Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
by: unregistered | 6 KB | 03-10-2020 | 898 ጊዜ ተነቧል | 578 ጊዜ ውርዷል
ደራሲ: Genet Ayele Anbesie
ኰሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ግንቦት 19 ቀን 1933 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ኃይለማርያም ወልዴ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ብዙነሽ ወልደአማኑኤል ተወለዱ፡፡ አባታቸውም ሆኑ እናታቸው የሸዋ ሰዎች ናቸው:: የእናታቸው የትውልድ ሥፍራ ተጉለት ሲሆን የአባታቸው ደግሞ በደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ አቅጣጫ በሚገኘው ረጲ በተባለው አካባቢ ነው:: የሌተና ኰሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች በተባለው መፅሃፍ ውስጥ እራሳቸው ኰሎኔል መንግሥቱ ተጠይቀው እንዳብራሩት "መንግሥቱ" የሚለው ስም የወጣላቸው የጣሊያን የወረራ አገዛዝ አብቅቶ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደገና ተቋቁሞ የአንድ ወር ጊዜ እንኳን ሳይቆዩ የመወለዳቸው ያንን ታሪካዊ ክስተት ለማስታወስ ሲባል ነው:: ከህይወት ታሪካቸው ለመረዳት እንደሚ ቻለው የአባታቸው አባት አቶ ወልዴ አያና የገበሬ ሠራዊት ነፍጠኛ ነበሩ፡፡ የእናታቸው አያት ወልደአማኑኤል ጐርፍነህ እንዲሁ በአፄ ምኒልክ ዘመን የገበሬ ሠራዊት አለቃ ነበሩ፡፡ የወልደአማኑኤል ሁለት ታላላቅ ወንድሞቻቸው ደግሞ አድዋ ዘምተው ሲዋጉ በጦር ሜዳ ወድቀዋል::
Mengistu Haile Mariam