Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ነገረ ድኅነት ውስጥ የሰው ልጅ ይድን ዘንድ ማድረግ የሚገባውን ሁሉ በማድረግ አሳይቶታል በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ማለትም በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በማመን በፍቅሩ እንዲኖር በባሕርይ ልጁ አስተምሮታል ዮሐራ ዮሐ የሕይወትን መንገድ ከፍቶ «መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ» ብሎ ቢበድል ከበደሉ የሚነጻበትን የንስሐ በር ከፍቶለታል ማቴ ኃይልና ብርታትን አግኝቶ ዲያቢሎስን እንዲያሸንፍ ከእርሱ ጋር አንድ ሆኖ ይኖር ዘንድ ሥጋውንና ደሙን ሰጥቶታል ዮሐ «እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ አዳነ» ማለት «ዕዳችን ተከፍሏል ድካማችን ተቃሏል የድኅነት መንገዱ ተከፍቷል» ማለት ነው። በዚህ ነገር «እሺ» ብሎ ለመጠ ቀም «እምቢ» ብሎ ለመጉዳት ለሰው ልጅ ነጻ ፈቃድ አለው ጌታችን አልዓዛርን ከመቃብር ሲያስነሣ የመቃብሩን ድንጋይ ሰዎች እንዲያነሥ ሲያደርግ እርሱ ግን ሙቱን ጠርቶ አስነሣ ይህንን ማድረጉ ሰው በድኅነቱ ላይ የራሱ የሆነ ድርሻ እንዳለው ለማሳየት ነው።
እግዚአብሔር ለምን ሰው ሆነ። እግዚአብሔር ሰው ሆነ ስንል እንዴት ነው። ሞት ሠለጠ ነበት የሞት ባርያም ሆነ «ከአዳም እስከ ሙሴ ሞት ነገሠ» ሮሜ እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ የአዳም ንጉሥነት ቀርቶ ባርያ ሆነ ሕያውነትን አጣ አዳም ሕያው ሆኖ ይኖር ዘንድ ቢፈጠርም ሞትን በገዛ እጁ በመጋበዙ ሟች ሆነ እንደ እንስሳት መሞት መበስበስ ግድ ሆነበት ፈቃዱን እንደ ፈጸመለት እንደ ዲያብሎስ በነፍስ ወደ ሲዖል መውረድን ተቀበለጉ ይሠዋው የነበረው መሥዋዕትም ሟች ሕይወትን በማያመጣሞት የሚያሸንፈው የእንስሳት መሥዋዕት ሆነ እግዚአብሔርን መምሰል አጣ «እኔ ግን አማልክት ናችሁ አልሁ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ ነገር ግን እንደ ዲያብሎስ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ መዝዮሕ ሰው አምላክ ዘበጸጋ ነበር ነገር ግን እንደዲያብሎስ ከአለቆች አንዳንዱ በመውደቁ እግዚአብሔርን የመምሰል ክብር አጣ ባለዕዳ ሆነ አዳም በባሕርይው ነጻ ሰው ነበር አሁን ግን ዕዳን በገዛ እጁ አመጣ ሞትን ያህል ዕዳ ተሸከመ ደግሞም ዕዳውን መክፈል አልቻለም ገነትን አጣ አዳም የነበረችውን ርስት አጥቶ ተባረረሱጹ ገነት ተዘጋችበት ስደተኛም ሆነ እግዚአብሔር የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም ማቴራ አዳምና ሔዋን ግን ሞትን ተሸከሙ ስለዚህም ከሕያዋን አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ግንኙነት ተቋረጠ ለአዳም የሚያስፈልገው ማነው። አዳምን ከምድር አፈር ያበጀው የሕይወት እስትንፋስንም የሰጠው እግዚአብሔር ነው «አዳም ሆይ መሬት ነህና ወደ መሬትም ትመለሳለህ» ብሎ የፈረደበትም እግዚአብሔር ነው ሕያው አዳምን ሞት እንዲያሸንፈው ፍርድ የሰጠበትም እግዚአብሔር ነው ስለዚህም ከመሬት ያበጀውን ወደ መሬትም የመለሰውን መልሶ ከመሬት ለማንሣት ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው ሕይወት ለሰጠው ሰው ሞት የፈረደበት መልሶም ከሞት ቀንበር አላቅቆ ሕይወት መስጠት የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው የቀደመው ሰው አዳም በእግዚአብሔር ተፈጥሮ በእግዚአብሔር የከበረ ነበር የዳነው አዳም ግን «በፍጡር የተፈጠረ» የፍጡር «የዳነ» በፍጡር «የከበረ» ቢሆን አዳም ወደ ጥታ ሇፍሩ ሦመጋ ፍጹም ድንታታ ለ ማሐም ሳፖሦቻ ያርረፓ ምጂሟሥራም ዖፇደመው ፅሪዳም ዕጸጳሂለጨረ ፇፈጥሮ በእግዚአብሔር ከብሮ የሚኖር በመሆኑ ከኋለኛው አዳም ይበልጣል ያሰኛልና ነው እግዚአብሔር አዳምን ሲፈጥር ማንንም አላማከረም ሲፈርድበትም የማንንም ሀሳብ አልጠየቀም በመሆኑም እንዴት እንደፈጠረውም እንዴት እንደፈረደበትም ምሥጢሩን የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነው ሊያድነው ወደ ጥንት ክብሩ ሊመልሰው ፅውቀቱም ጥበቡም ሥልጣኑም ያለው እርሱ ብቻ ነው ለአዳም ቀዳሚቷን ሕግ የሰጠ እግዚአብሔር ነው አዳም ሕጉን በጣሰ ጊዜ የቀጣው እግዚአብሔር ነው ሁለተኛዋን ሕግ የመስጠት ሥልጣን ያለውም እግዚአብሔር ነው ስለዚህም አዳምን ሊያድነው ከወደቀበት ሊያነሣው ወደ ጥንት ርስቱ ሊመልሰው «ኦ አዳም አይቴ ሀሎከ» እያለ የመጣው መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው ፍጡር አይደለም መልአክ አይደለም ነቢይ አይደለም ምንም እንኳ ነቢይነት ገንዘቡ ቢሆን ለነቢያትም ሀብተ ትንቢትን የሚሰጠው እርሱ ቢሆን እግዚአብሔር ለምን ሰው ሆነ። ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው ከፍጥረት መካከል አሟልቶ አጠናቆ ያውቀው ይመረምረው ዘንድ የሚቻለው የለም መንፈስ ቅዱስ የገለጠላቸው አበው የነገሩንን እነሆ እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር «ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳልነ» ብሎ ከምድር አፈር አበጀው ይህ በአብ ልብነት አስበውበወልድ ቃልነት ተናግረውበመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት የፈጠሩት ሰው ቢወድቅ ንግበር ሰብአ» ብሎ የተናገረው ቃል ወደ አዳም መጣ ከመሬት ያበጀው እጅክንድተዘረጋ ኦ አዳም መሬት አንተ ወትገብእ ውስተ መሬት» ብለው ሥላሴ በአብ ልብነት አስበው በወልድ ቃልነት ፈርደውበመንፈስ ቅዱስ ሕያውነትአጽንተውት የኖሩትን ፍርድ ሊያነሣ የፈረደበት ቃል ወደ አዳም መጣ ዓለም በኃጢአቱ ምክንያት የእግዚአብሔርን ድምፅ ፈርቶ ይኖር ነበር ዘፍ እሥራኤል እግዚአብሔር በሲና ተራራ በተናገራቸው ጊዜ ሙሴን «አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን እንዳንሞት ግን እግዚአብሔር አይናገረን» ዘጸ እንዳሉት ይህን የኃጢአት ፍርሃት ከሰዎች ያርቅ ዘንድ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ከእኛ ጋር ተገኘ አማኑኤል የሰው ቋንቋ እየተናገረ በሰው ሥርዓት ተመላለሰ ድምፁን አሰምቶ በበለስ ሥር የተደበቀውን አዳም ፈለገው አገኘውም የሰው ልጅ በትእዛዛት የተሰጠውን ሕግ ይፈጽም ዘንድ አልቻለም ሠርቶ ፈጽሞ አድርጐ ያሳየው የለምና በመሆኑም እግዚአብሔር ወደኛ መጥቶ ሠርቶ አዲሲቷን ሕገ ወንጌልን ሰጠን የቀረውን መንፈሰ ቅዱስ ይግለጥልን ዳሂዳወ»ሬረ ው ዳፇ ዳዳንዕው አበው እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ፖዖ ዕው ያኖ ቁምሥሃ ይፍያፖምፖ ጥራኦራ ይዕጳማላለ ይጎራ ምያ ሥራም ዕዶሁም ጥር ኅሊናን የሚያስደንቅ ምሥጢር ተፈጽሟልና የአዳምን ዕዳ ፍጡራን ሊከፍሉት አልቻሉም እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆኖ ፅዳችንን ከፈለልን አዳም ሊቀበለው ይገባል የነበረውን ሁሉ ተቀብሎ አዳምን ነፃ አወጣው አዳም በበደሉ ከገነት ወደ ሲዖል ቢሰደድ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ያለ በደሉ የገነት ምሳሌ ከሆነች ከነዓን የሲዖል ምሳሌ ወደ ሆነች ግብጽ ተሰደደ አዳም ከዓለመ መላእክት ተሰድዶ በእንስሳት መካከል ቢገኝ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በከብቶች በረት ተወለደ አዳም ከኅቱም መሬት ተገኝቶ ቢሳሳት መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከኅቱም ድንግል ከእመቤታችን ተወልዶ አዳነው አዳም ከንጹሕ ምድር መርገም ካልደረሰባት ተገነኘቶ ቢሳሳት መድኃኔዓለም ክርስቶስ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ከሌለባት ከንጽሕት እመቤታችን ተወልዶ አዳነው አዳም የሠላሳ ዘመን ጉልማሳ ሆኖ ተፈጥሮሰባት ዓመት በገነት ኖሮበምክረ ከይሲ ተታሎ ልጅነቱን ቢያጣመድኃኔዓለም ክርስቶስ በሠላሳ ዓመቱ ተጠምቆ አዳነው አዳም በመብል ድል ተነሥቶ ከገነት ቢወጣ መድኃኔዓለም ክርስቶስ «ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም በእግዚአብሔር ቃል ጭምር እንጂ ብሎ ፈቃደ ሥጋን ስስትን ድል ነሣለት» ዲያብሎስ አዳምን ከምድር ተለይታ የምትገኝ ገነት ለብቻው በመብል ድል ቢያደርገው ጌታም ዲያብሎስን ከከተማ ርቃ በምትገኝ ገዳመ ቆሮንቶስ በጾም ድል ነሣው አዳም ሕግ ጥሶ ከጸጋ ቢራቆት መድኃዓለም ክርስቶስ ራቁቱን በመልዕልተ መስቀል ተሰቀለለት የአዳም እጅና እግር ወደ ዕፀ በለስ ቢያመሩ የመድኃኔዓለም እጅና እግር በቅንዋት ተቸነከሩ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ አምላክ ወልደ እግዚአብሔር ፍጹም ካሣን ካሠልን የአዳም ዐጽም ካረፈበት በጎልጎታ ትርጓሜው የራስ ቅል ነው ተሰቅሎ ሞትን መውጊያ አሳጣው የመቃብርም ኃይል ተሻረ ርቀን የነበርነውን ልጆቼ አለን ማቴቆሮ የተዘጋች ገነት ተከፈተች ዕድሜውን በሙሉ በኃጢአት ሲናውዝ ለነበረው ለፈያታዊ ዘየማን ታላቁ ብሥራት ተነገረው «ከኔ ጋር በገነት ዛሬ ትሆናለህ» ሉቃ ገነት ከኃጢ አት ወደ ጽድቅ ተመልሰው በቀኙ ለሚቆሙ መከፈቷን አበሠረን ሞት በሞት ሞተ «እግዚአብሔር ሰው ሆነ ስንል እንዴት ነው። አንድ ሰው «አምላክ ሰው ሆነ» «እንዴት ሰው ሆነ» የሚለውንም በደንብ መረዳት ይኖርበታልና እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሥጋ ማርያም ሰለመገለጡ ስንናገር በዙሪያው ማወቅ የሚገባን ብዙ ነገር አለ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከባሕርይ አባቱ ከአብ ድኅረ ዓለም ያለ አባት ከድንግል ማርያም በሥጋ የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ነሥቶ ሰው የመሆኑ ነገር ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው ታላቅ ምሥጢር ነው ጢሞ ስለዚህ ይህን በሚገባ መረዳት አለብን ይህንን ስንል በራሳችን ተፈላስፈን እንመርምር ማለት አይደለም ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት በገለጡልን ዕውቀት መሠረት የሆነ እንዴት ሰው እንደሆነ እንረዳ ማለታችን እንጂ ጌታችን ጴጥሮስን «አንተ ዐለት ነህ በዚህ ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ ማቴ ያለው የሃይማኖት መሠረት እምነት እንዳለው የተናገረለት«አንተ መሲሁ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ» ስላለ ነበር ማቴ በፊቱ የቆመውን ወልደ አምላክ የአብ የባሕርይ ልጅ ብሎ በመጥራቱ ብፁዕ ተባለ ዛሬም ብዙዎች እንደሚሉት በተሳሳተ መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስን የማይገባ ስም ሰጥተን ከመጥራት ተቆጥበንከስህሀተት ድነንመለኮት ከሥጋ ፈጹም መዋሐዱን አምነንኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነ አምላክ ነውየአብ የባሕርይ ልጁ ነው ብለን ከአመን ያድነናል ስለዚህ እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆነ ስንል በምን መልኩ። ዘጸዘፍ አንድ ነገር ተለወጠ ስንል የቀደመ ባሕርይውን ለቆ ሌላ ይሆናል የሚል ትርጉም ይሰጠናልፅ የአምላክ ሰው የመሆን ምሥጢር ግን በመለወጥ አይደለም ምክንያቱም መለኮት ወደ ሥጋነት ተለወጠ ካልን መለኮት የቀድሞ ማንነቱን ለቆ ሰው ብቻ ሆኗልና ዓለም አልዳነም ማለት ይሆንብናል ይህ ደግሞ መለኮት ከሥጋ ጋር ስላልተዋሐደ ሥጋ ብቻውን ከሆነ መከራ መቀበሉ መሰቀሉ ሁሉ ለከንቱ ነው ያስብላል በሥጋ ብቻ በፍጡር ደም ዓለም አይድንምና በሌላ በኩል ሥጋ ተለውጦ መለኮትን ሆኗል በመለኮት ተውጧል ልንልም አንችልም አምላክ ሰው ሆነ ካልን ፈፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑንም ከመረዳት ጋር መሆን አለበት ምክንያቱም ሥጋ ባሕርይውን ለቅቆ ወደ መለኮትነት ተለውጧል ካልን