Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ነገረ ማርያም መጽሐፋቸው ላይ ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ ማአከለ ማኅበር ፍሱሓን ተአምረኪ እንዘ እነቡ እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዐጽ እሌቡ ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ ትንቢት ከተነገረለት ከአንበሳ ጉድጓድ ድንግል ሙሽራ በተገኘሽ ጊዜ የንጉሦች ንጉሥ የሰሎሞን ልቡ እንደተደሰተ ደስ ባላቸው በመላእአከት አንድነት ፊት ታምርሽን እየተናገርቱ የሐና አበባ ማርያም እዘምርሻለኀ ወተትን ጠብቶ አንደሚዘል እንቦሳም ዝለል ዝለል ይለኛል በማለት ሰሎሞን ስለ ቅድስት ድንግል ይኸንን ያኸል ታላቅ ኾና መለኮትን የተሸከመችቱን የአምላክ እናት ከብርን እንደምን ይነፍጓታል ይከለከሏታል የአምላከ እናት ማለት ድንግል ማርያም ናታ በማለት የተሰጣትን ከብር በማድነቅ አስተም ሯል ተረፈ ቄርሎስ የባሕርይ አምላከ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በማኅፀኗ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን መሸከሟ በአጅጉ ይደንቃል ምከንያቱም አርሷ በማኅፀኗ የቻለችው በጀርባዋ ያዘለችው በከንዷ የታቀፈችው ልጄን ዙፏኑን የተሸከሙት ኪሩቤል ሱራፌል እሳተ መለኮቱ እንዳያቃጥላቸው በፍርሐት በረዐድ ኾነው በኹለት ከንፋቸው እግራቸውን ሸፍነው ኹለት ከንፋቸው ወዲያና ወዲህ አድርገው ይንቀጠቀጡለታልና ነው ሊቁ አባ ሕርያቆስም ኹለት ተቃራኒ ነገሮችን ማለት እናትነትን ከአገልጋይነት ድንግልናና ወተትን በአንድ ላይ አስተባብራ መገኘቷ ከሕሊና ኹሉ የራቀና አድናቆት የሚገባው መኾኑን በቅዳሴው ላይ ከአገልጋይነት ጋር እናትነት እንደምን ያለ ነው።
ነገረ ማርያም በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላከ አሜን ይህ የነገረ ማርያም ለላቨ ትምህርት ስለ እመቤታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከፅንሰቷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷ ስላለው የሕይወቷን ዝከረ ታሪክከ ስለ እመ አምላክነቷ ስለ ዘላለማዊ ድንግልናዋ በነገረ ሥጋዌ ስላላት ሱታፌ ድርሻ ስለ ንጽሕናዋና ስለ ተሰጣት ክብር የምናጠናበት የሃይማኖት ትምህርት ከፍል ነው የከርስትና አምነት በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላካዊ የቤዛነት ሥራ በፈሰሰው ወርቀ ደም የተመሠረተ የሕይወትና የድኅነት መንገድ ነው ስለዚህም በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ነገረ ድኅነት ፎ የትምህርተ ሃይማኖት ሁሉ አከሊል ጉልላት ነው ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድና ሥምረት በጥንተ ተፈጥሮ የተፈጠረው የሰው ልጅ ዳግመኛ በሐዲስ ተፈጥሮ በመታደሱ ምከንያት በመንፈስ ልደት ከብሯል ስለዚህ ማንም በከርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው አሮጌው አልፎአል ሁሉም እንሆ አዲስ ሆኗል ቆሮ እባ አባት ብለን የምጮህበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ ሮሜኣ ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ ለእነርሱ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው ዮሐ ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በአግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ ጴጥ የሚሉት ቃላተ መጻሕፍት ይህን እውነት የሚያስረዱ ናቸው ይህ አምላካዊ የቸርነት ሥራም አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተዋሕዶ በነሣው ሥጋና ነፍስ የተከናወነ ነው ስለሆነም የዚህ ፍሬ ድኅነት ተካፋዮች የሆንን ክርስቲያኖች ሁሉ የቤተ ከርስቲያን ራስ የሆነው ኢየሱስ ከርስቶስን ስለወለደች የሰው ልጅ የመዳን ቀን ከሰው ልጆች በቅድሚያ ስላወቀት ለእግዚአብሔር የማዳን ሥራ መሣርያ በመሆን አዳኙን መሲሑን ስለወለደች የእግዚአብሔር ታማኝ የምሥጢር መዝገብ ስለሆነች ስለ እመቤታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከፅንሰቷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷ ስላለው የሕይወቷን ታሪክ ስለ እመ አምላከነቷ በነገረ ድኅነት ውስጥ ስላላት ወሳኝ ሚናና ከፍተኛ ሱታፌ ስለ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ስለ ንጽሕናዋና ስለ ተሰጣት ከብር በሚገባ ጠንቅቀን ማወቅና መረዳት ይገባናል ወደ ኋላ መለስ ብለን የቤተ ከርስቲያንን ታሪከ ስንመረምር ስናጠና ከአንደኛው እስከ አምስተኛው መቶ ከፍለ ዘመን የነበሩ ሊቃውንተ ቤተ ከርስቲያን ነገረ ከርስቶስን ርከጪ ከነገረ ማርያም ለላነ ጋር ያለውን ጥልቅ የምሥጢር ግንኝነት በመረዳታቸው ምሥጢረ ሥጋዌን ከማስተማራቸው አስቀድሞ ነገረ ማርያምን በጥልቀት ይማሩና ያስተምሩ አንደ ነበር እናስተውላለን ይህ ጥልቅና ድንቅ ምሥጢር ስፍሐ አእምሮ ያላቸውና የነገረ መለኩትን ትምህርት ፐከር በቅጥነተ ኅሊና የመመርመርና የማራቀቅ ተውህቦና ከኅሎት የተሰጣቸው እነዚህ ኦርቶዶከሳውያን ሊቃውንት ባስተማሩት ሕያው ትምህርትና በጻፏቸው አያሌ የአዕማደ ምሥጢር ሾቨ ር ለክ ፎሃ መጽሐፎቻቸው ከርሠ ምሥጢር እንደ ፅንቁ ፈርጥ ሲያበራ የምናገኘው ነው ሊቃውንቱ በትምህርታቸው ሁሉ ነገረ ማርያም የሃይማኖት ከፍል መሆኑን አብራርተው ገልጠውታል ምከንያቱም ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደው ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አካላዊ ቃል ዘመን ሲፈጸም ያለ አባት ከቅድስት ድንግል ማርያም በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና ተወለደ እርሱ በአውነት የባሕርይ አምላከ ነው አርሷም በአውነት የአምላከ አናት ናት ብሎ መመስከር ሃይማኖት ነውና ማንኛውም በድንግል ማርያም ላይ የምንናገረው ነገር ነገረ ክርስቶስንና ነገረ ድኅነትን የሚነካ በመሆኑ ሃይማኖት ነው ጥንታዊት ሐዋርያዊት የሆነችው ቤተ ከርስቲያናችንም ይህን ይዛ በዘወትር ሥርዓተ አምልኮቷ ጊዜ በምትገለገልባቸው የተለያዩ የጸሎትና የቅዳስያት መጻሕፍት ሁሉ የነገረ ማርያም አስተምህሮዋን በስፋትና በጥልቀት ትመሰከራለች ይልቁንም ደግሞ ፍጹም ሰማያዊና መንፈሳዊ የሆነው ሥርዓተ ቅዳሴዋ በማኅፀነ ድንግል ማርያም የተጀመረውን በድንግልናዊ ልደት የተገለጠውን በቀራንዮ አደባባይ የተፈጸመውንና በዕለተ ትንሣኤ የተረጋገጠውን የድኅነተ ዓለም ጉዞ ዘወትር የሚያዘከርና የነገረ ማርያምና የነገረ ድኅነት የምሥጢር መድብል ነው በዚህም የአመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሁለንተናዊ ሕይወት ከአግዚአብሔር የማዳን ሥራ ዐ ጋር በእጅጉ የተዋሐደና በቀጥታ የተገናኘ መሆኑን እናስተውላለን ከብሯ ከመላእከትና ከደቂቀ አዳም ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ መሆኑ የባሕርይ አምላከ አካላዊ ቃል ከርስቶስን በኅቱም ድንግልና ፀንሳ በኅቱም ድንግልና የወለደች በመሆኗ ወላዲተ አምላክከ ፐከር እላክርዮ አመ እግዚአብሔር ጸባኦት አመ ብርሃን ማኅደረ መለኩት እያለች ሥያሜዋን ታስተምራለች በሥጋዋ በኅሊናዋ ድንግል በከልኤ የተባለች ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ፀኒስ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ፀኒስ ጊዜ ወሲድ ድኅረ ፀኒስ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት ኾዩዞዩ ሃኩዌክ ናት በመሆኑም አምላከን ስትወልደው ማኅተመ ድንግልናዋ አለመለወጡ አምላከም ሰው ሲሆን ባሕርየ መለኩቱ ላለመለወጡ ዳግመኛም ድንግል ወእም ስትባል መኖሯ አምላከ ወሰብእ ሲባል የመኖሩን ይህንን ታላቅ የሥጋዌ ምሥጢር ያወቅንባት የተረዳንባት መሆኗን ታስረዳለች በተጨማሪም ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና አያለች ከጡቶቿ ወተት ተገኝተው በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብ መጋቤ ፍጥረታት አምላከን የመገበች እሳታውያን የሚሆኑ ኪሩቤል ሱራፍኤል በፍርሐት በረዐድ በመንቀጥቀጥ ሁነው ዙፋኑን የሚሸከሙት አሳተ መለኩት ጌታን ዘጠኝ ወር ከአምስተ ቀን በማኅፀኗ የተሸከመቸ በከንዷ የታቀፈች በጀርባዋ ያዘለች እናትነትን ከድንግልና አገልጋይነትን ከእናትነት ወተትን ከድንግልና ጋር አጣምራ የያዘች ምልዕተ ከብር ምልዕተ ጸጋ መሆኗን ዓለም እስከሚያልፍ ድረስ ስትመሰከር ትኖራለች የቤተ ከርስቲያን ሊቃውንት እንዳስተማሩትና እንደጻፉት በእናቷ በሐና በኩል ያሉ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ጴጥሪቃ ቴከታ ሲባሉ ወኮኑ ከልኤሆሙ ጻድቃን ወፈራህያነ እግዚአብሔር ወይትአመንዎ ለአምላኮሙ በጥቡዕ ልብ እንበለ ኑፋቄ ይላል ኹለቱም ሰዎች ደጋጐችና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ያለምንም መጠራጠር በፍጹም ልቡናቸው በአምላካቸው የሚተማመኑ ነበሩ እነሱም በጊዜው ይኸ ቀራችጐ የማይባሉ ባለጠጎች ነበሩ ከሀብታቸው ብዛት የተነሣ ወርቁን ብሩን ንደ ዋንጫ እያሠሩ ከላሙ ከበሬው ቀንድ ይሰኩት ነበር ይኸን ያኸል አቅርንተ ወርቅ አቅርንተ ብሩር እየተባለ ይቄጠር ነበር የዕንቁ ጽዋ እንኳ ድ ሇ ያኸል ነበራቸው ከአለታት ባንዳቸው ጴጥሪቃ ከቤተ መዛግብቱ ገብቶ የሀብቱን ብዛት አይቶ ሚስቱ ቴከታን ለመኑ ዘዘገብነ መዛግብቲነ አልብነ ውሉድ ዘይወርሰነ አንቲኒ ወአነሂ መካን ንሕነ የሰበሰብነው ገንዘብ ስንኳን ለኛ ለልጅ ልጅ ይተርፍ ነበር አንቺም እኔም መካን ነንና የሚወርሰን ልጅ የለንም በማለት ተናገራት ርሷም አንዲኸ ማለቱ ወላድ የፈለገ መስሏት በሐዘን አምላከ አስራኤል ከኔ ልጅ ባይሰጥኸ ከሌላ ይሰጥኸ ይኾናልና ሌላ አግብተኸ ውለድ አለችው ርሱም አነሂ ኢይፈቅድ የአምር አምላከ አስራኤል ከመ ኢየሐስቦ ለልብየ ይኸንስ እንዳላደርገው በልቤም እንዳላስበው የእስራኤል አምላከ ያውቃል በማለት ተናገረ ርሷም ዐዝና ሳለ ራእይ ታያለች ነጭ እምቦሳ ከማሕፀኗ ስትወጣ አንቦሳዩቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ሰባት ስትደርስ ሰባተኛዋ ጨረቃ ጨረቃ ፀሓይን ስትወልድ አይታ በአድናቆት ለባሏ ግሩም ግብሩ ለእግዚአብሔር ትማልም ርኢኩ በሕልምየ ጸዐዳ ጣዕዋ ወጽአት እምከርሥየ ይእቲኒ ወለደት ጸዐዳ ጣዕዋ እስከ ሰብዐቲሆን ወሳብእትኒ ወለደት ወርኀ ወወርኅኒ ወለደት ፀሓየ የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው ትናንትና ማታ በሕልሜ ነጭ ጥጃ ከማሕፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ደግሞ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንደዚኸ እየኾነ እስከ ሰባት ትውልድ ሲደርሱ ሰባተኛዬቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየጐ በማለት አስረዳችው ርሱም በአጅጉ ተደንቆ ሕልም ከሚፈታ ሰው ዘንድ በመኹድ የሚስቱን ራእይ ነገረው ያም ሕልም ተርጓሚ ምስጢር ተገልጾለት ሰባት አንስት ጥጆች መውለዳችኑጐ ሰባት ሴቶች ልጆች ይወለዳሉ ነጭ መኾናቸው ደጋግ ልጆች መኾናቸው ሲኾን ወሳብእትኒ ትከብር እመላእክት ወትትሌአል እምኩሉ ሰብአ ወበእንተ ፀሓይኒ ኢያአመርኩ ሰባተኛዩቱ ጨረቃን መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእከት የከበረች ናትየፀሓይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም በማለት ተረጐመለት ርሱም ለሚስቱ ነገራት ርሷም የአስራኤል አምላከ የሚያደርገውን ርሱ ያውቃል በማለት ፈጣሪዋን አመሰገነቶ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሔሜን አሏት ሔሜን ዴርዴን ወለደች ዴርዴም ቶናን ቶናም ሲካርን ወለደች ሲካርም ሴትናን ሴትናም ሔርሜላን ወለደች ሔርሜላም የተከበረችና የተመረጠች ዓለሙን ኹሉ ለፈጠረ ጌታ አያት ለመኾን የበቃቾ ሐናን ወልዳለች የዝማሬና የትንቢት ጸጋ ከአግዚአብሔር የተሰጡት ከቡር ዳዊት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከብር በተለይም ስለ ሥርወ ልደቷ አምላከን ስለ መውለዷ አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት በመዝ ሇ ላይ መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው በማለት የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥት ከቤተ ከህነት ከኾኑት ከተቀደሱት ከቅዱሱ ኢያቄምና ከቅድስቲቱ ሐና የመኾኑን ነገር በምሳሌ የገለጸው ሊፈጸም ሐና በመልካም አስተዳደግ አድጋ አካለ መጠን ስታደርስ ከነገደ ይሁዳ ከመንግሥት ወገን ኢያቄም የሚባል ደግና ጻድቅ ሰው ዐጭተው አጋቧት ይኸነኑ የሥርወ ልደቷን ነገር በመቅድመ ተአምር ላይ ኢትዮጵያውያን የቤተ ከርስቲያን ሊቃውንት ወሥርወ ልደታ ለእግዝእትነ ማርያም እምቤተ ዳዊት ንጉሥ መንገለ አቡሃ ወእምቤተ አሮን መንገለ አማ ስመ አቡሃ ኢያቄም ወስመ ወላዲታ ሐና የእመቤታችን ማርያም ትውልዷ ባባቷ በኩል ከንጉሠ ከዳዊት ወገን ነው በናቷም በኩል ከካህኑ ከአሮን ወገን ነው የአባቷ ስም ኢያቄም ነው የእናቷም ስመ ሐና ነው ሲል የዘር ሐረግዋ ከቤተ መንግሥት ከቤተ ከህነት ወገን እንደኾነ አስተምረዋል ዳዊት ብቻ ሳይኾን ቀጥሩ ከዐበይት ነቢያት መኻከል የኾነው ነቢዩ ኢሳይያስ ጥበብን በሚገልጽ ትንቢትን በሚያናግር በመንፈስ ቅዱስ አእየተመራ ቅድስት ድንግል ማርያም ከነገደ ዕሴይ ወገን የምትወለድ ስለመኾኗና ከርሷም ጽጌ አበባ የተባለ አካላዊ ቃል ከርስቶስ እንደሚወለድ ተገልጾለት በምዕ ላይ ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣላች አበባም ከርሷ ይወጣል በማለት አስደናቂ ትንቢትን ተናግሮ ነበር በምስጢር የተራቀቀና ከፍተኛ የነገረ ማርያም ዕውቀት የነበረው አባ ጊዮርጊስ ስለ ትውልዷ ኢሳይያስ የተናገረውን ትንቢት በመጽሐፈ ምስጢር ላይ ሲተረጉም በከመ ፈቀደ ወአልቦ ዘይከልኦ ገቢረ ዘኀለየ በከመ ጽሑፍ ዘይብል ትወፅእ በትር አምሥርወ ፅሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምገንዱ ምንት ውእቱ ፀአተ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምገንዱ ምንት ውእቱ ፀአተ በትር እምሥርው ዘእንበለ ዘርዐ ሙላድ ዘቅድስት ድንግል እንተ ኮነት እምኀበ ኢያቄም ውስተ ማሕፀነ ሐና አስመ ዘርዐ ዕሴይ ውእቱ ኢያቄም አቡሃ ለማርያም ወምንትኑመ ካዕበ ዕርገተ ጽጌ እምገንድ ዘእንበለ ሥጋዌ መለኮት እምወለቱ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች ከግንዱም አበባ ይወጣል የሚል እንደተጻፈ ያሰበውን ለማድረግ የሚከለከለው የለም ከኢያቄም ተከፍላ በሐና ማሕፀን ከተፀነሰች ከቅድስት ድንግል የትውልድ ዘር በቀር የበትር ከሥሩ መውጣት ምንድን ነው። ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላከን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን አመቤታችንን የምትወልድ መኾኗን ሲያጠይቅ ነው ከነሱም አስቀድሞ የሳሙኤል እናት ሐና በቤተ መቅደስ ኾና አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ የባሪያኸን መዋረድ ተመልከተኸ ብታስበኝ እኔንም ባትረሳ ለባሪያኸም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ኹሉ ለአግዚአብሔር እሰጠዋለጎኀ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም ብላ ስአለት አንደተሳለች ኹሉ ሳሙል ኢያቄምና ሐናም ይኸነን ራእይ ሐምሌ ቋዉ ካዩ በኋላ ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ ይርዳን አንልም ለቤተ አግዚአብሔር አገልጋይ ይኾናል ሴትም ብንወልድ ለቤተ አግዚአብሔር መጋረጃ ፈትላ ትኑር ብለው ስእለት ከተሳሉ በኋላ ራእይ አየን ብለው ዕለቱን አልተገናኙም አዳምንና ሔዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ የተናገረው አምላክ ለእኛም ይግለጽልን ብለው ፅለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ሰባት ቀን ደረስ አየብቻቸው ሰነበቱ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእከት ኹሉ የከበረች ልጅ ትወልዳላችጐ ብሎ መልአኩ ለሐና ነግሯት በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአከ እመቤታችን ነሐሴ ሰባት እሑድ ተፀንሳለች ከሊቃውንት መኻከል አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ሚ ቡርከት ወቅድስት ይእቲ ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ አሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ ወድኀኒተ ኩሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኸል የተባረከች የተቀደሰች ናት ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኸል የተባረከች የተቀደሰች ናት አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለጐ በማለት ዓለምን ኹሉ በደሙ ፈሳሽነት ያዳነ ንጉሣችን ፈጣሪያችን ከርስቶስን በድንቅ ተአምር ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ የወለደችልን ምከንያት ድቲን ርግበ ሰሎሞን የተባለች የቅድስት ድንግልን የመፀነሷን ነገር በአድናቆት ገልጸዋል ታላቁ ሊቅ በተለይም ዐምስት የሚኾኑ የነገረ ማርያም መጻሕፍትን የጻፈው አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በአርጋኖን መጽሐፉ ላይ የዜና ጽንሰቷን ነገር ሲገልጽ ወይእዜኒ ኦ ውሉደ እግዚአብሔር ወማኅበረ ቅድስት ቤተ ከርስቲያን ናስተብፅዖሙ ለሐና ወለኢያቄም ዘወለዱ ለነ ዛተ ቡርከተ ወቅድስተ መርዓተ አይ ይእቲ ዕለት ፅለተ ሩካቤሆሙ ንጽሕት እንተ ባቲ ሐንበበት ፍሬ ቡርከተ ድንግልተ አስራኤል አጽዕልተ አይ ይእቲ ዛቲ ዕለት ቅድስት ዕለተ ድማሬሆሙ ለአሱ በሥምረተ እግዚአብሔር ተገብረ ተፀንሶታ ለርግብ ንጽሕት ዘአምቤተ ይሁዳ አይ ይእቲ ፅለት ዕለተ ፍሥሓ እንተ ባቲ ኮነ ተመሥርቶ ንድቅ ለማኅፈደ ንጉሥ አኹንም የአግዚአብሔር የጸጋ ልጆችና የቅድስት ቤተ ከርስቲያን ማኅበሮች ሆይ ይኸቺን የተባረከችና የተመረጠች መሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናመስግናቸው የማትነቀፍ የአስራኤል ድንግልን የተባረከችዋን ፍሬ ያፈራችበትን ንጽሕት የምትኾን የሩካቤያቸው ዕለት እንደምን ያለች ዕለት ናት። በማለት እንደ ፀሓይ የሞቀ እንደ ጨረቃ የደመቀ ንጽሕናዋና ቅድስናዋ የመልኳ ደም ግባት በነቢያት ትንቢት አስቀድሞ የተጉጐበኘላት የእውነት ፀሓይ የከርስቶስ አናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ከብርና ደም ግባቷን እንደተናገረ በሊባኖስ ተራራ በግንቦት በተወለደች ጊዜ ፊቷ እንደ ፀሓይ ያበራ ነበር መዐዛዋም ከሽቱ ኹሉ ይበልጥ ነበር የመዐዛዋን ድንቅነት ይኸው አባት ሰሎሞን መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት ይኸነንም በተለያዩ ድንቅ መዐዛ ባላቸው ሽቱዎች መስሎ ሲናገር ቡቃያሽ ሮማንና የተመረጠ ፍሬ ቆዕ ከናርዶስ ጋር ያለበት ገነት ነው ናርዶስ ከቀጋ ጋር የሸቱ ሣርና ቀረፋ ከልዩ ልዩ ፅጣን ጋር ከርቤና አሬት ከከቡር ሽቱ ኹሱ ጋር አንቺ የገነት ምንጭ የሕይወት ውሃ ገ«ድጓድ ከሊባኖስም የሚፈስስ ወንዝ ነሽ በማለት የሕይወት ውሃ የከርስቶስ እናቱ በሊባኖስ የተወለደቺው የቅድስት ድንግል ማርያምን ልዩና ድንቅ መዐዛ ተናግሯል ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም የመዐዛዋን አስደናቂነት በሰሎሞንን ቃል በአንቀጸ ብርሃን መጽሐፉ ላይ ሲገልጸው አባትሽ ሰሎሞን ያፍንጫሽ መዐዛ እንደ ነጭ ዕጣን መዐዛ ነው ብሎ ትንቢት ተናገረ እቴ ሙሽራዬ ሆይ የታጠርሽ ተከል ነሸ መንገድሽም የታጠረች ተከል የታተመች ጐድጓድ ናት ከሽቱ ቅመም ጋራ ሽቱ አለሽ ቆዕ የሚባል ሽቱ ናርዶስ ከሚባል ሽቱ ጋር አለሽ ናርዶስ የሚባል ሽቱ መጽርይ ከሚባል ሽቱ ጋር አለሽ ቀጺመታት ቀናንሞስ የሚባሉ ሽቶች ከደጋ ሽቶች ጋር አሉሽ ከሽቶች ኹሉ የሚበልጡ ከርቤና ዐልው የሚባሉ ሽቶች ከነዚኸ ኹሉ ሽቶች ጋር አሉሽ የገነት ፈሳሽ ሆይ ከደጋ የሚፈስስ የሕይወት ውሃ ጉድጓድ ነሽ በማለት የመዐዛዋን ነገር አድንቋል የእመቤታችን ጣዕመ ውዳሴዋ በእጅጉ የበዛለት ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በአርጋኖን ምስጋናው ከሰሎሞን ቃል በመነሣት የመዐዛዋን ነገር ሲያደንቅ ወእወዲ ውስተ አፉየ እምፍሬ ከርሥኪ ጥዑም ለጉርዔየ ደመ አስካልኪ ወመድምም ሰለአንፍየ መዐዛ ዕፍረትኪ ከመ ዘሰትየ ወይነ ከራሜ ያስተፌሥሖ ለልብየ ስብሐተ ድንግልናኪ ሚመጠን ፍሥሓየ በአንቲኣኪ ወሚመጠን ሐሜትየ በእንተ ከብርኪ አዳም ንባብኪ ወመዓርዒር ቃልኪ ሙሐዘ ፍሥሐ ከናፍርኪ ወሙሒዘ ስብሐት ልሳንኪ ጥቀ ሠነይኪ ወጥቀ አደምኪ አፈቅሮ ለፍግዕኪ ዘቆምኪ ይመስል በቀልተ ወጹና አልባስኪ ከመ ርሔ አፈው ወና አንፍኪ ከመ ጹና ወይን ማሕ ጂኗ ወመክሥተ አፉኪ ምዑዝ ከመ ጹና ጽጌ ቀናንሞስ ዘምስለ ኩሉ ዕፀወ ሊባኖስ ከማሕፀንሽም ፍሬ ወደ አፌ እጨምራለቱ የፍሬሽ ደምም ለጉሮሮዬ የጣፈጠ ነው የሽቱሽ መዐዛም ለአፍንጫዬ ያማረ ነው የድንግልናሽ ከብርም ልቡናዬን አንደ ከረመ ንጹሕ ወይን ደስ ያሰኘዋል ስለ አንቺ ያለኝ ደስታ ምን ያኸል ነው አነጋገርሽ ያማረ ነው ቃልሽም የጣፈጠ ነው ከንፈሮችሽም የደስታ ምንጭ ናቸው አንደበትሽም የምስጋና መፍለቂያ ነው እጅግ በጣም አማርሽ ቁመትሽ የሰሌን ዛፍ የልብሶችሽ መዐዛም አፈው በመባል አንደሚታወቀው ሽቱ የአፍንጫሽ መዐዛም እንደ ወይን አበባ ሽታ የሚኾንልሽ ድንግል ሆይ ደስታሽን እወደዋለጐ ማሕ ጂ የአፍሸም አከፋፈት እንደ ቀናንሞስ አበባ የጣፈጠ ነው ከሊባኖስ ዕንጨቶች ኹሉ ጋር ማሕ በማለት አንደ ሰሎሞን ርሱም የፈጣሪውን እናት አመስግኗል ሐናና ኢያቄምም በእጅጉ ተደስተው በተወለደች በቿ ቀኗ ስሟን ማርያም ብለው ሰየሟት ቅድስት ድንግል ማርያምም እስከ ሦስት ዓመት ድረስ በእናት በአባቷ ቤት ውስጥ ኖራለች ይኸነን በእናት በአባቷ ቤት የነበራትን አስተዳደግ ጥዮርካዩሀከክ ፕሮቶቫንጊሊዩም ኦፍ ጀምስ በሚለው ጥንታዊዉ መጽሐፍ ሲገልጽ ሕፃኗም ከቀን ወደ ቀን በኀይልና በብርታት እያደገች ኬደች የስድስት ወር ልጅ በኾነች ጊዜ እናቷ መቆም ትችል አንደኾነ ለማየት መሬት ላይ አቆመቻት ርሷም ሰባት ርምጃ ተራምዳ ወደእናቷ ዕቅፍ ውስጥ ገባች አናቷም እንዲኸ አለቻት ወደ ጌታ አግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አስከወስድሽ ድረስ በራስች አንዳትራመጂ አለቻትና በመኝታ ቤቷ ውስጥ ውስጥ የቅድስና ስፍራ አበጀችላት አንድ ዓመት በኾናት ጊዜም ኢያቄም ታላቅ ግብዣ አድርጎ ካህናቱን ጸሐፈትን ታላቆችንና ሕዝብን ጠራ ከዚያም ኢያቄም ልጁን ወደ ካህናቱ አቀረባት እነርሱም አባታችን እግዚአብሔር ሆይ ይኽቺን ልጅ ባርካት በትውልድ ኹሉ የሚጠራ ማብቂያ የሌለው ስምን ስጣት እያሉ ባረኳት ሕዝቡም ኹሉ ይደረግ ይኹን ይጽና አሜን አሉ ከዚያም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወሰዳት ርሱም ልዑል አግዚአብሔር ሆይ ይኸቺን ልጅ ተመልከት ለዘላለም በሚኖር በፍጹም በረከትም ባርካት በማለት ባረካት ሐናም ይዛት ወደ ተቀደሰው የማደሪያዋ ከፍል በመውሰድ ጡትን ሰጠቻት ይላል ከዚኽ በኋላ እናቷ ሐና ልጄ ሦስት ዓመት በኾናት ጊዜ ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፈ መክብብ ምዕ ላይ ሰነፎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልኸ ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ የተሳልኸውን ፈጽመው ተስለኸ የማትፈጽም ብትኾን ባትሳል ይሻላል ብሎ የተናገረውን በማሰብ ባሏ ኢያቄምን ይኸቺ ብላቴና የብጽአት ገንዘብ እንደኾነች ታውቃለኸ ወስደን ለቤተ እግዚአብሔር አንስጣት አለቸው ርሱም ፍቅርሽ ይለቅልሽ ብዬ ነው እንጂ አኔማ ፈቃዴ ነው አለ ኢያቄም ይኸነን ማለቱ ሐና እመቤታችንን በመካንነት ኑራ ያገኘቻት አንድያ ልጄ ናትና ከፍቅሯ ጽናት የተነሣ ተለይታት አታውቅም ነበርና ነው ጥበብ ሥጋዊ ጥበብ መንፈሳዊ በእጅጉ የተሰጠው ሰሎሞን አስቀድሞ በመንፈሰ እግዚአብሔር በመቃኘት የሐና አንድያ ልጄ የኾነቺው በየዋህነቷ በርግብ የተመሰለች ቅድስት ድንግል ማርያምን ስፍር ቀጥር ከሌላቸው ከሌሎች ሴቶች ተለይታ ለአምላከ እናትነት ብቸኛ ተመራጭ መኾኗን በማሕ ላይ አዋልድ አለ አልቦን ጐልቀ ቀጥር የሌላቸው ቆነዣዥት አሉ በማለት ስፍር ቀጥር የሌላቸው እጅግ የበዙ ሴቶች መኖራቸው ከተናገረ በኋላ አሐቲ ይእቲ እምኔሆን ርግብየ ፍጽምትየ ርግቤ መደምደሚያዬ አንዲት ናት ብሎ ከነዚያ ኹሉ ተለይታ በየዋህነቷ በርግብ የተመሰለችው ቅድስት ድንግል ብቸኛ እናት ትኾነው ዘንድ በአምላከ የመመረጧን ነገር ከተናገረ በኋላ አሐቲ ይእቲ ለእማ ወኅሪት ይእቲ ለእንተ ወለደታ ለእናቷ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት በማለት አናቷ ቅድስት ሐና በመካንነት ከኖረች በኋላ የወለደቻት ምርጥ ልጄ መኾኗ ተገልጾለት ተናግሯል ከዚኸ በኋላ ዳዊት በመዝ ጓጳቿ ሀ ላይ እግዚአብሔር በቀን ቸርነቱን ያዝዛል በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይኾናል የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላከ ነውበሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ኢየሩሳሌም ሆይ በመካከልሽም ሃሌሉያ እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በአግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ መቅደሱንም አመለከት ዘንድ በማለት እንደተናገረ ኢያቄምና ሐና እግዚአብሔርን በማመስገን ካህኑ ዘካርያስን ይኸቺ ብላቴና ተስለን አምላካችን በቸርነቱ የሰጠን ናትና ተቀበለን አሉት ርሱም ቢያያት እንደ ፀሓይ የምታበራ አንደ መብረቅ ግርማዋ የሚያስፈራ የምታበራ ፅንቄ ባሕርይ መስላ ታየቸው ርሱም በአድናቆት ይኸቺን የመሰለች ፍጥረት ምን እናደርጋታለን ምን እናበላታለን ምንስ እናጠጣታለን ምን እናነጥፍላታለን ምን እንጋርድላታለን ብሎ ሕዝቡን ሰብስቦ ሲጨነቁ ለአስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ ለኤልያስም በመልአኩ አጅ በመሶበ ወርቅ ኅብሥት የመገበ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል አጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት ዘፀ ወ ነገ ዕዝ ሱቱ የቿጓዷ። ይኸም ፋኑኤል የተባለው መልአከ ቀጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእከት አንደኛው ሲኾን ሐዋርያው ይሁዳ ከቀነዐደ ላይ ስለመጽሐፉ የጠቀሰለት የአዳም ሰባተኛ ትውልድ የኾነው ሞትን ሳያይ የተሰወረው ታላቁ አባት ሔኖከ በምዕ ደ ላይ አራተኛው የዘላለም ሕይወት የሚወርሱ ሰዎች ተስፋ ሊኾን ንስሐ በሚገቡ ሰዎች ላይ የተሾመ ፋኑኤል ነው በማለት የመልአኩን ከብር መስከሮለታል ወሶቤሃ ወረደ ፋኑኤል ሊቀ መላእከት ወጸለላ በአከናፊሁ ወተለዐለ ላዕለ መጠነ ቆመ ብአሲ ወወሃባ ወመጠዋ ወዐርገ ውስተ ሰማይ ይላል በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእከት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ወረደ ዘካርያስ ለርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ሊቀበል ቢነሣ ወደ ላይ ሰቀቀበት ያን ጊዜ ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርምና ለዚኸች ብላቴና የመጣ ሀብት ይኾናል እስኪ እልፍ አድርጋችጐ አኑሯት አለ እልፍ አድርገው ቢያኖሯት ድንኩል ድንኩል እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ከንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያኸል ከፍ ብሎ ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ የነገረ ማርያም መጽሐፋቸው ላይ በመልአኩ አጅ የመመገቧን ነገር ሲገልጹ የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድከትምና አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና ወያሥተፌስሐኒ ካዕበ ትአምርተ ልሕቀትኪ በቅድስና ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን አየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል በማለት አመስግነዋል ካህናቱም ሕዝቡም የምግቧማ ነገር ከተያዘ ከሰው ጋራ ምን ያጋፋታል ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይኹን እንጂ ብለው ዙፋኑን ዘርግተው ምንጣፉን አንጥፈው ግራና ቀኝ መጋረጃውን ጋርደው ነቢዩ ዳዊትም በመዝ ላይ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና በዓል የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ በማለት እንደተናገረ ስላዩትና ስለተደረገው ነገር ኹሉ አግዚአብሔርን እያመሰገኑ አማናዊት የአምላከ መቅደስ የአካላዊ ቃል ታቦት እመቤታችንን ወደ ቤተ መቅደስ በሺሕ ሀየፐቿ ዓመተ ዓለም በሦስት ዓመቷ አስገቧት አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእናቷ ከአባቷ ቤት ተለይታ በእግዚአብሔር ቤት በቤተ መቅደስ እንደምታድግ ነቢዩ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ ተገልጾለት በመዝ ማፀዐዘል ላይ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች ልጄ ሆይ ስሚ እዩ ጆሮሽንም አዘንብዩ ወገንሸን ያባትሸንም ቤት እርሺ ንጉሥ ውበትሸን ወድዶአልና እርሱ ጌታሽ ነውና በማለት የተናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም አማናዊት መቅደስ ርሷ ምሳሌዋ ወደሚኾነው ቤተ መቅደስ አንድትገባ ባለቤቱ አድርጓል በቤተ መቅደስ ውስጥ በንጽሕናና እግዚአብሔርን እያገለገሉ ስለማደግና ስለመኖር መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት ሲገልጽ ከዚኸ ውስጥ በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከተወለደ በኋላ በስለት ተሰጦ የእግዚአብሔር አገልጋይ ኹኖ በቤተ መቅደስ ያደገው ሳሙኤል ሲጠቀስ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ ከአሴር ወገንም የነበረችው የፋኑኤል ልጅ ነቢይት ሐና ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ከኖረች በኋላ ሰማኒያ አራት ዓመት ያህል መበለት ኾና በጣም አርጅታ ሳይቀር በጾምና በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም እንደነበር ተጽፎ እናነባለን ጸሳሙ ሱቃ ወሂወኒ አማናዊት የአምላከ መቅደስ እመቤታችንም ምሳሌዋ በኾነ በቤተ መቅደስ ከገባች ዝዥምሮ መላእከት እያረጋጓት ካህናት አያመሰገኗት ኅብስት ሰማያዊ እየመገቧት ጽዋዕ ሰማያዊ አያጠጧት ለዐሥራ ኹለት ዓመት ያኸል በቤተ መቅደስ ስለመቀመጧ በየ ዓም የተወለደው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን የነገረ ማርያም መጽሐፉ ላይ ሲገልጽ አንቲ ውእቱ ንጽሕት እም ንጹሓን ድንግል ኅሪት ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ ሥርግው በወርቅ ንጡፍ ወልቡጥ በዕንቄ ባሕርይ ዘየሐቱ ዘብዙኅ ጫጡ ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ወመላእከት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ተ ወተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኅበ መላእከት ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የኾንሽ አንቺ ነሽ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደተሠራ በወርቅ አንደተጌጠና ዋጋው ብዙ በኾነ በሚያበራ ዕንቀ እንደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ አንዲኸ ኾነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ መላእከት ዘወትር ምግብሸን ያመጡ ነበር መላእከት አየጐበኙሽ እንዲኸ ዐሥራ ኹለት ዓመት ኖርሽመጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር አባትሽ ዳዊት በመሰንቆ አመሰገነ በትንቢት መንፈስም በመንፈስ ቅዱስ በገና እየደረደረ አንዲኸ ብሎ ዘመረ ልጄ ሆይ ስሚ እዩም ፐሮሽንም አዘንብዩ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት ርሺ ንጉሥ ደም ግባትሽን ወዷልና ርሱ ጌታሽ ነው ለርሱ ትሰግጃለሽ መዝ ጃፀ በማለት በቤተ መቅደስ በነበረችበት ወቅት የተደረገውን ተአምራት አድንቋል ሊቁ አባ ሕርያቆስም በተመሳሳይ መልኩ በቅዳሴ ማርያም መጽሐፉ ላይ ድንግል ሆይ አንገታቸውን አንደሚያገዝፉ እንደ ፅብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው አንጂ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች ፅድፍን የምታውቂ አይደለሽም በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለሽም የሰማይ መላእከት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ በማለት እመቤታችን በቤተ መቅደስ በነበረችበት ዐሥራ ኹለት ዓመታት የተደረገላትን ድንቅ ሥራ ገልጾታል አመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ አንዴት አንደገባችና በቤተ መቅደስ ውስጥ የነበራትን ቆይታ ቀደምት የቤተ ከርስቲያን ሊቃውንት በጥልቀት ጽፈዋል ከእነዚኸ መኻከል ሊቁ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤሏፋንዮስ የቤተ መቅደስ ቅድስናዊ አኗኗሯን ሲጽፍ ዔከ ነ ፐጡዩ ዐጩጠበበሩርበ ከክ ከርዮ ርቪክ እመቤታችን በኹሉም አርምጃዎቿ ጐበዝና የተከበረች ነበረች የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲኾን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚኾንበት ብቻ ነበር በጣም ዝግጁ ኾና የምትሰማና በቀላሉ ንግግር ለማድረግ የምትችል ናት ለእያንዳንዱ ሰው አከብሮትና ከብር ሰላምታ ትሰጣለች ቁመቷ መኻከለኛ ሲኾን አንዳንዶች ግን ቁመቷ ከፍ ያለ አንደነበር ይናገራሉ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለምንም ፍርሃት በግልጽነት ያለምንም ሳቅና መጪሟኸ ትናገራለች በተለይ ፈጽማ ለቁጣ የምትጋበዝ አልነበረችም መልኳ እንደ ደረሰ የስንዴ አዝመራ ያማረ ጸጐሯ ቀይማ ነው ዐይኖቿ ብሩሃትና የዋህ የኾኑ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ቡናማ ኾኖ የዐይኖቿ ብሌኖች የዘይት አረንጓዴ ይመስላል የዐይኖቿ ቅንድብ ሸፋሽፍት ከፊል ክብና ደማቅ ጥቁር ናቸው አፍንጪዋም ረዥም ከናፍሮቿ ቀይና ምሉዕ ሲኾኑ በቃላቷ ጣፋጭነት የተጥለቀለቁ ነበሩ ፊቷ ክብ ሳይኾን ግን አንቁላልማ ዐይነት ቅርጽ ነበረው እጆቿ ረዥምና ጣቶቿም በጣም ረዣዥም ነበሩ ከማንኛውም ያልተገባ ኩራት ሙሉ በሙሉ የነጻች ስትኾን ግድ የለሽነት ፈጽሞ ጨርሶ የለባትም ነበር የሚመጡትን ነገራት በፍጹም ትሕትና ትቀበል ነበር ተፈጥሯዊ ቀለማት ያላቸው ማለትም በቤት ድር የተሠሩ ልብሶችን ታረግ ነበር ይኸም በእጅጉ አብሯት የሚኹደው አለባበስና ይኸ አውነታ በራሷ ላይ በምታደርገው ቅዱስ ልብስ አኹን ቅሉ ሊረጋገጥ የሚችል እውነታ ነው ለማጠቃለል ያኸል በመንገዶቿ ኹሉ በመለኮታዊ ጸጋ የተመላች ነበረት በማለት የመልኳን አስደናቂ ደም ግባትና የአኗኗሯን ነገር መንፈስ ቅዱስ በገለጸለት መጠን ጥንታውያን አባቶች እነያዕቆብ የተናገሩትን መነሻ በማድረግ ጽፎታል የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ዲሜጥሮስ በከርስቶስ ልደት በታኅሣሥ ዕለት በሚነበበው ድርሳኑ ላይ የአመቤታችንን የቤተ መቅደስ ሕይወት ሲያስተምር ላቲ ሂከዩ ክክዐጠዩክቪ ነሃከፀክ ከርፐ ክበ። እያሉ ፈጣሪያቸውን ሲመረምሩ ኅጢአት በሌለበት በዚያ ሰማይ ሊቀ መላእከት የነበረው ሳጥናኤል ሐሰትን ከራሱ አምንጭቶ አነ ፈጠርኩከሙ እኔ ፈጠርኋችሁ በማለት ሐሰትን ሲናገር ይኸንን የሐሰት ቃሉን የተቀበሉት ከእርሱ ጋር አብረው እንጦርጦስ ወርደዋል ኢሳዐ ራዕ እኒኸ የወደቁት መላእከት ኀጢአት በሌለበት በዚያ ዓለመ መላእከት እያሉ እንኳ ሐሰትን አመንጭተውና ተቀብለው ከቅዱሳን መላእከት አንድነት ስለ መለየታቸው ሊቁ በመቅድመ ተአምር ሲገልጽ ለመላእከትሂ ኢተከህሎሙ ድንጋሌ ኅሊና አስመ አበሱ በፍትወት ወወረዱ ምድረ በመዋዕል ዘቀዳሚ ኀጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ለመላእክት ለሳጥናኤልና ለሠራዊቱ አልተቻላቸውም በቀደመው ዘመን ያልተሰጣቸውን አምላከነትን ሽተው በድለው ከሰማይ ወርደዋልና ብሏል አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን በተለየ መልኩ ኀጢአት አንደ ጉም እንደ ደመና በከበበው