Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ «ሁሉም በአርሱ ሆነ ከሆነውም ያለአርሱ ምንም የሆነ የለም» ብሎ የመሰከረለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም «ይኸውም የማይታይ እግዚአብሔርን የሚመስለው በባሕርይ የሚተካ ከለው ከፍጥረቱ ሁሉ በላይ የሆነ በኩር ነው። የፈጠረውን ፍጥረት የሚገዛ የፍጥረታት አለቃ ነው።
ነገረ ማርያም በቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው «አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሴኪ» መኃ የትንቢተ ነቢያት ማረፊያ የስብከተ ሐዋርያት መነሻ የሊቃውንተ ቤተ ከርስቲያን ምሥጢር ነገረ ማርያም ነው ያለ ነገረ ማርያም ነገረ ከርስቶስን መናገር አይቻልም በከርስትና ሃይማኖት ታሪከ የተነሥ አያሌ መናፍቃን የመጀመሪያ ችግራቸው የነገረ ማርያምን አማናዊ ትምህርት መቀበል ነበር ያም ችግራቸው ከርስቶስን በትከከል እንዳያምኑት አድርጓቸዋል በነገረ ማርያም ላይ የተጣራ ትምህርትና እምነት ቢኖራቸው ኖሮ ለኑፋቄ አይጋለጡም ነበር ንስጥሮስ «አምላከ ወልደ አምላከ» ብሎ በከርስቶስ ለማመን የተሳነው «ወላዲተ አምላከ ወላዲተ ቃል አመ እግዚአብሔር» ብሎ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ለማመን በመቸገሩ ነበር ነገረ ማርያምን ከነገረ ከርስቶስ መለየት አይቻልም የተዋሐደ ነው ስለ አመቤታችን የሚነገረው ከፉም ሆነ በጎ ክርስቶስን ይነካዋል የአግዚአብሔርን የማዳን ሥራ በምንናገርበት ጊዜ እመቤታችንን ወደ ጎን መተው አይቻልምና ምከንያቱም ወልዳ ያስገኘች አዝላ የተሰደደች በማስተማር ጊዜው ከአገር አገር አብራው የተንከራተተች ናትና በተሰቀለበት ዕለትም ከአግረ መስቀሉ አልተለየችም በአጠቃላይ አነጋገር ምክንያተ ድቲን አድርጓታል ስለ ነገረ ድኅነት ስንናገር ጌታ ድኅነታችንን በመስቀል ላይ ፈጸመ የምንለው የዕለት ፅንስ ሆኖ በእመቤታችን ማኅፀን የጀመረውን ነው ሥጋውን ቆረሰልን ደሙን አፈሰሰልን ነፍሱን አሳልፎ ሰጠልን ብንል ከእርሷ የነሳውን ነው ከእርሷ ነሥቶ በመስቀል ላይ የፈተተውን ሥጋውን አና ደሙንም የሕይወት ማዕድ አድርጎ ሰጥቶናል መለኩታዊውን ፍህም በማኅፀን ከመሸከም ጀምሮ ይህ ታላቅ ምሥጢር የተፈጸመባት በመሆኑ መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ ሆና ትመሰገናለች በመዝሙራችንም ሆነ በቅዳሴአችን ከስመ ሥላሴ ቀጥሎ የምንዘምረው የእመቤታችንን ምሥጋና ነው ቅዱስ ዳዊት «መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ አግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው ነገር ድንቅ ነው» ያለው ለዚህ ነው መዝ እርሷም አሳተ መለኩትን በማኅፀንዋ ተሸከማ «ሰውነቴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች ልቡናዬም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች የባርያውን ትሕትና ተመልከቷልና ትንቢተ ኢሳይያስን ተመልከቼ አምላከን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ከምትወልደው አመቤት ዘመን ቢያደርሰኝ ገረድ ሆፔ አገለግላታለሁ የሚለውን የልቤን አሳብ አይቷልና እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብዕፅት ይሉኛል ታላቅ ሥራን ሠርቶልኛልና ስሙም ቅዱስ ነው» ብላለች ሉቃ ለእመቤታችን የተደረገላት ታላቅ ሥራ ፍሩ ከጥንተ አብሶ ነፃ ሆና መፈጠሯ ነው ከሀልዮ ከነቢብ ከገቢር ኃጢአት ነፃ መሆኗ ነው ፍሩ ከልማደ አንስት ነፃ መሆኗ ነው ፍ ሰማይና ምድር የማይችሉትን ኪሩቤል እሳታዊ መንበሩን የሚሸከሙለትን ሱራፌል መንበሩን የሚያጥኑለትን መላእከት የሚንቀጠቀጡለትን በማኅፀኗ መሸከሟ ነው በመሆኑም አንደ ቅዱስ ዳዊት «ሀገረ እግዚአብሔር ድንግል ማርያም ሆይ ለአንቺ የተደረገው ነገር ፅፁብ ድንቅ ነው» እያልን እናመሰግናታለን አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕት