Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ጋሽ አምሃ ባማርኛ ቋንቋ ለየት ያለ ያጻጻፍ ስልት ችሎታውን ያሳየ እና ታላቅ ገጣሚነቱን ያስመሰከረ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር ነው። ያልታተመ ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት። የወሎ ሕዝብስ ሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ ወንዱም ሆነ ሴቱ ልጁም ሆነ አዋቂው የተማሪውም ሆነ ያልተማረው የከተማውም ሆነ የገጠሩ ኅብረተሰብ ስለ ሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች ዋርዳው መጣና ቆይ አለኝ አንድ ዓመት ጫት ቅመን ዓለሙን ስንድር ንጉሥ እየፈራኝ ሳይጠላኝ አሽከር ወዲያው ስሜ ታውቆ ሸዋና ሐረር እኔም በመስታወት ዓይኔን ሳሳምር ቃሌ ሳይዛነፍ ሳልደናገር አላህ ሲያሳምረው ሰው እጣው ሲወጣ ዓመት አስቀመጠኝ ከኸለዋ ሳልወጣ ወዲያው መናም አየሁ አንበሳ ሲወጣ ነብር እየመራኝ ጅብ ከፊቴ መጣ ግመል ተሸክሞኝ የሆነ መላጣ መናቡ አይቼ ለሰው ሳላወራ በሰባተኛው ቀን መጣ አንድ ቀብራራ መሰንቆና ዋሽንት በእጁ ይዞ ጭራ ከኔ ጋራ አደረ ጫት ሲቅም ሲያወራ መሰንቆ እየመታ ሲዘፍን ሲያቅራራ አላህ ሲያሳድገው ነገሩ ሲሰላ በስምንተኛው ቀን ጫት ስንቅም ስንበላ ሁሴን ቡን አፍላልኝ ነገሩ እንዲሰላ ስምንት ተን ሳትናገር አፈ የቤቴን ግድግዳ ግንዱን ተደግፌ ፊቴን እያጠብኩኝ እንዳይመጣ እንቅልፌ እንዲቀመጡበት ጋቢዬን አንጥፌ አይገርማችሁም ወይ ሳልነግድ ማትረፌ መናውን ፈሰርነው አንተ ሳትናገር ድቤውም ዋሽንቱም መሰንቆው ጭራ አይቀር ጠጅና ጉማሬ ጫት ጀባ ብለንሃል በዚሂር መነጸር ሐሲድ የሚመታ አንድ እንኩዋን ሹም ሳይቀር አላህ ካደረገን የኸልቁ ወዳጅ በድቤና በጫት ልጀምር በጠጆ ጫት ባፋችን ይዘን ጠጅ እየጠጣን ጥቁር ጭራ ይዘን ድቤ እየመታን ሐሲድ እንዳይነካን አውሊያ እየጠራን አምስት አውቃት ሶላት እየሰጋገድን ሰው ያልነካው እቃ ጀሊለ ሰጠን መጪውን አየነው ጉድ አጃኢበት ዓለም ትስቅብኝ እኔ ሳቅኩባት ለአዳም መህሉቃት ከወንድም ከሴት ሸዋ የዚያን ጊዜ የለውም ዕረፍት ቀጥሎ ይነዳል የጀርባው እሳት እንኳን ለኢያሱና ሳይታይ አባቱ ምን ብለናት ነብር ትመስክር እናቱ እስከሚሞት ድረስ ኋላ ባሟሟቱ ደግሞ አጹ ዮሐንስ መተማ ሳይዘምቱ ትዝ አይላችሁም ወይ በጫት የማልኩቱ ክፉ ዱላ አለን የማይምር እስተውሎ የሚመታ በሩቅ የማይስት እኔ ሹም አልፈራም ጉድ ካየሁበት እንዴት ጥንብ ሰጡኝ አያውቅም መስሎት ማነው ያሳሳተው ያደለው እሳት። ጥይት እህል ሆኖ ሐበሻ ላይ ቦካ ቦታና መሬቱን ከተወሰደበት ወዲያው መዓት ይወርዳል እርስ በርስ ጦርነት በአማራ በእስላም ይገባል ድህነት በተለይ አሥመራ ትሆናለች ዱቄት ሸዋ ጠላት ገዛ ጥይት እረከሰበት ተፈሪን አውርደው ተፈሪ ከገዛ ለትንሽ ቀን እንጂ እጅግም አይገዛ ለዕለት ተጠንቀቀው አይምሰልህ ዋዛ በጉልበት ካልሆነ በፍቅርም አይገዛ ኋላ ግን ያራሉ እንደ እሳት እራት ሸዋ ጦሩን ሰዶ አጣበት ተፈሪ መኮንን እንዴት ያለ ሰው ነበር። ዲንህን አጥፍተህ ዘመድክን ሳትሰትር መሸነፉን ሲያውቀው ጀግና እርቅ ይወዳል እርቅሽ እሦቢ ካለ አገሩ ፍቹን ድረስበት እርቁ ይሻልሃል የተፈሪ ይብቃ መዓት ይወርድብሃል ዉ ነበር ሸዋ ጠፋ ውልድ አስኮላ ግባ አሉት ኋላ እንዲህ ሊነድ ልጁን መቅጣት ነበር ብልግናን ሳይለምድ ሳዱላ አበላሽቶ ትንባሆን ሳይለምድ ምኑ ይነወራል ሰው ቢገላምጥ ቢያዋርድ የአማራ የእስላሙን መብላት የለመደ ሐበሻ ላም ሆና ታስራ ከታለበች ጡቷን መዥገር ወሮት ጥጃዋን ገደለች ላምዋም ትሞታለች እየመነመነች ወተት ቢሉ አይገኝ አንደዜ ሙታለች ይዘገያል እንጅ ኋላ ትድናለች የሐበሻ መሬት ሌት ቀን ሲጨልም ሐረር ወዲያ ማዶ ይፈሳል ብዙ ደም ቂሙም አይረሳ እስከ ዘለዓለም መንገድ ይፈልጋሉ ሐበሻን ሊቀሙ ከስንቱ ጋር ይሆን ሐበሻ እምትገጥም። ጀርባውን ምች መታው ወደ ትግሬ ሲያይ ሲተክሏቸው ጥሩ ሲበቅሉ ጠማማ ታመጣው ይሆናል ወይንስ ከማማ አላህ ያሳያችሁ የወሎ ኡለማ ደረጃው ምንድን ነው።
ዶክተር ኤሏ ፊኬ ደግሞ አንድ መቶ ስልሳ ግጥሞች ያሉት የሸህ ሁሴንን ትንቢቶች ወደ ፈረንሳይኛ ተርጉሟል ኤሏ ያገኘው ቅጂ ከአቶ ዓሊ ይመር ሲሆን አርእስቱ ትንቢተ ሼህ ሁሴን የሚል ነው በተጨማሪም በቅርቡ በ ዓም የታተመው የአቶ ጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ ቤተ የታሪክ መጽሐፍ አንዳንድ የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞችን እንዳቀረበ መጥቀስ ያስፈልጋል የሼህ ሁሴን ትንቢታዊ ግጥሞች ከማኅበራዊ ታሪካዊ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ ያላቸው ባህላዊ ፎክሎራዊና ሥነ ጥበባዊ ዋጋ እጅግ ከፍተኛ ነው ምናልባት ግጥሞቹ የሼህ ሁሴን ጅብሪል የራሳቸው ትንቢቶች ስለመሆናቸው በርግጠኝነት መናገር አይቻል ይሆናል ይሁን እንጂ የተለያዩ የታሪክ የሥነቃልና የፎክሎር መረጃዎችን በመሰብሰብና በጥንቃቄ በማጥናት ታዋቂ ሸሆችንና የእስልምና ሊቃውንትን በማነጋገር ግጥሞቹ በሼህ ሁሴን በቃል ስለመገጠማቸውና ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል ስለመተላለፋቸው በርግጠኝነት መናገር ይቻል ይሆናል ግጥሞቹ በወሎ ኅብረተሰብ ዘንድ በስፋት መታወቃቸውና ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል እየተላለፉ መተረካቸው እንዲሁም መቼ በማንና በምን አጋጣሜ እንደሚዜሙ ታሪክን ባህልን ልማድንና እምነትን መሠረት ያደረጉ ክፍለ ሀገራዊ እምነታዊ ፎክሎራዊና ታሪካዊ ሁናቴዎችን መመርመርና ማገናዘብ ስለሚቻል ነው እንደሚታወቀው ወሎ ውስጥ በርካታ የታወቁ ሼሆችና የእስልምና እምነት ማምለኪያ ቦታዎች ይገኛሉ ሕዝቡም በአብዛኛው ወደ ታዋቂ ሼሆች እየሄደ በጸሎት በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ በዓላትና መጅሊሶች ስብሰባዎች ላይ እየተገኘ በተለይ በግጥም የሚባለውን መንዙማ የመስማት አብሮ የማዜምና በቃል የማጥናት ባህሉ ከፍተኛ እንደሆነ በስፋት ይታወቃል በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ ወሎ የግጥም የዜማ የዘፈንና የልዩ ልዩ ባህላዊ ጨዋታዎች ምንጭና መሠረት መሆኑ የታወቀ ነው እስካሁን የታተሙትን ሥራዎች ስንመረምር በአቶ ቦጋለ ተፈሪ መጽሐፍ ውስጥ ግጥሞች ከትንታኔ ጋር ቀርበዋል በትንታኔው ውሰጥ ከቀረቡት መካከል ስለ አጹ ዮሐንስ ስለ ሙሐመድ አሊ ስለተፈሪ መኮንን ግጥሞች ትንታኔ ተደርጎባቸዋል በተጨማሪም በጣም ብዙ ግጥሞች በፈደል ተራ ያለ ትንታኔ ተጽፈዋል ቀጥሎም እንደዚሁ በርካታ ግጥሞች ከአንዳንድ አጫጭር ማብራሪያዎች ጋር ቀርበዋል ከዚህ መጽሐፍ በፊት የሼህ ሁሴንን ትንቢታዊ ግጥሞች በተመለከተ ምንም መጽሐፍም ሆነ መጣጥፍ እንዳልታተመ ደራሲው በመግቢያቸው ላይ ጠቅሰዋል መጽሐፉ ስለ ወሎ ክፍለ ሀገር ታሪክ ባጭሩ የዳሰሰ ሲሆን የሼህ ሁሴንን የሕይወት ታሪክም አቅርቧል በዶክተር ኤሏ ፊኬ ቪከ ፓሪስ ጥናት ውስጥ ደግሞ ግጥሞች ወደ ፈረንሳይኛ ተተርጉመው ቀርበዋል ፊኬ የሰበሰባቸው ግጥሞች አጭር መግቢያ በአረብኛ ቋንቋ ያላቸው ሲሆን የአቶ ዓሊ ይመር ቅጂ ቨርሲዮን አንደሆነም ጠቅሷል ኤሏ ፊኬ ለግጥሞቹ አንዳንድ አጫጭር ማብራሪያዎች በግርፄ ማስታዎሻ ሥር ከመስጠቱ በስተቀር ሰፋ ያለ ትንታኔ ወይም ማብራሪያ አላደረገም የፊኬ የትርጉም ሥራ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አልታተመም ነበር ቦጋለ ተፈሪ ዓም ሼህ ሁሴን ጅብሪልና ግጥሞቻቸው። የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች ዋርዳው መጣና ቆይ አለኝ አንድ ዓመት ጫትክን እየበላህ ሳታድር ከሴት አምሬን እየሞላህ ጠጅን ሳታሸት ደረሳህን ይዘህ ሳትወጣ ከቤት እኔም ኸልዋ ገባሁ ቆየሁ አንድ ዓመት አንድ ዓመት ጫት ቅመን ዓለሙን ስንድር ንጉሥ እየፈራኝ ሳይጠላኝ አሽከር ወዲያው ስሜ ታውቆ ሸዋና ሐረር እኔም በመስታወት ዓይኔን ሳሳምር ቃሌ ሳይዛነፍ ሳልደናገር አላህ ሲያሳምረው ሰው እጣው ሲወጣ ዓመት አስቀመጠኝ ከኸለዋ ሳልወጣ ወዲያው መናም አየሁ አንበሳ ሲወጣ ነብር እየመራኝ ጅብ ከፊቴ መጣ ግመል ተሸክሞኝ የሆነ መላጣ መናቡ አይቼ ለሰው ሳላወራ በሰባተኛው ቀን መጣ አንድ ቀብራራ መሰንቆና ዋሽንት በእጁ ይዞ ጭራ ከኔ ጋራ አደረ ጫት ሲቅም ሲያወራ መሰንቆ እየመታ ሲዘፍን ሲያቅራራ አላህ ሲያሳድገው ነገሩ ሲሰላ በስምንተኛው ቀን ጫት ስንቅም ስንበላ ሁሴን ቡን አፍላልኝ ነገሩ እንዲሰላ ስምንት ተን ሳትናገር አፈ የቤቴን ግድግዳ ግንዱን ተደግፌ ፊቴን እያጠብኩኝ እንዳይመጣ እንቅልፌ እንዲቀመጡበት ጋቢዬን አንጥፌ አይገርማችሁም ወይ ሳልነግድ ማትረፌ መናውን ፈሰርነው አንተ ሳትናገር ድቤውም ዋሽንቱም መሰንቆው ጭራ አይቀር ጠጅና ጉማሬ ጫት ጀባ ብለንሃል በዚሂር መነጸር ሐሲድ የሚመታ አንድ እንኩዋን ሹም ሳይቀር አላህ ካደረገን የኸልቁ ወዳጅ በድቤና በጫት ልጀምር በጠጆ ጫት ባፋችን ይዘን ጠጅ እየጠጣን ጥቁር ጭራ ይዘን ድቤ እየመታን ሐሲድ እንዳይነካን አውሊያ እየጠራን አምስት አውቃት ሶላት እየሰጋገድን ሰው ያልነካው እቃ ጀሊለ ሰጠን መጪውን አየነው ጉድ አጃኢበት ዓለም ትስቅብኝ እኔ ሳቅኩባት ለአዳም መህሉቃት ከወንድም ከሴት ካለቁት በስተቀር ያሉት በሐያት ተከትቦ አየዋለሁ ስሙን ወደፊት ስሙን ይነግረኛል ዋሪዳው ሳይስት ገና በእናቱ ሆድ «ት ለወልይ ለንጉሥ ለራስ መሳፍንት ምን አስለፈለፈኝ ሊታይ ወደፊት እኔም በል የሦዐወክት ሃምሳ ዓመት ስናገር ሰምተው ጉድ እያሉ እንደ ፍልፈል አፈር ሰው ሲፈለፍሉ እኛም ሰደድናቸው ከአፈር እን እንዳይሉ ሃምሳ ዓመት ደመኝ መሐመድ ኑር ዒሳ መና ወረቀት ከእጁ ሳይነሣ ይከትበው ነበረ ዋሪዳው ሲነሣ የፈረድኩትን አንድ ቀን ሳይረሳ መጪውን ፈርጃለሁ ዓለም እስቲከሳ ቃሊቾችም ጠሉኝ ጠጅ ይጠጣል ብለው ደብተራውም ጠላኝ ሹም ተጠጋው ብሎ ባለዛም ጠላኝ ሰው ሄደሸት ብሉ ፋቅራውም ተጠጋኝ ምን ይፈርዳል ብሎ እኒህን ችዬ ነው የሰጠሸ ጀሊሉ ጀግና አጹ ዮሐንስ ያበሶች ወንድም የዛሬን ማርልኝ ያለ ዛሬ አይለምድም በነገረ ሠሪ ሰው አይታረድም እንዲህ ከሆነማ አንድ ስው አይተርፍም እየደነገጡ ይሄዳሉ የትም ዓባይ በጣና ላይ መሄዱ ለምን ነው። ሱዳን አገር ዋሪዳው ካመራ ደፈረኝ ካሉ ሳዳቶችን ልጥራ አሁን ድረሱልኝ ይዞኛል ደብተራ ወትሮም የመሐዲ ዘር አስላችሁ አይኮራ ገላገላችሁኝ አልቅሼ ብጣራ ቢደፍሯቸው እዳ ዝም ብል ችግር ዋሪዳው መጣና አለኝ ተናገር እንግሊዝ ከሱዳን ሽተ አገር ይዘገያል እንጅ ኋላ አለ ነገር መሕዲ ዘር ሸለታ ሲል ሰባት ቋንቋ አላቸው ሁሉም በጠቅላላ የሱዳንን ነገር በስንቱ ላውሳቸው ካላስፈነደዳ አስላቸው ከእኛም ሰው አይተፋ ጭ ያስተመችራቸው የወንዱስ መላ አልቋል ሴቱ አላህ ኛው ስንቡል እያጠበች ገልባ ከሰጠችው ድርቡሽና ሱዳን መልካቸው ጥቁር ነው አገሩ አንድ ቢሆን ቋንቋው እየቅል ነው ጥንቱም ፍጥረታቸው ዘራቸው ልዩ ነው በዚሂር ሲጠሩ ስማቸው እስላም ነው ቸርነት አያጡም እጃቸው ለጋስ ነው ድርቡሽ ጥሩ እስላም ልባቸው የጠራ ሶላትን አይተውም ቢበዛበት ሥራ ችግርም ቢገጥመው ይችላል መከራ አገራቸው ሜዳ የለውም ተራራ ልብሳቸው ቀሚስ ነው የለውም ዳኢም ታጥቀው ሥራ ከእኔ ተመርቀው ሴት ልጅ ከወለዱ ለጉግሳ ይዳሯት እንዳትዛመዱ ሌላም አያገባት ፈርዶታል መዱ እንግዲህ እሜቴ ጫት ቃሚሜን ይውደዱ አሁን ነው መሸመት ደጎቹ ሳይሄዱ በአዳራሹ ገብተህ በእልፍኙ ውጣ እንደምንም ብለህ ሸዋረጋን አምጣ የተያዝክ እንደሆን እኔ በጉድ ልውጣ እኔ ፈርጃለሁ ሌላ እንዳታመጣ ወንድ ትወልዳለች ግን የለውም ዕጣ በራስህ ገብቼ በሆድህ ብወጣ ከትርንጎ በቀር ሌላ ምንም ታጣ ይኸ ያልሆነ እንደሁ እኔ በጉድ ልውጣ ሆድህን የሚገልጥ ሸማግሌ ይምጣ ይኸንን ጉድ ሳላይ ከቤትም አልወጣ ተው አቶ ሙቀጫ እኔን አታላግጣ ጌሾና ቡናህን ውጣና ቀጥቅጣ በሽታም እንደሆንክ እኔ በጉድ ልውጣ ማንን ታሞኛለህ እኔ አልወድም ላግጣ እኔ እሳት አልገባም ነግረንሃል ቁርጣ ምኒልክ ክፉ ነው በስንቱ ፈተነኝ እንድአለፉት ጠንቋይ በእሳት ሊያቃጥለኝ በሰው እጅ አልጠፋም አላህ ደለኝ እንኳን ከመምሬ ፊት አላህ ሊቅ አረገኝ እፈራው ነበረ በጀ እንዳይጠልፈኝ የምኒልክ ጠንቋይ ዋና ደብተራው ያስፈጨው ነበረ እንደ ሰው በርበሬ ነበረ የሚቋደሰው ጅኑን እየላከ ስንቱን ሰው ፈጀው መምሬ ሐሲድ ነው ከመጀመሪያው እንግዲህ ወንድሜ ስማኝ የኔን ፍርድ መውለድህ አይቀርም ከጭኸገረድ ቁርኣን የሚቀራ ኢልምሽ የሟወድ መጨረሻው ከፍሮ ካልሆነ ፈሳድ ቴዎድሮስ ለጋሥ ሰው ነው ቸርነት አያጣም ዘሩም ደኅና ሰው ነው ቢገጥም አይወጋም ማንም ያሞኘዋል ያሳዝናል በጣም ለሰውም ደኅና ነው እስላምን አይጎዳም እራቅ ይላል እንጅ የእስላም ዘር አያጣም ዮሐንስ ንፉግ ነው ሰው ቢበላ አይወድም የሰው ያየ ጊዜ ያደርጋል ጉድምድም ሆዱም ለብቻው ነው ሰው አያስቀርብም ለጦር ግን ጀግና ነው ቢሄድ አይታክትም የጠንቋይ ውዴታ ፍቅር ይቅርብህ ለአንተ ሲህር አያጣም ይኸው ነገርኩህ ቢያጣ አርን አያጣም እንዳይጥልብህ ስታልፍ እንድትረግጠው ሰው እንዲስድብህ አሩ ይሸታል ብለው ሰው እንዳይቀርብህ አሥር ዓመት ብችል ሊያርዱኝ ተሰለፉ ለካስ ለዚህ ነውይ እምቢ ለኝ እንቅልፉ ለአላህ ትቼው ነበር በዱኒያ እንዲያልፉ እንግዲህ ዘላለም መሬሸ ይቀፉ በቶሎ ገላግለኝ ሰው እንዳያለፉ በእነ ቀለመወርቅ ነሱር ባላገኝ በመምሬ ጉርሙ ነሱር ባላገኝ በእነ አለቃ ሣህሉ ነሱር ባላገኝ በእነ አለቃ ውብነህ ነሱር ባላገኝ ተዋርደው ነው ንጉሥ የፈራኝ በእለቃ ቀለመወርቅ ነሱር ባላገኝ በእነ ይመር አደም ነሱር ባላገኝ በእነ አለቃ እዮብ ነሱር ባላገኝ ችለን ሰደድናቸው እንቅልፍ ነሱኝ ነግሬአቸው ነበር ፊት ሳልታመም አሁንም አየሁት አላህ ሲፈርም አፈሩን በጥብጦ በጥቁር ቀለም ቃልቻ ይኸን ፈሥር እንዳትታመም በቀር ትጓዛለህ አምተህ ሳትሰልም አላማጣን አልፈህ ማይጨው ትዘምታለህ ነጭ አሥመራ መጥቶ አድዋ ትገጥማለህ አድዋን እንዳያልፍ በጣም ትዋጋለህ ጦርህ ግን ያልቃሉ ድል ግን ታደርጋለህ በመከርኩህ ቨ ነጃ ትወጣለህሀ የሸዋረጋ እናት ሐለቴን ያውቃሉ ሁሴን መጣ ሲባል ጋንዎን ያጥባሉ ቄጠማ ጎዝጉዘው አርስ ያቀርባሉ ደስ ደስ እያለዎት በጣም ይስቃሉ መጋረጃ ጋርደው ቁጭ ብለው ያድራሉ መምጣቴን ሰምተው ልደር ካሉ ቄሱ ሐለቴን ያውቃሉ ጣይቱን ያስታውሱ አዱርስ ጨሰ ብለው እንዳይወሰውሱ ጫት በአፋችን ከያዝን ጠጅን እንዳቀምሱ ዋሪዳው ይማታል ይወድም መጅጆሊሱ የነሸ ስ አባትዎ ከሆኑ እህ ቄስ ቁጭ ብለው ይደሩ ከእኛ ጋር መጅሊስ አትወዱም ጳጳስና ቄስ ግን ለአጹ ምኒልክ እንዲላቸው ደስ ሰው ዝም ብሎ ያድራል እንኳን ሊደግስ አርባ ጊዜ መጣሁ የልብህ ይድረስ ፊትም ዱአ አርገናል አንተ እንድትነግ ቀልብህ ደኅና ቢሆን ብትወድ መጅሊስ ገርፈህ ባትሰቅል እንደ ዮሐንስ ስንቱ እስላም ወደደህ ሁሉን አለው ደስ ጎጃም ተክለ ሃይማኖት ጎንደር እራስ ተሰማ ራስ አሉላ አባ ጅፋር ጅማ ሐረር ራስ መኮንን ዘራቸው የገማ እኔ ተናገርኩኝ ያልሰማህም ስማ ከጉግሣ ዘር በቀር የለም የሜለማ መች ባንተ ይሆናል ምኒልክ ንጉሥ አንተ አስበህ ነበር ልትሰጥ ለእያሱ እንኳን ሊነግሥና ይያዛል ለራሱ በራስ መኮንን እጅ ትጠፋለች ነሱ ከጌታ ተፈርዷል አርደውት ሊነግሥ ከገረድ ተወልዶ እደግ ብንለው ጥንብ አቀረበልን እዩት ይህን ሰው ከሸዋረጋ ፊት አሁን ላዋርደው ልልክበት ነበር ዳግሚያ እንዳይለምደው አይለምደውም ነበር ቄስ ወርቁን ቢያየው። ሜካኤል ተው ተብት በኩፍር ሳትቀጣ ይበቃሃል የሟል ከአላህ አዋጅ መጣ እንዴት ያለች ንፋስ የሆነች ባላንጣ በጥፊ ብትመታው በአፍንጫው ደም ጉቨሥ ተቃረበ ሩሁ ልትወጣ ጉግሣና ራስ ላ አጹ ዮሐንስ ሚሜካኤል ምኒልክና አጴጹ ቴዎድሮስ ዘውዲቱና ፈረንጅ ተፈሪ ድረስ በብልሃት ገቼት አልጋው እንዳይፈርስ መጨረሻው ከፍቶ ኔንደዶርኩስ የአላህን ትተው በውሻ የሚመሩ በሐበሻ መሬት ግፍን የሚሠሩ ቁመታቸው አጭር መልካቸው የሚያምሩ አይነግሥም ብላችሁ አትወዳደሩ ሃምሳ ዓመት ይነግሣል እግረ ውትርትሩ ባሕር ወዲያ ማዶ ጣ ሊጠቅም ግድግዳው የሜያምር በሽንጥ የሚጠቅም ቅጠሉ ለስላሳ ቁመቱ ረዣዥም እሱን ያልተከለ እንዴት ይለም ሸዋ በተለየ ያለሱ አይቆምም ሥራቸው ባለፄ አህያ የሚበሉ ባሕር ወዲያ ማዶ ክፉ ሰዎች አሌ ሐበሻን ለመውረር ሐሳብ ያስባሉ የኋላ የኋላ መምጣት ይመጣሉ አምስት ዓመት ገዝተው ወዲያው ይሄዳሌሉ ድንጋይ ዱቄት አርገው መንገድ የሚያበጁ ገመድን ዘርተው መብራት የሚያበጁ አህያ የሚያርዱ አሞራ የሚፈጁ መጡ እየተማሩ ሐበሻን ሊያበጁ ማማሩን አማረች ግን ብዙ ሰው ፈጁ እግሩ እንደ ሙቀጫ የሚንከባለል ቢሄድ አይታክተው አቀበት ቁልቁል ጭቃ ካለው መንገድ መሄድ የማይችል ገደል የሚያንሸራትተው የሚንከባለል ይህንን የገዛ ንሦ አያይል በገዛ እጁ ነድፎ ፈት የሟሠራ ሰውን የሚያስገርም የሚሠራው ሥራ ልብሱ ተፈላጊ ሰውን የሚያኮራ ልብሱን ላይሸከሽክ አስተውሎ የሚሠራ በዚህ አይግረምህ ሌላ አለ የሚሠራ እፍ ቢሉት አይነድ እፍ ቢሉት አይጠፋ እንደ እሳት አይጫር ሲበራ ቀልጣፋ ደጅ ሲበራ የሚያድር በዝናብ አይጠፋ ሲነቡት የሜገድል ሰውን የሚያጠፋ ነጮች ያበጁታል ሐበሻ ሳይለፋ የአጴጹ ምኒልክ ዘር መዓት ወረደባቸው የቤታቸው አሽከር እንደ ጤፍ ዘራቸው ጠንካራ ሰው ጠፍቶ ምች ቀብሩ እንዳይታወቅ ሰው እንዳይቀብራቸው እያሱ እንኳን