Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
መብቱ የተጠበቀ ነው። አይዞሽ» ብሎ ተሰናበተኝ ሴቷ ፖሊስ ያሰለቸኝን «ምን አርገሽ ነው።» ብሎ ዘጋኝ በዚህ መሀል በእደኞቿ ተመልምላ ወደ «አንክቴነት» ሥራ ተሠማራች በከርቸሌ ግቢ ከሚፈሩ ሰዎች መካከል አንዷ ወንዳወንድ ነች አለባበሷም የፀጉር እስታይሏም ይህች ልጅ የከርቸሌ ልዩ ስሟ «አፄ በጉልበቱ» ነው ነገር ግን እንደጎዳና ተዳዳሪነቷ አይደለችም ገንዘብ ከከፈሏት ልብስ ጭምር ታጥባለች ከምንም ነገር በላይ የሲጋራ ሱስ አትችልም ለሲጋራ ገንዘብ ጠይቃ ገንዘብ ያለውን በምን እንደምታውቅ እንጃ ከከለከሏት አለቀ ጥምድ አድርጋ ትይዛለች በተለይ አሮጊቶቹ ላይ ትብሳለች ቡና አፍልተው እርግማን ከምርቃት ደባልቀው የሚሉትን በደህና ቀን የሰማችውን ገለባብጣ መራገም ትጀምራለች የአድባሩን የአውጋሩን ስም ሁላ ትጠራና «እነኝህ ኑሮ መሯቸው ትልቅ ወንጀል እየሠሩ የሚገቡትን የኛን የተመላሉዎችን ቦታ የሚያጣብቡትን ሁሉ ቅዱስ ሚካኤል የዘላለም ቤታቸው ያድርግላቸው ጠያቂዎቻቸው ይሰልቹዋቸው ዞር ብሎ የሚያያቸው ይጥፋ ወጣት ወጣቱ ብቻ ይውጣ።» ነው የሙስሊሙን በዓል ደማቅ የሚያደርገው ሌላ ልዩ ነገር የሚቀርበው በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ነው።» የሚል መልዕክት ሳከልኝ እስር ቤት ልጆቼን ይዞ መጥቶ አሳይቶኝ ሁሉ ያውቃል ከርቸሌ እንደገባሁ ኮሎኔል ጠፋ የልጆቼን አያት እንዲያፈላልጉልኝ ብማፀንም ፈልገው አጡት ንብረቱን ሁሉ ሻሸሽጦ ገንዘቡን አሰባስቦ እኔንም ዕድሜ ልክ እስራት ሲፈረድባት ነው ዕውነቱን ለኛንኳን ያጫወተችን እናም በይግባኝ ሁሉን ነገር ልታፍረጠርጥ ወሰነች ግን አልሆነም። እውነት ሰው ገለሽ ነው የታሰርሽው።
ከርቸሌ «ከርቸሌ» በውስጥ ዓይን እውነተኛ የታሪክ ማስታወሻ ስንዱ አበበ ዓም በውስጥ ዓይን ከርቸሌ መታሰቢያነቱ ለሕፃን ዮፍታሄ ብዙዓለምአየሁ። አሳታሚ ስንዱ አበበ ዓም የኮምፒተር ጽሑፍና የሽፋን ስዕል ሕይወት ፀጋዬ በውስጥ ዓይን ከርቸሌ መግቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በነበረው «ከርቸሌ» የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች የቀድሞ ቦታው ለሌላ ጉዳይ ስለተፈለገ እየፈረሰ መሆኑን ሰማሁና ለረዥም ዓመታት በዕጄ የሚጉላላው የአንዲት ደኛዬ የከርቸሌ ቆይታ ሰነድ ትዝ አለኝ ከዓም ማለቂያ ለሦስት ተከታታይ ግዜያቶች አንድ ዓመት ቆይታ የወጣችው ደኛዬ ስለከርቸሌ ማውራት ባትወድም በብዙ ጉትጎታ የቻለችውን በማስታወሻ የጎደለ የመሰለኝን በጥያቄና መልስ ሞልቼ ይህን መረጃ አግኝቻለሁ ይህ መረጃ በሴቶች እስረኞች የመኖሪያ ክልል ያለውን ሁኔታ ብቻ የሚያሳይ ከከርቸሌ ብዙ ገድሎች «አባይን በጭልፋ» ታክል የተቆነጠረ እውነተኛ ታሪክ ነው በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ከፍርድ ቤት ወደ ከርቸሌ የሚያግዘን መኪና ላይ ተቆጥረን ከተጫንን እስረኞች መካከል አንድ ብቸኛ ሴት እስረኛ ነኝ መኪናው የፍርድ ቤቱን ግቢ ለቆ እንዲወጣ «ንዳው። » ተባለ ነገ ለመቀጠል ተስማምተን ወደየመኝታችን አመራን ጩጨ ውጨ በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ከንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት በር ተከፈተ ደንብ ነው ተጣጠብንና ቁርስ በየክፍላችን ዳቦ ታደለን ዳቦ ተሰጠኝ ሻይ ግን «ገና ኮታ አልተመደበልሽም» ተባልኩ ሌሎቹ ከየድርሻቸው በኩባያ አካፈሉኝ ከቁርስ በኋላ እንደመጤነቴ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመርኩ የሴቶች እስር ቤት «ክልል አምስት» በመባል ይታወቃል ቁጥር አንድ የእንግዳ መቀበያ ትልቅ አዳራሽ ነው በውስጡ ሁለት ጊዳ ተጨማሪ ክፍሎች አሉት ከፊት ለፊቱ የፖሊሶች ማማ ይገኛልቡ ራቅ ብሎ ደግሞ ከሁለት ቁጥር እስከ ስድስት የተቀጣጠሉና በኮሪደር የተከፋፈሉ ክፍሎች ናቸው ወደ መቶ ሀምሳ አራት ታራሚዎች በነዚህ ቤቶች ይስተናገዳሉ ከቁጥር ሁለት እስከ ስድስት ላሉት ክፍሎች አራት የመፀዳጃና የመታጠቢያ ቤቶችን በጋራ ይጠቀማሉ በከርቸሌው የእስር ክፍሎች ሞት የዕድሜ ልክ ፍርደኛ የአዕምሮ በሽተኛ ሌቦች በአንድነት በተመደቡበት ክፍል ይኖራሉ ቁጥር አንድ እስከ ሀምሳ ሰዎችን የቀሩት በየራሳቸው እስከ ሰላሳ አምስት ሰዎች ይታጎሩባቸዋል ከፖሊሶቹ ማማ ፊት ለፊት የተንጣለለ የኳስ መጫወቻ ሜዳ አለ ታራሚ ሲያጠፋ ወታደራዌዊ ስፖርታዊ ቅጣትም በዚህ ሜዳ ሳይ ይከናወናል የሜዳውን ጥግ ቢሮዎችና የመሰብሰቢያ አዳራሹ ይጋሩታል በሌላው ጎኑ የፅዕመጫቶች መታሰሪያ ክፍል ክሊኒክና መጋዘን ሲገኝ በመጋዘኑና ከቁጥር ሁለት እስከ ስድስት ባለው መሀል ቦታ በሲሚንቶ የተመረገውና ቆርቆሮ የለበሰው ጨለማ ቤት አለ በጨለማው ቤት ከባድ ጥፋት ያጠፋ ለምሳሌ ግብረሰዶም ሲፈፅሙ የተያዙ የተደባደቡ ይታሰሩበታል መብራትንኳ የለውም ጨለማ ቤት ከገቡ በቀን ሁለቴ ለሽንት ብቻ ይወጣሉ አለበለዚያ ምግብንኳ በፖሊስ አጃቢነት ነው የሚሰጥዎ። » አለች ሌላዋ በማላገጥ በውስጥ ዓይን ከርቸሌ «ዕድሜ ለመንግሥት። » በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ከርቸሌ ጠያቂ ካላቸው እስረኞች ላቦሮዋ አንዷ ናት እናቷና ደኞቿ ይጠይቋታል እሷም የማዳበሪያ ጥልፍ እየሠራች ትሸጣለች «ሥራ የጀመርኩ ዘመን ገና ልጅ ነበርኩ አስራ ሁለት አስራ ሦስት ዓመቴ ቢሆን ነው በዛ ላይ አልተማርኩም «ዶላር» ሲባል እንጂ አይቼንኳ አላውቅም አንድ ቤት ያውም ያልተጠና አለፍ ስል ነው ያየሁት ዘው ብዬ ገባሁና ሳምሶናይት አገኘሁ ሸብ አድርጌው ወደፍሬንዶች ገሰገስኩ ስደርስ ማንም የለም አስቀምጨው ወደ ሌላ የተጠና ሥራ ሄድኩ» «ከፍተሽንኳ አላየሽውም። በውስጥ ዓይን ከርቸሌ በከርቸሌ ካለን ታራሚዎች ውስጥ የከርቸሌዋ ንግሥት ያላቸው ሥልጣንና ኃላፊነት ከሁላችንም የላቀ ነው እሳቸው የፈለጉትን ቢያደርጉ የሥነሥርዓትም ሆነ ሌሎች ኮሚቴዎች አያገባቸውም ኮሚቴዎች የሳቸውን ችግር እንዲፈቱ መጠየቅ የእስረኛ መብታቸው ቢሆንም ንግሥቲቱን ግን ክብራቸው አይፈቅድላቸውምና አያደርጉትም አስተዳደሩም ለእሳቸው ልዩ ዓይን ነው ያለው በእጅም በእግርም በምላስም ትልቅ ቦታ አላቸው ላቦሮዋም ለሳቸው አግዛ የፈለገችውን ብትሳደብ ብትማታ ኮሚቴ ለአስተዳደር ቢያሳውቅም ትዕዛዙ የልዕልቲቱ መሆኑ ስለሚታወቅ ዝም ይባላል ላቦሮዋ የተጠራችበት ደርሳ ስትመለስ ጨዋታው በሞቀ ሁኔታ ቀጠለ ከሩቅ ብቻቸውን ጀርባቸውን ሰጥተውን የተቀመጡትን በሀምሳዎቹ መጀመሪያ ዕድሜ ላይ ያሉት ታራሚ ላይ እያላገጠች የሳቸውን ገድል ቀጠለች የሀምሳ ዓመቷ አሮጊት በማረሚያ ቤቱ ካሉ ሰዎች ጋር ሁሉ ፀበኛ ናቸው ሁሉም ሰው ያጠቃቸዋል እብዶቹ ሳይቀሩ ወንጀላቸው ከውሽማቸው ጋር «መርፌና ክር» እንደሆኑ ባል ደረሰ ካልገደልኩ ብሎ ሲጋበዝ «በለው በለው» ብለው ውሽማቸውን በባላቸው እጅ ማስገደላቸው ተጣርቶ እሳቸው ወሮዋ አስራ አምስት ዓመት ባላቸው ፅድሜ ልክ ተፈርዶባቸው ነው የገቡት ላቦሮዋ ማንንም ሰው አታከብርም እሳቸውንም ሆነ ከሳቸው ዕድሜ በላይ ያሉትን ሁሉ «አንቺ» ነው ምትለው «ትልቅ የአህያ ብቻ ነው። » ብለን እንሰጋለን በግድ ለሷ መታዘዝና ማሸርገድ የሁሉም እስረኛ ግዴታ በመሆኑ ሲፀልዩ «ከልዕልቲቱ ዓይን ሰውረኝ» የሚሉ አሉ ልዕልቲቱ ቆንጆ ሴት ይወዳሉ አገልጋዮቻቸው ከግቢው ታራሚዎች የተመረጡት ናቸው ቆንጆ አዲስ ታራሚ ከገባች በፍጥነት ለአገልጋይነት ትታጫለች ከአገልጋይ አገልጋይ የየራሱ የሥራ ድርሻ አለው ከወሬ ማቀበል መታመንና እስከ ቤት ዕዳት ሥራ የተመደቡ አገልጋዮች በየአስራ አምስት ቀኑ ከሥራ ሥራ ይቀያየራሉ የሚሾሙ የሚሻሩም ሞልተዋል ላገለገሉበት ከጥሬ ገንዘብ እስከ ሶፍት ሳሙናና ምግብ እንደየቅርበታቸው ይሰጣል ዋናዋ ተመርጣ የምትመደበው ልዕልቲቱን ማሸት ማሳጅ ለማድረግ ነው በርሳቸው ክፍል የተመደቡት ሁሉ ንፅህናቸው በንግሥቲቱ ቁጥጥርና ክትትል ስር ነው ንፅህናዋን የማትጠብቅ ንግሥቲቱ ከመተኛታቸው በፊት ያሸለባት ያንቀላፋች አሳቸው ከመንቃታቸው በፊት ነቅታ የምታወራ የምታሾካሹክ ብቻ በሰበብ በአስባቡ ጉዷ ይፈላል በርሳቸው ክፍል ያለች ታራሚ ታማ እንኳን ቢሆን ንግሥቲቱ እንደነቃች መነሳት ግዴታዋ ነው ደፍራ በፀጥታ ተኝታ ካረፈደች ቀስቃሽ ሰው ይላክባታል ከማለዳው ቆጠራ በኋላ መተኛት አይፈቀድላቸውም «ቤቱ ሊፀዳ ነው ብሳችሁ አስነሱዋቸው» የሚል ቀጭን የልዕልቲቱ ትዕዛዝ ይፈፀማል ልዕልቲቱ ዘወትር ከዕንቅልፋቸው ተነስተው በደንቡ መሠረት አንደኛ ተቆጥረው መታጠቢያ ቤት ይገባሉ ረዥም ሰዓት መታጠቢያ ቤት ያሳልፋሉ በዚህ ሰዓት አገልጋዮች ከአራት ዓይነት ያላነሰ ቁርስና ጭማቂ አዘጋጅተው ይቆያሉ ንግሥቲቱ ቁርሳቸውን በእርጋታ ተመግበው ልክ ቢሮ እንደምትሄድ ሴት ተኳኩለውና ተጋጊጠው እስኪጨርሱ ግቢው በተለመደ የራሳቸው ቦታ ላይ ቡና መቀራረብ ይጀምራል የርሳቸው ቡና ሲቀራርብ ለዕለቱ የተመረጡት አጣጭና አጨዋቾች ቦታቸውን ይይዛሉ አንዳንዴም ለነገ ቡና ዛሬ የአክብሮት ጥሪ የሚደርሳት ሴት በዕለቱ ዘንጣ እንድትመጣ ትዕዛዝ ይደርሳታል በመጨረሻ ንግሥቲቱ ይመጡና በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ ይታደማሉ በውስጥ ዓይን ከርቸሌ በማጨሻው ላይ እሳት ተደርጎ ከዕጣን ጋር ይቀርብላትና በማንም ሳትሰማ ፀሎቷን አሳርጋ እጣኑን ቡል አርጋ ታጨሳለችፁ የቡና ቁርሱም በመጀመሪያ ለሷ ይቀርብላትና ቀምሳ በመለጠቅ ለዕድምተኛው ይዞራል በሷ የቡና ሥነሥርዓት የታደመ ማንም ሰው ቡናው ሳያከትም መንቀሳቀስ አይችልም አፍሊዋን «በአደብ ሆነሽ አፍይው። » ትላለች ቤተሰቦቿ ባይፈቅዱም እነሱ ስለተዋደዱ እምቢ ብለው ተደግሶ ተዳሩ ለካንስ ሌላ የሚወዳትና የሚፈልጋት የሰፈር ጎረምሳ አለ በማግባቷ ተበሳጭቶ መረበሽ ጀመረ ከባልዋ አልፎ ቤተሰቦቿ ጭምር ጉዳዩን አውቀዋል ጎረምሳውም አልተቻለም አንድ ቀን ከባልዋ ጋር አመሻሸተው ወደ ቤታቸው ሲገቡ መንገድ ጠብቆ ፀብ ገጠሙ ጎረምሳው የታጠቀውን ርጩቤ ሲመዝ ባል አስጣለና ነጥቆ ደጋግሞ ወጋው እሷም በድንጋጤ ከባልዋ እጅ ዕጩቤውን ነጥቃ «ተንደርድሬ ሰው ቤት ገብቼ ጩቤውን ሽንት ቤት ከተትኩት» ትላለች በዕለቱ ከሆነው የምታስታውሰው ይህን አጋጣሚ ብቻ ነው አሷም ባሏም ከርቸሌ ናቸው ይህች መልከ መልካም ወጣት በየዕለቱ የምትናፍቀው አጋጣሚ አላት የጠበቃዋን መምጣት ጠበቃዋ ሲመጣ ቢሮ ትጠራና ከባልዋ ጋር ዓይን ለዓይን ይተያያሉ ጠበቃዋ መጥቶ ባሏን አይታ ከመጣች በኋላ እንደ አዲስ ማልቀስ ማስታወስ መረበሽ ትጀምራለች ቾ ቾ ቾ በከርቸሌ የሴቶች የእስር ክልል ከፍተኛውን ቁጥር የሚሸፍኑት አብዛኛዎቹ ገጠር ቀመስ ከተሜ የፖለቲካ እስረኞች ናቸው በዕድሜ ሕፃናት የሆኑ ከአስራ አምስት ዓመት በታች አሉ እነኝህን መሰሎቹ ፍርድ ቤቱ ለዕድሜ ምርመራ እንደላካቸው ይናገራሉ ከዛ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው አያውቁም ከሦስት ዓመታት በላይ የቆዩ ይገኙበታል እነኝህ የፖለቲካ እስረኞች ፊታቸው ላይ የጀግንነት የቆራጥነት የጉብዝና ስሜት ይነበባል ብሔራቸውን የአምልኮት ያህል ያፈቅራሉ ሌት ተቀን ስለብሔራቸው ስለትግል ታሪካቸው ማውራትን መስበክ ይወዳሉ በዚሁም መኩራራት ያበዛሉ ለየዘራቸው ለየአካባቢያቸው ያደላሉ በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ከመሀላቸው ማናቸውም «ወንጀለኞች» ነን ብለው አያስቡም አያምኑም አልፎ አልፎ በወሬያቸው መሀል ግን ጨካኝ ገለፃዎቻቸው ያስደነግጣሉ ከገለፃቸው ምን ያህል ጨካኝ እንደሆኑ ለመገመት ይቻላል እንኳን ከሌላ የርስ በርስ ፀባቸው ያስፈራል ከነሱ ጋር ፀብ በፍፁም አያስፈልግም በሚያደርጉት ድርጊት ሁሉ መኩራራትና መመፃደቅን ያበዛሉ ሁሉም እስረኛ ከነሱ ፀብ ተጠንቅቆ ነው ኩርፊያቸው ለትዕግሥትም ለመግባባትም አያመችም በሁሉም ጉዳይ ቶሎ ለፀብ ይጋበዛሉ እርስ በርስ ሲጣሉና ሲሰዳደቡ ቃላትንኳን አይመርጡም ከንግግር በላይ እጅና እግራቸውን እየተጠቀሙ የሚሰዳደቡትን ማየት ያስፈራል ለነሱ ግን ደንታቸውም አይደለ ሁሉም ስለተከሰሱበት ወንጀል ሲያወሩ በጣም እያቃለሉ ነው አንዷ «ቤት አከራየሽ ተብዬ» ሲስተሯ ደግሞ «ወንጀለኛ አክመሻል ተብዬ» ዓይነት ሲጣሉ ግን በፀብ ስድድብ ሰዓት «የሰው ደም ከላሰ ሰው ጋር ንግግር ጨረስኩ። » ይባባላሉ አብዛኛዎቹ ከዝዋይ ወደ ከርቸሌው እስር ቤት የሚመጡት ለህክምና ወይም ለፍርድ ቤት ቀጠሮ ነው «ጉዳያችን በክልላችን ባለ ፍርድ ቤት ይታይልን ብንል የሚሰማን አጣን» ሲሉም ይማረራሉ ከዝዋይ ሲመጡ ለሚወዱት ሰው ከሰል የገንፎ እህል ቅንጨ በማምጣት ያከፋፍላሉ ካልመጡም የሚሳክ ሰው ካገኙ ይልካሉ ደብዳቤብ ይፅፉልናል እኛም በአፀፋው ምላሽ እንሰጣለን እስረኛ ለእስረኛ በአብዛኛው የምግብና የህመም ጉዳዮች ላይ ይተሳሰባል ቾፍ ቾ በከርቸሌ ያሉ የአዕምሮ በሽተኞች ዓይነት ብዛት ደግሞ ሌላው የግቢውን ገፅታ የሚያሳይ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን የእብደታቸው ዓይነትና ሥርዓት ደግሞ የተለያየ ነው በመድሀኒት የሚታዘዙ መድሀኒታቸው አልቆ የፈዘዙና የደነዘዙ ገና ሆስፒታል ለመሄድ በቀጠሮ የሚጠባበቁ ተኝተው የሚውሉ የሚጨፍሩ ፀብፀብ የሚላቸው ዓይነቱ ብዙ ነው ደኛሞች የነበሩትን ሁለቱን እብዶች ግን አልረሳቸውም በውስጥ ዓይን ከርቸሊ ሁለቱም ከኔ በኋላ በአስራ አምስት ቀን ልዩነት ተከታትለው ነው ከርቸሌ የገቡት አንዷ የምታወራው መያዣ መጨበጫ የሌለው ወሬ ነው ብቻ «ባሌ ልጄን ቀምቶኝ ነው ለዚህ የበቃሁት» ትላለች «እሰው ግቢ ተኝቼ ተገኝቼ ሌባ ብለው እዚህ አጋዙኝ» የምትለው ታማሚ ታራሚ ሰው ቤት ተቀጥራ ስትሠራ የሴትየዋ ባል ደፍሯት እንዳረገዘችና ስታረግዝም ከቤታቸው እንዳባረሯት ትናገራለች ተቸግራ ወልዳ ሄዳ የልጂ አባት እንዲረዳት ስትጠይቀው ልጁን ነጥቆ ለዚህ እንዳበቃት እርግጠኛ ሆና ቀኑን ሙሉ በረዥሙ እየጮኸች ስታወራ ትውልና ሲደክማት አንድ ጥግ ኩርምት ብላ በማይሰማ ሁኔታ ከራሷ ጋር ማውራቷን መሳቋን ማልቀሷን ትቀጥላለች ቡና ሲፈላ ያየችበት ሄዳ ቁጭ ትላለች አትጠይቅም ከሰጡዋት ግን ትጠጣለች ከሰው ጋር ጨርሶ አትነጋገርምፈ ሁሌ ብቻዋን እንዳወራች ነው አማኑኤል ሆስፒታል ልትወሰድ ወረፋ እየጠበቀች ነው በጣም ስለምታሳዝን ብዙው ሰው ይራራላታል ስትመጣ ጫማንኳ አልተጫማችም የግቢዋ ንግሥት ለጤና ኮሚቴ ተናግረው ልብሷን እንድትቀይር ገላዋንና ፀጉሯንም እንድትተጣጠብ አስደረጉ ቅባት ጫማና ልብስ እሳቸው ሰጡዋች ቡናም ስትፈልግ እሳቸው ጋር እንድትጠጣ ነገሯት ተራዋ ደርሶ አማኑኤል ሆስፒታል ልትወሰድ እንድትዘጋጅ ተደረገና ተወሰደች መድኅኒት ታዞላት መጣች ጧትና ማታ አንድ አንድ ፍሬ የሚዋጥ ከአማኑኤል ስትመለስ መኪና ውስጥ ተኝታ መጣች እንደመጣች በግድ ተቀስቅሳ ምሳ እንኳ ሳትበላ ተኛች እራት በመከራ ተቀስቅሳ በላች ተኛች መተኛት መተኛት ጭራሽ ለመፀዳዳትንኳ መነሳት አቃታት ሽንቷን በተኛችበት መልቀቅ ሆነ የሷን ፍራሽና ብርድ ልብስ በየቀኑ መቀየር የሰለቻቸው የጤና ኮሚቴዎች ለበላይ አካል አሳወቁና ቦታ እንድትቀይር እዛው ክፍል የሽንት ቤቱ መግቢያ አጠገብ እንድትሆን ተደረገ ግን ሰላማዊ ዕብድ ነበረች ነች ሌላዋ ደግሞ «ቡና ቤት ደህና ስሠራ ተቀናቃኝ መድሀኒት አበላችኝ መድሀኒት አደረገችብኝ» ነው የምትለው በውስጥ ዓይን ከርቸሌ የታክሲ መስታወት ሰብራ ነው ከርቸሌ የገባችው «አሁንም አልለቃት አነካክተዋለሁ። አንቺ ሆዳም » እያለች ትወርድባቸዋለችነፁ እሳቸው ላይ የምትብሰው ምንም ስለማያቀምሏሷት ነው እየደጋገመች እየጨማመረች ስትጮህባቸው «ኮሚቴዎች ልብ አርጉልኝ ኋላ በኔ እንዳይሳበብ ከስሼ እንደታሰረች ጨለማ ቤት ነው የማስገባት» እያሉ ይፎክራሉ እሳቸው አዘውትረው «ጨለማ ቤት ጨለማ ቤት» ማለት ያበዛሉ በውስጥ ዓይን ከርቸሌ እሳቸው ጨለማ ቤት መግባት በጣም ይፈልጋሉ ተብለው ይታማሉ ምን አድርገው እንደሆነ ንጃ እኔ ከመታሰሬ በፊት ለአንድ ወር ጨለማ ቤት ተፈርዶባቸው ገብተው እንደነበር ከጨለማ ቤት ሲወጡ እጅግ አምሮባቸው እንደወጡ የሚያስታውሱ አጫውተውኛል ለካንስ «እኔን ያየ ይቀጣ። » በሚል ዝም ብለዋል ከአምስት ወራት ጥበቃ በኋላ ተራዋ ደርሶ አማኑኤል ሆስፒታል ተወሰደች መድሀኒቱም አላበረዳት ያው እጂንም እግሯንም እንደታሰረች ከርቸሌ በከርቸሌ ወዳሉ ቡድኖች ስንመጣ ደግሞ ተመራርጠው ጊዜያቸውን አብረው የሚያሳልፉ ደኛሞችን እናገኛለን ከንግሥቲቱ ቀጥሎ ሠራተኛም ያላቸው በቂ ጠያቂና ገንዘብም ያላቸውና ከየወንጀሉ ዓይነት ተመራርጠው በጋራ የተጎዳኙ ናቸው ከነኝህ ታራሚዎች መካከል «በከባድ ስርቆት» ተከስሳ ገና ፍርድ ቤት የምትመላለሰው ወጣትና «በማጭበርበር» አራት ዓመት የተፈረደባት ታራሚ በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ከሌሎች ሦስት ታራሚዎች ጋር በመሆን የጋራ ግዜን በማሳለፍ ይታወቃሉ ትንሽ ቆይቶ ሁለቱ ወጣቶች ሴትነታቸውን ረስተው እንደ ባልና ሚስት መሆን ጀመሩ ከቆጠራ በኋላ አንዳቸው ፍራሽ ላይ አንድ ጋቢ ለሁለት እየለበሱ ይተሻሻሉ ሰው ሁሉ ተኝቶ ቴሌቪዥን ጠፍቶ እነሱ አይላቀቁም ይህን ሁኔታ ብዙ ጊዜ በምክር በቅጣት ቢታለፉም አሻፈረን ብለው ቀጥለውበታል አንድ ቀን ኮሚቴዎችና የክልል ሀላፊዎች ተነጋግረው ቤት መቀያየርን እንደ አማራጭ አድርገው አንዷን ወደ ሌላ ክፍል ቀየሯት ወጣቷ ደኛዋ ይህን ውሳኔ ስትሰማ ራሷን ስታ ሲሚንቶው ላይ ተፈጠፈጠች ሚስት ስለሆነች ነው እንዲህ የሆነችው ይላሉኃ ራሷን አውቃ ስትነቃ በለቅሶና በሀዘን ምግብ መብላትንኳ አቃታት ታማሚ ሆነች ቀን ቀን ግቢው ውስጥ ጥግ መርጠው መቀመጥ ሲጀምሩም ተከለከሉ ትንሽ ቆይተው አረሳሱና አብረው መዋል ጀመሩ እነሱን ላለማየትና ለማለያየት ብዙ ቢሞከርም አልተቻለም ጭራሽ አንዷ «ተውንጂ አብረን መብላት እንኳ ይፈቀድልን» ብላ አስፈቀደች እስከ አራት ሰዓት ምሽቱን አብረው መሆን ተፈቀደላቸው ፍቅራቸው ያስቀናል በጣም ይተሳሰባሉ በተለይ ታናሽየዋ ታሳዝናለች ብዙ ጠያቂ ስላላት ወዳጅዋ በምንም ነገር አትቸገርም ቾፍ ቾ ከርቸሌ አስራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸው ከአስራ ሦስት አስራ ሰባት ዓመት የሚገመቱ በርካታ ታራሚዎች አሉ «ተመላሉ» ይባላሉ «ተመላሉ» ተመላላሽ እስረኞች ማለት ሲሆን ከነኝህ ውስጥ በርካታዎቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች ናቸው ፍርድ ቤት ዕድሜያቸውን ከግምት እያስገባነው መሰል ትልቁ ፍርዳቸው