Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
መጋጄዩቐክጨራ ብርቅርቅታ ፖረፇረታ ከዳንኤላ ስቲል ተርጉም በዓቢይ ደምሴ ብርቅርቅታ ብርቅርቅታ ሠ ክፍል ሶላንጅ እንደማኅተም በልብህ እንደማኀተም በክንድህ አኑረኝ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨክነች ናትና ርመ ጋጅ ብርቅርቅታ ምዕራፍ አንድ ከሚወርደው ዶፍ ክብደት የተነሳ ቀኑ የቀን ጨለማ ሆኗል በኔፕልስ ከተማ ዙሪያ ባሉት ተራሮች ላይም እያፏጨ የሚያልፈው ነፋስ ደም ስር ይጠዘጥዛል አጥንት ሰርስሮ ይገባል የዎከር ከንፈሮች በድን ሆነዋል ጣቶቹም ደንዝዘዋል ሱስ ቢያቅበጠብጠውም ቆርጦ ያስቀመጣትን ቁራጭ ሲጋራ በዝናቡ በስብሳ ፍርክስክስ አለች ያን ጊዜም በርህራፄ አመለካከት አየችው ዎከር እሺ የምትለው መስሎት ፊቱ ፈካ እንደ ማለት አለ ልጅቱ ግን አሁንም ራሷን አወዛወዘችና ስለማልችል አዝናለሁ ብላ ጥላው ፈጠን ፈጠን እያለች ተራምዳ ሄደች አሁን ግን ምከር አልተከተላትም ቢከተላትም ዋጋ እንደማይኖረው ያውቃል ያገኘው አንድ ተስፋ ጭላንጭል ብቻ ነበር በአነጋገረችው ወቅት ወደ ጣቶቿ አየት አድርጎ ቀለበት አለማድረጓዓን ልብ ብሏል አላገባችም ነበር ማለት ነው።
መጋጄዩቐክጨራ ብርቅርቅታ ፖረፇረታ ከዳንኤላ ስቲል ተርጉም በዓቢይ ደምሴ ብርቅርቅታ ብርቅርቅታ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው ልዘ ዌከክኬ ርዩየኘ ቄ የመጀመሪያ ዕትም ሶስተኛ ዕትም ዋና አከፋፋይ ዓይናለም መጻህፍት መደብር ለራሔል ዓቢይ አድራሻ ከብሔራዊ ቴአትር ጀርባ እና ስልክ ለታናናሽ እህቶቿ ሞባይል ለኤልሳቤጥ ለሴቤተልሔም ለኢየሩሳሌም ይሁንልኝ የኮምፒውተር ለቀማና ገፅ ቅንብር ትዕግስት ንብረቱ ስልክ ዐ ዐ ብርቅርቅታ እንደሚታወቀው ተርጓሚ እጅግ ቭዙ ከሆኑ የፈጠራ ሥራዎች መካከል አማርጦ ጥሩ የመሰለውን ለአንባቢ የማስታዋወቅ ዕድል አለው የተርጓሚ ጭንቀቱ የትኛውን ሥራ ልምረጥ ብሎ ከመዋተቱ እንጂ ከተለያዩ ከያኒያን አእምሮ የፈለቁትን ስራዎች ወደ ፈለገው ቋንቋ ለመመለስ ችሎታው አስከፈቀደለት ድረስ ምርጫው ወሰን የለውም ስለዚህም ነው እኔም ቀደም ሲል ጃኩሊን ና ሳልሳዊቷ ልጃገረድ የተባሉትን የእግሊዛዊቷን የአጋታ ከሪስቲን ልቦለዶች እንደተረጐምሁኝ ሁሉ ወደ ሩቅ ምስራቅ ተሻግሬ የዘለዓለማዊውን ቻይናዊ ደራሲ የሉህ ሱንን ትዝታን በፀፀት ወደ አማርኛ ለመመለስ የሞከርኩት ይህ የአሁኑ አራተኛ የትርጉም ሥራዬ ደግሞ ወደ አውሮፖና አሜሪካ አህጉሮች የሚወስደን ነው ዕውቋ ደራሲ ዳኒኤላ ስቲል ክላይደስኮፐ በሚል ርዕስ የፃፈችውን ልቦለድ ብርቅርቅታ የሚል ስያሜ በመስጠት ወደ አማርኛ ተርጉሜዋለሁ አተረጓጐሜም ቃል በቃል ሳይሆን የተዛምዶ ትርጉም ነው አንዲህም ያደረግሁት ያለምክንያት አይደለም የዚህ የፈጠራ ሥራ ዋነኛ ጭብጥና ሥነ ፅሑፋዊ ለዛ አንደተጠበቀ አንዲሆን አስፈላጊውን ጥረት ሳደርግ በሌላ በኩል ግን ፅሑፉ ከሚተረጐምለት ሕብረተሰብ ባህል ወግና ሥነልቦናዊ ግንዛቤ ጋር ፍፁም የማይጣጣሙ ወይም እንግዳ ይሆናሉ የምላቸውን አንዳንድ አመለካከቶች አስወግጃለሁ በተረፈ ግን ደራሲዋ የጠቆመቻቸው ታሪካዊ ጂኦግራፊያዊም ሆነ ሌሎችም ተጨባጭ ገፅታዎች ፈር እንዳይለቁ በቂ ጥንቃቄ አድርጌአለሁ ስለሆነም አንዳንድ ገለፃምችና ምልልሶች የፅሑፉን ይዘት እንዳያጐድፉና ለፍሰቱ መጠበቅ ሲባል ቢዘለሉ ሆነ ተብሎ ለመደረጉ አንባቢያን ከወዲሁ እንዲያጤኑልኝ አሳስባለሁ ለማጠቃለል ይህ የትርጉም ሥራ አማርኛ አማርኛ ብሎ እንዲነበብ ጥረት ከማድረግም ባሻገር እንዲያዝናናና እንዲያስተምር በጥንቃቄ የተደከመበት መሆኑን በተጨማሪ እገልፃለሁ ተርጓሚው ብርቅርቅታ እሐይወሥ ስልምልምታ ዝልፍልፍታ ጭልምልምታ ፍልቅልቅታ ውልብልብታ ብርቅርቅታ እውነትም ሕይወት እንደማለዳ ፀሐይ ብርሃን ስትፈነጥቅ አንደባህር አልማዝ ስትፍለቀለቅ እንደሳት ላንቃ አብረቅርቃ ከቀትር ፀሐይ በርታ ደምቃ ስትጀምር ማለት ድንግዝግዝ መባባት አይቀር መተከዝ ሕይወ ፀፀት ትዝታን ደርድራ ምኞትን ከህልም አዋቅራ በብቸኝነት ስታማቅቅ ቀን ክሌት አትል ስታስጨንቅ ሕይወታ ብርቅርቅታ ናትና ታበራለች ቀን ጠብቃ እንደጨለመች አትቀርም እንዳኩረፈች ተደብቃ ውሎ ቢያድርም ታበራለች በሕብረ ቀለም አሸብርቃ ጋሕይወ ድቅስቅስታ ዝውርውርታ ጥብርብርታ ጥንጥን በረቅ ብልጭልጭታ ብርቅርቅታ ብርቅርቅታ ሠ ክፍል ሶላንጅ እንደማኅተም በልብህ እንደማኀተም በክንድህ አኑረኝ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨክነች ናትና ርመ ጋጅ ብርቅርቅታ ምዕራፍ አንድ ከሚወርደው ዶፍ ክብደት የተነሳ ቀኑ የቀን ጨለማ ሆኗል በኔፕልስ ከተማ ዙሪያ ባሉት ተራሮች ላይም እያፏጨ የሚያልፈው ነፋስ የጆሮ ታምቡር ይበሳል ውሽንፍሩም የዓይን ቆብ አያስገልጥም ዎክር የለበስውን የዝናብ ካፖርት ክሳድ ከጆሮው በላይ ድረስ ጎትቶ ብርድ ያቆረፈዳቸው እጆቹን ወደ ጠመንጃው ቃታ መለሰ ያቺም የቆምባት የቀበሮ ጉድጓድ መለስተኛ ኩሬ ሆናለች ሳም ዎክር የፃያ አንድ ዓመት ወጣት አሜሪካዊ ሲሆን ወደ አውሮፓም ለመምጣት ምክንያት የሆነው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ነበረ ዎከር ለመጀመሪያ ጊዜ በጦር ሜዳ ላይ የዋለው በሰሜን አፍሪካ ነው በዚያም ለነበረው የአሜሪካ ጦር የሜዲትራንያንን ባህር አቋርጦ ከዋናው የጣልያን ግዛት ለመድረስ ዓመት ከመንፈቅ ፈጅቶበታል ጦሩም አሁን መሽጉ የነበረው ከኔፕልስ ክተማ በስተ ስሜን ምስራቅ ነበር ሳም ዎከር የሰሜን አፍሪካ ትዝታ በታወሰው ቁጥር ያንገሸግሽዋል ሐሩሩ ያሳብዳል ሙቀቱ ፅርቃን ያስኬዳል የበርሃው ነፋስ የሚያንገዋልለው የአሽዋ ሞገድ ግማሽ ዕውር የደርጋል ቀኑን ሙሉ ዓይን አንደለበለበ እንዳስለቀሰ ነበር የሚውለው የዛሬ የኔፕልስ ከተማ አካባቢ ዶፍና ውሽንፍር ግን ከዚያ የባሰ የሚሸነቁጥ ሆነበት በምሽጉ ዙሪያ ያለማቋረጥ እያፏጨ የሚያልፈው ነፋስ ደም ስር ይጠዘጥዛል አጥንት ሰርስሮ ይገባል የዎከር ከንፈሮች በድን ሆነዋል ጣቶቹም ደንዝዘዋል ሱስ ቢያቅበጠብጠውም ቆርጦ ያስቀመጣትን ቁራጭ ሲጋራ ከክንፈሩ ለማድረስ ክብሪት ጭሮ ለማቀጣጠል አልቻለም ያን ጊዜም ነበረ የረገመውን ሰሜን አፍሪካን ማረኝ ወደ ማለቱ የተቃረበው ሳም ዎከር በጄኔራል ክላርክ በሚመራው ክፍለ ጦር ውስጥ የኛው እግረኛ ሻለቃ ባልደረባ ነበር ክፍለ ጦሩ የሲሲሊን ደሴት በሐምሌ ወር በድል አድራጊነት ከያዘ በኋላ ከኔፕልስ ለመድረስ አራት ወራት ፈጅቶበታል አሁን ደግሞ ወደ ሮም ከተማ በመግፋት ላይ ነበርር ሆኖም ባላንጣው የጀርመን ጦር በቀላሉ የሚበገር ኃይል አልነበረም ብርቅርቅታ ስስቪህ ስእያንዳንዲ ጋት መሬት አይከፍሉ መሥዋዕት መክፈል ነበረበት ለሮም የሚደረገው ጦርነት አጅግ አዝጋሚ ሲበዛ የሚዘገንን ነበር የሁለቱም ተፋላሚዎች ደም እንደውሃ ፈሶበታል በኔፕልስ አካባቢ ሽለቆና ተራሮች ጋራና ሸንተረሮች ላይ በአልፍ የሚቆጠሩ ወጣቶች ረግፈውበታል ፄ ዎክር የደነዘዙ ጣቶቹን እፉ ውስጥ ከቶ ከሆዱ በሚወጣው ሞቃት አየርነፍስ ሊዘራላችው ሞከረ ከዚያም እጁን ወደ ኪሱ በመክተት ቁራሟን ሲጋራ አውጥቶ ከከንፈሩ ሰካት የነበረው የመጨረሻው የክብሪት እንጨት ግን ውፃ ገብቶት ቶሉ አልጫልርህ በማለቱ እስከዚያ ከከንፈሩ ላይ ያደረጋት ቁራጭ ሲጋራ በዝናቡ በስብሳ ፍርክስክስ አለች ያን ጊዜም በንዴት ሺት ብሎ የክብሪት ቤቱን ከቅል ጥሙ ድረስ ካጠለቀው ኩሬ ውስጥ ወረወረው ጃፓን የአሜሪካ ይዞታ የነበረችውን የፐርል ወደብ በአውሮፕላን በደበደበች ጊዜና አሜሪካም በጃፓን በጀርመንና በጣሲያን ላይ ጦርነት ባወጀችበት ወቅት ዎክር የዝነኛው የሐርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበር ዎከርም የሚታየው ሆሉ አንደ ቀድሞዎቹ የሐርቫርድ ምሩቃን አርሱም ትምህርቱን ጨርሶ ወፍራም ደምወዝ የሚያስገኝ ሥራ ሲያማርጥ የገጠርና የክተማ መኖሪያ ቤት ሲኖረው ትዳርም መስርቶ የልጆች አባት ሲሆን ነበር ወላጆቹ በአስራ አምስት ዓመት እድሜው በአደጋ ሰሰሞቱበት በሐርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ለመከታተል ለሦስት ዓመታት ያህል በትርፍ ሰዓቱ በትያትር ቤት ውስጥ በተላላኪነት ጉርሻ እየተሰጠው ስርቷል ታላቅ እህቱ የነበረችው ኢሲንም ከራሷ ተርፏት ለርሱ የምትረዳው ሴት አልነበረችም በወታደርነት በመመልመሉም ሲሰናበታት በሔደ ጊዜ ቡና ቤት ውስጥ ተቀጥራ ስትሰራ ነበር ያገኛት ኢሲን በታናሽ ወንድሟ ወደ ጦር ሜዳ መላክ ቅንጣት ያህል ሐዘኔታ አልተሰማትም እንደ እህት ክአንገቱ ተጠምጥማ አልቅሳ ልትሸኘው ቀርቶ በደህና ተመሰስ የሚለውን የተለመደ የበጎ ምኞት መግስጫ እንኳን ነፍጋዋለች ሴት አዳሪዋ ኢሊን ዎክርን የምትጠላበት ምክንያት ነበራት ዎክር ከሕፃንነቱ ጀምሮ ብሩህ አአምሮ የነበረው ልጅ ነበር በትምህርቱ የሦስት ዓመት ታላቁ የነበረችውን ኢሊንን ቀድሟት በመሔዱ በወላጆቿ የተጠላች የአካባቢውም መዘባበቻ ሆና ነበረ በዚያም ላይ ደግሞ ዎክር መልክ መልካም ተግባቢ ልጅ ሲሆን እንደ ፀጉሯ መቅላት ደመ ፍሉ የነበረችው ኢሲን ግን ቀጭንና ያለ ዕድሜዋ የበሰለች ተንኮለኛና ምላሰኛ ልጅ ነበረች አሥራ ሦስት ዓመት እንደሞሳትም ክአንድ ጎረምሳ ብርቅርቅታ ጋር ኮበለለች ከዚያን ወዲህ ብዙ ወንዶች አቀያይራለች ዎክርም ሊሰናበታት በሄደ ጊዜ በስድስት ዓመት ታናጂ የሚሆን የአስራ ስምንት ዓመት ጎረምሳ ቅምጥ ነበረች ጎረምሳው ስራ አልነበረውም ኢሊን ከቡና ቤት በሚከፈላት አነስተኛ ደመወዝና ሲቀናትም ከሌላ ወንድ ጋር በመውጣት በምታገኘው ገንዘብ ነበር የሚተዳደሩትቡ ሆኖም ኢሊንም ሆነች ያ ጎረምሳዋ የሚያድሩት ክሞቀ ቤት ነው የምግብና የመጠጥ ችግር አልነበረባቸውም በልብስ አልታረዙም ዎከር ግን በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ ዓመት ተማሪ ነበር በወታደርነትም ተመልምሎ መጀመሪያ ወደ ሰሜን አፍሪካ ተላክ ዓመት ከመንፈቅ በሰሜን አፍሪካ በረፃ ሲዋጋ ቁቀየ ከዚያም እረፍት ሳያገኝ ወደ ሲስላ ብሎም ወደ ኔፕልስ መጣ አሁን ደግሞ ወደ ሮም አቅጣጫ በሚወስደው የጦር ሜዳ ላይ ይገኛል ታዲያ ዎክር እንደልቡ የሚያጨሰው ሲጋራ እንኳን አላገኘም ምናልባት ዕድለኛም ከሆነ ሮም ይደርስ ይሆናል ሮምን መያዝ ማለት ደግሞ የጦርነት ማብቂያ ነው ማለት አልነበርም ስለሆነም ከሮምስ በቷሳ የሚጠብቀው ምን ዕድል ነበረ። አለው ከጐኑ ጐኑ ይራመድ የነበረው ፓተርሰን ዎክር ቆሞ ፓተርሰንን አየት አደረገውና ቶሎ ሲል ከዓይኖቹ እንዳትሰወርበት ስሰፈራ ወደ ልጅቷ ተመለሰ ለፓተርሰንም መልስ ሳይሰጠው የእርምጃውን ፍጥነት ጨመረ ፓተርሰንም ልጅቱን ያያት በዚያን ጊዜ ነበረ እንደ አጋጣሚ ገልመጥ ብላ ስለነበረ መልኳን ለማጤን ዕድል አገኘ ውበቷ ዓለማዊ አይመሰልም ነበረ ቁንጅናዋንም ልዩና ፍፁም የሚያደርገው ደግሞ አንድ የተለየ ፀጋ ነበራት አረን ጓዴዎቹ ትላልቅ ዓይኖቿ የብርሃን ጨረር የሚወረውሩ ይመስሱ ነበሩ ለሰኮንድ ፍንካችም ቢሆን እነኛ ዓይኖች በዎክር ላይ ማረፋቸውን ፓተርሰን ተመልክቷል ክብርህን ጠብቅኮ የሚል ማስጠንቀቂያ የሚያስተላልፉ ነበሩ ዎክር ፈረንሳይኛ ለመናገር ባለመቻሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን የረገመው በዚያን ቀን ነው የልጅቱም ግልምጫ እንደ አሳት የሚስበ ልብ ነበረ ያም ሆኖ ልጅቱን የመከታተል ስሜቱ ይበልጥ ጠነከረ ወደ ፊት ሰፊቱም እያየ ይቺን የመለሰች ልጅ አይተህ ታውቃለህ አለው ፓተርሰንን መልስም ሳይጠብቅ በዓስም ውስጥ ተወዳዳሪ ብርቅርቅታ የማይገኝላት ውብ ናት ሲል ዎከር በተጨማሪ ተናገረ በአርግጥም ያቺ ልጅ እንደ ሌሎቹ የፓሪስ ልጃገረዶች ፖሪስን ነዓ ባወጡት የቃል ኪዳን መንግስታት ወታደሮች ላይ ከመንገድ ዳር ቆማ አበባ የምትበትን ዓይነት አልነበረችም እንደ ሌሎቹም ከወታደሮቹ አንገት ተጠምጥማ ደስታዋን የምትገልፅ ልጅ አይደለችም ህለመናዋ ፀዳል የሚያንፀባርቅ ቀንበጥ ገላ ያላትና በሩቅ የምትማርክ ልጅ ነበረች በጀርመን አገዛዝ ሥር ያሳለፈቻቸው እነቿ አራት የግፍ ዓመታት እንኳን አንደ ሌሎቹ ቅስሟን አልሰበሩትም እንደ ሌሎችም አንገቷን አላስደፏትም በመሆኑም በማንም ሆነ በማን የምትደፈር ዓይነት ልጅ አልነበረችም እንዳልከው በጣም ቆንጆ ናት ግን አስተያየቷ ስሳላማረኝ ብንመለስ ይሻል ይመስልሀል ሲል ፓተርሰን አለሳልሶ ተናገረ እንመለስ አለና ዎከር ጮኸበት ይልቁኑስ በምታውቀው ቋንቋ የሆነ ነገር አናግራት እነስ አላበድኩም ጌታዬ። » ሲል ዎከር ፓተርስንን ጠየቀው ፓተርሰን ልጅቱ ያለችውን መልሶ ለመናገር ዕፍረት ስለሰተስማው ዝም አለ ዎክር ደግሞ ስላነጋገረችው ብቻ የልብ ልብ ተስማውና ፈጠን ፈጠን እያለ ተከተላት ፓተርሰን ከዎከር ጋር ከተዋወቁባት ዕለት ጆምሮ ብርቅርቅታ እንደዛን ቀን ቂላ ቂልና ሐሳበ ግትር ሆኖበት አያውቅም ስለ ሴቶችም ቢሆን ሁሰቱም ከልምዳቸው