Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
Author: ዓለማየሁ ገላጋይ
አንድ የአማርኛ መምህር ከአርሲ ነገሌ በሰራ ቅያሪ አዲስ አበባ ወደምትገኝ ወሪሳ በምትባል ሰፈር አክስቱ ለጊዜው ወዳወረሱት ቤት ይገባል:: መምህሩ በዚህች ሰፈር እንዲሁም በጎረቤት ሰፈሯ "እሪ በከንቱ" የሚያጋጥመውን የመላመድና የመኖር ፈተና ፣ ግጭት ፣ መስማማት ፣ ተንኮል ፣ ፍቅር ፣ አጣብቂኝ ፣ ውዝግብ ፣ እንዲሁም የሚሰማቸውን ወግና ታሪክ(ተረት) ይተርካል::
መፅሐፉ የሚያነሳችው ወጎች ፣ ተረትና ምሳሌዎች ፣ ታሪኮች(ተረቶች) ተምሳሌያዊነትን ያዘሉ ሲሆን የኢትዮጵያን ያለፈ እና የአሁኑን ታሪክ: የአሁኑ ትውልድ የሚያይበትን የተዛባ ዓይን ፣ በአሁኑ ትውልድ ውስጥ ስላሉት የተለያዩ ነባራዊ ሐቆች እንዲሁም ልዩነት ያላቸው ተጎራባቾች ላለፈው ታሪክ የሚያድርጉትን ሽሚያ እና ሽኩቻን ያሳያል::