ከዓመት አይበልጥም ይፈታሉ ግን በዓመቱ በተለይ ክረምት ሲመጣ ተመልሰው ይመጣሉ እነሱም ይህን ጠንቅቀው ያውቃሉ ወንጀል መሥራቱንም ሥራዬ ብለው እንደተያያዙት ይናገራሉ «የክረምቱን ብርድና ችግር ማን ይችለዋል እዚህ ገብቶ በመንግሥት መቀለብ ነውንጂ ለኛ ብሎ አይደለም የሚቀልበን ግዴታው ነው የዜግነት በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ድርሻችን ነው። » ነች ሜጣን ሁሉም ሰው ይወዳታል ከታራሚ እስከ ፖሊስ ፀጉር ስትሾርብ ትውላለች ፖሊሶች ጠቀም ያለ ፍራንክ ይሰጡዋታል በየክልሉ ብዙ ዓይኑካዎች አሉዋት ኪነትም ነች ለአንድ ዓመት በዓል ከክልላችን ወደ ሌላ ክልል ተወስደን ኪነት በማየት ላይ እንዳለን መሸለም ተፈቀደ በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ሚሜጣን የማይሸልማት የማይስማት ወንድ አልነበረም ከኪነቶች ሁሉ እሷ ብዙ የገንዘብ የከረሜላና የማስቲካ ስጦታ ጎረፈላት ተንበሽብሻ መጣች በማረሚያ ቤቱ ብዙ የዓመት በዓላቶችን አሳልፌያለሁ በተለይ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን እጅግ ይደምቃል የዘመን መለወጫ በዓል ሊደርስ ሲቃረብ የማረሚያ ቤቱ የኪነት ቡድን ልምምዱን ይጀምራል ዘፈን ድራማ ጭውውት ቀልዳቀልዶች ይዘጋጃሉ የኪነት ቁሳቁሶችንና አልባሳቱን የሚያቀርበው ማረሚያ ቤቱ ነው በነኅሴ ወር መገባደጃ የ«አሸንዳ» በዓልን የትግራይ ተወላጅ ታራሚዎች እጅግ ተውበውና ደምቀው ቤት ለቤት እየገቡ እንደ አበባ ሆዬ ሆይ ነው ይጨፍራሉ ፖሊሶች ጭምር ገንዘብ ይሰጣሉ ከዚህ ጀምሮ የበዓል ዝግጅቱ ይጧጧፋል እኛም እንደየሙዳችን ተመራርጠን የበዓል ዝግጅቱን እናጧጡፋለን ለበዓሉ ቀን የሚጠጣ ነገር ለማዘጋጀት ኦፖፕ የተገኙ መድሀኒቶች በሙሉ ተጨምረውበት ይበጠበጣል ለዚህ ሥራ ማንኛውም መድሀኒት ተስማሚ ነው የአዕምሮ በሽተኞች ኪኒን አምፒሲሊን ቴትራሳይክሊን ማስታገሻዎች አይጠፉም እንዲያፈላው ኮካ ወይንም ፔፕሲ ይጨመርበታል ጠንከር ያለ መጠጥ ይወጣዋል በበዓሉ ዕለት ማረሚያ ቤቱ ከወትሮው ለየት ያለ ሥጋ ጣልጣል የተደረገበት ምሳ ያቀርብልናል ከቤተሰብ የሚመጣ ስንቅም ተረፍረፍ ይልልናል ከምሳ በኋላ ንግሥቲቱ የሚያስመጡት ድፎ ዳቦ ይቀርባል ታራሚ በሙሉ የክት ልብሱን እንደየ ባህሉና ሀይማኖቱ ለባብሶና ተጋጊጦ ዝግጅቱን ማየት በሚችልበት በተዘጋጀው ቦታ ይታደማል ይጀመራል በፌሽታና በደስታ እስከ ቀኑ አስር ሰዓት ይከናወናል ከአስራ አንድ ሰዓቱ ቆጠራ በፊት እቃው ይነሳሳናእቃቃ ጨዋታው ተጠናቆ ተቆጥረን ይቆለፍብናል የከርቸሌ ሴቶች ኪነት ቡድን በሀበሻ ቀሚስ ተውበው አበባዬ ሆይን አንዲህ እያሉ ያዜማሉ «አበባዬ ሆይ ለምለም ባልንጀሮቼ ስሙኝ በተራ በውስጥ ዓይን ከርቸሌ እንጨት ሰብሬ ቤት አንድሠራ እንኳን ቤትና የለኝም አጥር ከርቸሌ አድራለሁ ፍርዴን ስቆጥር። » የሚል ስሜት የሚታይባቸው እኝህ ታራሚ ለሰባት ጊዜ እሳቸው ጋር ተመላልሳ ያስወረደች ሴት እንዳለች ይናገራሉ «በነፍስ ማጥፋት» ቢከሰሱም አሳቸው ግን የጎረቤት ጠላት ተነስቶባቸው ለእስር እንደበቁ ከዚህ በፊት ቀበሌዎች እጅ ከፍንጅ ይዘዋቸው በምክር እንደተለቀቁ እያሰቡ ተስፋ ያደርጋሉ አሮጊቷ እዛው ከርቸሌ እንዳሉ ክስ በክስ ተደራርቦባቸዋል እሳቸው ፍርድ ቤት የማይቀርቡበት ወር ያለው ፍርድ ቤቱ በክረምት ሲዘጋ ብቻ ነው ተደራራቢና ተመሳሳይ አስራ አንድ ክስ አለባቸው ገና በመታየት ላይ ያሉት እንዳሉ ሆነው በተዘጉት ፋይሎቻቸው በድምሩ ዘጠኝ ዓመት ተፈርዶባቸዋል በተመሳሳይ ፅንስ በማጨናገፍ በአፖርሽን የገባች ሌላዋ ታራሚ ደግሞ እድሜዋ ወደ አርባዎቹ መጀመሪያ የሚገመት ሲሆን የሁለት ልጆች እናት ነች ቤተሰቧን የምታስተዳድረው ከዚህ ሥራ በምታገኘው ገንዘብ እንደነበርና ጥሩ ገንዘብ ስለምታገኝ ጥሩ ኑሮ ትኖር እንደነበር ታወራለች ባሏ እሷ ከርቸሌ ስትጋዝ ልጆቻቸውን ለእናቷ ለአያታቸው ጥሎ መጥፋቱን ሰምታ ተደናግጣለች በግቢው ውስጥ ለደቂቃንኳ እረፍት የላትም ጥልፉንም ሴንጀሩንም ፈትሉንም ፀጉር ሥራውንም አከታትላ እየተማረችና እየሠራች ገንዘብ አጠራቅማ ለልጆቿ ትልካለች ይህች ምንም ፋታ የሌላት ታራሚ ከቀን ቀን ሰውነቷ እየከሳ እየመነመነች ሄደች ማታ ማታ በክፍሏ ካሉ ታራሚዎች ጋር አትነጋገርም ተኝታ ገንዘብ ስለሚያስገኝ ሥራ ስታወጣና ስታወርድ ስታሰላስል ነው የምታመሸው እንቅልፍ አጥታለች ሀሳቡና በሸታው ተደራርበው አደቀቁዋት ለልጆችዋ የምትልከው ስታጣ ሁለተኛ ማንም ሰው መጥቶ እንዳይጠይቃት አደረገች ጠያቂዎቿም በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ወር ሁለት ወር እያሉ ጠፉ። እደዚህ ዓይነት የጥሪ ምሽቶች የተለመዱ ነበሩ ለየት ያለ ዝግጅት ሲኖራቸው እንደዚህ ነው የሚጠሩን በጥሪ ቀን ቁጥ ቁጥ ብሎ ነገር የለም እምብርታችን እስኪገለበጥ መብላት ነው በልተን ጠጥተን ጨፍረን አመስግነንና መርቀን የዓመት በዓል ስጦታዎች ተሰጥተውን እንሸኛለን» ብቻ የነሱ ዘመን ከርቸሌ ይሞካሻል ቾፍ በማረሚያ ቤቱ ታራሚዎች ሌላው በከፍተኛ ደረጃ የሚወራውና ሁሌ በተስፋ የሚጠበቅ ጉዳይ ደግሞ የባለስልጣናትና የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ድርጅት የሚያደርጉት ድንገተኛ ጉብኝት ዋናው ሲሆን እንደ «የአገር ሉአላዊነት መደፈር» እና «ድልም» ለማረሚያ ቤት ታራሚዎች ትልቅ የመኖር ተስፋን የሚያጭሩ ታላቅ ታሪካዊ ክስተቶች በመሆናቸው በጉጉት ይናፈቃሉ ዳኞች ባለሥልጣኖችና ቀይ መስቀሎች በፖሊስ አጃቢነት «ጉብኝት» ሊያደርጉ መሆኑ ሲሰማ ገና የሁሉም እስረኛ ሀሳብ «ምህረት ይኖር ይሆናል» ወደሜል አቅጣጫ ይዞራል በተለይ ጉብኝቱ ዓመት በዓል መቃረቢያ ላይ ወይም በዓልን አስታኮ ከሆነማ «የምህረት» ተስፋ ግቢውን ያጥለቀልቀዋል «ምህረት የሚደረገው ለከባድ ወንጀለኞችና ከአስር ዓመት በላይ ለተፈረደባቸው ፍርደኞች ነው» ብለው የሚከራከሩ ይበዛሉ ያምሆነ ይህ ጉብኝቱ የሚያመጣው ምህረት የለም ፀጥፀጥ በዛው ይረሳል የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ጉብኝት ወቅት ደግሞ ተሰባስበው በፖሊስ አጃቢነት በተለይ የፖለቲካ እስረኞችንና ጋዜጠኞችን ለብቻ እስከማናገር ይደርሳሉ ቶሎ ቶሎ ባይመጡም በመጡ ጊዜ የወር አበባ መቀበያ ሞዴስ ሳሙና ሶፍት የመሳሰሉ ቁሳቁሶችን በርከት አድርገው ስለሚሰጡን መምጣታቸው ይናፈቃል ታራሚውን ብቻ ሳይሆን ቢሮውንም በልገሳ ስለሚያንበሸብሹት እነሱ ሲመጡ የግቢው መልክ ትንሽ ቀየር ያለ ሁኔታ ውስጥ ይገባል ቾፍ ት በማረሚያ ቤቱ የሴቶች እስረኞች ክልል ካሉ ጥሩ ነገሮች አንዱ ቤተ መጽሐፍት ላይብረሪው ነው ቤተመጽሐፍት ገብቶ ማንበብ ወይም መጽሐፍ ተውሶ በኪራይ በሳምንት ሳንቲም አንድ መጽሐፍ ይከራያል ማንበብ ይቻላል ተማሪዎች የሆኑ ታራሚዎች እንደልብ መጽሐፍ ያገኛሉ በተለይ እንግሊዘኛ መጽሐፍቶች ይበዛሉ «በእርዳታ ስለሚገኙ ነው» ይባላል ጋዜጦች አዲስ ዘመንና አብዮታዊ ዲሞክራሲ እንደልብ ወቅት ጠብቀው ይመጣሉ የግል ፕሬሶች ግን አንዳንድ ታራሚዎች በግል ከሚያስገቡዋቸው በስተቀር በላይብረሪው ውስጥ አይገኙም ከሰኞ አርብ ባሉት የሥራ ቀናቶች በቤተሰብ አማካኝነት የየዕለት በውስጥ ዓይን ከርቸሌ ጋዜጣ የሚደርሳቸውና ሁሉንም ጋዜጦች የሚከታተሉ ንግሥቲቱ ብቻ ናቸው ደግነቱ ለራሳቸው አንብበው ሌላውም እንዲያነብ ስለሚፈቅዱ ተራዎን ጠብቀው ይደርስዎታል በዚህ መልኩ የየቀኑ ሁኔታ ይደርሰናል