Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ይህንን የመመረቂያ ፁሒፍ በትዕግስትና በትጋት በፍፅም ትህትና በማረም በማስተካከል ጠቃሚ ሀሣብ በመስጠት ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉልኝ አማካሪዬ ለአቶ አየለ ፍቅሬ ምስጋናዬ የላቀ ነው በመጨረሻም ይህንን ፅሑፍ በመተየብ በማስተካከል ለረዱኝ ለኪዳነምህረት ፎቶ ስትዲዮ ሠራተኞች በሙሉ በተለይም ለወሪት አዜብ አሻግሬ ምስጋናዬ ወደር የለውም ማውጫ አርዕስት መግቢያ የጥናቱ ዳራ ው ው የገፀባህርይ ምንነት የገፀባህርይ አሳሳል ደረጃዎች መ ዓዓ ውጫዊ ገጽታ ተ ዓዓ የገፀባህርይ አቀራረብ ዘዴዎች ናቸው ርፅቱ የአቀራረብ ዘዴ በአብዛኛው የገፀ ባህርያት አስፈላጊነት ከግምት ውስጥ መግባት አለበት በዝተው የልቦለዱን ታሪክ መያዣ መጨበጫ እንዳያሳጡት አንሰውም ጎደሎ እንዳያደርጉት በተገቢው የቁጥር መጠን መቅረብ አለባቸው ለታሪኩ ፍሰት ምሰሶና ማገር ሆነው መዋቅሩን የሚገነቡ ለታሪኩ ህያውነት ዋና የሆኑ ገፀ ባህርያት የሚባሉት ናቸው የገፀባህሪ አሳሳል በጠፍ ከዋክብት ረዥም ልቦለድ የጠፍ ከዋክብት ለመሆኑ አቶ ኪዳኔ ምን አደረግሁህ። አንተ ለኔ ንጹህ ወንድሜ ነህ አንድ የነብስ አባት አለን ሁለታችንም ክርስቲያኖች ነን የአንድ አገር ሰዎች ነን ዘመዶቻችን እርስ በእርሳቸው ተጋብተዋል መጋባት ብቻ ሣይሆን ተዋልደዋል እና ለምን እኔን ሁል ጊዜ በጣሊያኖች ላይ ትከሰኛለህ።
ተብለው ቢጠየቁ አሳዛኝ ወይም አስደሳች አልያም ልብ ሰቃይ ነው አይደለም በሚል በድፍኑ ጅምላ ሐሳባቸውን ሊሰጡ ይችላሉ ዛያሲ ግን እንዲህ አይደለም እንዲህ ነው ብሎ ለሚሰጠው እያንዳንዱ አስተያየት ምክንያት አለው ከዚህ በተጨማሪም አንድ የልቦለድ ድርሰትን አንብቦ አስተያየት ለመስጠት ሲነሳ ለልቦለዱ መገኘት አንደ ድርና ማግ ሆነው የሚያገለግሉትን አላባውያንን ጨምሮ አስከ የልቦለድ ዘዴዎች ከዚያም ሲያልፍ ከልቦለዱ ርዕስ እስከ የሽፋን ገጽ ስዕል ድረስ በጥልቀት ይመለከታል ከዚያም በሚችለው መጠን በአንዱ ወይም በሌላው የድርሰቱ አካል ላይ ጅምላ አሊያም ንጥል ሂስ ይሰጣል የዚህ ጥናት አጥኝም የጠፍ ከዋክብት በተባለው ታሪክ ጠቀስ ረጅም ልቦለድ ላይ ከአላባውያን አንዱ በሆነው ገፀ ባህሪ በተለይም በገፀ ባህሪ አሳሳል ላይ ትኩረት በማድረግ ድርሰቱን ለመፈተሽ ይሞክራል ሸንቁጥ አየለ በልቦለድ ደራሲነት ወደ መድረክ ብቅ ያለው በ ዓም የጠፍ ከዋክብት በተባለው ረዥም ልቦለድ አማካኝነት ነው ደራሲው ልቦለድን ለተደራሲ ማቅረብ የመጀመሪያው እንደመሆኑ መጠን በገፀባህሪይ አሣሣል ረገድ ጠንካራና ደካማ ጐኖቹን ለመመልከት ችያለሁ ስለሆነም ለዚህ ጥናት አነሣሽ ምክንያቴ ይህንን ድክመት መተንተን ነው ሁለተኛው ምክንያቴ ስለመፀሐፉ ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ጥናት አለመደረጉ ሲሆን ሶስተኛና የመጨረሻው ምክንያቴ የሥነፁሑፍ ተማሪ እንደመሆኔ መጠን በየጠፍ ከዋክብት ልቦለድ ውስጥ የሚገኙትን ገፀባህሪያት እንዴት ተቀርፀዋል የሚለውን ለማጥናት ወሰንኩ የጥናቱ ዓላማ የዚህ ጥናት አላማ የጠፍ ከዋክብት በተሰኘው ልቦለድ ውስጥ ያሉትን ገፀባህሪያት ምንነት አሣሣል አቀራረብ ዘዴዎችና አይነቶችን የተለያዩ ምሁራንን ንድፈ ፃሣባዊ መሠረቶች በመመርኮዝ ጥንካሬና ድክመቱን ማሳየት ነው የጥናቱ ጠቀሜታ የጠፍ ከዋክብት በተሰኘው ረዥም ልቦለድ ድርሰት ላይ የተደረገው የገፀ ባህሪያት አሳሳል ብዙ ጠቀሜታዎች ይኖሩታል ብሉ አጥኝው ያምናል በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ረዥም ልቦለድ ድርሰት ሊያስተላልፍ ከፈለገው ማንበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ አንፃር የገፀ ባህሪያት አሳሳል ላይ በሚቀርበው ትንታኔ አንባቢ በመስኩ ያለውን የዕውቀት ክፍተት መሙላት ያስችለዋል በሁለተኛ ደረጃ የዚህ ጥናት ትኩረት የገፀ ባህሪያት አሳሳል ላይ ትንተና መስጠት ስለሆነ ለሌሎች አጥፒዎች በመነሻነት ሊያገለግል ይችላል የጥናቱ ገደብ ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ የጠፍ ከዋክብት የተባለውን ረጅም ልቦለድ ድርሰት ከሁሉም የልቦለድ አላባውያን ወይም ዘዴዎች አንፃር ለመመዘን የሚሞክር አይደለም ከርዕሱ ለመረዳት እንደሚቻለው ትኩረቱ ከልቦለድ አላባውያን አንዱ በሆነው ገፀባህሪ ላይ ብቻ ይሆናል እንጂ ከዚህ አልፎ ልቦለዱ በእያንዳንዱ የረጅም ልቦለድ አላባውያን ሲመዘን የሚኖረውን ድክመትና ጥንካሬ ይህ ጥናት በጥልቀት አያትትም የጥናቱ ዘዴ ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ መሠረት የሚያደርገው ገላጭ ምርምር ሲሆን የገጽ ንባብ ትንተና ስልት ላይ በመመስረት በተመረጠው ልቦለድ ውስጥ የገፀባህርያትን አሳሳል ለመዳሰስ ይሞክራልስለ አሰራር ሂደቱም በቅድሚያ ልቦለዱን በተደጋጋሚ በማንበብ የገፀ ባህርያቱን አሳሳል