አኳያ የተጫወቷቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ ፓተርስንም በዓይኑ እንዳየው ዎከር ለሴት በቀላሉ የሚሸነፍ ወጣት አልነበረም በሮም ከተማ ባሳሰፉቸው ቀናት ውስጥ ፓተርሰን ከአንዷ ሴት ወደ ሴላዋ ሲል ዎከር ግን ቁጥብ ሆኖ ነበረ የከረመው ዛሬስ ዎክር በአር ላይ መን ለምንድን ይሆን ሲል ፓተርስን ተገረመ ቢፈራና ክትትሉንም ቢያቋርጥ ሲተረጉምለት ፈጠ ያቋ ሲል ልጅቱ የተናገረችውን እማ ዎከር። አለው አሁንም ፓተርሰን። ከዕድሜህ በሳይ አመዛዛኝ ሰው ትመስለኝ ነበር ግን ዛሬ ምን እንደነካህ አላውቅም አኔ ግን ልሄድ መሆኑን እንድታወቀወ አለና ፓተርሰን ጥሉት ሊሄድ ሲል ዎከር ፃሳቡን ቀየረና ተከተለው በየሄዳበትና በየደረሱበት ሁሉ ለዎከር የምትታየው ያቺ ልጅ ብቻ ናት ከፊቱ ድቅን ትልበታለች ክአረንጓዴ ዓይኖቿ ውስጥ ያነበበው የሀዘን አመለካክቷ ልቡን አስጨንቆታል የአለባበሷም መጉሳቆል ሆድ ሆዱን በልቶታል እሺ የማለቷ ነገር አጠራጣሪ ሆነበት እንጂ ያቺን ልጅ ለማስደሰት የተጠየቀውን መስዋዕት ለመክፈል ፈቃደኛ ነበር አራት ከበሉ በኋላ ፓተርሰን ከሶስት ልጃገረዶች ጋር በመዳራት ላይ እንዳለ ዎከር ጣለውና ተሾልኮ ወጣ ከቪቢያም በዱአርኩል ጉዳና አድርጉ በሰዬን ወንዝ ላይ ወደ ተሰራው ድልድይ አመራፅ ድልድዩንም ተሻግሮ ወደ ሞንትቤል አውራ ጎዳና ታጠፈ ብዙ ከተጓዘ በኋላ ከግራንድ ዲግሪ መንገድ ደረሰ ወደ ልጅቱም ቤት አቅጣጫ አሳብሮ ሄደ ከበራፍም ቆመና ጥቂት ሲያስብ ቆቁየ ከዚያም ከፊት ለፊቱ ወደ ነበረው ቡና ቤት ገባና ከልጅቱ በር ትይዩ የነበረ ወንበር መርጦ ተቀምጦ ቡና እዘበ ያንንም መራራ ቡና መጠጣት ጀመረ ዓይኖቹ ግን በዚያች ልጅ ቤት በር ላይ እንደተሰኩ ነበር በሩ ከአሁን አሁን ተከፍቶ ልጅቱ ትወጣለች ብሎ ሲጠብቅ ሲጠብቅ ቆየ በራፉ ግን አንዴም አልተከፈተም ዎከርም ከተቀመ ጠበተ አልተንቀሳተሰም በመጨረሻ ላይ ልጅቱ ቀን ከፄደችበት አቅጣጫ ስትመለስ አየ በአጂም መዓህፍ እንደያዘች ነበረች ደረጃዎቹን ወጥታ ከበራፍ እንደደረሰች የሳንቲም መያዣዋን ቦርሳ ከፍታ ቁልፍ ትፈልግ ጀመር በዚያን ጊዜም ዎከር ጥቂት ሳንቲምች አውጥቶ ከጠረጴዛው ላይ ቫኖረ በኋላ አየተቻኮለ ጠጣ ሮጠናም መንገዱን አቋረጠ ልጅቱም የሩጫ ኮቴ በመስማቷ ተደናግጣ ዝወር አለች ከምከርም ጋር ዓይን ለዓይን ተጋጩ ወደኋላዋ ለማፈግፈግ እንደ መከጀል ብላ ነበር ሆኖም መፍራት እንደማይኖርባት ደግሞ ወዲያውኑ ተሰማትና ባለችበት በልበ ሙሉነት ቆመች ዛሬ ነጻ በወጣችው ፓሪስ ሳይሆን በጀርመን ይዞታ ስር በነበረችበትም ወቀት ቢሆን ያቺ ልጅ የፍርፃት መንፈስ አሳይታ አታውቅም አና አሁንም ዎክርን ባየችው ጊዜ አመለካከቷ የመደንገጥ ሳይሆን የመሰልቸት ነበረ ብርቅርቅታ ለዎክር አድራጎቱ ሁሉ የህጻን መስሉ ተሰማው ልጅቱንም በማስቸገሩ ተፀፀተ ሆኖም አንድ ጊዜ አድርጎታልና ከእንግዲህ ወደኋሳ መመለስ እልቻለምፅ ድፍረትም በመጨመር ወይዘሪት እንደምን አምሽተሻልሦ ሲል ሰላምታ ሰጣት አናት ህጻን ልጂ ሲባልግ ሰታየው እራሷን በማወዛወዝ እንደምትገስጸው ሁሉ ያችም ልጅ በትዝብት እራሷን አወዛወዘችና ጥጭርኳ ሹመ ፐርሴዩቬ። ከልብ ብሎ ነገር የለም አለችው ብርቅርቅታ ለምን። ማስተከዝ ማስሰቀሱ ከዚያ በፊት ደርሶበት አላየውም የዚያኑም ያህል ደግሞ ፍቅር ሕይወትን ለዛ የሚያላብስ የሚያድስ የሚያስደስት የሚያስፈነድቅ ነበረ እነሂህ ስሜቶች ሁሉ ዎክር ሶላንጅን ካያት ደቂቃ ጀምሮ ጐሻሽመውታል ከሁሉም በላይ ደግሞ ፍቅር መተሳስብንም የሚያጉለብት ኃይል ነበረ የሶላንጅ መጐሳቆል ምከርን ሲበዛ አሳስቦታል የሰውነቷን መክሳት ልብ ብሎ አይቶታል ልብስና ጫማዋም እንደነገሩ ነበረ የሶላንጅ በራስ የመተማመን ስሜት ላለመንካት ዎክር መጠንቀቅ ነበረበት ስለ ልብስና ጫማዋ ጉዳይ ጊዜ ያደርሰዋል ሆኖም ፓሪስን ከመልቀቁ በፊት ለሶላንጅ አንድ ነገር ማድረግ ነበረበት የተጠመደባቸውን እነኛን አረንጓዴ ዓይኖቿን ስማየት ብቻ ሳይሆን ሶላንጅን በየቀኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ እያገኘ ደህና ምግብ መጋበዝ ነበረበት ዳግመኛ ካልተገናኘን ሲል ዎከር እንደ ልማዱ ሙዝዝ አለባት እርሷም በረጅሙ ተነፈስች ማንነቷን ደህና አድርጋ ብታውቀውም ከዎክር ጋር ስአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማግስቱ ለመገናኘት እሺ አለችው ፓሪስ በጀርመን ይዞታ ሥር በቆየችባቸው ዓመታት ውስጥ ከአንድም የጀርመን ወታደር ጋር ተነጋግራ አታውቅም ፓሪስ በአሁኑ ጊዜ ነዛ ስስወጣች ደግሞ ሶላንጅ እንደ ሌሎቹ ልጃገረዶች ከአሜሪካ ወታደሮች ጋር የመታየት ፍላጐት ጨርሶ የላትም ከፊቷ ተቀምጦ ይለማመጣት የነበረውን ወታደር ግን ትክ ብላ አየችው በመልኩም ሆነ በፀባዩ የሚጠላ ልጅ ዓይነት አልነበረም አመስግናለሁ አስና ዎክር ከመቀመጫው ተነሳ እንዳመጣ ጣቸው መህፍቱን በግራ እጁ እርሷን ደግሞበቀኝ እጁ ይዞ መንገዱን አቋረጡ ደረጃውንም ወጥተው ከበራፉ ሲደርሱ ቆም አሉ ሶላንጅ ስለ ግብዣው አመስገነችውና ደህና እደር ስትል እጁን ጨብጣው ገባች ከበስተውስጥም በራፉን ቆለፈች ብርቅርቅታ ዎከር በዚያን ምሽት በፓሪስ ጐዳናዎች ላይ ብቻውን በሚጓዝበት ወቅት በሕይወቱ ላይ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን አውቆታል ከአንግዲህም የዱሮው ግዴለሽና ደፋሩ ዎከር ስመሆን አይችልም በጥቂት ስዓታት ውስጥ አስተሳስቡ ተለወጧል ያቺ ልጅ ያቺ ልዩ ፍጥረት ያቺ ባለአረንጓዴ ዓይን ልጅ ያጋጠመችው ያለምክንያት አስመሆኑም ገብቶታል ከአሁኑም እንደ ግማሸ አካሉ ያህል ቆጠራት ብርቅርቅታ ዴጫ ጩ ምፅራፍ ሁለት ጥት ነው ትናንትና ማታ ያመሸኸው። የዱሮው ብቸኝነቷ በተሻላትም ነበረ በገዛ እጂ መድኃኒት የማይገኝስት ፍቅር የሚሉት በሽታ ገዛች በህይወት እያሉ ስፍቅረኞች መስያየት ደግሞ ከሞትም የባሰ መራራ ነበረ ለሶላንጅ ሰቆቃ አንዳችም አፅናፒ ኃይል አይገኝለትም በመጨረሻውም ምሽት ከደረቱ ላይ ተኝታ ያስማቋረጥ ትንሰቀስቅ የነበረችውን ሶላንጅን ምከር ሊያፅናናት ሞከረ የጀርመን ጦር ዙሪያውን ተከቧል ከእንግዲህ በርሊንን ስለመያዝ ግፋ ቢል ሶስት ወር ቢፈጅ ነው ከሶስት ወራት በኋላ አብረን እንሆናስን ማለት ነው የገናን በዓል ብቻሽን አትውይም ሲል ከወርቅ የጠራ ፀጉሯን እያሻሸ ነገራት ዓይኖቿን ብርቅርቅታ ጄ ዱዴ ጉንጮቿን ከንፈሯን አፍንጫዋን ግንባሯን ሁሉ ተራ በተራ እየሳመ እንደ ህፃን ልጅ አባበላት ሶላንጅ የኔ ፍቅር ላንቺ ያለኝን ፍቅር ቃላት ሊገልፁት አይችሉም ልቤ የአንቺ ብቻ መሆኑን እምልልሻለሁ» አላት እንደ ሶላንጅ ያስች ልጅ የትም አላየም በፓሪስ ውስጥ በጣሊያን በሐርቫርድ አላሳጋጠመውም የመጀመሪያ ፍቅሩም ሶላንጅ ነበረች ጦርነቱ አንዳለቀ ወዲያውኑ ነው የምንጋባው አላት ዎክር ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ ዓይን ዓይኗን እያየ አሁንም እንባዋ አያቋርጥ እንጂ መልስ አልሰጠችውም እሺ በይኝ እንጂ ሶላንጅ ሲል መልሶ ጠየቃት መልስ ልትስጠው አሁንም አልፈስገችም ነበረ እንጋባስን ስትይ ቃል ግቢልኝ። ብዛታቸው ሶስት መቶ ዛያ አምስት ቪህ ይ የጀርመን ወታደሮች ተማረኩ በመጋቢት አስራ ስምንት ቀንም ከ ስራት ወደ ምዕራብ እየገፋ የመጣው የሶቭየቸ ጦርና ከምዓራብ ወደ ሰራቶ በመገስገስ ላይ የሚገኘው የአሜሪካ ጦኗ በቶርጋው መንደር ተገናች በርሊንም ሚያዝያ አንድ ቀን ተያዘች በስሜን አፍሪካ በርሃ በጣሊያን ተራሮች በፈረንሳይ ሸለቆዎችና በጀርመን ሜዳዎች ላይ የተ ደው የነዎክር የጦርነት ገድል በርሊን ላይ አበቃ ዎከርና ፓተርሰን ኣን ወንድማማች ተቃቅፈው አለቀሱ ከጐናቸው ብዙዎቹ ዓደ ያው ወድቀዋል ፓተርስን አይወደኝም የሚለው አለቃ እንኳን ያቺን ዕለት ለማየት ዕድል አላገኘም ነበረ ብርቅርቅታ ምዕራፍ ሶስት ለምክር የተሰጠው የሶስት ቀናት ፈቃድ ብቻ ነበር ከዚያ በኋላ ግን በቀጥታ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ ተነግሮታል እርሱም በቀጥታ ወደ ፓሪስ ሄደ ሶላንጆም ከበፊቱ ይልቅ የከሳች ብትመስልም እንደ ነበረች አገኛት በእነኛ በሶስት ቀናት ውስጥ እንደ ሁለቱ ፍቅረኞች ደስተኛ ሰው አልነበረም ስለዚህም እነፒህ ቀናት ለነሶላንጅ ፈጠነኑባቸው በመጨረሻም ዎክር ወደ በርሊን የሚመለስብት ዕለት ደረሰ ሶላንጅ ባቡር ጣቢያ ድረስ ሄዳ ሸኘችው ዎከር አሁን ልበ ሙሉ ነበረ ከእንግዲህ ከሶላንጅ የሚለየው ኃይል አይኖርም እሞታለሁ የሚለውም ስጋት ቀርቷል ስለዚህ ሶላንጅ ባቡር ጣቢያ ድረስ መጥታ ብትሸኝውም