Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
by: NAHU | 18433 KB | 01-02-2023 | 425 يقرأ | 696 التنزيلات
مؤلف: ይስማእከ ወርቁ
ዮራቶራድ (ዴርቶጋዳ 4)
ይስማእከ ወርቁ ዴርቶጋዳ በተሰኘ መጽሐፉ የአንባቢውን ልብ ከተቆጣጠረ በኋላ ራማቶሓራ እና ዣንቶዣራ በተሰኙት የዚሁ መጽሐፍ ቁጥር 2 እና 3 የንባብ ጥማችንን ሲቆርጥ እንደነበር አያጠራጥርም፡፡
በገጸ ባሕርይ አሳሳሉ፤ በጭብጡ፤ በግጭት አመሠራረቱ፤ በሴራ አሰናሰሉ፤ በታሪክ አገነባቡ ከምንም በላይ ደግሞ በገሀዱ ዓለም ካሉ እውነታዎችና ክስተቶች ጋር ገጸ ባሕርያቱንም ሆነ ታሪኩን የማገናኘት ብቃቱ ብዙ ስሕተት ከማይታይበትና ከሚስበው የመቼት አወቃቀሩ ጋር የአማተር አንባቢነቴን ቀልብ ጎትቶት ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ዴርቶጋዳ ተፈላጊነታቸውን እንዲጨምር ያደረገው የቀድሞ ሥራዎቹ (የግጥም መድበሎቹ) “የቀንድ አውጣ ኑሮ”ና “የወንድ ምጥ” ተስገብግቤ ካነበብኳቸው መጻሕፍት ጨመርኳቸው፡፡