በዚኽ ዓለም እያለች ብቻዋን ከኀልዮ ከማሰብ ከነቢብ ከመናገር ከገቢር ከመሥራት ኀጢአት ተቆጥባ በሃይማኖት በምግባር በንጽሕና በቅድስና በድንግልና ጸንታ በመገኘቷ ንጽሕተ ንጹሐን ከንጹሐን ይልቅ ንጹሕ ተብላ ትጠራለች መዝፀ ሸኳጁ ሠ ኢሳ ሉቃሟ ሉቃአ ሣ ጠቢቡ ሰሎሞንም በመንፈሰ እግዚአብሔር በመቃኘት በመኀ ላይ ወከመ ጽጌ ደንጐላት በማእከለ አሥዋከክ ከማሁ አንቲኒ እንተ ኀቤየ በማእከለ አዋልድ በእሾኸ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ አንዲሁ ወዳጄ በቆነጃጅት መካከል ነሸ በማለት ንጽሕናዋን በሱፍ አበባ መስሎ አስተምሯል ይኸውም የሱፍ አበባ ዙርያዋን እሾኸ ከቧት ሳለ በእሾኸ መካከል አብባ አፍርታ አእንድትገኝ ቅድስት ድንግል ማርያምም ኀጢአት እንደ እሾኸ በከበባቸው በአይሁድ መካከል ሳለች ብቻዋን በንጽሕና በቅድስና ጸንታ የሕይወት ፍሬ ከርስቶስን አፍርታ ተገኝታለችና ንጽሕናዋ አስደናቂ ነው ከሊቃውንት መካከል አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሓንታ በማኅሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ሰሉሞን ልዩ ስለኾነው ንጽሕናዋ የተናገረውን ኃይለ ቃል ሲተረጐሙ ጽጌ ደንጐላ ዘቄላ ወአኮ ዘደደከ ዘጸገይከ ጽጌ በማዕከለ አይሁድ አሥዋክ ተአምረ ድቲን ማርያም ዘልማድከ ምሒክ በእሾኾች በአይሁድ መካከል የደጋ ያይደለ የቄላ የሱፍ አበባን ያበብሽ ልማድሽ ምሕረት የሆነ ማርያም በማለት ንጽሕናዋን መስከረዋል ንጉሥ ሰሎሞን በሥጋዋም በነፍሷም በሕሊናዋም ንጽሕት ስለኾነችው ስለ አርሷ በመኀቭ ላይ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ ወዳጄ ሆይ ኹለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽ በማለት መስከሯልና አመቤታችንን በምናመሰግንበት ሰላምታ ላይ ድንግል በሥጋኪ ወድንግል በሕሊናኪ በሥጋሽም ድንግል ነሸ በሐሳብሽም ድንግል ነሽ በማለት የማመስገናችን ምሥጢር ስለዚኽ ነው ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በመጽሐፈ ድጓው ላይ ማርያምሰ ተሐቱ እምትካት ውስተ ከርሠ ለአዳም ከመ ባሕርይ ፀዐዳ ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ፅንቁ ታበራለች በማለት ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ተለይታ በንጽሕና በቅድስና ፀንታ ስለመገኘቷ ሲያስተምር የመንፈስ ቅዱስ ዕንዚራ በመባል የሚጠራው ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግም በመጽሐፉ ላይ አምላካችን በምድር ያሉትን ኹሉንም ሴቶች ተመለከተ ከአነርሱም መኻል መልካም የነበረችውን እርሷን አርሱ ለራሱ መረጣት መረመራት ትሕትናና ቅድስና በእርሷ ውስጥ አየ ንጹሕ ልብ ያላትና አምላኳንም አጥብቃ የምትሻ ነበረች የተቀደሰ ልብና የፍጹምነት ባሕርይ በሙሉ ነበራት ስለዚኸም ከኹሉ ይልቅ ንጽሕትና ቅን የኾነችውን እርሷን ለራሱ መረጣት ከሥፍራው ወርዶ ከሴቶች ኹሉ መካከል ብጽዕት በኾነችው በእርሷ አደረ ምክንያቱም ከእርሷ ጋር የሚተካከል አንድ ስንኳ በምድር አልተገኘምና አርሷ ብቻዋን ትሑት ንጽሕት ፅዱዕ አና መርገም የሌለባት ናት ስለዚኸም ሌላ ማንም ሳትኾን አርሷ ብቻ እናቱ መኾን የተገባት ኾነች ከክፋት የራቀች ከአመጻ የፀዳች መኾኗን እርሱ ተመለከተ በውስጧም አንድ ስንኳ የረከሰ መሻት አለመኖሩን አየ ምንም ዓይነት የቅንጦት ኣሳብ የላትም በጭካኔ የሚጐዳ ዓለማዊ ምከርም የለባትም የምድራዊ ኩራት መሻትም በእርሷ ውስጥ አይነድም ልቧም በተራና በርካሽ ነገሮች አልተያዘም እርሷን የሚመስል ከአርሷም ጋር አቻ የሚኾን ነገሮች አልታዘዘም አይቶ እናት ትኾነው ዘንድ እና መልካም ወተት ከእርሷ ይጠባ ዘንድ እርሷን መርጦ ወሰዳት በማለት ልዩ ስለኾነው ንጽሕናዋ በስፋትና በጥልቀት አስተምሯል ሰዐኮ ዐ የህጄ ክ የከ እቪክ ኮ ታላቁ ሊቅ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው ላይ እግዚአብሔር አብ በሰማይ ኾኖ ምሥራቅንና ምዕራብን ሰሜንና ደቡብን ዳርቻዎችን ኹሉ በእውነት ተመለከተ ተነፈሰ አሻተተም እንዳንቺ ያለች አላገኘም ያንቺንም መዐዛ ወደደ የሚወደውንም ልጁን ወዳንቺ ሰደደ በማለት ንጽሐ ሥጋን ንጽሐ ነፍስን ንጽሐ ልቡናን አስተባብራ የተገኘችው ቅድስት ድንግል ማርያም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ ልጅ የአካላዊ ቃል እናት ትኾን ዘንድ የመመረጧን ነገር አስተምሯል ቅዳሴ ማርያም ቁጽዐ በመኾኑም እኛ ከርስቲያኖች አንደ ቅዱሳን አባቶቻችን ትውልድ ኹሉ ብጽዕት እያለ የሚያመሰግናትን አናታችንን ንዕድት ነሽ ከብርት ነሽ በማለት ንጽሕናዋን ቅድስናዋን እንናገራለን በሠ ዓም በኤፌሶን ጉባዔ ላይ በንጽሕና በቅድስና በድንግልና ፀንታ ሰማይና ምድርን የፈጠረ የአካላዊ ቃል የከርስቶስ እናት ለመኾን የበቃች የቅድስት ድንግል ማርያምን የአምላከ እናትነትን የካደ ንስጥሮስን አውግዘው የለዩ ኹለት መቶ ቅዱሳን አባቶች በቅዱስ ቄርሎስ መሪነት ቅድስት ድንግል ማርያምን አመ አምላከ ወላዲተ አምላክ ፐከርዐ ናት በማለት አስተምረውናል በቅዱስ ቄርሎስ የተመራውና ኹለት መቶ አባቶች ያለበት ይህ የኤፌሶን ጉባዔ በሦስተኛው የዓለም አብያተ ከርስቲያናት ሲኖዶስ ነው እነርሱም ዓድረት የሚለውን ከላይ የድያድርስን ከታች የንስጥሮስን ትምህርት አውግዘው ተዋሕዶ በሚለው ተስማምተው ድንግል ማርያምም ቅደመ ዓለም የነበረውን አምላክከ በዘመን በሥጋ ስለወለደችው በአማን ወላዲተ አምላክ ናት ብለው የሐዋርያት ትምህርት በውሳኔአቸው አጽድቀዋል የቤተ ከርስቲያን ታሪከ ገጽ ሣእ በመኾኑም ቅድስት ቤተ ከርስቲያናችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በኅቱም ድንግልና ጸንሳ በኅቱም ድንግልና የወለደች በመኾኗ እመ አምላከ ፐከር ወላዲተ አምላከ እመ እግዚአብሔር ጸባዖት አመ ብርሃን ማኅደረ መለኮት ተብላ ትጠራለች ስለዚህ ድንቅ ምሥጢር ቅዱስ ኤፍሬም ሲገልጥ ኦ ለዝንቱ መንከር ልዑል ላዕለ ኩሉ ሕሊናት ብእሲት ምድራዊት ወለደቶ ለአግዚአብሔር ቃል ዘኮነ ሰብአ ድንግል ወለደቶ ለገባሪሃ ወለሊሁ ፈጠረ ወላዲቶ ከሕሊና ኹሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አድናቆት ይገባል ምድራዊት ሴት ሰው የኾነ የእግዚአብሔር ቃልን ወለደችው እርሱ እናቱን