መተንተን እና ለልቦለዱ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ለማሳየት ይሞክራል የጥናቱ አደረጃጀት የዚህ ጥናት አደረጃጀት በአብዛኛው የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴ የሚረዱ በታተሙ ረጅም ልቦለድ አላባውያን መርጃ መጽሐፍቶች የመመረቂያ ጽሑፎች አና ስለ ገፀ ባህርያት አሳሳል በተገኙ መረጃዎች መሠረት የሚከናወን እና የሚደራጅ ነው ጥናቱ ለአሠራር ያመች ዘንድ በሶስት ምዕራፎች ተከፍሏል በመጀመሪያው ምዕራፍ የጥናቱ ዳራ የጥናቱ ዓላማ የጥናቱ ጠቀሜታ የጥናቱ ገደብ የጥናቱ ዘዴ እና የጥናቱ አደረጃጀት ይገኙበታል በሁለተኛው ምዕራፍ የተዛማጅ ፅሑፎች ቅኝትና ንድፈ ሃሣባዊ መሠረትን ሲይዝ ሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ የጥናቱ ዋና ትኩረት የሆነውን የገፀ ባህሪይ አሳሳል ትንተናን ይዚል በመጨረሻም ማጠቃለያ ዋቢ መጽሐፍትየመመረቂያ ጽሑፎች ተካተዋል ክለሳ ድርሳናት የተዛማጅ ጽሑፎች ቅኝት ይህን ጥናት ለማድረግ ከአኔ ጥናት ርዕስ ጋር የተሻለ ቅርበት ያላቸውን በርካታ የዲግሪ ሟሟያ ፅሁፎች ለመቃኘት ሞክሪያለሁ ከነዚህም ውስጥ የደሣለኝ አሰፋ ዓምሥነ ጽሑፋዊ ሂስ በኢቫንጋዲ እና ከቡስካ በስተጀርባአንዱ ነው ደሳለኝ በሁለቱ መጽሐፎች ላይ ሥነ ጽሑፋዊ ሂስ በማድረግ የመጽሐፎቹን ጥንካሬና ቀርነት አሳይቶ በድክመቱ ላይ የመፍትፄ ሃሳብ መጠቆምን አላማው አድርጎ ተነስቷል በዚህም መሠረት የገፀባህሪያትን አሣሣል ከባህሪ ዘላቂነትና ታዓማኒነት አንፃር እንዲሁ የደራሲውን የቋንቋ አጠቃቀም ለመገምገም ሞክራልአጥፒው ከተነሳበት ዓላማ አንፃር በገፀ ባህሪም ሆነ በደራሲው የቋንቋ አጠቃቀም ላይ የታዩትን ድክመትና ጥንካሬ ለማሳየት ሞክሯል ይ። የሚል ጥያቄ በማንሣት ታሪኩን ይጀምራል የአቶ በሼ ቤት የሮም ወታደር ኃላፊ የሆነውን ጄነራል ፍራንኮ እና በዱር በገደል ለኢትዮጵያ ነፃነት የሚዋጉትን አርበኞች ያስተናግዳል የሮም ወታደሮችን በግልጽ አርበኞችን በሚስጢር ለራስ ብቻ በሚገባ ልዩ ሚስጢራዊ መልዕክት ተበታትነው ያሉትን አርበኞች መልዕክት በመቀበልየተቀበሉትን ለሌላኛው በማስተላለፍ አንዲሁም ቀለብ የመሣሪያ አቅርቦት ከሮም ወታደር የሰሙትን ሚስጢር ለአርበኞቹ በመላክ አገራዊ ግዴታቸውን የሚወጡ ሰው ናቸው ነገር ግን ሁለት መልክ ያላቸው ብልህና አስተዋይ አርበኛ ሲሆኑ ሴማዊትም የአባቷን ዱካ በመከተል የድርሻዋን የምትወጣ ውብ ጠይም ወጣት ሴት ናት ጄነራል ፍራንኮ እና ምክትሉ ሲልቪዬ በቀላሉ አገሪቱን ለመቆጣጠር የሚቻልበትን መንገድ ቀና ለማድረግ የአገራቸውን ግዳጅ ለመወጣት ቢመጡም አንድ ቀን እንኳ በሃሣብ ተግባብተው የማያውቁ አዛዥና ታዛዥ ናቸው ምክትሉ ለሮማ መንግስት እውነተኛ ወዳጅ ናቸው የሚላቸው ኪዳፄና ፊታውራሪ መነሻ የሚባሉት ሰዎች ብቻ ናቸው ሲል በአንፃሩ አቶ በሼን የሚጠራጠር ሰው ነው ጄነራል ፍራንኮ ግን አቶ በሼና ቤተሰቦቻቸውን እውነተኛ የሮም ወዳጅ አንደሆኑ ይመሠከርላቸዋል በዚህም የተነሣ ምክትሉ ምንም ማድረግ ባለመቻሉ አቶ በሼን እንደተጠራጠረ ብሎም የአለቃው መታወር እያሣዘነው ግራ ሲጋባ ይስተዋላል ተፈሪ ግርማ ሞገሱ የሚያስፈራ ወጣት ሲሆን ለአገሩና ለወገኑ ፍቅር ሲል ወንዶች በረፃ የሚባል ጫካ ውስጥ ገብቶ የሚዋጋና የሚያዋጋ አርበኛ ነው ተፈሪ የአቶ በሼ እህት ልጅ ሲሆን አስፈላጊውን መረጃ ቀለብና ቁሣቁስ በአቶ በሼ በኩል ስለሚደርሰው ለሮም ወታደር የጐን ውጋት ለመሆን በቅቷል ይህንንም ኪዳኔ የተባለው የሮማ ባንዳ አቶ በሼ ከሮማ መኮንኖች መረጃ ለተፈሪ አንደሚሰጡ ለማጋለጥ ያደረገው ጥረት በአቶ በሼ ጥበባዊ መልስ እንዲሁም በሴማዊት ብልፃት ሊከሽፍበት ቢችልም አቶ ኪዳኔና ፊታውራሪ መነሻ የተባሉት ባንዳዎች የሴማዊትን ባል የተፈሪ የቅርብ ወዳጅ የሆነውን ሠርቀኃይልን ትነግሣለህ በሚል ሀሰተኛ ትንቢት በአንድ ቄስ በኩል በማስነገር ተፈሪን አስከድተው ለማስገደል ጥረት ያደርጋሉ ተፈሪ ጣልያንን ለማስወጣት በሚደረገው ማንኛውም ትግል ላይ ተሣትፎ የሚያደርግ ወጣት አርበኛ መሆኑን የተገነዘበው ቅጣው የተባለ አርበኛ እንደ ተፈሪ አገራቸውን ነፃ ለማውጣት በዱር በገደል ያሉ አንቱ የተባሉትን የጐጃምና የሸዋ የጦር ሰዎች በቅንጅት ጠላትን ለማጥቃት ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለመወያየት መራቤቴ በተባለ አገር በተሰበሰቡበት ወቅት የተፈሪ የቅርብ እረዳት የሆነው ሰረቀኃይል አጠገቡ አልነበረም በውይይታቸው ወቅት አጀንዳቸው ጠላትን እንዴት ማጥቃት አንዳለባቸው ለመነጋገር ቢሆንም በንጉሱ ጉዳይ ጭቅጭቅ መፍጠራቸውና አለመግባባታቸው ጐልቶ የታየበት ነበር በዚህ ጊዜ የሰበሰባቸው ቅጣው የተባለ አርበኛ ሰረቀኃይልን ጫካ ውስጥ ይመሰከተዋል ወዲያውኑም ለተሰብሣቢ ጓደኞቹ ቦታ እአንዲለወጡ ያደረግና ከጥቃት ያመልጣሉበዚህ ሁኔታም ይለያያሉ ተፈሪ ሰረቀኃይል ከባንዶች ወገን እንደሆነና አንደከዳው ብሎም ሊያጠፋው እንደሆነ ከአጐቱ ልጅ ከሴማዊት ይሰማል ሰረቀኃይል የሴማዊት ባል ሲሆን ጫካ የገባውም በሚስቱ ገፋፊነት እና ባልገዛም ባይነት ነውሠረቀኃይል ከተፈሪ ዋነኛ ተዋጊዎች መሀል አንዱ ነው ሆኖም ግን ሴማዊት ሠረቀኃይል እንደከዳ መረጃውን ከጣሊያኑ ጄነራል እንዳገኘች በማያወላውል መልኩ ለተፈሪ አስረዳቸው ተፈሪም ለስብሰባ መራቤቴ በሄደበት ወቅት እንዲከተለው ነግሮት ነበርነገር ግን ሰረቀኃይል አእንዳልተከተለው ብሉም ጥቃት አንደተሰነዘረም አስታውሶ ስብሳባ እንደነበር ለጣሊያኖች የተናገረውና ሊያስጨርሣቸውም የነበረው ሠረቀኃይል መሆኑን ተረዳ ተፈሪ በዚህም በጣም አዘነ ከዚያም መዝሙረ ዳዊት አወጥቶ ማንበብ ጀመረ ሴማዊትም እርሷ እንድትገለው የሶስት ቀን እድሜ እንዲሰጣት ትለምነውና ይለያያሉ ሴማዊትም ተፈሪን እንዲከዳው አሣምነዋለሁ በሚል ሰበብ በጄነራል ፍራንኮ አማካይነት ከሠረቀኃይል ጋር የሚገናኝበትን ስፍራ ታመቻችና ሠረቀይልን ታገኝዋለች እንዳገኘኽችውም መሣሪያ ጭንቅላቱ ላይ በማነጣጠር አንተ ባንዳ ወድሜን ከዳህውኢትዮጵያን ከዳሀት እና ለጠላት አጎበደድክ ፍቅሬንም ረገጥክ ቃልኪዳንህንም በጭቃ ለውሰህ ቀበርከው በማለት እየተሳደበች እያለ ከርቀት ምክትል ጀነራል ሲልቪዬ ሠረቀኃይል ላይ መሣሪያ እንዳነጣጠረች ያስተውላል በዚህ ቅፅበት ሠረቀኃይልን ተኩሣ ትገለዋለች ወዲያው ምክትል ጀነራል ሴማዊት ላይ ይተኩሳል አርሷም ዞራ ትተኩሣለች በዚህ ሁኔታ ተከትለዋት የነበሩት ጀሌዎቿምክትል ጄነራሉና ተከታዬቹ ላይ ተኩስ ይከፍታሉ በዚህም ሣቢያ በአካባቢው ጦርነት ይቀሰቅሳል ሴማዊትም የተከተሏትም ሰዎች ምክትል ጄነራሉም ይሞታሉ አካባቢው ላይ ተፈሪ መጥቶ ጦርነቱ ይፋፋማል በመጨረሻም አርበኞቹ ድል ያደረጉና የጣሊያን ሠራዊት ከአገሪቱ ጥርግርግ ብሎ ሲወጣ ጄነራል ፍራንኮም በምርኮ ወደ አገሩ ይገባል ንጉሱም ከተሰደዱበት አገር ወደ አገራቸው ይመለሳሉ ተፈሪም በጦርነቱ ወቅት ሞተ ተብሎ በመወራቱ የጣሊያን ወታደሮችም ሞተ ብለው አስበው ነበር ሞተ ብለው ያስወሩት ግን አጐቱ አቶ በሼ በመቁሰሉ ምክንያት በደንብ እንዲያገግም የጣሊያን ወታደሮች አስሰው እንዳያገኙት ያደረጉት ዘዴ ነበር በቆሰለ በሰባተኛ ወሩ አገሪቱ ነፃ ወጣች ተባለ እርሱም አገሬ ነፃ ወጣች ብሎ አጐትህ አስጠርተውሀል ሲባል ከነበረበት ወደ አጐቱ ቤት በፈረሱ እየጋለበ ሲሄድ ወታደሮች ከበው እጅ ስጥ ይሉታል እርሱ ግን ምን እጠፋሁና ይላል በዚህም ምክንያት ጦርነት ውስጥ ይገባል ለአገሬ በተዋጋሁ ለነፃነቷ በቆሰልኩ እንዴት እጅ ስጥና ይቅርታ ጠይቅ እአእባላለሁ በማለት በነገሮች በማዘን መልሶ ጦርነት ውስጥ ይገባል ጥይት መጨረሱን ሲረዳ ፈረሱ ላይ እንዳለ ፊቱን ወደ ገደል አዙሮ የቀሩትን ሁለት ጥይቶች አንድ ለፈረሱ አንድ ለራሱ በመተኮስ ፈረሱንም አራሱንም ያጠፋል ባንዳ የነበሩት ኪዳኔና ጄሌዎቹ ጣሊያን ሲወጣ የውስጥ አርበኛ በመባል ራስ ተብለው ተሾሙ አቶ በሼ ለሹመት ቢጠሩም ወደ አዲስ አበባ ሣይሄዱ ቀሩ ከጦርነቱ በፊት ጠፍቶ የነበረው የተፈሪ ወንድም አየለ ወደ አገሩ ሲመለስ የሆነውን ሁሉ ሰማ በመጨረሻም አቶ በሼና አየለ የኢትዮጵያንና የተፈሪን ጠላቶች ለመግደል ይወጥናሉ አቶ በሼ ራስ ኪዳኔን የተፈሪ ወንድም አየለ ደግሞ አራት ያህል ጄሌዎቹን የሹመት ልብሣቸውን አስወልቀው በመግደል የሹመት ልብሣቸውንም የአቶ በሼ ውሻዎች የተቀበሩበት ቦታ ላይ ያቃጥላሉ በመጨረሻም ጥቂት የተፈሪ ጓደኞች በወታደር ተከቦ እራሱን መግደሉን ሲሰሙ የሹመት ልብሳቸውን አውጥተው በማቃጠል ሹመታቸውን በራሣቸው ፈቃድ ሲጥሉ ጥቂት ጓደኖቹ በተፈሪ ሁፄታ በማዘን አራሣቸውን ወደ ገደል በመወርወር ያጠፋሉ ባንዳዎቹ በነዛይቱ ኢትዮጵያ ሊታመን በማይችል መልኩ የበላይነት ተጐጉናፅፈዋል በማለት ታሪኩ ይጠናቀቃል የዋና ገፀባህሪ አሳሳል አካላዊ ገለፃ ደራሲያን በልቦለዶቻቸው ውስጥ ገፀባህርያትን በልዩ ልዩ አሣሣል ሊስሉ ይችላሉ በተለይ የልቦለዱ ዋና ዋና ገፀባህርያትን አጉልቶ ለማሣየት እንዳንድ ደራሲያን ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች መካከል የገፀባህርያቱን አካላዊ ማንነት በደራሲው በዋና ገፀባህሪው በተራኪው ወይም በንዑሣን ገፀባህሪያት አማካይነት እንዲገለጽ ያደርጋሉ አካላዊ ገለፃ በዋናነት አፋዊ መልክ መዘርዘር በስም ማስተዋወቅና አልባሳት በመግለፅ የሚካተቱበት ሲሆኑ ተደራሲው በቀላሉ የዋና ገፀባህርይውን አፋዊ ማንነት እንዲለይ ያደርገዋል ዘሪሁን በዚሁ መሠረት የየጠፍ ከዋክብት ውስጥ ሴማዊት ጄነራል ፍራንኮ ምክትል ጄነራል ሲልቪዬአቶ በሼተፈሪና ኪዳኔ አካላዊ መልክ ለመቃኘት እንሞክራለን የሴማዊት አካላዊ አሳሳል ነጩ ጀግና ጀነራል ፍራንኮ ከሴማዊት ፍቅር የጀመረው አገሩ የጣለችበትን ግዳጅ ለመወጣት ጁሩ የሚባል አገር በተገኘበት ወቅት ነው ሴማዊትን ያያት አባቷን አቶ በሼን ለማማከር ወደ ቤታቸው በሚመላለሰው ወቅት ነው ጀነራሉ በፍቅራ እንዲህ ሊወድቅ የቻለው ባላት አካላዊ መልክ ሲሆን አካላዊ ማንነቷንም ደራሲው እንዲህ ሲል ይገልፃታል ጠይሙና መስህባዊ ፊቷ ከተስተካከለ እንዝርት አቋሟ ጋር የጠፍ ከዋክብት በማለት ታሪኩ ይጀመራል በዚህም ብቻ ሳይቆም በታሪኩ ሂደት አካላዊ መልኳ እንደሚከተለው ተገልጂል የተዋበ የሀበሻ ቀሚስ ለብሣ ኩታ ደርባለች ፀጉራም ውብ አድርጋ ተሰርታለች አለባበሷን ሲያስተውል በአውሮፓ እንኳን አንዲህ ዓይነት ውብ አለባበስ አላየሁም ሲል ተደነቀ ። የጠፍ ከዋክብት ከዚህ የምንረዳው ውበቷ መልኳ ብቻ ሣይሆን የአመለካከት አቋሟ ጭምር መሆንን ልብ ይላል ይህ አይነቱ የገፀባህርይ አካላዊ ገለፃ ርቱዕ አቀራረብ ከሚባለው ዘዴ እንዱ ነው ይህም አንባቢ ገፀባህርይውን ሰው ነው ብሎ እንዲቀበል ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን በክለሣ ድርሣኑ ላይ ተጠቅሷል በዚህ ፅንሰ ዛፃሣብ መሠረት ስለ ሴማዊት የተሰጠው ገለባ ሴማዊትን በስም ብቻ ሣይሆን በመልኳና በተክለ ሰውነቷ ልንለያት እንድንችልና ምስል እንድንፈጥርላት አድርጓል በመሆኑም በሴማዊት አካላዊ ገለ መሠረት አንባቢው በገሀዱ አለም ከሚያውቃቸው የገጠሪቷ ኢትዮጵያ ሴቶች መርጦ ሴማዊት ይች ትሆን ሊል ያስችለዋል ምክንያቱም የቀረበው ገለፃ በታሪኩ ውስጥ አንድ ቦታ ላይ ብቻ ሣይሆን በታሪኩ የተለያየ ቦታ በመጠቀም ምስል ከሣች አድርጐታልና የጄነራል ፍራንኮና የምክትል ጄነራል ሲልቪዬ አካላዊ አሣሣል ደራሲው የጄነራል ፍራንኮንና የምክትል ጄነራል ሲልቪዬን ቁንጽል በሆነ አካላዊ ገለፃ አስቀምጧቸዋል እነዚህ ሁለት የማይዋደዱ አዛዥና ታዛዥ የጦር መኮንኖች በተራኪው አንደበት በታሪክ ሂደት ውስጥ በተለያየ ቦታ ተገኝተው አእናያለን ነገር ግን አካላዊ ገለፃቸው ውስን በሆነ መልኩ አንድ ቦታ ላይ ብቻ በጥምረት አስቀምጦታል ይህም እንዲህ ይነበባል ፁጉራቸው በሽጋ ሁኔታ የተበጠረግሩም ወታደራዊ አለባበስ የለበሱ እጅግ የሚማርክ አቋም ያላቸው ሁለት አውሮፓውያን ቆመው ይወያይሉ ፁጉራቸው ንፋስ ብትን ብትንትን ያደርገውና መልሶ ደግሞ ዘንፈልፈል ያደርገዋል ከሩቅ ለሚመለከታቸው የአግዜር መልዕክተኛ የመላዕክት ዝርያ ይመስላሉ ውበታቸው ግርማቸው ቆራጥነታቸው እአና አጠቃላይ ሁኔታቸው ያሉበት አካባቢን ውበት ፀዳል አብርቶታልየጠፍ ከዋክብት ከዚህ እንደምንረዳው ደራሲው የተጠቀመው አካላዊ ገለፃ የሁለቱን አውሮፓውያን ወታደሮች መልክአቋምና አለባበስ ለመግለፅ ሞክራል ይህም ሴማዊትን ከተገለፀችበት አካላዊ ገለፃ ዝቅያለ በመሆኑ የታሪኩን አጓጊነት ቁጥብ አንዲሆን አድርጎታል በተለይ ጄነራል ፍራንኮ ከምክትል ጄነራል ሲልቪዬ ተነጥሎ ቢገለፅ ኖሮ የተሻለ ይሆን ነበር ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሁለቱም አውሮፓዊ አካላዊ ገለፃ አንድ አይነት ተደርጐ መሣሉ የታሪኩን ፍሰት ያስተጓጉለዋል ምክንያቱም አንዱን ከአንዱ የምንለይበት መልክ ባለመኖሩ ነው በአጠቃላይ ከላይ በአየነው አካላዊ ገለፃ መሠረት አንባቢው በገሀዱ አለም ከሚያውቃቸው አውሮፓውያን መርጦ ጄነራል ፍራንኮ ይሄ ነው ምክትል ጄነራል ሲልቪዬ ይሄ ነው ሊል አያስችለውም የአቶ በሼ አካላዊ አሳሳል በዚህ ልቦለድ ውስጥ ሌላው ዋና ገፀ ባህሪይ አቶ በሼ ናቸው በሼ ከታሪኩ እንደምንረዳው የሴማዊት አባት የተፈሪ አጐት ናቸው አቶ በሼ ኢትዮጵያ በጣሊያን በተወረረችበት ወቅት ለጣሊያኑ ጄነራል የቅርብ አማካሪ በመሆን ሲያገለግሉ አናያቸዋለን ነገር ግን ከጣልያን ጄነራል የሰሙትን መረጃ ባልገዛም ባይነት ጫካ ላሉት አርበኞች መረጃ የጦር መሣሪያና ስንቅ አያደራጁ ሲልኩ የሚታዩ እውነተኛና ብልፃተኛ በአድሜያቸው መግፋት ምክንያት ጫካ ገብቶ አርበኛ መሆን ያልቻሉ ሆነው ከመሳላቸው በተጨማሪ ደራሲው አካላዊ አሣሣላቸውን እንዲህ ተገልጾዋል በሼ ፈገግ አሉና ረዥም ቁመታቸውን ቀጥ አርገው አቆሙት የጠፍ ከዋክብትሲል የአካላዊ አሳሳላቸውን አንዱን ክፍል ጠቅሶ ብቻ ሣያቆም ተጨማሪ መልክ ሲሰጣቸው ይታያል ይኸውምአቶ በሼ አድሜያቸው በስልሣዎቹ ውስጥ ያለ ቁመታቸው ረዥም ሰውነታቸው ደልዳላ ዳ የጠናፍ ከዋክብት በታሪኩ ውስጥ አቶ በሼ ከአካላዊ ገለፃቸው ይበልጥ በህሊናዊ ገለፃቸው የማይረሱ ቢሆኑም አካላዊ ገለፃቸውም ከሎሎች ገፀባህሪያት ለይተን አቶ በሼን ለማወቅና ለተደራሲያን ቅርብ ለማድረግ ጠቃሚ ነው ሆኖም ግን አካላዊ ገለፃቸው እንደ ጄነራሎቹ ሁሉ ቁጥብ በመሆኑ ምክንያት ይህን ይመስላሉ ሊያስብለን አይችልም የተፈሪ አካላዊ አሳሳል ተፈሪ ወጣት ቆራጥ አስተዋይ ተደርጐ የተሣለ ነው ከአካላዊው ገለፃ ጎን ለጎን እንደ በሼ ሁሉ በህሊናው አሣሣል የማንረሳው ገፀባህርይ ቢሆንም አካላዊ ገለፃው ከሌሎች ገፀ ባህርያት ለይተን ለማወቅ ብሎም ለተደራስያን ቅርብ ለማድረግ ጠቃሚ ነው ሆኖም ግን ገለፃው አርግጥ በታሪኩ ፍሰት ውስጥ ጣልቃ እየገባ ቢጻፍም አካላዊው ገለፃ አንድ አይነት በመሆኑ ለታሪኩ የበለጠ ፋይዳ እንዳይኖረው አርጐታልበታሪኩ ውስጥ በተለያየ ቦታ ደራሲው እንዲህ ሲል ገልጾታል የተፈሪ አጐት በሼ የተፈሪን ደብዳቤ እንብበው ሲጨርሱ ስለተፈሪ ማሰብ ጀምሩ ተፈሪ በፈረስ ተቀምጦ ፀጉሩ ወደጋላ ለቆ በግራ አለንጋውን እያውለበለበ መሣሪያውን እንዳነገተ በሜዳው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሽፍትነት የገባ ጊዜ ያሣየው ትርኢት ታስባቸውየጠፍ ከዋክብት በአየር ውስጥ እያዩት ከሚያሽቃብጠውና ከሚያናጥረው ቀይ ፈረስ ላይ የተቀመጠውን ያን ግርማ ሞገሳም ፁጉራም አስፈሪ ጀግና በአንከሮ በህሊናቸው እያስተዋሉ ፈገግ አሉ የጠፍ ከዋክብት ከዚህ እንደምንረዳው አጎቱ በሼ በምልሰት ሆነው የተመለከቱት አካላዊ መልኩ እንድናይ አርጐ ብቻ አይቆምም ከዚህም ባሻገር አርበኛ የትግል ጓዶቹ ስለ ተፈሪ እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ በተለይ የተፈሪ ግራ እጅ ተወናጭፎዞማ ፀጉር በንፋስ ብትንትን ብሎ ወደፊት ሲወረወር ወደላና ወደፊት ተሽከርክሮ ሲፎክር ወደ ግራ ወደቀኝ ዞሮ ሲፎክር የጠፍ ከዋክብት በአንድ ወቅት አርበኞች ጠላትን ለማስወጣት የጥምረት እንቅስቅሴ ለማድረግ ተሰብስበው በመወያየት ላይ ሣሉ ደራሲው ወጣቱን ጀግና እንዲህ ሲል ይገልፀዋል ይፄ የሃያ ስምንት አመት ጎረምሣ አስተያየት ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ ፀጥ ብሎ መቀመጡ የገረማቸው ሁሉ አይናቸውን ወደ ተፈሪ ወረወሩት እዚያ ከተሰበሰቡት በአድሜ ትንሹ ተፈሪ ነው ሲሸፍት ዛያ አምስት አመቱ ነበር አሁን ግን ፃያ ስምንት አመቱ ግርማ ሞገሱ ግን ማንንም ማስበርገግ እና የማስደመም ኃይል አለው እንጂ የፃዛያ ስምንት አመት ሰው መሆኑን አይመሰክርምፁ የጠፍ ከዋክብት ዐ በታሪኩ ውስጥ ተፈሪ አካላዊ ገለፃ ከላይ በተዘረዘረው መልኩ ቢቀርብም በህልናዊው አሣሣል የማንረሣው ገፀባህርይም ነው በአካላዊው ገለፃም ከሌሎች ገፀባህርያት ለይተን ለማወቅና ይህን ይመስላል ብሎ ለመናገር ቢያስችለንም ገለፃው አንድ አይነት አና ድግግሞሽ በመብዛቱ አስልቺ አድርጓታል ይህም ሲባል ስለመልኩ በመቀጠል ስለአለባበሱ ብሉም ስለአቋቋሙና ስለፈረሱ በታሪኩ ሂደት ጣልቃ እየገባ ቢጠቀሱ ኖሮ ታሪኩ ይበልጥ አጓጊና አስደሣች ይሆን ነበር የኪዳኔ አካላዊ አሳሳል በዚህ ልብወለድ ውስጥ ሌላው ገፀባህርይ አቶ ኪዳኔ ነው ኪዳኔ ከታሪኩ እንደምንረዳው ለጣሊያን በባንዳነት የሚሠራና አቶ በሼን እንዲሁም ዘመዶቻቸውን ለማጥቃት በበቀልም እራሱን ለማስደሰት ብሎም ከጣሊያን መንግስት ሹመት ለማግኘት ጠንቋይ አቤቱ እስከማስቀመጥና እስከማስጠንቆቀል የደረሰ ሰው ነው በመሆኑም ደራሲው ኪዳኔን የገለፀው ሲያስጠነቁል የለበሰውን ልብስ እያሳየንና በጉልበቱ ተንበርክኮ መሬት ሲስም ነው ልብሱን ሲያሳየን እንዲህ ተፅፏል አቶ ኪዳኔ ጥቁር ጥለት ያለውን ጋቢውን አጣፍቷል የጠፍ ክዋክብት ካለ በኋላ ስለመንበርከኩ ደግሞ ደራሲው እንዲህ ፅፎታል ሑትኩር ብሉ የተደፋውን ኪዳኔን አየው። ቃል ኪዳንህን በጭቃ ለወስህ ቀበርከው የጠፍ ከዋክብት ከሩቅ ሰው መምጣቱን የተረዳችው ተኮላ አማራጭ በፍጥነት ወሰደች በሰረቀኃይል ላይ በግንባሩ ለቀቀችበት ደገመችው ለሶስተኛ ጊዜ ተኮሰችየጠፍ ከዋክብት በዚህ ብቻም አላበቃም ሠረቀኃይልን ሊያስጥለው የመጣውን ምክትል ጄነራል ሲልቪዬ ለተኮሰባት ጥይት አፀፋውን ስትተኩስ ይስተዋላል ይህም ምን ያህል ቆራጥና ጀግና ለአላማዋ ፅናት ለኢትዮጵያ ነፃነት በብልሃትና በቆራጥነት ማድረግ የፈለገችውን የምታደርግ ጀግና ገፀባህሪይ ተደርጋ የተሣለች ናት ለዚህም አብነት ይሆነን ዘንድ ከሠረቀ ኃይል ሌላ ምክትል ጀነራሉ ላይ የወሰደችው የተኩሰ አፀፋ ታሪኩ እንዲህ ያስነብበናል ምክትል ጄነራሉ በተወሰነ ርቀት ተዘርሯል ሴማዊት የተኮሰችው ጥይት ደረቱን መታው የጠፍ ከዋክብትዐ ታሪኩ እንደሚያስረዳው በተኩስ ልውውጡ ወቅት ሴማዊትም መመታቷና መሞቷን ነው ይህም ዋቢ የሚያደርገው ለአላማዋ እስከ ሞት መስዋአትነት የከፈለች ጀግና ሴት መሆኗን ነው የጄነራል ፍራንኮ ህሊናዊ አሳሳል የጄነራል ፍራንኮ ህሊናዊ አሣሣል በበቀለኝነት በንቀት በሴሰኝነትና በሞኝነት የተሞላ ነው ጄነራሉ ፍራንኮ አገሩ የጣለችበትን ግዳጅ ለመወጣት በአውሮፓዊ ኩራትና ከኛ በላይ ሰው ላሳር በሚል ትምክህት አባቶቹ ያጡትን ክብር እርሱ ለመመለስ ብሎም ሊበቀልላቸው ቃል ገብቶ አገሩንና ወገኑን ክብር ለማጐናፀፍ ቆርጦ የመጣ ጄነራል ነው ደራሲውም እንዲህ ያብራራዋል አየህ እነዚህ ህዝቦች በቅኝ ግዛትነት ብቻ አይደለም ልንገዛቸው የሚገባው ልንበቀላቸውም ይገባል ምክንያቱም አዋርደውናል በአለም ፊት አስቀውብናል የጠፍ ከዋክብት ሲል ጄነራሉ ለምክትሉ ሲያስረዳ ይነበባል ለዚሁም አባባሉ ደራሲው በተለያየ የታሪኩ ቦታ ላይ ጄነራሉን ይገልፀዋል በታሪኩ ሂደት የጄነራል ፍራንኮን በቀለኝነት የሚያሣዩ ጉዳዮች ተገልፀው እአናገኛለን ለተልዕኮው መሣካት ሲል አማራና ኦሮምን በማጋጨት ትርፍ ለማግኘት የወጠነው ጄነራል ስለበቀል ያለውን ጥመኝነት እንዲህ ሲል ይደመጣል ፍራንኮ ምን ነካህ። በደህናህ ነው አባት ልጃቸውን ጠየቁ በደህናዬ ሣይሆን ጭኘው የነበረውን መሣሪያና ሰንቅ ጣሊያኑ ይዞብኝ ነው የመጣሁት ያ የተረገመ ምክትል ጄነራል እያለ ጤና የለም የጠፍ ከዋክብት የአቶ በሼ ልጅ አስፋው ምሬት የሚያሣየው ምክትል ጀነራሉ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ነው የበሼ ህሊናዊ አሳሳል አቶ በሼ ባላባት ሀብታም ጥቃትን የማይወዱ አልገዛም ባይ ሁለት መልክ ያላቸው አንደበተ ርዕቱ ጠንቃቃ ቆራጥ አገር ወዳድ ዛይማኖተኛ ስልጣኔ ወዳድ ሆነው የተቀረፁ ገፀባህሪይ ናቸው በሸዋ ጁሩ አካባቢ የሚኖሩት በሼ ጣሊያን ኢትዮጵያ አገራቸውን በመውረሩ ምከንያት የውጊያ ስልታቸውን ጣሊያኖች አፍንጫ ሥር ሆነው ለመዋጋት በነደፉት ስልት መሠረት ፍጹም የጣሊያን ወዳጅ መስለው ጫካ ላሉ አርበኞች የመረጃሻ የቁሣቁስና ስንቅ አቅርቦት የሚያደርጉ ሰው ናቸው እነዚህን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ብሎም አገራዊ ግዴታን ለመወጣት የወጠኑት ውጥን ይህን ይመስል ነበር በሼ የነገር አካፄዱ ገና ከጅምሩ የሚገባቸው ነበሩና ኢትዮጵያ እጃ በጣሊያን እንደተያዘች አልተለመደም ባይ ልጆቿ ዱር ቤቴ ያሉ ጊዜ ነው ነገሩ ግልፅ የሆነላቸው አሳቸው ደግሞ አብረው እንደይሸፈቱ እርጅና እጃቸውን ይዚቸዋል ያ ብቻ አይደለም የጠፍ ከዋክብት ሽፍተነት ጫካ ብቻ እንዳልሆነ ብልሁ ሰው ብዙ ያውታሉ አጠላት አፍንጫ ሥር ሆነው ሽፍትነት እንዳለ ተገንዝበውታል የጠፍ ከዋክብት በመሆኑም አቶ በሼ ከጣሊያኖች ያገኙትንመረጃ የጦር መሣሪያና ስንቅ በጫካ ላሉ ኢትዮጵያን ነፃ ለማስወጣት ለሚዋጉ አርበኞች በማቀበል ድጋፍ የሚያደርጉ ገፀባህሪይ ተደርገው የተቀረፁ ናቸው በአንድ ወቅትም የአቶ በሼ ልጅ አስፋው ለአርበኞች ስንቅና የጦር መሣሪያ ጭኖ ይዞ ሲሄድ የጫናቸውን ፈረሶች ምክትል ጄነራል ሲልቪዬ ይይዛቸዋል ምክትል ጄነራሉም እንዲህ ሲል ይገልፃል ይህን ስንቅና መሣሪያ ማን እንደላከው ለማን እንደተላከ ባያቅም ይህን ያህል የመሣሪያና የስንቅ ዝግጅት አድርጎ ዱር ቤቴ ላለ ሽፍታ የሚልክ ጥሩ የሀብት አቅም ያለው ጥሩ ወኔ ያለው እና ወደ ራሣቸው ወደ ጣሊያኖች አፍንጫ ሥር የተጠጋ ሰው መሆኑን ተረድቷልየጠፍ ከዋክብት ከዚህ እንደምንረዳው ይህንን የማድረግ አቅምና ወጌ ያላቸው አቶ በሼ ብቻ ናቸው አቶ በሼ ራሣቸው አዘጋጅተው የላኩትን ስንቅና የጦር መሣሪያ ማን እንደላከው በሚያጣራው ኮሚቴ ውስጥ ሲካቱቱ ያሣየናል ከዚህም የምንረዳው ለጣሊያኖች በተለይ ለዋናው ጀነራል ፍራንኮ የቅርብ ወዳጅ መሆናቸውን ነው ይህንንም ደራሲው እንዲህ ሲል ይገልጸዋል ስለሆነም የዚህን ሰው ማንነት ለመለየት አጣሪ ኮሚቴ ማዋቀር ጀመሩ ሆኖም ጄነራል ፍራንኮ አቶ በሼም አጣሪ ኮሚቴ ውስጥ መግባት አለባቸው ብሉ ድርቅ አለ የጠፍ ከዋክብት ከታሪኩ እንደምንረዳው አቶ በሼ ጣሊያኖችን በተለይም ከዋናው ጄነራል ጋር ያላቸውን ቅርበት ያሳየናል እናም ባላቸው የማሣመን ችሎታ አገራቸውንና ወገናቸውን ነባ ለማውጣት በሚያደርጉት ትግል ታሪኩ ውስጣዊ ማንነታቸውንቆራጥ ሰብዕናቸውን ይነግረናል የአቶ በሼ ሌላው ህሊናዊ መልክ አሣሣላቸው ለስልጣኔ ያላቸው ጉጉት ምን ያህል እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል ይኸውም ከነጮቹ ጋር በዋሉ ቁጥር ስለ ስልጣኔ ይጠይቋቸዋል ስለፋብሪካ ስለማዕድናት ስለዘመናዊ ግብርና ስለዘመናዊ የውጊያ ስልት እና ስለሌሎች ስልጣኔ ስለወለዳቸው ነገሮች አንስተው ሚስጥሩን ለማወቅ ይሞክራሉ ሁሉም በፅንሰ ፃሣብ ደረጃ ቀላል ሆኖ ይታያቸዋልከባድ ሆኖ የሚያገኙት ግን አተገባበሩ ነውዛየጠፍ ከዋክብት ለዚህም ካላቸው ጉጉትና ፍላጎት እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ ህዝብን ወደ ስልጣኔ ጎዳና ሊወስድ የሚችለው ጀግና ወይስ ጠቢብ መሪ። በአርግጥ አኔ አሁን አንተን የማይህ ወዳጄ አንደሆንህ ሁሉ ነው ያንተን ግን አላውቀውም ሲሉ ተናገሩ ሆኖም ግን አቶ ኪዳኔ ይቅር ሊላቸው አልቻለም በመሆኑም አቶ በሼ ይቅር በመባባል ማስወገድ የፈለጉትን የጥላቻ መንፈስ ማስወገድ ባይችሉም ለይቅርታ ረዥም መንገድ መጓዛቸው ምን ያህል ስላም ወዳድነታቸው ከመመስከሩም ባሻገር ጠላታቸውን ወዳጅ በማድረግ የማያቋርጥ መረጃ ስንቅና የጦር መሣሪያ ማግኛ መንገዳቸው እንዳይነጥፍ ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላሉ በመጨረሻም በሚስጢር ታግለውና አታግለው አገሪቱ ነፃ ብትወጣም ያልገመቱትና ያላሰቡት ነገር የገጠማቸው በሼ አዝነውና ተከፍተው እናገኛቸዋለን የተከፉበት አንዱ ምክንያት ደግሞ ይቅርታ ጠይቀውና አስጠይቀው አሻፈረኝ ያላቸው ባንዳው ኪዳኔ ጣሊያን አገሪቱን ተቆጣጥራ በነበረበት ወቅት ያደረሰባቸው በደል አገሪቱ ነፃ ስትወጣ ተፈሪን ከንጉሱ ዘንድ በመክሰስ አንዲሞት በማድረጉ ለመግደል ሲሰናዱ ታሪኩ እንዲህ ይነግረናል አቶ በሼ ድንገት ከኋላው ብቅ አሉና የያዙትን መሣሪያ ኪዳኔ ላይ አነጣጠሩ የጠፍ ከዋክብት ይህን ለማድረግ የተገፋፉት ነፃ በወጣችው ኢትዮጵያ ለጣሊያን በመወገን እንደ ኪዳኔና