አሁንም ዓለም አልዳነም ወደ ሚል ሀሳብ ስለሚወስድ ነው ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው ብለን ካላመንን ሥጋ ተለውጧል ካልን መከራ የተቀበለው መለኮት ብቻውን ነው ያስብለናል ይህ ደግሞ ስሕተት ነው መለኮት ሊዳሰስ ሊሰቀልሊቀበር አይችልምና የግድ መከራን ለመቀበል የሥጋን ባሕርይ ባሕርይው ማድረግ ነበረበት ስለዚህ በአጠቃላይ ስናየው ሥጋም ወደ መለኮትነት መለኮትም ወደ ሥጋነት አልተለወጡም በተዐቅቦ በመጠባበቅ አንድ ሆኑ እንጂ እግዚአብሔር በባሕርይው መለወጥ ስለሌለበት ሚሜል በሥጋ ባሕርይ ተለወጠ ማለት ስሕተት ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትም ዛሬም እስከ ዘለዓለም ያው ነው ዕብ በኅድረት ነውን። አይደለም ይህ ሃሳብ የመጣው በምንታዌ በሁለትነት ከሚያምኑና በኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበሩ መናፍቃን ነው እነርሱም ሁለት አምላክ አለን አንዱ ክፉ ሌላው ደግ ክፉው ይህን ዓለም ሥጋን ፈጠረ ደጉ የማይታየውን ዓለም ነፍስን ፈጠረ ስለዚህ ነፍስ በደጉ ሥጋ በክፉ የተፈጠሩ በመሆናቸው ሁለቱ አይዋደዱም ነፍስ በሥጋ ታስራ ስትሰቃይ ትኖራለች አምላክ እርሷን ነፃ ሊያደርግ መጣ በሥጋ ላይ አድሮ ተመላለሰ ግን ሥጋ አልተዋሐደውም ምክንያቱም ሥጋ የክፉ አምላክ የእጁ ሥራ የረከሰ ፍጥረት ነውና ይላሉ ይህ አስቀድሞ በነበሩ በሁለት አማልክት በሚያምኑ መናፍቃን የተጀመረ የኅድረት ትምህርት ሥር በስተ መጨረሻ «በአንድ አምላክ እናምናለን» ወደሚሉ መናፍቃንም ደረሰ ስለዚህም ከቤተ ክርስቲያን የተነ እነንስጥሮስም አመሳክ ከድንግል ማርያም በተወለደው በኢየሱስ ላይ አደረበት እና የጸጋ አምላክ አደረገው እንጂ ሥጋን አልተዋሐደም አሉ ንስጥሮስ በ ዓም በኤፌሶን የተወገዘ መናፍቅ ነውህ ይህ መናፍቅ ዳዊት በማኀደሩ እንደሚያድር በማርያም ልጅ ኢየሱስ ላይ አምላክ አደረበት ድንግል ማርያም የወለደችው ሰው ነው ወላዲተ ሰብእ ይላታል ኋላ እርሷ በወለደችው ላይ ፈጣሪ አደረ ብሎ በድፍረት ያስተምር ነበር ይህንን የክህደት ትምህርት ይዘው ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ ነው ሥጋን አልተዋሐደም የሚሉ መናፍቃን ዛሬም አሉ ይህ ዓይነት አስተሳሰብ ግን ፈፁም ስሕተት ነው ምክንያቱም ሀ መናፍቃን እንደሚሉት እመቤታችን ሰውን ብቻ ወለደች ኋላ አምላክ መጥቶ አደረበት ካልን ከፅንሰቱ ጀምሮ በልደቱ ጊዜ የተደረገውን ነገር የተነገረለትን ቃል መሻር ስለሚሆንብን ነው ኢሳይያስ «ድንግል ትፀንሣለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች» ኢሳ አማኑኤል ትርጓሜው «እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው» ብሎ ተናግሯልርፎ ማቴራ የተወለደው ሕጻን አማኑኤል የተባለው ሲወለድም አመላክ በመሆኑ ሥጋን ነሥቶ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጥ ነበር ከዚህ ሌሳ አሁንም በትንቢት «ሕጻን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘለዓለም አባትየሰላም አለቃ ተብሎ ይጠ ራል» የሚል ቃል እናገኛለን ኢሳ በቤተልሔም ዋሻ ድንግል ማርያም የወለደችው ሰብአ ሰገል ወርቅ ዕጣንከርቤ መብዐ አድርገው ያቀረቡለት ሕፃን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ስለሆነ ስሙም ኃያል አምላክ ተብሎ ይጠራል ተባለለት ይህን ሕፃን ኤልሳቤጥ በማኅፀን ሳለ ገና ጌታዬ ብላ ጠርታዋለች። ሉቃ ስለዚህ መናፍቃን እንደሚሉት ድንግል ማርያም ወላዲተ ሰብእ የሰው እናት አይደችም የአምላክ እናት እንጂ ኢየሱስ ክርስቶስም አስቀድሞ ሰው የነበረ በኋላ በፀጋ የከበረ አይደለም ከድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የሆነ አምላክ እንጂ ለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ ነው መለኮትና ሥጋ አልተዋሐዱም ከተባለ ሰው ሕጠ ገና አልዳነም ማለት ይሆናልና በተዋሕዶ መለኮትና ሥጋ አንድ ካልሆኑ ኢሳይያስ በእውነተ ደዌያችንን ተቀበለ ሕማማችንንም ተሸክሟልስለመተላለፋችን ቆሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀተጨነቀተሰቃየ አፉን አልከፈተም» ኢሳ ብሎ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ባልተናገረ ነበር እርሱስ በተዋሕዶ መለኮትና ሥጋ አንድ መሆናቸውን በመንፈስ ተገልጾለት ተናገረ ለምን ቢሉ መታመምና መቸገር የመለኮት ባሕርይ አይደለምናበተዋሐደው ሥጋ ታመመተቸገረ ቆሰለ ለማለት ሥጋ ብቻውን ነው ካልን ግን ሰው የራሱን መከራ ራሱ ተቀብሏልና ገና አልዳነም ወደሜል ክህደት ይወስዳል ሰውም በሰው አይድንምና አዳም አልዳነም ማለትን ያስከትላል በተዋሕዶ ምሥጢር ግን መለኮት የሥጋን ገንዘብ የራሱ በማድረግ ታመመ ሥጋም የመለኮትን ገንዘብ የራሱ በማድረጉ መከራን ችሎ ታገሰና ተቀበለ እንላለን ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ አይደለም በመሆኑም ኅድረት የሜለው ቃል ክህደት ነው እግዚአብሔር አብ ስለ ባሕርይ ልጁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የምወልደው የምወደው ልጄ እርሱ ነው በማለት መስክሯልፁ መለኮትና ሥጋ በተዋሕዶ አንድ ባይሆኑ ኖሮ በነቅዱስ ጴጥሮስ ፊት የቆመውን ኢየሱስ ክርስቶስን ልጄ ብሎ ባልጠራው በዚህም ፈንታ የልጄ ማደሪያ ባለው ነበር ነገር ግን ሥጋ ከመለኮት ጋር በመዋሐዱ ማደሪያ ሳይሆን ልጄ ተብሎ ሥጋ የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ አድርጎ የአብ የባሕርይ ልጁ ተባለ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነው በኅድረት ሳይሆን በተዋሕዶ ነው በቱሳኤ ነውን። በነፍስ በሥጋ የተፈጠረ ሰው አንድ ነው እንጂ ይህንንስ ካወቅን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋሕዶ በፊት እርስ በርሳቸው አንድ ካልነበሩ ከተዋሕዶ በኋላም ከማይለያዩ ከሁለት