እምንጹሐን ቅድስት አምቅዱሳን ናት ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች ከተመረጡ የጠመረጠች ማለት ነው ይኸውም እንደሌላው መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ስላልወደቀባት ነው ይህም ይታወቅ ዘንድ ጠቢቡ ሰሎሞን «ለስእርተ ርአስከ ለርእስኪ ለገጽኪ ለቀራንብትኪ ለአዕይንትኪ ለአእዛንኪ ለመላትሕኪ ለአዕናፍኪ ለከናፍርኪ ለአፉኪ ለአስናንኪ ለከሣድኪ ለአጥባትኪ እያለ መልከአ ማርያምን ማለትም የውስጥ የአፍአ ውበቷን ከማድነቅ ጋር «ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ምንም ነውር የለብሽም» ብሏታል መኃ ነውር የተባለውም መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን ያመጣ የጥንት በደል ጥንተ አብሶ የሚባለው የአዳም ኃጢአት ነው አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ጸኒስና ቅድመ ወሊድ ጊዜ ጸኒስና ጊዜ ወሊድ ድኅረ ፀኒስና ድኅረ ወሊድ ድንግል እንደሆነች የታመነ ነው ኢሳ ካ ሕዝ ካ ይህም ንጽሐ ሥጋን ንጽሐ ነፍስንና ንጽሐ ልቡናን አስተባብራ አንድ አድርጋ ይዛ መገኘቷን ያረጋግጥልናል በመሆኑም ጠቢቡ «ምንም ነውር የለብሽም» ሲል የመላእከት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል «ደስ ያለሽ ጸጋንም የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረከሽ ነሽ» ብሎ ከማብሠሩ በፊት ባበሠራት ጊዜ ካበሠራትም በኋላ መሆኑን እንረዳለን ሱቃ ምከንያቱም መልአኩ ገብርኤል ወደ አንዲት ድንግል ተላከ ይላልና ነው ይህም ድንጋሌ ሥጋን ብቻ ሳይሆን ድንጋሌ ነፍስንም የሚያመለከት ነው ድንጋሌ ነፍስን ገንዘብ ማድረጓም አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጥንተ አብሶ የተያዘችበት ጊዜ ፈጽሞ እንዳልነበረ ያሳየናል ጠቢቡም «ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው» ማለቱ ለዚህ ነውና «ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ» ኢሳ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የነገረ ድኅነት ምሥጢር ተገልጦለት ያለፈውን ያለውን እና የሚመጣውን አገናዝቦ ሲናገር «የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ አንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር» ብሏል ኢሳ ይህም ለፍጻሜው ለእመቤታችን የተነገረ ትንቢት ነው ከዚህም በበለጠ ኹኔታ ትርጓሜ የማያሻው ደረቅ ትንቢት ሲናገረም «ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልከት ይሰጣችኋል አነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወልድንም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች» ብሏል ኢሳ ካሓ እነ ኢሳይያስ በጥንተ አብሶ ምከንያት «ሁላችን አንደ ርኩስ ሰው ሆነናል ጽድቃችንም ሁሉ አንደ መርገም ጨርቅ ነው» ኢሳ ጅ ቢሉም እግዚአብሔር ባወቀ ጥንተ አብሶ ፈጽሞ ባልደረሰባት በእመቤታችን ይመኩ ተስፋም ያደርጉ ነበር ለዚህም ነው « እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ ያሉት አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጥንተ አብሶ ገና ከጧቱ ንጽሕት ሆና የተዘጋጀች ጥንተ መድኃኒት ናትና ነው ቅዱስ ኤፍሬምም «መመኪያ አከሊላችን ጥንተ መድኃኒታችን የንጽሕናችን መሠረት» እያለ ያመሰገናት ለዚህ ነው «በአምላከ ኅሊና ታስባ ትኖር ነበር» አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር ነበር ይህንንም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ «ዘእንበለ ይትፈጠር ሰማይ ወምድር