Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ለመነሻ እነሆ በዓለማችን አዲስ የታሪክ ጐህ በሚቀድበት ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያኖች ላይ ደርሷል። መላው የዓለም ሕዝብም ለዚህ ታላቅ አላማ እንደሚተባበረን የምንጊዜም ፀሎቴ ነው።
አንድ ማለዳ እናቴ ሁሌም ወደምት ሳለመው ቤተክርስቲያን በሄደችበት ጊዜ የቤት አገልጋያችን እኔን በአንቀልባ አዝላ እንጀራ ለመጋገር ደፋ ቀና ስትል ሳይታሰብ ከጀርባዋ ላይ ተንሸራትቼ እሳት ላይ ወድቄ ኖሮ ዋል በዚያ እሳት ከተለበለበው ቁስል ለመዳን አንድ ዓመት ከመንፈቅ ከመፍጀቱም በላይ የቁስሉ ጠባሳ ዛሬም ቢሆን ማስ ታወሻዬ ሆኖ በጀርባዬና በአናቴ ላይ እንደተሸከምኩት እኖራለሁ። ምንም እንኳን የጉዞዋችን እቅድ ሁላችንም በእንግድነት የሄድንበት ቤት ውለን ለማደር ቢሆንም እናቴ ግን ለቤቷና ለቀሪ ልጆቿ በማሰብ ከእኛ ጋር በማደር ፋንታ ያንኑ ቀን ወደ ቤት ብቻዋን ተመለሰች። አንድ ዕለት ከዚያ በፊት አስቤው የማላውቀው ሀሳብ በድንገት ፍንትው አለልኝ። በጉዞዬም ላይ አንዳንድ መንገደኞች ከመታየታቸው በስተቀር ጐዳናው ጭር ያለ ነው በመሀሉ በድንገት እየመጣ ከሚያስጨንቀኝ የፍርሀት ስሜት ለመገላገል እራሴን በእራሴ እያደፋፈርኩት ከግማሽ ቀን ጉዞ በኋላ ከእህቴ ቤት በሰላም ደረስኩ። ምንም እንኳን እራሴን ለባርነት ሕይወት አሳልፌ መስጠቴ ቢታወቀኝም ይህን መሰል መከራ ከእህቴ ይጠብቀኛል ብዬ ግን ለአፍታ እንኳን አስቤው አላውቅም። ሁኔታው ሁሉ እየከበደኝና ከምችለው በላይም ስለሆነብኝ ምንም እንኳን መራራና አስከፊ ነገር እንደሚጠብቀኝ ባውቅም ወደ አባቴ ቤት ለመመለስ ወሰንኩ። እሱም እኔን ወደ አባቴ ቤት እንድመለስ ማድረግ። አንድ ቀን አባቴ ሳላስበው በድንገት ለጉዞ እንድዘጋጅ ነገረኝ። ምንም እንኳን የምሄድበትን ቦታ ባላውቅም ጉዞዋችን ግን ቀላል አልነበረም። ይሄ ሁሉ ግፍ ያነሰ ይመስል አንድ ቀን ባልና ሚስቱ ገዢዎቼ ብል ይቀለኛል። ቀስ በቀስም ከሌላ ሰው ቤት ለመቀጠርሥራ ማፈላለግ ጀመርኩ። ሁሌም ከስሯ መለየት የማይ ሆንለት አንድ ሰው አመለካከቱ አንድም ጊዜ ደስ ብሎኝ አያ ውቅም። አንድ ቀን ሴትየዋ ባልነበረችበት ሰዓት አጋጣሚውን ጠብቆ ያ ሰው እቤት መጣ። አንድ ጊዜ በአንድ የሳምንቱ መጨረሻ ቀን ከከተማው ወጥተን ለመናፈስ በምንጓዝበት ወቅት ያሽከረክራት የነበረች ጨ ጂኘ መኪና ወደ ገደል በመገልበጧ እሱ ወዲያው ሲሞት እኔ ግን ተረፍኩኝ። ምንም እንኳን ከሞት ብተርፍም በደረሰብኝ ጉዳት ምክንያት ከዚያው ከለመድኩት ሆስፒታል ተወስጄ ከሁለት ወር በላይ ከፍተኛ የሕክምና እርዳታ እየተደረገልኝ ቆየሁ። በዚህን ጊዜ ስሜን በመልካም የሚያነሳው ማንም ሰው አልነበረም። ስለዚህም አንድ ሃሳብ መጣልኝ። በዚህ ወቅት በእጄ ላይ አንዲት ሣንቲም እንኳን አልነበረኝም። አንድ ቀን ታዲያ በአካባቢው ከብት የሚጠብቅ እረኛ በቀጥታ ወደ እኔ በመምጣት በረጋና ትዕዛዝ በታከለበት አንደ በት ወደ አሥመራ እንድሄድ ተናገረኝ። መፍ ሬ ኃኃ ልመናዬም መና አልቀረም ከዕለታት አንድ ቀን ከዚያን በፊት አይቼው የማላውቀው ሰው ወደ ሱቄ መጣ ቀስ በቀስም እራሱን ካስተዋወቀኝ በኋላ ተመላልሶ እንደሚጠይቀኝ ቃል ገብቶልኝ ሄደ። ምንም እንኳን ቀን ቀን ከየጥሻው ሥር ብንሸጐጥም የአ ሩ ግለት ግን ጨርቅ የማያሰለብስ ነበር። አንድ ቀን ከተማውን እየተዘዋወርኩ ሥራ በማፈላለግ ላይ እንዳለሁ ድንገት ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ደረስኩኝ። ዕ በመጨረሻም ገና ከቤተክርስቲያኑ ወጥቼ ከዚያን ቀን በፊት ሄጄበት ወደማላውቀው መንገድ እንዳመራሁ ከአንድ ሕንፃ ፊት ለፊት በረድፍ የተሰለፉ ወንዶችና ሴቶች አየሁኝ። ታዲያ አንድ ቀን ከቤቱ አባወራ ጋር በመወያየት ላይ እንዳለን ስለወደፊቱ ዕቅዴ አንስቶ ጠየቀኝ። ይህን ጊዜ ነበር ተስፋ በመ ቁረጥ ለጊዜው እንኳን መተዳደሪያ የሚሆነኝ ሥራ ማፈላልግ የጀመርኩት። ታዲያ አንድ ምሽት የቴሌቪዝን ኘሮግራም በመክታተል ላይ እንዳለሁ ሰባኪው ፖትሮበርትሰን እንደ እኔ ዓይነት ችግር ስላጋጠ ማቸው ሰዎች አንሥቶ በእግዚአብሔር መታመን እንደሚ ገባቸው አጠንክሮ ካሳሰበ በኋላ አንድ ያልተጠበቀ መልእክት አስተላለፈ። ለካስ በዚህ መሀል አንድ የከተማ ወንበዴ የእንቅስቃሴዬን ሁኔታ ሲያጠና ቆይቶ አንድ ምሽት ሲከታተለኝ ኖሯል። ከአሜሪካ ቆይታዬ አንድ ቀላል ሆኖም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ትምህርት ገብይቻልሁ። ያም ሆኖ ግን እግዚአብሔር ሕዝቧን ሙሉ በሙሉ ረስቶታል ማለት አይደለም።