ባሕርያት አንድ እንደሆነ እናውቃለን ሃይአበዘቄርሎስ በእነዚህ ሁለት ምሳሌዎች እንደተመለከትነው ሁለት የተለያዩ ባሕርያት ያላቸው አካላት ተዋሕደው ያለመለያየት ያለመጠፋፋት አንድ ባሕርይ ስለሆኑ ተዋሐዱ ይባላል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥግው ቃል ሥጋን የተዋሐደ የእግዚአብሔር ቃል ነው ከተዋሕዶ በኋላ መለያየት አንችልም ይህ የመለኮት ነው ይህ የሥጋ ነው አይባልም ሁለቱ በፍጹም ተዋሕዶ አንድ ሆነዋልና ለምሳሌዐ ጌታችን የሠራቸው ተአምራት ለዚህ ማስረጃ ይሆናሉ ዓይነ ስውሩን በምራቁ አፈር ለውሶ በመቀባት አዳነው ምራቅ የሥጋ ገንዘብ የነበረ ተአምር የመሥራት ኃይል ያልነበረው ሲሆን አሁን ግን ሥጋ ፍፁም ከመለኮት ጋር ተዋሕዷልና ጌታችን በምራቁ ዓይን አበራ ይህን ዓይተን ተአምር የሠራው በሥጋው ነው በመለኮት ነው ብሎ መነጣጠል አይቻልም ጌታችን ከሐዋርያት ጋር በታንኳ ሲጓዝ አንቀላፋ ጌታ ሆይ ጠፋን ብለው ቀሰቀሱት ተነሥቶም ነፋሱን ገሠፀው እዚህ ላይ ከሥጋ ጋር የተዋሐደ መለኮት ሥጋ ሲያንቀላፋም አለ መለያት የለባቸውም ጌታ ተነሥቶ ማዕበሉን ገሠፀ ከላይ እንዳየነው ማንቀላፋት የሥጋ ባሕርይ ነውና ተኛ በመቀጠል ተነሥቶ ማዕበሉን ፀጥ አደረገው ባሕር መገሠዕ ፍጥረታትን ማዘዝ የመለኮት ባሕርይ በመሆኑ ይህንን አደረገ እያሉ መለያየት አይቻልም የተኛውም ተነሥቶ ማፅበሉን ፀጥ ያደረገውም አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው በመሆኑ ይተኛይበላይጠጣተአምር ይሠራ ሙት ያስነሣ ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ነሥቶ ሰው የሆነ አምላክ ነው ስንል ሰው በመሆኑ በባሕርይው ተዋራጅነት የለበትም። ቅዱስ አትናቴዎስ እንደተናገረው ሀ ሞት ከእኛ ጋር ተዋሕዶ ይኖር ነበርና ሞትን ይሽረው ይነቅለው ዘንድ መለኮት ከእኛ ሥጋ ጋር ተዋሐደ ለ ዲያብሎስ በእባብ ሥጋ ተሰውሮ አዳምና ሔዋንን አሳስቷቸው ነበርና መለኮትም የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ ድል ነሳው ምሥጢርን በምሥጢር መመለስ የእግዚአብሔር ጥበብ ነውና ጌታችን አየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ያስተምር በነበረበት ወቅት ሙት ያስነሣድውያንን ይፈውስማዕበሉን ይገሥዕ ነበር እነዚህ በፍጡር ሊሠሩ የማይችሉ ናቸው እርሱ አምላክ ስለሆነ አድርጓቸዋል በሌላ በኩል ይራብይጠማመከራ ይቀበል ነበር አምላክ የማይራብ የማይጠማ መከራ የማይቀበል ነው እሱ ግን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነውና ይህንን በፍቃዱ አድርጎታል ይህንን ለይተን እዚህ ላይ አምላክ ነበር በዚህ ቦታ ሰው ሆነ አንልምል ይልቅስ ወልደ አብ ወልደ ማርያም የአብ ልጅ የማርያም ልጅ ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው በመሆኑ ይህን አደረገ እንላለን እንጂ እሱ በተዋሕዶ አንድ ባሕርይ በመሆኑ የሥጋንም የመለኮትንም ሥራ ሠራ በእርሱ ባሕርይ ተከፍሎ መለያየት የለበትም።