ወዘእንበለ ይሣረር ምድረ ገነት ሀለወት ስብሕት ቅድስት ወቡርከት ይእቲ ማርያም እንተ ተሰምየት ሰንበተ ከርስቲያን ጽዮን ቅድስት እሞሙ ለሰማዕት ወአኅቶሙ ለመላአከት የመላእከት እህታቸው የሰማዕታት እናታቸው ጽዮን ቅድስት የከርስቲያን ሰንበት የተባለች የተመሰገነች በንጽሕና በድንግልና የተለየችና የተባረከቸ አርሷ ማርያም ሰማይና ምድር ሳይፈጠር የገነት ምድርም መሠረት ሳይጣል ነበረች ብሷል ዳግመኛም «በቤተልሔም ተወሊዶ መድኅን ከብረ ቅዱሳን ፍስሐ ለኩሉ ዓለም ወሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ወይቤላ እግዚአብሔር ለማርያም አዝማንየ አዝማንኪ አምጣንየ አምጣንኪ ማርያም ሐቀፍኪዮ ወአነ ዮም ወለድኩዎ ለዓለሙ ኹሉ ደስታ የሚሆን የቅዱሳን ከብር መድኃኔዓለም በቤተልሔም ተወልዶ ለሰው ልጅ ዕረፍት ሰንበትን ሠራ እግዚአብሔር ማርያምን ዘመኖቼ ዘመኖችሽ መጠኖቼ መጠኖችሽ ናቸው እኔ ዛሬ ወለድኩት ማርያም ሆይ አንቺ ታቀፍሺው» የሚል አለ ቅዱስ ያሬድ በድጓው አንደገለጠው እግዚአብሔር እመቤታችንን «ዘመኖቼ ዘመኖችሽ ናቸው» ማለቱ ዓለም ከመፈጠሩ ዘመን ከመቆጠሩ በፊት በእርሱ ኅሊና መኖሯን የሚያስረዳ ነው «መጠኖቼ መጠኖችሽ ናቸው» ማለቱ ደግሞ እርሱ ቅድመ ዓለም አካላዊ ቃል ወልድን ያለ እናት ወልዶት አባት እንደሆነው አርሷም ድኅረ ዓለም አካላዊ ቃል ወልድን ያለ አባት ወልዳው እናት አንደሆነችው የሚያመለከት ነው ምሥጢራዊ መልእከቱም «ወላጆች አባትና አናት ለወለዱት ልጅ እኩል እንደሆኑ ሁሉ ወልድን በመውለድ በወላጅነት መሰልሽኝ ተስተካከልሺኝ» ሲላት ነው ይህም ፈጣሪን እና ፍጡርን የማነፃፀር የማስተካከል ሳይሆን የተሰጣትን ከብርና ልዕልና የማሳየት ነው ለምሳሌ ጌታ ደቀመዛሙርቱን «እውነት እውነት አላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ አርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል» ብሏቸዋል ዮሒ ካ ይህም በማስተማርና ተአምራት በማድረግ እንደሚመስሉት ሲነግራቸው ነው «የሚበልጥ ያደርጋል» ማለቱም እርሱ ያስተማረው ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ነው እነርሱ ግን ከዚህ በላይ ሃያ ሠላሳ ዓመት የሚያስተምሩ ስለሆነ ነው እርሱ ለአብነት ሁለት ሦስት ሙት ቢያነሣ እነርሱ ደግሞ በስሙ ከዚያ በላይ ብዙ ስለሚያስነሠ ነው «እመቤታችን በአዳም ባሕርይ ውስጥ» «ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸአዳ እመቤታችን ማርያም ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ፅንቁ ታበራለች» ይላል ይህንንም በድጓው የተናገረው ቅዱስ ያሬድ ነው አመቤታችን በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ፅንቁ ማብራቷ ከጥንተ አብሶ ነፃ ሆና መፈጠሯን የሚያመለከት ነው አዳም ይኸንን ስለሚያውቅ ነው አመቤታችንን ተስፋ ያደረገው ምክንያቱም በውስጡ እንደ ነጭ ዕንቁ ስታበራ ይታወቀው ነበርና ነው አባ ሕርያቆስ ይህ ምሥጢር ተገልጦለት «ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነበርሽ» እያለ እመቤታችንን አመስግኗታል ይህም አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትአዛዝን በመተላለፍ በአዳም ላይ ከመጣ ጥንተ በደል በአምላካዊ ምሥጢር ተጠብቃ ከአዳም ወደ ሴት ከሴት ወደ ኖኅ ከኖኅ ወደ ሴም ከሴም ወደ አብርሃም ስትቀዳ የኖረች ንጽሕት ዘር መሆኗን ያስረዳል ከላይ እንደተገለጠው ነቢዩ ኢሳይያስ «እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ» ያለው ይኸንን ነው «አንዩሖ ሥጋሃ ቀዲሶ ኪያሃ ኀደረ ላዕሴሃራ ቅዱስ ያሬድ በሌላ አንቀጽ «ሥጋዋን አንጽቶ እርሷን ቀድሶ በእርሷ ላይ አደረ» ብሏል ይኸንን ንባብ በመያዝ ትርጓሜውንና ምሥጢሩን ቸል በማለት «ያነጻት የቀደሳት ከጥንተ አብሶ ነው» የሚሉ አሉ ነገር ግን አይደለም ጥንቱንም ንጽሕት ቅድስት አድርጐ በፈጠራት በእርሷ አደረ ማለት እንጂ «ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ ለየ» አንዲል መዝ ፉ ይህም ሁሉ ከተያዘበት ከጥንተ አብሶ ለይቶ ፈጠራት ማለት ነው ጊዜው ሲደርስ ሥላሴ አብ ለማጽናት ወልድ ለለቢሰ ሥጋ መንፈስ ቅዱስ ለማንፃት በማኅጸነ ድንግል አድረዋል እዚህ ላይ «መንፈስ ቅዱስ ለማንፃት» ማለቱ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ ማንፃት መቀደስ መሆኑን ለመግለጥ እንጂ አድፍ ጉድፍ ኖሮባት አይደለም ለምሳሌ እግዚአብሔር የሰማይ ማደሪያውን ባለማለፍ ጸንታ የምትኖረውን አሳታዊ ዙፋን የተዘረጋባትን ሰባት እሳታዊ መጋረጃዎች የተጋረዱባትን ፀዋርያነ መንበሩ ኪሩቤልና ዐጠንተ መንበር ሱራፌል ያሉባትን ጽርሐ አርያምን ጥንቱኑ ንጽሕት ቅድስት አድርጐ ፈጥሯታል ቅዱስ ያሬድ ይኸንን ምሳሌዋ በማድረግ እመቤታችንን «ከሰማያት በላይ ያለ የአርያም የልዑል ሥፍራ ምትክ በምድር ላይ ከፍተኛ አርያምን ሆንሼ ብሏታል በመሆኑም ያቺ ጥንቱኑ ንጽሕት ቅድስት ሆና እንደተፈጠረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ጥንቱኑ ንጽሕት ቅድስት ሆና ተፈጥራለች እንጂ ኖራ ኖራ በኋላ የነፃች አይደለችም ለምሳሌ «ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው» የሚል ገጸ ንባብ ይገኛል መዝ ይህም የእግዚአብሔር ቃል ልከ እንደ ቅቤ እንደ ብረት ወይም እንደ ወርቅ ኖሮ ኖሮ የነጠረ ወይም ነጥሮ እድፍ ጉድፍ የወጣለት ነው አያሰኝም በመሆኑም እመቤታችንን በአባ ሕርያቆስ ምስጋና እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሁኖ ምሥራቅንና ምዕራብን ሰሜንና ደቡብን ዳርቻዎችንም ሁሉ በእውነት ተመለከተ ተነፈሰ አሸተተም እንደ አንቺ ያለ አላገኘም የአንቺን መዓዛ ወደደ ደም ግባትሽንም ወደደ የሚወደውንም ልጁንም ወደ አንቺ ሰደደ» እያልን ልናመሰግናት ይገባል «አንደ አንቺ ያለ አላገኘም» ማለቱም «እንደ አንቺ በጥንተ አብሶ ሳይያዝ የተገኘ የለም ከአንቺ በቀር ሁሉ ተይዚል» ማለት ነው «ቀዳማዊ አዳም ወዳግማዊ አዳም» ቀዳማዊ አዳም የሚባለው ከምድር አፈር የተፈጠረው ሰው ነው «አግዚአብሔር አምላከም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ» እንዳለ ዘፍ ዳግማዊ አዳም የተባለው ደግሞ በተለየ አካሉ ከሰማይ ወርዶ በማኅጸነ ድንግል ማርያም አድሮ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ በተዋሕዶ ሰው ሁኖ የተወለደው የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ ከርስቶስ ነው ይኸንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «አሁንም ከርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ በኩር ሆኖ ተነሥቷል በመጀመሪያው ሰው በቀዳማዊ አዳም ሞት መጥቷል በሁለተኛው ሰው በዳግማዊ አዳም በከርስቶስ ትንሣኤ ሙታን ሆነ ሁሉ በአዳም እንደሚሞት እንዲሁ በከርስቶስ ሁሉ ሕያዋን ይሆናሉ መጽሐፍ እንዲህ ብሏል የመጀመሪያው ሰው አዳም በነፍስ ሕያው ሆኖ ተፈጠረ ሁለተኛው አዳም ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው ነገር ግን አስቀድሞ ሥጋዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም የመጀመሪያው ሰው ከመሬት የተገኘ መሬታዊ ነው ሁለተኛው ሰው ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ ነው» በማለት ገልጦታል ኛ ቆሮ ከዚህም የመጀመሪያው ፍጡር ሁለተኛው ፈጣሪ የመጀመሪያው ከምድር ሁለተኛው ከሰማይ መሆኑን አንረዳለን እንግዲህ የሚያንሰው ቀዳማዊ አዳም ከመጀመሪያው ንጽሕት ከነበረች መሬት ተፈጠረ እያልን የሚበልጠውን ዳግማዊ አዳምን ከመጀመሪያው ንጽሕት ካልነበረች በጥንተ አብሶ አድፋ ጐድፋ ከነበረች ከድንግል ማርያም ተወለደ ማለት ከርስቶስን ከአዳም ማሳነስ መሆኑን ማስተዋል ያስፈልጋል «ብሥራተ ገብርኤል ወፅንሰት» የመላአክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ወደ አመቤታችን በመጣ ጊዜ «ደስ ያለሽ ጸጋንም የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረከሽ ነሽ» በማለት አመስግኗታል ሱቃ ከአርሷ በፊት ይህን በሚመስል ምስጋና የተመሰገነ ማንም አልነበረም ለመጀመሪያ ጊዜ ለእመቤታችን የተሰጠ ምስጋና ነው አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጥንተ አብሶ ተይዛ ቢሆን ኖሮ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል «ጸጋን የተመላሽ ሆይ» አይላትም ነበር ምከንያቱም ጥንተ አብሶ ጸጋዋን ጐዶሎ ያሰኝባት ነበርና ከላይ እንደገለጥነው እነ ኢሳይያስን ጽድቃቸውን የመርገም ጨርቅ ያሰኘባቸው ጥንተ አብሶ ነው የቅድስናን ሥራ እየሠሩ «ሁላችንም እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል» ያሰኛቸው ይኸው ነው ኢሳ እነ ኤርምያስንም «ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም ስንዴ ዘሩ እሾህንም አጨዱ» አሰኝቷቸዋል ኤር እመቤታችን ግን ከመጀመሪያው ንጽሕት ቅድስት በመሆኗ «ጸጋን የተመላሽ ሆይ» ተብላለች አንዳንዶች ለእመቤታችን ጥንተ አብሶ የጠፋላት መልአኩ ባበሠራት ጊዜ ነው ይላሉ ይህም አባባላቸው ሁለት ጥያቄዎችን ያስነሣል አንደኛ ከዚህ በፊት መልአከ ያበሠራቸው ማኑሄና ሚስቱ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ለምን ጥንተ አብሶ አልጠፋላቸውም መሳ ሉቃ ሁለተኛ ጥንተ አብሶ የሚጠፋው በብሥራተ መልአክ ቢሆን ኖሮ አካላዊ ቃል ከሰማይ ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው መሆን መከራ መቀበልና በመስቀል ላይ መሞት ለምን አስፈለገው በልዑል መንበሩ አንደተቀመጠ እልፍ አዕላፋት ወትእልፊተ አዕላፋት መላእከትን ልኮ በብሥራት ብቻ ጥንተ አብሶን አያጠፋም ነበር አንዳንዶች ደግሞ «ጌታ በተፀነሰ ጊዜ በዚያ ቅጽበት ነው የጠፋላት» ይላሉ ይህም «ጌታ የመጣው ጥንተ አብሶን እንዴት አድርጐ ለማጥፋት ነው» የሚል ጥያቄ ያስነሣል መልሱም «በመስቀል ላይ በሚፈጽመው ቤዛነት በሚከፍለው መሥዋዕትነት ነው» የሚል ይሆናል እንግዲህ አመቤታችን ጥንተ አብሶ ነበረባት የሚሉ ከሆነ «አርሷም በጥንተ አብሶ አንደተያዙ እንደማናቸውም ሰው ናት» ማለታቸው ነው እንዲህ ከሆነ ደግሞ እንደማናቸውም ሰው በመስቀል ላይ በሚፈጸም ቤዛነት ብቻ ከጥንተ አብሶ ትድን ነበር እንጂ ተቃዋሚዎቹ እንደሚሉት ሊሆን አይቸልም « ሰው አይደለችም ወይ» ነቢዩ ኢሳይያስ «በትር ከእሴይ ሥር ትወጣለች አበባም ከእርሷ ይወጣል» በማለት ስለ እመቤታችንም ስለ ጌታም ትንቢት ተናግሯል ኢሳ የበትር ምሳሌነት ለአመቤታችን ሲሆን የአበባ ምሳሌነት ደግሞ ለጌታ ነው ቅዱስ ያሬድም በዚህ ትንቢት ላይ ተመሥርቶ « ትወጽእ በትር አምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ ይእቲ በትር አምሳለ ማርያም ቅድስት ይእቲ ወጽጌ ዘወጽአ እምኔሃ አምሳሉ ዘወልድ ዘኀደረ ላዕሌሃ ቃል ሥጋ ኮነ ወተወልደ እምኔሃ ከነገደ ዕሴይ በትር ትወጣለች አበባም ከእሷ ይወጣል ይህችውም በትር የማርያም አምሳል ናት ከእርሷ የሚወጣውም በትር የወልድ ምሳሌ ነው የአብ አካላዊ ቃል በማኅጸኗ አድሮ ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ነሥቶ በተዋሕዶ ሰው ሁኖ ከእርሷ ተወለደ» ብሏሷል ከዚህም በተጨማሪም ቅዱስ ማቴዎስ እንደነገረን የእመቤታችን የዘር ሐረግ የዘር ቅጂዋ ከዕሴይ ወደ ዳዊት ወደ ሰሎሞን ከዚያም ሲወርድ እስከ አልዓዛር ከዓልዓዛር ደግሞ ሴት ልጁ ወደምትሆን ወደ ቅሥራ ከቅሥራም ወደ ኢያቄም የደረሰ ነው በአናቷ በኩል ደግሞ ከሊቀ ካህናቱ ከአሮን ወገን ናት በመሆኑም ከሰው ወገን የተወለደች ሰው ናት ካቶሊኮች ጥንተ አብሶን የሸሹ መስሏቸው «ሰው አይደለችም ኃይል አርያማዊት ናት» እያሉ ነው ሌሎቹ ደግሞ ይኸንን የካቶሊኮች አመለካከት የሸሹ መስሏቸው «እንደማናቸውም ሰው ጥንተ አብሶ የነበረባት ሰው ናት» ይላሉ የሁለቱም «ከድጡ ወደ ማጡ» ነው የሁለተኛዎቹ አስተሳሰብ «ከሰው ወገን የተወለደች ሰው እስከሆነች ድረስ የሰው ልጅ ተብላ እስከተጠራች ድረስ የግድ ጥንተ አብሶ ነበረባት ያሰኛል» የሚል ነው ይህም አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሣል ይኸውም «የሰው ወገን የሰው ልጅ ለመባል የግድ የጥንተ አብሶ መኖር ያስፈልጋል ወይ» የሚል ነው አንዲህስ ከሆነ ቀዳማዊ አዳም ከመበደሉ በፊት ለምን ሰው ተባለ መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን ያጠፋ ዳግማዊ አዳም ከርስቶስም ለምን የሰው ልጅ ተባለ ያሰኛል መናፍቃኑ እነደሚሉት ቢሆን ኖሮ እነ ኢሳይያስ «እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ» እያሉ አይመኩባትም ነበር እነ ሰሎሞንም «አልብኪ ነውር» አያሉ አያመሰግኗትም ነበር እነ ቅዱስ ኤፍሬም «አከሊለ ምከሕነ ወጥንተ መድኃኒት ወመሠረተ ንጽሕነ» እነ አባ ሕርያቆስም «ወኢረከበ ዘከማኪ» አይሏትም ነበር ስለዚህ ብርሃኑን ከጨለማ በጐውን ከከፉ ስንዴውን ከእንከርዳድ ለይተን አባቶቻችን ባቆዩልን ልንጸና ያስፈልጋል ነገሩ የዕውቀት ብቻ ሳይሆን የእምነት ነውና የዕውቀት ሰዎች ሁለት ዓይነት ናቸው የመጀመሪያዎቹ እውቀታቸውን በትህትና ይዘው በእምነት የሚኖሩ ሲሆኑ ሁለተኛዎቹ ግን በዕውቀታቸው ሲታበዩ በጥርጥር ማዕበል የሚመቱ በኑፋቄ የሚለዩ በከህደት የሚወድቁ ናቸው ትእቢት ዲያቢሎስ የተያዘበት አሽከላ ነው በንስሐ የማይመለሰው ለዚህ ነው ዲያቢሎስ የትዕቢት እንጂ የእውቀትም የሥልጣንም ችግር አልነበረበትም እነ አርዮስ እነ ንስጥሮስ እነ መቅዶንዮስም የትዕቢት እንጂ የዕውቀት ችግር አልነበረባቸውም ነገር ግን እውቀታቸውን ለከፋት ተጠቀሙበት እስከ ዓለም ፍጻሜ ለሚነሥ መናፍቃንም መጥፎ አብነት ሆኑበት ስለዚህ ከዚህ እንዲሠውረን ተግተን ልንጸልይ ይገባናል ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት የንጽሕተ ንጹሐን የቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን «ታላቅ ምልክት በሰማይ ታየ ራእ ። ሥልጣን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ኢየሱስ ከርስቶስ የባህርይ አምላከ ነው ቅዱስ ዮሐንስ « የእግዚአብሔር ልጅ ወልደ አብ እንደመጣ ከሰማይ ወርዶ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ በተዋሕዶ ሰው ሁኖ እንደተወለደ አውነተኛም የሆነውን እግዚአብሔርን የባህርይ አባቱን አብን አናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደሰጠን አናውቃለን አውነተኛም በሆነው በአግዚአብሔር ልጅ በወልደ አብ በኢየሱስ ከርስቶስ በማመን እንኖራለን እርሱም እውነተኛ አምላከና የዘላለም ሕይወት ነው» እንዳለ። በመሆኑም በሰማይና በምድር ለእርሱ የማይገዛ ለእርሱ የማይንበረከከ የለም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «በዚህ ምከንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልከ ከፍ ከፍ አደረገው መለኩት የተዋሐደውን ሥጋ ወልደየ ንበር በየማንየ ልጄ በቀሄ ተቀመጥ አለው ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው መለኩት የተዋሐደው ሥጋ በተዋሕዶ አምላክከ ወልድ እግዚእ መባልን ገንዘብ አደረገ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ መላእከትና ደቂቀ አዳም ይሰግዱለት ዘንድ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ከብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰከር ዘንድ ነው አንደበት ሁሉ ኢየሱስ ከርስቶስ በአብ ጌትነት ያለ በከብር አንድ የሆነ ጌታ አንደሆነ ያምን ዘንድ ነው ያለው ለዚህ ነው። ሃይ አበው ጸ ። ሃይ አበው ሻ። ሃይ አበው ደ ጴ «ቃል» ቅዱስ ዮሐንስ «ቃል» ያለው ወልድን ነው ምከንያቱም በምሥጢረ ሥላሴ አብ ልብ ወልድ ቃል መንፈስ ቅዱስ አስትንፋስ ናቸውና። ሃይ አበው ቦ። ሃይ አበው ሷ። ሉ «እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም» ብሏል ዮሐ ቿ ጸ ጁ ቃል ሥጋሆነ ዮሐ ፀ ቅዱስ ዮሐንስ «ከእግዚአብሔር ተወለዱ» በማለት ግዙፋኑ ከረቂቁ ከእግዚአብሔር በመንፈስ በረቂቅ ልደት እንሚወለዱ የተናገረው ያለምከንያት አይደለም ሰው ከእግዚአብሔር በመንፈስ መንፈሳዊ ልደት ተወልዶ የእግዚአብሔር ልጅ አንደሚሆን ሁሉ ረቂቁ ከግዙፉ ማለትም አግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ የሰው ልጅ እንደሆነ ለመናገር ፈልጎ ነው። ሃይ አበው ል። ሃይ አበው ። ቅዱስ ኤራቅሊስም «አምላከን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው አካል ሥጋ ከእርሱ ጋር አንድ ሆነ ከባሕርያችን ተገኝቶ አምላከ የሆነ ሥጋ ነው መንፈስ ቅዱስ ሕይወቱ ሲሆን የምትናገር የሥጋ ሕይወት ነፍስ አለችው» ብሏል። ቅዱስ ቄርሎስም በበኩሉ «ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ከርስቶስ ከአብ ባሕርይ የተገኘ አንድ ወልድ ቃል እንደሆነ ተናገሩ ከባሕርይ አምላክ የተገኘ የባሕርይ አምላከ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ሁሉ የተፈጠረበት እርሱ ነፍስን ሥጋን ነሥቶ ሰው ሆነ ከድንግልም በሥጋ ይወለድ ዘንድ ወደደ በእኛም ባሕርይ ተገለጠ ሰው የሆነበት ባሕርይ ይህ ነውኔ በማለት የእውነት ምስከር ሆኗል። ሃይ አበው ደ። ሃይ አበው ሮፀበዓ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙም «ሁሉን የፈጠረ ነው ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ሰውም ሆኖ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ እግዚአብሔር ቃል ነውና እርሱ መቸም መች አንድ ነው የመለኮቱ ባሕርይ አልተለወጠም» ብሏሷል ሃይ ቿ። ሃይ አበው ኒ። ሃይ አበው ሮ። ሃይ አበው ሆ ፀ። ሃይ አበው ወ ። ሃይ አበው ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ «ነገር ግን እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ አንድ እንደሆነ ብንናገር ወዲህም ከእኛ ባሕርይ የተገኘ ሥጋ ያለመለየት በማይመረመር ተዋሕዶ ከቃል ጋር አንድ መሆኑን እኛ እናውቃለን ሥጋ የመለኮትን ባሕርይ አንዳልለወጠ መለኮትም እንዲሁ የሥጋን ባሕርይ አልለወጠም እርሱ ወልድ በተዋሕዶ ሰው የሆነ አምላከ ነው ብሏል። ቅዱስ አትናቴዎስም «እርሱ ሰው የሆነ አምላከ ነው ስለዚህም መለኮት ሥጋን ወደ መሆን ሥጋም መለኮትን ወደ መሆን አይለወጥም እርሱ ከመለወጥ ከመለዋወጥ ሁሉ የራቀ ነው ከተዋሕዶ በኋላ ግን ፈጽሞ መለየት የለበትም ሰው የሆነ ቃል አንድ አካል አንድ ባሕርይ መሆኑ እውነተኛ ተዋሕዶው የጸና ነው እግዚአብሔር ያደረባቸው አበው እንዳስተማሩን» ብሷል። ሃይ አበው ኮ። ሃይ አበው ዛ ። ሃይ አበው ቄ። በተጨማሪም «ዳግመኛም በከህደታቸው አስበው ማርያም የወለደችው ገዥ ፈጣሪ እንዳይደለ የሚናገሩ የመናፍቃን ልጆች ፈጽመው ምላሽ ይጡ አግዚአብሔር ቃል ሥጋን ካልተዋሐደ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ እንደምን አማኑኤል ተባለ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ ማለት ነው ኢሳ ፀ ማቴ ቫሟደ። መዝ ማቴ ቿ ሉቃ ጴ የማይለወጥ ንጹሕ ቃል የሚለወጥ የሰውን ባሕርይ ተዋሐደ ብሏል። ሃይ አበው ዉ። ቅዱስ አብሊድስ «ዳግመኛም ቃልን ከሥጋ አዋሕደን እንሰግድለታለን ፍጡር ሥጋን ፈጣሪ እንደተዋሐደው እናምናለን ፈጣሪ ከፍጡር በተዋሐደ ጊዜ አንድ አካል በመሆን የጸና አንድ ባሕርይ ሆነ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ አይደለም የመለኮትንና የትስብእትን ተዋሕዶ አናውቃለን ባሕርያችን ሁለት ነፍስና ሥጋ ሲሆን አንድ ይሆናል አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ያድጋል አንድ ሰውም ይባላል ዘፍ ዕብ ፀ» ብሏል። ሃይ አበው ጓ። በተጨማሪም «ተዋሕዶንም አስረዳለሁ አግዚአብሔር ቃል በአካሉ ፍጹም የሚሆን ነፍስ ዕውቀት ያለው ሥጋን ከእኛ ባሕርይ ነሥቷልና እርሱንም ተዋሕዷልና ስለዚህም ነፍስን ሥጋን ተዋሕዶ ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃል አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ እንናገራለን» ብሏል። ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ግብር በድንግልና የጸነሰችውን አምላከ በድንግልና የወለደችው መለኮት ከእርሷ የነሣውን ሥጋና ነፍስ በመዋሐዱ ነው ምከንያቱም በተዋሕዶ የመለኮት ገንዘብ ለሥጋ የሥጋም ገንዘብ ለመለኮት ሆኗልና የመላእከት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አመቤታችንን ባበሠራት ጊዜ «ከአንቺ የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል የእግዚአብሔር አብ ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ነው ከሦሥቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው ማለቱም ለምሥጢረ ተዋሕዶ ምስከር ነው። ጭ «ከዘላለም እስከ ዘለዓለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ» መዝ ዘዩ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ በተዋሕዶ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆኗል። በመሆኑም ኢየሱስ ከርስቶስ በተዋሕዶ አንድ አካል እና አንድ ባሕርይ ነው። ለሥጋውም ከመለኮቱ ወደ አንድ ወገን የተለየ ባሕርይ የለውም ሰው አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ ሁሉ ሰው የሆነ የባሕርይ ገዥ ከርስቶስም እንዲሁ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው እንጂ ፊል ። ነገር ግን በአውነት አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው እንዲሁም መለኮት ከትብስእት አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው ወደ ሁለት አካል ወደ ሁለት ባሕርይ አይከፈልም ዮሐ ሾኮ ሉቃ ዉ ያለዚያ ከሰማይ የወረደ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል እንጂ የሰው ልጅ አይባልም ከድንግል ማርያም የተወለደውም የሰው ልጅ ይባላል እንጂ የእግዚአብሔር ልጅ አይባልም ለእኛ ግን ከሰማይ በወረደ ከድንግል በተወለደ በአንድ እግዚአብሔር እናምን ዘንድ እግዚአብሔር ያጻፋቸው መጻሕፍት ያስተምሩናል። ሃይ አበው ወ። ቅዱስ ኤራቅሊስም «እግዚአብሔር ያለመለወጥ አንደምን ሰው እንደሆነ ቃል ከፈጠረው ሥጋ ጋር ያለ መቀላቀል እንደምን አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደ ሆነ አግዚአብሔር የሥጋን ባሕርይ ያለዘር ያለሩካቤ እንደምን እንደተዋሐደ መላልሰህ በልቡናህ ብትመርምር ይህ ድንቅ ምሥጢር የጎላ የተረዳ ሆኖ ታገኘዋለህ» ብሏል። ዮሐ ሾዉጪ ሃይ አበው ደ። ለእኛስ ከዚህ ትምህርት አንድነት የለንም በጎላ በተረዳ ልትናገሩት የሚገባውስ ይህ ነው ከድንግል ማርያም ነፍስን ሥጋን ነሥቶ ሰው የሆነ የእግዚአብሔር አብ ልጅ መድኃኒታችን ከርስቶስ አንድ ነው ማለት ነው ይህም በማይነገር በማይመረመር ድንቅ በሚሆን ተዋሕዶ ተደረገ የማይታየው እርሱ ከሚታየው ጋር ዘመን የማይቆጠርለት ዘመን ከሚቆጠርለት ጋር አንድ የኾነው አንዱ ነው ሁለት አይደለም ሳይለወጥ ሰው የኾነ እግዚአብሔር ቃል አንድ ባሕርይ አንድ አካል አንድ ገጽ ነው አንጂ ይላል። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርሰቶስ በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ አንጂ ከባሕርዩ ምንም አልተለወጠም የእኛን ባሕርይ በተዋሕዶ ገንዘብ አድርጎ ሰው ሆኗል።