ለእፍ ገጥመው በየደቂቃው ቆም እያሉ ያወራሉ ሂላሪ ከትንጂ እህታቸው ከሚጋን ጋር ለገና ወደ ፓሪስ እንደሚመጡ ብርቅርቅታ ለእሌክሳንድራ ቃል ገብታለች ያም ሆኖ የአሁኑ መለያየት ለሁለቱም ጨንቋቸዋል ባሉበት ቆመው ሲያወሩ ማርጋሬት ሕፃናቱን ወደ አውሮፕላን ውስጥ በማስገባት ላይ መሆኗ ታያቸው ሄነሪ ፈንጠር ብሎ ቆሞ ከነበረው ቻፕማን ጋር የመጨረሻ የስንብት ቃላት በመለዋወጥ ላይ ነበሩ ሂላሪ አህቷን እቅፋ አክሲ እንደ ድሮው ዛሬም ልትለይኝ ነው እያለች ተንሰቅስቃ ታለቅስ ጀመረ ፍርሃትና ጭንቀትሽ ይገባኛል ሂሊ ይገባኛል ብላ አሌክሳንድራም ራሷን በእህቷ ትከሻ ላይ ዘንበል አድርጋ አለቀሰች ሂላሪም ያንን ወርቃማ ፀጉሯን እያሻሸች አክሲ አወድሻለሁ ምን ጊዜም አንደምወድሽ እንድታውቂ የሚሉትን እነኛን የሕፃንነት ዘመቧን መሰናበቻ ቃላት ሲቃ እየተናነቃት ተናገረች አይዞሽ ሂሊ አይዞሽ ብቻ ራስሽን እንደምትጠብቂ ቃል ግቢልኝ እኔ ደግሞ በየዕለቱ ስልክ እየደወልኩ አነጋግርሻለሁ» ሁለቱን እህትማማቾች ለማላቀቅ ከፄነሪም ይልቅ ወኔ የነበረው ቻፕማን ነበረ ሂላሪን አቅፎ ወደኋላ ሲያስቀራት ሄነሪ ደግሞ የአሌክሳንድራን እጅ ይዞ በመንደረደር የአውሮፕላኑን መሰላል ወጣ ገና ከመግባታቸው በሩ ተዘጋ የሂላሪ ዕንባ በጉንጮቿ ላይ ይወርዳል ቻፕማን ከደረቱ አንዳቀፋት በርቺ ሂላሪ አይዞሽ ከአንግዲህ ደግሞ እኔ አለሁልሹ ሲላት ቀና ብላ በፈገግታ አየችው የተናገረው ከልቡ መሆኑን አምናበታለች ይበልጥም ወደ ሰውነቱ አስጠጋትና የምትፈልጊው ሁሉ ከአንግዲህ ተሟልቶልሻል አላት ብርቅርቅታ አስካሁን የጭን ቁስል ን መፅከፍን አላነበቡም በሸዙተክለ ጥላሁን ድ ም አ ጠየቀና ዘተኛ ዕትም በየመፅሀዩቶ ያነ ጠ ደዝ ያያቻታሪ መድረሱን ማየት ብቻ ይበቃዎታል።