እንደማያሰቅስ ታውቆት ነበረ እርሷ ግን ራሷን በዎከር ትከሻ ላይ አድርጋ ለረጅም ጊዜ ስትንሰቀለቅ ቆየች ባቡሩም መንቀሳቀስ ሲጀምር ነበረ ምክርን የለቀቀችው ዎከር ለሶላንጅ ቀለበት አድርጐላታል ከዚያም በኋላ ነው መቀያየሪያ የሚሆኑ ልብስና ጫማ የገዛላት ለአራት ወራት ያህልም ሊረዳት የሚችል መጠነኛ ገንዘብ አስገድዶ ሊሰጣት በቅቷል ፓሪስ ውስጥ ሊጋቡ ይችሉ ነበረ ግን ዎክር ቀደም ሲል ወደ አሜሪካ ሔዶ ለመኖሪያቸው የሚሆን ቤት እንዲያዘጋጅ ተሰማሙ በተጨማሪም ከወታደርነቱ ስለሚስናበት ለመተዳደሪያቸው ሥራ ማግኘት ነበረበት ከዚያም ጥቂት ገንዘብ አጠራቅሞ ሊልክከላትና እርሷ በቱሪስት ስም ወደ አሜሪካ እንድትመጣ ተነጋግረው ጨርሰው ነበረ ሶላንጅ ባቡሩ ለዓይን እስኪለወር ድረስ በቀኝ እጂ የያዘችውን ነጭ መሐረብ በማውለብለበ ላይ ነበረች ባቡሩም እኩለ ሌሊት ላይ ከበርሊን ደረሰ ዎከርም በቀጥታ ወደ ጦር ለሰፈሩ ሄደ ፓተርለን ከመኝታ ክፍላቸው ውስጥ አልነበረም ፓተርለን የበርሊንን ልጃገረዶች ሲያማርጥ ነበረ ውሎውና አዳሩፊ ዎክርም ከአልጋው ላይ ጋደም አለና ሕርሱና ሶላንጅ ስለሚመሰርቱት ትዳር ሲያስብ ቆየ በዚያው እንቅልፍ ወሰደው ፓተርሰን የበርሊን ኑሮ ጥሞት ነበረና ለሁለት ሳምንታት ም ብርቅርቅታ የመቆየት ዕድል ተሰጠው ከዎከርም ጋር በኒዮርክ ከተማ ለመገናኘት ተቀጣጥረው ዎከር በማግስቱ ወደ አሜሪካ በረረ ከፎርት ዲክስ የጦር ሰፈር ደርሶ ከሠራዊት አባልነቱም እንደተሰናበተ ወደ ኒውዮርክ ሄደ። የሚል የጥርጣሬ ጥያቄ የሚነበብባቸው ይመስሉ ነበረ ሶላንጅን ወደ ሆስፒታል አንዳመጣት ሁሉ ወደ ቤትም መልሶ የወሰዳት ፓተርለን ነበረ ዎክር ግን በልምምዱ ከባድነት እያመካኘ እንደ ወትሮው ወደ ቤት ሰዓት ጠብቆ መምጣት ትቷል ቢመጣም እንኳን መስወጡን ሶላንጅ አይታለች ከልብሉም ላይ ጠረኑ የርሷ ያልሆነ ሽቶ ሸቷታል ሆኖም ሁሉንም በትዕግስት ልታሳልፈው ፈለገች በዎክር ላይ ካደረባት ቅናትና ጥርጣሬ ይልቅ ለርሉ ያላት ፍቅር ያመዝን ነበረ ስለዚህ ልቦናው አሰኪመለስሰት በሰላም ልትተወው ወሰነች አራሷም ልጅ ክርስትና በተነሳችበት ዕለት ዎከር በሉል ያጌጠ የአንገት ድሪ ስጦታ አበረከተላት ከፍተኛ ገንዘብ ያወጣበት መሆኑን ሶላንጅ ታውቃለች ሰበደሉ ማካካሻ መሆኑን ሶላንጅ ተስምቷታል በተለይም ለአራሷ የክርስትና አባት ለሆነው ለቅርብ ወዳጃቸው ለፓተርስን ደግሞ የስጦታው መልዕክት በይበልጥ ግልፅ ሆናለታል የአራሷን ልጅ ብርቅርቅታፎሚመ የክርስትና ፅለት በፍቅር በደስታ አክብረውት ዋሉ ፓተርሰንም ለአዲሷ የክርስትና ልጁ አሌክሳንድራ የሚል ስም አኣወጣላት ዎክር በርግጥም የተዐዐተ መስሉ ነበረ ለጥቂት ቀናትም ሰቤተሰቡ የነበረውን ፍቅርና አክብሮት ሲገልፅ ከረመ መሥራት ስለነበረበት ደግሞ ወደ ትያትር ቤቶች መሔድ ነበረበትቁዲስም ተውኔት በመዘጋጀት ላይ ስለነበረ ዎከር ውሉ ባደረ ቁጥር የተሰመደ ሰዓት ማሳለፉን አመጣ ቆየትም ሲል እስከናካቴው ማደር ጀመረ ሶላንጅን ሊያፅናና የሚችል አንድ ሰው ብቻ ነበረ ፓተርሰን በሶላንጅና በዎከር መካከል ገብታ ስለምታምሳቸው አዲሷ ወጣት ኮረዳ አንድ በአንድ ደርሶበታል ለሶላንጅ ግን ሊነግራት አልፈለገም አንድ ቀን ፓተርለንን ምሳ ጋበዘችውና በመመገብ ሳይ እንዳሉ የናንተስ ጋብቻ እንዴት ነጡ። አንቺን የመሰለች ሴት ለማግኘ ት ማንም ቢሆን ቀኝ እጁን በሰጠ አለ ፓተርሰን ዓይን ዓይኗን እያየ እጅ ለእኔ ምን ያደርግልኛል ፓተርሰን አለችና ዓይኖቿን አባበሰች ቀና ብላም ፈገግ አለችና እኔ አጅ አልፈልግም የምፈልገው ልብ ነው የዎከርን ልብ ብቻ ጥፋት ሰርቶ በመጣ ቁጥር ለመደለያ ጌጣ ጌጥ ገዝቶልኝ ይመጣል በሳጥን የሚሞላ ዕንቁና አልማዝ አለኝ ግን ያ ሁሉ ሰእኔ ምኔም አይደለም ድሃ ሆሼ ዎከር የግሌ ቢሆንልኝ እመርጣለሁ አለች ሶላንጅ ይገባኖ አለና ፓተርሰን በተራው ሲተከዝ ቆየ ፓተርሰን ለዎክር ሙሉ ነገረ ፈጅ ከሆነ ውሎ አድሯል በመሆኑም ሰሰዎክር ሀብት ይዞታ ያውቃል ሶላንጅ ስለ አልማዝና ዕንቁ ስታወራ ትዝ ያለው ነገር ነበረ ለርሷ ብቻ አልነበረም ዎከር አልማዝና ዕንቁ የሚገባው በየጊዜው የሚቀያይራቸውን ፍቅረኞቹን ዋጋቸው በናረ ጌጣ ጌጦች ያስጌጥም ነበረ ለዎክር ገንዘብ መጫወቻው ሆኗል ሰሆነ ላልሆነም መርጨት መርጨት ነበረ ሥራው በየቀኑ የሚቀያይራቸው ልብሶች በእንግሊዝ ሀገር የተሰሩ ሱፎች ነበሩ ከህናናቱ አሻንጉሊት ጀምሮ የሐር ቀሚሶቻቸውም ሆኑ የሶላንጅ ካፖርቶች ጭምር የሚመጡላቸው ከፓሪሰ እየተገዙ ነው ፓተርሰን ዎከርን ገንዘብ እንዲቆጥብ ደጋግሞ መክሮታል የዎከር ገንዘብ ግን በገባበት መጠን መውጫ ቀዳዳ ይፈልጋል ምን ማድረግ እንደሚሻለኝ አላውቅም እምርሬ ልናገረው እቆርጥና ወዲያውኑ ደግሞ ሆዴ ይዋልልብኛል ዎከር ተመልሶ የእኔ መሆኑ ላይቀር አላሰቀይመው ስል አስባለሁ እስካሁንም መመለሱ አልቀረም አለችና የፖተርሰንን ዓይኖችእያየች ፈገግ አለች ፖተርሰንም በአድናቆት ሲመለከታት ቁቀየና እንደ አሜሪካዊ ሴቶች ሳይሆን ሚዛናዊ አመለካከት ያለሽ ልጅ ነሽ ይህን ጊዜ የአሜሪካ ሴቶች ቢሆኑ ኑሮ ስንት ጉድ ባፈሉ ነበረ ባላቸውን በምስጢር የሚከ ታተል ሰው ይቀጥራሉ ሰውየው መረጃ ያለባስባል ባልየውም በህግ ይከለስና ከፍተኛ ካሳ እንዲከፍ ይደረጋል አለ ፓተርሰን ጣሳ አልክ ፓተርሰን። አለች ሶላንጅ ከልቧ እንግዲህ መበርታት ይኖርብሻል ወደ አንቺ መመለሱ የማይቀር ነው አሁን የሚያደርገው ሁሉ ለርሱ ጨዋታ መስሎ ነው የሚታየው ይህንንም አውቀሽ መፅናናቱ ላይ ነው ቁምነገሩ አለ ፓተርሰን ጥሩ ምክር ነበረ በመጨረሻ ሳይ ፓተርሰን የሰጣት እርሱም እንዳለው ታገሰች ባሏም ከስድስት ወራት በኋላ ወደርሷ ማሪኝ ብሎ ተመለሰ በዚያ ተውኔት ውስጥ ከዎክከር ጋር ተካፋይ የነበረችው ልጅ ሚስቱን እንዲፈታና እንዲያገባት ትነዘንዘው ነበረ ዎከር ግን ለጊዜው ሶላንጅን በሌላ ሴት ቢቀይራትም ልቡን እንድ ጊዜ ፓሪስ ጎዳና ላይ ላያት ባለወርቃማ ፀጉርና ባለ አረንጓዴ ዓይኖች ለግላጋ ወጣት ሰጥቶት ስለነበረ እንደማይቻል ነገራት ያቺም ተዋናይ ራሷን ለመግደል ሞክራ ነበረ ይህም ለርሷና ለዎከር መቆራረጫቸው ሆነ ዎክር ማሪኝ ብሎ ወደ ሶላንጅ ከተመለሰ በኋላ ቤተሰቡን ይኮ ለዕረፍት ወደ አውሮፓ ሔደ ዎከር ቀደም ሲል ባደረገው ዝግጅት መሰረት ወደ ተከራየው ሆቴል እመሩ ዎክር ወደ ሶላንጅ ሔደና አንገቷን አቅፎ ራሱን ክትከሻዋ ላይ እደረገና አለቀሰ ሶላንጅም በተራዋ ከደረቷ አስጠግታ አቀፈችውና የደሰታ እንባ አነባች እየተንከባለለ የሚወርደው አምባዋም የዎከርን ጥቁር ፀጉር እራሰው እንዳቀፈችውም ወደ መኝታ ቤት ገቡ ብርቅርቅታ ሶላንጅ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ክብረንፅህናዋን በፍቅር ለዎከር እንደሰጠችው ዛሬም ዎክር ቀሚሷን አወለቀላት አንደ ዱሮአቸውም ተኘ ። ማሪኝም አለና ከጭኖቿ ላይ ተደፋ ፀጉሩንም ስታሻሸው ቆየችና ከተንበረከከበት ደግፋ እያስነሳችው አዲስ ተውኔት አዲስ ሴት ዋ ዎከርኑ አለችና የሌባ ጣቷን አወዛወዘችበት ከትላልቅ አረንጓዴ ዓይኖቿ የሚስረቀረቀው ብርፃን የዎከርን ልብ እንደ ጦር ወጋው ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ያቺን ተዋናይ ፍቅረኛውን ላለማየት ቆረጠ የዎከርና የሶላንጅ ኑሮ ጤናማ አየር ሰፈነበት ሶላንጅም ለሦስተኛ ጊዜ ፀነሰች በዜናው እንደ ሂላሪና አሌክሳንድራ የተደሰተ አልነበረም ሶላንጅ ምጥ የተያዘችው ዎከር ለሥራ ወደ ካሊፎርኒያ በሔደበት ጊዜ ነበረ እንደ ልማዱም ከሐኪም ቤት ያደረሳት ያው ፓተርሰን ነው ዎከርን በስልክ ለማግኘትና በደህና ሴት ልጅ የተገላገሰች መሆኗን ለመንገር ሁለት ቀን ሙሉ ፈጅቶበታል የሶላንጅም የተለመደ ጥርጣሬ መታደስ የጀመረው በዚያን ጊዜ ነበረ ዎከር ዜናውን ቢለማም ተቻኩሎ አልመጣም አራሷ ክርስትና የተነሳችውም እርሉ በሌለበት ነበረ እንደ ፊተኞቹ ሁለቱ ሁሉ በቅርቡ ለተወሰደችው አራስ ፓተርሰን የክርስትና አባት ማርጆሪ የክርስትና እናት ሆኗት ዎክር ወደ ኒውዮርክ የተመለሰው ሶላንጅ በወለደች በሦስተኛው ወር ነው በዚያን ወቅት ስለ ዎከር አዲስ ግንኙነቶች መፅሔቶች ና ጋዜጦች ብዙ ፅፈዋል የሚነፍሰውም ወሬ ሶላለጅን እጅግ አድርጎ አስቆግቷታል ዎክር እንደ በፊቱ በአንዲት ሴት ሳይቆጠብ የሆሊውድን ቆነጃጅት ተራ በተራ ማዳረስ ይዞ ነበረ በተለይም ደግሞ በየዕለቱ መጠጥ ኣብዝቶ በመውለዱ ሳይሰክር የማያድርበት ቀን እንደሌለም ሶላንጅ ሰምታለች ደሟ እንደፈላ ነበር የዎክርን መመለስ ስትጠባበቅ የሰነበተችው ኤ ሙ ዴኢጵኢጵ። ፓተርሰን ነው። ሚ መመ ብርቅርቅታ ሲያመዛዝነው የሚተርፈው ገንዘብ በጣም አናሳ ነበረ ዎክር አስከሚፈታ ወራት ሲያልፉ ይችላሉ የተረፈው ገንዘብ ደግሞ ለሞግዚት ለስራተኛ ደመወዝ ተከፍሎለት ለህፃናቱ ምግብና ልብስ ሆኖ ሰዚያን ያህል ጊዜ የሚቆይ አልነበረም ዎከር የገንዘብ ፀር ነበረ ታዲያ ሶሳንጅም ብትሆን ከብኩንነት እንዲታቀብ ብዙ ጥራለች ምከር ግን ገንዘብ ከማጠራቀም መቸርን ይመርጥ ነበር ስለዚህም ፓተቄሰን ከፊት ሰፊቱ የነበሩትን ስነዶች አመሳክሮ ሲጨርስ የተገኘው ገንዘብ መጠን ከአስር ሺህ ብር አይበልጥም ነበረ ፓተርሰን ዎከርን ቁጥብእንዲሆን በጥብቅ ሊመክረው በተገባ አንደነበረ የተሰማው በዚያን ወቅት ነበረ ዎከር ልጆቹን ሰድርብርብ ችግር አጋልጧቸዋል ማለት ነው አስር ሺህ ብር ህፃናቱ ለሚኖሩበት ቤት የስድስት ወር ኪራይ እንኳን አይበቃም ነበረ ፓተርሰን ልጆቹን ወደርሱ ቤት ለመወሰድ በመፈለት ባለቤቱን ማርጆሪን አማከራት አርሷ ደግሞ ቀድሞውንም ቢሆን አነዎከርን ስለማትዉወዳቸው ልጆቹ አብረዋት በአንድ ጣሪያ ስር አንዲኖሩ አልፈለገችም ፓተርስን በማስተዛዘን ደጋግሞ ለምኗት ነበረ አርሷ ግን ይብሱኑ ከነፍሰ ገዳይ ልጆች ጋር አብሬ አልኖርም ስትል ከነጭራሹ ተስፋውን አስቆረ ጠቸው ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት አንድ ጊዜ ከዎከር ጋር አንድ ጊዜ ደግሞ ከህፃናቱ ጋር ሲል ዋተተ በዚያም ሳይ የሶሳንጅን የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማስፈፀም ዝግጅት ማድረግ ነበረበት ዎከር በታስረ በሶስተኛው ቀን የሶላንጅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈዐመ አስከሬነ ሰሁለት ቀናት በክብር አርፎ በሺህ በሚቆጠሩ ሰዎ ስንብት ተደረገለት በሦስተኛውም ቀን የፍትሐት ፀሉት ሲካሄድ አረፈደ ትልቁንም ካቴድራል ባጣበቡት ስዎች ብዛት ፓተርስን መገረሙ አልቀረም አብዛኛዎቹም ለሰዎከር የነበራቸውን አክብሮት ለመግሰፅ ብቻ ሳይሆ ሶላንጅንም ይወዷት ነበረ ስለ ሶላንጅ አያነሱ የማያወሩት የሰም ተወዳዳሪ የማይገኝሳት ውብ ነበረች ባሏን ክመጠን በሳ ታፈቅረው ነበረ የፊልም ተዋናይ መሆን ነበረባት ለሞዴልነት ብ ጊዜ ተሰምና እንቢ አለች አቤት ልጆቿን ስትወድ። አሰቻት አሁንም አሌክሳንድራ ስሰሞተች ነው አክሲ አሰችና የእህቷን እጅ ጭብጥ አድርጋ ያዘችው የእናታቸውን አስክሬን የያዘው ሳጥን በአጠገባቸው እያለፈ ስሰነበረ የሂሳሪ ፊት በድንጋጤ ነጣ ቆም አለችና እጂን ከሳጥኑ ላይ በነበረው የአበባ ጉንጉን ላይ አሳረፈች ሁለት ነጫጭ ፅጌረዳዎችም መዛ አወጣች አንዱን ሰራሷ አስቀርታ ሌሳውን ፅጌረዳ ለአሌክሳንድራ ስጠቻት አሌክሳንድራ በዚያን ጊዜ ማልቀስ ጀመረች ሰምንድነው አናቴ አንዳትነሳ ሳጥኑን ከድነው የሚወስዷት ስትል ትንስቀስቅ ጀመረ ሞት የሚሉት ቃል ትርጉም አይግባት እንጂ ሞት መሰያየት መሆኑን ያወቀችው ጻኣ መ ጋ ጠጠ ብርቅርቅታ ይመስላሳል ሌላው ቀርቶ በሞግዚት እቅፍ የነበረችው ሚጋን እንኳን በዚያን ወቅት ከእናቷ መለየቷን ያወቀች ይመስል ከእህቷ ጋር አብራ አልቅሳለች ያን በመሰለ የደስ ደስ በነበረው ቀን ሶሳንጅ ትቀበራለች ለማለት ላሰበው ይከብድ ነበረ ባለፀጉረ ወርጆፈማዋ ሶላንጅ ባለ ብሩህ አረንጓዴ ዓይኖቿ ሶላንጅ ውቧና ለገላጋዋ ሶዳንጅ ያ ቀን ከባሏና ከልጆቿ ጋር የምትስቅበት የምትጫወትበት እንጂ ዯምትቀበርበት አልነበረም ለምን ያ ቀን የደስ ደስ እንደ ነበረው ለመገመት ያስቸግራል ፓተርሰን ህፃናቱን ከቤት ካደረሳቸው በኋላ ወደ መቃብር ቦታው ተመለሰ የቀብሩም ሥነ ሥርዓት በትክክል መፈፀሙን ካረጋገጠ በኋላ ዎከርን ለመጠየቅ ሔደ ሂሳሪና አሌከሳንድራ ከሬሳ ሳጥኑ ላይ የወሰዱትን ዓይነት ነጭ ፅጌረዳ ለዎከርም አምጥቶለት ነበረ ዛሬ ፓተርሰን ለዎክር ለየት ያለ ፍጥረት መስሎ ነበረ የታየው ቁመቱ ረዝሟል ሰውነቱ ቀጥኗል ፊቱ ገርጥቷል በዚያ ላይ ደግሞ ከነጭ ሸሚዙ በስተቀር ሌላው ልብሱ ጥቁር ነበረ በግራ እጁ የያዘውም ባርኔኒጣው ጥቁር ነው ጫማውም እንደዚሁ ልክ የሞት መላክተኛ መስሎ ነበረ የታየው በተዘዋዋሪም መንገድ ፓተርሰን የሞት መላክተኛ ነው ለማለት ይቻላል ዎከር ሶላንጅን ለመግደል የበቃው በርሉ የተነሳ ነበር ዎከር ቀና ብሎ ሲያየው መሳ ሰውነቱ በሆነ ስሜት ተንዘፈዘፈ ብዕላንጅ የሬሳ ሳጥን ላይ ነው ያመጣሁልሁ አለና ፓተርሰን ነጩን ፅጌረዳ ሊሰጠው እጁን ዘረጋ።