መሰሎቹ ያሉ ሰዎች ተሹመውና ተሸልመው ሲያዩ በአንፃሩ ለኢትዮጵያ ነፃነት በዱር በገደል ተዋግተው ነፃ ያወጧት አንደ ተፈሪ ያሉ ቁርጠኛ ልጆቿ እንደ ባንዳ ታይተው በወታደር ተከበው ሲረሸኑ በማየት በጥልቅ ሀዘንና ምሬት ኪዳኔን ሲናገሩት ይደመጣል ኪዳኔ እህቴን የገደልክ ተፈሪን ከባንዶች ጋር ሆነህ በንጉስ ዘንድ እንዲጠላ ነገር የሰራህ ውሾቼን ያስገደልክ በጠላት በተደጋጋሚ ያጠቃኸኝ ለሴማዊት መገደል ሰበብ የሆንክ በዚህ አለም ላይ ያለኝን ነገር ሁላ እንዳጣ ያደረግኸኝ ሰው ነህና ልገልህ ይገባል የጠፍ ከዋክብት ከዚህ ጥቅስ እንደምንረዳው ምን ያህል እንደተጐዱና እንደተከፉ መረዳት ይቻላል ይህንንም ደራሲው ሲያረጋግጠውአረንዛው በሼ አንኳን ከንጉስ ነገሥቱ የራስነት ስልጣን ማዕረግ እንዲወስድ ተጠርቶ ነበር ግን በተፈሪ ጉዳይ አኩርፎ አዲስ አበባ ሲጠራ አልሄድም ብሎ እንጂ የጠፍ ከዋክብት በመሆኑም የኪዳኔን የሹመት ልብሱን አስወልቀው ከገደሉ በኋላ የሹመት ልብሱን ጣሊያኖቹ የገደሏቸው ውሾቻቸው መቃብር ቦታ ላይ ሲያቃጥሉ አናያለን ስለሆነም የአቶ በሼን ህሊናዊ መልክ ታሪኩ ከፋፍሎ ሊያሣየን ሞክሯራል አንደኛ ጣሊያኖችን ለማሣመን የፄዱበት መንገድ አሣማኝና ተቀባይነት ማግኘታቸው ሁለተኛ ያገኙትን ተቀባይነት በመጠቀም በወኔና በታላቅ ሀገር ፍቅር ለአርበኞች ድጋፍ ማድረጋቸውበሶስተኛ ደረጃ ጥላቻንና ቂምን በማስወገድ ሰላምና ፍቅር ወዳድ መሆናቸውን እንረዳለን በአራተኛ ደረጃ የሚወዷቸውን ሰው የገደሉ ብሎም ለመገደል ሰበብ የሆኑትን ሰዎች የተበቀሉ ሆኖው የተሣሉ ገፀባህሪይ ናቸው የተፈሪ ህሊናዊ አሣሣል ተፈሪ እንደሌሎች ገፀባህሪይ ሁሉ በህሊናዊ አሣሣል ልዩ ቦታ የተሰጠው ገፀባህሪይ ነው ተፈሪ አስተዋይ ወጣት ለአገሩ ለወገኑና ለእምነቱ ነዓ መውጣት ወንዶች በረፃ ገብቶ የሚዋጋ ለፍትህ የቆመ ፍርድ የሚሰጥ ሆኖ የተሣለ ገፀባህሪይ ነው ከዚህ በመነሣት የተፈሪን ህሊናዊ አሣሣል ተንተን አርገን ለማየት እንሞክራለን ሰለ ተፈሪ በተፈሪ ስም። የጠፍ ከዋክብት ብሎ የተናገረው ሰላም ፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር ለአስተዋይነቱ ምስክር ነው ይህንንም ሃሣብ ለማጠናከር ባሏ የሞተባት ሴት እንዲህ ስትል ተጽፉል ጨዋነቱን እኔ እራሴ አውቃለሁ ክርስትና ላንሣው ብሎ የመጣ ጊዜ ነው ትልቅና አስተዋይ ሰው እንደሚሆን የተረዳሁት የጠፍ ከዋክብት እናም ይህ ባህሪይው ከልጅነቱ ጀምሮ አብሮት ያደገና የጨዋ ባህሪይ የተላበሰ ተደርጐ የተፃፈ ነው የኪዳኔ ህሊናዊ አሣሣል አቶ ኪዳኔ ኢትዮጵያ በጣሊያንን በተወረረችበት ወቅት ከጣሊያን የወገነ ባንዳ ሆኖ የተሣለ ገፀ ባህሪይ ነው ባንዳ እንዲሆን የገፋፋው ነገር ደግሞ ለበቀል ካለው ፍላጎት በራስ አለመተማመን ስልጣን ወዳድ መሆኑና ፈሪነቱ ነው ከነዚህ ባህሪው በመነሣት በቀለኝነቱን እንተነትናለን በተለይ አቶ በሼንና ቤተሰቦቻቸው ላይ ጉልቶ የሚታየው የበቀለኝነት መንፈስ በሴማዊት ምክንያት መሆኑን ታሪኩ እንዲህ ያስረዳናል አቶ ኪዳኔ ከአምስት አመት በፊት ሴማዊትን አንዲድሩለት ይጠይቃል የአቶ በሼ ቤተሰብ ግን እነ ኪዳኔ ቁምጥና ስለአለባቸው ለአርሱ አንድርም አሉ የጠፍ ከዋክብትዐ በዚህ የተነሣ ከጣሊያን በመወገን ለአገርና ለወገን ተቆርቋሪ የሆኑትን በሼንና ቤተሰባቸውን ለመበቀል ከኢትዮጵያ አርበኞች ጋር ግንኙነት ያላቸው የሮማ መንግስት ጠላቶች ናቸው በማለት ለማጋለጥ የሚያደርገውን ትግል ደራሲው አንዲህ ይገልፀዋል አቶ ኪዳኔ በሼን ትክ ብሎ ሲያያቸው ከቆየ በኋላ ለራሱ በተገርሞ እንዲህ አለ ጠላቴ ባይሆን ኖሮ ጥሩ ነበር አሁን ግን አንዴ ጠላት ሆነናል ካሁን በኋላ ደስተኛ ልሆን የምችለው ነገር ቢኖር አንደዚህ አይነቱን ሀይለኛና ጠንካራ ጠላቴን ማሸነፍ ከቻልኩ ብቻ ነው የጠፍ ከዋክብት በዚህ ብቻ አላበቃም ምንም አንኳ አቶ በሼንና ዘመዶቻቸውን ለማጋለጥ ያደረገው ሙከራ ባይሣካለትም የበሼን አህት የተፈሪን እናት አንዲገድል ከጣሊያኑ ጄነራል ፍራንኮ ትፅዛዝ ሲሰጠው ያለውን እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላልኪዳኔ ፊቱ እንደ ብርሃን በራ የተፈሪን እናት መግደል እንዴት ግሩም ደስታ ይሰጣል መግደል እናቶችን ነው እንጂ ጀግና እንዳይወለዱ ሲል ተፈላሰፈ የጠፍ ከዋክብት ተፈላስፎ ብቻ አልቀረም የተፈሪን እናት አስካለ ማርያምን በብረትምጣድ አእየተጠበሰች ሳለ ኪዳኔ ደጋግሞ በጥይት ደበደባት ከዚህ የምንረዳው ኪዳኔ ምንም ርህራፄ የሌለው የበቀል ጥም ያሰከረው ሰው መሆኑን ነው ኪዳኔ ከተፈሪ አናት በተጨማሪም ይጠነቁልለት የነበረው ጉምዴን በመጥረቢያ አንገቱን ሲቆርጠው ታሪኩ ይነግረናል ይህንንም ያደረገው ጠንቋዩ በገዛ ፈቃዱ ለኪዳኔ አልጠነቁልም በማለቱና በጠንቋይ በመሰደቡ የኋላ ጊላ መታለሉ ስለገባው ነው ደራሲውም እንዲህ ይገልፀዋልንዴቱን ለመወጣት ደግሞ አእጉምዴ ላይ አፍጥጦ ጮኸበት አንተ ውሻ አታለልከኝ አይደል። እበቀልፃለሁ ብሎ መጥረቢያውን ከፍ አድርጐ ያበዘ የጠፍ ከዋክብትዐ በዚህ ብቻ ሣይቆም አንገቱን እንዴት እንደቆረጠው እንዲህ ይገልፃል አቶ ኪዳኔ መጥረብያውን ወደ ጉምዴ አንገት ሠንዘረውአቶ ኪዳኔ መጥረቢያውን ሲሰነዝር ጉምዴ መሣቅ ጀመረ አፃፃፃዛ አፃፃዛ አንገቱ ለብቻው ቱር ብሎ ሄደ አንገቱመ ለብቻው ተቀንጥሶ እአወደቀበት መሣቁን ቀጠለ የጠፍ ከዋክብትዐ ከጥቅሱ የምንረዳው ምን ያህል ጨካኝና በቀለኛ መሆኑን ነው ከዚሁ ጐን ለጐን ለስልጣን ካለው ፍቅር የተነሣ ከጣሊያኖች ሽልማትና ሹመት ለማግኘት ጉምዴ የተባለ ጠንቋይ እቤቱ በማስቀመጥ ሲያስጠነቁል እናገኘዋለንበዚህም ምክንያት በጠንቋይ ትፅዛዝ መሠረት ሰው እስከመግደል የደረሰ ስልጣንና ዝና ያስከረው መሆኑን ታሪኩ እንዲህ ይነግረናል አቶ ኪዳኔ አንደለመደው በግንባሩ ተደፋ አንዲህ ሲል ተማፀነ አጉምዴ ላይ የሰፈሩትን አጋንንቶች የወደፊት እድሎን እንዴት አንደሚቀና ጠላቶቼ እንዴት እንደሚጠፋ እና የጣሊያን መንግስት አንዴት ወዳጅ ሊሆነኝ እንደሚችል ስልቱን ይነግረኝ ዘንድ አማፀናለሁ የጠፍ ከዋክብት የዚህ መልክዕክት በዋናነት ዕድሉን አቃንቶ ጠላቶቹን አጥፍቶ የጣሊያን መንግስት ይሁንታን አግኝቶ ሹም ለመሆን ያለውን ፍላጐት እንድንረዳ ያደርገናል ሌላው የኪዳኔ ሰብዕፅና ፊሪ ነገሮችን ፊት ለፊት የማይጋፈጥና በራሱ የማይተማመን ሆኖ ተስሏል ይህንንም ሚስቱ የነበረችው የዝማ እና ቤቱ ያስቀመጠው ጠንቋይ ጉምዴ እንዲህ ሲሉ ይገልፃሉ ይሄን ወኔ ቢስ በራሱ የማይተማመን ባል አግብቼ እንዲህ ልቃጠል የጠፍ ከዋክብት ስትል እንሰማታለን በተጨማሪም ጉመዴ የተባለው ጠንቋዩ ደግሞ እንዲህ ይጋልፀዋል አቶ ኪዳኔ ሲታሰበው ደግሞ ለኪዳኔ አፈረለት ሁልጊዜ ሽጓባና ፊር ሰዎች አለምን ፊት ለፊት መግጠም ስለሚሣናቸው በአጅ አዙርና በጥንቆላ ሊያሸንፉት ይታገላሉ የጠፍ ከዋክብት ዐ ከዚህ ጥቅስ እንደምንረዳው የኪዳኔ የህሊናዊ መልኮች ጥሩ ሆነው ያልተሣሉ በገሀዱ አለምም የሚታዩና ሊገኙ የሚችሉ ሆነው የተቀረፁ ናቸው ማጠቃለያ የጠፍ ከዋክብት ረዥም ልቦለድ ውስጥ ያሉትን ስድስት ዋናዋና ገፀ ባህሪያት አካላዊና ህሊናዊ አሳሳላቸውን ተመልክቻለሁ አብዛኛዎቹ ገፀባህሪያት በውጫዊ ማንነታቸው የገዛፃዱ አለም ሰዎችን የሚመስል አለባበስ ተክለሰውነት ስያሜ ይዘው የተቀረፁ ናቸው ምንም እንኳ ውጫዊ መልካቸው በተለይ ከአንዲ ገፀባህሪ በቀር አለባበሳቸው ተንተን ተደርገው ባለመቅረባቸውና በተለያየ ቦታ አንድ አይነት የሆነ አካላዊ አንቅስቃሴ ማድረጋቸው ገፀባህሪያቱ ምንም አዲስ ነገር ሲያደርጉ አለመታየታቸው ለተደራሲ ሳቢነት አንዳይኖረው አድርጎታል ከዚህም ሌላ ደራሲው የኪዳኔን ውጫዊ መልክ ተንትኖ ሳይገልጽ በስም ብቻ አስተዋውቆን ማለፉ አንባቢ ምስል እንዳይከስትለትና ከሌሎቹ ገፀባህሪያት እንዳይለይ አድርጓታል እንዲሁም የጄነራል ፍራንኮንና የምክትል ጄነራል ሲልቪዮን አካላዊ ገለፃ በአንድ ላይና በአንድ ቦታ መቅረጹ ለተደራሲ ብዥታ የሚፈጥር ከመሆኑም ባሻገር ጄነራል ፍራንኮ ይኸን ይመስላላ ምክትል ጄነራል ሲልቪዮ ይኸንን ይመስላል ለማለት የማያስችል በመሆኑ የታሪኩን አጓጊነት የሚቀንሰው በመሆኑ እንደድክመት የሚጠቀስ ነውበአጠቃላይ ደራሲው በአካላዊ ገለባ በኩል ሰፊ ክፍተትና ጉድለት ታይተውበታል ሌላው ገፀባህሪያቱ በውስጣዊ ማንነታቸው ሰዋዊ ባህሪያትን የተጎናፀፉ ናቸው አያንዳንዱ ገፀባህሪ ለአላማቸው መሳካት በሚያደርጉት ፍትጊያ አንዱ ከሌላውጋ ሲጋጭ ሲፋቀር ወይም ሲመካከር ይስተዋላልየተሰጣቸውንም ሥነ ምግባር ዕምነትና ሞራል ወዘተ አንዱን ገፀ ባህሪ ከሌላው እንድንለየው ከማስቻሉም በላይ በገሃዱ አለም ያሉ ሰዎች የተለያዩ የሕይወት ገጽታዎች እንዳሏቸው የሚያመለክቱ ናቸው ስለዚህም ከአካላዊ ገለባ የተሻለ ትንታኔ የተሰጠበትና የደራሲው ጠንካራ ጎኑ የታየበት ነው በአጠቃላይ ልቦለዱ ከአማርኛ ልቦለድ ዕድገት አንፃር ሲፈተሽ ጥሩ ሥራ ነው ለማለት አያስደፍርም ምክንያቱም ከላይ እንደተጠቀሰው ገፀባህሪያቱ አካላዊ መልካቸው በአግባቡ የተቀረጸ ባለመሆኑ ትልቅ ክፍተት አሳይቷልና ዋቢ ጽሑፎች ሸንቁጥ አየለየጠፍ ክዋክብት አዲስ አበባቦሌ ማተሚያ ቤት ዓም ሽባባው ወሌ የጭብጥ የግጭትና የገፀ ባህርያት ትንተና በአደፍርስና ከአድማስ ባሻገር ውስጥ የቋንቋዎች ጥናት ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዓም ዲማጽ አማረ ማሞ የልቦለድ ድርሰት አፃዛፍ መሠረታዊ መመሪያ አዲስ አበባ ኦክስፎርድ ዩኒቪርሲቲ ፕሬስ ደሳለኝ አሰፋ ሥነ ፍሑፋዊ ሂስ በኢቫንጋዲ እና ከቡስካ በስተጀርባ የቋንቋዎች ጥናት ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዓም ዲማጽ ዘሪሁን አስፋው የስነፍሑፍ መሰረታውያን አዲስ አበባ ንግድ ማተሚያ ድርጅት ዓም ዮሴፍ ጌትነት ሽፍትነት በጥቁር ደም ልቦለድ የገፀ ባህርያት አቀራረጽ የቋንቋዎች ጥናት ተቋም አዲስ አበባ የኒቨርስቲ ዓም ዲማጽ ፋንታሁን እንግዳ ዝክረ ተውኔት አዲስ አበባ ብርፃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ዐ ዓም በጠፎፊኦርከቋፎ ዘዛ።