ፈጠረ በማለት የተሰጣትን የአምላከ እናትነት ከብርን አድንቋል ሃይማኖተ አበው ዘኤፍሬም ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላከ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በተፈትሖ በማይመረመር ማኅፀኗ የቻለች የአምላክ እናት ስለመኾኗ ኢሳይያስ በምዕኋ ላይ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድር የእግሬ መረገጫ ነው በማለት የተናገረው የባሕርይ አምላከን የወለደችው መኾኗን ዳግሚት ሰማይ «ክ ዝኳፀክ በሚለው መጽሐፉ ሲገልጽ ታላቅ ሰማይና ታናሽ ማኅፀን ለማደሪያው ይገባታልና በዚህም ሊወሰንና ሊመጠን የማይትል በኹሉም ያለ መኾኑን አስረዳ ወልድ የሌለበት የአብ ፅሪና የለም ግን በማኅፀን ተወስኗልና በሰማይ በኹሉ ቦታ አለና በሰማይ አልጐደለም በምድርም አልጨመረም ከእነርሱ ስፋት በላይ ነውና የታናሽ አገልጋይ የድንግል ማኅፀን ለአርሱ ትንሽ አይደለም ራሱን ሊወስን ደግሞም ወሰን የሌለው ሊያደርግ ይቻለዋልና ከሰማያት ወርዶ በማኅፀኗ ዐደረ በማለት ሰማይና ምድርን የፈጠረውን ጌታ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ የቻለችው በአውነት የአምላከ እናት መኾኗን ሰማይንና ቅድስት ድንግል ማርያምን በማነጻጸር አስተምሯል ሰኩ ክዷ ክ ፐከፎ እኗቪክ ዞ ይህ ቅዱስ አባት በዚህ ጥልቅ ሃይማኖታዊ ትምህርቱ ድንግል ማርያምንና ሰማይን ቢነጻጸር አንኳ የእመቤታችን ከብር ከሰማይ በእጅጉ የበለጠ መኾኑን ሳያስተምር አላለፈም ምክንያቱም ድንግል ማርያም በሰማይ ብትመሰል እንኳ ሰማይን የፈጠረ ጌታን በድንግልና የወለደች የድንግልና ጡቶቿን ያጠባችት ወላዲተ አምላከ የመኾኗን ምሥጢር ሲገልጽ ሰማይና እመቤታችን ማርያምም ለአምላከ ማደርያነት አኩል ኾኑ በድንግል ማርያም ማኅፀን ባደረ ጊዜ ግን አኩል አይደለም ለሚያስተውል አምላከ ማደርያው ትኾን ዘንድ መርጧታልና አመቤታችን ማርያም ታላቅ ኾነች ሰማይ ዙፋኑ ነው እመቤታችን ማርያም ግን እናቱ ናት እነሆ እመቤታችን ማርያም በለጠች ዙፋን ከእናት ጋር አይነጻጸርምና ሰማይንና እመቤታችንን መረጠ አንዱን ዙፋኑ አንዷን እናቱ አንዲኾኑ አደረገ አመቤታችን ማርያምን ሰማይ አልልም ከብሯን ማሳነስ ነውና የንጉሥ እናትን በዙፋን አምሳል ላነጻጽራት ከቶ አይገባምና አንተ ጥበበኛ እስቲ ፍረድ። ታናሽ ሙሽራ ስትኾፒ በማለት አሳተ መለኮት ጌታን የተሸከመች የቅድስት ድንግልን ነገር አድንቋል ቅዳሴ ማርያም ቁ ሸጉ ኢትዮሏጴያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስም ሱራፌል ኪሩቤል ዙፋኑን በፍርሐት በረዐድ የሚሸከሙትን የዓለማት ፈጣሪ ጌታን የወለደች መኾኗን በፕኅተ ብርሃን መጽሐፉ ላይ ሲገልጽ አንቲ ተዓብዩ እምኪሩቤል ወትፈደፍዲ አምሱራፌል እምሱራፌል ወኪሩቤል በሠረገላ እሳት ይጸውርዎ ወበምጽንዐ እሳት ይጹንዑ መንበሮ ወአንቲሰ ጾርኪዮ በከርሥኪ ወሐዘልኪዮ በዘባንኪ ወሐቀፍኪዮ በአብራከኪ ህየንተ ሠረገላ እሳተ አብራከኪ ኮነ ወህየንተ ምጽንዐቲሁ ዘአሳተ አደውኪ ኮና ከኪሩቤል ይልቅ አንቺ ትበልጫለሽ ከሱራፌልም ይልቅ አንቺ ትልቂያለሽ ኪሩቤልና ሱራፈል በእሳት ሠረገላ ተሸከመውታልና አንቺ ግን በማኅፀንሽ ወሰንሺው በዥርባሽም አዘልሺው በጉልበቶችሽም ዐቀፍሸው ጉልበቶችሽም እንደ አሳት ሠረገላ ኾኑ እጆችቸሽም አንደ እሳት አፅማድ ኾኑ በማለት የተሰጣት ከብር ከኪሩቤል ከሱራፈል የበለጠ መኾኑን አስተምሯል አናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተሰጣት የአምላከ እናትነት ከብር ባሻገር ማናቸውም እናቶች የማያገኙት እናትነት ከድንግልና አገልጋይነት ከእናትነት ወተትን ከድንግልና ጋር በማስገኘት ልዩ ጸጋና ከብር ተሰጥቷታል ታላቁ የቤተ ከርስቲያን መምህር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለማንም ሴት ያልተሰጠ ለድንግል ማርያም ብቻ የተሰጠ ድንግልና ከእናትነት ጋር አስተባብራ ስለ መገኘቷ ሲገልጥ ወሰቦሂ ወለደቶ ዐቀበ ድንግልና ዘአንበለ ርኩስ ከመ በፀንሳ መንከር ትኩን መራሂተ ለሃይማኖት ዐባይ ከድንግል ተወለደ በወለደችውም ጊዜ ድንግልናዋ ያለመለወጥ አጸና ድንቅ የሚኾን ፅንሷ ለደገኛው ሃይማኖት መሪ ትኾን ዘንድ በማለት ቅድስት ድንግል ማርያም አምላከን ስትወልድው ማኅተመ ድንግልናዋ እንዳልተለወጠ ጌታም ሰው ሲኾን ባሕርየ መለኮቱ ላለመለወጡ እርሷ ድንግል ወአም ድንግልም እናትም ስትባል አንደምትኖር አካላዊ ቃል ከርስቶስም አምላክ ወሰብእ ሰው የኾነ አምላከ ሲባል የሚኖር የመኾኑን የተዋሕዶ ልዩ ምሥጢርን ያወቅንባት የተረዳንባት እርሷ ብቻ መኾኗን አስተምሯል ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምዕጆቿ ቅድስት ድንግል ማርያም በተሰጣት ከብር እናትነት ከድንግልና ጋር ደርባ መገኘት ብቻ ሳይኾን እናትነት ከአገልጋይነት ጋር ደርባ ተገኝታለቹ ይኸውም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አምላከን አንድምተወልድ የብሥራትን ቃል ባሰማት ጊዜ ነገሩን በእምነት ተቀብላ እነሆኝ የጌታ አገልጋይ አንደ ቃልህ ይኹንልኝ በማለት የጌታ አገልጋይ መኾኗን መስከራለች ሉቃወቿ ኾኖም ግን ለመቤታቻን ፍረ ዖሚሟፇሃፍምረኦ ጁታ ዖሚሟፇጓሄተዶ ዖሄፖ ብቻ ታሾቻን ዳና ሐምሾኦው ፇታጾና ይዞሆ ጁሐሥ ዲዴጋለዕሥባ ሪራ መፖሯጀሯ ምሳሪሥ ዲጋ ይዕሯታሳ ይህንንም ምሥጢር የቤተ ከርስቲያናችን የዜማ አባት ቅዱስ ያሬድ እንዘ አመቱ አመ ረሰያ አገልጋዩ ስትኾን አናት አደረጋት በማለት እናትነትን ከአገልጋይነት አስተባብራ የተገኘች መኾኗን አስተምሯል መጽሐፈ ድጓ ገጽ ኮየሇ ዳግመኛም ለማንም ሴት ያልተሰጠውን እና የማይሰጠውን ወተትን ከድግልና አስተባብሮ የመገኘት ጸጋ ለእርሷ ብቻ ተደርጐላታል ይኸውም መአስባት የወለዱ ያገቡ ሴቶች ቢመግቧቸው ወተትን ያስገኛሱ ደናግላን ግን ቢመግቧቸው ወተትን አያስገኙም አመቤታችን ግን በድንግልና እያለች ከድንግልና ጡቶቿ ወተት መገኘት ፅፁብ ድንቅ ብሎ የጌታን ሥራ ከማድነቅ በስተቀር ቃል ከቶ ሊገልጠው አይቻለውም ይበልጥ እጅጉን የሚደንቀው ግን ይህ የድንግልና ጡቶቿን የጠባው የተመገበው ፍጥረትን ኹሉ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግበው የዓለም አስገኝ ፈጣሪያችን መኾኑ ነው ሰም ይርዕኦድግሰ ማርያሮምሥመጋዎንና ፍፖረፖሥጋ ቦሟመግለምጎያ ዕደ ታቃፉ ደዮድጋግሳና ጡዶቿን ቦዖመ።