በየሳምንቱ ከአስር በላይ ጋዜጦችን ተዋውሰን እናነባለን ከላይብረሪው ውጭ ከቤተሰብም መጽሐፍ ከተሳከ ይገባልናል ንግሥቲቱ በጣም ብዙ የእንግሊዝኛ መጽሐፍቶችን ሲያነቡ የሚውሉት ከውጭ እያስገቡ ነው አንዳንዴም ፊልሞችና ድራማዎች በቪዲዮ ካሴት ይመጡላቸዋል በነገራችን ላይ በከርቸሌ ካሉ ክፍሎች ከቁጥር አራት በስተቀር ሌሎቹ ጋር ቴሌቪዥኖች አሉ ቁጥር አራት ለምን እንደተዘለለ እንጃ። ይህች ታራሚ ፍርዷን የሰማች ጊዜ የሆነችውንና ያደረገችው ነገር እጅግ ዘግናኝ ነበር በሷ ሀሳብ ለይግባኝ በላከችው ማመልከቻ መሠረት ፍርድ ቤት ስትቀርብ እውነቱን ሁሉ ዝክዝክ አድርጋ ልትናገር ከኛ ጋር ሁሉ ተመካክራ ጨርሳ ፀጉሯን ሳይቀር ተሠራርታ የቀጠሮዋን ቀን ስትጠባበቅ የዕድሜ ልክ ፍርዷ ከተፈረደ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ማቅረብ የሚፈቀደውን የይግባኝ ማመልከቻ ሰሚው አካል አይቶ ተከሳሹ በአካል በተገኘበት የመጨረሻ ፍርድና ፊርማ ይሰፍርበታል ማንም ተከሳሽ የይግባኙን መጨረሻ በአካል ተገኝቶ እንደሚሰማ በአሠራር ተቀምጦ እያለ የዚች ታራሚ የይግባኝ ቀጠሮ ባልታወቀ ምክንያት ተዘለለ በዕለቱ ፍርድ ቤት የሚቀርቡት ስም ዝርዝራቸው ተጠርቶ እንዲዘጋጁ ሲነገር የእርሷ ግን ስሟ ሳይጠራ ቀረ በመጨረሻው የይግባኝ ቀን ልታፍረጠርጥ የነበረው የአሰበችውና የተማከረችው ሁሉ ገደል ገባ ባልታወቀ ምክንያት የይግባኝ ውሳኔዋ እዛው ከርቸሌ በፖሊሶች ተሳላከ በጽሑፍ ነበር የተላከው ትዕዛዙን ይዘው የመጡት ፖሊሶች በቀጥታ ለራሷ መስጠት ስላሰጋቸው ከማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ጋር ተነጋገሩና በጥንቃቄ እንዲነገራት ተወሰነ እሷ ግን ይህ ሁሉ አልገባትምና ፍርድ ቤት ለይግባኝ መቼ እንደተቀጠረች ለማወቅ መወትወቷን አብዝታለች በውስጥ ዓይን ከርቸሌ አንድ ቀን ቢሮ ተጠርታ እንድትረጋጋ ተመከረችና ውሳኔዋን እንድታነብ ተሰጣት በፀጥታና በእርጋታ አንብባ ስትጨርስ ራሷን ስታ ተዘረረች ፖሊሶች አፋፍሰው ሆስፒታል ወሰዱዋት ሀኪሙ ከአጠገቧ ሰው እንዳይጠፋ አዘዘ የግቢው ታራሚ በሙሉ በሷ ሁኔታ ተረበሸ ግቢው ሀዘን አረበበበት በየተራ ተመድበን እንጠብቃታለን ለሦስት ቀናት ራሷን ሳታውቀ ከረመች ንግሥቲቱን ጨምሮ መላው ታራሚ ተንከባከቡዋት አገግማ ከክሊኒክ ወደ ክፍሏ እንደተመለሰች ራሷን ለማጥፋት ኤሌክትሪክ ያዘች በኃይል አፈረጣትንጂ አልገደላትም በኃይል ከመውደቋ የተነሳ ጣውላው ቤት የተናደ እስኪመሰል ጩኸት አሰማ ፖሊሶችና ታራሚዎች ግር ብለን ስንገባ ራሷን ስታ ላብበላብ ሆና ተዘርራለች አፋፍሰን ክሊኒክ አስተኛናት በጣም ጎድቷታል ሁለመናዋ ነጭ ሆነ ብዙ ፈሳሽ እንድትጠጣ ታዘዘ የፀጉር ቅቤ ሳይቀር እየቀባን እያጠብን ተንከባክበን ያዝናት ከአስራ አምስት ቀናቶች በኋላ ራሷን ማወቅ መንቃት ጀመረች በርግጥ እራስን በራስ ማጥፋት ትልቅ ወንጀል ሆኖ ቢያስከስስም ከባድ ቅጣት እንደሚያስቀጣም ቢታወቅም እሷ ግን በከባድ ማስጠንቀቂያ በተግሳፅና በምክር ታለፈች ቾ ቾ ይህች ታራሚ ባሏን ገደለች ተብላ እድሜ ልክ ቢፈረድባትም እርሷ ግን ጨርሶ ባሏን እንዳልገደለች ትናገራለች « ቡና ቤቴን ሸጩ ከሱ ጋር ተጠቃለን በትዳር ስንኖር የባለቤቴ የገንዘብ ምንጭ ምን እንደሆንኳን አላውቅም ያለኝን የነገረኝን አምጌ ነው የምኖረው አባቱ ሞተዋል ወላጅ እናቱ ግን በሞትና በሕይወት ባላ የተንጠለጠሉ ባልቴት ናቸው ጥሩ ሕይወት እንደኖሩ ያስታውቃሉ እጅግ ፀሎትና ፆም አጥባቂ ሰውወዳድ አዛውንት ናቸው ሦስት እህቶቹ ከሀገር ውጭ ናቸው እናትየው በደርግ ዘመን ውትድርና ዘምቶ ድምፁ ስለጠፋው ልጃቸው ዘወትር ይጨነቃሉ በውስጥ ዓይን ከርቸሌ «የልጄን ዓይን አይቼ በማግሥቱ ልሙት።