እንዳይተርፍ ፈጃሾቸ አልጋው ደኅና ሳለ አሽከር ሳይሰፍርበት ልጆቹን ቢተካ እንዴት ባማረበት ሰውም ስይደነግጥ ቀን ሳይጨልምበት እሱም ይኖር ነበር በለዛ በክብረት የምኒልክ ዘር አልቆ መነን ትቀራለች ተፈሪን አግብታ ዱቄት ትወልዳለች ልጆቿም ያልቃሉ እሷም ጉድ ታያለች የባሏን መከራ ሳታይ ትሞታለች ሐበቫ ተን ትነፋፍሳለች መነን ልትሞት ትንሽ ቀን ሲቀር ሸዋ በተለየ ይሆናል ሽብር አልጋውን ለመያዝ ለመወዳደር መቼ ይዘገያል የሰው ደም አይቀር እጃቸው ይያዛል አያገኙም ተፈሪ መኮንን አሥመራ እጁን ሰዶ ትግሬን በጠቅላላ አደረገው ባዶ ዘለዓለም እንዲኖር በሐዘን በመርዶ እኩሉም ይኖራል ቤቱ ነዶ ነዶ እኩሉም ይሄዳል ወደ ገርብ ተሰዶ የትግሬን መከራ የወሎን ችግር የሚበላው አጥቶ ሲፐገር ሐበሻ የዚያን ቀን የለውም ቀራር ውሸት እንዳይመስልህ በወሬም አይቀር ያችን ቀን ለፈ የለውም ችግር ወሎ በረሃብ አልቆ ሞት የበዛ እንደሆን የሸዋ መኳንንት ዳርቻው ምን ይሆን። የጁን አግኝቶታል እንግዲህ ሰው አይሆን ተፈሪ መኮንን የተያዘ እንደሆን እንግዲህ ሐበሻ ምን ይበጀው ይሆን አሥመራና ሸዋ ይሆናል እንዳይሆን ወያኔ ተነሥቶ አሥመራ እሳት ሲሆን ጋላና ጉራጌ የሸዋ ሙንቨር ሌት እንቅልፍ የላቸው ቀኑን በነገር ሸዋን ይይዙታል አንድ እንኳን ሳይቀር ድንጋዩን በድንጋይ አድርገው ንብርብር አጃኢቡን ሳላይ መሬት ስትሆን ብር ካለፉት ይሻላል ነ እንጅ ተፈሪ መኮንን ለእስላም አይበጅ እኩሉን ሲያስለቅስ እኩሉን ሲያበጅ ሃምሳ ዓመት ይነግሣል ዘር የለውም እንጅ እንቁላሉ ገምቶ ጠፋ በሰው እጅ ተፈሪ መኮንን ትልቁ ልጃቸው አልጋውን ለመያዝ ያስባል ልባቸው የኋላ የኋላ ጀ ላቸው ሸዋ ክፉ ሰው ነው ከሥር ነቀላቸው ነ ን« ይገኙ ከእነልጅ ልጃቸው አልጋው በወደቀ በሁለት ዓመት ንጭር ንጭር ይላል አይሆንም መስሎት ደስ ይለዋል ያገኘጀ ሠስሉት ማለቁን ሳያውቀው በረሃብ በጥማት ጌታውን ይገድላል ቦታና መሬት ሀብታም የዚያን ጊዜ ይወድቃል መሬት ባሪያ ሁር ተብሎ ከሆነ ፈራጅ ገላጋዩ ማነው። እኔም ዝም አልልም ዲኑን ሲያረክሰው ሶላት ካልሰገደ አብሮኝ እንዳይቅም ሐድራ ያበላሻል የለውም ጥቅም አይሰግድም ከመባል አይሻልም አላህ አይለቀውም እስከ ዘለዓላም ነገሬ ካልገባው ይጠይቅ ዓሊም የመተማን ትተን የሐውሳን እናውጋ ሦስት ቀን ጨልሞ በአራተኛው ነጋ ለዕለት ታግሎ ነበር ሐውሳ እንዳይወጋ ስሙ የታወቀ ትልቅ ባለጸጋ ሳይያዝ ያመልጣል ሐውሳ ግን ተወጋ ነገሩ እማይገባ የተወላገደ በአሥመራ በትግሬ ሄዶ እየነደደ እንዴት ያለ እሳት ከሸዋ ነደደ ቢያጠፉት እምቢ አለ እየተዛመደ አንበሳ እግሩን ታሞ ደም ሲያለቃቅስ ማማው ምስጥ በልቶት ይሆናል ብስብስ ወደቅ ወደቅ ይላል ወፉን ሊያጨርስ የዚያን ቀን አሳማ ይሆናል ንጉሥ ሺምጦ የሚበላ ሰው የሚያስለቅስ ተፈሪ ክፉ ነው ልቡም አይገኝ ለሰው ይመስለዋል ይናገራል ቀኝ ኋላ እንዲህ ሊዋረድ ፍዳውን ሊያገኝ እሳት ሰደዱበት ዳግሚያ እንዳይገኝ ዘላለም የማዝበርድ በደም የሚያዋኝ የተማረ ወድቆ ደንቆሮው ከገዛው ማን አለብኝ ብሎ አገሩን ወረሰው ጥሩ አርጎ ባለበት በገዛ እጁ ናደው ምድር ሊቆረቁር ኋላ እንዲህ ሊቆጨው አላህ ዝም ብሎ መንግሥት ሊያሳስት ሰው እንደፍሪዳ ሲታረድበት ምን ይችል ሐበሻ ጉድ አጃኢበት በጦሩ ጨፍጭፎ ላይረጋ መሬት እንኳንም አልደረስን ስትነድ መሬት አሥመራ ልትጠፋ ገመዱ ሲላላ በሸዋ ከተማ ይኸለቃል በላ በሦስት ቀን ይያዛል ጎንደር ላሊበላ አክሱም የዚያን ጊዜ ትሆናለች ሌላ ማርያም ትጠፋለች አያዋጣም ብላ ምን ኑሮ ይገኛል መንግሥት ከከፋ ሰውን ለመግደል ጦሩን ከአስፋፋ ውሸት እንዳይመስልህ ይሆናል በይፋ ጠብቀው ዘመኑን እንዳታንቀላፋ ወቅታቸው እስኪቀርብ እስኪዘልቅ በይፋቶ አይጥ ጠብመንጃ ይዞ ከገባ ከዋሻ ሳትታይ አትቀርም አሥመራ አላህ ቢሻ በደም ተጨማልቋል ትሆናለች እርሻ ብዙ ሰው ይጠፋል ሳይገኝ ወጌሻ ክፉ ነፋስ ነፍሶ አልብሶት ቆሻሻ የአሥመራ ወያኔ ከያዘ ጠመንጃ ደንግጦ ይሞታል የአሥመራ ስልቻ የኋላ የኋላ ከቲማውን እንጃ ምን አስለፈለፈኝ ላይገኝ ፈረጃ ነስሩም አይታወቅ ዘላለም ጦር ብቻ የአሥመራ ጦርነት ታኅሣሥ ሲጀምር ብዙ ሰው ይጠፋል ነገሩ ሳያምር አይሰድም መስሏቸው ሸዋ ብዙ ጦር ወዲያው ሰደዳቸው በሰማይ በምድር ወያኔው ይሞታል አያገኝም ነስር ቀልባቸው ነጃሳ ስማቸው እስላም ንጉሣቸው ሰወው ይበላል ጅም ላም በስሙ የሜመራ ዓለም ለዓለም ለዲን ተቆርቋሪ ለሁሉ የሚጠቅም በኋላ ያልቃሉ ቀኑ ሲጨልም ባሕር ወዲያ ማዶ አራት ሰዎች አሉ ከእነዚህ ሁለቱ በቀንድ ይበልጣሉ የጌታችን መቃም አየነው ባይሉ ለአዳም ፍጥረቶች በላዕ ይሆናሉ በአመጡት በላዕ እነሱ ያልቃሉሌ ሐበሻ ሁለት ነጭ ሳይገቡም አይቀር አንደኛው በፍቅር አንደኛው በጦር አስበው ነበረ ሊያረጓት አገር አምስት ዓመት ገዚት ሲል ደንገር ደንገር እኩሉን በሥራ እኩሉን በጦር ዘመን ተበላሽቶ ወደቅ ወደቅ ሲል ነጭ ከባሕር መጥቶ ይስላሉ ሲል ተፈሪ የዚያን ቀን ይሆናል ትል ሜዳ ላይ ይወድቃል ሳያገኝ ጅልል አላህን ሰደብኩት ማን አለው ጠበቃ ምን ሥፍራ ኖሮት ነው ለራሱ የሚበቃ በዱኒያ እንደሆነ ይበልጣል የእኔ ዕቃ ቃልቻ ይመሰክር አላህ ካለው ዕቃ አውራ በሬ ታርዶ አንበሳ ሲያለቅስ ሐበሻ የዚያን ቀን ትሆናለች ኩስ ሽታዋ የሚያስከፋ የምታስነጥስ የዚያን ዕለት ይወድቃል እስላምና ቄስ የዚያን ቀን ያስፈራል አገር እንዳይፈርስ እኛ አፈር በገባን በአንድ መቶ ዓመት ተፈሪ ዓይኑን ታሞ ይገባል መሬት ማር የላሰ ሁሉ ይቀምሳል እሬት የበላውም አይቀር ሽቅብ ሲያስተፉት ካለው ይገድሉታል ለገዘብ ስስት ሸዋ እባቡን ሳይዝ ምስጢሩን በዝብዞ ድርቡሽ አገር ገባ የሰውን ላብ ይዞ እባብ ልቡ አይገኝ መጣ መርዙን ይዞ ዓለሙ ላይ ተፋው ያገሩን ጅብ ሰዶ አብሮ የሚበላ አንጀትን በዝብኮ ሷሊህና ቃሲም አብደላህና ዙበኗር በወልቃይት ብቅ አሉ ትግሬ ሲበረበር ኩታበር ገራዶ ትሆናለች ጠጠር ጎጃም ትጠፋለች ሳትውል ሳታድር ብዙ ሰው ይጠፋል ያውም ከባላገር አሥመራ ተወግቶ ወልቃይት መርዙን ተፋ ሽሬና መቀሌ ይሆናል የከፋ እንቅልፍ እንዳይወስድህ እርብ ሳይጠፋ ይመስላል ላየው ሰው ቂያማ የተደፋ እርብ ስንቱን ጣለው ጠብቆ ወረፋ ጋይንት ንፋስ መውጫ ድራና ፎገራ እርብ ላይ ሞልቶ ሲዘፍን ሲያጎራ ነጋዴው ይጮሃል መቀሌና አሥመራ ምን ይበጀው ይሆን ጅልጋና ፎገራ። ወትሮ ጭቡ ሱሪ ሰው ያስወነጅልሃል ያልሆነውን ሆነ እያለ ያወራል ከአሜሪካ ወዲያ አለ ጥሩ ባሕር ሃያ አምስት ያስኬዳል በግምት በእግር ከዚያ አንድ ጎራ አለ ተተክሎ እንደ ጦር ነጮች ከዚያች ሥፍራ ሳይደርሱም አይቀር ላዩ ግን ሜዳ ነው የአንድ ጋሻ አገር ከአሜሪካ ወዲያ አለ ጥሩ አገር ተራራውን ወጥቶ ከተገኘ ቀድጽር ላዩ ግን ሜዳ ነው የሚያጭበረብር ሥፍራው ከንዝ አያጣም ለሆነ ዘኪር እዚህም አይደርሱ እንኳን ከቀመር ነጮች ሄዷል ካሉ ነጭን ከጨረቃ መወሊድ የለም ካሉ ዚያራ ሰደቃ ነቢን ከጠሏቸው የኸልቁን ጠበቃ እንኳን ማውራት ቀርቶ መስማትም አይበቃ ልባቸው እርኩስ ነው ሥራቸ ጨምላቃ አምስተኛው መዝሕብ ተሺጦ ሲለማ ኋላ ጉድ ታያለህ የወሎ ኡለማ የማታውቀው ነገር ቀርቧል ልትሰማ ሰምተህ እንዳትከፍር ጆሮህ እየሰማ አሟት እንዳይረግምህ አህያ ስትሰማ ምስክር የለኝ ተናግሬ አልሸሽ አዋጁን ተከተል ሳትከፍር ብላሽ በሁለት መንግሥት እንዳትቆሽሽ ያሲን መስክሮታል ቁርዓንም አይዋሽ ሌላ ካልፈሠሩት ሰው እንዲበላሽሸ በአምስትና በአራት በሦስት ሰጠር ሲከትበው አየሁት ሼህ መሐመድ ኑር ቆንጥሮ ያወራል መንደር ለመንደር ጠቅላላ ሳይዘው ቀርቶ ሳይከርር ሰውን እያየሁ ነው ጠልፎ ሲናገር ፈረስ ደኅና ሰንብት አላህ ይሁንህ ነጭ ሐበሻ ገብቶ ጉድ አሸከመህ የናታውቀው ነገር ጭኖ አስጎተተህ ጉድክን ወደ ኋላ እንዳታይ ሆነህ በአንዱ ስታለቅስ ሦስት ሰው ጫኑህ አረብ አገራችን ሳይለምድም አይቀር ወልደው ይከብዳሉ ያደርጋሉ አገር ግን ልጁ ሸይጣን ነው አንድ የለውም ኸይር ሶላትም አይሰግድ እንደ ዱር ሲቀር መልከ ቆንጆ አይመርጡም ብትሆን ባሪያ ኩፍር ሀብታም ወራሽ መንግሥት ተሹሞ ሲመጣ ሙክት የዚያን ጊዜ ይሆናሉ ቋንጣ ሁሉም ይጎዳዋል ፀሐይ እስኪወጣ ታስሮ ከመገደል ምናልባት ቢወጣ የአላህ በል የዚያን ቀን እንዲህ ያል ሲመጣ ዘመን ተለውጦ ጥቅምት ሲደርስ በአሥመራ ከተማ ይነፍሳል ነፋስ የዚያን ቀን ሐበሻ ይላል ፈረስረስ ሃምሳ ቀን ይቆያል ሴት ወንዱ ሲያለቅስ ወንፊት ጉድ እስኪወልድ እስኪሆን አራስ መንግሥታቶች አሥራ አምስት ሲቀሩ ከድንጋጤ በቀር ይርቃል ኸይሩ በረካም አይገኝ እስኪ ቁርዓን ቅሩ መድፈርም አይበቃ ደብዳቤ መቅበሩ ለሰው ግን ጥሩ ነው በአማን ማደሩ በመካ አንድ ንጉሥ በገርብ ሦስት ሲቀር ድርቡሽ የዚያን ጊዜ ያስባሉ ሸር የዚያን ቀን ያየ ሰው ሲጫጫር በሰበቡ አሥመራ ትሆናለች አር እኛ አፈር በገባን በስድሳ አምስት ንጉሥ የተባለ የለውም ሐያት እጁ እየተያዘ ይገባል እሳት ዘሩ እየታደነ እንደ አውሬ እንደ እሳት ከእኛም ሳይመጣ አይቀር ኋላ ወደፊት አጹ ኢያሱ ነግሦ በሸዋ መሬት ጥቅልል አርጎ ይዞ የአያቱን ግዛት በኋላ እንደገና አላህ ሽቶበት ዘኒ ሆነ ብለው በቀን በሌሊት አይቶ እማይለቅ ሆኖ የምታምር ሴት እንኳን ሌላይቱን እህቱን ጣላት በሏ በሌለበት እሱ አስረገዛት ከአልጋው ያወርዱታል በሥራው ክፋት ለጥቃ ተሾመች ዘውዲቱ የሜሏት ሦስት ዓመት ገዛች ይች ቆንጆ ሴት የራስ መኮንን ልጅ ተፈሪ የሚሉት መቃ ሠራ በሷ ገድሎ ቀበራት እቤት ውስጥ ቀብሮ መደብ ሠራባት በመቃ ይሎታል መች ሲቀርለት ታተጥቆ ተሾመ ተፈሪ አባ መላ ሃምሳ ዓመት ይገዛል ሐበሻን በሞላ የሚገዛበት ነው በብልሃት በመላ ባይሆን ቀኑ ሲደርስ ሃምሳ ዓመት ሲሞላ የገዛ አሽከሮቹ ያዝ አርገው በመላ ከአልጋው ያወርዱታል በችግር ሊቆላ ከዚያ ያበሉታል ቸኮሌ ባቄላ ችግረን ቅመሰው ጮማህን ሳትበላ ሕዝብን ስትቀጠቅጥ ለድሃ አታዝን ክብር ስታሳዳግ አርገርህ የልቡን በመሥሪያ ቤቱ ዘመዶችህን እስኪ ይድረሱልህ እንዲህ ስትሆን ከአልጋው አምዘግዝገው ምድር ይጥሉታል ወዲያው የፊጥኝ እጆቹን ያስሩታል በፊት መቃ መሥራት እንዲህ ያንገላታል ከሞላው አሟሟት በእሱ ይበረታል ሳያስበው ድንገት ከአልጋው ያወርዱታል ቸኮሌ እያበሉ እልፍኙ ያስሩታል ሕዝቡን እንደቀጣ ችግር ያበሉታል መስከረም አንድ ቀን ደንገት ይይዙታል አሥራ አምስት ቀን ለዓመት ሲቀረው ይሞታል አንተ በእልፍኝህ ውስጥ በልተህ ጮማህን ድሃው ቶሙን ውሎ ቀምሶ ጥሬውን ትንሽ እዝነት የለህ ቅመሳት አሁን የገዛ አሸከሮቹ ያሳደጋቸው በዙፋን ባልጋው ላይ ያሞናደላቸው ከአልጋው ያወርዱታል አላህ ሠልጧቸው እሑድ ቀን ሰንበቱ እንሂድ ብለው ዘውዱን ከራሱ ላይ ሉሉን ቀምተው አመድ ያቅሙታል ትዝ ሳይለው የዳግሚያ መኮንን የአልጋ ወራሽ አባት የመነን አስፋው ባል አጴጹ ኃይለ ሥላሴ ባለ ብዙ ብልሃት ደርጎች ያወርዱታል ከእልፍኝ ከኩራት በዘውዲቱ ጡር ውሎ መቃ በሠራበት ጥቃቱን ይቀምሳል ኩስ እሬት ያለበት በእሱ ጊዜ ያሉት ሹሞችም ባላባት ከእዛ ያድኑታል ሁሉም በያሉበት ዱአ አድራጊ ድሁ መቼም ምን የለበት አደብ ካጣች በቀር ጌታችን ሽቶበት አጴጹ መባል ቀርቶ አሮኔው ይሉታል እሬት ኮሶ ቀምሶ አመድ ያለብሱታል ከአልጋው አውርደውት አልቅሶ ይሞታል እራሱ ጡር ውሎ መቃ ፊቱ ታለ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ዘጠና ዓመት አራት መቶ ሳይሆን እዚህ መሃል ናት ተፈሪ አባል መላ የሚወድምበት ኃይሌ መቃ ሠርቶ በዘውዲቱ ሬሳ በሺች መደቡ ላይ ቢሞትባት እሳ ጌታችን መቼ ነው ጀዛን የሚረሳ። ጉ ያን ጊዜ ይበጃል ክልል የሚሉት እንዳይገናኙ ከእነኛ ሐዋይት ከያዘ በስተቀር ትንሽ ወረቀት ይህንን ነገረኝ በይሩስ የሚሉት የዒፍሩት ወንድም ነው በአባትም በእናት ያዝ ጊዜ ይነዳል ውሃም እንደ እሳት በቅሎም ትወልዳለች መሐንም ከሴት ሸምበቆም ያፈራል ልጠው ቢያቆሙት ይህንን ተናግሯል በቁርዓን አያት ወኢዘል ቢኋሩ ብሎ ሲጅረት ያን ጊዜ ይበዛል ጦርና ዱለት ደላንታ ይዋጋል ቦረና መሬት አላሽም ይዋጋል ኤርትራ እሚሉት በሸዋ በደሴ የሚያልቀው ፍጥረት ያን ጊዜ ነበር አላህ የሻለት ሌት ቀኑን መወትወት ነው በአሕመድ ሶላዋት ዱአ በቀኝ እጁ አድርጎ መያዝ ያን ቀን ያድነዋል ከብዙ መዘዝ ወንድሜ ልንገርህ እንዳትፋዘከዝ ይመጣሉ እነዚያ እነ አይራራ እነጨካኝ ደርጎች የሚሏቸው ዱአ አድራጊ በቀር የለም የሚችላቸው እነዚያ ኃይለኞች እነዚያ ጨካኞች እነዚያ አሽብሮች እነዚያ አንበሶች በክፉ ያዩትን እነዚያ እርጉሞች በደግ ለታያቸው እነዚያ ደጎች ደርጎች አይቀሩም ይመጣሉ ዝመቱ መንገድ ሥሩ መሬትን ክፈሉ እኩል የሚሉ ሰማዩን በባላ ገድፉት ባይሉ ደርጎች ኤርትራ ሕዝቦች ጋር ሦስት ጊዜ ዘምቶ የሰላም ንጉሥ ይመጣል ጥቂት ቀን ሰንብቶ ስድስት ዓመት ይገዛል ዲኑን እስላም ነግሦ ደስታ ይሆናል ለሱስማ አብሶ በፊት የቆሰለ ያን ጊዜ ያሽራል ድሉ ለኡስማ ያን ጊዜ ይዞራል የደርጎች ዘመቻ ኤርትራ በኋላ በስተጀንበር መግቢያ አለ በመቅደላ ይህ ዘመቻ ነው አለቃው ዘመቻ የሄደው አይመጣም የቀረውን እንጃ መቅደላ ያልኩህ የርብን ጉባዔ ነው አሥራ ሁለት ኮርማ የሚገጥምበት የጎበዞች ሥፍራ እርብ የሚሏት የርብን ጦርነት ልንገርህ ጥቂት ሰው ይታደላል ስንዴና መሬት ደግሞ ሁለተኛ ብርና ጥይት ሰው ያበዛል ሐሰድና ውሸት እርስ በርሱ መዚለም ነው ድርቅና ኩራት ወራቷም ሚያዚያ ናት ቀኗም እሮብ ናት ሦስት ሰዓት አንስቶ ሰኞ ድረስ ናት አዋጁን ልንገርህ እንድትጠብቃት ዱአ እያደረግክ በቀን በሌሊት መሬት የምትከጅል ደግሞም ልብስ ጉርስ ገበያ እንገናኝ መቅደላ ድረስ የጡርንባው ብዛት ሦስት መቶ ይሆናል መህሉቃቱ ሁሉ አንደዜ ይሰፍራል እንኳን ያየለው ሰው ጥቂት ልጅነት ሽማግሌ ባልቴት በምርኩዝ በከብት ጡሩንባውን ነፍቶ አዋጅ ያደርግና ወንዱንና ሴቱን ክተት ይልና በመድፍ በመትረየስ ያንደቀድቅና ይቆላዋል ከዚያ መኻል ያደርግና አዋጅ ሊደረግ ሲሉ ክተት የራሕመት ደመና ያጠለለለት ማቄን ጨርቄን ሳይል አውድማ ክትት ባቄላ ፍሬ አለች ዲቃን የሚሏት ስትቀቀል ውላ ፍላት አይነካት ከርብ መከራ ኔታ የሚያወጣት አንድ ሺህ ሦስት መቶ ከዘጠና ውስጥ አራት መቶ ሳይሆን እዚያ ውስጥ ናት የፍጥረቱ አውድማ እርብ የሚሟሏት የርብን መከራ ስንቱን ልንገርህ ቂያማ ቀን ይመስላልገና ሲቀርብህ ኸልቁ ይሸበራል እንደ ቂያማ ዕለት ቀኗንም ወራቷንም ከዋሸንላችሁ እንዳትሄዱ አደራ የእኛ የሆናቸሁ የራሕመት ደመና ሸፍን ያድርጋችሁ ነቢ ተናግረዋል ኸይረል በርያት ክፉ ነፋስ አለች ሐበሻ መሬት ኸልቁን የምትጨርስ ቀንና ሌሊት ማእናውን ልንገርህ ንፋስ ያልንበት ሽብርና ጭንቀት የበዛባት ናት እጦሩ መካከል አለ አሉ ድንገት ከርብ ጦርነት ወዲያ ያለቸው ሰዓት ክብረትና አፊሠያ ናት ደስታ ውበት ምናልባት ብትተርፍ ከሰዎች ጥቂት ጥሩም በሽታውም መከራው ብዛት ይበቃል ነበረ የአንድ ማሳ እሸት አላህ ላደረሰው በዚያች ዘመናት አባክህ አድርሰን እረቢል ግአዘት አዱኛ ደኅና ሁፒ ጋሰብኩሽ ምስክሬ አንቺ ነሽ አዋጅ እንዳትረሽ ዋቢ መጻሕፍት ሐሊማ መሐመድ ዓም ለባሌው ሼህ ሁሴን የተገጠሙ ግጥሞች ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል አአዩ ፈንታ ሀ የደብረ ማርቆስ ሙስሊሞች ቂሳ ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል አአዩ ኪሩቤል ሸንቁጤ የቃጥባሬው ሼህ ሁሴን የሕይወት ታሪክና የበዓላቸው አከባበር ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል አአዩ ሙሐመድ ኢ ሼሀ አደም ደርቃና ግጥሞቻቸው ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ክፍል አአዩ ሙሐመድ ጅ ሼህ ጫሊና የመውሊድ ግጥሞቻቸው ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል እአአዩ ሙሐመድ ይ በወረታ አካባቢ በዱአ ላይ የሚባሉ እንጉርጉሮዎች ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል አእአዩ ረታ ዓለማየሁ የወሎ ቃልቻ ግጥሞች ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል አእአዩ ጥበቡ ሰ የሐጂ ሀሚድ መንዙማዎች ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል አአዩ ጽጌ ንጋቱ አስቸናቂ የሰይድ ቡሸራ አፈታሪክና የመውሊድ በዓል አከባበር በገታለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል አአዩ ዑመር ዳውድ በአዲስ አበባ ሙስሎሞች በመጅሊስ ላይ የሚሏቸው እንጉርጉሮዎች ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል እአዩ ዮሴፍ ሰ በፋርሲ ወረዳ የወዳጃ ግጥሞች ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል አአዩ አበበ ኃይሌ የወዳጃ ትውስታ በሐረርጌ ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል አአዩ ቦጋለ ተፈሪ ዓም የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች አዲስ አበባ ዓም ሼህ ሁሴን ጅብሪልና ግጥሞቻቸው ያልታተመ ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ክፍል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከኪ ከሃከህ ር ከኘ ሃ ላ ከሃ ከሃ ልጀመሃ እላ ፐከርኗኗ በኗሀኪርዩ ዐ ጳዐሠ ከእኗ ሷ በዐፍ ላ ከከኳ በሃኗሃ ከከጪ እ ፐዩዚፎ ላ ሏ ኮዐፀከር ህ ፀቬፀ ቧ እኳእበ ን ፍዐር ቢ ዒ ሀከከ ነኪ ከ እከ ለ የበርበ ኪ ከከር እ ለኗኗፀፀ እበዐ ኗዐበፀ ዐቢበፀቪ።